en
Feedback
CRYPTO-FOREX™

CRYPTO-FOREX™

Open in Telegram
358
Subscribers
-124 hours
-57 days
-1830 days
Posts Archive
Just for fun😂😂😂😂
Just for fun😂😂😂😂

✍ #ክብደት_ለመጨመር 12 #ሳይንሳዊ መንገድገዶች ፡🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ✔ክብደት መጨመር ክብደት ለመቀነስ ከሚደረገው ተግባር እኩል ተመሳሳይ ትጋት ይፈልጋል፡፡ ውፍረት ከሽብር አደጋ ባልተናነሰ የዓለማችን ስጋት በሆነበት ዘመን የተስተካከለ አቋም እንዲኖረን በርካታ ጥረቶችን እናደርጋለን፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከልክ በማለፍ ሁኔታ ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሰዎችም፣ ለበሽታ ሊኖራቸው የሚችለውን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ ለብሰው እንዲያምርባቸውና በሂደቱ ሊከሰትባቸው የሚችለውን ምቾት ማጣት ለማስወገድም እንዲሁ፣ ተጨማሪ ኪሎ በሰውነታቸው ላይ ለመጨመር የመፍትሄ በሮችን ሁሉ ያንኳኳሉ፡፡ ባለሙያዎች ታዲያ፣ ከመፍትሄ አቅጣጫዎች የምናገኘው ስብ ወይስ ጡንቻ የሚለውን ቀድመን መለየት እንዳለብን ያስገነዝቡናል፡፡ አንዳንዶቹ በሰውነታቸው ላይ ስለሚጨምሩት ክብደት ትኩረት አይሰጡም፡፡ ጡንቻ፣ ስብ ወይም የሁለቱ ጥምረት፣ እነዚህ ሰዎች ከብዶና ወፍሮ መታየት ብቻ ስለሆነ ዓላማቸው ወደ ባሰ ሁኔታ ሊሸጋገሩ ይችላሉ፡፡ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች በተሻለ ሁኔታ ክብደት በሰውነታቸው ላይ መጨመር ስለሚችሉበት መንገድ፣ ከምርምር ውጤቶች የተገኙትን እነዚህ መመሪያዎች በተቻለ መጠን ለመተግበር እንሞክር፡፡ 👉1. #በቀ5-6 #ጊዜ_መመገብ፡- ክብደት ለመጨመር በቀን ከ5 እስከ 6 ጊዜ መመገብ መጀመር ይኖርብናል፡፡ ታዲያ የመመገቢያ ሰዓታችን በሚገባ መከፋፈል ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም በአንድ ጊዜ በምንወስደው ከፍተኛ ምግብ ሳቢያ ጨጓራችንም በስርዓት መፍጨት እንዳይችልና ሰውነታችን ሁሉንም ካሎሪዎች መቀበል እንዳይችል ምክንያት ይሆናል፡፡ እርግጥ ነው በየ3 ሰዓታት ልዩነት የምግብ ፍላጎታችን ላይነሳሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን ጫን ብለን መመገባችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡ በየዕለቱም የምግብ ፍላጎታችን እያደገ ስለሚመጣ፣ መቸገራችን ይቀንሳል፡፡ በተቻለ መጠን ታዲያ በአመጋገባችን ውስጥ ጤናማ ምግቦችን መምረጣችንን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ 👉2. #ክብደት_የማንሳት_ልምምዶችን በሳምንት ሶስት ጊዜ ማድረግ ለወንዶች፡- በክብደቶች በመታገዝ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ስንጀምር ጡንቻዎቻችንን ማሳደግ እንችላለን፡፡ በሂደትም የክብደቶቹን ሚዛን መጨመር ያስፈልጋል፡፡ ይሄ በተለይ ከሰውነት ክብደታችን ባሻገር ጥንካሬያችንን ማሳደግ እንድንችል የሚረዳን ነው፡፡ 👉3. ከ300-500 #ካሎሪዎችን_ማከማቸት ቀደም ሲል እንደተገለፀው፣ ከ300-500 የካሎሪ መጠን ማከማቸት፣ የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ የሚያደርገን ከሆነ መሞከሩ አይከፋም፡፡ ይሄንን የካሎሪ መጠን ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ ነው ማግኘት የምንችለው፡፡ 👉4. #ሁሉንም_የሰውነት_ክፍል_ማሰራት፡- በጂም ወይም በቤት ውስጥ ስፖርት የምንሰራ ወይም ክብደት