en
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Open in Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 19 932 subscribers, ranking 1 157 in the Medicine category and 1 680 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 19 932 subscribers.

According to the latest data from 29 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -533 over the last 30 days and by -12 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 28.33%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 7.18% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 5 649 views. Within the first day, a publication typically gains 1 431 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 9.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 30 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Medicine category.

19 932
Subscribers
-1224 hours
-1177 days
-53330 days
Posts Archive
ተጨማሪ ምክሮች • ችግሩ ለረጅም ጊዜ ያለ/የሚቀጥል ነዉ ብሎ ያለመዉሰድ • የትዳር ወይም የፍቅር አጋረዎን በመፍትሄዉም ይሁን በችግርዎ ዉስጥ አጋር ማድረግ • ጭንቀትን፣መረበሽንም ይሁን ማንኛዉንም የስነአዕምሮ ችግሮች ችላ ብሎ ያለማለፍ ነው 👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦ ✅ የዶክተር Sofonias የቴሌግራም ገፅ ፦ ቤተሰብ ይሁኑ @DrSofonias @DrSofonias @DrSofonias

የወንዶች የወሲብ ችግር ብዙዎቻቹ በ inbox የምትጠይቁኝ ነገር ነው በጥሞና አንብቡት እና በየ ግሩፖች ላይ በቅንንት ሼር አርጉ ((( @DrSofonias ))) የብልት ያለመቆም ችግር የብልት ያለመቆም ችግር አለ የምንለዉ የወንድ ብልት ለግብረ ስጋ ግንኙነት ሲዘጋጅ አልቆም ሲል ወይም የተወሰነ ቢቆምም ምንም ጥንካሬ የሌለዉ ከሆነ ነዉ፡፡ ይህ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ከቀጠለ በወንድየዉ ላይ ጭንቀትን፣በራስ ያለመተማመንንና የግብረስጋ ግንኙነት ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል፡፡ የወንዶች ብልት ያለመቆም ችግርን ለህክምና ባለሙያዎ ማወያየት የሚከብድ ቢመስልም ለብልት ያለመቆም ችግር መንስኤ የሆኑና ቢታከሙት ችግሩን ሊያቃልል የሚችሉ እንደ የልብና የስኳር ህመም ያሉ የውስጥ ደዌ ችገሮች ስላሉ ምንም ሳያፍሩ የህክምና ባለሙያዎን ማወያየት ይመከራል፡፡ ችግሩን ያመጡትን ነገሮችን በመታከም ለዉጥ ከሌለዉ ደግሞ ሌሎች ስንፈተ ወሲብን ሊያክሙ የሚችሉ መድሃኒቶች ስላሉ ባለሙያዎትን ማማከርን አይርሱ፡፡ የወንድ ብልት ያለመቆም ችግር ምልክቶች • የብልት አልቆም ማለት • የብልት ቆሞ ያለመቆየት/ ቶሎ መልፈስፈስ • የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ የህክምና ባለሙያዎትን ማማከር ያለቦት መቼ ነዉ? • የብልት ያለመቆም ችግር ወይም ሌሎች የወሲብ ችግሮች እርስዎንና አጋርዎን ካስጨነቅዎ • ከብልት ያለመቆም ችግር ጋር ተያያዥ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ የስኳር፣ የልብ ህመም ወይም ሌሎች የጤና ችግሮች ካለዎ • ከስንፈተ ወሲብ ጋር የሚገናኙ የማይመስሉ ሌሎች የህመም ምልክቶች ከስንፈተ ወሲብ ጋር አብሮ ካለዎ ለብልት ያለመቆም ችግር ምክንያቶች ምንድን ናቸዉ? ለወንዶች የወሲብ ስሜት መነቃቃት አእምሮ፣ ሆርሞኖች፣ ነርቮች፣ ጡንቻዎች፣ የደም ስሮችና ስሜት (emotions) የሚሳተፉ ሲሆን ይህ ሂደት እጅግ ውስብስብ ነዉ፡፡ የብልት ያለመቆም ችግር ከእነዚህ በአንዱ ወይም በሌለኛዉ ላይ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ሊመጣ ይችላል፡፡ ጭንቀትና የስነ አዕምሮ ችግሮች ችግሩን ሊያባብሱት ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳዮች የብልት ያለመቆም ችግርን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ የብልት ያለመቆም ችግርን ሊያመጡ የሚችሉ አካላዊ ችግሮች • የልብ ህመም • የደም ስሮች መዘጋት ( atherosclerosis) • የደም ግፊት መጨመር (የደም ብዛት) • የኮሌስትሮል መጨመር • የስኳር ህመም • ዉፍረት • የፓርኪንሰንስ ህመም • መልቲፕል ስኬሎሮሲስ • የወንዶች ሆርሞን (ቴስቴስትሮን) መጠን መቀነስ • በወንዶች ብልት ዉስጥ ጠባሳ መፈጠር • ለህክምና የሚታዘዙ መድሃኒቶች • መጠጥ (አልኮሆል)ና ሌሎች አደንዛዥ ዕፆች • የፕሮስቴት ዕጢ ማበጥ ወይም የፕሮስቴት ዕጢ ህክምና • በዳሌ አካባቢ ወይም በህብለሰረሰር ላይ በሚደረግ ቀዶጥገና ወቅት የሚደርስ አደጋ የብልት ያለመቆም ችግር የሚያመጡ ስነ ልቦናዊ ምክንያቶች፡­ አዕምሮ ተከታታይነት ያለዉ አካላዊ ሁነቶችን በማነሳሳት ለብልት መቆምና ወሲባዊ ደስታዎችን በማምጣት ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታል፡፡ ለወሲባዊ ስሜቶች ችግርና ለብልት ያለመቆም ችግርን የሚያባበሱ የተለያዩ አዕምሮአዊ ነገሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ፡­ • ድብርት፣መረበሽ ወይም ሌሎች የስነ አዕምሮ ችግሮች • ጭንቀት • በጭንቀት ምክንያት የግንኙነት ችግሮች፣ የሰዉ ከሰዉ ተግባቦት ችግር ወይም ሌሎች ነገሮች ለብልት ያለመቆም ችግር የሚያጋልጡ ነገሮች ዕድሜዎ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ብልት ለመቆም ረዘም ያለ ሰዓት የሚወስድ ሲሆን ከቆመም በኃላ በጣም ጠንካራ ላይሆን ይችላል፡፡ ዕድሜ እየጨመረ በሚመጣበት ወቅት የብልት ያለመቆም ችግር የሚከሰተዉ ከእድሜ መጨመር ጋር አብረዉ የሚመጡ የጤና ችግሮችና የሚወስዷቸዉ መድሃኒቶች ስላሉ ነዉ፡፡ ሌሎች ተጨማሪ ችግሮች • የውስጥ ደዌ ችግሮች፡­ ስኳርና የልብ ችግሮች • ሲጋራ ማጨስ • ዉፍረት፡­ በተለይ በጣም መወፈር • የተወሰኑ መድሃኒቶች፡­ ለድብርት፣ ለአለርጂዎች የሚሰጡ መድሃኒቶች፣ ለካንሰርና ለደም ግፊት ህክምና የሚሰጡ መድሃኒቶች • አደጋ፡­ በተለይ ለብልት መቆም የሚረዳዉ ነርቭ ላይ አደጋ ሲደርስ • ስነልቦናዊ ችግሮች፡­ ጭንቀት፣ድብርት • አደንዛዥ ዕፅና አልኮሆል የሚጠቀሙ፡­ በተለይ ረዘም ላለ ጊዜ ለተጠቀሙ ለረጅም ጊዜ ብስክሌት የሚያሽከረክሩ፡­ ይህ ነርቮችን ስለሚጫንና ወደ ብልት በሚሄደዉ የደም ዝዉዉር ላይ ግዜያዊ ጭነት ስለሚያመጣ ግዜያዊ የብልት ያለመቆም ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለብልት ያለመቆም ችግር ጊዜ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች፡­ • አካላዊ ምርመራ፡­ በብልትዎ፣ በዘር ፍሬዎና በነረቮች ላይ ምርመራ ማድረግ • የደም ምርመራዎች • የሽንት ምርመራ • የአልትራሳዉንድ ምርመራ • በእንቅልፍ ሰዓት የብልት መቆም ምርመራ፡­ • ስነልቦናዊ ምርመራዎች ለብልት ያለመቆም ችግር የሚደረጉ ህክምናዎች መጀመሪያ የሚደረገዉ ለሌላ ህመም እየወሰዱ ያለ መድሃኒት ካለ ለብልትዎ ያለመቆም ችግር ምክንያት መሆን ያለመሆኑን ማረጋገጥ በአፍ የሚዋጡ መድሃኒቶች • ሲልደንፊል (ቪያግራ) • ታደልፊል (ሲያሊስ) • ቫርድንፊል እነዚህ መድሃኒቶች የሚሰሩት ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ሲሆን የብልትዎን ጡንቻዎች በማላላትና ወደ ብልት የሚሄደዉን ደም በመጨመር ወሲባዊ መነቃቃት በሚፈጠርበት ወቅት ብልትዎ እንዲቆም ያደርጋሉ፡፡ እነዚህን መድሃኒቶች ከመዉሰድዎ በፊት የጤና ባለሙያዎትን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች የሚከተሉት ነገሮች ካሉ ላይሰሩ ይችላሉ ወይም ለጤና አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ፡­ • ናይትሬት ያላቸዉን መድሃኒቶች እየወሰዱ ከሆነ (ናይትሮግላይሴሪን) • ለደም ማቅጠኛ የሚሰጡ መድሃኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ፣ አልፋ ብሎከርስ የሚባሉና ለፕሮስቴት ህክምና እየወሰዱ ከሆነ፣ የደም ግፊት መቀነሻ መድሃኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ • የልብ ችግር ወይም ድካም ካለዎት • የደም ግፊት በጣም መቀነስ ካለዎት ወይም በህክምና ያልተቆጣጠረ የደም ብዛት ካለዎት • በስትሮክ ከዚህ በፊት ታመሁ ከሆነ • በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመም ካለዎት ሌሎች መድሃኒቶች (በኢትዮጵያ ውስጥ ላይገኝ ይችላል) • እራስን በራስ የሚወጉ አልፕሮስታዲል • በብልት የሚገቡ አልፕሮስታዲል • የወንዶች ሆርሞንን(ቴስቴስትሮን) መተካት ከመድሃኒቶች አልሰራ ካሉ ወይም በተለያ ምክንያት መድሃኒቶችን መጠቀም የማቻል ከሆነ ሀኪምዎ የሚከተሉትን ሊያዝሎት ይችላል • ፔኒስ ፓምፕ • ፔኒስ ኢምፕላንትስ • የደም ስር ቀዶጥገናዎች ስነልቦናዊ ምክሮች የብልት ያለመቆም ችግርዎ ከጭንቀት፣መረበሽ ወይም ድብርት ጋር የተገናኘ ከሆነ የስነዓዕምሮ ባለሙያዎችን ወይም የስነልቦና ባለሙያዎችን ማማከር ያስልጋል፡፡ የብልት ያለመቆም ችግር የመጣዉ አካላዊ በሆነ ችግር ቢሆን እንኳ ጭንቀትና የግንኙነት ችግር ማምጣቱ ስለማይቀር እነዚህን ባለሙያዎች ማማከር ይጠቅማል፡፡ የኑሮ ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ • ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቛረጥ • ክብደትን መቀነስ • የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ/ማዘዉተር • አደንዛዥ ዕፅ ወይም አልኮሆል በመዉሰድ እየተቸገሩ ከሆነ ህክምና ማግኘት • የግንኙነት ችግሮች ካለቦት መፍትሄ መፈለግ

