en
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Open in Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 19 967 subscribers, ranking 1 154 in the Medicine category and 1 678 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 19 967 subscribers.

According to the latest data from 26 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -547 over the last 30 days and by -20 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 24.05%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 7.27% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 805 views. Within the first day, a publication typically gains 1 453 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 9.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 27 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Medicine category.

19 967
Subscribers
-2024 hours
-1217 days
-54730 days
Posts Archive
ሁላችንም መጥፎ የአፍ ጠረን ያጋጥመናል። ምክንያቶቹም ብዙ ቢሆኑም 85%ቱ ከአፉ የመነጨ ነው። የድድ በሽታ እና የጥርስ መቦርቦር ጥርስ ተቦርሾም የማይጠፋ የአፊ ጠረን ምክንያቱ ይህ ሊሆን ይችላል።ባክቴሪያዋች በተቦረቦረው የጥርስ ክፍል በመቀርቀር መጥፎ ጠረን ያመጣሉ። ደረቅ አፍ ምራቅ ምግብን እንዲፍጭ ይረዳል፣የአፍ ባክቴርያ መጠኑን ይጠብቃል እናም ምግብን ከአፍ ለማጠብ ይረዳል። ምራቅ መመረት ሲያቆም ባክቴርያ ክምችት ስለሚኖር መጥፎ የአፍ ጠረን ያስከትላል። ቃር ወይም የጨጓራ አሲድ ወደ ጉሮሮ መምጣት ይህ የአንጀት ችግር ሲሆን የጨጓራ አሲድ ሽቅብ ወደ ጉሮሮ በመምጣት የደረት ማቃጠል ስሜት ብቻ ሳይሆን መጥፎ የአፍ ጠረንም ያስከትላል። አንዳንድ ተጓዳኝ በሽታዎችም ይህ የአፍ ጠረን ችግር ያመጣሉ። እነዚህም በጥቂቱ የስኳር በሽታ የኩላሊት በሽታ የጉበት በሽታ ጨጓራ በሽታ የአንጀት መዘጋት እና ሌሎችም ናቸው። አንዳንድ የምግብ አይነቶች ነጭ ሽንኩርት መጥፎ የአፍ ጠረን እንደሚያመጣ ሁሉም ያውቀዋል። የሚገርመው ግን ጠረኑ እስከ ሁለት ቀን ሊቆይ የሚችል መሆኑ ነው። ሽታውም የሚመጣው ከአፍ ሳይሆን ከሳምባ መሆኑ ይበልጥ አስገራሚ ያረገዋል። ነጭ ሽንኩርት ከአንጀት ደም ውስጥ ከገባ በኃላ በሳምባ በኩል ከአየር ጋር ተቀላቅሎ ይወጣል። ሲጋራ ማጨስ ሲጋራ እስትንፋስ ላይ እና የአፍ ድርቀት በማምጣት ብቻ ሳይሆን የድድ እና ጥርስ በሽታ በማምጣት ለመጥፎ ሽታ ያጋልጣል ። ከአፍንጫ ጀርባ የሚወርድ ንፍጥ(ጉንፋን ሲዘንና ሳይነስ ላለባቸዉ) ይህ ሁኔታ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ተጋላጭ እንደሚያረግ ይታወቃል ይህም ከአፍንጫ የሚገኝ ንፍጥ ባክቴሪያ የሚስብ ስለሆነ ወደ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲኖር ያረጋል። ቤት ውስጥ ልናረግ የምንችላቸው ህክምናዎች በቀን ሁለቴ ጥርስ መቦረሽ በጥርስ መሀል የሚሰገሰጉ ቆሻሻን ማውጣት ጤናማ ምግብ መመገብ (ስኳር ያለባቸው ምግቦችን መቀነስ) ምላስን መቦረሽ እርሾ ፋርማሲ የሚገኘዉን ማውዝ ዎሽ መጠቀም ካልቻልን ሌላው አማራጭ እርሾ ነው። ሁለት የሻይ ማንኪያ እርሾ ከ እንድ ኩባያ ሙቅ ውሀ ጋር በመቀላቀል ለ 30 ሰከንድ መግሞጥሞጥ አንድ ቀላል መንገድ ነው። ውሀን በብዛት መጠጣት ውሀ መጠጣት የአፍ ድርቀትን ስለሚከላከል ጥሩ የአፍ ጠረን መከላከያ መንገድ ነው።ሌላው አማራጭ ስኳር የለሽ ማስቲካዎችን ማኝክ ነው። የአናናስ ጁስ ብዙ ሰው አናናስ የአፍ ጠረን ይከላከላል ይላሉ በጥናት ባይረጋገጥም ጁሱን መጠጣት መይም መመገቡ አይከፋም። የዝንጅ ዘሮች በድሮ ጊዜ የዝንጅ ዘሮች የአፍ ጠረን መከላከያ አርገው ይጠቀሙ ነበር።በትንሽ ማንኪያ አፍ ላይ ማረግ ከምግብ በኃላ የአፍ ጠረንን ለመከላከል ይረዳል። @DrSofonias

