cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣ አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣ ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው። @MentalCounsel ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል! ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ! 🏠Welcome to your Home! 🏘 Personal Contact: @epha_aschalew Insta: instagra.com/epha_aschalew

Show more
Advertising posts
42 591Subscribers
-4924 hours
-2627 days
+48830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንድ ውሳኔ ብቻ! ፨፨፨////////፨፨፨ በህይወት ከባዱ ነገር ብረት ወይም ወርቅ አይደለም ይልቅ ያልተወሰኑ ውሳኔዎች ናቸው። የጭንቀታችሁ ትልቁ ምክንያት መወሰን ያለባችሁ ውሳኔ አለ ነገር ግን መወሰን አልቻላችሁም። - Alex Hormozi ኬትም ተነስተን ወዴትም እንሂድ የምንሔድበት ስፍራ የሚያደርሱን ተግባራዊ ውሳኔዎቻችን ናቸው። ወስናችሁ ማቆም ወይም ወስናችሁ መጀመር ያለባችሁ ጉዳይ እያለ እናንተ ግን ለመወሰን ካንገራገራችሁና በየሰዓቱ የውሳኔ ጊዜያችሁን የምታራዝሙ ከሆነ የውሳኔ ሃሳባችሁ ከሸክምም በላይ የጭንቀት ምንጭ መሆኑ የግድ ነው። ይብዛም ይነስም ነፃነታችን ያለው በምንወስናቸው እያንዳንዶቹ የህይወት ውሳኔዎች ውስጥ ነው። ሀላፊነት መውሰድ የሚፈሩ፣ አዲስ ነገር መሞከር የሚያስጨንቃቸው፣ እራሳቸውን ቻሌንጅ ማድረግና አደጋን መጋፈጥ የማይወዱ ሰዎች ሁሌም ቆራጥ ውሳኔ የመወሰን ችግር ይኖርባቸዋል። ውሳኔያቸው ብዙ ነገር እንደሚቀይርላቸው ያውቃሉ ነገር ግን ለመወሰን ድፍረቱ የላቸውም፣ ወደፊት ለመጓዝ ከባባድ ውሳኔዎች እንደሚያስፈልጉ በሚገባ ይረዳሉ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ውሳኔን እየሸሹ ህይወታቸውን በሙሉ በፍረሃትና በስጋት ጥግ ላይ ያሳልፋሉ። የውሳኔ ሰው እስካልሆናችሁ ድረስ ባላችሁበት ስፍራ ከመቅረትና በቁጪት ሸክም እራሳችሁን ከመጉዳት በቀር ምንም የምታተርፉት ነገር የለም። አዎ! ወስናችሁ ውጡ፣ ወስናችሁ ሸክማችሁን አራግፉ፣ በውሳኔያችሁ ነፃ ውጡ፣ በውሳኔያችሁ የሚጠቅማችሁን ጀብድ ፈፅሙ። መወሰን እያለባችሁ ሳትወስኑ በቀራችሁ ቁጥር ከትርፋችሁ በላይ ኪሳራችሁና የምታጡት ነገር እየበዛ ይመጣል። ዛሬ ከምትኖሩት ህይወት በይዘቱ፣ በጥራቱ፣ በትርፋማነቱም ሆነ በደስተኝነቱ የተለየው ህይወት ያለው ከአንዱ ወሳኝ ውሳኔያችሁ ጀርባ እንደሆነ አስታውሱ። ዛሬ የምትኖሩት ህይወት ወዳችሁም ሆነ ተገዳችሁ የወሰናችሁት ውሳኔያችሁ ውጤት ነው። ሀገር ብትቀይሩ፣ ስራ ብትቀይሩ፣ የምትከታተሉትን መርሃግብር ብትቀይሩ እንዲሁም ውሏችሁን፣ አስተሳሰባችሁንና የህይወት መርሆቻችሁን ብትቀይሩ ከለውጣችሁ ጀርባ ያለው ሁነኛ ግበዓት ቆራጥ ውሳኔያችሁ ነው። አሁን ወደፊት መጓዝ እንዳለባችሁ እያወቃችሁ እስካሁን ግን ወደፊት የሚያራምዳችሁን ውሳኔ ካልወሰናችሁ ከዚህ በላይ ጊዜ አታጥፉ፣ ልባችሁን አሸንፉ፣ ልማዳችሁን ተገዳደሩት፣ ለማንም ሳይሆን ለራሳችሁ ብላችሁ ወስኑ። አዎ! ጀግናዬ..! አንድ ውሳኔ ብቻ! የማቆም ወይም የመጀመር ውሳኔ፣ ህብረት የመፍጠር ወይም ከሚጎዳህ አካባቢ ነቆሎ የመውጣት ውሳኔ፣ ትምህርትን በአግባቡ መማር ካልሆነም ጨክኖ ፊትን ወደሌላ የማዞር ውሳኔ፣ በሱስ ላይ መጨከን ወይም ሱሱ ጨክኖ እንዲያጠፋህ የመፍቀድ ውሳኔ። ለሌላው የሆነው ሁሉ ላንተም ይሆናል ማለት አይደለም፣ ብዙ ሰውን ትርፋማ ያደረገ ቢዝነስ አንተንም ትርፋማ ያደርግሃል ማለት አይደለም፣ ጥቂቶችን ትልቅ ደረጃ ላይ ያደረሰ ትምህርት አንተንም ያደርስሃል ማለት አይደለም። ማንም ሰው ነፃ የሚወጣው የሰዎችን ተግባር በመከተል ሳይሆን የእራሱ የማያወላዳ ፅኑ አቋም ሲኖረው ብቻ ነው። የመጣው ቢመጣም ከውድቀትና በሰዎች ከመተቸት በቀር የሚመጣ ነገር የለምና በአዕምሮህ ተሸክመህ የምትሔደውን ውሳኔ በድፍረት ምድር ላይ አውርደው፣ አዕምሮህን ከግብ አልባው የማያባራ ሃሳብ ገላግለው። ጭንቀት ኖሮበት የተሻለ የህይወት ደረጃን የሚመኝ ሰው የለምና በቅድሚያ ባልተወሰኑ ውሳኔዎች የታጠረውን ጨንቀትህን ለመቀነስ ወስን፣ ለውሳኔህ ታመን፣ ወደምትመኘው የተለየ ህይወትም በድፍረት ጉዞ ጀምር። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Show all...
👍 11🔥 1
የደስተኛነት ምርጫ! ፨፨፨፨///////፨፨፨፨ አንደኛው ምርጫህ በኑሮህ የጎደለውን ነገር እየቆጠርክ ማዘንና መነጫነጭ ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ከሌለህና ከጎደለህ ነገር ላይ ትኩረትህን በማንሳት ባለህ ነገር ደስተኛ ሕይወትን ለመምራት መወሰን ነው፡፡   አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናገረ … "ከ13ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ስኳር የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ … ከ14ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት አባቶቻችን የኤሌክትሪክ ምድጃ ቀርቶ ከሰል የሚባል ነገር እንኳን አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች  ነበሩ …  ከ15ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን በቅጡ የተጋገረ ዳቦ የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ … ከ16ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ድንች የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ … ከ17ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ቡና፣ ሻይና ሾርባ የሚባሉ ትኩስ ነገሮች አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ … ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ኬክና የመሳሰሉት ጣፋጭ ምግቦች የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ … ከ19ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን እንቁላል፣ ክብሪትና የኤሌክትሪክ ኃይል የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ … ከ20ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ተዘጋጅቶ የታሸገ ምግብ የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …" (Unknown Source) በዚህ ላይ መጨመር ካለብን ከላይ በተዘረዘሩት ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ የነበሩ አባቶቻችንና እናቶቻችን ዛሬ የምናውቃቸውን የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ፡፡ ምናልባት ይህንን ጽሑፍ እያነበብክ ያለህበት የዓመቱ ስንተኛው ወር ላይ እንደሆነ ባላውቅም፣ እስቲ ዓመቱ ከገባ ጀምሮ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አለኝ በምትለውና ጎድሎኛል በምትለው ነገር አንጻር የነበረህን ዝንባሌ ለማስታወስ ሞክር፡፡ ምናልባት ስለሌለህ ነገር ስትበሳጭና ስሜትህ ሲቃወስ ራስህን አግኝተኸዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ አሁን በተያያዝከው ሕይወት ውስጥ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ያለማግኘትህ እውነታ ደስተኛነትህን እንድታዘገየው ከተጫነህ የሕይወት ዘይቤ ምርጫህን ማስተካከል እንዳለብህ ጠቋሚ ነው፡፡ የሆነውን ሳይሆን ያልሆነውን ማሰላሰል በርካታ ጠንቆች አሉት፡፡ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፣ በሌለንና በጎደለን ነገር ላይ ብቻ ማተኮር ታላቅ የሆነን የስሜት ቀውስ ያስከትላል፡፡ የመነሳሳትና ወደፊት ለመቀጠል የሚኖረንን ግለት ያበርድብናል፡፡ በሁኔታው የሚኖረንን የመነጫነጭ ባህሪ በመመልከት የቅርብ ወዳጆቻችን ቀስ በቀስ እየራቁንና ከእኛ ጋር ለመሆን ያላቸውን ፍላጎት እያጡ ይሄዳሉ፡፡ እንግዲህ ከእነዚህና ከመሰል አጉል ተጽእኖዎች ለመዳን ትክክለኛውን ምርጫ መከተል የግድ ነው፡፡ ዛሬ ለሌለህ ነገር እየሰራህና መለወጥ ወደምትፈልገው የተሻለ የባህሪይ ማንነት ለመለወጥ እየተጋህ ሳለህ፣ ባለህ ነገር ግን ደስተኛ መሆን ትችላለህ፡፡ /ከምርጫና ውሳኔ መጽሐፍ ገፆች/ ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Show all...
👍 27 1
ከሆንከው በላይ ነህ! ፨፨፨፨/////////፨፨፨፨ የቀድሞው ሞነክሴ የአሁኑ ፀሃፊ፣ ፖድካስተርና የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ ጄይ ሼቲይ (Jay Shetty) ይህን ይለናል "እንደ አማራጭ ለሚመለከትህ ሰው በፍፁም ቅድሚያ አትስጠው።" አዎ! ከሰዎች ጋር ባለን ግነኙነት ብዙዎቻችንን ከምናተርፈው ነገር የምናጠውና የምንከስርበት ሁኔታ ይበልጣል። ያላንተ ፍቃድ ማንም ሊጎዳህ ቢፈልግ ሊጎዳህ አይችልም። ለመጎዳት የምትፈቅደው፣ ሁን ብለህ የምትጠጋው፣ የምትቀርበው፣ የማይገባውን ስፍራ የምትሰጠው አንተ እራስህ ነህ። ለደቂቃ የማያስታውስህን ሰው ቀኑን ሙሉ እያሰቡ መዋል፣ ለአፍታም ትኩረት የማይሰጥህን ሰው በሙሉ ትኩረት መከታተል፣ አንዴም ሊያናግርህ ያልፈቀደን ሰው ደጋግመህ ደጅ መጥናት፣ መለመን፣ መለማመጥ ጤነኝነት ይመስልሃልን? እኔን ለማኝ እርሱን ተለማኝ፣ እኔን መራጭ እርሱን ተመራጭ፣ እኔን አሳቢ እርሱን ታሳቢ ያደረገው ነገር ምንድነው ብለህ እራስህን ጠይቅ። ምናልባትም ምላሽህ ደረጃህን እንድታውቅ ይረዳህ ይሆናል፤ እግረመንገዱንም እራስህን ለማግኘት ይጠቅምህ ይሆናል። ቻይ ነኝ ብለህ የማትወጣው ፉክክር ውስጥ አትግባ፤ ጊዜ አለኝ ብለህ የማይፈልግህን በመለማመጥ ጊዜህን አታባክን፤ ለምን አልተወደድኩም ብለህ እራስህን አትጣ። አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ከሆንከው በላይ ነህ፤ ሰዎች ከሚሰጡህ ክብር በላይ ይገባሃል፤ ካለህበት ስፍራ የተሻለ ቦታ ትደርሳለህ፤ ዛሬ ከናቁህ ሰዎች በላይ የሚያከብረህ ይመጣሉ፤ ዛሬ ሊያስቡህ ደቂቃ ካጠራቸው በላይ ለደቂቃዎች በመገኘትህ ትልቅ ተፅዕና የምትፈጥርበት ወቅት ይመጣል። ማንም እንደ አማራጭ ቢመለከትህ፣ ወደኋላ ቢገፋህ ቀዳሚ ምርጫው የሚያደርግህም እራስህን ያስቀደምክ እለት ከተፍ ይላል። ማንንም ልትወድ፣ ልታፈቅር፣ ልትወዳጅ፣ ልታደንቅ ትችላለህ በክብርህ እንዲመጣ፣ ማንነትህን እንዲገዳደር፣ አንተነትህን እንዲጋፋ ግን በፍፁም እንዳትፈቅድ። ሲቀር ለሚቀር ነገር የምትቃጠልበትና ሃፍረት የምትከናነብበት ምክንያት የለም። ክብር ያልወደደለት በገዛ ፍቃዱ ከክብሩ ይወርድ ዘንድ የግድ ነው። እያሳመመህ፣ እያሰቃየህ፣ እየገደለህ የምትሸከመው አላስፈላጊ ሸክም አይኖርም። የሚጣለውን ለመጣል፣ አላስፈላጊውን ለመራቅ፣ ጎጂውን ለመነጠል ድፍረት ይኑርህ። አዎ! ትልቁ ሃይል በእጅህ አለ። በእራስህ ጉዳይ ፈላጭ ቆራጩ፣ ወሳኙ አንተ ነህ። ክብርህ፣ ጥንካሬህ፣ ኩራትህ፣ ስብዕናህ፣ ማንነትህ አንተ ጋር ነው። ስትፈልግ የምታነሳው፣ ሳትፈልግ የምትጥለው እድገትና ውድቀቱ በእራስህ መልካም ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ወሳኝ የአንተነትህ መለኪያ ነገር አለህ። የእራስህን ክልል አብጅ፣ ቀዩን መስመር አብጅ፣ አልሚ መሳይ አፍራሽ፣ ወዳጅ መሳይ ጠላት፣ አፍቃሪ መሳይ ጎጂ እንዳይሻገረው በጥንቃቄ ጠብቀው። ማንነትህ የፍቃድህ ነፀብራቅ እንደሆነ አስተውል፤ የህይወት መርህህ አንተነትህንና ስብዕናህን እንደሚገነባ ተረዳ። ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Show all...