የምናነሳ ከሆነ ሁሉም የሰውነት ክፍላችን በሚገባ እየሰራ መሆኑን ነው በቅድሚያ ማረጋገጥ ያለብን፡፡ ምክንያቱም ብዙዎቻችን ትኩረት የምናደርግባቸው ብዙ የጡንቻ ክፍሎች አሉንና፡፡ ስፖርቱን የሚጀምሩ ብዙ ሰዎች በአንገታቸው፣ ደረታቸው ወይም ማጅራታቸው አካባ ብቻ ትኩረት በመስጠት ልምምድ በማድረግ ትልቅ ስህተት ይፈጽማሉ፡፡ ይሄ አካሄድ የሰውነታችን ሚዛን እንዲበላሽ በማድረግ ሰዎች የማይወዱትን ሰውነት እንድንላበስ ምክንያት ይሆናል፡፡ 👉5. #በፕሮቲን_የበለፀጉ_ምግቦችን_ማዘውተር፡- ቀደም ሲል እንደተገለፀው ከ300-500 የካሎሪ መጠን ማከማቸት፣ የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ የሚያደርገን ከሆነ ይሄንን የካሎሪ መጠን ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ ነው ማሳካት የምንችለው፡፡ 👉6. #ካሎሪዎች_መጠጣት፡- የተጠየቅነውን ካሎሪ በመብላት ብቻ ሟሟላት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ወተትና የወተት ተዋፅኦዎችን፣ እንዲሁም አነስተኛ ስኳር ጋር በፕሮቲን የበለፀጉ መጠጦችን ነው ማዘውተር ያለብን፡፡ 👉7. #በፍጥነት_መመገብ፡- ይሄ ምክር በተቃራኒ ውፍረታቸውን መቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች የሚታዘዝ ነው፡፡ ሰውነታችን በቂ ምግብ ስለማግኘቱ ምላሽ እንዲሰጠን የተወሰኑ ጊዜዎችን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በፍጥነት መመገባችን ከሰውነታችን የጥጋብ ምልክት ከማግኘታችን አስቀድመን ብዙ እንድንመገብ ያደርገናል፡፡ 👉8. #ለማገገሚያ_የተለያዩ #አማራጮችን_መከተል፡-የማፍታቻ እንቅስቃሴዎች፣ ሻወር፣ በካርቦን ሃይድሬት የበለፀጉ ምግቦች፣ ሰውነታችን በፍጥነት እንዲያገግም ይረዳዋል፡፡ ታዲያ የ8፡00 ሰዓት እንቅልፍ እንዳይዘነጋ፡፡ 👉9. #በራሳችን_ላይ_ትዕግስት ይኑረን፡- ጤናማ ባልሆነ አካሄድ በፍጥነት ተጨማሪ ክብደትን ማግኘት ተጨባጭ አይደለም፡፡ የተቀመጡ መመሪያዎችን በመከተል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ1-2 ኪሎ ብቻ ነው ማግኘት የሚቻለው፡፡ ባለሙያዎች ፈጣን ለውጥ ካላገኘን በቀላሉ ስሜታችን ሊጎዳብን አይገባም ይሉናል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ሰው ሰውነት ልዩነት ስላለው፡፡ 👉10. #በራስ_መተማመን፡- ክብደት ለመጨመር ያወጣነው ዕቅድ ክብደት የሚለካው ለስኬታማነቱ በራሳችን ላይ ያለን መተማመን ነው፡፡ ከጠንካራ ሥራ በኋላ ለውጥ ማየት ባንችልም፣ ሌላና እጅግ ጠንካራ ወደ ሆነ ልምምድ መግባት ይኖርብናል፡፡ ተጨማሪ ምግብ መመገብ፣ ተጨማሪ ክብደቶችን ማንሳት፣ የውስጥ ጥንካሬን አስጠብቆ መቆት ናቸው፣ ክብደት መጨመር ከሚፈልግና በራሱ ከሚተማመን ሰው የሚጠበቀው፡፡ 👉11. #ረዥም_ርቀት_መሮጥ_ውጤት የለውም፡- መሮጥ ግዴታ ከሆነ አጫጭር ርቀቶችን እና አቀበቶችን መውጣት ነው ተመራጩ፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የአጭር እና ረዥም ርቀት ሯጮችን ሰውነት መመልከት ነው፡፡ የትኛውን ነው መሆን የምፈልገው? በማለት ራስን መጠየቅ ደግሞ መሰረታዊ ነው፡፡ 👉12. #መተኛት፡- ከፍተኛ ክብደት ለመጨመር በቀን ቢያንስ 8 እና 9 ሰዓት መተኛት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ ሰውነታችን ምንም ስራ እንዳይሰራ በማድረግ በተኛበት ጡንቻ እንዲገነባ እናስችለዋለን፡፡ በቀን ውስጥ ከ6 እና ከዚያ በታች እንቅልፍ እያገኘን ከሆነ፣ በአመጋገባችንና በስፖርት እንቅስቃሴዎች ያመጣናቸውን ለውጦች ማስጠበቅ አንችልም፡፡ For more join @habeshabodybuilders

