cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🌷🌷Tech and Interesting stories 🌷🌷

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
303Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

​​. ስናፍቅሽ🌺 ❣ :¨"""""""""""""""""¨:❣ ናፍቆትሽን ለመግለፅ ቃላት ከየት ይገኛል ተፈጥሮሽ ይለያል ፍቅርሽ ይገርመኛል የክዋክብት ብርሀን የጨረቃ ድምቀት የበረዶ ንጣት የፀሀይም ሙቀት ሁሉ ቢደመሩም የፊትሽን ብርሀን ግማሽ አያበሩም ከአይኖችሽ ጨረር አይነፃፀርም ከንፈርሽን ፈልቅቆ የሚወጣው ፀአዳ ከጥርስሽ ፈገግታ አይወዳደሩም ስትናፊቅኝ ጊዜ... በሌሊት ወጥቼ ጨረቃን አየሁዋት ከጥርስሽ ፈገግታ እያወዳደርኳት በትካዜ ስሜት በጥልቀት ባያትም ያው ብርሀን እንጂ ፈገግታ የላትም የጨረቃ ብርሀን እንዳንቺ ፈገግታ አያስደነግጥም ሲያዩት ውለው ቢያድሩ ለልባዊ ሀሴት ስሜትን አይሰጥም በዙሪያዋ ያሉ ክዋክብትን ሁሉ ተመለከትኳቸው ፊትሽ ላይ ከማየው ፍንጥቅጣቂ ብርሀን አነፃፀርኳቸው እረ ይቅር በይኝ በፍፁም በፍፁም ዝብርቅርቅ ክዋክብት ካንቺ የፊት ብርሀን አይነፃፀርም እንደ ገፅሽ ፀአዳ ከሩቅ አያበሩም ነገም ለመታየት ናፍቆትን አይፈጥሩም የነሱ ብርሀን በግርዶሽ ይዋጣል ሲነጋ ተራውን ለፀሀይ ይሰጣል ከፊቴ ማይጠፋው ያንቺን ብርሀን ግን ምንም አይተካውም ድንገት በአጋጣሚ ትንሽ ብትርቂኝም በውስጤ ያበራል የተራራው ግርዶሽ ከቶ አይከልለውም ያንቺ የፊት ብርሀን ልክ እንደከዋክብት ዝብርቅርቅ አይደለም የውበት ማማ ነው ባለ ብዙ ህብር ባለ ብዙ ቀለም ስትናፍቂኝ ጊዜ... አድማሱን ገላልጣ በጠዋት ስትሰርቅ ቀን ሙቀቷ ሲግል ማታ ስትጠልቅ ከአንቺነሽ ብርሀን እያነፃፀርኳት በልዩ ተመሰጥኦ ፀሀይን አየሁዋት እረ ይቅር በይኝ.... ፀሀይ ካንቺ ጋራ በምን ትነፃፀር በምን ትወዳደር የሚያቃጥል ሙቀት የሚዋጋ ጨረር ተሸክማ ምትዞር የአንቺ የፊት ብርሀን ከፀሀይ ይልቃል ለማየት ያጓጓል ከስሜት ይረቃል ህሊናን ያፈዛል ልብን ያስጨንቃል ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ye chanalu admin negn lemwedat........... nafkeshignal❤️❤️
Show all...
የበዓል መልዕክት : በየትኛውም የምድር ክፍል የምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳዔ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን። በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ ከክፉ ድርጊት እና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል። በዚህ በዓል፦ ከጎናችን የተለዩ ንፁሃን ወገኖቻችን እያሰብን፣ ከቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ የወደቁትን ፣ የሚወዱትን ተነጥቀው በሀዘን ላይ የሚገኙ ቤተሰቦችን ፣ በሰላም እጦት ከሚኖሩበት ከቄያቸው ተሰደው በሰው ሀገር የሚንከራተቱትን ወገኖቻችን ፣ በየሆስፒታሉ የታመሙትን እያሰብን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን። በተጨማሪም በዓሉን ስናከብር በየዕለቱ የዜጎቻችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል እንዲሆን አደራ እንላለን ፤ ከተቻለ ከቤታችን ሳንወጣ እናሳልፍ ፤ መንቀሳቀስ ግድ የሚለን ከሆነ / ዘመድ ጥየቃ፣ ወዳጅ ጓደኛ ስንሰበሰብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እናድርግ። የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የበረከት በዓል ያድርግልን! ሀገራችን ሰላም ያድርግልን! ፈጣሪ የሰው ልጆችን ሁሉ ይጠብቅልን። መልካም የትንሳኤ በዓል @techs_and_more @techs_and_more
Show all...