ስለ ምትከታተሉን እናመሰግናለን #ዶክተር #ሶፊ #ጤና #መረጃ #እንዲደርሶ #አሁኑኑ #ቤተሰብ #ይሁኑ!!! #ሊንኩን #ተጭነው #የቴሌግራም #ገፅ #ይቀላቀሉ 👉👉👉 https://t.me/DrSofonias

የስንፈተ ወሲብ ችግር በወንዶች ላይ ብቻ የሚከሰት ችግር ነው ብለን የምናስብ ስንቶቻችን ነን? (በዶክተር ሶፊ) የሴቶች የወሲብ ችግር የተከበራችሁ ወዳጆቻችን፤ በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ ብዙዎቻችሁ ስለሴቶች የወሲብ ችግር መረጃ እንድንሰጣችሁ አስተያየቶቻችሁን ኢንቦክስ ባደረጋችሁልን መሰረት በሴቶች የወሲብ ችግር ላይ የተወሰኑ መረጃዎች እነሆ:­ ቀጣይነት ያለዉ ተደጋጋሚ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት ያለመኖር ችግር እርስዎን ወይም ግንኙነትዎን ካወከዎ በህክምናዉ የሴቶች የወሲብ ችግር አለ ልንል እንችላለን፡፡ ብዙ ሴቶች በህይወት ዘመናቸዉ በሆነ ጊዜ የወሲብ ችግር ሊገጥማቸዉ የሚችል ሲሆን ይህ ችግር በየትኛዉም የዕድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል፡፡ የሴቶች የወሲብ ችግሮች የሚከተሉትን የሚያጠቃልል ሲሆን አንዲት ሴት አንድ ወይም ከአንድ በላይ ችግሮች ሊኖሩዋት ይችላል፡፡ • ዝቅተኛ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት( Low sexual desire) ፡­ የፍላጎት መቀነስ ወይም ጭራሹኑ ያለመኖር ችግር • የግብረስጋ ፍላጎት የመነቃቃት ችግር( Sexual arousal disorder)፡­ የግብረስጋ ፍላጎት ችግር ላይኖር ይችላል፡፡ ችግሩ ያለዉ ለግብረስጋ ግንኙነት የመነቃቃት ላይ ሲሆን ይህም ለመነቃቃት መቸገር ወይም ጭራሹኑ መነቃቃት ያለመኖር ችግር ሊሆን ይችላል፡፡ • የመርካት ችግር( Orgasmic disorder)፡­ በቂ የሆነ የስሜት መነቃቃት ቢኖርም ለረጅም ጊዜ ወይም በተደጋጋሚ ያለ የመርካት ችግር ሲኖር • በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ ህመም መኖር( Sexual pain disorder) የሴቶች የወሲብ ችግር ምልክቶች የሴቶች የወሲብ ችግር በየትኛዉም ዕድሜ ክልል የሚከሰት ሲሆን ይህ ችግር ብዙዉን ጊዜ የሚመጣዉ የሆርሞኖች መዛባት በሚኖርበት ወቅት ነዉ፡፡ ለምሳሌ ልጅ ከወለዱ በኃላ ወይም የወር አበባ ዑደት በሚቛረጥበት ወቅት(በሚያርጡበት ወቅት)፡፡ በተጨማሪ የወሲብ ችግር የተለያዩ እንደ የስኳር ህመም፣ የልብ ችግር፣ የደም ቧንቧ ችግርና ካንሰር የመሳሰሉ የጤና ችግሮች በሚኖርበት ወቅትም ሊከሰት ይችላል፡፡ ከሚተሉት አንዱ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ምልክቶች ካለዎት የወሲብ ችግር አለዎት ተብሎ ሊወሰድ ይችላል • የግብረስጋ ግነኙነት የማድረግ ፍላጎትዎ ከቀነሰ ወይም ጭራሹኑ ከሌለ • የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት እያለዎ ለግንኙነት የስሜት መነቃቃት ችግር ካለዎ • በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ምንም እርካታ ከሌለዎ • በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ካለዎ የህክምና ባለሙያ ማየት የሚገባዎ መቼ ነዉ? የወሲብ ችግርዎ የአዕምሮ ሰላምዎን ከነሳዎ፣ የትዳር/ፍቅር ግንኙነትዎን ካወከዉ የህክምና ባለሙያ እንዲያማክሩ እንመክርዎታለን፡፡ ለሴቶች ወሲብ ችግር መንስዔዎች ለወሲብ ችግር ሊያጋልጡ የሚችሉ የተለያዩ መንስዔዎች ያሉ ሲሆን እርስ በርሳቸዉ ግንኙነት ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡ • አካላዊ ምክንያቶች፡­ የመገጣጠሚያ ችግሮች( arthritis)፣ የዳሌ ዉስጥ ቀዶ ጥገና፣ ድካም፣ የራስምታት፣ የሽንትና የአንጀት ችግሮች፣ የነርቭ ችግሮችና ሌሎች የጤና ችግሮች፡፡ ለድብርት፣ ለደም ግፊት፣ ለአለርጂ ህክምና የሚሰጡ እንደ አንታይሂስታሚንና ለካንሰር ህክምና የሚወሰዱ መድሃኒቶች የወሲብን ችግር ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ • ሆርሞኖች፡­ የሆርሞኖች መለዋወጥ የተለያዩ የወሲብ ችግሮችን ሊያመጡ ይችላሉ (በእርግዝና፣ ጡት ማጥባትና የወር አበባ ዑደት በሚቛረጥበት ወቅት) • ስነልቦናዊና ማህበራዊ ችግሮች፡­ ህክምና ያላገኘ ጭንቀትና ድብርት ካለ፤ ለረጅም ጊዜ የቆየ በወሲብም ይሁን በሌላ ምክንያቶች ከትዳር/ፍቅር አጋረዎ ጋር ያለመስማማት ካለዎ፤ በእርግዝና ወቅትና አዲስ እናት ሊኮን ሲል ያሉ ጭንቀቶች፤ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና የሰዉነት ቅርፅ ጉዳዮች ለሴቶች የወሲብ ችግር ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች • ጭንቀት ወይም ድብርት • የልብና የደም ቧንቧ ችግሮች ካሉ • የነርቭ ችግሮች ካሉ፡­ ለምሳሌ በህብለ ሰረሰር ላይ ችግር/ጉዳት ሲደርስ • የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ካሉ • መድሃኒቶች፡­ ለድብርትና ለደም ግፊት የሚሰጡ መድሃኒቶች • ስነልቦናዊና ስሜታዊ ጭንቀቶች ካሉ፡­ በተለይ ከትዳር/ፍቅር አጋርዎ ጋር ያለዎት ግንኙነት • ከዚህ በፊት ወሲባዊ ጥቃት ደርሶቦት ከሆነ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች • የህክምና ባለሙያዎ ስለእርስዎ ወሲባዊና የህክምና ታሪክዎን ይጠይቅዎታል፡­ ስለግል ሚስጥርዎ ለህክምና ባለሙያዎ ማዉራት ሊከብድ ይችላል፡፡ ነገርግን ይህን ማድረግዎ ሊደረግለዎ ስለሚገባዉ ህክምና አጋዥና ዋነኛዉ ክፍል ስለሆነ ምንም ሳያፍሩ መነጋገር ያስፈልግዎታል፡፡ • የማህፀን ምርመራ፡­ በዚህ የምርመራ ወቅት በብልትዎ አካባቢ ያለና ለችግሩ መንስኤ የሆነ ነገር እንዳለና እንደሌለ ለማረጋገጥ ምርመራ ሊደረግልዎ ይችላል፡፡ • የሆርሞን ምርመራ ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች ለወሲብ ችግር ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች የተለያዩ የዉስጥ ደዌ፣ ስነልቦናዊና ማኅበራዊ ችግሮችን ሊቀርፉ የሚችሉ የህክምና መንገዶችን በጋራ መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ከመድሃኒት ዉጪ ሊደረጉ የሚችሉ የወስብ ችግር ህክምናዎች • መናገርና ማድመጥ፡­ ከትዳር/ፍቅር አጋርዎ ጋር ግልፅና በእምነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ማድረግ በወሲብ እርካታዎ ላይ ትልቅ ለዉጥ ያመጣል፡፡ ከዚህ በፊት ስለሚወዱትና ስለማይወዱት ነገር የመወያየት ልምድ ባይኖርም ግንኙነትን በማያዉክ መልኩ ይህን ማድረግ መጀመርና ግብረመልስ መሰጣጣት ለቅርብርቦሽ ትልቅ ሚና አለዉ፡፡ • ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መለማመድ፡­ አልኮል በብዛት ያለመጠጣት(በብዛት መጠጣት የወሲብ ህይወትዎን ስለሚጎዳ)፣አለማጨስ(ማጨስ ወደብልትዎ የሚሄደዉን የደም ዝዉዉር ስለሚቀንስ ለግብረስጋ ግንኙነት መነቃቃትን ይቀንሳል)፣የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ(ስሜቶትን ለማነቃቃትይረዳል)፣ጭንቀትን ለመቀነስ መጣር • የምክር አገልግሎት ማግኘት • ማለስለሻዎችን መጠቀም፡­ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ካለዎት ወይም የብልት ፈሳሽ ከሌለዎ የብልት ማለስለሻዎችን መጠቀም ይችላሉ በመድሃኒት የሚደረግ የወሲብ ችግር ህክምና ለችግሩ እልባት ለመስጠት ለችግሩ መንስኤ የሆነዉን መሰረታዊ የውስጥ ደዌ ወይም የሆርሞን ችግር መታከም አለበት፡፡ መሰረታዊ የጤና ችግሮችን ለማከም የህክምና ባለሙያዎ ማማከር። • ለወሲብ ችግር ሊዳርጉ የሚችሉና እየወሰዱት ያለ መድሃኒት ካለ እንዲለወጥ ወይም እንዲስተካከል ሊያደርግ ይችላል • የታይሮይድ ወይም ሌሎች የሆርሞን ችግሮች ካሉ እንዲታከሙ ይደረጋል • ድብርት ወይም ጭንቀት ካለዎ ተገቢዉን ህክምና እንዲገኙ ይደረጋሉ • የዳሌ ዉስጥ ህመም ወይም ሌሎች ህመሞች ካለዎ ህክምና እንዲያገኙ ይደረጋሉ ከሆርሞን መዛባት ጋር የተገኛኘ የወሲብ ችግር ካለዎ • የኢስትሮጂን ሆረሞን ህክምና • የአንድሮጂን ሆርሞን ህክምና ሊደረጉ ይችላሉ የኑሮ ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና • ብዙ አልኮሆል ያለመዉሰድ • ሲጋራ ያለማጨስ • አካለዊ ንቃት እንዲኖሮት ማድረግ፡­ተከታታይነት ያለዉ የሰዉነት እንቅስቃሴ ማድረግ ስሜትዎን ከማነቃቃቱም በላይ የሰዉነት ቅርፅዎ እንዲስተካከል ያደርጋል • ለመዝናናትና ለመፍታታት ጊዜ መያዝ፡­ይህን ሲያደርጉ ጭንቀትን ይቀንሳሉ፣ፈታ ስለሚሉ የቀን ተቀን የኑሮ ጭንቀትን ይቀንሳሉ፡፡ ዘና ማለት በወሲብ ልምድዎ ላይ ትከረት ለመስጠት ስለሚያግዝዎ ጥሩ የሆነ የወሲብ መነቃቃትንና እርካታን አንዲገኙ ይረዳዎታል፡፡ መልካም ጤንነት!!!

