en
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Open in Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 19 977 subscribers, ranking 1 154 in the Medicine category and 1 680 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 19 977 subscribers.

According to the latest data from 25 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -558 over the last 30 days and by -23 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 22.78%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 5.94% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 556 views. Within the first day, a publication typically gains 1 188 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 11.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 26 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Medicine category.

19 977
Subscribers
-2324 hours
-1207 days
-55830 days
Posts Archive
የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል 99 በመቶ ውጤታማ ሆኗል ተባለ በሚዋጥ እንክብል መልክ የተዘጋጀው የወሊድ መከላከያው እርግዝናን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ነው ተብሏል አዲሱ የወሊድ መከላከያ በሴቶች ላይ ብቻ የነበረውን ጫና ያቃልላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል አዲስ እየተዘጋጀ ያለው የሚዋጥ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል እርግዝናን በመከላከል ረገድ 99 በመቶ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ። የወሊድ መከላከያ እንክብሉ በአይጥ ላይ በተደረገ ሙከራ እርግዝናን ለመከላከል ውጤታማ መሆኑ እንደተረጋገጠ ስካይ ኒውስ ዘግቧል። በቅርቡ በአሜሪካ ኬሚካል ሶሳይቲ ስብሰባ ላይ ግኝታቸውን ያቀረቡት ተመራማሪዎች፤ አዲሱ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል። አዲሱን ግኝት ያቀረቡት ዶክተር በአብደላ አል-ኖማ፤ ተመራማሪዎች ለአስርት ዓመታት ያክል በአፍ የሚወጥ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ለመፍጠር ሲጥሩ ቆይተዋል፤ ሆኖም ግን እስካሁን እውቅና የተሰጠው መድሃኒት በገበያ ላይ የለም ብለዋል። የወንዶች የወሲብ ሆርሞን ቴስቴስትሮንን ኢላማ ያደረጉ በርካታ ክሊኒካል ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን ያነሱት ዶክተር አብደላህ፤ ሆኖም ግን ከልክ ያለፈ የሰውነት ውፍረትን፣ ድብርትን እና ሌሎች የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ ናቸው ብለዋል። አሁን የተሰራው የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ግን ከሆርሞን ጋር ግንኙነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ፤ በቅርቡ በሰዎች ላይ ሙከራ ማድረግ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። አዲሱ የወሊድ መከላከያ በሴቶች ላይ ብቻ የነበረውን ጫና ያቃልላል የሚል ተስፋ እንደጣለበት ተነግሯል። ምክንያቱም ሴቶች እርግዝናን ለመከላከል የተለያዩ መድሃቶችን ከመዋጥ ጀምሮ ማህፀን ውስጥ የሚገቡ መሳሪያዎችን እስከመጠቀም ይገደዳሉ። በተቃራኒው ወንዶች ግን ኮኖዶምን የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ከዚህ ከዘለለ “ቫሴክቶሚ” የተባለ እና በቋሚነት እንዳይወልዱ የሚያደርገውን የቀዶ ጥገና አማራጭ ብቻ ነው ያለው። በወንዶች ላይ ለወሊድ መከላከያ የሚደረገው “ቫሴክቶሚ” የተባለው ቀዶ ጥገና ህክምና በዋጋው ውድ ሲሆን፤ ብዙም ስኬታማ እንዳልሆነ ይነገራል።

ፓፓያ እና ዉበት 👉የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ ፓፓያ ለቆዳ፣ ፀጉር እና ለጤናችን የሚያበረክተው ጥቅም የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ • የቆዳ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ • ጥሬ ፓፓያ ፊትዎን ለ 25 ደቂቃ በመቀባት ፊት ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ያበጡ ነጠብጣቦችን በቀላሉ ማስወገድ ይችላሉ፡፡ • ፓፓያን በቀጥታ ቆዳዎን በመቀባት ወይም በመመገብ የሚያምር ለስላሳ ቆዳን መጎናፀፍ ይቻላሉ፡፡ • የተፈጨ ፓፓያ የተሰነጣጠቀ ተረከዝን ለማከም ይጠቅማል፡፡ • ተፈጥሮአዊ የሞቱ ሴሎችን ከቆዳ ላይ ማስወገጃ መንገድ ነው፡፡ • የቆዳን ተፈጥሮአዊ ቀለም ለመመለስ ይረዳል፡፡ • ለሆድ ትላትል ህክምናነት ይጠቅማል፡፡ • በቆዳ ላይ የሚታዩ የእርጅና ምልክቶችን ለመቀነስና ለማከም ይረዳል፡፡ • ጥቁር ነጠብጣቦችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ • ራሰ በራነትን ይከላከላል፣ የፀጉር እድገትንና ጥንካሬን ይጨምራል፡፡ የፓፓያ ፍሬ ምን ያህል ለጤና ጠቃሚ እንደሆነስ ያውቃሉ?? አብዛኞቻችን ፓፓያ ገዝተን ከበላን በኋላ ፍሬውን እንጥለዋልን። ይህን ያውቁ ይሆን ??? የፓፓያ ፍሬ ምን ያህል ለጤና ጠቃሚ እንደሆነ በዛሬው ፖሰታችን ላይ ስለ ፓፓያ ፍሬ ጥቅም እናሳውቃችኋለን!!! የፓፓያ ፍሬ የጤና ጥቅም • የፓፓያ ፍሬ በውስጡ አልካሎይድነት ስላለው በሆድ ውሰጥ የሚገኙትን ትላትሎች ያስወግድልናል • እንደ አንቲ ባክቴሪያነት ጥቅም ስላለው ጎጂ የሆኑትን ባክቴሪያዎችን ያስወግድልናል • የፓፓያ ፍሬ ያልተለመደ የካንሰር ሴሎችን እድገታቸውን ይገታል / ከጡት ካንሰር ፣ ከሳንባ ካንስር ፣ከደም ካንሰር ይከላከልልናል • የጉበት ጤንነትን ይጠብቃል - ጉበት በአብዛኛውን ስራዋ መርዛማ የሆኑ ነጥረ ነገሮችን ማስወገድ ነው ስለሆነ ይህን ስራዋን በተሳካ ሁኔታ እንድትፈፅም ይረዳታል • በቫይረስ አማካኝነት የሚመጡ ኢንፌክሽኖችን ይከላከልልናል @DrSofonias

#ይሉኝታ እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ይነበብ #ይሉኝታ_ምንድን_ነው? ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት ነው፡፡ #የይሉኝታ_መንስኤዎች ✿ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት ✿በራስ መተማመን ማነስ ✿ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ ✿የውስጥ መረጋጋት ከሌለን ✿አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ ✿ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡- በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ #ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች ✿ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ? ✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ ✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ ✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ ✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር ✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር ✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል @DrSofonias

ሮዝሜሪ ማሽተት ንቁነትን ይጨምራል እና የማስታወስ ችሎታን ያሻሽላል ስለዚህ ከፈተና ወይም ከአስፈላጊ ስብሰባ በፊት ቀጥፈው ይያዙ።
ሮዝሜሪ ማሽተት ንቁነትን ይጨምራል እና የማስታወስ ችሎታን ያሻሽላል ስለዚህ ከፈተና ወይም ከአስፈላጊ ስብሰባ በፊት ቀጥፈው ይያዙ።

ጤና ይስጥልኝ ለመሆኑ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት ለምን ያህል ጊዜ መቀመጥ እንዳለበት ያውቁ ይሆን? ቀይ ሽንኩርት በተቻለ መጠን ሳይከተፍ ከነ ሽፋኑ ቢቀመጥ እጅግ ይመረጣል። ከተፍው ማስቀመጥ ከፈለጉ ፍሪጅ ውስጥ አድርገው እስከ 7 ቀን መጠቀም ይችላሉ። ከዚህ ውጭ ግን ቀይ ሽንኩርትን ከተፎ ማስቀመጥ በራስ ላይ መፍረድ ነው ይሉናል ጥናቶች። ምክንያት፤ ቀይ ሽንኩርት ተከትፎ በከባቢ አየር ላይ ከተቀመጠ እጅግ መርዛማ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው ብዙ መርዛማ ባክቴሪያዎች ለማደግና ለመራባት የተከተፈ ቀይ ሽንኩርትን በፍቅር ስለሚወዱት ነው ይለናል። እግረ መንገዴን አንድ ሚስጥር ላካፍላችሁ። ሽንኩርት ስንከትፍ አይናችን ለምን ያለቅሳል? ቀይ ሽንኩርት ጠረኑን ከሰጡት ኬሚካሎች አንዱ ሰልፈር(sulphur) ነው። ነገር ግን የሚያስለቅሰን ሰልፈሩ እራሱ አይደለም። ቀይ ሽንኩርት ሴንቴዝ (synthase) የሚባል ኢንዛይም በውስጡ ይዟል። ይሄ ኢንዛይም (enzyme) ሽንኩርት መክተፍ ስንጀምር ሰልፈሩን ሲን- ፕሮፔንታየል- ሰልፈር -ኦክሳይድ (syn-Propanethial S-oxide.) ወደ ተባለ ትነት ወይም ጋዝ ይቀይረዋል። ይህ ጋዝ በተፈጥሮ አይን ስለሚቆጠቁጥ ያስለቅሰናል ማለት ነው። ነገር ግን ከመቆጥቆጥ ያለፈ የጤና ጉዳት አያመጣም። ሽንኩርት ሲከትፉ በጣም ከተቸገሩ የሚከተሉት ዘዴዎች ይጠቀሙ 👉 ሽንኩርቱን ከመክተፍዎ በፊት ከ 15-30 ደቂቃ ያቀዝቅዙት። ይህም ኢንዛይሙን ስለሚያደክመው ብዙ ጋዝ እንዳያመርት ያደርገዋል። 👉ቬንትሌተር ይጠቀሙ ይህም የቬንትሌተሩ አየር ጋዙን በንፋስ ጠራርጎ ከእርስዎ እንዲያርቀው ይረዳል 👉 እንግዲህ ከላይ በጠቀስኳቸው ሁለት መንገዶች ካልተሳካልዎት ምንም ማድረግ አልችልም መከላከያ መነፅር (goggles) ይጠቀሙ። የረሳሁት ነገር ጆሮ ላይ ሽንኩርት ልጣጭ ማድረግ ፈፅሞ ከማንባት አያድንዎትም። 😊 ጠቃሚ ነውና share ያርጉት @DrSofonias

