cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية

جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 አስታዬት👇 @Seadtu

Show more
Advertising posts
1 700
Subscribers
-224 hours
-67 days
-2230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 አስታዬት👇 @Seadtu
Show all...
የፈቲ ባል ክፍል (2).mp36.74 MB
✍️እስልምና በጥሩ ያዘናል ከመጥፎም ነገርም ይከለክለናል። ከነገራቶችም ትምህርት እንድንወስድ   ያበረታታናል ።       ❤ እውን እስልምናችን ስለ ቤተሰብ ምስረታ ምን መምሰል እንዳለበት አይናገርምን?  የትዳር አጋሮች(ጥንዶች) መዋደድ እንዳለባቸው  ስለ አንድነት አያውጅምን?  ብዙ ጊዜ ደርሶች ላይ ስለዚህ ነገር ሲወሱ አይታይም እናም አስተማሪ ይሆናል ተብሎ የተዘጋጀውን «የፈቲ ባል» ተብሎ የተዘጋጀውን ታሪክ እነሆ ብለናል።        እንዲህ ይላል ታሪኩ የፈቲ ባል" (ክፍል ሁለት) የፍቅርን ሸማ ለብሶ ለፈቲ መዉደድን አጉርሶ በመኖር የተካነዉ ሙሀመድ ይሄ ፍቅር አሰጣጡ ጀሚላ እንድትወደዉ አድርጓታል፡፡ ሁሌም ስለሱ ታስባለች ከቤት የሚወጣበትን ሰአት እየጠበቀት ታየዋለች... ወደ ስራ ሲሄድ እሷም እንደ ፈቲ ከአይኗ እስኪጠፍ ድረስ በአይኗ ትሸኘዋለች!፡፡ ... ቀኑ እሁድ ቀን ነበር ረፋድ አከባቢ የጀሚላ እናትና አባት ከቤታቸዉ በረንዳ ላይ በልጃቸዉ ኻዳሚነት ቡና እየጠጡ ነዉ፡፡ ጨዋታዉ ደምቋል፡፡ የጀሚላ እናት (እማማ ነፊሳ) የልጅነት ቁንጅናቸዉ ዛሬም አለ፡፡ ፊታቸዉ ላይ ፈገግታቸዉ ያሳብቅባቸዋል፡፡ እሳቸዉን አይቶ ጀሚላን "ልጃችሁ ናት?" ማለት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ጀሚላን በካርቦን አስገድፈዉ የሳሏት እንጂ አምጠዉ የወለዷት ብቻ አትመስልም፡፡ ... ፈቲ አስከዛሬ ብቻዋን የምሰራዉን ስራ ዛሬ በማሜ አጋዥነት ቤታቸዉ በረንዳ ላይ እቃ ያጥባሉ፡፡ የነ ጀሚላ ቤትና የነ ማሜ ቤት ፊት ለፊት ስለሆነ ከቤት ዉጭ የሚደረጉ እያንዳንዳቸዉ ይተያያሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ጀሚላ ቡና ማፍላቷን ረስታ በነሱ ፍቅር ተስባ በመተዛዘናቸዉ ተደምማ  'ኧረ የኔ በሆነ" አይነት ስሜት ታያቸዋለች፡፡ ... ማሜ በስራቸዉ መካከል ሚስቱን ዉሃ ረጨት እያረገ ይቀልዳታል፤ በመሃል ደሞ ስራቸዉን ረስተዉ ይተያያሉ፡፡ በስስት ያያታል ሳያወሩ በአይን ይግባባሉ፡፡ እሷን ሲመለከት ልቡ ቦታዉን ለቆ አይኑ ላይ የመጣ ይመስላል፤ የአይኖቹ ብሌን ልብ ቅርፅ ይሰራሉ ምንም አይነጋገሩም ግን በአይኖቻቸዉ ፍቅርን ያዜማሉ፡፡ ... የሚገርመዉ ግን ሶስተኛ አይንም ነበረ፡፡ ጀሚላ! ... ጀሚላም በፈቲ ቦታ ራሷን ተክታ ማሜን ታየዋለች የራሷ ባል አስኪመስላት በስስት ታየዋለች፡፡ በሃሳብ ተጉዛ ራሷን ከማሜ ጋር አርጋ ነዉ የምታስበዉ፡፡ እናቷ ሲጠሯት እንኳ አሰማም፡፡ እማማ ነፊሳ ተጣሩ "ጀሚላ" ዝም መልስ የለም እሷ ክንፍ አዉጥታ በራለች ዘመናትን ተሻግራ ከማሜ ጋር ተጋብታ፤ ቆንጅዬ ልጆችን ወልዳ........... በሀሳብ ጭ.... ልጥ ብላለች፡፡ እናቷ እየተጣሩ ነዉ፡፡ "ጀሚላ" "ኧረ ጀሚላ" ብለዉ ሲጮሁ ደንግጣ ከሃሳቧ ብትት ከእንቅልፏ ንቅት አለች፡፡ ነገሩ የማማ ነፊሳ አጠራር የልጃቸዉን ብቻ  ሳይሆን የጥንዶችንም ፍቅር አናጥበዋቸዋል፡፡ ማሜ በስስት ፈቲን እየተመለከታት "አንቺ ባትኖሪኮ ምን እንደምሆን ሳስበዉ..." ብሎ ሳይጨርሰዉ ፈቲም "ከእኔ የተሻለች አሏህ ይሰጥህ ነበር" አለችዉ፡፡ ማሜ ሁሌም ቢሆን "ከኔ የተሻለች..." ስትል አይወድም፡፡ አሏህ የተሻለ አይሰጠኝም ብሎ አስቦ ሳይሆንነ ከእሷ የተሻለች ሴት አለ ብሎ ማሰብ ስለማይፈልግ፡፡ ነበር " ..."ፈቲዬ አንቺ ደሞ በዚች ቃል ሁሌ ታናጅኛለሻ?" እሷም ወሬ ለማስቀየር... "የኔ ማር..." ስትለዉ "እንደዉም ካንቺ የተሻለች አገባለሁ" ሲላት ንዴቱ ወደራሷ ዞረና "ሂድ" ብላ ዉሃ ረጨችበትና አኮረፈች፡፡ ፈቲ ስትስቅም ስታኮርፍም በጣም ዉብ ናት፡፡ ካኮረፈች ደግሞ እንደ ህፃን ልጅ ያረጋታል ፡፡ ማሜም ማባበል ጀመረ ቶሎ እንደማትስቅ ስለገባዉ ልመናዉን ተወና ለቅጣቱ ተዘጋጀ፡፡.... እሷ አታወራም አኩርፋለች "ዛሬ ራሴን ራሴ ነኝና የምቀጣዉ፡፡ ተመልከቺኝ ..." ብሎ እንደ ህፃን ልጅ ተንበረከከ እጁንም ወደላይ አርገበገበ፡፡ አሁንም እንዳኮረፈች ናት ከዚያ አጎጎበደደና ጆሮዉን ሲይዝ ፈቲ በሳቅ ፍርስ አለች፡፡ ... ጀሚላና ቤተሰቦቿም "ምንድዉ ያሳቃት?" ብለዉ ሲመለከቱ ማሜ ለፍቅሩ ተንበርክኮ ያስቃታል፡፡ ይሄኔ ጀሚላ በጣም ትቀናለች!፡፡ ፍቅሯ በዉስጧ መብሰልሰል ይዟል፡፡ አዉጥታ አታወራዉ.. ለማን? ግቢ ዉስጥ ያለችዉ የእድሜ እኩያዋ "ፈቲ" ናት፡፡ የወደደችዉ ወጣት ሚስት! " ሆ ሆ " ብላ ለራሷዉ ተሸማቀቀች፡፡ አዉጥታ መናገር እንዳለበት አምናለች ግን እንዴት ብላ ያዉም ባለ ትዳርና በትዳሩ ደስተኛ የሆነን ሰዉ...፡፡ ...ጀሚላ ሌቱን ሙሉ እንቅልፍ አልወሰዳትም ትገላበጣለች፤ ታስበዋለች፡፡ ሸለብ ሲያደርጋት በአይነ ህሊናዋ ያንን ቆንጆ ፊትና የሚያምር ጨዋታዉን ታያለች እንደገና ብትት ትልና ቁጭ ትላለች፡፡ ምን እንደምትሆን ግራ ገብቷታል?.... ነገር ግን አንድ ስሜት ዉስጧን ፈንቅሎ ወጣ "ነገ ልትነገሪዉ ይገባል" የሚል ድምፅ ሹክ ያላት መሰላት፡፡ "አዎ" ስትል አሰበች "ነገ ልነግረዉ ይገባል!" "ግን... እንዴት ነዉ የምነግረዉ?" "እወድሀለሁ" ልለዉ ትልና "ኧረ..." ትላለች፡፡ "እሺ አግባኝ ልበለዉ!?" ... በጣም ጨንቋታል ሰማይ ከመዉጣት በላይ ከብዷታል ... ይሄንን እያሰበች የነገዋን ንጋት በጉጉት እየጠበቀች ከሌሊቱ ስምንት ሰአት ገደማ እንደምንም ታግላ እንቅልፍ ሸለብ አደረጋት...! ክፍል 3⃣ ይቀጥላል...... ሙሉ ታሪኩን ለመጨረስ ወደ ቴሌግራም አካውንታችን ገራ ይበሉ 👇👇👇👇👇 جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 አስታዬት👇 @Seadtu
Show all...
