cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Animut Abraham

Show more
Ethiopia7 571Amharic7 154The category is not specified
Advertising posts
596
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"LEFT TO TELL" The story of Amhara survivors from Wellega mascare and residing in Debrebrhan IDP Camp ! Must listen !! youtube.com/live/5Cony_Knr
Show all...
- YouTube

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

በነቀምቴ እስር ቤት፣ ከባኮ ጀምሮ እስከ ሻምቡና ደንጎሮ፣ ከጊምቢ ጀምሮ እስከ ደንቢደሎ ያሉ እና በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች የህሊና እስረኞች የሚገኙበትን የእስር አያያዝና መከራ ጠቅለል አድርጎ የሚያሳይ ከእስር ቤት የወጣ መረጃ! እነ ሙሉቀን አንተነህ እና ሌሎች በማንነታቸው በበነቀምት በግፍ እስር ላይ የሚገኙ አማራዎች:_ 1ኛ- በመጀመሪያ ደረጃ የተከሰሱበት ክስ በኦሮሚያ የተጻፈ በመሆኑና እኛም በነበረው የትምህርት ስርዓት በአማራ የተማርን በመሆኑ የቋንቋ እጥረት ስለሚኖር በማለት ክሱን ቋንቋ በሚችሉ ሰዎች በማስተርጎም የክሱን ሁኔታ መረዳት፤ 2ኛ- የተከሰሱበት በሐሰት መስካሪዎች የተሞላ በመሆኑና በሶስት አይነት የክስ መዝገብ በመሆኑ በህግ ባለሙያዎች ማለትም ጠበቃ በመያዝ በከፍተኛ የፌዴራል ፍርድ ቤት ክሱን በዝርዝር በማቅረብ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ማድረግ ሲሆን ክሱ በከፍተኛ ወንጀል፣ በመካከለኛና አነስተኛ በሚል የተዘረዘረውን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ለጠበቃዎቹ በቅርበት መረጃዎቹን መግለጽና በጹሑፍ ማስረጃነት ማቅረብ፤ 3ኛ- በእዚህ ሁሉ እስረኞች ላይ የተፈጸመውንና እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ ጥሰት አያያዝ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ልክ እንደዚህ ቀደሙ በማስረዳት በቦታው ተገኝተው ለፍርድ ቤቱ ግብዓት የሚሆን በተቋሙ[ኢሰመጉ] የተረጋገጠ ለጠበቃዎቹ በቋሚነት ፊት ለፊት በመቅረብ ለተያዙት ጠበቃዎች ማስረጃዎችን ማቅረብ፤ 4ኛ- ለእስረኞቹ ጠበቃ ለተባሉት በአንዳንዳችን ለአንድ ጠበቃ 50ሺህ ብር ተብሎ የቀረበብንም ፍትሐዊ አለመሆኑንና የነቀምቴ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስረኞች ጠበቃ ይዘው መከላከያ ማቅረብ እንዳንችል መደረጋችንንም አንዱ ጫና መሆንና ፍርድ ቤቱ ያለምንም ይግባኝ ፅኑ ፍርድ ለመስጠት መሆኑን፤ 5ኛ- ክሱ በዘር ማጥፋት በሚል በመሆኑ ለዚህ ደግሞ እንዲያመቻቸው የትግራይ ተወላጆችንና የኦሮሞ ተወላጆችን ብቻ በመጥቀስ የአማራ ተወላጆች ሞትን ደግሞ እንደገዳይ በማስቆጠር መስራታቸውን ማስገንዘብ፤ 6ኛ- ክሱን አስመልክቶ በእለቱ ያልነበሩ የፈጠራቸውን የማይፈሩ ግለሰቦችን አቅርበው ለማስመስከር ስለሚችሉ፣ እነዚህን የሐሰት ምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ ለመጠየቅ ሰፊ ጊዜና ነፃነት ሊሰጡን ስለማይችሉ፥ "ፍርደ ገምድል" ስለሚሆን በተቻለ መጠን በህግ አግባብ እንዲቻል በየትኛውም መንገድ ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር መሞከር፤ 7ኛ- ማህበራዊ ሚድያን በሰፊው ስለመጠቀምና ማሳወቅ፣ ክሱ መርጠህ ወይም ፈልገህ ምታ እንጂ እውነተኛና የተጣራ ባለመሆኑ፣ በእለቱ በማን ችግር እንደተፈጸመ፣ ማን እንደፈጸመው፣ የጠፋው የሰውና የንብረት ውዲመት በማን እንደተፈጸመ በገለልተኛ አካል ሳይጣራ ክሱ መመስረት እንደሌለበት ማስረዳት፤ 8ኛ- የሞቱት ከሁሉም ብሔር ቢሆንም በክሱ የቀረበው ግን ሆን ተብሎ የክልሉ ሰዎችና ትናንት እንደውሻ ሲናጠቁ የነበሩትን የህወሐት ሰዎችን ዛሬ ተቆርቋሪ በመምሰል ማካተቱ በቀጣይ ሊሰሩት ያሰቡትን ቁማር በግልጽ ያሳያል። 9ኛ- ከክሱ ጀርባ ያሉ ምስክሮች ስም ዝርዝር በተመለከተ አንድ የከተማ አስተዳደር (የፀጥታ) መዋቅር "የዘር ማጥፋት" ወንጀል ትርጉም ምን እንደሆነ ሳይገነዘብ ፅፎ የላከው ደብዳቤን በተመለከተ በርካታ ብሔርን ከሚያስተዳድር አካል የሚጠበቅ እንዳልሆነና ዘር ማጥፋት ወንጀል ምንነቱን የማያውቅ መሆኑን እንደማስረጃ ተጽፎ ከቀረበው ማስገንዘብና በቀጣይ እንዴትስ ህዝቡን ሊመራ እንደሚችል፤ ዘር ማጥፋት ማለት በአንድ ቤተሰብ በአንድ ቦታ ላይ ባሉበት አንድም ሰው እንዳይተርፍ አድርጎ ለሚወሰድ እርምጃ ሲሆን በአንድ ሁኔታ ለተፈጠረ ግጭት ሊፃፍ ስለማይገባ፥ ዋና አላማው ይህ ደብዳቤ የሚያሳየው አስተዳደሩ የሚሰራው ለተለየ ወገን ብቻ መሆኑን ነው። 10ኛ- በባኮ ተወላጆችና በ10 ተወላጆች ላይ የተፈጸመው በተመሳሳይ በኛ ላይ ሊፈጽሙት እንደሆነ እየተገነዘብን ነው። ስለዚህ ይህ መልዕክት እንደደረሳችሁ ምንም ሳትሰላለቹ በሚድያና ለህግ አካል ጋር ጠበቃ በመያዝ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተጽዕኖ መፍጠር ይኖርባችኋል። "መቼም ይሁን መቼም እናሸንፋለን!" "መታሰር ሽንፈት አይደለም!" መልዕክቶች እና ሌሎች ተያያዥ ማስረጃዎችን በተከታታይ እናቀርባለን። ምንጭ_የአንገር ጉትን ልዩ ዞን ጥያቄ (አጉልዞ) ጥያቄ
Show all...
👍 3
Show all...
Anchor Media እኔ የምለው .....?! ክፍል 13፥ የሆነ ነገርማ አለ.....?!

Mesay Mekonnen

በአገዛዙ እና በወያኔ በኩል እየተደረገ ያለው የኢትዮጵያ ኮንፌዴሬሽን ምሥረታ ሒደት ነው። የቤተክርስቲያን ጉዳይ የሒደቱ አንድ አካል እንጂ በየጉዳዩ የሚቀጥል ነው። ኮንፌዴሬሽን ወያኔዎችንም ሆነ ኦነጋውያንን የሚያስማማ አጀንዳ ነው። It is a move to form an ETHIOPIAN CONFEDERATION !
Show all...
👍 2
"The Amhara people’s existential struggle is marked by paradoxical features and qualities mainly stemming from the contradictions of the massively corrupt Oromo identity regime against which they wage it. Most notably, while change-seeking Amhara freedom fighters and militia have been operating within the supposedly legal-constitutional confines of the ethnic order, such as it is, the ever deceitful, treacherous Abiy autocracy uses elements of these resistors and Amhara proxies to reinforce or protect its fascistic tribal grip on power. " https://borkena.com/2023/07/13/ethiopia-tribal-rule-overcoming-the-political-limits-of-the-resistance/?s=09#google_vignette
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
"ትልቅ መውረድና መቅለል፥ አማራ ሆኖ በአማራነት አለመታገል ፣ የአማራን ትግል አለመቀላቀል ነው" (ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ በማገር ሚድያ )
Show all...
👏 3👍 1👎 1
መካር ያጡ ፖለቲከኞች እና የቀነጨሩ ልሂቃን ከጦጣዋ በምን ይሻላሉ? [ በ Yared Hailemariam ] "Instead of 'failed or corrupted' politicians, let the monkeys govern the countries; at least they will steal only the bananas!" Mehmet Murat ildan ጠቅላዩ በዚህ ሳምንት በፖርላማ በሰጡት ማብራሪያ የጠቀሷት ጦጣ ከዛሬዎቹ የአገራችን ፖለቲከኞች የተሻለች መስላ ብትታየኝ ዘንዳ ይሄንን ለማለት ወደድኩ። አዎ ጦጣው ትክክለኛ ውሳኔ ወስናለች። ከገንዘብ ይልቅ አንድ ሙዝ መርጣለች። ለሷ ከሙዙ አጠገብ የወደቀው ወረቀት የሙዙን ያህል ዋጋ የለውም። ሙዙን ትታ ብሩን ብታነሳ ያበደች ወይም የጠገበች ጦጣ ትባል ነበር። ከኛ ፖለቲከኞች በተሻለ rational thinking እና rational choose እሷ ላይ ይታያል። አገርና ጎጥ፣ አገርና ገንዘብ፣ የግል ዝና እና ሕዝብ ከፊታቸው ቀርበውላቸው ሕዝብና አገርን ገፍተው ጎጣቸውን፣ ገንዘብንና የግል ዝናን ከመረጡ ጭንጋፍ ፖለቲከኞች ይልቅ ጦጣዋ ትክክለኛና ጤነኛ ውሳኔ ወስናለች። ጦጣዋ ገንዘቡን መርጣ ቢሆን ኖሮ ከፖለቲከኞቻችን አንዱን ትሆን ነበር። ፖለቲከኛ ያልተዋጣላት አገር ጥሩ መሪ ማብቀልም ሆነ መፍጠር አትችልም። ምክንያቱም መሪ የሚወጣው የፖለቲካውን ጎራ ከተቀላቀሉት መካከል ነውና። ፖለቲከኞቹ የሚወጡት ደግሞ ከማህበረሰቡ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሩ የፖለቲካ ማህበረሰብ፣ ጥሩ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ጥሩ መሪ መፍጠር አልቻለም። ከዚህ በፊትም ደጋግሜ እንደጻፍኩት የቀነጨሩ ልሂቃን በበዙበት አገር ፖለቲካውም እንዲሁ ይቀነጭራል፣ ይጨነግፋልም። አድሮም፣ ከርሞም እንጭጭ እንጅ አይበስልም። በእውቀት፣ በህይወት ልምድ፣ በሞራል ልዕልና እና በመርህ ኪሳራ የገጠመው የልሂቃን ስብስብ ባጋጣሚ እጁ ላይ የወደቀችን አገር የማንኮታኮት፣ የማዋረድ፣ የማፍረስ እና ሌላ በአዕምሮም በአካልም የቀነጨረ ትውልድ የመፍጠር አቅሙ ሰፊ ነው። የዛሬውን የመልዕክተ ቅዳሜ ትኩረት ብዙ ስለተወራለትና በዚህ ሳምንት በተካሄደው የፓርላማ 'የልቀቅ አለቅም' ድራማ መሰል ሙግት ላይ ባተኩር ደስ ይለኝ ነበር። በተለይም እጅግ የተጣረሰ፣ ከእውነት እና ከእውቀት በራቀው፣ መሬት ላይ የሚታየውን ያፈጠጠ ሀቅ ሽምጥጥ አድርጎ በካደው፣ በሕዝብ ስቃይና ቁስል መሳለቅ በሚመስለው፣ የአገሪቱን ያፈጠጡ እና ያገጠጡ፤ አለም ያወቃቸውን ችግሮች የመንደር ጉዳይ ለማስመሰል በሞከረው፣ እራስን ከተጠያቂነት ለማሸሽ በሚመስል አኳኋን የቀረበው (የሸገር ከተማ ጉዳይ እኔን አይመለከትም) የጠቅላዩ ሃተታ ላይ ለማተኮር አስቤ ነበር። ነገር ግን የከሰሩት ወይም below average የወረደ ፖለቲካ እየተጫወቱ ያሉት እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ሙሉ የአገራችን የፖለቲካ ተዋናዬችና ፖለቲከኞች ስለሆኑ ትልቁ ስዕል ላይ ለማተኮር ወደድኩ። አዎ ከላይ እንዳልኩት ከቀነጨሩ የፖለቲካ ልሂቃን ምርጥ የአገር መሪ መጠበቅ ከዝንጀሮ ቆንጆ እንደማበላለጥ ነው የሚሆነው። ስለዚህ የሚሻለው ኢትዮጵያ ዛሬ ለደረሰችበት ዝቅጠት የፖለቲካ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ልሂቃን የተጫወቱትን ሚና መፈተሽ የግድ ይላል። የፖለቲከኞችን ጭራ እየተከተለ ሲያብዱ አብሮ እሚያቤድ፣ ሲከንፉ አብሮ የሚከንፍ፣ ሲገድፉ አብሮ የሚገድፍ፣ በእብሪት ለጸብ ሲዘጋጁ የጸቡን መንስዔና አካሄድ ለማጥናት እና ጠይቆ ለመረዳት እንኳ የደቂቃ ትንፋሽ ሳይወስድ ከተፋላሚዎች ኋላ ጎራ ለይቶ በመሰለፍ በለው እያለ የሚፎክር፣ ጸበኛ ፖለቲከኞች ሲታረቁም ደግሞ እንዲሁ እልል እያለ የሚያዳምቅ፤ የጸቡም ሆነ የእርቁ ውሉ ሳይገባው ፖለቲከኞች ሲቆጡ እጥፍ የሚቀጣ፣ ፈገግ ሲሉ ድዱ እስኪታይ የሚያገጥ ልሂቃን በሞላበት አገር መሪና ፖለቲከኞችን ብቻ መንቀፍ ፍትሀዊነት የጎደለው ይመስለኛል። በቅርቡ እጅግ ክፉኛ አድቅቆን፣ እንደ ሀገር አዋርዶን፣ የሚሊዮኖችን ሕይወት አሳጥቶች፣ የግፍና ግፈኝነትን ጥግ አሳይቶን ያለፈው የሁለቱ አመት የእብደት ጦርነት ለዚህ የሞራል ልዕልና ክስረታቸን ጥሩ ማሳያ ይመስለኛል። በአገዛዝ ሥርዓቱ ላይ ያሉት ጤና የጎደላቸውና በፖለቲካ በቀል የታወሩ ሰዎች ጎራ ለይተው መቀሌና አዲስ አበባ መሽገው ሕዝብ ሲያጫርሱ አብሯቸው በግራና በቀኝ ያልቆመ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ቢቆጠር፤ ጦርነት አያዋጣንም በሕግ አምላክ ፖለቲከኞቻችን አደብ ግዙ ብሎ የተማጸነው፣ የጮኸውና ምክር የሰጠው ልሂቅ እፍኝ አይሞላም። ከታወቁ ፕሮፌሰሮች አንስቶ ቄሱም፣ ሼኹም፣ የአገር ሽማግሌውም፣ አባገዳውም፣ ምሁሩም፣ ጋዜጠኛውም፣ ተሟጋቹም፣ አንቂውም፣ አማካሪ ተብዮውም በሁለት አመቱ ጦርነት በቂምና ጥላቻ ስካር ውስጥ ሆኖ በለው ሲል የነበረበት ሁኔታ የቅርብ ትውስታችን ነው። እንደ እኔ እንደ እኔ የከሸፍነው እንደ ሀገር ነው። የተዋረድነውም በአገር ደረጃ ነው። ጠቅላዩ ፊት የተነሱበት የፖሪሱ የመሪዎች ጉባዔ ውርደትና መሸማቀቁ ለሳቸው ብቻ ሳይሆን የአገር ውርደትና ኢትዮጵያ ኮስሳ የታየችበት ነው። በሁሉም አቅጣጫ ተመሳሳይ ፈተናዎች ተደቅነውብናል። ዛሬ ለደረስንበት ዘርፈ ብዙ ኪሳራ የተጠያቂነት መጠኑ ይለያይ ይሆናል እንጂ ገዢው ፖርