cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

NIKAOHODOS MINISTRY

ይህ የንቃኦሆዶስ መንፈሳዊ የወንጌል አገልግሎት የቴልግራም ቻናል ነው፣ ከዝህ መንፈሳዊ የወንጌል አገልግሎት ቻናል ✅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶችን ✅ ጠቃም መልእክቶችን ✅ መንፈሳዊ መጽሐፍቶችን ✅ ነገረ መለኮታዊ ዳሰሳዎችን ✔️ ጨምሮ ለሎች ክርስቶስን በመምሰል ለማደግ የምጠቅሙ በርካታ ክርስቲያናዊ አግልግሎቶችን ከዝህ የወንጌል አገልግሎት ቻናል ያገኛሉ። በግል ለማግኘት ከፈለጉ @Yimesgenn

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
176
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#የቤተክርስትያን_ታርክ #የስህተት_አስተምህሮዎች_በሐዋርያት_ዘመን #ክፍል_ሃያ_አንድ #1ኛ_ግኖስቲዝም ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ መንፈስ የሆነ ሰላም፥ ጸጋና ምህረት ይብዛላችሁ። ግኖሲስ ከሚለው ቃል የወጣው የእንግዝሊዘኛው ግኖስቲዝም ትርጓሜው እውቀት ማለት ነው። በሐዋርያት ዘመን ላይ እውቀት አለን በማለት የሚመኩ ሰዎች በስሕተት ትምህርት ተጠልፈው ወድቀዋል። በ1ኛ ዮሐ 4፥3 ላይ ሐዋርያው በግልጽ እንዳስተማረው እነዝህ ሰዎች ክርስቶስ በሥጋ አልመጣም፥ ትክክለኛ ሰው አይደለም ይሉ ነበር። ሐዋርያው ዮሐንስ ግን ይህንን ትምህርት ክርስቶስን የሚቃወም ትምህርት ስል ግልጾታል። እንድሁ እነዝህ ሰዎች ትንሳኤ ሙታንን ይክዳሉ። ጳውሎስ ለጢሞትዎስ በፃፈው መልእክት 2ኛ ጢሞ 2፥18 ላይ እና ለቆሮንቶስ ሰዎች በፃፈው 1ኛ ቆሮ 15፥12-20 ላይ እነዝህ ሰዎች ምን እንደምያስተምሩ በግልጽ ጽፏል። የሥጋ ትንሳኤ ፈጽሞ እንደለለ እና ይህ ቀድሞ እንደሆነ በመግለጽ ወደፊት የመንፈስ ትንሳኤ ብቻ እንዳለ ያስተምሩ ነበር። ጳውሎስ ግን ይህንን ትምህርት የክርስቶስን ሞት ከንቱ የምያደርግ ትምህርት ስል አውግዞታል። እነዝህ ሰዎች መላእክት ሰውን ከአምላክ ጋር ያስታርቃሉ በማለት ይሰግዱላቸዋል። ጳውሎስም ይህንን በግልጽ ተቃውሞታል። ቆላ 2፥18 እንድሁ ከአይሁድ እምነት ብዙ ባሕሎችን በመውሰድ የተከለከለ ምግብና መጠጥ አለ ከማለት ጅምሮ ወንዶችና ሴቶች እንደ ምኩራብ ልማድ በአምልኮ ግዜ በጸሎት ቤት ለየብቻቸው ሊቀመጡ ይገባል ይሉ ነበር። እንድሁ የብሉይ ኪዳናት ባአላትን የአድስ ኪዳን መልክ በመስጥት መከበር አለበት ይላሉ። ጳውሎስ ግን እነዝህ ነገሮች ሁሉ ከክርስትና ጋር የሚያያዙ አለመሆናቸውን ገልጧል። ቆላ 16፡17 ምግብና መጠጥ ሁሉ መልካም ነው የሚወሰድና የሚጣል ተብሎ አይከፈል። ጢሞ 4፥3-5 እነዝህ አካላት ሥጋ ቅዱስ ነው እና ርኩስ ነው በሚሉ ከንቱ አመለካከቶ እራሳቸውን ከፍለዋል። ቅዱስ ነው ባዮች ኃጢአት ብንሰራ ሥጋችን አይረክስም በሚል ዕምነት በብዙ ነውሮች የማጠናሉ። 1ኛ ቆሮ 5፥1-9 ለሎችም ርኩስ ነው በሚል ሰበብ ገዳም በመግባትና በመሰል ሥራዎች ሥጋቸውን ይጎዳሉ። 1ኛ ቆሮ 6፥9-10 እነዝህ ሰዎች በዝህ ዕምነታቸው ጋብቻን እስከ መከልከል የሚደርስ እርምጃ ይወስዳሉ 1ኛ ጢሞ 4፥3 ሐዋርያ ጳውሎስ ግን ጋብቻ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን አስተምሯል። የጌታ ሰላም የአብ ፍቅር የመንፈስ ሕብረት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን ይቀጥላል። ከወንድማችሁ @Yimesgenn 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 📜📜📜 ይ🀄️ላ🀄️ሉ 📜📜📜 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @NIKAOHODOSMINISTRY @NIKAOHODOSMINISTRY
Show all...