የወር አበባ በየወሩ በሴቶች ላይ በሚከሰትበት ጊዜ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያውቃሉ? በወር አበባ ጊዜ ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች ! የወር አበባ የሴቶች ወርሀዊ ኡደት ሲሆን አንድ ሴት የመራቢያ እንቁሎችን ሰውነቷ ማምርት ከሚጀምርበት የእድሜ ክልል ጀምሮ እስከ ማረጥ ወይም ሰውነቷ እንቁላልን ማምረት እስከሚያቆምበት ጊዜ ድረስ በየወሩ የሚመጣ ነው፡፡ ታዲያ ይህ የወር አበባ በየወሩ በሴቶች ላይ በሚከሰትበት ጊዜ ተገቢውን ጥንቃቄ ካልተደረገ ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊያስከትል ይችላል፡፡ በዚህ ኡደት ጊዜ ሴቶች ለኢንፌክሽን የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ሲሆን፥ ይህ ኢንፌክሽን የሽንት መሽኚያ ቱቦዎችን እንዲሁም ማህፀንን ያጠቃል፤ በጊዜው ተገቢውን ህክምና ካላገኘም ከፍተኛ ህመምን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለዚህም በወር አበባ ጊዜ ሊደረጉ የሚገቡ የንጽህና እና ተያያዥ ጥንቃቄዎችን እናካፍላችሁ፤ 1. በየጊዜው መታጠብ ሴቶች በወር አበባ ጊዜ መታጠብ ወይም ዝናብ ላይ መውጣት የለባቸውም የሚል አባባል እንዳለ ይነገራል፤ እንደ ጤና ባለሙያዎች ገለፃ ግን ይህ ፈፅሞ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ የህክምና ባለሙያዎች አንዲት ሴት የወር አበባዋ ላይ በምትሆነበት ጊዜ በየጊዜው መታጠብ እንዲሁም ቢያንስ በቀን አንዴ ገላዋን መታጠብ እንዳለባት ይመክራሉ።ይህም ሊመጣ የሚችልን መጥፎ ጠረን እንዲሁም የሰውነታችንን ንፅህና ለመጠበቅ ይረዳል፤ ከዚህ በተጨማሪ ሽንት ቤት ገብተው በሚወጡበት ጊዜ እጃቸውን በሳሙና መታጠብ ይኖርባቸዋል። 2. ትክክለኛውን የልብስ አይነት መምረጥ አንዳንዶች በወር አበባ ጊዜ ከነጭ ልብሰ ውጪ የትኛውንም አይነት ልብስ መልበስ እንደሚቻል ሲናገሩ ይሰማል። በእርግጥም ነጭ ልብስ በወር አበባ ጊዜ መልበሱ እይመከርም፤ ሆኖም እንደ ጤና ባለሙያዎች በጣም አስፈላጊ የሆነው ጥንቃቄ በጣም ጠባብ እና ሰውነት ላይ የሚጣበቁ ልብሶችን፣ የጨርቃቸው አይነት ሰውነት ላይ እርጥበትን የሚፈጥሩ የልብስ አይነቶችን፣ ሙቀት እና የማሳከክ ሰሜት ያላቸውን የልብስ አይነቶችን እለመልበስን ይመክራሉ። ከጥጥ ጨርቅ የተሰሩ የውስጥ ሱሪዎችን ፓንቶችንኃ እንዲሁም ሰፊ ልብሶችን መልበስ እርጥበት እንዳይፈጠር ከመርዳቱም ባሻገር ጥሩ ስሜት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ 3. በየጊዜው የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስን በአግባቡ መቀየር በየጊዜው የንፅህንና መጠበቂያ ሞዴስን መቀየር ከንፅህና ጉድለት ከሚፈጠር የኢንፌክሽን ችግር ከመጠበቁም ባሻገር በዚህ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችን ማስቀረት ያስችላል። 4. ትክክለኛውን የሞዴስ አይነት መምረጥ ሞዴሶችን በምንጠቀምበት ጊዜ ትክክለኛውን የመምጠጥ አቅም ያለውን የሞዴስ አይነት እንድንመርጥ ይመከራል። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የመምጠጥ ባህሪያቸው ዝቅተኛ ያልሆነ ሞዴሶችን መጠቀም ተገቢ ነው። 4. በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመምን በተለያዩ መንገዶች ማስወገድ በወር አበባ መጀመሪያ እና መጨረሻ አካባቢ አንዳንዴ በመሀል ብዙ ሴቶች የሆድ እና የተለያዩ የሰውነት አካላት ህመም ያጋጥማቸዋል፡፡ ይህን ህመም ለማስወገድ ሊወሰዱ የሚችሉ መድሀኒቶች ቢኖሩም በቀላሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ህመሙን ማስወገድ ይቻላል፡፡ @DrSofonias