ደም ግፊት አለ የሚባለው ከ140/90 በላይ ሲሆን ተጓዳኝ የልብ በሽታ አምጪ መንስኤዎች ካሉ ልኬቱ ከ130/80 በላይ የሆነ ይሆናል። እነዚህም መንስኤዎች የኮሌስትሮል መጠን መዛባት እና ስኳርን ያጠቃልላሉ። በኢትዮጵያ በተደረገ ጥናት ከ30 ሚልዮን በላይ ህብረተሰብ የተጠቃ ሲሆን አብዛኛው የሚኖረውም ከተሞች ውስጥ ነው። የደም ግፊት የሚስተዋለውም ከ30-79 እድሜ ባሉት ውስጥ ሲሆን መንስኤው በአብዛኛው ህብረተሰብ ላይ አይታወቅም። ፨፨፨፨፨፨፨፨የደም ግፊት ምልክቶች፨፨፨፨፨፨፨ ይህ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ ምልክቶችን በግልፅ የማያሳይ ሲሆን ሕሙማን ለሌላ የጤና ችግር ወደ ጤና ተቋማት ሲሄዱ በአጋጣሚ በሕክምና በባለሙያ ምርመራ የሚገኝ የበሽታ ዓይነት ነው፡፡ ፨በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰት ከባድ የራስ ምታት ፨በትክክል አለማየት ሁኔታ ፨ማቅለሽለሽና ማስመለስ ፨ተደጋጋሚ ነስር ወይም በአፍንጫ ደም መፍሰስ ፨የማዞር እና ማጥወልወል ስሜት ፨፨፨፨፨፨፨የደም ግፊት ዓይነቶች፨፨፨፨፨፨፨፨፨ 1.የመጀመሪያ ደረጃ የደም ግፊት የመጀመሪያ ደረጃ ደም ግፊት ምክንያቱ በግልፅ ብዙም አይታወቅም ሆኖም በተለያዩ መንስዔዎች ምክንያት ይፈጥራል፡፡ በተለይም ዘረ-መል (Gene) ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ለውጦች እንደ ምክንያትነት ይቀርባሉ ነገር ግን በተጨባጭ የትኛው ዘረ-መል (Gene) ችግሩን ያስከትላል የሚለው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘም፡፡ 2.ሁለተኛ ደረጃ ደም ግፊት የዚህ ደም ግፊት ዓይነት መንስዔዎቹ በግልፅ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መንስዔዎች በመከላከል እና መቆጣጠር ደም ግፊቱን መቆጣጠር ይቻላል፡፡ ፨በኩላሊትና በአካባቢው በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰት የጤና ችግር ፨በከፍተኛ ውፍረት ምክንያት አላስፈላጊ የስብ ክምችት። ፨የስኳር ሕመም ፨እርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ፨ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል በየቀኑ መጠጣት ፨ሲጋራ ማጨስ ፨ለተለያዩ በሽታዎች የሚወሰዱ መድኃኒቶች የደም ግፊት መጠንን ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ በተለይም ስትሮይድስ (Steroids) ፨የተከለከሉና አደገኛ ዕፆችን መጠቀም ለምሳሌ ኮኬይን ፨በምግብ ላይ ከመጠን ያለፈ ጨው መጠቀም ፨፨፨፨፨፨፨የደም ግፊት ምርመራ፨፨፨፨፨፨ የደም ግፊት ልኬት በተደጋጋሚ መደረግ ያለበት ሲሆን ተመሳሳይ ውጤት ከተገኘ ችግር እንደተከሰተ አመልካች ነው፡፡ በአንድ ጊዜ ልኬት ብቻ የደም ግፊት አለ ብሎ ለመወሰን አስቸጋሪ ነው፡፡ ፨፨፨፨፨፨የደም ግፊት የሕክምና መንገዶቹ፨፨፨፨፨ 1.ከመድኃኒት ውጭ ሕክምና የደም ግፊት መጠንን አስቀድሞ እንዳይከሰት ለመከላከል የሚረዱ የተለያዩ አማራጭ መንገዶች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፡፡ ፨ከፍተኛ የሰውነት ክብደት በመቀነስ ፨የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ ፨የምንወስደውን የጨው መጠን በመቀነስ ፨ከፍተኛ የአልኮል መጠንን መቀነስ፣ ጫት አለመቃም፣ ሲጋራ ባለማጨስ፣ ሌሎች የሚያነቃቁ ንጥረ ነገሮችን በብዛት አለመውሰድ። ፨መጨነቅን መቀነስ ፨የደም ግፊት በሽታን የሚያመጡ ተያያዥ የጤና ችግሮችን ማስወገድ፡፡ 2.የመድኃኒት ሕክምና የደም ግፊት መቆጣጠሪያ መድኃኒት ማለት የደም ግፊትን በመቆጣጠር በሽታው ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት ወይም ሞት መቀነስ የሚችሉ ናቸው፡፡ መድኃኒቶቹም በትክክለኛ የሕክምና ባለሙያ የሚታዘዙ እና በዓይነት እና በመጠን በየጊዜው እንደ ሕሙማን የሕመም ደረጃ ይለያያሉ፡፡ የሚታዘዘው የመድኃኒት መጠን እና ዓይነት ከሕመሙ ደረጃ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለውና ይህንን ሁኔታ ለማስተካከልና ለመቆጣጠር በየጊዜው በጤና ተቋማት በመገኘት የጤና ክትትልን ማድረግ ይኖርብናል፡፡ በሽተውን ለመቆጣጠር በመጀመሪያ ደረጃ ከምንጠቀማቸው መድኃኒቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፣ 1.አንጆ ቴንሲን ኮንቨርቲንግ ኢንዛይም ኢቲቢተርስ (Angiotensin converting enzyme inhibitors) ይህ የመድኃኒት ዓይነት በአንጆቴንሲን-II ምክንያት የሚመጣውን የደም ቧንቧዎች መጥበብ እና የአልዶስትሮን መመንጨትን በመከላከል የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚያገለግል መድኃኒት ነው፡፡ ለምሳሌ ኢናላፕሪል፣ ሊስኖፕሪል እና የመሳሰሉት በዚህ የመድኃኒት ክፍል ውስጥ ይካተታሉ፡፡ የመድኃኒቶቹ ጎንዮሽ ጉዳት፡- እርግዝና፣ የኩላሊት ችግር፣ በሰውነት ውስጥ ከባድ የሆነ ፈሳሽ መቋጠር (Angioedema) እና ሌሎችም 2.