#የቤተክርስትያን_ታርክ #ሥረዓተ_ቤተክርስትያን #ክፍል_ሃያ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ መንፈስ የሆነ ሰላም፥ ጸጋና ምህረት ይብዛላችሁ። ቤተክርስትያን አሁን ባለንበት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደት አይነት ሥረዓትን ትከተላለች? በአሁኑ ግዜ ቤተክርስትያን ለምን በብዙ ሥረዓቶች ተወጠረች? እነዝህ ሁሉ ሥረዓቶች በሐዋርያት ዘመን ባለች ቤተክርስትያን ይከናወኑ ነበር? ብለን ለመጠየቅ አስቀድመን የሐዋርያት ቤተክርስትያንን ታርክ ማወቅ ይገባናል። ሐዋርያቶች እየሞቱ ስመጡና ለሎች ክርስትያኖች ቤተክርስትያንን ስረከቡ ፍጹም በሆነ መንገድ አልነበረም። ዘመኑ እየገፋ ሲመጣ የተሳሳተ መንገድ የተከቱሉ አብያተክርስትያናት ነበሩ። ሐዋርያው ጴጥሮስ በአንደኛ መልእክቱ 4፥10 ላይ ክርስትያኖች ሁሉ የጸጋ ስጦታ እንደተሰጣቸው ይናገራል። ክርስትያኖች በሐዋርያት ዘመን ሆነ ከሐዋርያት ቀጥሎ እንደ አንድ በተሰብ እጅግ ይፋቀሩ ነበር። በእነርሱ መካከል አዋቂ የለም፥ የበላይ የለም፥ አዛዥ የለም ሁሉም በአንድነት እንደ አንድ መልካምና ደስተኛ ቤተሰብ በፍቅር ይኖሩ ነበር። ይህ ሁሉ በለሎች ዘንድ ያስመሰግናቸው ነበር። ክርስርትያኖች በሐዋርያት ዘመን ለጸሎት፥ ለመዝሙር፥ ቃሉን ለመስማት፥ ለቅዱስ ቁርባን ይሰበሰቡ ነበር። ከመካከላቸው የታመመ ሰው ካለ በሕመምተኛው ቤተ በመጸለይ ቅዱስ ቁርባንን እንድካፈል ያደርጋሉ። ለጸሎትም የራሳቸው የሆነ ቋሚ ቤት እስክያገኙ ድረስ በየአማኞች ቤት ይሰበሰቡ ነበር። ቅዱስ ቁርባንን ለመካፈል ስሰበሰቡ ሥረዓቱን የምያከናውኑ ምዕመናን ነበር። በዘመን ብዛት ይህንን የምያከናውኑ ዲያቆናትና ሽማግሌዎች ሆኑ። ይህም እየቀረ በመምጣት ቄሶችና፥ ጳጳሳት ብቻ ይህንን ሥረዓት እንድያከናውኑ ተደረገ። ይህ ክስተት የምያሳየነ ቤተክርስትያን በአድስ ኪዳን አስተምህሮ ያልተደገፉ ተግባራትን እየተለማመደች መምጣቷን ነው። ይሁን እንጅ ይህ ተግባር በግዜ ርዝመት እውነትና ትክክል መስሎ ለክርስትያኖች በመታየቱ እስከ አሁን ድረስ ዘልቆ ልደርስ ችሏል። የጌታ ሰላም የአብ ፍቅር የመንፈስ ሕብረት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን ይቀጥላል። ከወንድማችሁ @Yimesgenn 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 📜📜📜 ይ🀄️ላ🀄️ሉ 📜📜📜 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @NIKAOHODOSMINISTRY @NIKAOHODOSMINISTRY
Show all...
#የቤተክርስትያን_ታርክ #አባ_ሰላማ_ከሣቴ_ብረሃን_የኢትዮጵያ_መጀመሪያው_የወንጌል_ሰባክ_ፍሬምናጦስ #ክፍል_አሥራ_ዘጠኝ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ መንፈስ የሆነ ሰላም፥ ጸጋና ምህረት ይብዛላችሁ። ታርኩ እንድህ ነው:- መሮጵዮስ የተባለ አንድ የግሪክ ነጋዴ ለንግድ ከሌሎች ሰዎች ጋር ወደ ሕንድ እየተጓዘ በኤርትራ ባሕር ወደብ ለእረፍት ባለበት ግዜ ጠላት ተንስቶ ከሁለቱ ልጆች በስተቀር ሁሉንም ሰዎች ገደለ። የአከባቢው ሰዎችም ለእነዝህ ሁለት ወጣቶች በማመዘን በሕይወት እንድኖሩ ፈቀዱላቸው። እነዝህን ወጣቶች ክርስትያኖች ነበሩ፥ የወጣቶቹ ስም የአንደኛው አድስዮስ ስሆን የሁለተኛው ፍሬምናጦስ ነው። ሁለቱም ወጣቶች ወደ አክሱም መንግስት ተጓዙ። ብዙም ሳይቆይ የአክሱም መንግስት ንጉስ ይሞታል። ንግስትቱም ዙፋኑን ማስተዳደር ጀመረች። በግዜው ንግስና ከባድ ስለሆነባት እነዝህን ሁለት ግሪካዊያንን አድስዮስንና ፍሬምናጦስን በማስተዳደር እንድረዱዋት ጠየቀች። እነርሱም ፈቃደኞች በመሆናቸው ሁለቱም ክርስትያኖች በአረማዊው የአክሱም መንግስት አስተዳደር ሁነው ያገለግሉ ጀመር። ይህንን አጋጣም በመጠቀም ፍሬምናጦስን ወንጌልን መስበክ ጀመረ። ለብዙዎች ክርስቶስን መሰከረላቸው። ክርስትናም በአክሱም መንግስት እየተስፋፋ ሲመጣ ፍሬምናጦስ ወደ እስክንድርያ በመጓዝ የእስክንድርያውን ሊቀ ጳጳስ አትናቴዎስን ተገናኝቶ ለኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ጳጳስ እንድሾምላት ጠየቀው። ሊቀ ጳጳሱም ከእርሱ የተሻለ ሰው ባለማግኘቱ በ329 ዓ.ም ፍሬምናጦስን መርቆ ወደ ኢትዮጵያ ላከው። ፍሬምናጦስም የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳ ሆኖ ተሾመ። ፍሬምናጦስም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ የስብከት አገልግሎቱን አጠናክሮ ቀጠለ። በኢትዮጵያ ታርክም አባ ሰላማ ከሣቴ ብረሃን የሚል ሲያመን አግኝቷል። ትርጉሙም ብርሃንን የገለጠ የሰላም አባት ማለት ነው። ፍሬምናጦስ ከሞተ በኋላም ሌላ ጳጳስ ተሹሞ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ገባ። ይህም ጳጳስ አቡነ ምናስ ይባላል። ኢትዮጵያ በ1951 ዓ.ም ኢትዮጵያዊ ጳጳስ እስክትሾም ድረስ ጳጳስት በሙሉ ይላኩ የነበሩት ከግብጽ ነበር። ከዝህም ባሻገር ተሰዓቱ ቅዱሳት ወይም ዘጠኙ ቅዱሳን የተባሉ ከሶርያ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ወንጌን በሥፋት እንደሰበኩ የታርክ መጽሐፍት ይተርካሉ። በዝህም ስብከት ብዙ አብያተክርስትያናት ተቋቁመዋል። መጽሐፍ ቅዱስም ከብኲረ ቋንቋው ወደ ዘመኑ ቋንቋ ወደ ሆነው ወደ ግዕዝ እንድተረጐም ተደርጓል። የጌታ ሰላም የአብ ፍቅር የመንፈስ ሕብረት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን ይቀጥላል። ከወንድማችሁ @Yimesgenn 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 📜📜📜 ይ🀄️ላ🀄️ሉ 📜📜📜 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @NIKAOHODOSMINISTRY @NIKAOHODOSMINISTRY
Show all...