የወንዶች ብልት መጠን ጉዳይ፤ እድገቱና አማካይ መጠኑ በዚህ ጉዳዩ ዙሪያ ባሰናዳነው የመጀመሪያው ክፍል ጽሁፋችን የወንድ ልጅ ብልት እድገት መቼ ጀምሮ መቼ እንደሚጠናቀቅ፣ እንዲሁም አማካይ የሚባለው የወንድ ልጅ የብልት መጠን ምን ያክል እንደሆነ የሳይንሳዊ ምርምር ውጤቶችን ዋቢ አድርገን ለማየት ሞክረናል። የብልት መጠንን ማሳደግ ይቻል እንደሆነም ጥያቄዎችን አንስተን፣ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ብልትን ለማሳደግ የሚደረጉ ሙከራዎችን አይተናል። እንቀጥል…. ☑️ ስለብልት መጠን የሚነገሩ አፈታሪኮች (Myths) ስለ ብለት መጠን እና ቅርጽ የሚነገሩ ብዙ አፈታሪኮች አሉ። እነዚህ አፈታሪኮች ብዙ ሰዎችን ለጭንቀት ሲዳርጉም ይስተዋላል። በስፋት ከሚነገሩት አፈታሪኮች መካከል የሚከተሉት በተደጋጋሚ የሚሰሙ ናቸው። 🍀 የእግር መዳፍ እርዝመትና የብልት እርዝመት እኩል ናቸው:- ይህ አፈታሪክ በሰፊው ሲነገር ቢሰማም ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው። የብልት መጠን ከዬትኛውም የሰውነታችን ክፍል ጋር እንደሚመጣጠን በጥናት የተረጋገጠ ነገር የለም። 🍀 ለግንኙነት ዝግጁ ያልሆነ (@flaccid state) እና ለግንኙነት ዝግጁ የሆነ (@erection state) ብልት በመጠን እኩል ናቸው:- ይህም ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ሚት ነው። ለግንኙነት ዝግጁ ያልሆነ ብልት መጠኑ በአየር ጠባይ ምክንያት ተለዋዋጭ ሊሆን ይችላል። 🍀 ሴቶች ትልቅ ብልት ያለው ወንድ ይመርጣሉ:- ብዙ ወንዶች የፍቅር አጋራቸው ብልታቸው ትልቅ ቢሆን እንደሚመርጡ ያስባሉ። ይሁንና በፈረንጆቹ 2006 ዓ.ም. የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በጥናቱ ከተሳተፉ ሴቶች 85% የሚሆኑት በፍቅር አጋራቸው የብልት መጠን ደስተኞች መሆናቸውን አመልክቷል። 🍀 ትልቅ ብልት የወሲብ እርካታን ይጨምራል:- ይህ ብዙ ወንዶችን የሚያስጨንቅ ሚት ነው። ከርዝመቱ ይልቅ የብልት ውፍረት ነው የወሲብ እርካታን የሚጨምረው የሚሉም አሉ። ያም ሆነ ይህ ግን ከብልት መጠን ይልቅ የሁለቱ መነጋገር እና እርስ በእርሳቸው አንዳቸው ለአንዳቸው የሚኖራቸው ስሜት የበለጠ የወሲብ እርካታን እንደሚጨምር ነው ጥናቶች የሚያመለክቱት። ☑️ ትንሽ ብልት (Micro penis) ምንድነው? ህክምናውስ? ማይክሮ ፒነስ (micro Penis) አንድ ህጻን ሲወለድ ብልቱ ምንም እንኳን ትክክለኛ ቅርጽና ይዘት ቢኖረውም መጠኑ ከሚገባው በታች የሆነ ሁኔታን የሚገልጽ የህክምና ቃል ነው። የአንድ ወጣት ወንድ ልጅ ብልት ለግንኙነት ዝግጁ በሆነበት (@erection state) ጊዜ ርዝመቱ ከ9.3 c.m. በታች ከሆነ የህክምና ባለሞያዎች ሁኔታውን micro Penis ነው ሲሉ ይገልጹታል። ይህ ችግር በጊዜ ከተደረሰበት (በልጅነት እድሜ) በሆርሞን ቴራፒ ህክምና የብልቱ እድገት እንዲነቃቃ የሚደረግበት እድል አለ። ማይክሮ ፒነስ (Micropenis) በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ሁኔታ ነው። ከ10,000 ወንድ ህጻናት 1.5 ቱ ብቻ ናቸው በዚህ ሁኔታ የመጠቃት እድል ያላቸው። ይሁንና ይህን ሁኔታ መገንዘብና አጠራጣሪ ነገር ስናስተውል ቶሎ ሀኪም ማማከሩ መልካም ነው። 👉 ማጠቃለያ:- ከብልት መጠንና ቅርጽ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ብዙ የሚነገሩ ከእውነትና ከሳይንስ የራቁ ነገሮች መኖራቸውን መገንዘብ ተገቢ ነው። ብልት የተፈጥሮ እድገቱን ካጠናቀቀ በኋላም የብልት መጠንን ለማሳደግ ሲባል ሰው ሰራሽ ዘዴዎችን መጠቀም የቆጡን አወርድ ብሎ የብብቱን ጣለ እንዲል የሀገሬ ሰው ለሌላ አላስፈላጊ ችግር ሊያጋልጥ እንደሚችል የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ። ስለዚህ እንዲህ ዓይነት አደገኛ ውሳኔ ከመወሰን በፊት የህክምና ባለሞያ ማማከሩ ተገቢ ነው። @DrSofonias