ስለ ቫዚሊን 8 አስገራሚ ነጥቦች share share share ቫዝሊን (ፔትሮሊየም ጄሊ) ወይም በተለምዶ ባዝሊን እያልን የምንጠራው የውበት መጠበቂያ እጅግ በርካታ ለየት ያሉ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ቀጥ
ስለ ቫዚሊን 8 አስገራሚ ነጥቦች share share share ቫዝሊን (ፔትሮሊየም ጄሊ) ወይም በተለምዶ ባዝሊን እያልን የምንጠራው የውበት መጠበቂያ እጅግ በርካታ ለየት ያሉ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ስምንት ነጥቦች ያብቧቸው… በቅድሚያ ግን ሼር ያድርጉት፡፡ 1. ማስቲካ ተለጥፎባቸው የተበላሹ ወለሎች አልያም ሌሎች እቃዎችን ቫዚሊን በመቀባት ማስለቀቅ ይቻለናል፡፡ 2. ቫዚሊን ቅንድብ እና የአይን ሽፋሽፍትን ለማጥቆር እና ለማሳደግ እንዲሁም እንዲበዛ ለማድረግ ያግዛል፡፡ ይህንንም ወደ መኝታችን ስናመራ መቀባት እና ጠዋት መታጠብ ይገባል፡፡ 3. አይናችን ላይ የተቀባናቸውን ማስዋቢያዎች ለማስለቀቅ ከቸገርን ቫዚሊን በመቀባት በጥጥ አልያም በንፁህ ጨርቅ በመጥረግ በቀላሉ ማስለቀቅም እንችላለን፡፡ 4. ቆዳችንን የተዋበ ለማድረግ ቫዚሊን ሞቅ በማድረግ ፊታችንን በመቀባት ልስላሴ እና ጥራትን መጎናፀፍ እንችላለን ይህንንም የምናደርገው ወደ መኝታችን ከማምራታችን በፊት ነው፡፡ 5. ቫዝሊን የተዋበ ጥፍር እንዲኖረንም ያግዘናል፡፡ 6. ሽቶ ለረጅም ጊዜ መዓዛው በሰውነታችን እንዲቆይ ከፈለግን የፈለግንበት ቦታ ላይ ቫዚሊኑን ተቀብተን ሽቶውን ማድረግ መልካም ለውጥን ያመጣልናል፡፡ 7. ፀጉርን ከሰውነታችን ለማስወገድ ስንሞክር የሚፈጠሩ ሽፍታዎችንና ጥቁር ነጠብጣቦችን ለመቀነስ አስቀድመን መቀባት ይገባናል፡፡ 8. መረጃውን አሁኑኑ ሼር አድርጉት፡፡ እንደወደዱት ተስፋ እናደርጋለን የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