👍 28 8🥰 3👏 3🤣 1
ትርጉሙን አስብ! ፨፨፨/////////፨፨፨ ባንተም ይሁን በወዳጅህ፣ በቤተሰብህም ሆነ በቅርብ ዘመድህ ላይ የሚደርስ ነገር ሊያስከፋህና ሊያሳዝንህ ይችላል። ነገር ግን ሀዘንህ ለመፍትሔ የሚያቀርብህ፣ መከፋትህም ለእርዳታ የሚዘጋጅህ ሊሆን እንደሚገባ አስተውል። ከንፈር መጦ፣ እንባ አፍስሶ፣ አንገት ደፍቶ ብቻ ዝም ማለት ትርጉም የለውም። እውነተኛ አዛኝ ከሃዘኑ በላይ መፍትሔ የሚፈልግና እንባ ለማበስ የሚሯሯጥ ነው። ሰው ለሰው ምንያክል እንደሚያስፈልግ ብዙ ነገር ደርሶብህ አይተህ ይሆናል። ወዳጅህ ቢወድቅ እጅህን ዘርጋለት፣ ቢታመም አሳክመው፣ ቢቸገር ድረስለት፣ ሲደክመው አበረታው። በክፉ ጊዜ አብሮህ የሚሆን ወዳጅህ የምርም የልብ ወዳጅህ ነው፤ በልብህ የሚኖረው ስፍራ እጅጉን የተለየ ይሆናል። በውስጥህ የሚፈጥረው ስሜት ሁሌም መልካምና ደግ ሰው እንድተሆን ያደርግሃል። አዎ! ጀግናዬ..! ምንም ቢገጥምህ፣ ምንም ቢደርስብህ ትርጉሙን አስብ። የደረሰብህ በደል ሳይሆን የምትሰጠው ምላሽ የበደሉን ትርጉም ያዛባል፤ ሃይል ባይኖረው እንኳን ሃይል ይሆነዋል፤ ጉዳቱ ያነሰ ቢሆንም የከፋ ያደርገዋል። ማንም ቢበድልህ ካንተ መበደል በላይ እርሱን ለበደል ያበቃውን ምክንያት ለመረዳት ሞክር። የሰው ልጅ በጤናው ክፉ አይሆንም፤ በሰላም በሰው ውድቀት ጮቤ አይረግጥም፤ ያለምክንያት መጥፎ ነገርን ለሰው አይመኝም። ነገሮች ሁሉ በምክንያት ከመሆናቸው አንፃር የእያንዳንዱ ሰው ደርጊት የጀርባ ታሪክ ይኖረዋል። ሰውነት በእራሱ መልካምነት ነውና ደግ የሚያደርግን መልከመልካም ሰው ጀርባውን ማጥናቱ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። የክፋት ካባ የለበሰ፣ በቅናት የታወረ፣ በጥላቻ የተተበተበ ሰው ግን በጤናው እዚህ ጤና ቢስ ስሜት ውስጥ እንደማይገባ እርግጥ ነውና ስለሁኔታው መመርመር ተገቢ ነው። አዎ! ጊዜያዊ ድርጊታቸው የሰዎችን ማንነት አይገልፅም፤ ማንም ቢሆን ባለፈ ታሪኩ አይወከልም። የትናንት ጭካኔያቸውን በዛሬ ርህራሔ የተኩ ሰዎች አሉ፤ የትናንት ምሬታቸውን በዛሬ ምስጋና የቀየሩ ሰዎች አሉ። የሰው ልጅ በህይወት እስካለ ድረስ ህይወቱን በሙሉ በተዓምር የተሞላ ማድረግ ይችላል። በማንም ከመፍረድህ በፊት፣ የማንንም ድርጊት የተለየ ትርጉም ከመስጠትህና የማይሆን ስም ከመለጠፍህ በፊት ሰውዬውን መርምር፣ ጀርባውን አጥና፤ የድርጊቱን ትርጉም አስብ። በቻልከው መጠን ሰዎች እንዲረዱህ የምትፈልገውን ያክል ሰዎችን ለመረዳት ሞክር። ስለሆነው የምትሰጠው ትርጉም እንዳያጠፋህ ተጠንቀቅ። ዋጋ የሚያስከፍልህ፣ ወዳልተገባ መንገድ የሚመራህ፣ ለማይሆን አኳሃን የሚያዳርግህ የደረሰብህ ነገር ሳይሆን የሰጠሀው ትርጉም እንደሚሆን አስተውል። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Show all...
👍 18 5👏 2
እጅ አትስጡ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE 📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/CPmho7jgeP0?si=-p2K2uLLODq6eJF6
Show all...
ትጋት፣ ብርታት፣ ጀብደኝነት ሁነኞቹ ተፅዕኖ ፈጣሪ እሴቶች፣ ወደኋላ እንዳትሉ!| ድንቅ የህይወት ትምህርት | Inspire Ethiopia | MIKRE AIMRO

