cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣ አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣ ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው። @MentalCounsel ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል! ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ! 🏠Welcome to your Home! 🏘 Personal Contact: @epha_aschalew Insta: instagra.com/epha_aschalew

Show more
Advertising posts
42 288
Subscribers
-3124 hours
-1967 days
-75430 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Traffic sources
  • Subscribers 90.35%
  • Channels 3.09%
  • Via the link 0.35%
  • Groups 3.30%
  • Telegram search 0.08%
  • Direct messages 2.69%
  • Other 0.13%
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
ነገ የለም! ፨፨////፨፨ ብዘዎቻችን ከነገ ጋር ያለን ፍቅር እጅጉን ይለያል፤ ነገ የሚባል ተጨባጭ ቀን ሳይኖር በውስጡ ተዓምራዊ ምቾት እንዳለው እናስባለን። በህይወት ዘመናችን እንደ ነገ የጠበቅነው፣ በጥበቃችን ልክም ያላገኘው ነገር የለም። ሁሉን ነገር ለማድረግ ነገን መጠበቅ፣ ምንም ለመጀመር ነገን መናፈቅ፣ ስንፍናን ለመሸፈን፣ ድካምን ለማስታገስ፣ ምቾትን ለመጠበቅ ነገ የተባለ ቀን ሁነኛ ምክንያት ሆኖልናል። ነገ የት ነው ቢባል ምላሽ የለም፤ ምንም የሚታቅ ነገር የለም። ለነገ ይታሰባል፤ ለወደፊት ይታቀዳል ነገ ግን አይኖርም፤ ወደፊት ውስጥ እቅዱ አይፈፀምም። የማይደርስ መስሎህ በነገ ስም ያራዘምከው ቀን ዛሬ ሆኖ ከፊትህ ይደቀናል፤ ዛሬ ነገ እያልክ ያሸጋገርከው ጉዳይ ነገን አያውቅምና በጊዜው አሁን መፈፀምን ይፈልጋል። ረጅም ጊዜ እንዳለህ እያሰብክ፣ ብዙ የምትኖረው እድሜ እንደቀረህ እያለምክ ለነገ የምትገፋቸው ጉዳዮችህ ዋጋ ማስከፈላቸው ግድ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ነገ የለም! ልያዘው ብትል አትይዘውም፤ ልጨብጠው ብትል አትጨብጠውም፤ ትርጉም ያለው ትርፋማ ነገር ላድርግበት ብትል አታደርግበትም። የምትናፍቀው ነገ ዛሬ ነው፤ የምትመኘው ተጨባጩ ወደፊት አሁን ነው። ፍቅር ለመስጠት፣ ያለህን ለማካፈል፣ የምትችለውን ለማድረግ፣ ጥረትህን ለመጨመር ያለህ ጊዜ አጭርና አሁን ብቻ ነው። ሃሳቦችህ የእራሳቸው ደረጃ አላቸው፤ እቅድችህ የቀን ገደብ ይኖራቸዋል እውንነታቸው ግን በዛሬ ውስጥ ነው። ትልቁ ህልምህ የሚኖረው አንድ በማይታወቅ ቀን ሳይሆን ዛሬ በሚታይ፣ በሚጨበጥ፣ በሚዳሰስና በሚታወቅ ቀን ነው። በነገ ምክንያት ያመለጡህን አጋጣሚዎች፣ የረሳሃቸውን አስገራሚ ሃሳቦች፣ ያጣሃቸውን ሰዎች፣ የደከሙብህን መገለጫዎችህን አስታውስ። ስታቅድ ኖረህ ስታቅድ ማለፍ አትፈልግምና በትንሹም ቢሆን መራመድ ጀምር። አዎ! ያንተ የሆነው የትም አይሔድም፤ ነገር ግን አንተ ከገፋሀው ለማንም ሳይሆን ያልፋል። ዛሬና ነገ በእጅጉ ይለያያሉ። ልዩነታቸውም በየሃሳብ ህልውናና በተግባር ህልውና ነው። ነገን ከሃሳብ ውጪ የምትይዝበት መንገድ የለም፤ ከምናብ በተለየ የምትዳስስበት ሁኔታ የለም። ህልውናው፣ መኖሩ በሙሉ ሃሳባዊ ነው። ዛሬ ግን አሁን ነው፤ ሙሉ ነው፤ የሚታይ፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ፣ ከሃሳብ የዘለል ተግባራዊ ህልውና ያለው ነው። በምናብ መኖር፣ በሃሳብ ማደግ ደስ ይላል፣ ተጨባጭ ግን አይደለም። ነገን እያለምክ በዛሬ ውስጥ ታስረህ አትቅር። ያሰብከውን ሁሉ ማድረግ የምትችለው ነገ ሲባሉ በነበሩ ዛሬዎች ውስጥ ነው። ሃሳባዊው ነገ በትንሹ ሊያስፈልግህ ይችላል፣ የህይወትህ መርህ ሊሆን ግን አይችልም። ማየት የሚገባህን የምታየው ዛሬ እንጂ ነገ አይደለም፤ ሃሳብህ እውን የሚሆነው አሁን እንጂ ቦሃላ አይደለም። መኖር የምትፈልገውን ህይወት በተሰጠህ ዛሬ ውስጥ ኑረው። ህይወትህን አንተው በሃሳብህ ሙሉ ካላደረካት አትሞላምና ለምትወዳቸው ሰዎች ፍቅርህን ለመግለፅ፣ የምታስበውን ስራ ለመጀመር፣ መሆን የምትፈልገውን ሰው ለመሆን ነገን መጠበቅ አቁም። የዛሬ ሃላፊነትህን ተወተህ ሃሳባዊውን ነገ ሙሉና ተጨባጭ አድርገው። ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
59510Loading...
02
ዋጋቢስ አትሁን! ፨፨፨///////፨፨፨ መልካም በተባሉ ነገሮች መማረክ፣ ጥሩ በሰራው መደነቅ፣ የሰዎችን ህይወት ማድመቅ ብሎም ማድነቅ ክፋት የለውም የእራስን መርሳትና ማደብዘዝ ግን ትልቅ ክፍተትን ከብዙ ችግር ጋር ይፈጥራል። የየለት አጀንዳህ የሰዎች ህይወትና አኗኗር ከሆነ ለእራስህ ጊዜ ሊኖርህ አይችልም። የእነርሱን ትንሽ አጀንዳ በማጉላት ከተጠመድክ ያንተው ትልቅና ወሳኝ አጀንዳ አስታዋሽ ያጣል። ይህ አስታዋሽ ያጣው ወሳኝ አጀንዳህም ቀስ በቀስ ስር እየሰደደ ውድቀትህን ሲያፈጥንና ችግሮችን ሲደራርብብህ ልትመለከት ትችላለህ። የሰው ህይወት የሰው ነው፣ ያንተም ህይወት ያንተ ነው። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንደተባለችው ሴት አትሁን። በሰው ቤት ሄደህ ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን ከመሞከርህ በፊት መጀመሪያ የራስህን ቤት አቅና፣ የራስህን ጎጆ በሚገባ ገንባ። ክብርህ በቤትህ ነው፣ ዋጋ የሚኖርህ ለራስህ በምትሰጠው ዋጋ ልክ ነው። የማይመለከተውን እየተነተነ ለሚመለከተው ጉዳይ ጊዜ ያጣ ብዙ ሰው አለ፣ የራሱን ችላ እያለ የሌሎችን የሚፈተፍት ብዙ ሰው አለ፣ ዋናው ትኩረቱ እራሱ መሆን ሲገባው ትኩረቱን ሌሎች ላይ ያደረገ ብዙ ሰው አለ። አዎ! ጀግናዬ..! ዋጋቢስ አትሁን! መራሩን እውነት ለመሸሽ አትዋደቅ። አንተ ለራስህ ዋጋ ካልሰጠህ ማንም ዋጋ ሊሰጥህ አይችልም። በየመንገዱ ለምታየው ነገር አስተያየት በመስጠት አትጠመድ፣ በአላፊ አግዳሚው አትማረክ፣ የእራስህን ጉዳይ የማትከታተል ለሰው ጉዳይ የምትዋደቅ፣ ለመወደድና ትኩረት ለማግኘት ላገኘሀው ሰው ሁሉ ድክመትህንና ከእርሱ ያነስክ እንደሆንክ የምታወራ አሳፋሪ ሰው አትሁን። ሰው አይደለም እቃ እንኳን የውድነቱ ማሳያ የዋጋው ጭማሬ ነው። ዋጋህ ካልጨመረ ማንም ሊያነሳህ እንደማይመጣ እወቅ። ይሔንን አስታውስ፦ "ዛሬ የእለት አጀንዳህ አንተ ነህ።" ዓለምን የማትሰማበት፣ ከጫጫታዋ ዞር የምትልበት፣ በማይረቡ አዳዲስ አጀንዳዎቿ የማትታለልበት፣ የማይጠቅምን የመረጃ በር የምትዘጋበት፣ አኗኗሪ መሆንህ የሚያበቃበት፣ ነዋሪነትህ የሚጀምርበት ጊዜ ዛሬ ነው፣ ከዛሬም አሁን ያለህበት ሰዓት ነው። በቅድሚያ የእራስን ሸክም ማራገፍ ስልጣኔ ነው። ሁን ተብሎ የሚሰራን ድራማ የህይወት አጀንዳ ማድረግ ቅለትና ብክነት ነው። አለም አዳዲስ አጀንዳ አታጠም፤ አዳዲስ ወሬ አታጣም። ያንተ በእርሷ ጊዜያዊ ድራማ መታለል ዋጋ ከማስከፈሉም በላይ ያንተንም ዋጋ እያሳነሰ ዋጋ ቢስ እንደሚያደርግህ እወቅ። አዎ! ፈተና ከተባለ እራስን ከማስረሳት በላይ የሚፈትን ነገር አይኖርም። ትኩረትህ ወደ ውጭ በሆነ ልክ ውስጥህ ባዶና ጥቅም አልባ እየሆነ ይመጣል፣ አይንህ አካባቢውን ብቻ መመልከት ከጀመረ የሚያስፈልገውን ነገር ማግኘት ያቅተዋል። ሁላችንም ጦርነት ውስጥ ነው። እራስን የመግዛት ጦርነት። ዓለም በዛኛው ወገን ልትገዛን ትጥራለች እኛም በነቃን ቁጥር በዚህ በኩል እራሳችንን ነፃ ለማውጣት እንታገላለን። በየቀኑ የሚመጡ የአለም ክስተቶች ለእራሳችን ጊዜ እንዳይኖረን፣ በእነርሱ ጉዳይ መጠመድና መብከንከን ዋነኛው ተግባራችን እንዲሆን እያደረጉን ነው። የሌላውን ስናደምቅ የእኛ ሲፈዝ፣ የሌላውን ስናሳምር የእኛ ሲበላሽብን መመልከት የየለት ተግባራችን ኋኗል። ህይወትህ ላይ ጠብታ ያክል ነገር የማይጨምር የአለምን ጋጋታ መከተልህ ማብቂያው አሁን ነው፣ መጨረሻ የሌለውን ጊዜያዊ አጀንዳ የመስማቱ ፍፃሜ አሁን ነው። በጊዜያት ለማይቀረው፣ በህይወት እስካለህ ድረስ አብሮህ ለሚኖረው ለእራስህ ጊዜ መስጠት ጀምር፤ ዓለም ካንተ ቦሃላ ነችና አራስህን ቀዳሚው የህይወት አጀንዳህ በማድረግ ለዓለም ጠቃሚና ከዓለም ተጠቃሚ ሆነህ ተገኝ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
1 02510Loading...
03
✝✝ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፣ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። ✝✝ "ምድር ጸዳች ሐሴት አደረገች  በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች።" እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! 💒✞❖ መልካም በዓል! 💒✞❖ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን! ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
1 37811Loading...
04
✅ ከፍርድ ተቆጠቡ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/2GmfpRhWHgE?si=KOdGj-snzJ8kqb5e
1 2261Loading...
05
ልማድን በልማድ! ፨፨፨/////////፨፨፨ በእድሜያቸው የሸመገሉ ሰዎች በሚኖሩበት የአዛውንት መጦሪያ ቤት የሚሰራ የእነሱ ተንከባካቢ ባለሞያ ወጣት ስራውን በጣም ስለሚወደው ለእነዚህ አዛውንት የሚሰጠውን እንክብካቤ ከልቡ ነበር የሚያደርገው፡፡ ነገር ግን፣ ይህንን ስራውን እጅግ አስቸጋሪ ያደረገበት አንድ ነገር ነበር፡፡ ሁለት በዚያ የጡረተኞች ቦታ ጓደኝነት የፈጠሩ አዛውንት ማታ ማታ ከቤት ወጥቶ በአካባቢው ተዘዋውሮ የመመለስ የብዙ አመታት ልማድ ስላላቸው አብረው ያንን ያደርጋሉ፡፡ በመቆያ ቦታው ሕግ መሰረት ግን ይህንን ማድረግ ክልክል ነው፡፡ ምክንያቱም በጣም ስለሸመገሉ አደጋ ሊደርስባቸው ስለሚችል ካለጠባቂ መውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ ይህንን ልማዳቸውን ለማስቆም ብዙ ሞክሮ ያቃተው ወጣት ሰራተኛ በመጨረሻ አንድ የስነ-ልቦና አዋቂ አማከረ፡፡ አማካሪውም ወዲያውኑ፣ “እነዚህ አዛውንት ማታ ከቤት ለመውጣት ሲያስቡ በፍጹም ሳይዙ ወይም ሳያደርጉ መውጣት የማይችሉት ልማድ አላቸው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ወጣቱ ትንሽ አሰበና፣ “አዎን፣ ሁለቱም ኮፍያቸውን ሳያደርጉ በፍጹም መውጣት አይወዱም፡፡ ኮፍያቸው ከታጠበ እንኳን እስከሚደርቅ ጠብቀውና አድርገው ነው የሚወጡት” አለው፡፡ አማካሪውም፣ “እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ አየህ አንድን ልማድ ለማቆም ሌላ ልማድ መጠቀም አለብህ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ አለፍ አለፍ እያልክ ኮፍያቸውን ደብቅባቸው፡፡ ኮፍያቸውን ሳያደርጉ መውጣት ያለመቻል ልማዳቸው ወደ ውጪ ከመውጣት ልማዳቸው ስለሚጠነክር በዚያ ምክንያት ከመውጣት ታስቀራቸዋውና ቀስ በቀስ እቤት ሲያመሹ ሌላ ከቤት የማያስወጣ ልማድ ያዳብራሉ” ብሎ መከረው፡፡ ወጣቱ ይህንን ምክር ገና ተግባር ላይ ከማዋሉ ውጤታማ በመሆኑ በጣም ተገረመ፡፡ አዛውንቱ ኮፍያቸውን ባጡባቸው ቀናት እቤታቸው ቁጭ ብለው የድሮ ታሪክ ሲያወሩና የድሮ ፊልሞችን እየከፈቱ ሲመለከቱ በማምሸት ማታ ወደውጪ የመውጣትን አደገኛ ልማድ በሌላ ጤናማ ልማድ ለመለወጥ ጊዜ አልፈጀባቸውም ነበር፡፡ ለወቅቱ “ጨለማ” የማይመች ልማድህ ምንድን ነው? እቤት መቀመጥ አለመቻል? ውጪ የመመገብ ልማድ? ከሰዎች ጋር ሳይሰባሰቡ አለመዋል? የወቅቱ ወረርሽኝ ላመጣብን “ጨለማ” የማይመጥነውን ከአንተ ጋር የከረመ ልማድህል ለመቀየር ቀላል ባይሆንም የማይቻል ግን አይደለም፡፡ ቀላሉ መንገድ ከዚያ ልማድህ የጠነከረ ሌላ ልማድ ማዳበር ነው፡፡ እቤት መዋልን እንድትወደው የሚያደርግ ልማድ ፍጠር፡፡ ከቤተሰብ ጋር ማሳለፍ፣ ማንበብን መልመድ፣ በሁለት ወር ውስጥ በአንድ አዲስ እውቀት ራስን ለማሰልጠን ማቀድ፣ የማትችለውን ምግብ ማብሰልን መልመድ፣ አንድን መጽሐፍ መምረጥና ከቤተሰብ አባላት ጋር በየቀኑ ማጥናትና መወያየት፣ ስፖርት መስራት . . .፡፡ መላው ብዙ ነው፡፡ አትርሳ፣ የሚያጠፋህም ሆነ የሚያለማህ ልማድህ ነው፡፡ ©ዶ/ር ኢዮብ ማሞ ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
1 84210Loading...
06