በምስሉ ላይ የምታየው ብልግና ነገር እንዳይመስልህ የተሰበረ የወንድ ልጅ ብልት ነው። የወንድ ልጅ ብልት እንደሚሰበር ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን እኛ እንቀጥል #ሼር እያረክ አምሽ ፈረንጆቹ Penile fracture ይሉታል በቃ ብልትህ ስብር ሲል በብዛት የሚከሰተው ከስንት አንዴ ቢሆንም ግብረ ስጋ ግንኙነት ሲደረግ የሚፈጠርም ነው (እግዚኦ ሰውየው እርሻ ጀመረ እንዴ መሬት ላይ ልትሉ ትችላላልሁ። 😄) የብልት መሰበር ሌሎች ላይ እንደምናውቀው የአጥንት መሰበር አይደለም ቀጥ ብሎ እንዲቆም ሃላፊነት ከተሰጣቸው coropora caveronsa እና penial sheath እልም ብሎ ከስራ መጥፋት ነው። ያኔ ምንም አይነት ተአምር ቢፈጠር ብልትህ አይቆምም ሽንት ራሱ መሽናት ከባድ ነው። ⚠ ምልክቶቹ - የብልት መሰበር ድምፅ በወቅቱ ይሰማል -በወቅቱ ቆሞ ከነበረ ድንገተኛ መተኛት -የብልት መድማት -ሽንት መሽናት ፈተና ይሆናል ከተጠቀሱት ምልክቶች ድንገት መተኛት እና የመሰበር ድምፅ የሚከሰተው በሌላ እንዳይመስልህ ሰውየው የተለየ ወሲብ አካሄድ ሲከተል በወሲብ ወቅት ነው። አልፎ አልፎ በግለ-ወሲብ ወይንም Masturbation ብለን በምንጠራው ወቅት በሚደረግ አደገኛ ትሽሽት ሰውየው በእጁ ሰብሮት ቁጭ ይላል። ስፖንጅ የመሰለ የጡንቻ ክፍል Corpora caveronsa በደም ሲሞላ እና ሲወጠር ያኔ ብልትህ ይቆማል ባሻዬ። ታድያ ከሁለቱ ጎኖችህ አንዱ ወይንም ሁለቱም ስራ በቃን ሲሉ ያኔ ተሰብሮልሀል። ⚠ መነሻ ምክኒያቶች - ቀጭን ሴት ከሆነ የምታደርገው በአጥንቷ በኩል ከታገልክ (እጥፍ ስብር ይልልሀል ጥንቃቄ ካልተሞላበት 😄) - ብልትህ ቆሞ ሳለ የሆነ አንዳች ነገር ቢገጨው በር ወይንም ጠረጴዛ ቢገጭ - ብትወድቅ እና ብልትህ እንደ ቆመ ብትተኛበት -አላስፈላጊ የግለ-ወሲብ ትሽሽት ወቅት ህክምናውም አደጋው ሲከሰት ibuprofen አይነት anti - inflammatory መድሃኒቶች ከመዋጥ ጀምሮ እስከ ቀዶ ጥገና ያደርሳል። ቀዶ ጥገናው ከተጠናቀቀ በውሃላ ለአንድ ወር ከወሲብ የምትታቀብ ሲሆን ችግር እንዳይገጥምህም ለብልትህ የእንቅልፍ መድሃኒት ይሰጡሃል። ለዚህ ነው ብዙ ጊዜ ወንዶች ባያቹት ነገር ሁሉ አይነሳባችሁ የምለው። መተኛትን የመሰለ ነገር የለም😊 እየተኛቹ መልካም ምሽት የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

ስንፈተ ወሲብ የስንፈተ ወሲብ አይነቶች ብዙ ቢሆኑም የብዙ ወንዶች ጥያቄ የሆነውን ቶሎ የመርጨት ችግር (Premature ejaculation) በዚህ ፅሁፍ እንዳስሳለን፡፡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ወንዶች በአማካይ በወሲብ ላይ የሚቆዩት (የወንዱ ብልት ሴቷ ብልት ውስጥ ከገባበት ሰአት ጀምሮ) 5.4 ደቂቃ አካባቢ ቢሆንም አንድ ወንድ ቶሎ የመርጨት ችግር ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ የሚቆየው ከሁለት ደቂቃ በላይ ይሁን በታች መታወቅ አለበት፡፡ ቶሎ የመርጨት ችግር በብዙ ምክንያቶች ሊከሰት ቢችልም ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡- 1. ግለወሲብን በብዛት መለማመድ 2. ከልክ ያለፈ ጭንቀትና ውጥረት 3 ድብርት 4. ፍርሀት. 5.ሱስ 6. ከልክ ያለፈ ውፍረት 7. የወሲብ ፊልሞች(Pornography) በብዛት መመልከት 8. የተለየዩ መድሀኒቶች 9. በልጅነት እድሜ ለወሲብ ጥቃት መጋለጥ 10. በራስ አለመተማመን ወሲብ ለህይወታችን አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ በስንፈተ ወሲብ(Premature ejaculation) የሚቸገሩ ወንዶች በከባድ ጭንቀትና ፍርሐት ውስጥ ያልፋሉ፡፡ በማህበረሰባችን ውስጥ እንዲህ ያለውን ነገር ደፍሮ የመነጋገር ልምድ ስለሌለ አንዳንዶች ችግሩ ይኑርባቸው አይኑርባቸው፤ መፍትሔ ይኑረው አይኑረው እንኳን በውል ሳያውቁ ከሚወዷቸው ሰዎች ሲለዩና ከትደራቸው ሲፋቱ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ለዚህ ችግር እንደ መፍትሔ ከሚጠቀሱ ነገሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡- 1. ጭንቀትን ቀስ በቀስ ማስወገድ 2. በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ 3. ሱስን ማስወገድ 4. ሰውነትን የሚያፍታቱ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር 5. እስፖርት መስራት 6. የጠዋት ወሲብን ማዘውተር ከላይ የተዘረዘሩት መፍትሔዎች ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ወሲብ የሁለት ሰዎችን ጥረት የሚጠይቅ ውህደት እንደመሆኑ መጠን አስደሳችና አርኪ ለማድረግ የሁለትዮሽ ጥረት አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ለወሲብ ሕይወታችን ማማርና መሳካት ስንል በግንኙነታችን ውስጥ ግልፅነትን እናዳብር፡፡ ስለስንፈተ ወሲብና ስለመፍትሔው የበለጠ ለማወቅ ባለሞያ ማማከር ይችላሉ፡፡ “መልካም የጤና ጊዜ” ሌሎች መረጃዎችን ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ @DrSofonias