ካልሲየም ቻናል ብሎከር (Calcium channel blocker)፡- ይህ ዓይነት መድኃኒት እንደ ኒፊዲፒን፣ አሚሎዲፒን እና የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል ሲሆን ካልሲየም የተባለውን ንጥረ ነገር ወደ ሴሎች እንዳይገባ በማድረግ ግፊትን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡ የጎንዮሽ ጉዳት፡- ራስ ምታት፣ የእግር እብጠትና ሌሎችም መድሃኒቱ የማይወሰድባቸው ሁኔታዎች የደም ማነስ፣ አንስቴብል አንጃይና የሚባለው የልብ ሕመምና የመሳሰሉት 3.ዳዩሪቲክስ (Diuretics)፡- በተለይ ታያዛይድ የሚባለው መድኃኒት ለምሳሌ ኃድሮክሎሮታያዛይድ (HCT) በሽንት መልክ ውኃና ንጥረ ነገሮች በተለይ ፖታሲየም የተባለውን ንጥረ ነገር እንዲወገድ በማድረግ ግፊትን ለመቆጣጠር ያገለግላል፡፡ የጎንዮሽ ጉዳት፡- የፖታሲየምና የሶዲየም መጠን መቀነስ፣ የዩሪክ አሲድ መጠን መጨመር፣ የወንድ ዘር ፍሬ ማነስና የመሳሰሉት መድኃኒቱ የማይወሰድባቸው ሁኔታዎች፡- የስኳር በሽታ፣ የስብ መጠን መዛባት፣ ከባድ የኩላሊት ችግር፣ የሪእ በሽታና ሌሎችም፡፡ 4.ቤታ ብሎ ከርስ (Beta-blockers)፡- ይህ ዓይነት መድኃኒት የልብ ምት፣ የሬኒን መመረት፣ የኖርኢፕንፊን ተግባርና የመሳሰሉት በመቀነስ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ያገለግላል፡፡ ለምሳሌ ፕሮፕራኖሎል፣ አቴኖሎል፣ ሜቶፕሮሎልና የመሳሰሉት የጎንዮሽ ጉዳት፡- የደም ግፊት ማነስ፣ የደረት ሕመም፣ ፈሳሽ መቋጠር፣ ድካም፣ ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ድርቀትና የመሳሰሉት መድኃኒቱ የማይወሰድባቸው ሁኔታዎች፡- እርግዝና፣ ጡት ማጥባት፣ ሳንባ ውስጥ የፈሳሽ መቋጠር፣ የልብ ድካምና የመሳሰሉት፡፡ 5.ሐይድራላዝን (Hydralizine)፡- ይህ ዓይነት መድኃኒት የደም ቧንቧዎችን በማስፋት (Dilating arteries) የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚያገለግል መድኃኒት ነው፡፡ የጎንዮሽ ጉዳት፡- የልብ ምት መጨመር፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ፈሳሽ መቋጠር፣ ራስ ምታት፣ ትኩሳት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ (Anorexia) እና የመሳሰሉት መድኃኒቱ የማይወሰድባቸው ሁኔታዎች፡- የደም ቅዳ በሽታ (Coronary artery disease)፣ የአእምሮ ችግር፣ ከመጠን በላይ የሆነ የልብ ምት መጨመር፣ የልብ ድካምና ድንገተኛ አደጋና ሌሎች ይህ በሽታ ያለበት ሰው መውሰድ ያለበት ጥንቃቄዎች የጎንዮሽ ጉዳት ሲያጋጥም መድኃኒቱን ሳያቋርጡ ለጤና ባለሙያ መናገር ያስፈልጋል፡፡ መድኃኒቱን ሕጋዊ ፍቃድ ካላቸው ተቋማት መግዛት ይገባል፡፡ስለ መድኃኒት አወሳሰድ የጤና ባለሙያን በሚገባ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ @DrSofonias

የልጃችሁ! ፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥ AFRODOCTORS ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦ ግርዛት መከናወን ያለበት በሙያው በሰለጠነ
የልጃችሁ! ፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥ AFRODOCTORS ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦ ግርዛት መከናወን ያለበት በሙያው በሰለጠነ ሰው ብቻ ነው ። የወንድ ልጅ ግርዛት የሚገኝባቸው ቦታዎች:- * ሆስፒታል፣ * ጤና ጣቢያ፣ * ክሊኒክ የልጃችሁ ጤና የተጠበቀ እንዲሆን በግርዛቱ ማግስት ቁስሉ በሐኪም እንዲታይ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህንንም በአቅራቢያ ወደሚገኝ የህክምና ባለሙያ በመሄድ ክትትል ማድረግ ይቻላል። https://t.me/DrSofonias

