cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🗣 የሚደሙ ቃላት ✍

ቃላት ሲደሙ ስሜት ይታከማል፤ቃላት ሲደሙ ማንነት ይጠራል፤ቃላት ሲደሙ ሀገር ትገነባለችም ትጠፋለችም ለበጎ መምጣቶች ስል በምናቤ ሹለት ሀሳቤን ሞርጄ ብዕርን ሳይሆን ቃላትን አደማለሁ!!! ስሜትን የሚያጎሉ ግጥሞች ፏ ያለ ሙዚቃ … ብቻ ምን አለፋችሁ የስነፅሁፍ ገበታ👉 @Seyamuhe For any comment @MelketenBtebebBot @Naolviva

Show more
Advertising posts
247
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዳናህ የሌለበት ሁሉ የሆነ ወና፤ ቅመምህ ያልከሸነው ቀልዳቸው ዳመና፤ ብርሀን ፈንጣቂ አንተ ብርቅርቅታ አንተ አሁን ገና ገባኝ ሳቅህ ያላጀበው ሳቃቸው ሲያስነባኝ!!። ✍ከ ናፊ
Show all...
"አልወድሽም" ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ "ቋ ቀጭ ቋ ቀጭ" ህይወት መጣች ሳቋን ይዛ አልቆየችም እንደ ጤዛ ... እቅፍ ሳም አንገቴ ስር ለወጠችኝ በቀይ ምስር .... ተሸጥኩላት ባገኘችው ተሞኘሁኝ እንዳለችው.... (አልወድሽም) ቋ ቀጭ ቋ ቀጭ ጫማዋን አወለቅች ልብሷን አወለቀች አብራኝ ተኛች አወላልቃ እኔ ከፋኝ እርሷ ስቃ (አልወድሽም) ህልሟ እንደጠፋባት እንደልጃገርድ ወዴት ለመሄድ ነው ከአልጋዬ የምወርድ? ወዴት ? ህይወት ራሷ ናት አንገቴን ብትቀላ በሰው ተመስላ:: ህይወት ራሷ ናት ውሸት ብታሰላ ሞቴን ያስመኝችኝ ፍቅር አስመስላ:: ህይወት ውሸት አሞኝችኝ ገላ ነፍሴን ቀደድችኝ አጎነበስኩ እንደስንዴ ይወጋኛል ዕንባ ቀንዴ "ህይወት በቃኝ" ስል ሰማችኝ ሳቀችብኝ እያየችኝ:: (አልወድሽም) እጠጋበት ባጣም እተኛበት ባጣም እሞትበት ባጣም እስቅበት ባጣም አለቅስበት ባጣም እናቅበት ባጣም እንደወደድ ባጣም እደርስበት ባጣም ከእቅፍሽ ባልወጣም ወዴትም ባልሸሽም ማርያም ምስክሬ ህይወት አልወድሽም:: አልወድሽም አልወድሽም አልወድሽም @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማረግ ይተባበሩን..!😊
Show all...
ለሸሸሁት ወንድነትህ ለሸሸኩት ሴትነቴ ለረሳሁት አንተነትህ ላልታወሰኝ ማንነቴ ታድያ እንደምን ለምን…ለምን ይቅርታህን የምለምን ለገፋኋቸው እጆችህ ለረገጥኳቸው እግሮችህ ወዝነት ላጣ መውደዴ ለብቸኝነት መንገዴ ለከረፋው ሽቶ ልቤ ለሞተብኝ ላለው ቀልቤ በየትኛው ጥፋቴ ይሆን?! እኔነቴን የገለበ ከቁርበትህ ያጋደመኝ ገሀድ ኑረቴን ነጥቆ ከቅዠትህ ያሳደመኝ የቱ ግፌ የቱ ዕድፌ ያደረገህ ከንቱ አባባል የሌት ትዳር የህልሜ ባል። እኔ ብኩን የሰውግርድፍ ወይ አልፆመው ወይ አልገድፍ። [ረድኤት ሰኢድ መሀመድ] @seyamuhe @seyamuhe
Show all...
"መሀል ቤት" እኔ ብኩን የሰው ግርድፍ ወይ አልፆመው ወይ አልገድፍ። አወይ ፍዳ ወይ መበደል ከቀረቡት አለመሙላት አለመጉደል! ለርጥብ ገላ ላልወረዛ ላላደፈ አዲስ ዕጣን ንፁህ መቅደስ ያልገደፈ ቢሆን ልኩ ግብረ-ግብሩ ተመሳስሎት ቢለካኩም የኔን ርጥብ ህልመገላ ለመቅደስህ ከቶ አልላኩም። ታድያ እንደምን ከላቦቴ ምተናኮል አዲስ ጠረን ሚኮለኮል አንደበቴ የያዘ ጣር አንድ ርምጃ አንድ ፍንጣር ለምን…ለምን ማረኝ እያልኩ የምለምን
Show all...
Repost from Smart store 🛍
00:21
Video unavailableShow in Telegram
😊🙏👏👏👏 ◉ Join Us, @Best_tik_tok_video
Show all...