"ምን ላድርግ?" ፨፨፨//////፨፨፨ መቼ፣ እንዴት፣ የት፣ በምን ደረጃ እንደምትገኝ አታውቅም። ብዙ ብታቅድም፣ ብዙ ብታስብም ሃሳብና እቅድህ ሚዛን ሳይደፋ፣ ሳይሳካ ያልገመትከውና ያላሰብከው ስፍራ እራስህን ልታገኝ ትችላለህ። ስኬትን አቅደህ ወድቀህ ይሆናል፣ ብረሃንን አስበህ በጨለማ ተከበህ ይሆናል፣ ብዙዎችን ለማገዝ አስበህ ተረጂ ሆነህ ይሆናል፣ ችግር ለመፍታት እየተንቀሳቀስክ ችግር ውስጥ ተገኝተህ ይሆናል። ተጨባጩ ክስተት፣ ያለው እውነታ ከሃሳብና እቅድህ በብዙ እጥፍ ተቃርኖ ቢገኝ፣ እጅጉን ቢራራቅ ያንተ ግብረመልስ ምን ሊሆን ይችላል? ከመቀበል ባሻገር ቀጣይ እርምጃህ ምንድነው? አዎ! ጀግናዬ..! ያለህበት ሁኔታ ያልታሰበና ያልተመቸህ፣ አቅደሀው የማታውቀው፣ ለማመን የከበደህ ቢሆንም እንኳን የያዝከውን ይዘህ፣ የደረሰብህን ችለህ፣ ህመምህን ውጠህ እራስህን አንድ ጥያቄ ጠይቅ። ስለሁኔታው " ምን ላድርግ? " ብለህ ጠንቅ።  "ካለሁበት አስከፊ ሁኔታ ለመውጣት ምን ላድርግ? ምን ልስራ? እንዴት ልስራ? እንዴት ላድርግ? ኬት ልጀምር? ከማን ጋር ልጀምር? " ብለህ እራስህን ጠይቅ። ብልሆች በእራሳቸው መልስ ያላገኙለትን ጥያቄ የሚያምኑተንና የሚረዳቸውን ሰው ይጠይቃሉ። በአጋጣሚም ሆነ ሁን ብለህ የተገኘህበተን ስፍራ ማሻሻል፣ ማደስ፣ መቀየር ከፈለክ በሚገባ ትችላለህ። ሁሌም በችግር፣ ሁሌም ምቾት በማጣት፣ ዘወትር በምሬ፣ ዘወትር በለቅሶ እንድኖር የፈረደብህ አካል የለም። ለውጥ የሚባል ስጦታ ላንተም ህይወት ተሰቷ፣ ባንተም እጣፋንታ፣ ባንተም ኪስ ውስጥ ይገኛል። አዎ! የምታስበውን ለውጥ ለማምጣት ተቸግረሃል? ህይወት ዳገት እንደመውጣት ከብዳሃለች? ወኔህ ክዶሃል? ጉልበትህ ተብረክርኮብሃል? ከጥያቄዎቹ ጀርባ "ለምን?" ብለህ ዳግም እራስህን ጠይቅ። ከምክንያቶቹ ጀርባ የሚገለጥልህ ምክንያት፣ ማድረግ የሚገባህ ተግባር ይኖራል። ማድረግ የሚገባህን ባታውቅ አምላክህን ተማፀነው፣ "ምን ላድርግ?" በለው፤ ሰዎችን ጠይቅ፣ መርምር፣ ከልምዳቸው ተካፈል፣ እግራቸው ስር ወድቀህ ተማር። አንተ ያላሰብክበት ችግርህ፣ አንተ ችላ ያልከው ሸክምህ ያላንተ ፍቃድ በማንም የሚፈታ፣ በማንም የሚቀረፍ፣ በማንም የሚወርድ አይደለም። ከማትወደው የህይወት ዘይቤ ለመላቀቅ እራስህን አሳምን፣ ያለህበትን ሁኔታ በሙሉ ልብህ ተቀበል፣ ማድረግ ስለማትችለው ሳይሆን ማድረግ፣ መቀየር ስለመትችለው ብቻ ማሰብ ጀምር። የትኛውንም ያንተን ሸክም የመሸከሙ ሃላፊነት ያንተ ነው፤ ሲከብድህም የማውረድ፣ ፋታ የመውሰድ መብቱ አለህ። በፋታህ ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለብህ ደጋግመህ አስብ፤ ከብዶኛል እያልክ የሚቀልህ ነገር እንደሌለ አስታውስ። ከባድ ቢሆንም ትችለዋለህ፣ ታደርገዋለህ፣ እንደቀላሉ ታልፈዋለህ፤ ትሻገረዋለህ። በርታ! ተበራታ! ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
1 86810Loading...
07
✅ ስሜታችሁን ተቆጣጠሩ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/eYFQfciJH-o?si=bAz3-EAq29VyndQD
1 7322Loading...
08
✝ ሕይወትን የሰራውን ከበደለኞች ጋር ሰቀሉት! ✝ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት በሰላም አደረሳችሁ! ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
1 9633Loading...
09
ረጅም ተጉዘሃል! ፨፨፨////////፨፨፨ ዛሬ ያለህበትና የጉዞህ መነሻ መሃል በጣም ሰፊ ርቀት አለ። ከዓመታት በፊት የህይወት አቅጣጫህ ሙሉ በሙሉ ከዛሬው የህይወት መንገድህ የተለየ ነበር። ማደግና መቀየርህ ያንተ ሁነኛ መንገድ ቢሆንም ለውጥህ ግን የዛሬ ስፍራህ እንደሚያደርስህ እርግጠኛ አልነበርክም። ተስፋ መቁረጥ ትችል ነበር፣ በእንቅፋቶችህ መሰናከል ትችል ነበር፣ በሰዎች ትቺትና ዘለፋ ማቋረጥ ትችል ነበር፣ ባለብህ የገንዘብና የጊዜ እጥረት ሃሳብህን እንደ ሃሳብ ብቻ መተው ትችል ነበር። ነገር ግን የጉዙህ እርዝማኔም ሆነ በየመሃሉ የሚያጋጥምህ መሰናክል እንቅፋት እንዲሆንህ አልፈቀድክምና ዛሬ ያለህበት ቦታ መድረስ ችለሃል። ማንም በምቾት መሃል ተጉዘህ እንደመጣህ ሊያስብ ይቸላል፣ ማንም ነገሮች አልጋ በአልጋ እንደነበሩ ሊያስብ ይችላል፣ ማንም ሁሉ ተመቻችቶልህ፣ ሁሉ ተዘጋጅቶልህ የመጣህ ሊመስለው ይችላል። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። ሰው የማያውቀው ብዙ መሰናክሎችን አልፈሃል፣ ለሰው ብትነግረውም የማይረዳህን የግል ጉዳይ ተወጥተሃል፣ ከዚህም በላይ አንተም ሆንክ ብዙ ሰው የሚያውቀው የግል ፈተና ነበረብህ ነገር ግን አልፈሀው መጥተሃል። ይሔንን ሁሉ ያደረከውም እራስህን በተግባር ስለምትወደው ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ረጅም ተጉዘሃል! ብዙ መጥተሃል፣ ብዙ ወርደሃል፣ ለዛሬው መዳረሻህ ብዙ ጥረሃል፣ ብዙ ትተሃል፣ ከብዙ ሰው ተራርቀሃል። የከፈልከው ዋጋ አለ፣ ያወጣሀው ወጪ አለ፣ የተወጣሀው ከባድ ሃላፊነት አለ፣ የተሻገርከው ብዙ መሰናክል አለ። ጥረትህ እስከምን እንደነበረ አንተ ታውቃለህ፣ ምንያህል እንደታገልክ አንተ ታውቃለህ፣ ምንያህል መሱዋዕት እንደከፈልክ ካንተ የተሰወረ አይደለም። ፍረሃት ቀላል ስሜት አይደለም፣ ጭንቀት፣ ተስፋ ማድረግ፣ ትዕግሥት፣ ፅናት፣ ወጥነት፣ ዲሲፕሊን፣ እራስን መግዛት፣ ለአላማ መፋለም እያንዳንዳቸው ቀላል ነገሮች አይደሉም። ከባድ ስለሆኑ ብቻ ሌሎች ሰዎች እንኳን ሊካፈሉህ አይችሉም፣ ለወዳጆችህ ማካፈል አትችልም፣ የቅርብ ሰዎችህ ሊያግዙህ ቢፈልጉ እንኳን ማድረግ አይችሉም። እያንዳንዶቹ የግል ስሜቶች ያንተ የግል የቤት ስራዎችህ ናቸው፤ የምትጋፈጣቸው አንተ እራስህ ብቻ ነህ። ሞክረህ ሞክረህ፣ ተጉዘህ ተጉዘህ፣ መጥተህ መጥተህ ማቆም ትችል ነበር ነገር ግን አላቆምክምና ዛሬ ቀና ብለህ ለመራመድ በቅተሃል፣ ዛሬ ብዙዎች የሚመኙትን የሰውነት አቋም መገንባት ጀምረሃል፣ ዛሬ ብዙዎች ሊወዳጁት የሚፈልጉት ብርቱ ሰው ሆነሃል። ክፍያህ ምንያህል እንደጣርክ አመልካች ነው፤ የመጨረሻው መዳረሻህ የተወጣሀውን ሃላፊነት የሚያሳይ ነው። አዎ! ቆራጥ ብቻ አልነበርክም የተግባር ሰውም ነበርክ፣ ታጋሽ ብቻ አልነበርክ የትዕግስትህን ምክንያትም ታውቅ ነበር፣ አዋቂ ብቻ አልነበርክም ይልቅ ጥበብንም ተላብሰሃል። ፅናትህ ድንቅ ነበር፣ ተነሳሽነትህ ያስገርማል፣ ውስጣዊ ፍላጎትህ ግሩም ድንቅ ነበር። እራስህን መሆንህ ከምንም በላይ ጠቅሞሃል፣ የተግባር ሰው መሆንህ ማንነትህን ቀይሮታል፣ ውስጣዊ አቅምህን በሚገባ መረዳትህ ፅኑ አድርጎሃል፣ ለውጥን አለመፍራትህ፣ ላመንክበት አላማ እራስህን መስጠትህ ከፍታህን ጨምሮታል፣ ለቁጪት እድል አለመስጠትህ ከምታስበው በላይ ብርቱና መንፈሰ ጠንካራ አድርጎሃል። ትናንትህን አስታውስ፣ ጅማሬህን ወደኋላ ተመልከት፣ መነሻህን አስተውል። የዛሬው ስኬትህ ትልቁ ቁልፍ ከምንም በላይ መነሻህ እንደሆነ እወቅ። "ባልጀምር ምን ይፈጠር ነበር?" ብለህ ጠይቅ። በእርግጠኝነት የዛሬው ህይወትህ ምኞት ብቻ ይሆን ነበር። የመጀመርን ዋጋ በልበሙሉነት መናገር የሚችለው እርሱ ጀምሮ ሳያቋርጥ ታግሎ፣ ዋጋ ከፍሎ፣ ጥሮ ግሮ የተመኘውን ህይወት መኖር የጀመረው ብርቱ ሰው ነው። ሃላፊነትህን ስለተወጣህ ዛሬህን አሸንፈሃልና በየቀኑ መወጣት የሚኖርብህን ሃላፊነት ተወጣ፣ ለወሬ ቦታ አትስጥ፣ ስራህን ቀጥል፣ ለሌሎች ምኞት የሆነውን ህይወትም መኖርህን ቀጥል። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
1 97211Loading...
10
Media files
1 6010Loading...
11
ዛሬም ሰላም መሆን ይቻላል! ፨፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨፨ ዛሬም ሰላምን ማውረድ፣ በሰላም መቆየት፣ በሰላም መነጋገር ይቻላል። ያለፉት መልካም የአብሮነት ጊዜያት ቢያበቁም ዛሬ በሰላማዊና ጥሩ ሁኔታ ግንኙነትን ማስኬድ ይቻላል። በተበደልኩ ስሜት ለበዛ ጥላቻ መሰናዳት አያስፈልግም፣ የማይረባ እልህ መገባት አያዋጣም። መለያየቱ የተሻለ ምርጫ እስከሆነ ድረስ ያለፉትን አስደሳች ጊዜያት በመዘንጋት ክፋትን ብቻ መቁጠር፣ በአሉታዊ መንገድ ብቻ መፈረጅ ጤነኛ አመለካከት አይደለም። መሆን ስላለበት ሆኖልና ያለፈ ግንኙነትን እንከን ብቻ መፈለግ ዋጋ የለውም። አዎ! ጀግኒት..! ምንም ቢሆን የሆነ ጊዜ የደስታሽ ምክንያት እርሱ ነበር፤ ሲንከባከብሽ፣ ሲያዝንልሽ የነበረው ሰው እርሱ ነው። ሁኔታዎች የግንኙነቱን ቀጣይነት ባለመፍቀዳቸው ማብቃቱ እንዳለ ሆኖ፣ ልዩነቱም በስምምነትና በፍቅር መሆን ይችላል። ከዛም ቦሃላ ሰላማዊ ግንኙነት መፍጠር፣ ከተበዳይነት ስሜት መውጣትና የተረጋጋ ሰላማዊ ግንኙነት መፍጠሩ ለሁለቱም አካል እጅግ ተመራጭ አካሔድ ነው። አዎ! በውስጥህ ቂምን አዝለህ፣ ለበቀል እየተንደረደርክ መቼም የተረጋጋ ህይወት ሊኖርህ አይችልም። በዳይ ሆንክ ተበዳይ፣ ጎጂም ሆንክ ተጎጂ ከፀፀት የምትድነው፣ ወደፊት የምታስበው፣ የተሻለ የምታደርገው፣ ጥሩ ተማሪ የምትሆነው በይቀርባይነት ስትታነፅ፣ በደልን ስትተውና ቂምን ስትረሳ ብቻ ነው። አብራቹ በነበራቹ ሰዓት የሚደረግልህን ነገር ካልጠበክ ስላም የማትሆንበትና ነፃ የማትሆንበት ምክንያት የለም። ሰው ተጎዳድቶ በይቅርታ ይታረቃል፤ ምንም ታሪክ አብሮ ያላሳለፈ ሰው በሰዓታት ግጪት ቢጣላ አንድ የሚያደርገውን፣ የሚያስማማውን ነገር ላያገኝ ይችላል። ለረጅም ጊዜ አብሮ የቆየ፣ ብዙ ነገር አብሮ ያሳለፈ ሰው ግን ቢያንስ አንድ የሚያስማማውና የሚያስታርቀው ነገር አያጣም። ዳግም መስማማት በምትችለው ቁርሾ ሰላምህን አትጣ። ዛሬም ሰላም መሆን ይቻላልና ልዩነትን በፀጋ፣ ጉዳትንም በይቅርታ ማለፉን ለእራስህ ብለህ እወቅበት። ማንም ሁን ብሎ ቢበድለህ ከበዳይነት ነፃ እስከሆንክ ድረስ እራስህን አረጋጋ፣ ህሊናህን ነፃ አውጣ፣ ተጠያቂነትን ከእራስህ ላይ አውርድ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 02621Loading...
12
✅ ወዳጅ ምረጡ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/Dr4tw5ATc6w?si=3RQWlM28o8WijS-N
1 9051Loading...
13
RESPECT YOURSELF! ፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨ No one will come and listen to your inner speech, no one cares about your private speech. Self-respect is simply trusting yourself. Obviously it's not easy. Thoughts that seem real, that can really make a real difference, may come to you again and again, perhaps painful events from the past may come to you in the form of memories. If you don't know what to do with these thoughts, your self-esteem and self-worth are at risk. If you don't start respecting yourself in practice, if you can't trust your word in work, if you can't spend your long time only with yourself, the world of life will gradually lose your identity, strip your dignity, and make you a mediocre person or a person who has descended from a mediocre person. Yes! My hero..! RESPECT YOURSELF! Do you have faith that will carry you through anything, how far will your faith push you? What does it lead you to? How much confidence do you have in yourself? How scared are you of the enormity of your thoughts, the complexity of your inner voice? Remember that your main struggle is not to change the world, but to change yourself, your own thinking and your life. Respect is something you earn, obedience is something you pay for, not a gift that someone gives you out of pity. Nothing can change in your life unless you change the way you think about yourself. A person can run away from his external enemy, but he can never run away from his own self. Either he listens to himself, understands his needs and increases his dignity, or he runs away from himself, despises his thoughts, suffers from his history, and diminishes his dignity and insults his identity. It is always the owner's choice. Yes! The journey to self-respect is a lonely journey. We may not even have anyone watching us, let alone traveling with us. We know what we know about ourselves, we understand our situation, we understand our potential, and it is clear where our efforts will lead us. Make sure you understand yourself as much as you need to understand. Always be a better person and know that you are expected to do better. If you have to separate from others to find yourself, get out of the chaos of the world, get away from the environment that confuses you, set yourself free, spend long quiet moments with yourself. Don't lose your self-respect in any way. Remember that negative feelings and events such as failure, brokenness, fear, inferiority are mainly caused by the place and respect you give to yourself. Until you can know yourself well and feel that you are enough for yourself, know that your main problem is your relationship with yourself and with God. (Epha A.) Mental Counsel for better tomorrow! 🦋 🔺🔻Thank You for Being Our YouTube Family! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIzv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 @MentalCounsel 😊💪‌‌