Show all...
ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

قال الله تعالى ( وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ )البقرة (42) አሏህ በእርግጥም አለ፦[እውነትን በውሸት አትሸፍኑ እናንተ እውነታውን እያወቃቹህ] ምንጭ፦«ሱረቱ አል–በቀራህ አንቀፅ /42/ በኡስታዝ ሐምዛ [አሰዱሏህ]

አል መዕዋ ኢስላማዊ ድርጅት የተለያዩ መድረሳዎችን ሐሪማዎችን ኡለማዎችን በመርዳት ላይ ይገኛል። አልመዕዋ እንዴት እንደተመሰረተ እና ምን ምን ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ከ አልመዕዋ መስራች ኡስታዝ አንዋር አህመድ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በዩቲውብ ይከታተሉ ። https://youtu.be/-jVv30U1Ozs?si=VFASU-FiAiuSrPr0 https://youtu.be/-jVv30U1Ozs?si=VFASU-FiAiuSrPr0 https://youtu.be/-jVv30U1Ozs?si=VFASU-FiAiuSrPr0
Show all...
መድረሳዎችን እና ዑለማዎችን ታሳቢ አድርጎ የተመሰረተው አልመዕዋ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከየት ወዴት

________________________ ዩቲውብ ሊንክ

https://www.youtube.com/c/HarimaTv

________________________ በኢትዮ-ሳት Frequency - 11545 Symbol rate - 45000 Polarisation - H እንዲከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን ________________________ በስልክ ቁጥራችን +251 953 68 68 68 +251 954 68 68 68 ያግኙን ሐሪማ ቲቪ "የምጥቀት መሠላል!"

Photo unavailable
☞አይቀርም አይቀርም አይቀርም።አልቀርምም።ማርፈድ አያሸልምም። ☞ ዛሬ ምሽት በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም እንደነበረን ለሚቀጥለው ደርስ ላይቭ ለመግባት ሁላችንም መዘጋጀት ይገባናል።ይህን ፎቶ ፕሮፋይል እናድርግ ቀደም ብለን 2:40 ላይ  እንገናኝ። https://t.me/eitavb1 https://t.me/eitavb1 https://t.me/eitavb1 https://t.me/eitavb1 https://t.me/eitavb1 https://t.me/eitavb1 ሼር ሼር ሼር።።።።።። 👆👆👆👆👆👆👆
Show all...
Photo unavailable
ያርሱለሏህ ሲከፋኝ መሳቄ ሀዘኔን አምቄ... ህመሜን ደብቄ እምባየን አድርቄ... ከሰው ስቀላቀል ምንም እንዳልሆነ... ከት ብየ ስቄ ውስጤም እያዘነ... ከህመሜ በላይ ሳቄ እያመዘነ ለሰው ብናገረው ላይረዳኝ ነገር ከሰው የተሻለ ሰው ቢኖር ምን ነበር ውስጤን የሚረዳ አፊ ሳይናገር ሰው ስላጣሁ እንጅ ሁል ግዜ መሳቄ ብዙ ....ዙዙ ህመም አለ የያዝኩት አምቄ ካንቱ ባይደበቅ በጀሰድ ርቄ ዘይንየ ልንገርሁ መዲና ዘልቄ @limugenet
Show all...