82314089d6e74937aaaff32362868fab.mp42.03 MB
ትናፍቀኛለህ😍 @seyamuhe @seyamuhr
Show all...
8.33 KB
ዋ! ሰብዕ ይኸውልህ አለሜ እኔ ያንተው ገፊ ከትናንት አንደበት ከዛሬው ልሳኔ ከነገ ቃል ዋጀሁ ይሆል እያልኩኝ በይሆናል ተስፋ ስንት ዘመን ፈጀሁ። ሰባት ሀሳብ ይዞ ራስን የሚያህል ድብቅ ወርቅ ግልጥ ሰም ዝተታም ማፍቀርህ ከነጣው ልቤ ላይ እንደምን ምን ይክሰም?! መክሰሙስ ባልከፋ… ብን እብስ ይበለው እስከአመዳም መልኩ ወትሮስ ፍቅር ተባይ እሳት አይደል ልኩ?! ይኸውልህ ዛሬም… ከሰባቴ ሰባት አንድ አላገኝ ብዬ ስባዝን ስባዝን ቀን ሄዶ ቀን ጠባ በሀዘኔ ሳዝን። አሁንማ… ተለማመድኩ መሰል ከሳቀው ሳቅ መዋስ መፍጠር አዲስ ህዋስ ያልፋልን እላለሁ ተስፋ አነጋለሁ ተስፋ አመሻለሁ እኔ ያንተው አፍቃሪ መቼ እሸሻለሁ?¡ ግን አንድ እድፍ አለኝ ከሁሉም ከሁሉም ገዝፎ የሚታየኝ ነጥሮ ሚጎላብኝ ግን…ደሞ የወደደ ሁሉ መሳ አይወደድም ቆብ ከዐይን ቢተኛም እንቅልፍ ሳይረገዝ ህልም አይወለድም(…አይደል?) ያኔ…ድሮ በኮልታፋ አንደበት ሀ-ግዕዝ ሁ-ካዕብ… እለፍፈው ነበር ፊደል እያዳፋው አሁን ዛሬ በተሳለ ምላስ ዋ-ሰብዕ እላለሁ ምንስ ፊደል አለው መናገር ለጠፋው?! [ረድኤት ሰኢድ መሀመድ] @seyamuhe @seyamuhe
Show all...
?አዎ ማለት ማንን ገደለ? ፩(1)………እየሄድን ነው ወደ አስኳላችን እየተጓዝን ድንገት አይኔ ከጓደኛዬ ትከሻ ትይዩ መሆኑን ልብ አልኩ እናም አንድ ነገር ውል አለኝ። ከ፪ ዓመት በፊት የነበረን የቁመት ልዩነት… እሷ ጡቷን አንከርፍፋ ወደ ልጇ አፍ እንደምትሰድ እናት…እኔ የእናቱን ጡት ሽቅብ ቁልጭ ቁልጭእያለ እንደሚያይ ህፃን… "እኔ ምልሽ ፂ ፲(10) ያ ክፍል እያለን ትዝ ይልሻል ቁመታችን? "ስላት "አዎ እና አሁንስ?"አለች "እንዴ አሁን እኮ ገሚስ ጭንቅላቴ ትከሻሽን ተሻግሯል" እላታለሁ "ባክሽ እኔ አጥሬ ነው" አትል! ኧረ ወገን አንጨካከን! ምንአለበት አሁን አዎ ብትል?! የእኔ ቁመት ለማደጉ ምይሁን ብሎ ነው የእሷ ቁመት የሚያጥር? ደሞ ፈጣሪ የእኔን ቁመት ለመጨመር የእሷን ቁመት የሚያሳጥር የቁመት ደሀ አይደለም! ፪(2)………እየሄድን ነው ወደ ቤቷ እየሸኘኋት ለሚያየን እኮ ሴትናሴት አንመስልም። በፀሀይ ብርሀን ተሸሽገው ጨረቃ ብቅ ስትል እንደሚያጅቧት ክዋክብት ጨለማን ተገን አድርገን ነው ምንሸኛኝ። ቤቷ በራፍ ደረስን እያወራን……እያወራን ድንገት አይኔ ከትከሻዋ ትይዩ ሆነ (የእኔ መለሎ ጭንቅላት) የሆነ ነገር ትውስ አለኝ… ከቤተክስያን ስንመለስ እግር የሚያህለው እጇ ከትከሻዬ ግዛት አልፎ በነፃ ከባቢው ላይ ሲንዘላፈፍ በዛ ላይ መአት የሚያህለው ጭንቅላቷን አስደግፋብኝ እንዴት ሹልክ ብዬ እንደወጣሁ¡ (ከዘራ አደረገችኝ እኮ…) "እኔ ምልሽ ሄሉ ቁመት ደረስኩብሽ ኣ?"ስላት… "አዎ አንቺ! አሁን እኮ ለማቀፍም እኮ ትመቻለሽ" አለችና "ምን ባክሽ ግን እኮ እኔ ስለወፈርኩ ነው " አትል?! ኧረ ተዉ! እንደግበት እንጂ ጎበዝ! ምን አለበት አሁን "አዎ" የሚለው ምላሿ ቢፀና?! በራስ በሚመች ቃል ሸርተት? ኧረ ለመሆኑ የእኔ ቁመት ለማደጉ በምን ስሌት ይሆን የእሷ ውፍረት የሚጨምር? ደሞ…ፈጣሪ የአንዱን ቁመት ለመጨምር ሌላውን የሚያወፍር የቁመት ደሀ አይደለም! "አዎ" ማለት ስለሚከብደን እኮ ነው "አይ" ማለትም የሚከብደን የምር! ✍… @seyamuhe @seyamuhe
Show all...