2 14110Loading...
14
ከነድካምህ ትጠቅማለህ! ፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨ ሰው ከነድካሙ፣ ሰው ከነህመሙ፣ ሰው ከነጉድለቱ ከነክፈተቱ ይጠቅማል። ቢወድቀም ይነሳል፣ ቢጠፋም ይመለሳል፣ ተስፋን ቢያጣ፣ መንገድ ቢስት፣ አዙሪት ውስጥ ቢገባም ዳግም ተስፋን ያገኛል፣ መልሶ ተስፋን ይዘራል፣ ደግም ትክክለኛውን መንገድ ያገኛል። ይሔን ብርታቱን ያገኘው ከራሱ ሳይሆን ከህያው አምላኩ ነው፣ ይሔ ፀጋ እንዲሁ የተሰጠውም አይደለም። ወኔው ታይቶ፣ ፍላጎቱ ተለክቶና ተነሳሽነቱ ተመዝኖ ነው። ተስፋ ቆርጦ ደግም ተስፋን የሚሰንቅ ሰው ቀላል ሰው አይደለም፣ ከጠፋበት ስፍራ የሚመለስ ሰው ማንም አይደለም፣ የህይወቱን ፈተና በፅናት የሚጋፈጥ ሰው ለእራሱ ቦታ የማይሰጥ ሰው አይደለም። የሰው ልጅ ምንም ከማግኘቱና ምንም ከማጣቱ በፊት አንድም በእግዚአብሔር አምላኩ ይመዘናል፣ ሌላም በአምሳያው የሰው ልጅ ይገመገማል። አባት ልጁን ሲያምንበት ሃላፊነት ይሰጠዋል፣ እናት በልጇ ስትተማመን እንደማያሳፍራት ከልብ ታምንበታለች። ሰማያዊው ህያው አባት በልጁ ላይ ያለው እምነት ግን ከዚህ በላይ ነው። ምናልባትም ልክ እንደ አብረሃም አባታችን ልጁ እስከ የእኔ የሚለውን ልጁን እንኳን ለመሰዋት የሚያበቃው እምነትን ይሰጠዋል። ፈጣሪ የፍቃድ አምላክ ነውና ማንም ልቡን ቢከፍትለት ያራራዋል፣ ማንም ልቡን ቢያደነድነውም ፍላጎቱን ያከብርለታል። አዎ! ጀግናዬ..! ከነድካምህ ትጠቅማለህ፣ ከነህመምና ጉድለትህ ዋጋ አለህ። ዋነኛው ሚዛንህ ያለህ ወይም ያጣሀው ነገር ሳይሆን ሰውነትህ ነው። ማንም ሰው እርሱ ካለበት ደረጃ አንፃር የበታቹን የመናቅና የመጠየፍ መብት የለውም። ብታጣ ሰርተህ ታገኛለህ፣ ብታገኝም ያገኘሀውን መቼ እንደምታጣ አታውቅምና በማጣትም ሆነ በማግኘት መኮፈስም ሆነ አንገትን መድፋት አያስፈልግህም። "እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ" ብሎ የመቀበልን ብርታት እስካለህ ድረስ በህይወትህ የማይመጣልህ በጎ ነገር አይኖርም። የሰው ልጅ የጥንካሬው ምንጭ ከሆኑት ውስጥ መቀበልን የመሰለ ፀጋ ከቶ የለም። ብርታቱ እውነታውን የመቀበል አቅሙ ውስጥ ነው፣ ጥንካሬው ታሪኩን መቀበሉ ውስጥ ነው፣ ተስፋው፣ ለውጡ፣ እድገቱ ሁሉ አሁን ያለበትን ተቀብሎ የወደፊቱን መቀየር እንደሚችል ማመኑ ነው። አንተ ለእራስህ ጥሩ ቦታ እስከሰጠህና እራስህን እስከተቀበልክ ድረስ ድክመት እያለብህም ሆነ ስህተት ሰረተህ ሰው ይቀበልሃል፣ ጥሩ ቦታም ይሰጥሃል። በችግር ውስጥ ያላለፈ፣ ስቃይ ያልደቆሰው፣ ፈተና ያልተፈራረቀበት፣ በማጣትና በማግኘት መንገድ ውስጥ ያላለፈ ሰው የለም። አዎ! እውነታውን መቀበል ባትፈልግም እውነታው ግን ሰውነትህ በራሱ የሆነ ደረጃ ላይ ደካማና አቅመቢስ እንደሚያደርግህ ነው። ነገር ግን የተሰጠህ መንፈሳዊ ፀጋ ከድካምህ በላይ እንድትኖርና ዋጋህን እንድትጨምር ያደርግሃል። ማንም ሰው ያለተስፋ ለደቂቃዎች መኖር አይችልም። ከሀገሩ ወጥቶ ለረጅም ሰዓት የሚሰራው ሰው አንድ ቀን ወደ ሀገሩ ተመልሶ የእራሱንም ሆነ የቤተሰቦቹን ህይወት የመቀየር ተስፋ ስላለውነው፣ ማንም ሰው ዛሬ አቀርቅሮ ችግሩን ችሎ፣ በሰው መገፋቱን፣ ጫናውንና በደሉን ተቋቁሞ አቀርቅሮ መስራቱ ነገ ቀን ይወጣልኛል፣ ነገ ቀና እላለው የሚል ተስፋ ስላለው ነው። ተስፋ በተስፋ እንጂ በምንም ሊተካ አይችልም። ይህ መተኪያ የሌለው ስጦታ ደግሞ እግዚአብሔር አምላክ ነው። ከሰው፣ ካፈራው ንብረትና ከገነባው ዝና በላይ ባጣም ባገኘም፣ በወደቀም በተነሳም፣ በተገፋም በተወደደም ሰዓት ፈጣሪውን ተስፋ የሚያደርግ ሰው መቼም ወድቆ አይወድቅም፣ እንዴትም ባዶ እጁን ሊመለስ አይችልም። "ደካማ ነኝ" ብለህ የበታችነት አይሰማህ፣ "ሃጥዕ ነኝ፣ ጥፋቴ በዝቷል፣ ፈጣሪዬን አሳዝኜዋለሁ" ብለህ ሸሽተህ የማታመልጠውን አምላክህን አትሽሽ። ምንም ብትሆን በሰውነትህ ብቻ ለእራስህ፣ ለሰውና ለፈጣሪህ እንደምታስፈልግ እመን። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 31424Loading...
15
Media files
1 8740Loading...
16
የእራስሽ እቅድ አለሽ! ፨፨፨፨//////////፨፨፨፨ ጫናዎች ሲበረቱ፣ ከየአቅጣጫው ሲያይሉ የእራስሽ እቅድ እንዳለሽ አስታውሺ። ከዚህም ከዛም ግፊቶች ሲበዙ፣ አቋምሽን ሲያብረከርኩ፣ በውሳኔዎችሽ ጣልቃ ሲገቡ፣ በገዛ ህይወትሽ አዋቂ ለመሆን ሲሞክሩ ቆም ብለሽ እራስሽን ተመልከቺ። " እውን እኔ ለእራሴ አንሼ ነውን የሰዎች ሃሳብ ማስፈፀሚያ የምሆነው " ብለሽ ጠይቂ ። ምንምእንኳን የታቀደልሽ ጥሩ ቢሆንም፣ የታሰበልሽ መልካም ቢሆንም አንቺ ለእራስሽ ካቀድሽው ግን ሊበልጥ አይችልም። እራስሽን የምትውቂው አንቺ፣ የምትወጂውን የምትጠይውን የምታውቂው አንቺ። በእራስሽ እንደማትጨከኚ ግልፅ ነውና አንቺ ለእራስሽ ከምታስቢው፣ ከምታዝኚው በላይ የሚያስብልሽና የሚያዝንልሽ እንደማይኖር አስተውዪ። አዎ! ጀግኒት..! የእራስሽ እቅድ አለሽ። ጓደኛሽ ስላገባች አታገቢም፣ እኩያሽ ስራ ስለቀየረች አትቀይሪም፣ ወዳጅሽ ፍቅር ስለጀመረች አትጀምሪም። ለሁሉም ነገር ብቁና ዝግጁ ስትሆኚ የመጀመር ፅኑ አቋም አለሽ፤ ፍላጎትሽን ጠንቅቀሽ ታውቂያለሽ፤ የመረጥሽው እንጂ የተመረጠልሽ እንደማይበጅሽ ታውቂያለሽ። ማንም ቢሆን እንድትመስይው ይፈልጋል፤ ብቻውን ችግሮቹን መጋፈጥ አይፈልግም፤ ያየውን እንድታዪና እንዳትፈርጂበት ይፈልጋል። በእራሱ ህይወት የከበደውን ባንቺ ህይወት አቅልሎ እንድታደርጊው ይመክርሻል። አዎ! የአቋምሽ ፈተና፣ የእቅድሽ ፅናት መታወቅ የሚጀምረው ውጫዊ ጫናዎች ሲበረቱና አውቅልሻለሁ ባዮች ሲበዙ ነው። ምክረ ሃሳቦችን እየለየሽ በቀናነት ተቀበይ፣ ትዕዛዝ ሲሆን ግን ለምን፣ እንዴት ማለት ጀምሪ። የአንዱን ሃሳብ ብትፈፅሚ ሌላኛው ማውራቱ አይቀርም፤ የአንደኛውን ምክር ብትሰሚ ሌላኛውም የራሱን ይቀጥላል። የእራስሽን እቅዶች አስታውሺ፣ ደጋግመሽ መርምሪያቸው፣ መጨረስ ያለብሽን ሳትጨርሺ፣ መድረስ ያለብሽ ቦታ ሳትደርሽ የማይሆን ውሳኔ ከመወሰን ተቆጠቢ። ዋጋሽን በእቅድሽ ውስጥ፣ ፍላጎትሽንም በተግባርሽ ውስጥ ተመልከቺው። አዎ! ጀግናዬ..! " አለማቀድ ፣ ለውድቀት እንደማቀድ ነው " እንደሚባለው ሁሉ ሳታቅድ ስትቀር የሚማርክህ ሃሳብ ብዛቱ፣ የሚገዛህ ትዕዛዝ ማየሉ የማይቀር ጉዳይ ነው። በጫና ውስጥ የተወሰኑ ውሳኔዎች የማይመለከቱህ ጭንቀት ውስጥ ሲከቱህ ትመለከታለህ፤ የብዙ ሃሳቦች ተቀባይ መሆን ከየትኛውም ሳትሆን ያስቀርሃል፤ አቋም አልባ ጉዞ መቋጫ የለውም። መስማት ያለብህን ስማ የተባልከው ሁሉ ግን እውነት እንዳልሆነ ተገንዘብ። ወሳኝ የተባሉ የህይወት መርሆችህን ለይተህ አስቀምጥ፤ የሚረብሹህን ሃሳቦች እየጣልክ ጠቃሚዎቹን እየተቀበልክ በእራስህ መንገድ መኖርህን ቀጥል። እቅድህ የሚተገበር፣ ሃሳብህም በተጨባጭ የሚኖር ይሁን። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 33229Loading...
17
✅ ለራሳችሁ ሁኑ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/Sm46inI9_Yk
2 1481Loading...
18
መከራ እውነተኛ የሕይወት ፈተና ነው። /ከዴቪድ ጎጊንስ አንደበት/ በእያንዳንዱ እርምጃህ የሚገጥምህ ውጣውረድ የመኖርህ ማረጋገጫ ነው። ያለፈተና ህይወት የለም፤ ያለድካም መኖር አይቻልም። ተቀምጠህ እንኳን በሃሳብ ትደክማለህ፣ ትፈተናለህ ታወጣለህ፣ ታወርዳለህ፣ ትጨነቃለህ። ይህም ሌላኛው ከመራመድ፣ ከመብላት፣ ከመጠጣት ውጪ የመኖርህ ማሳያ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! በህይወት መኖርህ ብቻ ለህይወት ፈተና ይዳርግሃል፤ እየሮጡ አይድከመኝ አይባልም፤ እየተራመዱ እንቅፋት አይምታኝ ማለት አይቻልም። ሁሌም በምቾት ልትኖር አትችልም፤ ዘወትር በመደላደል የተሞላ መከራ የሌለበት ያልተፈተነ ህይወት አይገኝም። ችግሮችህን እየቀረፍክ፣ እየረሳሀቸው ትጓዛለህ፤ ደግሞም ለሌላ ፈተና ትዘጋጃለህ፤ ጠንክረህ ትቀርባለህ፤ የህይወትን ውጣውረድ ትጋፈጣለህ፤ እያለፍከው ጠንካራውን ማንነት ትገነባለህ። አዎ! ህይወት ልትቀልህና ልታስደስትህ የምትችለው አንተ ባቀለልካት፣ ልትደሰትባት ዝግጁ በሆንከው ልክና ስለፈተናዎቿ መጨነቁን አቁመመህ ፊትለፊት ተጋፍጠህ ማሸንፍና ማለፍ ስትችል ብቻ ነው። መከራን ተጋፈጥ፤ ፈተናህን እለፍ፤ ህይወትን አሸንፍ። ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻 SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ! https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 26511Loading...
19
✅ ልካችሁን አስቀምጡ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/tA-MSFnveG4?si=4a0xAre4kdQA7sR7
2 5162Loading...
20
ማንም አያዝንላችሁም! ፨፨፨፨////////////፨፨፨፨ ማንም ሁኑ የምትኖሩት የእራሳችሁን ህይወት ነው፤ ምንም አግኙ የእናንተን ነገር በዋናነት የምትጠቀሙት እናንተው ናቹ። የሚገባችሁ ነገር ዛሬ ካላችሁ ነገር የሚበልጥ እንደሆነ ማረጋገጥ እስካልቻላችሁ ድረስ ህይወት የተለመደውን ነገር ትሰጣችኋለች፣ በተለመደው መንገድ ትመራችኋለች፣ የሚመጥናችሁ ቦታ ታደርሳችኋለች። እርግጥ ነው ህይወት ከባድ ነች። በተለይ ሀዘን ሲደራረብ፣ መኖር ትርጉም ሲያጣ፣ ግፊቶች ሲበዙ፣ ብቸኝነት ሲያጠቃን፣ ውስጣዊ ሰላምና መረጋጋት ሲጠፋ ህይወት ከባድ ነች። ክብደቷ የሚቀንሰውም እያንዳንዱን ጥያቄ በጥልቀት መርምሮ ምላሽ በመስጠት ብቻ ነው። ህይወት ትርጉም ካልሰጣችሁ ትርጉሙን ፈልጉ፣ የተፈጠራችሁለትን አላማ መርምሩ፣ ግብ አስቀምጡ። በብቸኝነት ከተቸገራችሁ፣ ሰዎች ከራቋችሁ በቅድሚያ የእራሳችሁ ወዳጅ መሆን ጀምሩ፣ ለእራሳችሁ ጊዜና ቦታ መስጠት ጀምሩ። ሀዘናችሁን መቋጫ አብጁለት፣ ስንፍናችሁን ወደኋላ በሉት፣ ለውስጣዊ ሰላምና መረጋጋታችሁ ትኩረት ስጡ። ሁሌም ቢሆን ጥረታችሁ ለማሸነፍ ይሁን፣ ሁሌም ቢሆን ሙከራችሁ የተሻለ ስፍራ ለመገኘት ይሁን። አዎ! በሚያሳዝን ሁኔታ ካላችሁበት ከባድ ሁኔታ አንፃር ሰዎች እንዲያዝኑላችሁ፣ ሰዎች ስለእናንተ ተጨንቀው ጊዜ እንዲሰጧችሁ ብትፈልጉም ማንም አያዝንላችሁም። ችግራችሁ የእናንተ ብቻ ነውና ችግራችሁን ለመጋፈጥ የምትወስኑት ውሳኔም የእናንተ ነው። ከእግዚአብሔር ቀጥሎ የሚያስብላችሁ ሰው እራሳችሁ ናችሁ።ሁሌም ቢሆን የሰው ነገር የአንድ ሰሞን ጉዳይ ነው። አንድ ሰሞን ያዝንላችሁ ይሆናል፣ አንድ ሰሞን ሊረዳችሁ ይሞክር ይሆናል፣ አንድ ሰሞን ከጎናችሁ ይቆም ይሆናል ነገር ግን በፍፁም የህይወት ዘመናችሁን በሙሉ ሊያዝንላችሁ፣ ሊደግፋችሁና ከጎናችሁ ሊቆም አይችልም። ምክንያቱም እርሱም እንደእናንተ የሚያዝንለትና የሚደግፈው ይፈልጋልና። የህይወት ዘመን ድጋፋችሁ ፈጣሪያችሁ ብቻ ነው፤ መፅናኛችሁ፣ አሳቢያችሁና ነፃ አውጪያችሁ አምላካችሁ ብቻ ነው። ሰው እንዲያዝንላችሁ አትጠብቁ፣ ሰው ከንፈር እንዲመጥላችሁ አትመኙ። ይልቅ ፈጣሪያችሁ እንዲያስባችሁ ተማፀኑት፣ እግዚአብሔር እንዲመለከታችሁ ጠይቁት። ብትሰበሩ የሚያቀናችሁ፣ ብትወድቁም የሚያነሳችሁ ሃይል አላችሁ ሃይላችሁም ምንጩ የአምላካችሁ መንፈስ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ያንተ ጉዳይ ትናንት የእራስህ ጉዳይ ነበረ፣ ዛሬም ያንተ ጉዳይ ነው፣ ነገም እንዲሁ የእራስህ ጉዳይ ነው። ሸክም ቢኖርብህ ከብደቱን የምታውቀውም ሆነ የማውረድህን ዋጋ የምትረዳው አንተው። የሰው ልጅ ችግርህን እንዳቅሙ ሊካፈልህ ወይም ሊረዳህ ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን የችግርህ መፍትሔ ሙሉ በሙሉ ያለው ባንተ እጅ ነው። "እንዲህ አድርግ፣ እንደዛ አድርግ፣ ይሔንን አቁም፣ ያንን ጀመር" ትባላለህ የተባልከውን ካላደረክ ግን ዛሬም እዛው ትናንት የነበርክበት ስፍራ ትሆናለህ። ያንተ መንቀሳቀስ ጥቅሙ ለእራስህ ነው፣ መቀመጥህም እንዲሁ ጉዳቱ ለእራስህ ነው። በዚህ ሰዓት ካንተና ከፈጣሪህ በቀር ምን እንደሚያስፈልግህ የሚያውቅ ሰው የለም። ተጨንቀህ ይሁን ተረጋግተህ፣ ከፍቶህ ይሁን ነፃ ሆነህ፣ አዝነህ ይሁን ተደስተህ ማንም መረጃው የለውም። ለእራስህ ማድረግ ያለብህን አድርግ፣ በቻልከው ልክ ሰው ባስፈለገህ ሰዓት ለእራስህ ቀድመህ ተገኝ፣ እንዳቅምህ ህመምህን እራስህ አክመው፣ ከሰው በላይ ፈጣሪ እንዲያግዝህ አድርግ፣ እጅህን ለአምላክህ ስጥ። መቆም በሌለብህ ሰዓት አትቁም፣ እግዚአብሔር አምላክህን ተደግፈህ መኖርህን ቀጥል፣ በፈጣሪህ መሪነት ወደፊት መጓዝህን ቀጥል። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 84031Loading...
