Man City Addis
Open in Telegram
Man City Addis is official Supporter Club of Manchester City fans in Ethiopia. Contact +251944309760
Show more4 967
Subscribers
+424 hours
+237 days
+8830 days
Posts Archive
4 967
በእርግጠኝነት እንደ በፊቱ ሁለት አስቆጥሮ የሚሰማው ደስታ አልተሰማውም! ሜዳ ውስጥ እጅግ ረሃብተኛ ኧርሊንግ ነበር ኳሶች ቶሎ ቶሎ ወደፊት እንዲመጡ ትዕዛዝ ሲሰጥ ነበር፣ ማሸነፉ ከዚህም በላይ እንዲሆን ነበር የፈለገው፣ በነገራችን ላይ የቡድኑ ሁለተኛ ካፒቴን ነው ኧርሊንግ ጎል አስቆጣሪ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በኋላ ተደማጭም ጭምር ነው! እንዲህ መሆኑን ወድጄዋለሁ!
ሁለት ጎል አስቆጥሮ፣ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ፣ የክለቡን ሌጀንድ ጎል ሪከርድ ተጋርቶ ያ በቂ አይደለም ብሎ ደስተኛ ያልሆነ አጥቂ ነው ያለን እኛ የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች!
መታደል!🫠❤️
4 967
Fc Porto አንድም ሙከራ ወደ ጎል ሙሉ ዘጠና ደቂቃ ሳይሞክር ጨረሰ ካሉህ ይህን ፎቶ አሳያቸው!!!.....አንተ ይችላል ብቻ አይገልፀውም!!!!👌
እጅግ ሰላም ያለው ተጨዋች!🙏🔥🔥🔥
4 967
በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እስከ ዛሬዋ ምሽት ድረስ በ2026 በሜዳው ተሸንፎ የማያውቀውን ፖርቶን ከሜዳችን ውጪ 2-0 አሸንፈን መመለሳችን እጅግ በጣም ትልቅ ድል ነው! 🔥🩵
በአጠቃላይ የአጨዋወት ደረጃችን ጥሩ የነበረበትም፣ የተቀዛቀዘበትም አጋጣሚ ነበር። ነገር ግን በግልፅ መስተካከል ያለበት ነገር ቢኖር የምንፈጥራቸውን እድሎች ወደ ጎል መለወጥ finishing ላይ ያለው ክፍተት ነው። ቡድኑ ገና አዲስ በመሆኑ መግባባት እና ቅንጅት ለመፍጠር ጊዜ እንደሚያስፈልገው ግልፅ ነው ይሄ በአንድ ጀምበር የሚገነባ አይደለም።
ነገር ግን ከኮቨንትሪ ጋር የነበረው ጨዋታ በቀላሉ 6-0፣ የዛሬው ደግሞ በይበልጥ 4 ወይም 5 ለ 0 ማለቅ የነበረበት ነው!
የዕድል ፈጠራው፣ የቦታ ቅያየሬው፣ ቦታ አያያዝ እና የተቀናጀው አጨዋወታችን እጅግ ማራኪ ነው። አሁን የሚቀረን ጨዋታዎችን ገና በጊዜ ገድሎ መውጣት ብቻ ነው።
የተጫዋቾች ብቃት ስንመለከት፦
🔹 ኤሊዮት አንደርሰን — እውነተኛ ጉልበት እና ጥንካሬ ያለው ሞተር ነው! በየሳምንቱ ድንቅ ነው። እስካሁን ተጫውቶ ሳያስገርመን የወጣበት ጨዋታ የለም።
🔹 አዩብ ቦአዲ — በእጃችን ላይ ያለ እጅግ ድንቅ ታላቅ ተስፋ! ከኋላ ተነስቶ የተጫወተው ሚና፣ የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን የጨዋታ ክፍል ያገናኘበት መንገድ እና ጫናዎችን የተቋቋመበት ብቃት የሚያስደንቅ ነው። መጨረሻ ላይ ኳስ አዝግሞ በማስረዘም ካጣቸው ሁለት አጋጣሚዎች ተምሮ ውሳኔዎቹን ማፋጠን ሲጀምር ይበልጥ አሪፍ ይሆናል።
🔹 አርሊንግ ሀላንድ — ምን ዓይነት አደገኛ አጥቂ ነው! ስለ እሱ የሚነገሩ የሙገሳ ቃላት ሁሉ አልቀዋል።
በዛሬው ጨዋታ ጌሂ፣ ቦአዲ፣ ኤንዞ፣ ሀላንድ እና ፎደን ምርጥ የነበሩ ሲሆን ሰሜንዮ እና ግቫርዲኦል በኩል ደግሞ ትንሽ ፈራ ተባ የማለት ነገር ይታይባቸው ነበር።
Come on City! 🩵🔥
4 967
ማሬስካ ስለ ቡአዲ 🗣️
በፈጣሪ ስም ! ምንም አይነት መደናገጥ አይታይበትም ፤ በጣም አሪፍ ነበር ። ከሱ ያየዉት ችሎታ የማይታመን ነበር
4 967
ማሬስካ ስለ ቡአዲ 🗣️
በፈጣሪ ስም ! ምንም አይነት መደናገጥ አይታይበትም ፤ በጣም አሪፍ ነበር ። ከሱ ያየዉት ችሎታ የማይታመን ነበር
4 967
ኤንዞ 🗣️
ያመነብኝን አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካን ማመስገን ፈልጋለዉ እና በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ የሚፈልገዉን ሁሉ ላደርግለት ዝግጁ ነኝ
4 967
ኤንዞ 🗣️
ማን ሲቲዎች ጥሩ ብቃት ያላቸዉ ተጨዋቾች ብቻ አይደሉም ። እዉነተኛ ቅንነት ያላቸዉ ሰዎች ናቸዉ።
ደጋፊዎቻችንም እጅግ በጣም አስገራሚ ናቸዉ። የህይወቴን አዲሱን ምዕራፍ ወድጄዋለዉ እና ወደፊቴን በጉጉት እንድጠብቀዉ አድርጎኛል።
🩵
4 967
🚨| ኤርሊንግ ሃላንድ በማንቸስተር ሲቲ የቻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ 36 ጎሎችን በማግባት ከአጉዌሮ እኩል የክለቡ ከፍተኛው ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።
4 967
የኢንዞ ማሬስካን ሲቲ እስከሚያገኙ ድረስ ፖርቶ ለ9 ወራት በሜዳው አልተሸነፍ ነበር።
ማሬስካ ከ 4 ጨዋታ 4 ድል 🔥
ስለ አዲሱ አለቃችን ምን አስተያየት አላቹ ?
4 967
ፖርቶ እና ሲቲ 4 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን:
*ማንችስተር ሲቲ ሶስቴ ሲያሸንፍ ✅
*አንድ ጊዜ አቻ ተለያይተዋል🟰
*ፖርቶ በአንፃሩ ሲቲን አሸንፎ አያውቅም!🤷
