cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ንቁ ትውልድ-Niku Twld

እኛ ንቁ ትውልዶች ነን!

Show more
Advertising posts
4 089Subscribers
-124 hours
-197 days
-7130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እንኳን አደረሳችሁ!🙏🙏     #ሆሳዕና   💛 @Ei_du 💛
Show all...
🙏 7
"እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል" የሚባል አባባል አለ፤ መጀመሪያ ራስህን አድን፣ ራስህ ላይ አተኩር! እንዲህ ባደርግ ሰዎች ይደሰቱብኛል ማለቱን ተወውና 'እኔን ደስተኛ የሚያደርገኝ ምን ባደርግ ነው?' በል። አንተ ደስተኛ ስትሆን አለም አብራህ ትስቃለች፤ ሰዎች የደስታህን ምንጭ ለማወቅ ሲሉ አክብረው ያደምጡሀል፤ አየህ ራስህ ላይ ስታተኩር ሰዎች ደግሞ አንተ ላይ ማተኮራቸው ግድ ነው። ወዳጄ ደስ የሚለኝ ነገር አንተ ደግሞ ለራስህ ደስታ አታንስም! ሰናይ ቀን🙏 ✍️ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
Show all...
👍 10🥰 2
💧አንድ ቀን ባለፈ ቁጥር ለፍፃሜ ቀናችን አንድ እርምጃ እየቀረብን ነው፤ አስቡት ቀኑን በጭንቀት ወይ ምንም በማይጠቅመን ካሳለፍነው ደግሞ ደግመን የማናገኘውን ሀብት ሜዳ ላይ እየበተነው ነው። መቼ እንደምናልፍ ስለማናውቅ ለፍፃሜያችን በጣም እየቀረብን እንደሆነ አስበን በሙሉ አቅማችን መስራት፣ ህይወትን ያለጭንቀት ማጣጣም አለብን! ወዳጄ መቼም ይሄን ወርቃማ ጊዜ ማንም ደግሞ አይሰጥህም፤ የዛሬ 50 አመት ወይ አቅም አንሶህ አርጅተሀል ወይ ደግሞ አልፈሀል...ይሄንን አስብና ያኔ እንዳይቆጭህ ማድረግ ያለብህን ሁሉ አድርግ። የንቃት ቀን ተመኘንላችሁ🙏
Show all...
👍 11
ውስጥህን የሚረዳልህ ላይኖር ይችላል፤ አንተስ ግን ውስጥህን ትረዳዋለህ? ምን አንደምትፈልግ ታውቃለህ? ወይስ እንዲሁ ነው እየኖርክ ያለኸው? እነዚህን ጥያቄዎች እየደጋገምክ በጠየክ ቁጥር የምታገኘው መልስ ህይወትን በአንዴ አስገራሚና አጓጊ የሚያደርግ ነው። ጠይቅ ወዳጄ! ካለመጠየቅ ደጃዝማችነት ይቀራል ይባላል፤ ራስህን ጠይቅ! ፈጣሪህን ጠይቅ! ከሁሉም በላይ ግን የምትጠይቀውን ለይተህ እወቅ፤ ለዛ ነው ከላይ ያሉትን ጥያቄዎች መመለስ ያለብህ። መልካም ቀን ተመኘንላችሁ🙏 ✍ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
Show all...
👌 8🥰 1🙏 1
#ፍቅር ሰዎችን ሳይወዱን መውደዱ አናውቅበትም፤ ብናውቅበት እንኳን ሞኝነት ይመስለናል። ሰዎች ይቅር ሳይሉን ይቅር ማለቱን አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የተበለጥን ይመስለናል። ሰዎች ሳያከብሩን ማክበሩን አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የተዋረድን ይመስለናል። ሰዎች ካልረዱን መርዳት አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የዋህ የሆንን ይመስለናል። ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ እንሻለን፤ ለፍቅራችን፤ ለደግነታችን፤ ለይቅርታችን፤ ለክብራችን ምላሽ ካልተሰጠን ደስተኞች አይደለንም። ለዚህ ነው ኩርፊያ እና ቂም በትንሽ በትልቁ ብቅ የሚሉት። "እኔ እንዲህ አድርጌለት" "እኔ ለሱ ጊዜ እንዲህ ነበርኩኝ?" "ለእኔ የሚገባኝ ይህ ነው?" እያልን የገዛ ደስታችንን የምናጠፋው ያለምላሽ ማፍቀር፤ ያለ ምላሽ ማድረግ ስላለመድን ነው። ስንሰጥ ምላሽ ካልጠብቅን ሰዎች ክፉ ቢሆኑብን ግር አይለንም። ስንወድ ለመወደድ ብለን ካልሆነ፤ ፍቅራችን ሲገፋ አይከፋንም። ስንረዳ ለክፉ ቀናችን ብለን ካልሆነ፤ ሰዎች እርዳታቸውን ሲነፍጉን አይደንቀንም። የምናደርገው ነገር ሁሉ ከልባችን ሲሆን፤ ደስታችን ሌሎች በሚሰጡን ምላሽ ላይ አይወሰንም። #ፍሬ_ሃሳብ ፍቅር ማለት መስጠት እንጂ መልስ ጠብቆ መስጠት አይደለም! ሰናይ ቀን🙏 ✍ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
Show all...