21
የትኛው ነህ? ፨፨//////፨፨ አንዲት ከአባቷ ጋብር የምትኖር ህፃን ልጅ ነበረች። በህይወቷ ደስተኛ አልነበረችም፣ ከሰዎች ጋር ባላት ግንኙነት ትበሳጫለች፣ ትምህርት ቤት በጓደኞችዋ መቀለጃ ሆናለች፣ ለትምህርቷ ትኩረት ሰጥታ መከታተል አልቻለችም፣ በሰዎች የሚደርስባት ጫና እጅጉን እያሳሰባት መጥቷል። በራሷ መንገድ ነገሮችን ለማስተካከል ብትሞክርም አልቻለችም። በስተመጨረሻም ከአቅሟ በላይ ሲሆን ያለችበትን ሁኔታ በሃዘንና ተስፋ በመቁረጥ ስሜት ሁኔታውን መቋቋም እንዳልቻለች ለአባቷ ትነግረዋለች። አባትም ካረጋጋት ቦሃላ በምሳሌ ሊያስረዳት ስለፈለገ አእጇን ይዞ ወደ ኩሽና ይዟት ይገባል። በመቀጠልም ድንች መቀቀል ይጀምራል፣ ድንቹ ከበሰለ ቦሃላም እንደገና እንቁላል ይቀቅላል፣ ከእንቁላሉም ቦሃላ ቡና አፍልቶ ያሳያታል። ህፃንዋም እነዚህ የሚያደርጋቸው ነገሮች ሊገቧት አልቻሉም። ጥያቄውን በተሳሳተ መንገድ እንደተረዳ መገመተ ጀመረች። አባት ግን ጥያቄዋን በሚገባ ተረድቷት ነበር። መልሱንም እንዲሁ በደፈናው ከሚነግራት በምሳሌ አድርጎ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትገባም ሁሌም እያስታወሰችው እንድትኖር በማሰብ እራሷን እንደ ድንች፣ እንደ እንቁላልና እንደ የቡና ዱቄት እንድታስብ ይነግራታል። በመቀጠልም ይህን በአፅንዖት ያስረዳታል። "ድንቹ በፈላ ውሃ ከመቀቀሉ በፊት ጠንካራ ነበር ከተቀቀለ ቦሃላ ግን ለስላሳ ሆነ፣ እንቁላሉ ከመቀቀሉ በፊት ፈሳሽ ነበረ ከተቀቀለ ቦሃላ ግን ጠንካራ ሆነ፣ ቡናውም ከመፈላቱ በፊት የተፈጨ የቡና ዱቄት ነበር ከውሃ ጋር ተዋህዶ ከተፈላ ቦሃላ ግን ብዙዎች በፍቅር የሚወዱትንና የሚጠጡትን ቡና ሆነ።" አላት። ንግግሩን ቀጠለ፦ "አሁን ያለሽበትን ሁኔታ እንደፈላው ውሃ ውሰጂው እራስሽን ደግሞ በሶስቱ ደንች፣ እንቁላልና የቡና ቦታ አስቀምጪ። የፈላ ውሃ ውስጥ ከመግባትሽ በፊት እንደ ድንቹ ጠንካራ ነበርሽ? ወይስ እንደ እንቁላሉ ለስላሳ ወይም ፈሳሽ ነበርሽ? ወይስ ደግሞ እንዲሁ በእሳት ላይ ተቆልቶ ተፈጭቶና በስተመጨረሻ ለመጠጥነት ለመቅረብ ከውሃ ጋር እንደተፈላው የቡና ዱቄት ነሽ? የትኛው አንቺን የሚወክል ይመስልሻል? ብሎ ድጋሜ ጠይቋት ግራመጋባቷን ስላወቀ ይበልጥ ማብራራቱን ቀጠለ። እንዲም አላት "ሁሉም ነገሮች በተፈጥሯቸው ምክንያት ለገቡበት የፈላ ውሃ ተገቢውን ምላሽ ሰጥተዋል። እኛ የሰው ልጆች ግን ምንም ከባድ ሁኔታ ውስጥ ብንገባ ከዛ ሁኔታ ስንወጣ የምንሆነውን ማንነት የምንወስነው እኛው እራሳችን ነን። "ጓደኞቼ እያሾፉብኝ ነው፣ ሰዎች የሚሰጡኝ ቦታ ያስጨንቀኛል፣ ትምህርቴ ላይ ማተኮር አልቻልኩም" ብለሽ ልክ እንደ ደንቹ ቀድሞ የነበረሽን ጥንካሬና በራስመተማመን በመተው ልፍስፍስ የመሆኑ ምርጫ ያንቺ ነው፣ እንዲሁም ልክ እንደ እንቁላሉ በዚሁ ምክንያት ይበልጥ ጠንካራ መሆንሽን የማሳየቱ ምርጫ ያንቺ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ልክ ከመቆላት ተነስቶ ለመጠጥነት እስከሚደርሰው ቡና እያንዳንዱን የሚደርስብሽን ጫና በመቋቋም በብዙዎች ዘንድ የምትወደጂና የምትፈለጊ ሰው የመሆን ምርጫ አለሽ።" ብሎ አስረዳት። ልጅቱም አባቷ በዚህ መልክ ካስረዳት ቦሃላ በህይወት የሚገጥማትን የትኛውንም ሁኔታ በተለየ መንገድ መመልከት ጀመረች። አዎ! ጀግናዬ..! አንተስ የትኛው ነህ? ልክ እንደ ድንቹ ለሁኔታዎች እጅ ሰተህ የምትልፈሰፈስ ነህን? ወይስ ልክ እንደ እንቁላሉ ከገጠመህ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ጠንካራና የተሻልክ ሰው ሆነህ የምትወጣ ነህ? ወይስ ደግሞ ልክ እንደ ቡናው ብዙ ፈተናንን ተቋቁመህ በማለፍ ተወዳጅና ተፈላጊ ማንነትን የምትፈጥር ነህ? አሁን ምንም ነገር ሊገጥምህ ይችላል ከገጠመህ ነገር ቦሃላ የምትሆነውን ሰው የምትወስነው ግን አንተ ነህ። ማናችንም በምን ውስጥ እንደምናልፍ አናውቅም፣ ማናችንም ነገ ምን እንደሚገጥመን አናውቅም። ነገር ግን አንድ ነገር በሚገባ ልናውቅ ይገባል "በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ አልፈን የተሻለ ሰው የመሆንም ሆነ በሁኔታው ተሰብረን የመቅረት ምርጫ አለን።" ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ህይወት አልጋ በአልጋ ሆና አታውቅምም ወደፊትም ልትሆን አትችልምና አንተ ከገጠመህ ሁኔታ በላይ እንደሆንክ ለማሳየት ተዘጋጅ። ምንም ቋሚ ነገር በሌለበት ዓለም ቶሎ እጅ ለመስጠት አትንደርደር። ተረጋጋ፣ ደጋግመህ አስብ፣ ሞክር፣ ጥረትህን ቀጥል፣ በከባድ ሁኔታዎች መሃል የተሻለ ማንነትን ለመገንበት ሞክር። ምንም ውስጥ ብትሆን ለውጥና እድገትህን በፍፁም እንዳታቆም። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 04724Loading...
22
Media files
2 4121Loading...
23
18 40 60 መርህ! ፨፨፨//////////፨፨፨ በአስራ ስምንት ዓመትህ ሰዎች ሁሉ ስላንተ የሚያወሩ፣ አንተን ብቻ የሚመለከቱ፣ የሚከታተሉህ፣ የዘወትር ጉዳያቸው አንተ እንደሆንክ ታስባለህ። በዚህም ልክ ከእራስህ በላይ ሰዎች ስለሚሰጡህ ስምና ከእነርሱ ስለምታገኘው ምላሽ በመጨነቅ ጊዜህን ታባክናለህ፤ እራስህን ከማስደሰት በላይ ለሰዎች ደስታና እርካታ ትልቅ ዋጋ ትከፍላለህ፤ ሰው ምን ይለኛል በሚል ሃፍረት ትታሰራለህ፤ ነፃነትህን ለማወጅ ባሰብክ ቁጥር የሰው ምላስ ከፊትህ ተደቅኖ ትመለከታለህ፤ ባጠቃላይ ህይወትህ በሙሉ ለሰዎች በሚከፈል መሱዓትነት ይሞላል። በአርባ ዓመትህ የሰው ነገር ምንም አይመስልህም፤ ምንም ብትባል ግድ አይሰጥህም፤ ስለፈለጉት ቢያወሩብህ፣ ስምህን ቢያጠፉ፣ ስራህን ቢተቹ፣ አንተን ቢነቅፉህ ምርጫቸው እንደሆነ ይገባሃል። በቀደሙት አመታት ሲያስጨንቁህ የነበሩ ጉዳዮች ማስጨነቃቸውን ያቆማሉ፤ ሌላ የተለየ አጀንዳ ውስጥ ትገባለህ። በስልሳ ዓመትህ የሁለቱንም ልዩነት ማመዛዘን ትጀምራለህ፤ ለሰዎች ብለህ ያጣሀው ነገር ካለ በእርሱ ትቆጫለህ፤ ማንም ግድ በማይሰጠው ጉዳይ ስትጨነቅ እንደነበር ታስተውላለህ፤ የሰዎች ስጋትና ፍራቻ ሁሉ የውሸት እንደነበር ይገባሃል። አዎ! ጀግናዬ..! መርሁን አስተውል፤ በሚገባ ተረዳው። ብዙዎች ስላላወቁት ይሸወዳሉ አንተ ግን ካወከው ዘንዳ፣ ከተረዳሀው፣ ከገባህ ለመተግበር ወደኋላ አትበል። ማንም ሰው ግድ ለማይሰጠው ጉዳይ እየፈራህና እየተጨነክ አትኑር። ያዩኛል፣ ይከታተሉኛል፣ ይተቹኛል፣ ምን ይሉኛል ብለህ የምትጨነቅላቸው ሰዎች በሙሉ የእራሳቸው የማያልቅ ጉዳይ አለባቸው። ማንም ያንተ አዲስ ነገር መጀመር፣ በተለየ መንገድ መጓዝ፣ በአዲስ አቋም መታደስ አያሳስበውም። ሁሉም የግሉ ሩጫ ላይ ነው። ምናልባት በአጋጣሚ ሲያይህ የመጣበትን ቃል ሊሰነዝርብህ ይችላል ከዛ ቦሃላ ግን ትዝም አትለውም። እያንዳንዱ ሰው በግል ጡዘት በተጠመደበት ጊዜ አይኖች ሁሉ እኔ ላይ ናቸው ብለህ አትሸወድ። ማንም ስታልፍ ያይህ ይሆናል እንጂ ጉዞህን በሙሉ እየተከታተለ አይኖርም። የእራስህን ኑሮ መኖር ላይ አተኩር፣ ከፈጣሪህና ግድ የሚሰጠሁን ሰዎች እስካላሳዘንክ ድረስ ሌላው ነገር ትርፍ ነው። መጀመሪያ የምትኖረው ለእራስህ እንጂ ለሰው አይደለም። አዎ! ሰበብ አታብዛ ደስታ የሚሰጥህን፣ ያመንክበትን፣ የሚጠቅምህን ነገር በጊዜ አድርግ። ህይወትህን በፍረሃት አትሰራት፤ መኖርን በማይሆን ገደብ አትከልላት። በትንሹም ቢሆን ጥረትህን ጀምር፤ ደስታህን ወደ መፍጠር ተሸጋገር፤ የእራስህን አለም አበጃጅ፤ ፈጣሪህ ያይሃል፤ አምላክ ያውቅልሃል፤ ይረዳሃል፤ ይቀድምልሃል። ስለመጪው ጊዜ ቁጪትና ብትስጪት የምትጨነቅበት ምክንያት የለህም። በአጋጣሚ ያገኘህና የተመለከተህ ባላወቀህ መጠን ሊናገር ይችላል፤ አስቦና ፈልጎ የሚመለከትህ ግን በእርግጥም ሊደግፍህ እንደሚመጣ አትጠራጠር። ልዩነት መፍጠሩን አሁኑኑ ጀምር፤ በልብህ የያዝከውን፣ በአዕምሮህ ያነገብከውን ሃሳባዊ አለም ከምድራዊው ተጨባጭ አለም ጋር ቀላቅለው። የመጣው ይምጣ፤ የሆነው ይሁን፤ የማይቀር ነገር እንደሆነ የመጣውን ተቀበል። በእራስህ ተመማመን፤ ለእራስህ ብለህ ድፈር፤ ጠንክር፤ ለእራስህ ብለህ ህይወትህን በሙላት ኑር። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 16739Loading...
24
✅ ወስናችሁ አቁሙት! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/tvuAKCg-Nqk?si=VNiiYlg3uzaI8aVc
2 6635Loading...
25
ተሰጦና ክህሎት! ፨፨፨፨////፨፨፨፨ "ተሰጦ ከአምላክህ የሚሰጥህ ስጦታ ነው፣ አንተም እርሱን ተጠቅመህ የምትሰራው ስራ ለአምላክህ መልሰህ የምትሰጠው ስጦታ ነው።"                                -Leo Buscaglia ተሰጦህ (talent) ምንም ሊሆን ይችላል ጠንክረህ ካልሰራህበት ግን ምንም ነው። ዓለም በብዙ ባለተሰጦዎች ተሞልታለች ነገር ግን እነዚህ ባለተሰጦዎች በሙሉ ስኬታሞች አይደሉም። ማንም ሰው ስኬትን ይጎናፀፍ ዘንድ ተሰጦውን በማያቋርጥ ጥረት መደገፍ አለበት ወይም አንድ በፅናት የሚሰራበት ክህሎት (skill) ያስፈልገዋል። ጠንክሮ የመስራትን ዋጋ ማሳነስ ስትጀምር ውድቀትህ ይጀምራል። የህይወትህን ዋጋ በመንፈሳዊነት፣ በተሰጦና በክህሎት መሃል ታገኘዋለህ። መንፈሳዊነት እንደ ክህሎትና ተሰጦ ጠንክሮ በመስራትም ሆነ ሌትከቀን በመልፋት የሚዳብር ነገር አይደለም። መንፈሳዊነት ለፈጣሪ እጅ መስጠትና ለእርሱ መገዛት ነው። የተቀሩት ሁለቱ የህይወት ምሰሶዎች ግን ይለያሉ። ተሰጦ ካልተሰራበት ይባክናል፣ ክህሎት ግን ገና ከጅምሩ ሊመጣ የሚችለው በጥረትና በማያቋርጥ ትጋት ነውና መቼም ውጤት አልባ ሊሆን አይችልም። በተሰማራህበት የስራ ዘርፍ ፈፅሞ ጠንክሮ የመስራትን ዋጋ አቅልለህ እንዳትመለከት። በፅናት የመፋለምን ቦታ እራሱ በፅናት መፋለም ካልሆነ በቀር ምንም ሊተካው እንደማይችል እወቅ። አዎ! ጀግናዬ..! ተሰጦና ክህሎት ጉዟቸው ለየቅል ነው። ተሰጦህን ብቻ ተማምነህ ህይወትን ልታሸንፍ አትችልም፤ ክህሎትህን በማዳበር ግን የምትመኘውን ህይወት መኖር ትችላለህ። ዓለም የምትመራው በባለተሰጦዎች ሳይሆን ክህሎታቸውን አዳብረው የዘርፉን ከፍታ በተቆናጠጡ ሰዎች ነው። እግር ኳስ ተጫዋች ብትሆን ስመጥርና ተመራጭ ለመሆን ልክ እንደ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጠንክሮ መስራት አማራጭ የሌለው ብቸኛ አማራጭህ ነው፣ ልክ እንደ ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ ብዙ የዓለም ሪኮርዶችን በመሰባበር ስመጥር ዓለማቀፍ አትሌት ለመሆን ለረጅም ዓመታት የማያቋርጥ ልምምድና ዲሲፕሊን ግዴታህ ነው። በተሰጦህ ብቻ መደበኛ ህይወት ልትኖር ትችላለህ፣ ባዳበርከው ክህሎት ግን ጥራት ያለው ከራስ በላይ ለሰው የሚፈስ ህይወት መኖር ትችላለህ። ማንም ህልም የሌለው ሰው የለም፣ ማንም ምኞት የሌለው ሰው የለም። ህልምና ምኞቱን ለማሳካትም ደግሞ ክህሎትና ገንዘብ ያስፈልገዋል። የሚያዳብረው ክህሎት ህልሙን እውን የሚያደርግበትን ገንዘብ በእጅ እንዲያስገባ ያግዘዋል። ጠንክሮ ለሚሰራ ብርቱ ሰው ገንዘብ ማግኘት ከባድ ሊሆን አይችልም፤ ተሰጦውን ተማምኖ ለሚቀመጥ ሰው ግን የሚመኘውን ያህል ገንዘብ ማግኘት በጣም ከባድ ነው። አዎ! መርጠህ ተለማምደህ ካዳበርከው ክህሎትና ከእግዚአብሔር ከተሰጠህ ተሰጦ በየትኛው መተማመን እንዳለብህ በሚገባ እወቅ። በእርግጥ ተሰጦህን ችላ ማለት፣ ከፈጣሪህ በተሰጠህ ነገር አለመተማመን ከፈጣሪ እምነትና ክብር ጋር የሚያገናኘው ነገር ላይኖር ይችላል ነገር ግን እስካወከው ድረስ ከቻልክ በተሰጠህ አንድም ሆነ ሁለትም ሆነ አምስት መክሊት የማትረፍና ለሰጪህ ትርፉን የመመለስ ግዴታ አለብህ። ጥረህ ግረህ ብላ መባሉ አንድም ቅጣት ሌላም ግዴታ ነው። ማንም የሰው ልጅ ሆኖ ያለልፋቱ የሚያገኘው ነገር ሊባረክለት አይችልም። በቀላሉ የምታገኘው የትኛውም ነገር በቀላሉ ሲጠፋ ትመለከታለህ። ረጅም ርቀት ተጉዘህ፣ ብዙ ተምረህበት፣ ብዙ አውቀህበት፣ ለረጅም ጊዜ ጥረህለት ያመጣሀው ነገር በአንድ ሌሊት ቢጠፋ እንኳን እንዴት አድርገህ ድጋሜ ልታገኘው እንደምትችል ጠንቅቀህ ታውቃለህ። በተሰጦህ አትዘናጋ፣ ባለህ አቅም ሁሉ በየጊዜው አሳድገው፣ ስራበት፣ ያለማቋረጥ አዳብረው፣ ከሌላው ሰው በተለየ ትርፍን አግኝበት። ካልሆነ አንድ ክህሎት መርጠህ አዳብር፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ማስተር አድርገው፣ ንገስበት፣ ከሌላው ሰው በተሻለ ተቆጣጠረው፣ እራስህን አስገዛለት፣ ስኬትንም በእርሱ መንገድ እጅህ አስገባው። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 10023Loading...
26
Media files
2 5520Loading...
27