የአእምሮ ጤና እና ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ በብዙ የህይወት መንገዶች አዕምሯችንን መጠቀም በምንፈልግበት ቦታ በትምህርት ቤት፣ በስራ ቦታ፣ በፈተና እና በተለያዩ ቦታዎች መቀመጥን እናዘወትራለን፡፡ በአንድ ወቅት የወጣ ጥናት ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ የአእምሮ ነዳጅ አቅርቦት ላይ ተጽኖ ከማሳደር ባሻገር በአእምሮም ጤና ላይ አሉታዊ ተጽኖ ሊያመጣ እንደሚችል አመላክቷል፡፡ አዕምሯችን ጉሉኮስ የተራበ አካል ነው፡፡ ምንም አንኳን የሰውነታችንን ክብደት 2% ብቻ የሚሸፍን ቢሆንም 20% የኛን ሀይል አልያም ኢነርጂ የሚጠቀመው እርሱ ነው፡፡ ይህ ሀይል ደግሞ በአብዛኛው የመጀመሪ ደረጃ የአዕምሮ ነዳጅ በሆነው ጉሉኮስ መልክ የሚገኝ ነው፡፡ የዚህ ሀይል ስርጭት ከተቋረጠ የአዕምሯችንን ሴሎች ሊጎዳ ይችላል፡፡ ስለዚህ የጉሉኮስ በበቂ ደረጃ መኖር ከአይምሮ ጤንነት ጋር ቀጥተኛ ዝምድና አለው፡፡ አዕምሯችን ለከፍተኛ ጉሉኮስ መጠንም ይሁን ለአነሰተኛ ጉሉኮስ መጋለጥ ዲሜንሺያ ለተሰኘው ህመም የመጋለጥ አደጋን ይጨምርበታል፡፡ ይህም የሚጠቁመው በተገቢው መንገድ ጉሉኮስን መቆጣጠር ለአእምሮ ጤና እጅግ አስፈላጊ አስፈላጊመሆኑን ነው፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ ከሚያመጣቸው የጤና እክሎች መካከል ጥቂቶቹ 💎 በለጋ ዕድሜ ለሞት የመጋለጥ (early death) አደጋን ከፍ ያደርገዋል፡፡ በግምት 60-75 መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በቀን ስምንት ሰዓት በመቀመጥ የሚመጣን በለጋ አድሜ ለሞት የመጋለጥ አደጋን ለማጥፋት ይረዳል፡፡ 💎 ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ የጉሉኮስ መጠንን በማዛባት ለአእምሮ ጤና ችግር ያጋልጥል፡፡ 💎 ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ በአእምሯችን የደም ስርጭትን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ከመቀመጥ ይልቅ መራመድ በአእምሯችን የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖር ይረዳል፡፡ የአእምሮ የደም ዝውውር ለአእምሮ የሚቀርበውን የጉልኮስ መጠን በመቆጣጠር አእምሮ ጤና ላይ አወንታዊ ተጽኖ ይፈጥራል፡፡ በአእምሮ የደም ዝውውር መቀነስ የአእምሮ ስራ በፍጥነት እንዲቀንስ የማድረግ እና ከመርሳት በሽታ ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ ☑️ መፍትሄ 🍀 ከምግብ በኋላ የመቀመጥ መጠናችንን መቀነስ 🍀 ከምሳ በኋላ የእግር ጉዞ ማድረግ 🍀 ከእራት በኋላ በተለያየ መንገድ እንቅስቃሴ ማድረግ 🍀 ጠዋት ወደ ስራ ስንሄድ ወይም ከስራ በኋላ በእግር መጓዝ። @DrSofonias