Miki from addis ababa @habeshabodybuilders
Miki from addis ababa @habeshabodybuilders

Obsi from Addis Ababa. @habeshabodybuilders
Obsi from Addis Ababa. @habeshabodybuilders

=> በሁለተኛ ደረጃ ሚፈጸም ስህተት የሰውነትህን ትልቅ ጡንቻዎች አለማወቅና በአግባቡ ሚያስፈልጋቸውን ክብደት አለመጠቀም። ይህ ምን ማለት ነው? የሰውነትህ ትልቁ ጡንቻዎች የእግርህ ጡንቻዎች ናቸው። ከዛ ቀጥሎ ጀርባ፣ ከዛም ደረት፣ ከዛም ትከሻ፣ በመጨረሻም የእጅ ጡንቻዎች። ስለዚህም እግርህ እንዲያድግ ከሌሎቹ አካሎች በላይ ትልቅ ክብደት ይጠይቃል ማለት ነው። ስለዚህ ቤንች 80 ኪሎ ከገፋህ እግርህ ፕሮፖርሽኑን እንዲጠብቅ ስኳት ቢያንስ ቢያንስ 120 ኪሎ መቻል አለብህ ማለት ነው። ከዚህ ቀጥለን ስትሰራ የሰውነትህ ምን ያህል ክብደት ለማንሳት ማቀድ እንዳለብህ እንይ፦ 1) ስኳት (እግር) - የሰውነትህን ክብደት 2 እጥፍ ያህል ለማንሳት አልም 2) ዴድ ሊፍት (ጀርባ እና እግር በትንሹ) - » 2.5 X » 3) ቤንች (ደረት) - » 1.5X » 4) ሚሊተሪ ፕሬስ (ትከሻ) - » 1X » ስለዚህ 80 ኪሎ ብትመዝን ስኳትህ 160 ኪሎ ፣ ዴድ ሊፍትህ 200 ኪሎ፣ ቤንች 120 ኪሎ፣ ሚሊተሪ ፕሬስ ደግሞ 80 ኪሎ ለማድረስ ብለህ የረጅም ጊዜ እቅድ አልመህ መንቀሳቀስ አለብህ። በሚቀጥሉት ፖስቶች ስለ ሌሎች ስህተቶች ፖስት እናደርጋለን። እስከዛ ቻናላችን ሼር አድርጉ። @habeshbodybuilders

Just for fun😂😂😂 @habeshabodybuilders
Just for fun😂😂😂 @habeshabodybuilders

=> ጀማሪ ብረት አንሺዎች ሚሰሩት ስህተቶች በሀገራችን ብረት ማንሳት ሰውነት እንደማበላሸት ተደርጎ ይታያል። ይህም ሊሆን የቻለው አብዛኛው ብረት ማንሳት ሚያዘወትር ወጣት ሰውነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይብስ እያስጠላ ሰለሚሄድ ነው። ይህ ለምን ሊሆን ቻለ? የዚህ መልስ አብዛኛው ወጣት ጂም በገባ ቁጥር ሚቀጠቅጠው የፈረደበት እጅ እና ደረት ነው። ትከሻ የለም፣ ጀርባ የለም፣ እግር ደግሞ ፈጣሪ ይወቀው። መጨረሻ ላይ ሰው ከመምሰል ወጥተው ጦጣ መምሰል ትጀምራለህ። ሰውነት ከማስጠላትም አልፎ ይብስ ይደክማል። - ከወገብ በታች ልክ ስትጀምር የነበሩህ ስቴኪኒ እግሮችህ ይዘህ ደረትህ እና እጅህ ሲጨምር center of gravityህ ይዛባል፣ ባላንስህ ይጠፋል፣ ይባስ ብሎ በቀላሉ ትገፋለህ። - ደረትህ አድጎ ጀርባህ ግን ስትጀምር የነበረው ጀርባ ማይባል ቆዳ ከሆነ ትጎብጣለህ። ላለ መጉበጥ ስትል በግድ ደረትህን ወደ ኋላ ትስባለህ፣ ልክ ደረቱ እንደተነፋ የፈረንጅ ዶሮ! ጀርባህን ብታሰራ ኖሮ የደረትህን ሸክም ጀርባህ በቀላሉ ይችለው ነበር። - እጅህ አድጎ ትከሻህ አጥንት ከሆነ የእጅህ ጡንቻ ጡንቻ ሳይሆን እጢ ይመስላል። እነዚህን እንዴት እንደምናስተካክል በቀጣዩ ፖስቶቻችን እንዳስሳቸዋለን። For more join us @habeshabodybuilders

photo content

Bini from addis ababa
Bini from addis ababa

photo content

photo content

photo content

photo content

አሰራራችን እናስተካክል💪💪💪💪
አሰራራችን እናስተካክል💪💪💪💪

Dani from addis ababa @habeshabodybuilders
Dani from addis ababa @habeshabodybuilders

Wendi Mak Ethiopian artist from Addis Ababa. @habeshabodybuilders
Wendi Mak Ethiopian artist from Addis Ababa. @habeshabodybuilders

Amleset Muchie Ethiopian model and actress from Addis Ababa. @habeshabodybuilders
Amleset Muchie Ethiopian model and actress from Addis Ababa. @habeshabodybuilders

Habetesh from addis ababa ("shiro meda)
Habetesh from addis ababa ("shiro meda)

Biniyam from addis abeba 💪
Biniyam from addis abeba 💪

photo content