ለመፀነስ የምትፈልጊ ከሆነ ለእድል መተው ላያስፈልግ ይችላል። የወር አበባ ዑደት በመረዳት እና የመፀነስ አቅምን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን ከተገበርን የመፀነስ እድልን በከፉተኛ መጨመር እንደሚቻል እርግጥ ነው። ኦቩሌሽን ማለት በጤናማ አካል ላይ የሚከሰት የእንቁላል ከሚመረትበት የማህፀን ክፍል ሲለቀቅ ሲሆን በዚህ 6 ቀናት ውስጥ አንድ እንቁላል ከ12-24 ሰአታት ውስጥ ለፅንስ ብቁ የሚሆንበት ጊዜ ነው። ሌላው እውነታ ስፐርም በማህፀን በትክክለኛው ሁኔታ እስከ 5 ቀን ሊቆይ እንደሚችል የታወቀ ነው። ስለዚህ ጊዜውን አስልተን በዚህ አምስት ቀናት ውስጥ ግንኙነት ከተደረገ የመፀነስ እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። በአማካይ የወር አበባ ኡደት በ28 ቀኑ ሊሆን ይችላል። ኦቩሌሽንም ከመጨረሻ ወር አበባ ያየንበት ጀምሮ እስከ 14 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። ግን ከብዛኛው ሴቶች ኦቩሌሽን የሚኖራቸው በወር አበባ ኡደት በአማካይ ባሉት ቀናት ውስጥ ነው። እንደአብዛኛው ሴቶች ወር አበባቸው ለመቁጠር አስቸጋሪ ከሆነ የወር አበባ ካላንደር መጠቀም አንድ አማራጭ ነው። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ከካላደር በተጨማሪ የኦቩሌሽን አካላዊ ምልክቶችን ማስተዋል ሌላ አማራጭ ነው። ከነዚህም መካከል፦ ፨የማህፀን ፈሳሽ ለውጥ- ከኦቩሌሽን በፊት የማህፀን ፈሳሽ ወደ ውሀ መልክ፣እርጥበት ያለው እና የሚዝለገለግ አይነት ይሆናል። ኦቩሌሽን ባለፈ ጊዜ ይሄው ፈሳሽ መጠን መቀነስ፣ደመና መልክ እና ወፍራም ይሆናል። ፨የሰውነት ሙቀት መጨመር- የሰውነት ሙቀት በኦቩሌሽን ጊዜ ይጨምራል። በሙቀት መለኪያ ሰውነትሽን በየቀኑ በመለካት ማወቅ ይቻላል። ኦቩሌሽን ከመምጣቱ 3ቀን ቀደም ብሎ ይህ ሙቀት እንደሚከሰት ይታወቃል። ፨፨የመፀነስ እድልን ለመጨመር ምን ማረግ ይኖርብናል?፨፨ ከላይ በተጠቀሱት በተጨማሪ ፨ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ግንኙነት በየቀኑ ወይም በየአንድ ቀኑ የሚያረጉ ጥንዶች የመፀነስ ከፍተኛ እድል እንዳላቸው ነው። ፨ በየቀኑ ግንኙነት አመቺ ካልሆነ ወር አበባ ከቆመበት ጊዜ ጀምሮ በሳምን ሁለት ወይም ሶስቴ ግንኙነት ማረግ ሌላ አማራጭ ነው። ፨ የሰውነት ክብደትን በጤናማ መንገድ ማስተካከል። የሰውነት ክብደታቸው አናሳ ወይም በጣም ከፍተኛ የሆኑ እናቶች ለመፀነስ እንደሚቸገሩ ጥናቶች ይጠቁማሉ። የጤና ባለሙያ ካነጋገርን የአፈጣጠር ችግሮች እንዳይከሰቱ ፎሊክ አሲድ ለሰውነት ጠቃሚ ንጥረነገር ከመፀነስሽ በፊት ሊያዙ ይችላሉ። ለመፀነስ አዳጋች የሚያረጉ ተግባሮች፦ በአንድም ወይም በሌላ መንገድ መፀነስን የሚከለክሉ ነገሮች አንዱ ማጨስ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ አልኮሆል ነው። እንዲሁም ከተገቢ በላይ ቡና መጠጣትም ፅንስ አፈጣጠር ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳለው ተደርሶበታል። ሌላውና የመጨረሻው መድኃኒቶች ሲሆኑ ያለትእዛዝም ሆነ በትእዛዝ የምንወስዳቸው መድኃኒቶች ፅንስ እንዳይኖር ሊገቱ የሚችሉ ስለሆኑ ሀኪሞን ማማከር ይኖርብሻል። ፨፨መቼ ሀኪሞን ማማከር ይኖሮቦታል፦፨፨ ከ35 እድሜ በታች የሆኑ ጤናማ ጥንዶች ለአንድ አመት ያለ ጥንቃቄ ግንኙነት በማድረግ ለመፀነስ እንዲሞክሩ ይመከራል። 35 እና ከዛ በላይ እድሜ በላይ እና ከዚህ በፊት የመፀነስ ችግር የነበረባቸው ጥንዶች ሀኪም ማማከር ይኖርባቸዋል። በመጨረሻ መካንነት የሴቷ ምክንያት ብቻ ሳይሆን የወንዱም ሊሆን እንደሚችል በመረዳት ከላይ የተጠቀሱትን መንገዶች በመጠቀም መሞከር አማራጭ ሲሆን ከዚህ በላይ አስቸጋሪ ሆኖ ከተገኝ የህክምና ባለሙያዎች በየደረጃው ሊረዷቸሁ እንደሚችሁ መገንዘብ ያስልጋል። @DrSofonias

አንዳንድ ሰዎች የዋሉበት ቦታ ወይም የነበሩበት ሁኔታ አስገድዷቸው የሰውነታቸው ጠረን ይቀየራል። ከዚህ ባለፈ ግን የተጫሙት ጫማ አካባቢያቸው ያለን ሰው ምቾት ሲነሳም ይስተዋላል። እንደ ቀልድ ችላ የሚባል ግን በማህበራዊ ህይዎት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የሚያሳርፈው ይህ መጥፎ የእግር ጠረን ለባለቤቱ ባይታወቅም አጠገቡ ያለን ሰው በመጥፎ ሽታ ምቾት ይነሳዋል። በእግር እና በጫማ ውስጥ በሚፈጠር ከፍተኛ ሙቀት እና የእግር ቁስለት ፣ ባክቴሪያ፣ ለእግር የማይስማሙ የካልሲ ምርቶች እና ጫማዎችን መጫማት ለዚህ ችግር እንደ መንስኤ ይወሰዳሉ። ታዲያ ይህን ከሰው የሚያቆራርጥ መጥፎ የእግር እና የጫማ ጠረን እንዴት መከላከል እንዳለብዎት ከዚህ በታች ያሉትን መፍትሄዎች ይመልከቱ። ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, መፍትሄዎች """"""""""""""""""""""""" ፨፨፨፨፨፨፨ ለእግር ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ 1~ሻይ ቅጠል ሁለት ጥቅል የሻይ ቅጠሎችን በሶስት ብርጭቆ ውሃ ማፍላት እና ከፈላ በኋላ በማውጣት። ከዛም በግማሽ ባልዲ ውሃ ቀዝቀዝ ማድረግ እና የውሃ ሙቀቱ ለእግር ተመጣጣኝ ከሆነ እግርን ዘፍዝፎ ከ15 እስከ 20 ደቂቃዎች ማቆየት እና ለሳምንት ያህል ይህን መደጋገም። 