ፍርዱ የእሱ ሆኖ ሰው በከንቱ ይጨነቃል እንኳን ያስብነውን ቀርቶ ጌታ የልብ ያ ው ቃ ል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
Show all...
አጣጥለህ አትነሳ አጣጥለህ አትነሳ ያንዱን ውድቀት፣ አትደገፍ ጥረህ ፣ግረህ ፣ሰርተህ እለፍ አሊያ አንደኛ ብትወጣ... አያጠግብህ የሚበላ፣ አያረካህ የሚጠጣ አያምርብህ የሚለበስ በሰው ልፋት፣ አንተ ስትደርስ ያለ ቦታህ ስትሰየም፣ ያለ ጊዜህ ስትገኝ ያለእውቀትህ ስትሞገስ፣ ያለ ሞያህ ስትቀኝ ውጭህ ሙላት፣ ውስጥህ ባዶ ስኬት አይባልም የራስን መካብ፣ የሌላውን ንዶ!፡
Show all...
ከ እየሩሳሌም ወደ አለም ከእየሩሳሌም ሸሽቶ እርቆ ያለምን ደስታ ውበት ናፍቆ ከ ኮበለለ ሰነባብቷል ከ ክንአን ወቶ ካራን ገብቷል፡፡ ............................................ ምን ቢጨንቀው ነው ምን ቢጠፋ እየሩሳሌም ምን ብትከፋ ከ አበምኔቱ አልተጣላ ከ ማህሌቱ አልታጎለ እየሩሳሌም ምን ብትከፋ ከ ቅጥሯ ወጥቶ ኮበለለ? ...................................... ከ ደብሯ ቆሞ ዳዊት ደግሞ ቅኔ ማህሌት ቆሞ በሌት መስቀል ተሳልሞ ጉልበት ስሞ ከ የኔታ ጋር አልተጣላ ከ አብነቱ አልታጎለ እየሩሳሌም ምን ብትከፋ ከ ደጇ ርቆ ኮበለለ? ....................................... ተላምዷት ኖሮ ለ አመታት ከቤተ መቅደስ ሲቀድሳት ቃልም ሳይሰጣት ለመመለስ ወይ ተቀብቶ ሳይባል ቄስ በ ወግ ደጃፏን አልዳበሰ ጠበል ጠዲቋን አልቀመሰ እየሩሳሌም ሳትከፋ ልቤ ሸፍቶ ቢጠፋ ከ ደጇ ህይወት ሳያጣ ከ አለም መኖር ቢቃጣ ያጠናውን ቃል ከሱ ዳስ ቃለ ወንጌሉን ሲያስታውስ እንደው ትርጉሙ ቢዘልቀው ልቤን እውነታው አነቀው፡፡ ....................
Show all...