ሀንግኦቨር ሀንግኦቨር ለበርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የጤና እክሎች የሚያጋልጥ ከልክ በላይ የአልኮል መጠጥ በመጠጣት ምክንያት የሚከሰት ህመም ነው። ☑️ ምልክቶች 💎 ድካም 💎 ከመጠን በላይ ጥማት እና የአፍ መድረቅ 💎 ራስ ምታት እና የጡንቻ ህመም 💎 ማቅለሽለሽ ማስታወክ ወይም የሆድ ህመም 💎 በቂ እንቅልፍ አለመተኛት 💎 በብርሃን እና በድምፅ ቶሎ መረበሽ 💎 ማዞር 💎 የማተኮር ችሎታ መቀነስ 💎 እንደ ድብርት ጭንቀት እና ብስጭት ያሉ የስሜት መቃወስ 💎 ፈጣን የልብ ምት። ☑️ አጋለጭ ሁኔታዎች 🔹 በባዶ ሆድ መጠጣት 🔹 እንደ ኒኮቲን ይዘት ያላቸው ሌሎች ነገሮችን ከአልኮል ጋር መጠቀም ለምሳሌ ሲጋራ ማጨስ 🔹 ከጠጡ በኋላ በደንብ እንቅልፍ አለመተኛት። ☑️ ውስብስብ ችግሮች 🦋 የመርሳት ችግር 🦋 ለማተኮር መቸገር 🦋 ከስራ መቅረት 🦋 ተግባሮችን ማጠናቀቅ ላይ ችግር 🦋 ከሌሎች ጋር ግጭት 🦋 በትምህርት ቤት ወይም በሥራ ቦታ መተኛት። ☑️ መከላከያ መንገዶች ሀንግኦቨር ለመከላከል ብቸኛው የተረጋገጠ መንገድ የአልኮል መጠጥን ማስወገድ ነው። ነገርግን አልኮል የሚጠቀሙ ከሆነ የሚከተሉትን ቢያደርጉ ለውጥ ማየት ይችላሉ:- 💥 ከመጠጣትዎ በፊት እና ሲጠጡ ይበሉ 💥 የሚጠጡትን መጠጥ በጥንቃቄ ይምረጡ 💥 በመጠጥ መካከል ውሃ ይጠጡ 💥 ገደብዎን ይወቁ እና በመጠኑ ብቻ ይጠጡ 💥 ቀስ ብለው ይውሰዱት 💥 በአንድ ሰዓት ውስጥ ከአንድ በላይ የአልኮል መጠጥ ከመጠጣት ይቆጠቡ 💥 ገደብዎ (ወይም ከዚያ በፊት) ሲደርሱ ሙሉ በሙሉ መጠጣትዎን ያቁሙ። 👉 ከሀንግኦቨር ለመውጣት የሚረዱ የቤት ውሰጥ መፍትሄዎች 💥 ብዙ ውሃ ማጠጣት 💥 ቁርስ መብላት 💥 አንቲኦክሲደንት ይዘት ያላቸውን ምግቦች ይጠቀሙ። 👉 ጥሩ የአንቲኦክሲደንት ምንጮች የሚከተሉትን ያካትታሉ:- 🍀 ስትሮቤሪ 🍀 የወይን ፍሬ 🍀 ሮማን 🍀 ካሮት 🍀 ሙዝ 🍀 ስፒናች 🍀 ዝንጅብል 🍀 ጥቁር ቸኮሌት 🍀 ለውዝ 🍀 አረንጓዴ እና ጥቁር ሻይ ናቸው።

ዝንጅብል እንዳይጠቀሙ የሚመከሩ ሰዎች ዝንጅብል በርካታ የጤና በረከቶች እንዳሉት ተደጋግሞ የተነገረ ሀቅ ነው። ይሁን እንጂ ዝንጅብል ለሁሉም አይነት የጤና ችግር መፍትሄ ይሆናል ማለት አይደለም። ☑️ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዝንጅብል መጠቀም የማይኖርባቸው ወይም የሌለባቸው ሰዎች ናቸው:- 👉 ነፍሰ ጡር ሴቶች! ዝንጅብል በውስጡ የያዘው ሀይለኛ አነቃቂ ንጥረ ነገር ከመደበኛው ጊዜ አስቀድሞ መውለድን ሊያስከትል ይችላል። በተለይም መውለጃዋ የተቃረበ እንስት ዝንጅብል ባትወስድ ይመከራል። 👉 ክብደት መጨመር የሚፈልጉ ሰዎች! ዝንጅብል ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች ተመራጭ ነው። በአንፃሩ ክብደት መጨመር ለሚፈልጉ ሰዎች ምኞታቸውን ገደል የሚከት ነው ተብሏል። ዝንጅብል ከሻይ ጋር ቀላቅለንም ሆነ በሌላ መንገድ ስንወስድ የጥጋብ ስሜት እንዲሰማን ከማድረጉም ባለፈ በሰውነታችን ውስጥ የተከማቸ ስብን ለማቅለጥ ያግዛል። በመሆኑም ክብደትዎን ለመጨመር ከፈለጉ ከዝንጅብል ራቁ ተብላችኋል። 👉 ከደም ጋር የተያያዘ ችግር ያለባቸው ሰዎች! ዝንጅብል የደም ዝውውርን ያፋጥናል። የደም ማነስ፣ የደም መፍሰስ ችግር (ሄሞፊሊያ)፣ የደም መርጋት፣ የተለያዩ የደም ካንሰሮች (ሊኩሚያ፣ ሊምፎማ እና ሚይሎማ) ያሉባቸው ሰዎች ዝንጅብል ቢጠቀሙ የተለየ ተፅእኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል። 👉 የደም ግፊት እና ስኳር ህመምተኞች! የደም ግፊት አልያም የስኳር ህመምን ለመቆጣጠር መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎችም ዝንጅብል በጭራሽ መውሰድ የለባቸውም ተብሏል። ይህም ዝንጅብል የህክምና ክትትሉን ሊያዛባባቸው ስለሚችል ነው። በተለይ ከፍተኛ የደም ግፊትን እና ደም መርጋትን ለመቀነስ ከሚወሰዱ መድሃኒቶች ጋር ዝንጅብል አብሮ መውሰድ አደገኛ መሆኑን ባለሙዎች ይናገራሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት አካላት ዝንጅብል መመገብ ቢያምራቸው እንኳን በአቅራቢያ የሚገኝ የህክምና ባለሙያ አማክረው ቢሆን ይመከራል፡፡ @DrSofonias