2~ ዝንጅብል መካከለኛ ቁመት ያለውን ዝንጅብል በመቆራረጥ እና ለ15 ደቂቃዎች ያህል ውሃ በመጨመር ማፍላት። ቀጥሎም ፈልቶ የወረደው ዝንጅብል ላይ የተወቀጠ የቡና ዱቄት መጨመር። ከዛም የሁለቱን ውህድ በአግባቡ አማስሎ በመቀላቀል ውስጠኛውን የእግር ክፍል ዘወትር ከመኝታ በፊት ለተከታታይ ሁለት ሳምንት በአግባቡ አዳርሶ ማሸት። 3~ ጨው እግርን ለብ ባለ ጨዋማ ውሃ መዝፍዘፍም ሌላው መፍትሄ ነው። አንድ ተኩል የሾርባ ማንኪያ ጨውን በአንድ ጆግ ውሃ በማፍላት ቀዝቀዝ አድርጎ እግርን ለ20 ደቂቃ መዝፈዝፍና ይህንንም ለሁለት ሳምንታት ያህል መሞከር። 4~ አልኮል እግርን በደንብ ታጥቦ ማፅዳት እና ማደራረቅ ቀጥሎም የተወሰነ አልኮልን ውስጠኛው እግር ላይ በማፍሰስ ማዳረስ እና ማሻሸት በደንብ ሲደርቅም እግርን አናፍሶ ከደቂቃዎች በኋላ ጫማ ማድረግ። ፨፨፨፨፨፨ መጥፎ ጠረን ላለው ጫማ ፨፨፨፨፨፨፨፨ 1~ ጫማውን አደራርቀውና በአልኮል የተነከረ ስፖንጅ ወይም ቀጠን ያለ አሮጌ ፎጣን ተጠቅመው ጫማው ውስጥ ማስቀመጥ ለተወሰነ ጊዜ በዛ መልኩ ማቆየት። ቀጥሎም ጫማዎን ማደራረቅ እና አናፍሶ መጠቀም። 2~ ከዚህ ባለፈም 4 ተነክረው የወጡ የሻይ ቅጠል ጥቅሎችን ያስቸገረዎት ጫማ ውስጥ ለአንድ ሌሊት አስቀምጦ ማውጣትና ጫማውን አደራርቆ መጠቀምም ይቻላል። ይህን ሲያደርጉ ጫማው ውስጥ የተፈጠረው አላስፈላጊ እና አስቸጋሪ ሽታ ከላይ በተጠቀሱት ውህዶች አማካኝነት ተመጦ መውጣት እና መስተካከል ይጀምራል። ከዚህ ባሻገር ግን ጫማን ቶሎ ቶሎ እና በአግባቡ ማጽዳት። ካልሲን በየጊዜው መቀየያር እና ማጽዳት። አንድን ጫማ በተለይም ደግሞ ካልሲን ከአንድ ቀን በላይ አለማድረግ። ሁልጊዜ የሚያደርጉትን ሽፍን ጫማ መቀየር እና ሰንደል ወይም ክፍት ጫማዎችን መጫማት እና መጠቀም ከሚፈጠር የእግር ውስጥ ሙቀት እና ላብ እና ያንን ተከትሎ ከሚመጣ አላስፈላጊ ሽታ እና መጥፎ ጠረን ለመዳን ይረዳል። ከናይለንና ፖሊስተር የተሰሩ የካልሲ ምርቶችም ለዚህ ችግር መንስኤዎች ናቸውና ባለሙያዎች አይጠቀሟቸው ሲሉም ይመክራሉ። እናም በደረሱበት ቦታ ጫማዎን አውልቀው እና ቀለል ብሎዎት መዝናናት እና መጫዎት ፈልገው ባለው አመል ምክንያት ፍላጎትዎን እንዳይገድቡ መፍትሄወቹን በአግባቡ ይጠቀሙባቸው። ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, አይርሱ... """"""""""""""" ከላይ የተጠቀሱትን መፍትሄዎች ተጠቅመው ካልተሻሎት የህክምና ባለሙያ ያማክሩ! @DrSofonias

ፎሮፎር እንዴት ይከሰታል? ፎሮፎር የአለም ግማሹን ህብረተሰብ የሚያጠቃ ችግር ሲሆን ማሳከክ እና ነጭ ብናኝ የሚፈጥር የፀጉር ችግር ነው። ፎሮፎር በምን ይከሰታል ፨በላብ አመንጪ ህዋሶች ፨የቆዳ ፈንገስ ክምችት ፨በደንብ አለመታጠብ ወይም ቶሎ ቶሎ ፀጉር በመታጠብ ጸጉር እንዲደርቅ ማድረግ ፨የቆዳ ድርቀት ፨ፀጉርን ከሚገባው በላይ ማበጠርና ከፍተኛ ፍትጊያ በመፍጠር ፨ማላሴዝያ የሚባል ጭንቅላት ላይ የሚገኝ ህዋስ ፨ከፍተኛ ፀሀይ ብርሀን ፨ከፍተኛ ፀጉር ላይ የሚፈጠር የመጨፍለቅ ጫና (ኮፍያ ሁልጊዜ ማድረግ) ፨አመጋገብ ፨ለአቧራ ተጋላጭነት ወንዶች ከሴቶች በላይ ፎሮፎር ይገኝባቸዋል። ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት አንዳንድ ሰዎችም ከሌላው በላይ ተጋላጭ ይሆናሉ። ቅባታማ ፀጉር ያላቸው እና በተለይ ልክ እንደ ኤች.አይ.ቪ ተጓዳኝ በሽታ ያላቸው የበለጠ ለፎሮፎር ተጋላጭ ናቸው። ፨፨፨፨ በቤት ሆነን ምን መፍትሄ እናገኛለን፨፨፨ ፨ እርሾ በዝግታ በማረግ ከትንሽ ደቂቃ በኃላ መታጠብ ፨ አፕል ሳይደር ቪኒግር የተባለ በብርጭቆ1/4 በማድረግ ከ1/4 ብርጭቆ ውሀ ጋር በማቀላቀል ፀጉር ላይ ከ15-60 ደቂቃ ማድረግ ቀጥሎም መታጠብ። ይህንን በሳምንት ሁለቴ ማድረግ። ፨ የኮኮናት ቅባት፦ ሁለት ማንኪያ ፀጉርን በመቀባት ከአንድ ሰአት በኃላ መታጠብ። ፨ ሎሚ፦ ሁለት ማንኪያ ሎሚ በማድረግ ከትንሽ ደቂቃ በኃላ መታጠብ። ቀጥሎ እንደገና አንድ ማንኪያ ሎሚ ከውሀ ጋር በማድረግ መቀባት። ይህንን በየቀኑ ማድረግ። ፨አሎ ቬራ፦ ፀጉር ከመታጠባችን በፊት የጭንቅላት ቆዳን በደንብ መቀባተ። ፨የወይራ ዘይት፦ ማታ እስከ 10 ነጠብጣብ ድረስ ፀጉርን በማድረግ አሳድሮ ጠዋት በሻምፖ መታጠብ። ፨፨፨፨፨ በህክምና ምን ሊደረግ ይችላል፨፨፨፨ ዋነኛው ለፎሮፎር ህክምና የፎሮፎር ሻምፖ እና የጭንቅላት ቆዳ ህክምናዎች ናቸው። ይህንን ተግዳሮቶች እንከተል፦ የተለያዩ የፎሮፎር ሻምፖ አሉና እላያቸው ላይ የተፃፉ ትእዛዞችን መከተል ያስፈልጋል። ከተቀባን በኃላ ምንያህል መቆየት አለብን የሚለውን ማስተዋል ያስፈልጋል። የተለያዩ አይነት ፀጉሮች የተለያየ አይነት እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል። ትክክለኛው አማራጭ የቆዳ ስፔሻሊስት በማማከር ለፀጉራችሁ ተገቢውን የሻምፖ አይነት መገንዘብ እና መጠቀም ነው። አንዴንድ ሻምፖ የመድኃኒትነት መጠናቸው ከፍ ያለ ስለሆነ ፋርማሲ ብቻ ወይም በሀኪም ትእዛዝ ብቻ ሊያገኙ ይችላሉ። ከነዚህም ውስጥ፦ ኬቶኮናዞል፣ሰሊንየም ሰልፋይድ፣ኮል ታር እና ዚንክ ፓይሪቲዬን ናቸው። ጤና ይስጥልኝ!! ለበለጠ የጤና መረጃዎች በቴሌግራም ይከታተሉን። ፕሮ ኬር በቅርቡ የነፃ ስልክ ጥሪ ስለሚጀምር ይከታተሉን። @DrSofonias

