358
Subscribers
-124 hours
-57 days
-1830 days
Posts Archive
ከሰውነትዎ ውስጥ የተወሰነ ያህል ስብ እንዲቀልጥ የሚፈልጉ ከሆነ እነዚህ 10 ምግቦች ስብን የማቅለጥ ብቃት ያላቸው ናቸው፡፡
1. አጃ፡ ጥሩ ጣዕም ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ ከተመገቡት በኋላ የረሀብ ስሜት እንዳይሰማዎት ያደርጋል፤ በፋይበር የበለጸገ በመሆኑም የኮልስትሮል መጠንን ያስተካክላል፡፡
2. እንቁላል፡ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ሆኖ የካሎሪ መጠኑ ግን አነስተኛ የሆነ ነው፡፡ እንቁላል ጡንቻዎችንና ጥሩውን የኮልስትሮል ዓይነት ለመገንባት ይረዳል፡፡
3. አፕል፡ በአንቲኦክሲዳንቶችና በሌሎችም የበለጸገው አፕል በተለይም በውስጡ የሚገኘው ፔክቲን የስብ መጠንን ይቀንሳል፡፡
4. አረንጓዴ ቃሪያ፡ በአረንጓዴ ቃሪያ ውስጥ የሚገኘው ካፕሴሲን የአካላችን የእድገት ህዋሳት እንዲዳብሩ በመርዳት ስብ በፍጥነት እንዲቃጠል ይረዳል፡፡
5. ነጭ ሽንኩርት፡ በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኘው አሊሲን የጸረ-ባክቴሪያ ባህሪ አለው፣ ይህም ስብ እንዲቀንስና በደም ውስጥ የሚገኘው መጥፎው ኮልስትሮል እንዲወገድ ያደርጋል፡፡
6. ማር፡ ስብን ለማቃጠል ማር ዋንኛው ተመራጭ ነው፡፡ ለዚህም ማርን በሙቅ ውሃ በጥብጦ ጠዋት ጠዋት መጠጣት ተገቢ ነው፡፡
7. አረንጓዴ ሻይ፡ አረንጓዴ ሻይ ውስጥ የሚገኘው አንቲኦክሲዳንት የሰውነትን ክብደት ለማስተካከል ተመራጭ ነው፡፡ ለዚህም በየቀኑ ሁለት ብርጭቆ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት ይመከራል፡፡
8. ህዊት ግራስ (Wheat grass) የተሰኘው ተክል፡ ስብ እንዲቃጠል ይረዳል፡፡
9. ቲማቲም፡ ስብን በፍጥነት የማቃጠል ብቃት ስላለው በምግባችን ውስጥ ብናካትተው ተመራጭ ነው፡፡
10. ጥቁር ቸኮሌት፡ በውስጡ የሚገኘው ፍላቮኖይድስ በደም ውስጥ የሚገኘውን ኮልስትሮል ለመቀነስ ይረዳል፡፡
@habeshabodybuilders