10Loading...
28
ማህበራዊ ስኬት! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ ሲታዩ ደስተኛ መምሰል፣ ለይስሙላ ለባብሶ ደምቆ መውጣት፣ ሰው ፊት እንዲወራልን መጠበቅ፣ ሁሌም ተከብረን፣ ተሞግሰን፣ ተደንቀን መኖርን መመኘትን የማህበራዊ ስኬት ጥማት እንለዋለን። እያንዳንዱ ጉዟችን ለእኛ ሳይሆን ለስማችን ነው፤ ለሚሰጠን ክብርና ዝና ነው፤ በሰው ዘንድ ለምናገኘው ቦታ ነው። ለእራሰህ ያልሆነህ፣ አንተን ያላስደሰትህ፣ ላንተ ያልጠቀመህ ስኬትም ይሁን ከፍታ በሰው ፊት ቢያስከብርህ፣ ከፍ ቢያስደርግህ ለከፋው ውድቀት ከማመቻቸት ውጪ ምንም ጥቅም የለውም። የምትችለው ነገር ብዙ ሆኖ ሳለ ለሰዎች ጭብጨባና አድናቆት ብቻ መልፋትህን አቁም። ዛሬ ብትነሳ ነገ ላለመውደቅህ ምንም ዋስትና እንደሌለህ ተረዳ። ትናንት ያነሳህ፣ ያሞገሰህ፣ የደገፈህ ሰው ዛሬ በተራው ሊጥልህ እንደሚችል አስብ። አዎ! ጀግናዬ..! የማህበራዊ ስኬት ጥማትህን ገታ አድርገው፤ በሰው ለመወደድ፣ ይሁንታን ለማግኘት፣ ዝናን ለማትረፍ ከመሯሯጥ መለስ በል። እራስህን ማስደሰት ሳትችል ደስተኛ ሆኖ መታየት ሸክም እንጂ ምንም ትርፍ አያመጣልህም። የሆንከውን ብትሆን ሰው ቢቀበልህ ባይቀበልህ፣ ቢያጨበጭብልህ ባያጨበጭብልህ፣ ቢደግፍህ ባይደግፍህ ዋናው ቁብ ነገር አንተ የእራስህ ደጋፊ መሆንህ ነው። ለእራሱ የሚወግንን ሰው ማንም ሊያስቆመው አይችልም። ምክንያቱም አብሮት ያለው ሁሉን ማድረግ የሚችለው አምላክ ነውና። ዛሬ አንተ ደክመህ፣ ለፍተህ፣ እራስህን አተህ፣ ተጋግጠህ ያመጣሀውን ዝና ነገ በሌላ ነገር የሚቀይረው በወረት የሚመራ የሰው ልጅ ውስጥ እንዳለህ አስታውስ። ትናንት ሲመረቁ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ሲረገሙ ማየት አዲስ አይደለም። ቦታህን ይዘህ የምትቀጥለው በሰዎች ስሜት ስለተነዳህ ሳይሆን እራስህን ስለሆንክና እራስህን ከማስደሰት ስለተነሳህ ነው። አዎ! ለመታየት፣ ለመደነቅ፣ ለመሞገስ ሳይሆን ዋጋህን ለመጨመር፣ ጥራትህን ለማሳደግ፣ ማንነትህን ለማሳየት ትጋ። ከምንም በላይ እራሱን ማውጣትና ከፍ አድርጎ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችለው እራሱ ሰውዬው ነው። አለም በቅፅበታት ትቀያየራለች፣ የሚቀይራትም የሰው ልጅ ቅፅበታዊ ስሜት ነው። በምክንያት ቢወድህ በምክንያት ሊጠላህ ከሚችል ሰው ጋር እየኖርክ ለእርሱ ደስታና እርካታ፣ ከእርሱ ቅቡልነትን ለማግኘት ብትሰቃይ ዋጋህን ከማሳነስ በቀር የምታተርፈው ነገር አይኖርም። ሁላችንም የተለያየ አቅም አለን። ያ አቅም ሰዎችን Impress ለማድረግ ሳይሆን እራሳችንን በጠለቀ የመሞላት ስሜት ለማነፅ ብንጠቀመው ስሜቱ በእራሱ ውጫዊውን ድባብ ሲቀይረው ለመመልከት ጊዜ አይፈጅብንም። ለመታየት ሳይሆን ብቁ ለመሆን ስራ፤ ለተቀባይነት ሳይሆን ለውስጥ መሻትህ ትጋ፤ ለስምና ዝና ሳይሆን ለእውነተኛው መጠራትህ እራስህን ስጥ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
3 23011Loading...
29
የተረጋጋ ሰው ሁን! ፨፨፨/////////፨፨፨ ከሰው ልጅ ባህሪያት መካከል እንደ ግራማምገስ የሚያስከብር እንደ ተረጋጋ ስብዕናም የሚማርክ ነገር ምን አለ? አስቡት ስማችሁ ሲነሳ ግርማችሁ ሲከተላችሁ፣ ለትንሹም ለትልቁም መደንገጥ ስታቆሙ ሰዎች እናንተን መከተል ሲጀምሩ፣ አስቡት በምንም ሁኔታ ውስጥ የተረጋጋችሁና ለተፈጠረባችሁ ነገር ፈጣን ምላሽ የማትሰጡ እንዲሁም በቀላሉ የማትረበሹ ስትሆኑ ምንያህል ተፅዕኖ መፍጠር እንደምትጀምሩ። መጣል የጀመረው ዝናብ እስኪያባራ ተረጋጉ፣ ንዴታችሁ አስኪበርድ ተረጋጉ፣ የለመናችሁት ነገር እስኪሆንላችሁ ተረጋግታችሁ ጠበቁ፣ ፈልጋችሁ ያጣችሁት ሰው ወደ ህይወታችሁ እስኪመጣ፣ የሚያስፈልጋችሁ ስራ ከፈጣሪ እስኪሰጣችሁ ተረጋጉ። የእናንተ ካልሆነ ስለቸኮላችሁ የምታገኙት ክብርም ሆነ ሽልማት አይኖርም፣ ካልተፈቀደላችሁ አለቀሳችሁም፣ ተነጫነጫችሁም፣ ተናደዳችሁም የእናንተ የሚሆን ነገር የለም። የሀገራችን አባባል እንዲ ይላል፦ "የቸኮለች አፍሳ ለቀመች።" ባትቸኩልና ብትረጋጋ የያዘችውን እህል ተገቢው ስፍራ ሳታደርስ አፍሳ ለመልቀም ባልበቃች ነበር። አዎ! ጀግናዬ..! አትዋከብ የተረጋጋ ሰው ሁን፤ እራስህን አታስጨንቅ ጊዜ የሚፈታቸውን ጉዳዮች ለጊዜ ሰጥ። ስለቸኮልክ ብቻ የምትደርስበትና በፍጥነትህ ምክንያት ብቻ በእጅህ የምታስገባው ነገር የለም። ህይወት የራሷ የህይወት መንገድ፣ የእራሷ የቀን ገደብ አላት። አንተ ስላዘንክ ፈጥኖ የሚደረግልህ አንተም ስለተደሰትክ በፍጥነት ከእጅህ የሚዘጣ ነገር አይኖርም። አንዳንድ ያለመረጋጋቶች የሚፈጠሩት የያዝነውን እንዳናጣ ወይም የሚመጣው እንዳያመልጠን ይሆናል። እውነታው ግን በመርበትበት ያለንን ማቆየት ወይም የሚመጣውን ማግኘት አለመቻላችን ነው። ንዴትና ብስጪታችን የሆነን መጥፎ ነገር እንዳልሆነ ቢያደርገው ጥሩ ነበር፣ ችኮላና ሩጫችንን የዛሬ ዓመት መድረስ ያለብህን ስፍራ ዛሬ ቢያደርሰን መልካም ነበር፣ የማያባራው ፍላጎትና ምኞታችን ብቻ አሁኑ ያሰኘንን ነገር በእጃችን ቢያስገባ ጥሩ ነበር። ነገር ግን የተፈጥሮ አሰራር ከዚህ የተለየ ነው። የምትመኘውን ትልቅ ነገር ለማግኘት መታገስ አለብህ፣ መድረስ የምትፈልገው ስፍራ ለመድረስ ተረጋግተህ ሁሌም ጉዞ ላይ መሆን ይኖርብሃል፣ የስሜት ብለሃትህን ለማሻሻል፣ በአስተሳሰብና በማንነት ልቆ ለመገኘት ለምላሾች መዘግየት፣ እራስን መግዛትና የተጠኑ እርምጃዎችን ማድረግ ይኖርብሃል። አዎ! በህይወት ሽንፈትም አሸናፊነትም አለ፣ በህይወት ደስታም ሀዘንም አለ፣ ማግኘትም ማጣትም አለ፣ ማትረፍም መክሰርም አለ፣ ፍቅርም ጥላቻም አለ። ትልቁ ቁብነገር በእነዚህ ሁሉ ተቃራኒ ሁኔታዎች ውስጥ አቋምን አክብሮ፣ ስሜትን ገዝቶ፣ እራስን ገስፆና ተረጋግቶ ነገሮችን ማሳለፍ መቻል ነው። ጊዜ እንደ ወረጅ ወንዝ ነው። ወራጁ ውሃ በወንዙ ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ቀስበቀስ እያጠራ እንደመምጣቱ ጊዜም እንዲሁ በህይወትህ ያለውን አላስፈላጊ ነገር በሂደት እያስወገደ ይመጣል። ይህም የሚሆነው ስለቸኮልክ ወይም ያዙኝ ልቀቁኝ ስላልክ አይደለም። ለጥያቄዎችህ በሙሉ ፈጣሪ በጊዜ ምላሽ እንዲሰጥህ ስትፈቅድ የሚሆንህና የሚገባህ ነገር በሰዓቱ ይደረግልሃል። መቆጣጠር የምትችለውን የህይወትህን ክፍል ተቆጣጠር፣ ማስተካከል የምትችለውን ጉዳይ አስተካክል፣ ከአቅምህ በላይ የሆነን ጉዳይ በመታገል ጊዜህን አታጥፋ። ተረጋጋ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምላሽ በትዕግስት ጠብቅ፣ የፈጣሪን ትክክለኛ ሰዓት ተጠባበቅ። ከሆነብህ በላይ ለሆነብህ ጉዳይ የምትሰጠው ምላሽ ያንተን ጥበብና ብስለት እንደሚያሳይ እወቅ። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 38359Loading...
30
በሰዎች ሰትናቁ! ፨፨፨///////፨፨፨ ሰው የሰወን ልጅ እንደ ሰውነቱ ያከብር ዘንድ ግዴታ አለበት። ነገር ግን ይህን ግዴታውን በመሻር ክብራችሁን የሚነካና የሚንቃችሁ ከሆነ ለእራሳችሁ ዘብ የምትቆሙት፣ ንቀቱን የምታስታግሱትና ደረጃችሁን የምታሳዩት እራሳችሁ ናችሁ። እየተናቁ መኖር ልብን የሚነካ ህመም አለው። እየተገፉ፣ እንደ አማራጭ እየታዩ፣ ችላ እየተባሉ መኖር ልብ ላይ የሚያሳርፈው ጠባሳ እጅግ ከባድ ነው። ምናልባት አንዳንዶች ንቀትን ተላምደው ይኖሩ ይሆናል፣ ቢገፉም፣ ቢጣሉም ላይሰማቸው ይችል ይሆናል። ነገር ግን በሰዓቱ ባይሆንም ነገሮች በተደራረበባቸውና አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በገቡ ሰዓት ይሔም ጉዳይ ጫና ውስጥ ይከታቸዋል። አትናቁ እንድትናቁም አትፍቀዱ፣ ሰውን አታራክሱ እንተንም ማንም እንዲያራክሳችሁ አትፍቀዱ፣ በሰው ክብር ላይ አትረማመዱ ሰውም ክብራችሁን እንዲነካ አትፍቀዱ። እያዩ እንዳላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ መሆን እየተቻለ የንቀት ባህሪ ካላቸው ሰዎች ጋር ግብ ግብ ውስጥ አትግቡ። ንቀትን ንቆ ማለፍ ጥበብም ብለሃትም ነው። አዎ! አስተውሉ ንቀትን በግብግብ አታሸንፉም፣ ንቀትን በሃይልና በብስጭት አታልፉትም። ስትናቁ አጥብቃችሁ ጥበብን ተማሩ፣ ያለምንም ቅድመሁኔታ መርሳት የተባለን ስጦታችሁን ተጠቀሙ። የሚገባችሁ ቦታ ሲነፈጋችሁ፣ እየሰራችሁ፣ እየጣራችሁ የልፋታችሁን ዋጋ እየተነፈጋችሁ፣ መደነቅ ሲገባችሁ ስትተቹ፣ መሞገስ እያለባችሁ ስትሰደቡ እንደማንኛውም ሰው ስሜታችሁ መጎዳቱ፣ ለምንም ነገር ተነሳሽነት ማጣታችሁና ለጥልና በቀል መዘጋጀታችሁ አይቀርም። ነገር ግን በዚህ ምላሽ ይበልጥ ለጥቃትና ለንቀት እራሳችሁን ብታጋልጡ እንጂ የደረሰባችሁን ጉዳት ልታስቀሩት አትችሉም። የሚወራባችሁን በጥቂቱ ስሙ፣ በቻላችሁት አቅም የሰውን ፊት ለማንበብ ሞክሩ፣ ሁኔታዎች በጥቂቱ መርምሩ፣ ለምላሽና ለሰጣገባ አትቸኩሉ፣ ለጥቂት ጊዜ በዝምታ ቆዩ፣ ታገሱ፣ የጊዜ ገደብ አስቀምጡ። በስተመጨረሻ ግን ለእራሳችሁ ክብር ስትሉ ፊታችሁን አዙሩ፣ ንቀታቸውን ላለመመልከት ወስኑ፣ ከደረጃችሁ ወርዳችሁ የሚያሳንሳችሁን ተመሳሳይ ተግባር ላለመፈፀም ለእራሳችሁ ቃል ግጉ። የእራሳችሁን መስመር አስምሩ፣ እነርሱም ከመስመሩ ውጪ እንደፈለጉ እንዲሆኑ በመተው እርሷቸው። አዎ! ጀግናዬ..! ትልቁ ጥበብ ንቀትን ንቆ ማለፍ ነው። ጉዳይህ በማታውቀው ሳይሆን በምታውቀው ሰው እንኳን ስትናቅ ስለምትሰጠው ምላሽ መጨነቅ አይደለም፣ ጉዳይህ በምርጫና በፍላጎት ስለመገፋትህ ተቀምጦ መቆዘም አይደለም። ዋናው ጉዳይህ በሰውነትህ የሚገባህን ክብር ማግኘትህ ነው። የሰው ልጅ ምንም ባይኖረው፣ የትም ባይደርስ፣ ምንም ቢጎድለው ሰውነቱ ብቻ፣ በአምላኩ አምሳል መፈጠሩ ብቻ ክብርንና ትኩረትን ያሰጠዋል። ቦታ በሰጠውት ሰው ቦታ አልተሰጠኝም፣ በወደድኩት ሰው ተጠላው፣ ትኩረት በሰጠውት ሰው ትኩረት ተነፈኩ፣ ባከበርኩት ሰው ተናቅኩ ብለህ እራስህን አታጨናንቅ። ክብርህን ያልተረዳ ሰው ቢንቅህና ቢገፋህ ምን እንዳጣ ማሳየት የምትችለው አንተ እንደሆንክ አስተውል። የበዛ ስምና ዝና ተቆልሎብህ ከምትወድቅ ተንቀህና ተገፍተህ በስራህ ከፍ ብትል ይሻልሃል። ሰው ያንኑ የለመደውንና ያደገበትን ያደርግብሃልና አትሸበር። አንተ አድናቂና ደጋፊ ስመሆንህ አስብ እንጂ ሲሔድ ለሚሔደው ባዶ ንቀትና ጥላቻ ቦታ አትስጥ፣ አንተም ንቀህ ተወው። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
3 23229Loading...
31
✅ ፍረሃታችሁን አሳዱት! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/LNY-ZRH9IhE?si=iOtnZThPNEngmvt3
2 9371Loading...
32
ተማሪ ናችሁ?? ✅ እራሳችሁን በገቢ መቻል ትፈልጋለችሁ? ✅ ከትምህርታችሁ ጎን ለጎን የሚሔድ ሥራ መሥራት ትፈልጋለችሁ? ከትምህርቱ ጎን ለጎን ሥራ በመሥራት ህይወቱን መለወጥ የሚፈልግ ሁሉ ይሔው ቪዲዮ ተዘጋጅቷል👇👇👇 https://youtu.be/8VZQJSF4V5g?Sub_confirmation=1 https://youtu.be/8VZQJSF4V5g?Sub_confirmation=1 https://youtu.be/8VZQJSF4V5g?Sub_confirmation=1   👆👆ቋሚ ገቢ ማግኘት የሚፈልግ ሁሉ ሊያየው የሚገባ
7421Loading...
33
😊መልካም ዜና ይዘናል! ባሉበት ሆነው በኦንላይን ተቀጥረው መስራት ይፈልጋሉ? እንዲሁም በኦንላይን ባለሞያ ቀጥረው ማሰራት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ በየዘርፉ ባለሞያዎች እና ቀጣሪዎች ያሉበትን የቴሌግራም ፕላትፎርም አሁኑኑ Join/ይቀላቀሉ        👇👇 👉@Maroset Maroset is dedicated to connecting talented professionals with exciting remote job opportunities. As an employer, you can easily find skilled and experienced professionals. As an employee, you can explore a wide range of remote job opportunities across various industries. 👉@Maroset
2 0993Loading...
34
ከሃዲ አትሁን! ፨፨፨////፨፨፨ አንድ ነገር አስተውሱ፦ "የምትኖሩት ከሰዎች ጋር ነው፣ ሰዎችም ስህተትን የሚሰሩት ፍጡራን ናቸው፣ ስህተታቸውም ክህደት እስከተባለ ከባድ ጥፋት ሊያደርሳቸው ይችላልና በመከዳታችሁ ብዙ አትሸበሩ።" በሰው ከመከዳት በላይ የሚጎዳችሁ እራስን መካድ እንደሆነ አስተውሉ። እግዚአብሔር አምላክ በብዙ መንገድ ያስተምረናል። ከእርሱ በላይ በሰው ስንታመን ሰውየውን መጥፎና ጎጂ ያደርገዋል፣ ከእርሱ በላይ ሰውን ስንደገፍ ሰውዬውን ከሃዲና ጨካኝ ያደርገዋል። አንድ ቀን የሚክደንን ሰው አምልኮት የቀረውን ቦታ ሰጥተን ስንከተለው፣ ለፈጣሪያችን መስጠት የሚገባንን ክብርና ጊዜ ለእርሱ ስንሰጠው፣ ለአምላካችን ሊኖረን የሚገባውን ጥብቅ ግንኙነት ከእርሱ ጋር ስናደርግ ትልቁ የህይወት ትምህርት በእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ይሰጠናል። በስቃይ እንድንማር፣ አምኖ በመከዳት እንድንነቃ፣ አግኝቶ በማጣት ወደ እራሳችን እንድንመለስ፣ ብቻችንን በመቅረት ወደ ፈጣሪያችን እንድንመለስ እንደረጋለን። ክህደት ብርቅ አይደለም። እንኳን ሰው ሰውን ይቅርና የሰው ልጅ አምላኩን ይክደዋል፣ እርሱ እያኖረው መኖሩን እርግፍ አድርጎ ይክዳል፣ ህልውናው ላይ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ያነሳል። ሰው ምኞቱ አያልቅምና ክህደቱንም እራሱ ካልገታው መቋጫ የለውም። አዎ! በክህደት አትሸበሩ! ዘመን በዘመን ሲተካ ከሃዲውም ታማኙም እኩል አዲሱን ዘመን ለመመልከት ይበቃሉ፣ ፈጣሪ እንደ ሰው አይደለምና ለሁሉም እኩል የመመለሻ ጊዜ ይሰጣል። ጥፋተኛ በጥፋቱ አይዘልቅም፣ ከሃዲውም እንዲሁ ዘመኑን ሙሉ በክህደቱ ሰውን እያስለቀሰ፣ በሰው ህይወት እየተጫወተና ደጋግሞ ሰውን እየጎዳ አይኖርም። ቢዘገይም ማንም የዘራውን ያንኑ ያጭዳል፣ በሰው ላይ ካደረገው በላይ እራሱ ተደርጎበት ይመለከታል። ዛሬ በጥፋት ዘመን ማስተዋል ሊያጣ ይችላል፣ በመጥፎ ልማዱና በጎጂ ማንነቱ ሊተማመን ይችላል። አንዴ ሲወድቅ ግን ወድቀቱ የከፋ ይሆናል፣ አንዴ መንገዱን ሲስት ግን የሚከፍለው ዋጋ እጅግ የበዛ ይሆናል። መከዳታችሁ ጊዜያዊ ህመምን ሊያስከትልባችሁ ይችላል፣ ባመናችሁት መዋሸታችሁና መታለላችሁ ትልቅ ጠባሳን ሊጥልባችሁ ይችላል ነገር ግን ከከሃዲነት ፀፀትና እረፍት ከማይሰጠው የጥፋተኝነት ስሜት ነፃ ናችሁ። ህመማችሁ ይድናል ያሳመሟችሁ ሰዎች ግን መጥፎ ስራቸው ሲያቅበዘብዛቸው ይኖራል፣ ጉዳታችሁ ይሻራል ሁን ብለው የጎዷችሁና ሰላም ያሳጧችሁ ግን በጥፋተኝነት ስሜታቸው ዘመናቸውን በሙሉ እራሳቸውን ሲወቀሱ ይኖራሉ። አዎ! ጀግናዬ..! ከሃዲ አትሁን! እምነትን ከመብላት፣ ቃልን ከማጠፍ፣ ባሉት ካለመገኘት ተቆጠብ። ክህደት ምንያህል ጎጂ እንደሆነ ለማወቅ የግድ ተከድተህ ማየት አይኖርብህም፣ ቃልን ማጠፍ ምንያህል እንደሚያቆስል ለማወቅ በሌሎች ቃል ታጥፎብህ መጎዳት አይኖርብህም። ጥቂት የማይባል ሰው በክህደት ምክንያት ህይወቱ እንዳልነበር ሆኗል፣ በቃል በሊታዎች ምክንያት ከባድ የህይወት ፈተና ውስጥ ገብቷል፣ በአስመሳዮችና በውሸታሞች ምክንያት ያልጠበቀው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ከቻልክ አስቀድሞ የማይመችህ ነገር ውስጥ አትግባ፣ ገብተህም ቢሆን ነገሮችን በግልፅ ለማስረዳት ሞክር እንጂ የክህደትን መዘዝ እያወክ በፍፁም ከሃዲ አትሁን፣ በድብቅ አታሲር፣ በውሸት አትደልል። እራስህ በዘረጋሀው ገመድ እራስህ ተጠልፈህ እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ፣ በገዛ ሴራህ መቀመቅ ከመግባት እራስህን ጠብቅ። ክፉዎች በይቅርታና በንሰሃ እስካልተመለሱ ድረስ ሁሌም ቢሆን መጨረሻቸው ጥፋት ነው። ከሃዲዎችም ቢሆኑ ከፈጣሪያቸው ጀምረው መካድን ሲለማመዱ አወዳደቃቸው እጅግ የከፋ ይሆናል። የፈጣሪህን ቦታ ለማንም አትስጥ፣ ክህደትን ተጠየፍ፣ በታማኝነትህ እራስህን አስከብር። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 36719Loading...
35
Media files
2 5270Loading...
36
መሔድ አለብህ! ፨፨፨////////፨፨፨ እውነት ነው፦ ፈርተሃል፣ ውስጥህ ተጨንቋል፣ ልብህ ደጋግሞ ይመታል፣ እግርህ ተሳስሯል፣ እጆችህ ይንቀጠቀጣል፣ ፊትህ በላብ ተጠምቋል ነገር በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነህም መሔድ አለብህ፣ ወፊት መጓዝ አለብህ፣ ጉዞህን መቀጠል ይኖርብሃል። እነዚህን ከባባድ ሁኔታዎች ልታሸንፋቸው የምትችለው በመቆም ወይም በመሸሸ አይደለም አሸናፊነትህ በብቸኝነት ያለው ጉዞህ ውስጥ ብቻ ነው። ብዙ ሰው ቆሞ ባለበት ዓለም መቆም ብርቅ ሆኖ አያውቅም፤ ብዙ ሰው በሚፈራበት ሀገር ፍረሃት አጀንዳ ሆኖ አያውቅም፣ መሸሽና መደበቅ እንደ ጨዋነት በሚቆጠርበት ማህበረሰብ ሁሉም ስፍራ አንገት መድፋት እንደ ጥሩነት እንጂ እንደ ጎጂ ፍረሃት ተወስዶ አያውቅም። ዓለም የተስማማበት የትኛውም እሳቤ ላንተ ከመስራት በላይ አንተ ላይ የሚሰራ፣ አንተን ከመጥቀም በላይ ባንተ የሚጠቀም ከሆነ ቆም ብለህ እራስህን መጠየቅ ያለብህ ትክክለኛ ጊዜ ያ ነው። ጥያቄህ ከተቀመጥክበት የሚያነሳህ ነው፣ ጥያቄህ ፍረሃትህን ፈንቅለህ እንድትወጣ የሚያደርግህ ነው፣ ጥያቄህ ወደፊት የሚያስጉዝህና አቋምህን የሚቀይር ነው። ጥያቄህም ይሔ ነው፦ "ቆሞ መቅረት ብቸኛ ምርጫዬ ነውን?" አዎ! ጀግናዬ..! መሔድ አለብህ፣ መጓዝ አለብህ፣ እንቅስቃሴን መምረጥ፣ ጥረትህን መቀጠል፣ ለመጪው ጊዜ ዋጋ መክፈል ይኖርብሃል። መድረስ የምትፈልገው ቦታ ይኖረል፣ የህይወት ዘመን ምኞት ይኖርሃል፣ ቢሆንልኝ ብለህ የምትለው የህይወት ከፍታ አለ። ያለምንም እንቅስቃሴና ያለምንም ጉዞ መኖሩ ብቻ ግን እውን ለመሆኑ ዋስትና አይደለም። አሸናፊዎች የሚያሸንፉት አሸናፊነት መጥቶላቸው ሳይሆን እራሳቸው ሂደው፣ አሳደው፣ ለዘመናት ሌትከቀን ሰርተውበት አግኝተውት ነው። ልብህ የሚያምንበት የህይወት አቅጣጫ ካለ በእርሱ መንገድ ለመጓዝ አትፍራ። ስራ የዘላለም አይደለም፣ ጉዞህ ማብቂያ የሌለው አይደለም፣ ጥረትህ መጨረሻ አልባ አይደለም። ትሔዳለህ፣ ትሔዳለህ፣ ትጓዛለህ መድረስ የሚገባህ ቦታ ስትደርስ ከመዳረሻህ ቦሃላ እርፍት አድርገህ ዳግም ወደ አዲሱ መዳረሻህ ትጓዛለህ። አቅምህ እስከፈቀደ፣ እድሜህ እስካስቻለህ ትጓዛለህ፣ ትሞክራለህ፣ ትሰራለህ የሚገባህ ህይወትህም በዛው ልክ ይሰጥሃል። አዎ! ጉዞህ በማንም እይታ ውስጥ የመግባት ግዴታ የለበትም፣ ጥረትህ በማንም ዘንድ ተቀባይነት የማግኘት ግዴታ የለበትም፣ እንቅልፍህን ማጣትህ፣ በጨለማ መሞከርህ፣ ብቻህን መጋፈጥህ ለማንም የመታየት ግዴታ የለበትም። የምትጓዘው ማንም ሳያይህ ብቻህን ነው፣ ስትደርስ ግን ብዙዎች ያዩሃል፣ ብዙዎች ይደነቁብሃል፣ ጥረትህን አላዩምና ብዙዎች እዛው የበቀልክ ይመስላቸዋል። ጉዞ ላይ እንደሆንክ ከተሰማህ ስለመድረስህ አትጠራጠር፣ እየሔድክ ከሆነ በማደግህ አትጠራጠር። እርግጥ ነው በአንድ ጀምበር አትደርስም፣ እንዲሁ አንድ ቀን ስለሞከርክ፣ ሁለት ቀን ስለጣርክ፣ ሶስት ቀን ስለለፋህ፣ ለሳምንታት፣ ለወራት፣ ለአመታት ስለተጋህ ላታሳካው ትችላለህ። ነገር ግን ይህንን እውነት አስታውስ፦ ጥረትህን ካላቆምክ በእርግጥም አንድ ቀን ታሳካዋለህ፣ አንድ ቀን እዛ ስታልመው የነበርከው፣ እዛ ልብህ የሚያሞቀው፣ እዛ ልዩ ስሜት የሚሰጥህ ስፍራ ትደርሳለህ። ምንም ውስጥ ብትሆን መጓዝ አለብህ፣ ምንም ቢገጥምህ እንዳቅምህ መንቀሳቀስ ይኖርብሃል። ተቀምጠህ ሳይሆን ተነስተህ አግኘው፣ ቆመህ ሳይሆን ሔደህ በእጅህ አስገባው። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 14411Loading...
37
✅ በፅናት ጠብቁ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/TimoyF8pBNo?si=oJ0Bo0xSduRUuELJ
3 1972Loading...
38
VACANY ANNOUNCEMENT! JOB TITLE: YouTube VIDEO EDITOR Channel: Mikre Aimro Salary: 150 ETB/12 min video Work quantity: 7 videos per week Description: We need a video editor for our Educational, Self improvement and Motivational YouTube Automation channel which is in Amharic language. The videos are easy to edit, simple stock footage but a fast paced video with subtitles that keeps the audience engaged. We will provide the voice over with its subtitle. It's more prefereable if the editor is more interested in inspirational and personal development contents. The editor might also need to use free stock footage that matches the message that's being said on the video. The editor will edit 10 - 15 minutes (mostly 12 minutes) videos With unique and most engaging editing styles that show his creativity and skill. The candidate must have a fast internet connection. Reliability is key and we don't accept any unrealistic excuses for not delivering the work on time or not being punctual. The candidate must have knowledge about YouTube's copyright and fair use policy. Please apply only if you agree on the given description. NOTE: - DON'T FORGET to attach your previous works (YouTube videos) or be ready to edit 2 minutes sample video by using the voice over and subtitle we send you. Use the opportunity properly, your today's small effort will pay you more. As much as possible consider norm and value of our community in your video. To be more computative feel free to check out our channel and come up with a better engaging video editing style. Priority for pro video editors! Contact: @VERegistrationBot
5 25414Loading...
39
አንድ ውሳኔ ብቻ! ፨፨፨////////፨፨፨ በህይወት ከባዱ ነገር ብረት ወይም ወርቅ አይደለም ይልቅ ያልተወሰኑ ውሳኔዎች ናቸው። የጭንቀታችሁ ትልቁ ምክንያት መወሰን ያለባችሁ ውሳኔ አለ ነገር ግን መወሰን አልቻላችሁም። - Alex Hormozi ኬትም ተነስተን ወዴትም እንሂድ የምንሔድበት ስፍራ የሚያደርሱን ተግባራዊ ውሳኔዎቻችን ናቸው። ወስናችሁ ማቆም ወይም ወስናችሁ መጀመር ያለባችሁ ጉዳይ እያለ እናንተ ግን ለመወሰን ካንገራገራችሁና በየሰዓቱ የውሳኔ ጊዜያችሁን የምታራዝሙ ከሆነ የውሳኔ ሃሳባችሁ ከሸክምም በላይ የጭንቀት ምንጭ መሆኑ የግድ ነው። ይብዛም ይነስም ነፃነታችን ያለው በምንወስናቸው እያንዳንዶቹ የህይወት ውሳኔዎች ውስጥ ነው። ሀላፊነት መውሰድ የሚፈሩ፣ አዲስ ነገር መሞከር የሚያስጨንቃቸው፣ እራሳቸውን ቻሌንጅ ማድረግና አደጋን መጋፈጥ የማይወዱ ሰዎች ሁሌም ቆራጥ ውሳኔ የመወሰን ችግር ይኖርባቸዋል። ውሳኔያቸው ብዙ ነገር እንደሚቀይርላቸው ያውቃሉ ነገር ግን ለመወሰን ድፍረቱ የላቸውም፣ ወደፊት ለመጓዝ ከባባድ ውሳኔዎች እንደሚያስፈልጉ በሚገባ ይረዳሉ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ውሳኔን እየሸሹ ህይወታቸውን በሙሉ በፍረሃትና በስጋት ጥግ ላይ ያሳልፋሉ። የውሳኔ ሰው እስካልሆናችሁ ድረስ ባላችሁበት ስፍራ ከመቅረትና በቁጪት ሸክም እራሳችሁን ከመጉዳት በቀር ምንም የምታተርፉት ነገር የለም። አዎ! ወስናችሁ ውጡ፣ ወስናችሁ ሸክማችሁን አራግፉ፣ በውሳኔያችሁ ነፃ ውጡ፣ በውሳኔያችሁ የሚጠቅማችሁን ጀብድ ፈፅሙ። መወሰን እያለባችሁ ሳትወስኑ በቀራችሁ ቁጥር ከትርፋችሁ በላይ ኪሳራችሁና የምታጡት ነገር እየበዛ ይመጣል። ዛሬ ከምትኖሩት ህይወት በይዘቱ፣ በጥራቱ፣ በትርፋማነቱም ሆነ በደስተኝነቱ የተለየው ህይወት ያለው ከአንዱ ወሳኝ ውሳኔያችሁ ጀርባ እንደሆነ አስታውሱ። ዛሬ የምትኖሩት ህይወት ወዳችሁም ሆነ ተገዳችሁ የወሰናችሁት ውሳኔያችሁ ውጤት ነው። ሀገር ብትቀይሩ፣ ስራ ብትቀይሩ፣ የምትከታተሉትን መርሃግብር ብትቀይሩ እንዲሁም ውሏችሁን፣ አስተሳሰባችሁንና የህይወት መርሆቻችሁን ብትቀይሩ ከለውጣችሁ ጀርባ ያለው ሁነኛ ግበዓት ቆራጥ ውሳኔያችሁ ነው። አሁን ወደፊት መጓዝ እንዳለባችሁ እያወቃችሁ እስካሁን ግን ወደፊት የሚያራምዳችሁን ውሳኔ ካልወሰናችሁ ከዚህ በላይ ጊዜ አታጥፉ፣ ልባችሁን አሸንፉ፣ ልማዳችሁን ተገዳደሩት፣ ለማንም ሳይሆን ለራሳችሁ ብላችሁ ወስኑ። አዎ! ጀግናዬ..! አንድ ውሳኔ ብቻ! የማቆም ወይም የመጀመር ውሳኔ፣ ህብረት የመፍጠር ወይም ከሚጎዳህ አካባቢ ነቆሎ የመውጣት ውሳኔ፣ ትምህርትን በአግባቡ መማር ካልሆነም ጨክኖ ፊትን ወደሌላ የማዞር ውሳኔ፣ በሱስ ላይ መጨከን ወይም ሱሱ ጨክኖ እንዲያጠፋህ የመፍቀድ ውሳኔ። ለሌላው የሆነው ሁሉ ላንተም ይሆናል ማለት አይደለም፣ ብዙ ሰውን ትርፋማ ያደረገ ቢዝነስ አንተንም ትርፋማ ያደርግሃል ማለት አይደለም፣ ጥቂቶችን ትልቅ ደረጃ ላይ ያደረሰ ትምህርት አንተንም ያደርስሃል ማለት አይደለም። ማንም ሰው ነፃ የሚወጣው የሰዎችን ተግባር በመከተል ሳይሆን የእራሱ የማያወላዳ ፅኑ አቋም ሲኖረው ብቻ ነው። የመጣው ቢመጣም ከውድቀትና በሰዎች ከመተቸት በቀር የሚመጣ ነገር የለምና በአዕምሮህ ተሸክመህ የምትሔደውን ውሳኔ በድፍረት ምድር ላይ አውርደው፣ አዕምሮህን ከግብ አልባው የማያባራ ሃሳብ ገላግለው። ጭንቀት ኖሮበት የተሻለ የህይወት ደረጃን የሚመኝ ሰው የለምና በቅድሚያ ባልተወሰኑ ውሳኔዎች የታጠረውን ጨንቀትህን ለመቀነስ ወስን፣ ለውሳኔህ ታመን፣ ወደምትመኘው የተለየ ህይወትም በድፍረት ጉዞ ጀምር። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 48223Loading...
40
Media files
2 6600Loading...
ነገ የለም! ፨፨////፨፨ ብዘዎቻችን ከነገ ጋር ያለን ፍቅር እጅጉን ይለያል፤ ነገ የሚባል ተጨባጭ ቀን ሳይኖር በውስጡ ተዓምራዊ ምቾት እንዳለው እናስባለን። በህይወት ዘመናችን እንደ ነገ የጠበቅነው፣ በጥበቃችን ልክም ያላገኘው ነገር የለም። ሁሉን ነገር ለማድረግ ነገን መጠበቅ፣ ምንም ለመጀመር ነገን መናፈቅ፣ ስንፍናን ለመሸፈን፣ ድካምን ለማስታገስ፣ ምቾትን ለመጠበቅ ነገ የተባለ ቀን ሁነኛ ምክንያት ሆኖልናል። ነገ የት ነው ቢባል ምላሽ የለም፤ ምንም የሚታቅ ነገር የለም። ለነገ ይታሰባል፤ ለወደፊት ይታቀዳል ነገ ግን አይኖርም፤ ወደፊት ውስጥ እቅዱ አይፈፀምም። የማይደርስ መስሎህ በነገ ስም ያራዘምከው ቀን ዛሬ ሆኖ ከፊትህ ይደቀናል፤ ዛሬ ነገ እያልክ ያሸጋገርከው ጉዳይ ነገን አያውቅምና በጊዜው አሁን መፈፀምን ይፈልጋል። ረጅም ጊዜ እንዳለህ እያሰብክ፣ ብዙ የምትኖረው እድሜ እንደቀረህ እያለምክ ለነገ የምትገፋቸው ጉዳዮችህ ዋጋ ማስከፈላቸው ግድ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ነገ የለም! ልያዘው ብትል አትይዘውም፤ ልጨብጠው ብትል አትጨብጠውም፤ ትርጉም ያለው ትርፋማ ነገር ላድርግበት ብትል አታደርግበትም። የምትናፍቀው ነገ ዛሬ ነው፤ የምትመኘው ተጨባጩ ወደፊት አሁን ነው። ፍቅር ለመስጠት፣ ያለህን ለማካፈል፣ የምትችለውን ለማድረግ፣ ጥረትህን ለመጨመር ያለህ ጊዜ አጭርና አሁን ብቻ ነው። ሃሳቦችህ የእራሳቸው ደረጃ አላቸው፤ እቅድችህ የቀን ገደብ ይኖራቸዋል እውንነታቸው ግን በዛሬ ውስጥ ነው። ትልቁ ህልምህ የሚኖረው አንድ በማይታወቅ ቀን ሳይሆን ዛሬ በሚታይ፣ በሚጨበጥ፣ በሚዳሰስና በሚታወቅ ቀን ነው። በነገ ምክንያት ያመለጡህን አጋጣሚዎች፣ የረሳሃቸውን አስገራሚ ሃሳቦች፣ ያጣሃቸውን ሰዎች፣ የደከሙብህን መገለጫዎችህን አስታውስ። ስታቅድ ኖረህ ስታቅድ ማለፍ አትፈልግምና በትንሹም ቢሆን መራመድ ጀምር። አዎ! ያንተ የሆነው የትም አይሔድም፤ ነገር ግን አንተ ከገፋሀው ለማንም ሳይሆን ያልፋል። ዛሬና ነገ በእጅጉ ይለያያሉ። ልዩነታቸውም በየሃሳብ ህልውናና በተግባር ህልውና ነው። ነገን ከሃሳብ ውጪ የምትይዝበት መንገድ የለም፤ ከምናብ በተለየ የምትዳስስበት ሁኔታ የለም። ህልውናው፣ መኖሩ በሙሉ ሃሳባዊ ነው። ዛሬ ግን አሁን ነው፤ ሙሉ ነው፤ የሚታይ፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ፣ ከሃሳብ የዘለል ተግባራዊ ህልውና ያለው ነው። በምናብ መኖር፣ በሃሳብ ማደግ ደስ ይላል፣ ተጨባጭ ግን አይደለም። ነገን እያለምክ በዛሬ ውስጥ ታስረህ አትቅር። ያሰብከውን ሁሉ ማድረግ የምትችለው ነገ ሲባሉ በነበሩ ዛሬዎች ውስጥ ነው። ሃሳባዊው ነገ በትንሹ ሊያስፈልግህ ይችላል፣ የህይወትህ መርህ ሊሆን ግን አይችልም። ማየት የሚገባህን የምታየው ዛሬ እንጂ ነገ አይደለም፤ ሃሳብህ እውን የሚሆነው አሁን እንጂ ቦሃላ አይደለም። መኖር የምትፈልገውን ህይወት በተሰጠህ ዛሬ ውስጥ ኑረው። ህይወትህን አንተው በሃሳብህ ሙሉ ካላደረካት አትሞላምና ለምትወዳቸው ሰዎች ፍቅርህን ለመግለፅ፣ የምታስበውን ስራ ለመጀመር፣ መሆን የምትፈልገውን ሰው ለመሆን ነገን መጠበቅ አቁም። የዛሬ ሃላፊነትህን ተወተህ ሃሳባዊውን ነገ ሙሉና ተጨባጭ አድርገው። ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Show all...
👍 13🥰 2🔥 1👏 1🙏 1
ዋጋቢስ አትሁን! ፨፨፨///////፨፨፨ መልካም በተባሉ ነገሮች መማረክ፣ ጥሩ በሰራው መደነቅ፣ የሰዎችን ህይወት ማድመቅ ብሎም ማድነቅ ክፋት የለውም የእራስን መርሳትና ማደብዘዝ ግን ትልቅ ክፍተትን ከብዙ ችግር ጋር ይፈጥራል። የየለት አጀንዳህ የሰዎች ህይወትና አኗኗር ከሆነ ለእራስህ ጊዜ ሊኖርህ አይችልም። የእነርሱን ትንሽ አጀንዳ በማጉላት ከተጠመድክ ያንተው ትልቅና ወሳኝ አጀንዳ አስታዋሽ ያጣል። ይህ አስታዋሽ ያጣው ወሳኝ አጀንዳህም ቀስ በቀስ ስር እየሰደደ ውድቀትህን ሲያፈጥንና ችግሮችን ሲደራርብብህ ልትመለከት ትችላለህ። የሰው ህይወት የሰው ነው፣ ያንተም ህይወት ያንተ ነው። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንደተባለችው ሴት አትሁን። በሰው ቤት ሄደህ ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን ከመሞከርህ በፊት መጀመሪያ የራስህን ቤት አቅና፣ የራስህን ጎጆ በሚገባ ገንባ። ክብርህ በቤትህ ነው፣ ዋጋ የሚኖርህ ለራስህ በምትሰጠው ዋጋ ልክ ነው። የማይመለከተውን እየተነተነ ለሚመለከተው ጉዳይ ጊዜ ያጣ ብዙ ሰው አለ፣ የራሱን ችላ እያለ የሌሎችን የሚፈተፍት ብዙ ሰው አለ፣ ዋናው ትኩረቱ እራሱ መሆን ሲገባው ትኩረቱን ሌሎች ላይ ያደረገ ብዙ ሰው አለ። አዎ! ጀግናዬ..! ዋጋቢስ አትሁን! መራሩን እውነት ለመሸሽ አትዋደቅ። አንተ ለራስህ ዋጋ ካልሰጠህ ማንም ዋጋ ሊሰጥህ አይችልም። በየመንገዱ ለምታየው ነገር አስተያየት በመስጠት አትጠመድ፣ በአላፊ አግዳሚው አትማረክ፣ የእራስህን ጉዳይ የማትከታተል ለሰው ጉዳይ የምትዋደቅ፣ ለመወደድና ትኩረት ለማግኘት ላገኘሀው ሰው ሁሉ ድክመትህንና ከእርሱ ያነስክ እንደሆንክ የምታወራ አሳፋሪ ሰው አትሁን። ሰው አይደለም እቃ እንኳን የውድነቱ ማሳያ የዋጋው ጭማሬ ነው። ዋጋህ ካልጨመረ ማንም ሊያነሳህ እንደማይመጣ እወቅ። ይሔንን አስታውስ፦ "ዛሬ የእለት አጀንዳህ አንተ ነህ።" ዓለምን የማትሰማበት፣ ከጫጫታዋ ዞር የምትልበት፣ በማይረቡ አዳዲስ አጀንዳዎቿ የማትታለልበት፣ የማይጠቅምን የመረጃ በር የምትዘጋበት፣ አኗኗሪ መሆንህ የሚያበቃበት፣ ነዋሪነትህ የሚጀምርበት ጊዜ ዛሬ ነው፣ ከዛሬም አሁን ያለህበት ሰዓት ነው። በቅድሚያ የእራስን ሸክም ማራገፍ ስልጣኔ ነው። ሁን ተብሎ የሚሰራን ድራማ የህይወት አጀንዳ ማድረግ ቅለትና ብክነት ነው። አለም አዳዲስ አጀንዳ አታጠም፤ አዳዲስ ወሬ አታጣም። ያንተ በእርሷ ጊዜያዊ ድራማ መታለል ዋጋ ከማስከፈሉም በላይ ያንተንም ዋጋ እያሳነሰ ዋጋ ቢስ እንደሚያደርግህ እወቅ። አዎ! ፈተና ከተባለ እራስን ከማስረሳት በላይ የሚፈትን ነገር አይኖርም። ትኩረትህ ወደ ውጭ በሆነ ልክ ውስጥህ ባዶና ጥቅም አልባ እየሆነ ይመጣል፣ አይንህ አካባቢውን ብቻ መመልከት ከጀመረ የሚያስፈልገውን ነገር ማግኘት ያቅተዋል። ሁላችንም ጦርነት ውስጥ ነው። እራስን የመግዛት ጦርነት። ዓለም በዛኛው ወገን ልትገዛን ትጥራለች እኛም በነቃን ቁጥር በዚህ በኩል እራሳችንን ነፃ ለማውጣት እንታገላለን። በየቀኑ የሚመጡ የአለም ክስተቶች ለእራሳችን ጊዜ እንዳይኖረን፣ በእነርሱ ጉዳይ መጠመድና መብከንከን ዋነኛው ተግባራችን እንዲሆን እያደረጉን ነው። የሌላውን ስናደምቅ የእኛ ሲፈዝ፣ የሌላውን ስናሳምር የእኛ ሲበላሽብን መመልከት የየለት ተግባራችን ኋኗል። ህይወትህ ላይ ጠብታ ያክል ነገር የማይጨምር የአለምን ጋጋታ መከተልህ ማብቂያው አሁን ነው፣ መጨረሻ የሌለውን ጊዜያዊ አጀንዳ የመስማቱ ፍፃሜ አሁን ነው። በጊዜያት ለማይቀረው፣ በህይወት እስካለህ ድረስ አብሮህ ለሚኖረው ለእራስህ ጊዜ መስጠት ጀምር፤ ዓለም ካንተ ቦሃላ ነችና አራስህን ቀዳሚው የህይወት አጀንዳህ በማድረግ ለዓለም ጠቃሚና ከዓለም ተጠቃሚ ሆነህ ተገኝ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Show all...
👍 11 4🥰 3👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
✝✝ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፣ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። ✝✝ "ምድር ጸዳች ሐሴት አደረገች  በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች።" እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! 💒✞❖ መልካም በዓል! 💒✞❖ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን! ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Show all...
🥰 12 9👍 3🙏 3🔥 1
ከፍርድ ተቆጠቡ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/2GmfpRhWHgE?si=KOdGj-snzJ8kqb5e
Show all...
ሚዛናዊ ሁኑ፤ በሰፈራችሁት ቁና እንዳትሰፈሩ ተጠንቀቁ! | ድንቅ የህይወት ትምህርት | Inspire Ethiopia | | MIKRE AIMRO