ለሴቶች እህቶቼ ጠቃሚ መልእክት በደንብ ይነበብ ለጥፍሮችሽ ምን ያህል ትኩረት ትሰጪያለሽ ለቁንጅናዋ የምትጨነቅ ማንም ሴት ለጥፍሮቿ ጤንነትና ውበት ትጨነቃለች፡፡ ምክንያቱም ጥፍሮች አንዱ የወበት መገለጫ ናቸው እና፡፡ ጥፍሮች የኬራንቲን እርብርቦች ናቸው፡፡ የጥፍር ሥር ያሉት ሕዋሳት በመባዛት ጥፍር የሚገነቡ ሲሆን ከዚያ በታች ያሉት ደምስሮች ደግሞ ለእድገት የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች ኦክስጂን ያቀርባሉ፡፡ ከጥፍሮች ስር ነጣ ብለው የሚታዩና ገና እንደምትፈነድቅ ጸሐይ በግማሽ የሚታዩት የጥፍሮችሽ ክፍል ህዋሳትና ደም ሥር ያሉበት አካባቢ ነው፡፡ ጥፍሮችሽን በደንብ ለመንከባከብ የሚከተሉትን ጠቃሚ ምክሮች ተከተይ 1. ጥፍርሽን በአጭሩ ቁረጪ፡፡ በአካባቢው ያለው ቆዳ እንዳይጎዳ ጥንቃቄ አድርጊ፡፡ 2. የእግር ጥፍርሽን ስትቆርጪ በቀጥታ መስመር ቁረጪ፡፡ከዳርና ዳር ወደ ውስጥ ገባ አድርገሽ ከቆረጥሽ ጥፍሩ ሰውነትሽ ውስጥ ስለሚገባ፣ሊቆስልና ችግር ሊያመጣ ይችላል፡፡ 3. ከባድና አደገኛ ሥራ በእጅሽ አትስሪ ፣ጓንት ወይም ሽፋን አድርጊ፡፡ 4. ጥፍርሽ አካባቢ ያለው ቆዳ እየተሰነጣጠቀ እንዳያስቸግርሽ (ፈለግ እንዳይኖር ) ቆዳዎችሽን በወር አንድ ጊዜ ወደ ኃላ ግፊያቸው፡፡ በደረቁ መግፋት የሚያምሽ ከሆነ መጀመሪያ ሞቅ ያለ ውሃ ውስጥ ጠፍሮሽችን ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዘፍዝፊያቸው፡፡ ከዚያ በኃላ ጠፍጠፍ ባለ ነገር (ለዚሁ ተብለው በሚሸጡ መሳሪያዎች) በጠፍጣፋ እንጨት ወይም ማንኪያ ወደ ኃለ መግፋት ትችያለሽ፡፡ 5. የጥፍር ማበጥ የውስጥ አካል በሽታዎች ምልክት ሊሆን ስለሚችል ሐኪም አማክሪ፡፡ 6. ጥፍሮችሽን የመብላት ልምድ ካለብሽ ይሄንኑ ለማቆም ጥረት አድርጊ፡፡ መልካም ልምምድ መልካም አዲሱ አመት የጤና ጊዜ ይሁንላቹ

#የሆድ_ድርቀትን_የሚያባብሱ_8_ምግቦች """""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""" ዘወትር የሆድ ድርቀት የሚያጋጥምዎ ከሆነ ለአመጋገብዎ ትኩረት መስጠት ይኖርብዎታል። ብዙ የምንበላቸው ምግቦች ለሆድ ድርቀት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። የሚከተሉት ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ ሆድ ድርቀት እንዲፈጠር ያደርጋል መጥኖ መመገብ ይገባል። 1) የወተት ምርቶች ወተትን አብዝቶ መጠጣት ወይም ቺዝ አዘውትሮ መመገብ የሆድ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል። ነገር ግን የወተት ምርቶችን ሙሉ በሙሉ ማቆም ላይኖርብን ይችላል። የምንወስደውን መጠን መቀነስ ብዙ ግዜ በቂ ነው። 2) በዘይት ተነክረው የሚጠበሱ ምግቦች በዘይት ውስጥ ተነክረው የሚጠበሱ ብዙ ምግቦች የስብ መጠናቸው ከፍተኛ ነው። እነዚህን ምግቦች አንጀት በቀላሉ መፍጨት ስለማይችል ምግቡ በአንጀት ሲያልፍ ቀስ ብሎ ነው። ምግብ በአንጀት የሚያልፍበት ፍጥነት ዘገምተኛ ሲሆን አንጀት ከምግቡ በበለጠ ሁኔታ ውሃ ይመጣል። እንዲህ ሲሆን ሰገራችን ደረቅ እና የጠነከረ ይሆናል። 3) እንቁላል እንቁላል ጥሩ የፕሮቲን ምንጭ ቢሆንም የፋይበር መጠኑ ዝቅተኛ ነው። እንቁላልን መብላት ማቆም የለብንም። ነገር ግን የፋይበር መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ምግብ አብሮ መብላት ይመከራል። እንቁላልን በቲማቲም ወይም በአትክልት መስራት ጥሩ አማራጭ ነው። 4) ስጋ ስጋ የፕሮቲን እና ፋት ምንጭ ነው። የፋይበር መጠኑ ግን አነስተኛ ነው። ስጋን ልክ እንደ እንቁላል ከሌላ የፋይበር መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ ምግብ ጋር አብሮ መብላት ይመከራል። 5) ጣፋጭ ምግቦች እንደ ብስኩት እና ኬክ አይነት ጣፋጭ ምግቦች የስኳር እና ፋት መጠናቸው ከፍተኛ፥ የፋይበር እና ፈሳሽ መጠናቸው ዝቅተኛ ናቸው። የሆድ ድርቀት ለሚያስቸግራቸው ሰዎች ብዙ አይመከሩም። ለተሟላ ጤንነት ጣፋጭ ነገሮችን አልፎ አልፎ እንጂ አዘውትረን መመገብ የልብንም። 6) ነጭ ዳቦ ነጭ ዳቦ አብዝቶ መመገብ የሆድ ድርቀት ያስከትላል። ነጭ ዳቦ የሚሰራበት ነጭ ዱቄት የፋይበር መጠኑ ዝቅተኛ ነው። ካገኘን ሆል ግሬይን ዳቦ ብንመገብ ለሆድ ልስላሴ የትሻለ ይሆናል። 7) ቡና ብዙ ኩባያ ቡና መጠጣት የሆድ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል። ቡና እና ለስላሳ መጠጦች ውስጥ ያለው ካፊን በሰውነት ውስጥ ውሃ እንዳያቀመጥ ሊያደርግ ይችላል። የሆድ ድርቀት ካለብዎ ከአንድ ስኒ ቡና በላይ እንዳይጠጡ ይመከራል። 8. አልኮል ልክ እንደ ቡና አልኮል መጠጦች ሰውነት ውሃ እንዳያጠራቅም ሊያደርጉ ይችላሉ። ለሆድ ድርቀት መጠጥ አለማብዛት ይመከራል። መልካም ጤንተት @DrSofonias

የኪንታሮት ህመም (ሄሞሮይድስ) የኪንታሮት ህመም በታችኛ የትልቁ አንጀትና ፊንጥጣ አካበቢ ያሉ የደም መልስ( veins) የደም ቧንቧዎች በሚያብጡበትና በሚቆጡበት ወቅት የሚከሰት የህመም አይነት ነዉ፡፡ የኪንታሮት ህመም ሰገራ በሚወጡበት ወቅት ሲያምጡ፣ ወይም በፊንጥጣና በታችኛዉ የትልቁ አንጀት አካበቢ ባሉ የደም ስሮች ላይ እንደ እርግዝናና ሌሎች ጭነትን ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት የሚከሰት ነዉ፡፡ ኪንታሮት በታችኛዉ የትልቁ አንጀት ዉስጥ የሚገኙ የዉስጠኛዉ ኪነታሮት(internal hemorrhoids) ወይም በፊንጥጣ ዙሪያ ባለዉ ቆዳ ስር የሚታይ የዉጨኛዉ ኪንታሮት (external hemorrhoids) አይነት በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡ የህመሙ ምልክቶች • የኪንታሮት ህመም ምልክቶች እንደኪንታሮቱ ቦታ የሚወሰን ሲሆን የዉስጠኛዉ የኪንታሮት አይነት ብዙዉን ጊዜ በአይን የማይታይ ቢሆንም በሚፀዳዱበት ወቅት ማማጥ ካለዎ የደም ስሮቹ ሊቆጡና በቀላለ ሊደሙ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ በሚያምጡበት ወቅት የዉስጠኛዉ ኪንታሮት አይነት ወደታች በመምጣትና በፊንጥጣ ዉስጥ በማለፍ ህመምና የመቆጥቆጥ ስሜት ሊኖረዉ ይችላል፡፡ • የዉጪኛዉ የኪንታሮት አይነት በፊንጥጣ ዙሪያ ባለዉ ቆዳ ስር የሚገኝ ሲሆን የደም ስሮቹ በሚቆጡበት ወቅት ሊያሳክኩ ወይም ሊደሙ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ ደም በዉጭኛዉ ኪንታሮት ዉስጥ በመጠራቀምና በመርጋት ከፍተኛ ህመም፣ እብጠትንና መቆጣትን/መለብለብን ሊያመጣ ይችላል፡፡ • በሚፀዳዱበት ወቅት/ሰገራ በሚወጡበት ወቅት ከፊንጥጣ የሚወጣ ህመም የሌለዉ ደም/መድማት፡- ይህን ክስተት በመፀደጃ ሳህን ላይ ወይም በሶፍት ላይ ሊያዩ ይችላሉ፡፡ • በፊንጥጣ አካባቢ የማሳከክ ወይም የማቃጠል ስሜት ካለዎ • በፊንጥጣ አካባቢ ህመም ወይም ምቾተ ያለመሰማት ካለዎ • በፊንጥጣ ዙሪያ እብጠት ካለዎ • የሰገራ ማምለጥ ካለዎ የህክምና ባለሙያ ማየት የሚገባዎ መቼ ነዉ? ምንም እንኳ ለኪንታሮት ዋነኛ ምልክቱ በሚፀዳዱበት ወቅት የደም መፍሰስ ቢሆንም በፊንጥጣ ደም መምጣት ሁሌ ከኪንታሮት ጋር ብቻ የተያዘ ሳይሆን እንደ የትልቁ አንጀት ካንሰር ወይም የፊንጥጣ ካንሰር ምልክትም ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ • ኪንታሮት ህመም ካለዉ፣ በተደጋጋሚ ወይም በጣም የሚደማ ከሆነ፣ወይም በኪንታሮት ማስታገሻ ህመሙ የማይሻሻል ከሆነ • ከኪንታሮት የህመም ምልክቶች ጋር አስፋልት/ሬንጅ የመሰለ ሰገራ ካለዎ፣የረጋ ደም ካለዎ፣ከሰገራዎ ጋር ደም ካዩ • በጣም ከፍ ያለ የደም መፍሰስ ካለዎ፣ የመደበር ወይም የማዞር ስሜት ካለዎ የኪንታሮት ምክንያቶች ኪንታሮት በፊንጥጣ ዙሪያ ባሉ የደም መልስ ላይ ጫና በሚበዛበት ወይም በሚፈጠርበት ወቅት የደም ስሮቹ ስለሚያብጡና ስለሚወጠሩ የህመሙ ምልክቶች ይታያሉ፡፡ በደም ስሮቹ ላይ ጫና እንዲጨምር ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ • በሚፀዳዱበት ወቅት ማማጥ ካለ • መፀዳጃ ላይ ለረጅም ጊዜ መቀመጥ • ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት ረዘም ላለ ጊዜ ከነበረዎ • ውፍረት መኖር • እርግዝና • የፋይበር መጠናቸዉ አነስተኛ ወይም ፋይበር የሌላለቸዉን ምግቦች ማዘዉተር ናቸዉ፡፡ የኪንታሮት ህመም ጉዳቶች • የደም ማነስ እንዲከሰት ያደርጋል • የኪንታሮት መታነቅ/ Strangulated hemorrhoid ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች • የህክምና ባለሙያዎ አካላዊ ምርመራ በፊንጥጣዎ ላይ ሊያደርጉልዎ ይችላሉ • የህክምና ባለሙያዎ የሚከተሉት ችግሮች ሊኖረዎ ይችላሉ ብለዉ ካሰቡ እንደ ኮሎንስኮፒ ያሉ ከፍ ያለ ምርመራ ሊያደርጉልዎ ይችላሉ -ከኪንታሮቱ በተጨማሪ ሌላ የትልቁ አንጀት ችግር ይኖራል ብለዉ ካሰቡ -ለትልቁ አንጀት ካንሰር ተጋላጭነት ካለዎ -እድሜዎ ከ50 አመት በላይ ከሆነና በቅርቡ የኮሎንስኮፒ ምርመራ አድርገሁ የማያዉቁ ከሆነ ለኪንታሮት ህመም ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች ብዙዉን ጊዜ ለኪንታሮት ህምመ ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ እንደ የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ያሉና እርስዎ በራስዎ ሊተገብሩት የሚችሉ እርምጃዎችን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡አንዳንዴ ደግሞ ለኪንታሮት የሚሰጡ መድሃኒቶችንና መለስተኛ የቀዶ ጥገና የህክምና ዘዴዎች ሊደረጉልዎ ይችላሉ፡፡ መድሃኒቶች የኪንታሮት ህመምዎ መጠነኛ የሆነ ምቾት ያለመሰማት ወይም መጠነኛ ህመም ብቻ ከሆነ ያለዉ በኪንታሮቱ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ወይም በፊንጥጣ ሊደረጉ የሚችሉ ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ መድሃኒቶች ህመሙን ለተወሰነ ጊዜ ስለሚያስታግሱልዎ ገዝተሁ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የህክምና ባለሙያዎ ካላዘዘልዎ በስተቀር ያለሀኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ መድሃኒቶች እንደ የቆዳ መሳሳሰትን፣ የቆዳ መቆጣትንና ሽፍታን የመሳሰሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊያመጡ ስለሚችሉ ከአንድ ሳምንት በላይ መጠቀም የለብዎትም፡፡ @DrSofonias

ሰውነት ላይ የሚታዩ የጤና እክል ማስጠንቀቂያዎች በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚታዩ ውጫዊ ገጽታዎች ስለ አጠቃላዩ የጤና ደህንነት ብዙ እንደሚናገሩ ጥናቶች ያሳያሉ። በውጫዊው የሰውነት ክፍል ላይ የሚታይ ምልክትም ውስጣዊ የጤና ችግር ስለመኖሩም ማሳያ ነው።እነዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምልክቶች ደግሞ አንዳች የጤና እክልን ማሳያዎች ናቸው። ■ አይን፦የአይን የታችኛው ቆዳ ላይ የሚታይ የመሸብሸብ እና የማበጥ ምልክት ሲኖር፥ ጨው የበዛበት ምግብ አብዝተው በመውሰድ ጤናዎን አደጋ ላይ እየጣሉ መሆኑን ያሳያል።ከዚህ ባለፈም ከፍተኛ መጠን ያለው የአልኮል መጠጥ እየጠጡ ከኩላሊት ጋር የተያያዙ የጤና እክሎችን እያስተናገዱ ነው። ምናልባትም ሲወስዷቸው ለእርስዎ ሰውነት የማይስማሙ የምግብ አይነቶች እንዳሉም ማሳያ ነው፤ ወተትና የወተት ተዋጽኦ ወይም ደግሞ የስንዴ ዘሮች።የአይንዎ ቀለም ወደ ቢጫነት ከተቀየረ ደግሞ የጉበት በሽታ ተጠቂመሆንዎን ያመላክታል:: ■ ቆዳ፦የእርጅና ምልክት ተደርጎ የሚታሰበው የቆዳ መሸብሸብ ከአጥንት ጋር የተያያዙ ከፍተኛ ችግሮች መከሰታቸውን ማሳያም ነው።አየሩ ቀዝቀዝ ሲል ደረቅ፣ የቀለም መቀየር እና የሚያሳክክ ምልክት በቆዳ ላይ ሲከሰት ደግሞ፤ ከመተንፈሻ አካል ጋር የተያያዘ የጤና እክል እንዳለ የሚያመላክት ነው።የቆዳ ላይ ሽፍታ እና ቀይ ነጠብጣብ ምልክቶች ደግሞ፤ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ድብርት እና ፍርሃት ሲበዛ የሚከሰቱ ናቸው። ■ ፀጉር፦በጊዜ ሂደት የሚፈጠር የፀጉር መሳሳትም፥ ከጭንቀት፣ ከተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ አልፎ አልፎም በእርግዝና ወቅት፣ በሚወሰድ የወሊድ መከላከያ መድሃኒት፣ የክብደት መቀነስ እና መጠነኛ የጤና እክል መኖሩን ማሳያ ነው። ■ ከንፈር፦ደረቅ እና የተሰነጣጠቀ ከንፈር ሰውነት ከፍተኛ የሆነ የፈሳሽ መጠን እንዳነሰው ማሳያ ነው።ሰውነት የሚያስፈልገው ቅባት ሲያንሰው እና ይህን ተከትሎም መገጣጠሚያ አካባቢ ችግር መፈጠሩንም ያመላክታል።የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም መዳከሙንና በባክቴሪያ ወይም በሌላ ተዛማጅ ቫይረስ ከንፈር ላይ ጉዳት መድረሱን ማሳያም ነው። ■ ጥፍር፦ጥፍር ሲሰነጠቅ እና ሲሰረጎድ ሰውነት ውስጥ ያለ የብረትመጠን ማነስ፣ የደም ማነስ እና ከልብ ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለ ማሳያ ይሆናል።ጥፍር አብዝቶ ነጭ ሲሆን ወይም ሃምራዊ የሚመስል ቀለም ሲይዝ ደግሞ የጉበት እና ኩላሊት ላይ አደጋ ስለመኖሩ ማሳያ ነው። እናም እነዚህ ምልክቶች ሲከሰቱ ችላ ከማለት የህክምና ባለሙያ ማማከር እና ተገቢውን ክትትል ማድረጉ አስፈላጊ ነው። @DrSofonias