የዋና መሠረታዊ የጤና ጥቅሞች ዋና ሙሉ ሰውነትን እና የ ካርዲዮ-ቫስኩላር ስረዓታችንን የሚያሰራ ስፖርት ነው። ለአንድ ስዓት ያክል መዋኘት ለተመሳሳይ ሰዓት የመሮጥን ያክል ካሎሪን የማቃጠል አቅም አለው። ያውም አጥንታችንን እና መገጣጠሚያዎቻችንን ደህንነታቸው ተጠብቆ። ☑️ ለመሆኑ ውሃ ዋና የሚሰጠን ዋና ዋና ጥቅሞች ምንድን ናቸው? 1️⃣ ሙሉ ሰውነታችን እንዲንቀሳቀስ ያደርጋል በምንዋኝበት ጊዜ ከእግር ጣታችን እስከ ጭንቅላታችን ያሉ የሰውነት ክፍሎቻችን በሙሉ ይንቀሳቀሳሉ። በዚህም እንቅስቃሴ የሰውነታችን ጫናን የመቋቋም አቅም (Endurance) ይጨምራል። አካላችንም ይጠነክራል። የተለያዩ አይነት የዋና ስልቶች የተለያዩ ጡንቻዎቻችንን በመገንባት ጥሩ ቁመና እንዲኖረንም ይረዳል። 2️⃣ ሳንባና ልብን ያጎለብታል ዋና ለላይኛው (ለሚታየው) የሰውነት ክፍላችን ከሚሰጠው የጤና ጥቅም በተጨማሪ ለውስጠኛው የሰውነት ክፍሎቻችን ጤንነትም ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለው። ልብን እና ሳንባን በማጎልበት ረገድ ከሚሰጠን ጥቅም በተጨማሪ ውሃ ዋና የደም ግፊት እና ስኳርን ከመሳሰሉ የጤና ምስቅልቅሎች እራስን ለመጠበቅ ሁነኛ መላ መሆኑን በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ውጤት ያመለክታል። 3️⃣ ለአስም ታማሚዎች የአስም በሽታ ተጠቂ ለሆኑ ሰዎች ዋና እጅግ ተመካሪ ስፖርት ነው። ሰዎች በሚዋኙበት ወቅት ረዘም ላለ ሰዓት ትንፋሻቸውን ውጠው መቆየት ስለሚለማመዱ የአተነፋፈስ ሥርዓታቸውን የመቆጣጠር ብቃትን ያዳብራሉ። ይህም አስም ለሚያሰቃያቸው ሰዎች አንዱ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ባለሞያዎቹ ይመክራሉ። 👉 ጥንቃቄ:- አንዳንድ ጊዜ የመዋኛ ገንዳ ለማጽዳት ጥቅም ላይ የሚውሉ ኬሚካሎች በራሳቸው አስምን የማባባስ እድል አላቸው። ስለዚህ ከመዋኘቶ በፊት ስለመዋኛ ገንዳው ንጽህና ግንዛቤ ሊኖሮት ይገባል። 4️⃣ ለጥሩ እንቅልፍ ኤንሲቢአይ ላይ የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ውሃ ዋና ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት የሚመከር እንቅስቃሴ ነው። በእንቅልፍ ማጣት (Insomnia) የሚቸገሩ ሰዎች ዋና በመዋኘት ጥሩ እንቅልፍ የማግኘት እድላቸውን ከፍ ማድረግ ይችላሉ። 5️⃣ ስሜትን ለማነቃቃት ሳይንቲስቶች የመርሳት በሽታ (Dementia) ባለባቸው ሰዎች ላይ ለ12 ወራት በዋና ላይ ተመስርተው ባደረጉት ጥናት ውጤት መሰረት ዋና በሰዎች ስነ ልቦና እና የስሜት መነቃቃት ላይ አዎንታዊ ሚና እንዳለው ተገልጿል። በተጨማሪም ጭንቀትን በመቆጣጠር ረገድ የዋና ጥቅም ከፍተኛ መሆኑን ጥናቶች አመልክተዋል። 6️⃣ ለጤናማ እርግዝና ኔቸር ዶት ኮም ላይ የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው እናቶች በእርግዝና ወራት የሚያደርጉት የዋና እንቅስቃሴ በጽንሱ የአዕምሮ እድገት ላይ አዎንታዊ የሆነ ተጽዕኖ አለው። የሚዋኙ እርጉዝ ሴቶች አካላዊ ጉዳት ያለበት ልጅ የመውለድ እድላቸውም የቀነሰ ይሆናል። እርጉዝ ሴቶች በዬትኛውም የእርግዝናቸው ወቅት ላይ መዋኘት ይችላሉ። @DrSofonias