🔥 11👍 1
የሚሞትለት አላማ የሌለው ሰው ለመኖር ብቁ አይደለም። "ማርቲን ሉተርኪንግ" እውነት ነው ሰው ለመኖር ብቁ የምንሆነው የሚሞትለት መክሊት ፤ትልቅ ራዕይ ፤ስኬት ሲኖር ነው። ምንድነው የምንሞትለት ህልማችን ምንድነው?? መክሊታችን ውስጣችን የተቀበረው ታምር ምንድን ነው። ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ቁም ነገር ሰርተህ አሻራህን ጥለህ የማይሞት ማንነትን ተክለህ እለፍ  ማለት ነው እንጂ። ካነበብኩት የወደድኩት ድንቅ  የህይወት ታሪክ ለምጣዱ ሲባል...! አንዲት ሴትዮ ጓዳቸው ውስጥ እየተንጎዳጎዱ ድንገት አንዲት አይጥ ምጣዳቸው ላይ ትወጣለች ወንድ ልጃቸው እንጨት ያነሳና አይጧን ለመምታት ሊሰነዝር ሲል ሴትየዋ አስቆሙትና <ልጄ አይጧን ስትመታ እንጀራ ማብሰያችንን ምጣዶን ሰበርከው ማለት ነው ስለዚህ እስኪ ግድ የለም ለምጣዱ ሲባል አይጧን ዝም እንበላት> አሉት አሉ፡፡ #ጭብጥ  ሁሌም ለምንፈልገው ነገር ስንል ብዙ ነገሮች መታገስ እንዳለብን፤ከድርጊት በፊት አስተውለን መወሰን እንዳለብን እንረዳለን። ✍ጣፋጭ ታሪኮች ና ወጎች ውብ ቀን ተመኘንላችሁ🙏
Show all...
🥰 10👍 4 1
🔊 ያንተ ህይወት አሁን ነው። በኋላ ወይም ነገ አይደለም። 🔰 ከዩኒቨርስቲ በምትመረቅበት ጊዜ አይደለም። 🔰 ጡረታ በምትወጣበት ጊዜ አይደለም። 🔰 የምታፈቅረው ሰው አብሮህ ሲሆን አይደለም። 🔰 ወደ አዲሱ ቤትህ በምትገባበት ጊዜ አይደለም። 🔰 አሪፍ የሆነ ስራ በምታገኝበት ጊዜ አይደለም። 🔊 ያንተ ህይወት አሁን ነው። 🔰 ሁሌም አሁን ብቻ ነው። 🔰 ካሁን ጀምሮ በህይወትህ መደሰት ጀምር ምክንያቱም ከ አሁን ውጭ ምቹ ጊዜ አታገኝምና። 🔰 አሁን በህይወትህ ላይ የምትወስነው እያንዳንዱ ውሳኔ ነገ ለሚመጣብህ ነገር መሰረት ነውና ውሳኔዎችንም አስብባቸው። መልካም ምሽት🙏
Show all...
👍 10👏 2👌 1
100%👍
Show all...