#የቤተክርስትያን_ታርክ #ክርስትና_በአክሱም_ዘመነ_መንግስት_በንጉስ_ኢዛና_ዘመን_ወደ_ኢትዮጵያ_ስለመግባቱ። #ክፍል_አሥራ_ስምንት ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ መንፈስ የሆነ ሰላም፥ ጸጋና ምህረት ይብዛላችሁ። ክርስትያና በኃያሏ ሮም ውስጥ በብዙ ፈተናዎች አልፎ በቆስጠንጢኖስ ዘመን የመንግስት ኃይማኖት እስክሆን ድረስ በለሎች አገሮችም ወንጌል ይስፋፋ ነበር። ይህም በምስራቅ በኩል እስከ ፋርስ፥ እስከ ሕንድ ድረስ ያሉት አገሮች ድረስ ወንጌል ይሰበክ ነበር። በደቡብም እስከ አረብ ድረስ ወንጌል ተሰብኮ ብዙ አብያተክርስትያኖች ተቋቁመው ነበር። ይህም የወንጌል ስብከት በመስፋፋት እስከ ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ድረስ ደርሰዋል። በሐዋርያት ሥራ 8፥26 ላይ የተጠቀሰው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ታርክ እናገኛለን። ይህ ጃንደረባ በወንጌላዊው ፊልጶስ እጅ ተጠምቆ ወደ ሐገሩ እንደተመለሰ ተገልጿል። ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ ተብላ የተጠራችው ይህች አገር የአሁኗ የምስራቅ አፍርቃዋ ኢትዮጵያ እንዳይደለች ብዙ የታርክ ምሁራን ይስማማሉ። ብዙዎችም እንደምሉት ከሆነ ህንደኬ የተባለችው ንግስት ከአሁኗ ኢትዮጵያ በስተ ሰሜን ብኩል የምትገኝ ኖባ የምትባል አገር ስትሆን መናገሻ ከተማዋ መርዌ ነው። ይህም አሁን ላይ የሰሜን ሱዳንን ጭምሮ ምስራቃዊ ኤርትራን የምያካትት ግዛት ነው። ይሁን እንጅ በዝህች አገር እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ አረማዊያን ነግስታት እንደነገሱ ከታርክ መዛግብት እንረዳለን። የአክሱም ዘመነ መንግስት መናገሻውን በአሁኗ አክሱም ከተማ ያደረገ መንግስት ነበር። በዝህም መንግስት እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ያሉ የጣኦት አምልኮዎች እንደሆኑ ከሥነ ሕንፃ ጥበቦችና ከሥነ ጹሑፎች በዝህ ዘመን ብዙ ማስረጃዎች ተገኝተዋል። ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ በዘመኑ የአይሁድን እምነት ያቀፈች አገር መሆኑ የማይካድ ሐቅ ነው።ብዙዎች በአፈታርክና በፍተሐ ነገሥት መጽሐፍ የተጠቀሰውን ታርክ ዋብ አድርገው በንግስት ሳብ ልጅ ቀዳማዊ ሚኒልክ አማካይነት የአይሁድ እምነት ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ብናገሩም፥ ብዙ የሥነ ታርክ ሊቃውንት ግን በደቡባዊ ግብጽ አማካይነት ይኖሩ በነበሩ ብዙ የአይሁድ ማህበረሰብ አማካይነት ይህ እምነት ሳይስፋፋ እንዳልቀረ ይገምታሉ። ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ ቀደም ብሎ የአይሁድ እምነት አልፎ አልፎ ብኖርም፥ የአክሱም መንግስት ግን አረማዊ መንግስት ነበር። እራሱን የመሕረም ልጅ እያለ የምጥራው ኢዛና ወይም አብርሃ የተባለው የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ንጉስ ሆኖ በአክሱም መንግስት ተሾመ። ይህ ሰው እራሱን የመሕረም ልጅ እያለ የምጥራው፥ መሕረም የተባለው የአማልክት ስም ስለ ሆነ ነው። መሕረም ማለት "የጨረቃ አማላክ" የምጠራበት ስም ነው። ስለዝህ ኢዛና የጣኦት አምላክ ነበር። ነገር ግን በ330 ዓ.ም ላይ ይህ ሰው እምነቱን ቀየረ። ይህንን የምንረዳው ከታርክ መዛግብት ብቻ ሳይሆን በግዜው ከነበሩ ቁሶችም ጭምር ነው። ይህ ሰው በነገሰው በመጀመሪያዎች ዓመታ በአገርቱ ገንዘብና በሕንፃዎች ላይ የጨረቃን ምልክት ይጠቀም ነበር። ክርስትናን ከተቀበለ በኋላ ግን ይህንን በመተው በሕንፃዎች ላይ፥ በሳንትሞች፥ በቁሶች ሁሉ ላይ የእግዚአብሔርን ስምና የመስቀል ምልክት አኑሯል። ስለዝህ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው በአክሱም ዘመነ መንግስት በንጉሥ ኢዛና ዘመን መሆኑ ታውቋል። የጌታ ሰላም የአብ ፍቅር የመንፈስ ሕብረት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን ይቀጥላል። ከወንድማችሁ @Yimesgenn 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 📜📜📜 ይ🀄️ላ🀄️ሉ 📜📜📜 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @NIKAOHODOSMINISTRY @NIKAOHODOSMINISTRY
Show all...
#Share__Share__Share ✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️ ይህ የንቃኦሆዶስ መንፈሳዊ የወንጌል አገልግሎት የቴልግራም ቻናል ነው፣ ከዝህ መንፈሳዊ የወንጌል አገልግሎት ቻናል ✅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶችን ✅ ጠቃም መልእክቶችን ✅ መንፈሳዊ መጽሐፍቶችን ✅ ነገረ መለኮታዊ ዳሰሳዎችን ✔️ ጨምሮ ለሎች ክርስቶስን በመምሰል ለማደግ የምጠቅሙ በርካታ ክርስቲያናዊ አግልግሎቶችን ከዝህ የወንጌል አገልግሎት ቻናል ያገኛሉ። በግል ለማግኘት ከፈለጉ @Yimesgenn 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 📜📜📜 ይ🀄️ላ🀄️ሉ 📜📜📜 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @NIKAOHODOSMINISTRY @NIKAOHODOSMINISTRY
Show all...
#የቤተክርስትያን_ታርክ #ክርስትና_በኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ መንፈስ የሆነ ሰላም፥ ጸጋና ምህረት ይብዛላችሁ። እስከ አሁን ድረስ ያየነው የቤተክርስትያን ታርክ እጅግ እንደጠቀማችሁ እምነቴ ነው። አሁን ቀጥለን ክርስትና ወደ አገራችን ኢትዮጵያ እንደት እንደገባና የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን በጥንቱ የቤተክርስትያን ታርክ ምን ያህል ድርሻ እንዳላት እንዳሥሳለን። አስተያየት ካላችሁ @Yimesgenn ላኩልን የጌታ ሰላም የአብ ፍቅር የመንፈስ ሕብረት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን ይቀጥላል። ከወንድማችሁ @Yimesgenn 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 📜📜📜 ይ🀄️ላ🀄️ሉ 📜📜📜 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @NIKAOHODOSMINISTRY @NIKAOHODOSMINISTRY
Show all...