ጤናማ ያልሆነ እንቁላል በማህፀን ውስጥ ፣ ይህንንም ማሻሻያ አመጋገብ ብዙውን ጊዜ ፅንስ ያለመፈጠር ሴቶቹን ሲያስጨንቅና ሲያሳስባቸው ይስተዋላል ። ባልታወቁና በተለያዩ መንገዶች ሴቶች አለእርግዝና ጊዜያትን ያስቆጥራሉ ። ከሚገጥሟቸው ችግሮች በዋናነት የሆርሞን መዛባት ፣ የማህፀን ውሃ መቋጠር ወይንም እጢ ፣ የእንቁላል አመንጪው ክፍል መጎዳቱ እንዲሁም የማህፀን ማነሰ ዋነኞቹ ናቸው ። ልብ የማይባለው የእንቁላል ጤናማነት የዚህ ችግር አካልም ነው ። የእንቁላል ጤናማ አለመሆን ከሚያስከትላቸው ዋነኞቹ የወር አበባ ቋሚና የተስተካከለ አለመሆንና ለመውለድ መቸገር ቅድሚያዎቹ ናቸው ። ስለዚህም ጤናማ እንቁላል እንዲኖርና እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የአመጋገብ ስርዓትን ማስተካከልና መመርመር ተገቢ ነው ። ከእነዚህ ውስጥም 1 አቦካዶ አቦካዶ በጣም ልዩ የሆነ በስብ የበለፀገ በመሆኑ እንቁላል ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል ። በዚህ ምክንያትም የሰውነት የመራባት ኢደት ዝግጁ እንዲሆን ይረዳል ። 2 ጥራጥሬ በሰውነታችሁ ውስጥ በሚፈጠር የአይረን እጥረት አማካኝነት ጤናማ እንቁላል እንዳይፈጠር ያደርጋል ። ስለሆነም ጥራጥሬን መመገብ ጤናማ የሆነ እንቁላል እንዲፈጠር ያደርጋል ። 3 ሆቾሎኒ ሆቾሎኒ በፕሮቲንና በቫይታሚን እንዲሁም በሚነራል የበለፀገ በመሆኑ እንቁላል ላይ የሚደርሰዎን ችግር ይከለከላል ። ውስጡ ባለው አደካ ተከላካይ ውህድ አማካኝነት የተሻለ እንቁላል እንዲመረት ያደርጋል ። 4 አረንጓዴ ቅጠላማ ጎመኖች እንደ ሰላጣ ፣ ጥቅል ጎመንና ጠጥቁር ጎመን የመሰሉ አትክልቶችን መመገብ ውስጣቸው ያለውን ካልሺየም ፣ ቫይታሚንና አይረንን ስለምታገኙ ጤናማ የሆነ እንቁላል እንዲመረት ይረዳል ። ስለሆነም በአመጋገብ ስርዓታችሁ ውስጥ ልታዘወትሩት ይገባል ። 5 ቀረፋ ቀረፋን በተለያዩ የአመጋገብ ስርዓቶች መጠቀም እንቁላል አመንጪ ክፍል ጤንነቱ እንዲጠበቅ በማድረግ ጤናማ እንቁላል እንዲመረት ያደርጋል ። 6 ውሃ ውሃ ከምግብ የሚመደብ ባይሆንም ለጤናማ እንቁላል መመረት ወሳኝ በመሆኑ ተካቷል ። ከሌሎች መጠጦች በመራቅ ውሃን ማዘውተር ተገቢ ነው ። ስለሆነም በቀን ቢያንስ ስምንት ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ለጤናማ እንቁላል መፈጠር ወሳኝ ሚና አለው ። እነዚህን ነገሮች ተግባራዊ በማድረግ ጤንነታችሁን አረጋግጡ ለማለት እንወዳለን ። መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ለበለጠ መረጃ የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ Join Telegram channel https://t.me/DrSofonias Comment Share

FB_IMG_16136534804712203.jpg0.75 KB

የጫት ጥቅምና ጉዳት ጫት አነቃቂ ና ሱስ አምጪ ከሚባሉ ዕፆች መካከል አንዱ ነው። ጫት ለመጀመሪያ ጊዜ የበቀለው በኢትዮጵያ ሲሆን በ15ኛው ክፍለ ዘመን ወደ የመንና ሎሎች የአረብ ሀገራት እንደተስፋፋ
የጫት ጥቅምና ጉዳት ጫት አነቃቂ ና ሱስ አምጪ ከሚባሉ ዕፆች መካከል አንዱ ነው። ጫት ለመጀመሪያ ጊዜ የበቀለው በኢትዮጵያ ሲሆን በ15ኛው ክፍለ ዘመን ወደ የመንና ሎሎች የአረብ ሀገራት እንደተስፋፋ ይነገራል ። በአሁኑ ጊዜ በየመን ፣በኬንያ ፣በግብፅ ፣ሱዳን፣ሶማሌ ፣ጅቡቲ ና ኢትዮጵያ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል። በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለው የጫት ክፍል ቅጠሉ ሲሆን በውስጡ ከ30 በላይ ኬሚካሎችን አሉት ። ከነዚህም መካከል ዋናዋናዎቹ ፦ ካቲን ካቲነን ካቲናይን ካቲዲን ኢዱላይን ኢፊድሪን ወዘተ ናቸው ። ካቲን ና ካቲነን የበለጠ የሚያነቃቁ ና የአይን ብሌን እንዲሰፋ የሚያደርጉ ናቸው ። የጫት ኬሚካል ይዘት እንደ ጫቱ መገኛ አካባቢ ፣ አይነትና ጥራት የሚለያይ ሲሆን ቀላ ያለው የጫት አይነት በአብዛኛው በተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ነው ። የጫት ጥቅሞች ° በማነቃቃት የደስታ ስሜት ይፈጥራል ° ረሀብን ይቀንሳል °ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል ° የማሰብ ብቃትን ይጨምራል ። የጎንዮሽ ጉዳቶች ፨የሆድ ድርቀት ያስከትላል ፨ደም ግፊትን ይጨምራል ፨ የአፍና የጨጓራ ካንሰር ያመጣል ፨ የአንጀት መቁሰል ያስከትላል ፨ የወሲብ ስሜትን ይቀንሳል ፨ የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳል ፨ ድብርትና ከማህበረሰብ መገለልን ያመጣል ። መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ለበለጠ መረጃ የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ Join Telegram channel https://t.me/DrSofonias Comment Share