👍 4👌 3
📍«በሰው ዘንድ አለቀ ተቆረጠ የተባለን ነገር ሁሉ በእምነት ከጠበቅን #ፈጣሪ  የተቆረጠን ነገርን ይቀጥላል!» : 📍እምነት ማለት ማመን መታመን ማለት ነው። ፈጣሪ መኖሩን ዓለምን ያስገኘ አንድ አምላክ መኖሩን ሳናይ ሳንዳስስ ሳንጨብጥ ያለጥርጥር ይደረግልኛል ይሆንልኛል ማለት #ማመን ነው። ፡ 👉ይህን ማመናችንን የምናረጋግጠው ደግሞ በመታመን ብቻ ነው። መታመን ማለት እምነትን በሥራ መግለጥ ማለት ነው። መጾም፣ መጸለይ፣ መስገድ፣ መመጽወት መታመንን ይገልጣሉ። ፡ ↪አንድ ሰው ፈጣሪ ያዘዘውን ካልሠራ ታመነ አይባልም። ፈጣሪ ያስተማረህን እንድትሆን ያዘዘህን ሆነህ መገኘት ካልቻልህ ታማኝ አይደለህም ማለት ነው። ፡ ↪እምነት መታመን ከሌለበት ከንቱ ነው። ዝም ብሎ ጠዋት ማታ ጌታዬ ጌታዬ ማለት ብቻውን አያድንም። ፡ ↪አንድ ዘበኛ ቤት እንዲጠብቅ ተቀጥሮ ሳለ የቀጣሪውን ንብረት ከሰረቀ ታማኝ እንደማይባልና ከሥራ እንደሚባረር ሁሉ እምነታችንም መታመን ከሌለበት ከእምነት ለመውጣት እንገደዳለን። ፡ ↪እምነት የምትታመንበት ነው እንጅ በአፍህ ብቻ አምናለሁ እያልህ የምትቀልድበትና የምታሾፍበት አይደለም። ፡ ↪ለማመንህ መገለጫው መታመንህ ነው። አምንሃለሁ ለምትለው ፈጣሪ ልትገዛ ትእዛዙን ልትጠብቅ ያስፈልጋል። ፡ ➊.አትብላ ሲልህ አለመብላት፣ ፡ ➋.አትስረቅ ሲልህ አለመስረቅ፣ ፡ ➌.አትዋሽ ሲልህ አለመዋሸት፤ ፡ ➍.አመስግነኝ ሲልህ ማመስገን፤ ፡ ➎.ጹም ሲልህ መጾም፣ ፡ ➏.ጸልይ ሲልህ መጸለይ ወዘተ አለብህ የመገዛትህ ወይም የመታመንህ መገለጫ ነውና። : ↪ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ምጽዋት የሌለበት እምነት ከንቱ ነው። ለምታምነው አምላክ የመገዛትህን መገለጫ ማቅረብ አለብህ። ፡ ↪ይህ የመታመንህ መገለጫ ደግሞ በዘፈቀደ የሚደረግ ሳይሆን ሥርዓት ሊኖረው ግድ ይላል። ፡ ♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡ ፡ መልካም ቀን🙏🙏
Show all...
8🥰 2
✅ በአንድ መንደር ውስጥ ሥዕል እየሳለ በውድ ዋጋ በመሸጥ የሚተዳደር ሽማግሌ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን አንድ የመንደሩ ነዋሪ የሆነ የኔ ቢጤ መጣና "አንተ ሠዓሊ ነህ። ሥዕል እየሳልክ ብዙ ስለምታገኝ ሀብተም ሆነሀል፤ ግን ለድሆች አትሰጥም፤ ባለ ልኳንዳ ቤቱ እንኳ ሁሌ ሥጋ ለድሆች በነጻ ያድላል።" አለው ሽማግሌው ሠዓሊም ፈገግ ከማለት ውጪ ምንም መልስ አልሰጠውም . . ድሀው ሰውዬም በመንደሩ እየዞረ ሽማግሌው ሀብታም እንደሆነና ግን ስስታም እንደሆነ አናፈሰ። የመንደሩ ሰዎች አዛውንቱን ጠሉት . . ከጊዚያት በኃላ አዛውንቱ ታመመ። አንድ እንኳ የሚያስታምመው ሰው አጥቶ ሞተ . . ከዚያን ቀን በኋላ ባለ ልኳንዳው ሥጋ ማደሉን አቆመ። ለምን እንዳቆመ የመንደሩ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁት . "እስከ ዛሬ የማድላችሁ እኮ ሠዓሊው ስለሚከፍለኝ ነው" ብሎ መለሰላቸው። . . አንዳንዴ ነገሮችን ሳናረጋግጥ ለውሳኔ አንቸኩል። ምርጥ መጣጥፎች መልካም ቀን🙏🙏
Show all...
🙏 11👍 3