ያለ መሱአትነት የሚመጣ ድል የለም። @mikre_aimro ቪድዮውን 👍 LIKE ስለምታደርጉና ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! Motivational Speech in Amharic | Amharic Motivational Video | Ethiopian motivation | amharic motivation | አነቃቂ ንግግሮች | አነቃቂ ምክሮች | inspire Ethiopia | dawit dreams | shanta | daggy's life class | manyazewal podcast | inspire podcast | dawit dreams podcast #making_money #sidehustle #business #ethiopianmotivation #inspire_ethiopia #inspirationalvideo MOTIVATION + DISCIPLINE = UNWAVERING SUCCESS! @mikre_aimro ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ይመልከቱ፡ 👇👇

https://youtu.be/HntYXoAUrN4

https://youtu.be/BgtOdHqO_1U

ቪድዮውን ላይክ 👍 ማድረግ እንዳይረሱ! ቻናላችንን ሰብስክራብ ያድርጉ! የደውል ምልክትን ይጫኑ! Comment ያስቀምጡልን!እናመሰግናለን! 🙏🙏🙏 Social Media: INSTAGRAM:

https://www.instagram.com/epha_aschalew

YOUTUBE:

https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1

FACEBOOK:

https://www.facebook.com/EthioMentalCounsel

TELEGRAM:

https://t.me/MentalCounsel

TIKTOK:

https://www.tiktok.com/@mentalcounsel

Music from #InAudio:

https://inaudio.org/

Track Name. inaudio - Infraction - Rebellion inaudio - Infraction - Distance inaudio - Infraction - Slow Motion inaudio - Infraction - MokkaMusic - Calmness motivational አነቃቂ ጥቅሶች አነቃቂ ንግግሮች አነቃቂ ዘፈኖች አነቃቂ አጭር ልቦለድ አነቃቂ ቪዲዮ motivational ethiopia motivational music motivalional motivationalmotivalional motivational speech motivalional songs motivational short story motivational video ethiopia yosan getahun oromo music 2023 motivational videos for students tointerview study hard motivalional songs with lyrics motivate me speaker motivate little mix motivation motivate motivation video motivate molivate motivational eshetu manyazewal motivational manyazewal eshetu manyazewal eshetu in schoolkeysofmoon inspire ethiopia inspire people manyazewalinspire ethiopia new video inspire ethiopia new inspire ethiopia motivation Anki andbet,Manyazewal,Dawit dreams,እነቃቂ,አላማ,Inspire,Motivated,Motivate 2 ethiopia EBS Motivate ethiopia,Inspire Ethiopia,Ethiopia,Success,Motivations,Motivational,Motivation,Manyazewal eshetu,motivational video,motivational speech,motivation,motivational songs,abel birhanu

4🔥 2👍 1
ኢጎህን ቅበረው! ፨፨፨//////፨፨፨ ትንሽ ሰረትህ ስትደነቅ እራስህን አትኮፍስ፣ የሆነ ሰው በደገፍክ ቁጥር ውሃ አይንካኝ አትበል፣ ከብዙ ሰው የተሻለ ህይወት መኖር ስትጀምር ከእኔ በላይ ሰው የለም አትበል። እራስህን ስታመፃድቅ ሰው እንኳን አይቶህ ከማያወጣህ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንዳትገባ ተጠንቀቅ። ኢጎህን ካልቀበርክ፣ ይሔንን በባዶ ትምክህት፣ በትንሽ መኮፈስህን ካላቆምክ ቢዘገይም ኢጎህ እራሱ አንተን ቀብሮህ አፈር እንደሚያለብስህ አትጠራጠር። ጥቂት የማይባሉ ዝነኞችን ተመልከት በዋናነት ከከፍታቸው እያምዘገዘገ ወደታች የሚወረውራቸው አቅም ማጣታቸው፣ እውቀት ማጣታቸው ወይም ከህሎት ማጣታቸው አይደለም። ትንሽ ሰሩና ልባቸው አበጠ፣ ከእኔ በቀር ሰው የለም አሉ፣ ያዙኝ ልቀቁኝ አበዙ፣ ሰውን መናቅ ጀመሩ፣ እራሳቸውን መኮፈስ ጀመሩ፣ ያለማቋረጠ ኢጓቸውን በትምክህትና በባዶ ትርክት አሳበጡት እርሱም በስተመጨረሻ እያምዘገዘገ ወደ ጥልቁ የውድቀት ጉድጓድ ወረወራቸው። በገዛ እጃቸው የጋለ ብረት ጨበጡ፣ ብረቱም የጋለ ነውና እጃቸውን ክፉኛ ጎዳው። ማንም ከእራሱ ኢጎ የሚበልጥ ክፉ ጠላት የለውም፣ ማንም ከእራሱ የሚበልጥ መሰናክል የለውም። አዎ! ጀግናዬ..! የላቀ ከፍታን ከፈለክ፣ ዓለምህ እንዲቀየር፣ ማንነትህ እንዲታነፅ፣ አንተነህ እንዲጎለብት ከፈለክ ምንም ሳትል ኢጎህን ቅበረው፣ እኔ ብቻ ልብላ፣ እኔ ብቻ ልደመጥ፣ እኔ ብቻ ልታይ፣ እንዲሁ እንደ አህያዋ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ከሚል አጉል ቅጥ ያጣ እራስወዳድነትና በግል ፍቅር መታወር በፍጥነት ተላቀቅ። ከልክ በላይ እኔ እኔ የሚሉ ሰዎች ደጋግመው የተመኩበት እኔያቸው ከምንም ሲያድናቸው አልተመለከትንም። እኔ ብቻ ብለው ተኮፍሰው አንድ ትንሽ ፈተና ሲገጥማቸው ተነፍቶ እንደተነፈሰ ፊኛ ተኮማትረው ይቀመጣሉ። እኛ ማለት ማንን ገደለ? ማንንም። ትሁት መሆን፣ ከክብር ወርዶ ዝቅ ብሎ ማገልገል ምን አሳጣን? ምንም። ተወዳጁ Ego is the Enemy የተሰኘው መፅሐፍ ይሔንን ሃይል ያለው ቁብነገር አስፍሯል፦ "ዓለም እውነታውን ታሳይሃለች፣ ነገር ግን ማንም እንድትቀበለው አያስገድድህም።" አንተ ተቀበልካትም አልተቀበልካትም፣ ፈፀምካትም አልፈፀምካትም እውነት ሁሌም እውነት ነች። በኢጎህ ጥላ ስር እየኖርክ ደግሞ መቼም እውነትን ልትቀበል ብሎም ልትኖራት አትችልም። አዎ! የኢጎ ጉዞ ወዴትም የማይደረግ፣ እዛው አንድ ቦታ የሚያስቀር ጉዞ ነው። "እኔ እንዲ ነኝ፣ እኔ እንደዛ ነኝ፣ ይሔንን ላደርግ ነው፣ በዚህ ልወጣ ነው፣ በዛ ልገባ ነው።" እያልክ እራስህን ትቀባባ ይሆናል ምድር ላይ ያለው ነገር ግን ምንም ባዶ ነው። ሰው ነህ ከሰው ጋር መኖር አለብህ፣ ሰው ያስፈልግሃል ስለዚህ አብዝተህ እኔነት ላይ መለጠፍ አቁም፣ ከልክ በላይ ፈጣሪህን ረስተህ፣ ያደረገልህን ዘንግተህ እራስህን እንደ ጣዖት የምታመልከው ኢጎስቲክ (Egoist) ሰው አትሁን። ለእራስ ክብር መስጠት፣ እራስን ማበርታትና ማደናነቅ የለና አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ከልክ ሲያልፍ ቀይ መስመር ሲያል፣ ሲደጋገምና በጣም ሲበዛ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበዛል። የኢጎህ ተጠቂ አትሁን፣ ረጅሙን የህይወትህን ጉዞ እራስህ በቀላሉ አታደናቅፈው፣ ያንተ ዓለም የምትደምቀውም የምትጠፋውም ባንተ ብቻ እንደሆነ አስተውል። ቀና ማለትን በቀናነት፣ የእራስ ፍቅርንም ሌላውን በማይጎዳና አንተንም በማያደናቅፍ መንገድ ተግብረው። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Show all...
👍 19🔥 9 5👏 2😍 1
ቅድስናችሁን አስቡ! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ አሁን ምንም ሁኔታ ውስጥ ልትሆኑ ትችላላችሁ ነገር ግን ይብዛም ይነስም፣ አውሯቸውም አታውሯቸውም፣ ቅረቧቸውም አትቅረቧቸውም በዙሪያችሁ ግን ሰዎች አሉ። አንዳንዴ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች የማይጠቅሙንና ስንፈልጋቸው ከጎናችን ካልሆኑ አስፈላጊ እንዳልሆኑ ልናስብ እንችላለን። ነገር ግን የሰዎች ጥቅም ሁሌም ለእኛ የሚታይ የማይሆንበት ጊዜም ይኖራል። ምንም ባያደርጉልን እንኳን ከለላዎቻችን ናቸው፣ በስማቸው ብቻ ይጋርዱናል፣ በመኖራቸው ብቻ ይጠብቁናል። ሰው የላቸውም ተብለው ብዙዎች ሲበደሉና ሲገፉ እንመለከታለን። ምናልባት ሲገፉ ከፊታቸው ቆሞ ግፊታቸውን የሚታገልላቸው ሰው እንኳን ባይኖር በስም ብቻ እገሌ አላቸው፣ እንትና እኮ ቤተሰባቸው ነው ቢባል እንኳን ከብዙ ጫናዎች ሊድኑ ይችላሉ። ሰው አትግፉ፣ እያጠፋም ቢሆን መኖሩን ምረጡ፣ እየገፋችሁም ቢሆን ክፉ አትመኙለት፣ ውድቀትን አታስቡበት። ማንንም እንደ ስራው የሚዳኘው የሰማይ አምላክ ብቻ ነው። ሰው ሰውን ልቅጣው ቢል እንኳን ቅጣቱ የሚገባው ላይሆን ይችላል። እግዚአብሔር አዋቂ እንደሆነ የምታምኑ ከሆነ ያጠቃችሁን ለማጥቃት ከመዘጋጀት በላይ ሁሉን ለእርሱ ትሰጣላችሁ። አዎ! ቅድስናችሁን አስቡ! የሰዎች በዙሪያችን መኖር ቅድስናችን ነው፣ የእኛ በሰዎች መታሰብ በራሱ በረከታችን ነው። ሰው የለመዱ፣ ሁሌም ትኩረት የሚስቡ ሰዎች መረሳት ያስፈራቸዋል፣ የለመዱት አይንና ጆሮ እንዳይነፈጋቸው አብዝተው ይጨነቃሉ። ጆሮ የሚሰጣችሁ ሰው ለምን አንድ አይሆን ለምን ምንም የማያውቅ ህፃን አይሆንም ጉዳያችሁን ጉዳዩ አድርጎ፣ ችግራችሁን ችግሩ፣ ደስታችሁንም ደስታው አድርጎ ቀርቧችኋልና በሰዓቱ ከምንም የሚበልጠው የፈጣሪ ስጦታችሁ እርሱ ነው። አንዳንዴ የሰው ልጅ ለምን የማይመለከተው ጉዳይ ውስጥ ገብቶ እንደሚያቦካ ታውቃላችሁ? አንድ ግራ ስለገባው ወይም ትኩረትን አብዝቶ ስለተጠማ ነው። በዚህ የሩጫ ዘመን ትኩረት ማግኘትን የመሰለ ትልቅ ሃይል የለም። በሆነ ሰው ስለመገፋታችሁም ስለመወደዳችሁ ብዙ አትጨነቁ፣ ይልቅ ሰውዬው ይሔንን ለምን እንደሚያደርግ ለማወቅ ሞክሩ። እየመጡ በሚሔዱ፣ ስትጠብቋቸው በሚቀሩ ሳትጠብቋቸውም በሚመጡ ሰዎች ብዙ አትገረሙ፣ ይልቅ ከዚህ ባህሪያቸው በስተጀርባ ያለውን ድክመታቸውን ለማወቅ ሞክሩ። አዎ! ጀግናዬ..! ሰውነት ሁለት ገፅ አለው። የድካምና የጥንካሬ ገፅ። የሰው ልጅ ደግሞ በህይወት እስካለ ድረስ ሁሌም ቢሆን የማንም ድክመት ያለመሆን መርጫ አለው። በህይወት መኖርህ የሚጠሉህን ጨምሮ ለብዙዎች በረከት ነው፤ ለአንተም እንዲሁ የምትጠላቸውን ጨምሮ የሰዎች በዙሪያህ መኖር በረከትህ ነው። ማን መቼ እንደሚቀየር አታውቅም፣ ማንም እንዴት ይህቺን ዓለም እንደሚሰናበት አታውቅም። በቻልከው አቅም የሰዎች ህመም ምክንያት አትሁን፣ ቂምን አዝለህ ለበቀል እየተዘጋጀህ አትኑር። በቻልከው መጠን ለማንኛውም ሰው መልካም ለመሆን ሞክር። የቅድስናህ ምንጭ፣ የበረከትህ ምክንያት፣ የትሩፋትህ መንስኤ የሆነውን የሰው ልጅም በቅርበት ያዘው፣ ብዙም እንዳይርቅህ አድርግ። ክፉ ቀን ቢያስተዛዝብም መልካም ቀን ግን አንድ ያደርጋልና የሚሆነው ሆኖ ቢያልፍም ፈፅሞ ምግባርህን ከማስተካል፣ መልካም ስብዕናህንም ከማጉላት አትቦዝን። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Show all...
15👍 10🔥 2🥰 2👏 1
ከምሬት ውጡ! 👍LIKE ✍️ COMMENT  SUBSCRIBE 📣SHARE 🙏 https://youtu.be/94WVdW9m4dQ?si=m-WAyB04WjTFCD0F
Show all...
አማራሪ አትሁኑ፤ ህይወት በጣም አጭር ነች! | ድንቅ የህይወት ትምህርት | Inspire Ethiopia | shanta | MIKRE AIMRO

ብዙ ጊዜ የቀራችሁ ቢመስላችሁም ያላችሁ ትንሽ ጊዜ ነው። @mikre_aimro ቪድዮውን 👍 LIKE ስለምታደርጉና ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! Motivational Speech in Amharic | Amharic Motivational Video | Ethiopian motivation | amharic motivation | አነቃቂ ንግግሮች | አነቃቂ ምክሮች | inspire Ethiopia | dawit dreams | shanta | daggy's life class | manyazewal podcast | inspire podcast | dawit dreams podcast #making_money #sidehustle #business #ethiopianmotivation #inspire_ethiopia #inspirationalvideo MOTIVATION + DISCIPLINE = UNWAVERING SUCCESS! @mikre_aimro ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ይመልከቱ፡ 👇👇

https://youtu.be/HntYXoAUrN4

https://youtu.be/BgtOdHqO_1U

ቪድዮውን ላይክ 👍 ማድረግ እንዳይረሱ! ቻናላችንን ሰብስክራብ ያድርጉ! የደውል ምልክትን ይጫኑ! Comment ያስቀምጡልን!እናመሰግናለን! 🙏🙏🙏 Social Media: INSTAGRAM:

https://www.instagram.com/epha_aschalew

YOUTUBE:

https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1

FACEBOOK:

https://www.facebook.com/EthioMentalCounsel

TELEGRAM:

https://t.me/MentalCounsel

TIKTOK:

https://www.tiktok.com/@mentalcounsel

Music from #InAudio:

https://inaudio.org/

Track Name. inaudio - Infraction - MokkaMusic - Calmness inaudio - Infraction - Majestic Vision motivational አነቃቂ ጥቅሶች አነቃቂ ንግግሮች አነቃቂ ዘፈኖች አነቃቂ አጭር ልቦለድ አነቃቂ ቪዲዮ motivational ethiopia motivational music motivalional motivationalmotivalional motivational speech motivalional songs motivational short story motivational video ethiopia yosan getahun oromo music 2023 motivational videos for students tointerview study hard motivalional songs with lyrics motivate me speaker motivate little mix motivation motivate motivation video motivate molivate motivational eshetu manyazewal motivational manyazewal eshetu manyazewal eshetu in schoolkeysofmoon inspire ethiopia inspire people manyazewalinspire ethiopia new video inspire ethiopia new inspire ethiopia motivation Anki andbet,Manyazewal,Dawit dreams,እነቃቂ,አላማ,Inspire,Motivated,Motivate 2 ethiopia EBS Motivate ethiopia,Inspire Ethiopia,Ethiopia,Success,Motivations,Motivational,Motivation,Manyazewal eshetu,motivational video,motivational speech,motivation,motivational songs,abel birhanu

👍 3👏 2 1🌭 1