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
ትንሽ ፅሁፏ ብትረዝምም ሳትሰለቹ አንብቡት ቁም ነገር ነው 🙏🙏🙏 ያገባኛል ይመለከተኛል ለሚል ሁሉ! ኡለሞች የነብያት ምትክ መሆናቸውን ለሚያውቅ ሁሉ! የኡለሞች መኖር በረካ በዱንያ አስተማሪ ብሎ በለአ ተከላካይ በዱአ ሀገር የሚያቆሙ በነሱ ሰበብ እንጂ እንደ ስራችንማ እንደ አድና ሰሙድ ህዝቦች ድሮ ነበር ጠፊነታችን። ኡለሞች ባለውለታዎቻችን ናቸው ለሀገርም ዋርካ ናቸው ህዝበ ሙስሊሙ ንቃተ ህሊናውና አመለካከቱ የተስተካከለ ቢሆን ዛሬ ሀገራችን ላይ አንድም የእውቀት ባልተቤት በዱንያ ችግር ተታሎ መስመር የሳተ አመለካከት ውስጥ ባልገባ ነበር።ቅኖች ሆነን የኡለማን ጥቅም ብንረዳ ኖሮ አንድም ኡለማ በድህነት አረንቋ ውስጥ ባልተገኘ ነበር።የኡለማ መኖር የሀገር መኖር መሆኑን ብናውቅ ኖሮ እኛ እያለን ኡለማ የህክምና ባላጣ ነበር።የኡለማ መቀመጥ መጠበቅ ያለው በረካ ቢገባን ኖሮ አንድም ኡለማ በማይመች ቤት ባልኖረ ነበር።ኡለማ ለጀነት እንደሚያበቃን ብናቅ ኖሮ አንድም ኡለማ በመንግስት ቤት ባልኖረ ነበር በትራንስፖርት ባልተንከራተተ ነበር። የሆነው ሆኖ የኡለማ መኖር የነገ ልጆቼ መኖር የቤቴ የሀገሬ የዲኔ መኖር ነው ለሚል ለሚመለከተው ሁሉ አንድ ሀሳብ ላጋራ አሰብኩ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለአያሌ አመታት ጉምቱ ኡለሞችን ስታፈራ ቆይታለች ከኢማም አህመድ እስከ ሙፍቲ ዳውድ ከዳንዩል አወል እስከ ሼህ ኢሳ ቃጥባሬ ከሼህ አሊ ጎንደር እስከ የአናጂናው ኮከብ ሼህ ኑር ሁሴን ባሌ ከጫልይ እስከ ሰይድ አበራሙዝ (አብሬትዬወች) ከሼህ መሀመድ ራፊ እስከ ሀጂ መሀመድ ሳኒ ከሀጂ ዘይኑ እስከ ሀጂ ሙሳ ከሼህ ፈድሉ እስከ ሼህ ሰይድ ሁሴን ከሀጂ መሀመድ ሰብዩ እስከ ተቀዳሚ ሙፍቲ ድረስ አረ ሌሎች አያሌ ኡለሞችም ስንት አሉ። ይሄ ሁሉ የተከበረ ኡለማ አንዱም ደልቶት አይደለም በስነስረአቱ ሳይቸገረ የኖረ አልነበረም ሀበሻን ሀበሻ አድርገው ያቆዩ አያሌ ኡለሞች በጣሙኑ ተፈትነዋል አስቡት እስቲ እነዚህ ሁሉ ኡለሞች ፓኪስታን ውስጥ ቢሆኑ ? አረብ ሀገራት ላይ ቢሆኑ ? አውሮፓ ውስጥ ቢሆኑ ? ሀበሻ የታደለች ሀገር ሆነችና እዝህ ሆኑ አለመታደላቸው ሆነና ከኛ መሀል ሆኑ። ዛሬም ድረስ ስለ ኡለሞቻችን መንገላታት እንሰማለን አንድ ትልቅ ኢማም ታላቅ መሻይኽ ሀፊዝ ሙፈሲር ዝርያቸው ሁሉ ኡለማ የሆኑ  በከፍተኛ ሁኔታ ታመው ነበር ከገፍላ መሀል አንዳንድ ኸይረኞች አሉና ህክምናቸውን ሸፈኑ፤ የገባው ማለት ይህ ነው።ዛሬም ታላቁ ሼሀችን የኑር መስጂድ ኑር የሆኑት ታላቁ አሊም ሀጂ መሀመድ ሰብዩ ቤታቸው ለሀገራዊ ልማት ሊፈርስ እንደሆነና 40 አመት አያሌ ትውልድን ካነፁበት መስጂድ ርቀው ወደ ቃሊቲ ሊሄዱ እንደሆነ ሰማን ይሄን ጉዳይ እንደ ሀገር ዋርካነታቸው መንግስት የሆነ ነገር ማድረግ አለበት! እንደ ሙስሊም ለማይከፈል ውለታቸው ደሞ እኛ ሙስሊሞች የሆነ ነገር ማድረግ አለብን! ቢሆን ቢሆን እሳቸውም ሆነ ህዝበ ሙስሊሙ ልማት ወዳድ ከመሆናቸው በላይ ለልማት ቀናኢ መሆናቸው አለም ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ነው ከመሆኑም ጋር ሰውን ለአመታት ላለሙ ጉምቱ ታላላቅ አባቶች በልማቱ መሀል ታሳቢ ቢደረጉና እንደ ሀገር ሀብት ጥበቃ ቢደረግላቸው መልካም ነበር። ያ አልሆነም ስለዚህ ይሄ ወጣት ትውልድ በወሬ ሳይሆን በተግባር ኡለማ መውደዱን ማሳየት አለበት እስቲ ዛሬ ተግባራዊ እንሁን 50 ሎሚ ለ50 ሰው ጌጡ ነው ና ተባብረን ታላቁ አባታችንን እንኻድም የተወሰኑ ትልልቅ ባለሀብቶች አረ እንደውም አንድ ባለሀብት የሚሸፍነው ነገር እኮ ነው።ጥሩ ቤት ለሀጂ መሀመድ ሰብዩ ገዝተን እንስጥ ዱአ እንቀበል በረካም አጅርም አለው ታሪክም እንሰራለን ፍቅራችንን በተግባር አባትነታቸውን በኺድማ ልጅነታችንን በመስጋና እንግለፅ። ኡለማ በሀያት እያሉ ሊካደሙ ይገባል! ኡለሞቻችን ማብራት የአይን ብሌኖቻችን ናቸው ለብሌኖቻችን ደሞ ጥበቃ ማድረግ ግዴታች ነው።
Show all...
جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 አስታዬት👇 @Seadtu
Show all...
የፈቲ ባል ክፍል (1).mp34.87 MB
السلام عليكم ورحمة الله تعالى وبركاته ✍️ እውን እስልምናችን ስለ ቤተሰብ ምስረታ ምን መምሰል እንዳለበት አይናገርምን?  የትዳር አጋሮች(ጥንዶች) መዋደድ እንዳለባቸው  ስለ አንድነት አያውጅምን?  ብዙ ጊዜ ደርሶች ላይ ስለዚህ ነገር ሲወሱ አይታይም እናም አስተማሪ ይሆናል ተብሎ የተዘጋጀውን «የፈቲ ባል» ተብሎ የተዘጋጀውን ታሪክ እነሆ ብናል          እንዲህ ይላል 👇 ✍️የፈቲ ባል" (ክፍል አንድ) . ... ጀሚላ ከረፋዱ አራት ሰአት አከባቢ የቤታቸዉን በረንዳ በማፅዳት ላይ ሳለች የግቢያቸዉ በር ተንኳኳ ኳ        ኳ        ኳ   ይል ጀመር፡፡ ማን ሊሆን ይችላል? ብላ እያሰበች ወደ በሩ ተጠጋች  ብላም አሰበች "አባዬና ኡሚ ዛሬ የስራ ቀን ስላልሆነ ቤት ዉስጥ ናቸዉ፡፡ " እና ማን ይሆን? እያለች የግቢዉን በር ጠጋ አለችና "ማን ነዉ?" አለች "እኔ ነኝ" የሚል ለስላሳ ድምፅ ከዉጭ የተሰጣት መልስ ነበር፡፡ ድምፁን ከዚህ በፊት ባታዉቀዉም ለዘብ ያለ ሰዉ እንደሆነ በድምፁ ስለተረዳች በሩን ከፈተችለት፡፡ በጣም ቆንጅዬ ወጣት ነበር፡፡ የሙስሊምነት ገፅታ ከፊቷ ላይ ስላነበበባት ሙስሊም ስለመሆኗ አልተጠራጠረም "አሰላሙ ዐለይኪ" አላት፡፡ እሷም "ወዐለይከ ሰላም" ብላ ስትመልስለት "የሚከራይ ቤት አለ ብለዉኝ ነበር... አለ እንዴ?" አላት የጀሚላ አባት ለረዢም ሰአት በር ላይ እንደቆመች ስላዩ "ማን ነዉ?" እያሉ ወደ በሩ ተጠጉ፡፡ ወጣቱንም ባዩት ጊዜ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ወጣቱ ልጅ ለጀሚላ የጠየቃትን ጥያቄ ለአባቷ ለጋሽ ይማም ደገመላቸዉ፡፡ ... ከዚህ ጊዜ በኃላ ነበር ጀሚላ ሙሀመድን ያወቀችዉ፡፡ ሙሀመድ እጅግ በጣም ዉብና ማራኪ ልጅ ነዉ፡፡ ሚስቱ ደግሞ ፈቲ ትባላለች፡፡ እጅግ ሲበዛ ዝምተኛ ናት፡፡ ቤት ስለምትዉልና ጀሚላም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ብትሆንም ሰመርን(ክረምትን) ከቤተሰቦቿ ጋር ስለምታሳልፍ ሁሌም አብረዉ ይዉል ነበር፡፡ ፈቲ ምንም ያክል ዝምተኛ ብትሆንም ለባሏ ግን ፍቅርን መስጠት የምትችል፣ አሷም  ልክ እነደ ባሏ መልከ መልካም አርቆ አሳቢና  ትሁት ልጅ ነበረች ። . ..... ሙሀመድ ከስራ ሊመጣ አከባቢ ፈቲ እጅግ በጣም ተዉባ ከወትሮዉ በተለዬ ይበልጥ አምራ የግቢዉን በር ለመክፈት ከቤቷ ወጥታ በሯ አጠገብ ትቀመጣለች፡፡ ልክ በሩ እንደተንኳኳ ሩጣ ትሄድና ቶሎ ትከፍታለች፡፡ ባሏ ሙሃመድም እቅፉ ዉስጥ አስገብቶ ሲስማት ለተወሰነ ሰአታት የተለያዩ ሳይሆን ለአመታት ተራርቀዉ ተነፋፍቀዉ የተገናኙ ይመስላሉ፡፡ ሙሀመድ ፍቅር መስጠት ተክኖበታል፡፡ እሷን ሲወዳት ሲንከባከባት ምድር ላይ ሌላ ሴት እንደ ሌለ አስመስሎ ነበር፡፡ ለሱ ሴት ማለት (በፍቅር እይታ)እሷ ብቻ ናት፡፡ እንደ እናት ያከብራታል፤ ያፈቅራታል በጣም ይሳሳላታል፡፡ ፍቅራቸዉ እንኳን አብሯቸዉ ለሚኖር ሰዉ ለአንድ ቀን በመንገድ ላይ ያያቸዉ ብቻ ይቀናባቸዋል፡፡ . ....ከግቢዉ ኗሪም ጋር በጣም ተግባብቷል፡፡ ጋሽ ይማምን ለብቻቸዉ ባገኛቸዉ ሰአት "አባባ ገና ወጣት ትመስላለሁ አረጅታችኃል የሚል ሰዉ ካለ ካላችሁ ጥንካሬ አንፃር  የተሳሳተ ይመስለኛል፡፡ አሁን እኔ እና አንቱ ሩጫ ብንሽቀዳደም አዝነሁ ካልተዉኩኝ በስተቀር ትበልጡኝ የለ እንዴ! አንቱኮ ሀይሌን ታስንቃለሁ፡፡" እያለ ይቀልዳቸዋል፡፡ እሳቸዉም የወጣትነት ጊዜያቸዉ ታዉሷቸዉ በጨዋታዉ ከሳቁ በኃላ "አይ ልጄ..." ብለዉ ትረካቸዉን ይጀምራሉ፡፡ ለወሬያቸዉ አክብሮ ጆሮ ስለሰጣቸዉ ከስራ የሚመለስበትን ሰአት እንደ ፈቲ እርሳቸዉም ይጠባበቃሉ፡፡ በተለይ ደሞ ጀሚላ...! ጀሚላ ለምን ይሆን የሱን መምጣት  የምትከታተለው    ..... ክፍል 2⃣ይቀጥላል ወደ ቴሌግራም አካውንታችን ለመቀላቀል جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6 አስታዬት👇 @Seadtu
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.