cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Chonbe Assefa

Channel

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
194
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ሱዳን ሱዳን በጎሳ ግጭት የተነሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች‼️ ሱዳን የጎሳ ግጭት በተስፋፋባቸዉ የሀገሪቱ ግዛቶች ላይ በምሽት መንቀሳቀስ የሚገድብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አዉጃለች፡፡በሱዳን የወደብ ከተማ ግጭቶች እንደነበሩ ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡የሱዳን መንግስታዊ የዜና ወኪል ሱና እንደዘገበዉ ከሆነ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሲገደሉ 13 ሰዎች ክፉኛ መቁሰላቸዉን ይፋ አድርጓል፡፡የቀይ ባህር ግዛት ገዢ በሰጡት መግለጫ ስለ ደረሰዉ የጉዳት መጠን በቁጥር የገለጹት መረጃ የለም፡፡በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ዉዝግብ የተነሳ በሱዳን በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች ይፈጠራሉ፡፡ Esat_tv
Show all...
#አቡበከር ናስር የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጫዋቾች ማኅበር የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስርን የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች አድርጎ መምረጡን አስታውቋል። ለመጀመርያ ጊዜ የዓመቱ ኮከቡን የመረጠው ማኅበሩ በቀጣይ የሚዘጋጅ የሽልማት ሥነ-ስርዓት እንደሚኖረው ለማወቅ ችለናል።
Show all...
#ከምርጫ_ቦርድ_የተሰጠ ማሳሰቢያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ተግባራት እያከናውነ ቆይቶ የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁ እና የመራጮች ምዝገብ ይፋ መደረጉ ይታወቃል። የመራጮች ምዝገባ ሂደት ከሞላ ጎደል በስኬታማነት የተጠናቀቀ ቢሆንም ሂደቱ እየተከናወነበት ባለበት ጊዜ አንስቶ የሚታዪ በተለይ የዝቅተኛ የመንግስት እርከን ሰራተኞች(ወረዳ፣ ቀበሌ…ወዘተ) ጣልቃ ገብነቶችን በተለያየ መንገድ ለሚመለከታቸው አካላት ሲያሳውቅ ቆይቷል። በቅርቡም ቦርዱ በግንባር ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ በነጻ የስልክ ጥሪ መስመር የሚመጡ ጥቆማዎችን በመከታተል፣ የክትትል ቡድኑን በማሰማራት የምዝገባ ሂደቱን ለመገምገም ሞክሯል። በዚህም መሰረት የዝቅተኛ የመንግስት እርከን ላይ የሚገኙ ሰራተኞች ምርጫ ጣቢያ ላይ ያለምንም ከቦርዱ የሚሰጥ የፓርቲ ወኪልነትን የሚያሳይ መታወቂያ መገኘት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን መረጃ መጠየቅ እና በአንዳንድ ሁኔታዎች የመራጮች ምዝገብን ለመጎብኘት እና መረጃዎችን ለመውሰድ ጥረት በማድረግ ጣልቃ መግባታቸውን ተረድቷል። ይህ በተለይ ወደ ድምጽ መስጫ ቀን እየተጠጋን በመጣን ጊዜ የምርጫ ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያውከው ከመሆኑም በላይ በምርጫ ህጉም ሆነ በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ የተቀመጠ ወንጀል በመሆኑ 1. ማንኛውም የዝቅተኛው መንግስት እርከን ሰራተኛ (ቀበሌ፣ ወረዳ….) ወይም ያልተፈቀደለት ሌላ አካል ምርጫ ጣቢያ ውስጥም ሆነ 200 ሜትር ርቀት ዙሪያ ላይ እንዳይገኝ 2. ቦርዱ ለፓርቲ ወኪሎች የእውቅና ባጅ በመስጠቱ የእውቅና ባጅ ከተሰጣቸው ፓርቲ ወኪሎች ውጪ ማንኛውም አካል የመራጮች ምዝገብ እና ተመዝጋቢዎች መረጃን አስመልክቶ ምርጫ ጣቢያም ሆነ የምርጫ ክልል አስፈጻሚዎችን እንዳይጠይቅ እንዲሁም በምርጫ ጣቢያው ውስጥ እና በ200 ሜትር ርቀት ዙሪያ እንዳይገኝ 3. ማንኛውም የመንግስት እርከን ሰራተኛ ከቦርዱ የበላይ ሃላፊዎች እውቅና በማግኘት ወይም በልዩ የደህንነት ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር ለምርጫ አስፈጻሚች ከምርጫ ጋር የተገናኘ ቁሳቁሶችን እንዲያቀንቀሳቅሱ፣ ትእዛዝ አቅጣጫ እና ጥቆማ እንዳይሰጥ እጅግ በጥብቅ ያሳስበባል። ይህ ሆኖ ቢገኝ ግን የምርጫ ወንጀል በመሆኑ ይህንን ተግባር የፈጸሙ ግለሰቦች በምርጫ ህጉ እና በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ተጠያቂ እንደሚሆኑ እየገለጽን የቦርዱ ምርጫ አስፈጻሚዎችም ማንኛውም የዝቅተኛ የመንግስት እርከን ሰራተኞች ወይም ሌሎች ያልተፈቀደላቸው አካላት ከምርጫ ጣቢያ ውስጥም ሆነ 200 ሜትር ርቀት ውስጥ እንዳይገኙ እንዲያደርጉ፣ ከቦርዱ ሰራተኞች እና ሃላፊዎች ውጪ ምንም አይነት ትእዛዝም ሆነ አቅጣጫ በፍጹም እንዳይቀበሉ በዚሁ አጋጣሚ እናሳስባለን። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም
Show all...
#ለ6ኛው ምርጫ ተወዳዳሪ ፓለቲካ ፓርቲዎች የመራጮች ምዝገባ ከተጠናቀቀ በኋላ ባሉት10 ቀናት የመራጮች መዝገብ ይፋ ተደርጎ ፓርቲዎች፣ ታዛቢዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ሲመለከቱት የቆዩ ሲሆን የመራጮች መዝገብ ይፋ ማድረግ ሂደት በዛሬው እለት ተጠናቋል። ቦርዱ የመራጮች መዝገብ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ የመጡ አቤቱታዎችን ከፓርቲዎች በመተባበር ለመመርመር እና ለመፍታት ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል። አሁን ግን የመራጮች ምዝገብ ይፋ ማድረጊያ ጊዜ በመጠናቀቁ ፓርቲዎች በሂደቱ የታዘባችሁትን እና መፈታት አለበት የምትሉትን አቤቱታ የምርጫ ክልል እና ጣቢያን በማካተት እስከ ነገ ማታ 11፡30 ድረስ ለቦርዱ እንድታስገቡ እየጠየቅን ቦርዱ የቀረቡለት አቤቱታዎችን ለመመርመር እና ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ መሆኑን እንገልጻለን። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም
Show all...
#መረጃ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ /ባልደራስ/ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ጨምሮ፣ አስቴር ስዩም፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ በመጪው ምርጫ በዕጩነት እንዲመዘገቡ፤ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ መስጠቱን፤ የባልደራስ የሕግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሔኖክ አክሊሉ ገልጸዋል ። ምንጭ፦ ባልደራስ ፓርቲ
Show all...