ወደው አይስቁ የውልሽ..... አንቺዬ በታዳሚያን ፊት ፥ አንዱ ወግ አዋቂ ዲስኩር ሲሰካካ እራሱን ኮርኩሮ ፥ አንቺም እንድትስቂ አላውቃት አታውቀኝ የነቀዘ ሰብል ፥ መች እኔን ሊደንቀኝ ከሁሉም አጣላኝ ፥ አምላክ ሊታረቀኝ ብሎ ክትክት አለ...በሳቁም ገደለኝ ። በኔና በሱ ቤት ድንግል ጎልማሳ አገር ፥ በእድሜዋ ማምሻ በደባ ተደፍራ ወልዳ ታርፍ ዘንዳ አምሮቷ እያደገ ሽታ እየነቀሰ ፥ በህዝብ እየሰፋ ተስፋ ተገዝግዞ ፥ ሰበዙ ሲለፋ ቀዩ ሰው ሲጠቁር ጥቁሩ ሰው ሲከፋ እንደ ሁሉ አገርሽ እንደ እንደልቡ ሁሉ እንደሞላለት የጭንቅን አቀበት በመታበይ ጉልበት ለመውጣት ማሰቡ ፥ በራሱ ይደንቃል ድሮስ ሹማምንቷ የልመና ስንዴ ፥ መቼ በልቶ ያውቃል ? አብርሃም ተክሉ @Abr_sh @getem @getem
Show all...
ቢሆን ምን አለበት? . . . ከአካልህ ጠረን ከገላህ ስር ዕጣን አንድ መዐዛ አለ ደርሶ የሚያወዳጅ ፃድቃንን ከሀ'ጣን ምንድን ነው ግን እሱ?! የነፍሴ ዝማሜ እያደር ሚብሰው የነፍስያህ ክፋይ እኔን ሚቀድሰው የገላዬ መዛል መውደቅ መብረክረኩ ጉልበቴ ሳይታጠፍ ደሞ መንበርከኩ ፀበል ተፀብዬ በገላዬ ላቦት ንገረኝ እባክህ ፅላት ነህ ወይ ታቦት? እግዚኦ…ጌታዬ ኢግዚኦ…አምላኬ ኢግዚኦ…ለስምህ በየቱ ከንፈሬ በየትኛው ፊቴ ልሳም ልሳለምህ? ሳትነካ ምታቃጥል ሳትዳሰስ የምትፋጅ የእሳት ዕትም እቶን ምስል ሰው አልልህ ሰው አትመስል! እቶን ገላህ እያራሰኝ ከሙቀትህ የከለሰኝ ከሞትኩበት የህይወት መደብ አፈሮቼን የሚገድብ ከደቃሁት ደረት ልቤ የምትፈልቅ ስውር ቀልቤ እሪታዬን የምትጋርድ ጫጫታዬን የምታርድ የዝምታዬ አለቃ የፀትታዬ ምንዳ የሰውነቴ መከራ የሴትነቴ ዕዳ ንገረኝ እስቲ በ'ኔ ሞት በዘመንህ ቀመር ክራሞት ያውቅ ኖሯል አካልክን አሞት? ከአካልህ ጠረን ከገላህ ስር ዕጣን አንድ መአዛ አለ ደርሶ የሚያወዳጅ ፃድቃንን ከሀ'ጣን የገላህ ስር ዕጣን ጢሱን ሲያተነው መአዛው እኔነቴን ሲበታትነው ያብረከርከኛል ያንበረክከኛል ቀድሽ ያሰኘኛል ዝማሬም ያሻኛል እዝል ይጠራኛል ግዕዝም አራራይ ግጥሙ ከኔ ነው ቅኝቱ ግን ኪራይ ጠጠር አንሺ ይለኛል ጎልያድን ግደይ ዘመን አምጪ ይለኛል አለምልሚ አደይ ብቻ…ብቻ…ብቻ እንዲህ ሁኚ ይለኛል ሲለው ይሰራኛል ሲሻውያፈርሰኛል ወደእዚያ ይወስደኛል ከዛ ይመልሰኛል ፀበል ተፀብዬ በገላዬ ላቦት ንገረኝ አንተዬ ፅላት ነህ ወይ ታቦት? እግዚኦ…ጌታዬ እግዚኦ…አምላኬ እግዚኦ…ለስምህ በየቱ ከንፈሬ በየትኛው ፊቴ ልሳም ልሳለምህ?! [ረድኤት ሰኢድ መሀመድ]
Show all...