ምቾት የሚነሷችሁን ሰዎች ራቁ! ቪድዮውን 👍 LIKE ስለምታደርጉና ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! Motivational Speech in Amharic | Amharic Motivational Video | Ethiopian motivation | amharic motivation | አነቃቂ ንግግሮች | አነቃቂ ምክሮች | inspire Ethiopia | dawit dreams | shanta | daggy's life class | manyazewal podcast | inspire podcast | dawit dreams podcast #making_money #sidehustle #business #ethiopianmotivation #inspire_ethiopia #inspirationalvideo MOTIVATION + DISCIPLINE = UNWAVERING SUCCESS! @mikre_aimro 🔶 ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ይመልከቱ፡ 👇👇 ♦️

https://youtu.be/HntYXoAUrN4

ቪድዮውን ላይክ 👍 ማድረግ እንዳይረሱ! ቻናላችንን ሰብስክራብ ያድርጉ! የደውል ምልክትን ይጫኑ! Comment ያስቀምጡልን!እናመሰግናለን! 🙏🙏🙏 Social Media: INSTAGRAM:

https://www.instagram.com/epha_aschalew

YOUTUBE:

https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1

FACEBOOK:

https://www.facebook.com/EthioMentalCounsel

TELEGRAM:

https://t.me/MentalCounsel

TIKTOK:

https://www.tiktok.com/@mentalcounsel

Music from #InAudio:

https://inaudio.org/

Track Name. inaudio - Infraction -Rebellion inaudio - Infraction - Majestic Vision inaudio - Infraction -Action motivational አነቃቂ ጥቅሶች አነቃቂ ንግግሮች አነቃቂ ዘፈኖች አነቃቂ አጭር ልቦለድ አነቃቂ ቪዲዮ motivational ethiopia motivational music motivalional motivationalmotivalional motivational speech motivalional songs motivational short story motivational video ethiopia yosan getahun oromo music 2023 motivational videos for students tointerview study hard motivalional songs with lyrics motivate me speaker motivate little mix motivation motivate motivation video motivate molivate motivational eshetu manyazewal motivational manyazewal eshetu manyazewal eshetu in schoolkeysofmoon inspire ethiopia inspire people manyazewalinspire ethiopia new video inspire ethiopia new inspire ethiopia motivation Anki andbet,Manyazewal,Dawit dreams,እነቃቂ,አላማ,Inspire,Motivated,Motivate 2 ethiopia EBS Motivate ethiopia,Inspire Ethiopia,Ethiopia,Success,Motivations,Motivational,Motivation,Manyazewal eshetu,motivational video,motivational speech,motivation,motivational songs,abel birhanu

4👍 2🔥 1🥰 1
ልማድን በልማድ! ፨፨፨/////////፨፨፨ በእድሜያቸው የሸመገሉ ሰዎች በሚኖሩበት የአዛውንት መጦሪያ ቤት የሚሰራ የእነሱ ተንከባካቢ ባለሞያ ወጣት ስራውን በጣም ስለሚወደው ለእነዚህ አዛውንት የሚሰጠውን እንክብካቤ ከልቡ ነበር የሚያደርገው፡፡ ነገር ግን፣ ይህንን ስራውን እጅግ አስቸጋሪ ያደረገበት አንድ ነገር ነበር፡፡ ሁለት በዚያ የጡረተኞች ቦታ ጓደኝነት የፈጠሩ አዛውንት ማታ ማታ ከቤት ወጥቶ በአካባቢው ተዘዋውሮ የመመለስ የብዙ አመታት ልማድ ስላላቸው አብረው ያንን ያደርጋሉ፡፡ በመቆያ ቦታው ሕግ መሰረት ግን ይህንን ማድረግ ክልክል ነው፡፡ ምክንያቱም በጣም ስለሸመገሉ አደጋ ሊደርስባቸው ስለሚችል ካለጠባቂ መውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ ይህንን ልማዳቸውን ለማስቆም ብዙ ሞክሮ ያቃተው ወጣት ሰራተኛ በመጨረሻ አንድ የስነ-ልቦና አዋቂ አማከረ፡፡ አማካሪውም ወዲያውኑ፣ “እነዚህ አዛውንት ማታ ከቤት ለመውጣት ሲያስቡ በፍጹም ሳይዙ ወይም ሳያደርጉ መውጣት የማይችሉት ልማድ አላቸው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ወጣቱ ትንሽ አሰበና፣ “አዎን፣ ሁለቱም ኮፍያቸውን ሳያደርጉ በፍጹም መውጣት አይወዱም፡፡ ኮፍያቸው ከታጠበ እንኳን እስከሚደርቅ ጠብቀውና አድርገው ነው የሚወጡት” አለው፡፡ አማካሪውም፣ “እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ አየህ አንድን ልማድ ለማቆም ሌላ ልማድ መጠቀም አለብህ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ አለፍ አለፍ እያልክ ኮፍያቸውን ደብቅባቸው፡፡ ኮፍያቸውን ሳያደርጉ መውጣት ያለመቻል ልማዳቸው ወደ ውጪ ከመውጣት ልማዳቸው ስለሚጠነክር በዚያ ምክንያት ከመውጣት ታስቀራቸዋውና ቀስ በቀስ እቤት ሲያመሹ ሌላ ከቤት የማያስወጣ ልማድ ያዳብራሉ” ብሎ መከረው፡፡ ወጣቱ ይህንን ምክር ገና ተግባር ላይ ከማዋሉ ውጤታማ በመሆኑ በጣም ተገረመ፡፡ አዛውንቱ ኮፍያቸውን ባጡባቸው ቀናት እቤታቸው ቁጭ ብለው የድሮ ታሪክ ሲያወሩና የድሮ ፊልሞችን እየከፈቱ ሲመለከቱ በማምሸት ማታ ወደውጪ የመውጣትን አደገኛ ልማድ በሌላ ጤናማ ልማድ ለመለወጥ ጊዜ አልፈጀባቸውም ነበር፡፡ ለወቅቱ “ጨለማ” የማይመች ልማድህ ምንድን ነው? እቤት መቀመጥ አለመቻል? ውጪ የመመገብ ልማድ? ከሰዎች ጋር ሳይሰባሰቡ አለመዋል? የወቅቱ ወረርሽኝ ላመጣብን “ጨለማ” የማይመጥነውን ከአንተ ጋር የከረመ ልማድህል ለመቀየር ቀላል ባይሆንም የማይቻል ግን አይደለም፡፡ ቀላሉ መንገድ ከዚያ ልማድህ የጠነከረ ሌላ ልማድ ማዳበር ነው፡፡ እቤት መዋልን እንድትወደው የሚያደርግ ልማድ ፍጠር፡፡ ከቤተሰብ ጋር ማሳለፍ፣ ማንበብን መልመድ፣ በሁለት ወር ውስጥ በአንድ አዲስ እውቀት ራስን ለማሰልጠን ማቀድ፣ የማትችለውን ምግብ ማብሰልን መልመድ፣ አንድን መጽሐፍ መምረጥና ከቤተሰብ አባላት ጋር በየቀኑ ማጥናትና መወያየት፣ ስፖርት መስራት . . .፡፡ መላው ብዙ ነው፡፡ አትርሳ፣ የሚያጠፋህም ሆነ የሚያለማህ ልማድህ ነው፡፡ ©ዶ/ር ኢዮብ ማሞ ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Show all...
👍 28 3👏 1
"ምን ላድርግ?" ፨፨፨//////፨፨፨ መቼ፣ እንዴት፣ የት፣ በምን ደረጃ እንደምትገኝ አታውቅም። ብዙ ብታቅድም፣ ብዙ ብታስብም ሃሳብና እቅድህ ሚዛን ሳይደፋ፣ ሳይሳካ ያልገመትከውና ያላሰብከው ስፍራ እራስህን ልታገኝ ትችላለህ። ስኬትን አቅደህ ወድቀህ ይሆናል፣ ብረሃንን አስበህ በጨለማ ተከበህ ይሆናል፣ ብዙዎችን ለማገዝ አስበህ ተረጂ ሆነህ ይሆናል፣ ችግር ለመፍታት እየተንቀሳቀስክ ችግር ውስጥ ተገኝተህ ይሆናል። ተጨባጩ ክስተት፣ ያለው እውነታ ከሃሳብና እቅድህ በብዙ እጥፍ ተቃርኖ ቢገኝ፣ እጅጉን ቢራራቅ ያንተ ግብረመልስ ምን ሊሆን ይችላል? ከመቀበል ባሻገር ቀጣይ እርምጃህ ምንድነው? አዎ! ጀግናዬ..! ያለህበት ሁኔታ ያልታሰበና ያልተመቸህ፣ አቅደሀው የማታውቀው፣ ለማመን የከበደህ ቢሆንም እንኳን የያዝከውን ይዘህ፣ የደረሰብህን ችለህ፣ ህመምህን ውጠህ እራስህን አንድ ጥያቄ ጠይቅ። ስለሁኔታው " ምን ላድርግ? " ብለህ ጠንቅ።  "ካለሁበት አስከፊ ሁኔታ ለመውጣት ምን ላድርግ? ምን ልስራ? እንዴት ልስራ? እንዴት ላድርግ? ኬት ልጀምር? ከማን ጋር ልጀምር? " ብለህ እራስህን ጠይቅ። ብልሆች በእራሳቸው መልስ ያላገኙለትን ጥያቄ የሚያምኑተንና የሚረዳቸውን ሰው ይጠይቃሉ። በአጋጣሚም ሆነ ሁን ብለህ የተገኘህበተን ስፍራ ማሻሻል፣ ማደስ፣ መቀየር ከፈለክ በሚገባ ትችላለህ። ሁሌም በችግር፣ ሁሌም ምቾት በማጣት፣ ዘወትር በምሬ፣ ዘወትር በለቅሶ እንድኖር የፈረደብህ አካል የለም። ለውጥ የሚባል ስጦታ ላንተም ህይወት ተሰቷ፣ ባንተም እጣፋንታ፣ ባንተም ኪስ ውስጥ ይገኛል። አዎ! የምታስበውን ለውጥ ለማምጣት ተቸግረሃል? ህይወት ዳገት እንደመውጣት ከብዳሃለች? ወኔህ ክዶሃል? ጉልበትህ ተብረክርኮብሃል? ከጥያቄዎቹ ጀርባ "ለምን?" ብለህ ዳግም እራስህን ጠይቅ። ከምክንያቶቹ ጀርባ የሚገለጥልህ ምክንያት፣ ማድረግ የሚገባህ ተግባር ይኖራል። ማድረግ የሚገባህን ባታውቅ አምላክህን ተማፀነው፣ "ምን ላድርግ?" በለው፤ ሰዎችን ጠይቅ፣ መርምር፣ ከልምዳቸው ተካፈል፣ እግራቸው ስር ወድቀህ ተማር። አንተ ያላሰብክበት ችግርህ፣ አንተ ችላ ያልከው ሸክምህ ያላንተ ፍቃድ በማንም የሚፈታ፣ በማንም የሚቀረፍ፣ በማንም የሚወርድ አይደለም። ከማትወደው የህይወት ዘይቤ ለመላቀቅ እራስህን አሳምን፣ ያለህበትን ሁኔታ በሙሉ ልብህ ተቀበል፣ ማድረግ ስለማትችለው ሳይሆን ማድረግ፣ መቀየር ስለመትችለው ብቻ ማሰብ ጀምር። የትኛውንም ያንተን ሸክም የመሸከሙ ሃላፊነት ያንተ ነው፤ ሲከብድህም የማውረድ፣ ፋታ የመውሰድ መብቱ አለህ። በፋታህ ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለብህ ደጋግመህ አስብ፤ ከብዶኛል እያልክ የሚቀልህ ነገር እንደሌለ አስታውስ። ከባድ ቢሆንም ትችለዋለህ፣ ታደርገዋለህ፣ እንደቀላሉ ታልፈዋለህ፤ ትሻገረዋለህ። በርታ! ተበራታ! ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Show all...
👍 20 6🔥 2🥰 1
ስሜታችሁን ተቆጣጠሩ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/eYFQfciJH-o?si=bAz3-EAq29VyndQD
Show all...
በጥልቀት አስቡ፤ አንድ መጥፎ ውሳኔ ህይወታችሁን ለማበላሸት በቂ ነው! | ድንቅ የህይወት ትምህርት | Inspire Ethiopia | | MIKRE AIMRO

ቆም ብላቹ አስቡ! ከቁጪት እራሳችሁን ታደጉ! @mikre_aimro ቪድዮውን 👍 LIKE ስለምታደርጉና ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! Motivational Speech in Amharic | Amharic Motivational Video | Ethiopian motivation | amharic motivation | አነቃቂ ንግግሮች | አነቃቂ ምክሮች | inspire Ethiopia | dawit dreams | shanta | daggy's life class | manyazewal podcast | inspire podcast | dawit dreams podcast #making_money #sidehustle #business #ethiopianmotivation #inspire_ethiopia #inspirationalvideo MOTIVATION + DISCIPLINE = UNWAVERING SUCCESS! @mikre_aimro 🔶 ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ይመልከቱ፡ 👇👇 ♦️

https://youtu.be/HntYXoAUrN4

ቪድዮውን ላይክ 👍 ማድረግ እንዳይረሱ! ቻናላችንን ሰብስክራብ ያድርጉ! የደውል ምልክትን ይጫኑ! Comment ያስቀምጡልን!እናመሰግናለን! 🙏🙏🙏 Social Media: INSTAGRAM:

https://www.instagram.com/epha_aschalew

YOUTUBE:

https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1

FACEBOOK:

https://www.facebook.com/EthioMentalCounsel

TELEGRAM:

https://t.me/MentalCounsel

TIKTOK:

https://www.tiktok.com/@mentalcounsel

Music from #InAudio:

https://inaudio.org/

Track Name. inaudio - Infraction - Atlas main version inaudio - Infraction -Memories inaudio - Infraction - Rebellion motivational አነቃቂ ጥቅሶች አነቃቂ ንግግሮች አነቃቂ ዘፈኖች አነቃቂ አጭር ልቦለድ አነቃቂ ቪዲዮ motivational ethiopia motivational music motivalional motivationalmotivalional motivational speech motivalional songs motivational short story motivational video ethiopia yosan getahun oromo music 2023 motivational videos for students tointerview study hard motivalional songs with lyrics motivate me speaker motivate little mix motivation motivate motivation video motivate molivate motivational eshetu manyazewal motivational manyazewal eshetu manyazewal eshetu in schoolkeysofmoon inspire ethiopia inspire people manyazewalinspire ethiopia new video inspire ethiopia new inspire ethiopia motivation Anki andbet,Manyazewal,Dawit dreams,እነቃቂ,አላማ,Inspire,Motivated,Motivate 2 ethiopia EBS Motivate ethiopia,Inspire Ethiopia,Ethiopia,Success,Motivations,Motivational,Motivation,Manyazewal eshetu,motivational video,motivational speech,motivation,motivational songs,abel birhanu

👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሕይወትን የሰራውን ከበደለኞች ጋር ሰቀሉት!እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት በሰላም አደረሳችሁ! ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Show all...
15🙏 7👍 3🥰 3🤔 1😢 1

9👍 7👏 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
4🥰 1