Ethiopia; የወንድ አይንና የሴት ዳሌ የሚያዋድዳቸው 6 ሚስጥራት[በዶ/ር Sofi] https://t.me/DrSofonias

#ማስታወቂያ በግንኙነት ወቅት የሚያጋጥሙ ድክመቶች መቅረፍ እንደሚቻል በግብር ስጋ ጊዜ የሚያጋጥሙ ሁሉንም ድክመቶችን መቀርፍ ወዲያዉ መጨረስን የሚያዘገይ የእቃን መጠንና እርዝመትና ውጥረት የሚያስተካ
#ማስታወቂያ በግንኙነት ወቅት የሚያጋጥሙ ድክመቶች መቅረፍ እንደሚቻል በግብር ስጋ ጊዜ የሚያጋጥሙ ሁሉንም ድክመቶችን መቀርፍ ወዲያዉ መጨረስን የሚያዘገይ የእቃን መጠንና እርዝመትና ውጥረት የሚያስተካክል ያሉበት ቦታ ድረስ ለተጨማሪ መረጃ (0992484672) በአዲስ አመራረት original vimax silver 60 capsual 🤗made in canada ✓ የብልትን መጠን ለመጨመር እንዲጨምር ✓ቶሎ የመጨረስ ችግር ✓ ለወሲብ ፍላጎት ማጣት በዘላቂነት ለመቅረፍ ፈለክ ስመጥር የሆነው new vimax silver 60 capsul እኛ ጋር ይገኛል። መፍትሄው አለ ከጎንዩሽ ጉዳት ነፃ  Tel ፦☎️ 0992484672 ዋጋ ፦3500ብር ብቻ ብዛት ለሚወስዱ ልዩ ቅናሽ እናደርጋለን 🚨በወሲብ ወቅት ብልቶ አልቆም ብሎ ወይም ቶሎ እየረጩ ወይም ቶሎ እየደከሙ ወይም ብልቶ ጥንካሬ በማጣት እየተልፈሰፈሰ ተቸግረዋል? በተጭማሪም ፦ 1) ብልት ውጥር እና ቀጥ ብሎ እንዲቆም 2)የብልትን ጡንቻዎች በማጠንከር የብልት መጠንን መጨመር(4 inch) 3)ቆዳ እንዲለጠጥ በማድረግ በዛው ልክ ውፍረት እንዲጨምር የሚያደርገውን ሁሉንም ግልጋሎት በአንድ ላይ የያዘውን ዘላቂ መፍትሄ   new vimax silver 60 capsul 💯%✓✓ original መሉ በሙኑ ከተፈጥሮ ንጥረነገሮች ብቻ የተሰራ የ ካናዳ ምርት የሆነውን አስመጥተናል ☎️ 0992484672 ላይ ይደውሉ Inbox👉 @bobmarliiii 🚘🚖 ክፉለሀገር ላላችሁ እና ሌሎች ክልል ከተሞች ላላችሁ customers በ ፈጣን ems (posta) እንልካለን 🔴አድራሻ አዲስ አበባ #Free Delivery in AA 📦ለክፍለ ሃገር ደንበኞቻችን በፖስታ እንልካለን 👉ተጨማሪ t.me/Herbal_treatment_end_marketing

ስንፈተ ወሲብ የስንፈተ ወሲብ አይነቶች ብዙ ቢሆኑም የብዙ ወንዶች ጥያቄ የሆነውን ቶሎ የመርጨት ችግር (Premature ejaculation) በዚህ ፅሁፍ እንዳስሳለን፡፡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ወንዶች በአማካይ በወሲብ ላይ የሚቆዩት (የወንዱ ብልት ሴቷ ብልት ውስጥ ከገባበት ሰአት ጀምሮ) 5.4 ደቂቃ አካባቢ ቢሆንም አንድ ወንድ ቶሎ የመርጨት ችግር ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ የሚቆየው ከሁለት ደቂቃ በላይ ይሁን በታች መታወቅ አለበት፡፡ ቶሎ የመርጨት ችግር በብዙ ምክንያቶች ሊከሰት ቢችልም ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡- 1. ግለወሲብን በብዛት መለማመድ 2. ከልክ ያለፈ ጭንቀትና ውጥረት 3 ድብርት 4. ፍርሀት. 5.ሱስ 6. ከልክ ያለፈ ውፍረት 7. የወሲብ ፊልሞች(Pornography) በብዛት መመልከት 8. የተለየዩ መድሀኒቶች 9. በልጅነት እድሜ ለወሲብ ጥቃት መጋለጥ 10. በራስ አለመተማመን ወሲብ ለህይወታችን አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ በስንፈተ ወሲብ(Premature ejaculation) የሚቸገሩ ወንዶች በከባድ ጭንቀትና ፍርሐት ውስጥ ያልፋሉ፡፡ በማህበረሰባችን ውስጥ እንዲህ ያለውን ነገር ደፍሮ የመነጋገር ልምድ ስለሌለ አንዳንዶች ችግሩ ይኑርባቸው አይኑርባቸው፤ መፍትሔ ይኑረው አይኑረው እንኳን በውል ሳያውቁ ከሚወዷቸው ሰዎች ሲለዩና ከትደራቸው ሲፋቱ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ለዚህ ችግር እንደ መፍትሔ ከሚጠቀሱ ነገሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡- 1. ጭንቀትን ቀስ በቀስ ማስወገድ 2. በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ 3. ሱስን ማስወገድ 4. ሰውነትን የሚያፍታቱ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር 5. እስፖርት መስራት 6. የጠዋት ወሲብን ማዘውተር ከላይ የተዘረዘሩት መፍትሔዎች ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ወሲብ የሁለት ሰዎችን ጥረት የሚጠይቅ ውህደት እንደመሆኑ መጠን አስደሳችና አርኪ ለማድረግ የሁለትዮሽ ጥረት አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ለወሲብ ሕይወታችን ማማርና መሳካት ስንል በግንኙነታችን ውስጥ ግልፅነትን እናዳብር፡፡ ስለስንፈተ ወሲብና ስለመፍትሔው የበለጠ ለማወቅ ባለሞያ ማማከር ይችላሉ፡፡ “መልካም የጤና ጊዜ” ሌሎች መረጃዎችን ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ @DrSofonias

Ethiopia;በ መቀመጫ የሚደረግ ወሲብ የሚያመጣው 5 አስከፊ መዘዞች[በዶ/ር ሶፊ] https://t.me/DrSofonias

Ethiopia// ስለ ወሲብ 13 የሀበሻ ሴቶች የሚወዱት የወንድ የብልት ቅርፅና መጠን[በዶ/ር ሶፊ] https://t.me/DrSofonias

ከስጋት ነፃ የሚሆኑባቸው መንገዶች በዶር ሶፊ የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከእርግዝና ስጋት ነፃ የሆኑ ቀናቶች የትኞቹ ናቸው? =========== እርግዝናን ለመከላከል የወሊድ መቆጣጠሪያ መጠቀም የማይፈልጉ ብዙ ጥንዶች ተፈጥሮአዊ የእርግዝና መከላከያ ዘዴን ይመርጣሉ፡፡ ይህ ስሌትን የሚጠይቅ ዘዴ በወር አበባ ጊዜ የሚካሄዱ ለውጦችን ማወቅ ይጠይቃል፡፡ ይህ የስሌት እርግዝናን መከላከያ ዘዴ የተሳካ እንዲሆን ሴቶች የወር አበባን ሶስት ደረጃዎች ማወቅ ግድ ይላል፡፡ የወር አበባ ሶስት ደረጃዎች! የወር አበባ ሶስት ደረጃዎችን ማወቅ በቀላሉ እርግዝናን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡ 1. የመጀመሪያ ደረጃ፦ ይህ ደረጃ በህክምና አጠራር ፎሊውክላር ፌዝ ይባላል የወር አበባ ካየሽበት ከሁለተኛው (2) ቀን እስከ 14ኛው ቀን ያለውን ያካትታል፡፡ በዚህ ወቅት ሰውነታችን ዕንቁላልን የሚሰሩ ሆርሞኖች ይለቃል፡፡ 2. ሁለተኛ ደረጃ፦ ይህ የወር አበባሽ የመካከለኛ ጊዜ ሲሆን ለጽንስ ዝግጁ የሆኑ የደረሱ/የበሰሉ ዕንቁላሎች ከእንቁልጢ የሚለቀቁበት ደረጃ ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሴት ዕንቁላል የሚፈለፈልበት ወቅት ስለሆነ ከፍተኛ የማርገዝ ዕድል ይኖርሻል፡፡ 3. ሶስተኛ ደረጃ፦ ሉቲያል ፌዝ የሚባል ሲሆን ይህ ደረጃ ዕንቁላል ከዕንቁልጢ(እንቁላል ዕጢ) ከተለቀቀበት ጊዜ ጀምሮ ይጀምራል፡፡ ይህ ደረጃ ከቀን 16 እስከ 28 ባለው ማንኛውም ጊዜ ሊከሰት ይችላል፡፡ የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከስጋት ነፃ የሆነው የወር አበባ ጊዜ የትኛው ነው? 1. ከስጋት ነፃ የሆነው የወር አበባ ጊዜ ምን ማለት ነው? የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) በሴት የመራቢያ አካል ውስጥ ከ 3 - 5 ቀናቶች በህይወት መቆየት ይችላል፤ የሴት ዕንቁላል በህይወት የሚቆየው ደግሞ 24 ሠዓት ብቻ ነው፡፡ የሴት ዕንቁላል ከሚፈለፈልበት ጊዜ በአማካይ ከአንድ ሳምንት በፊት እና ከአንድ ሳምንት በኋላ ያሉት ጊዜዎች እርግዝና በከፍተኛ ሁኔታ የሚከሰትባቸው ጊዜዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ሴቴች የተለያየ የዕንቁላል መፈልፈያ ጊዜ ሲኖራቸው ከቀን 12 እሰከ 19 ባለው የወር አበባ ኡደት ጊዜ ውስጥ ይከሰታል፡፡ ከነዚህ ቀኖች ውጪ ያሉት ጊዜዎች ከስጋት ነፃ የሆኑና እርግዝና የማይከሰትባቸው ቀናቶች ናቸው፡፡ 2. ከስጋት ነፃ የሆነው የወር አበባ ጊዜን እንዴት ማስላት ይቻላል? ከስጋት ነፃ የሆነው የወር አበባ ጊዜን ማስላት በጣም ቀላል ሲሆን እንዴት ማስላት እንደምንችል እንመልከት፦ • የመጨረሻው የወር አበባሽ መጀመሪያ ቀንን እወቂ፡፡ • ለተከታታይ 6 ወር የወር አበባሽን በመመልከት እረጂም እና አጭር የወር አበባ ኡደት ቀኖችሽን እወቂ፡፡ • በአማካይ ከ 26 – 32 ቀናቶች የሚቆይ የወር አበባ ኡደት የመጀመሪያው ሳምንት ከስጋት ነፃ የሆነ ጊዜ ነው። የወንድ የዘር ፈሳሽን በሴት የመራቢያ አካል ውስጥ ከ 3-5 ቀናቶችን እንደሚቆይ በማሰብ፡፡ ይህ ዘዴ የቀን አቆጣጠርን መሠረት ያደረገ ስለሆነ ውጤቱ ከሴት ወደ ሴትይለያያል፡፡ 3. ይህን ዘዴ መጠቀም የሚችሉት እነማን ናቸው? ይህን ዘዴ በመጠም የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከስጋት ነፃ የሆኑ ቀናቶችን በማወቅ መጠቀም ያለመሳካት ዕድሉ በአመት ውስጥ ከ 3-4% ነው ስለዚህ ይህን ዘዴ መጠቀም ያለውን አደጋ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ባለፉት 6 ወራቶች አማካይ የወር አበባሽ የሚመጣበት ጊዜ ከ 26 – 32 ቀናቶች ከሆነ ይህ ዘዴ በትክክል ይሰራል፡፡ 4. ይህን ዘዴ መጠቀም የማይችሉት እነማን ናቸው? ላለፉት ስድስት ወራቶች የወር አበባሽ የሚመጣበት ጊዜ ከ 26 – 32 ቀናቶች ወጪ ከሆነ አንቺ ይህን ዘዴ በፍጹም መጠቀም የለብሽም፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ (በቅርቡ) ህፃን ልጅ ያላት ሴት ከወለደች በኋላ በአማካይ ለ 6 ወራቶች የወር አበባ መጠበቅ ይኖርባታል፡፡ ሌሎች እርግዝናን ለመከላከል የሚረዱ ዘዴዎች 1. ለወንዶች፦ • ኮንደም • ማምከን ወይም መኮለስ (Male Sterilization) 2. ለሴቶች፦ • በአፍ የሚወሰድ እንክብል (Oral Contaceptives) • ዲያፍራም (Diaphragm) • ኢምፕላንትስ (Implants) ናቸው። መልካም ጤንነት!! ሌሎች ጠቃሚ የጤና መረጃዎች ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንኩን በመንካት ይቀላቀሉ ይሄንን መረጃ ሼር በማረግ ለሌሎች ያጋሩ @DrSofonias