#መግባባት_ካቃተን_ይቅር አንግባባ ምን አጠፋው እቴ ? ምንጎደለሽ እቴ? አብሬሽ ልታመም በነጋ በጠባ ይኮሰኩሰኛል ጥፋት አልባ ህመም በሀሜተኛ ወሬ ሳላውቅ አልሰቃይ ተይ ይቅርብሽ አንቺም ደሞ ታውቂዋለሽ በወሬ ድባቅ ላይ እውነት አይበጅም ቀጥረሽኝ አይደለ በፀሀይ የቆምኩት ናፍቄሽ አይደለ መቆም የታከትኩት ላይሽ አልነበረ አይኔን ያማተርኩት ላንቺ ብዬ አይደለ እራሴን የጣልኩት በፍቅርሽ አይደለ ድሄ የቀረሁት አንቺን ብዬ አይደል መንገዴን የሳትኩት አስታውሼሽ አይደል በንባዬ የሳኩት ስወድቅ እንደተውሽኝ እኔስ መች አወኩት አንሺኝ ብዬ ነበር ለእጅሽ የምጥረው በእግርሽ ተረግጬ ተደፍቼ የቀረው ለካ የወደቀ ሁሉ ዳግም ይረገጣል በደካማ አቅም ድል ይረጋገጣል ለካ ገመናን ሲነግሩት እንባ መች ሊገደው አይንም ይሳለቃል እምነት አልባ ቃልም ጆሮን ተንተርሶ ባአንደበት ይረቃል ለካ ከመሞትም በላይ አሟሟት ይከፋል ወድቆም የተነሳ ለሞቆም ይጋፋል ለጥልቻ መንሴው ባላሹት መወደድ እንቅፋት ነው ለካ ፍቅር ይሉት መንገድ ተይው እታለሜ አሁንማ ገባኝ አሁንስ አወኩት ማንኳኳት ነው ፅድቁ በሩን እየዘጉት @techs_and_more @techs_and_more @techs_and_more @techs_and_more
Show all...
ይገ....ባኛ...ል ይገባኛል ለምን ሄድሽ ብዬ አልጨቀጭቅሽም ተመለሺም ብዬ ከእግርሽ ስር አልወድቅም ልክ ነሽ የኔ ዉድ ከድሮ ቀንሷል ለኔ ያለሽ መውደድ ሆኗል እንደ አመድ በርግጥ አንዳች የለኝ አፍሼ ምሰጥሽ ለፍቅርሽ ማቆያ መደለያ እንዲሆንሽ ደግሞም እውነት አለሽ እኔ እንደሱ አልሆንኩም ሲርብሽ ሲጠማሽ አላጠጣሁሽም ሲከፋሽ ሲደላሽ ከጎንሽም ሆኜ አላፅናናሁሽም የበረደሽ ለታ ትከሻሽ ላይ ኩታ ጣል አላደረኩም አውቃለሁ ብኩን ነኝ ሞልቶ ማይሞላልኝ ሁሌም መንገደኛ ለጎጇችን ማገር ለመስራት ማልተኛ እኔ አልፈርድም ባንቺ ፍቅሬ ነው እሰልቺ ልክ ነሽ አለሜ እንደድሮ አይደለሁ ወድቆ ከስሟል አቅሜ እናምልሽ ውዴ ደና ሁኝ ልበልሽ ልፋ ሲለኝ እንጂ ድሮም የኔ አልነበርሽ @techs_and_more @techs_and_more @techs_and_more @techs_and_more
Show all...
እግዜር ዝቅ ብሎ -------------------------------------- አልመህ ካቀድከው - ከምኞትህ ሁላ በአይንህ መትረህ - ልብህ ከሚሞላ ከምድር በረከት - ስጋን ከሚያረካ ከሰማይ ረድኤት - ነፍስን ከሚያፈካ . . የትኛውን ልስጥህ - ብሎ ቢጠይቀኝ ካንድ አንቺ በስተቀር - የቱንም አልመኝ፡፡
Show all...
. ነፍሴ የሄደች ለት ነፍስሽም ካ'ካልሽ ፥ ስትለየው ወጥታ፤ መቃብር ላንቃ ውስጥ ጎን ለጎን ሆነን የተቀበርን ለታ . አንድ ቀን . . . አንድ ቀን ፥ ምናልባት ማን ያውቃል ፤ አንድ ሸክላ ሰሪ ካፈራችን ዘግኖ አንድ ሸክላ አድርጎ ፥ ይሰራን ይሆናል::
Show all...
የሰማይ ጣሪያ ጾማችን ቢበዛ በፍቅር ካልተቀኘ ሱበዔው አርምሞው ጥላቻን ካልዳኘ እርቅን ካልጎበኘ መከፋፈል ቀርቶ አንድነት ካልናኘ ጬኸታችን ገንኖ የአምላክ ስም ቢጠራ ፀሎት አይሰማም ምንስ ብንጣራ እንኳንስ ከሰማይ አይደርስም ከጣራ!!
Show all...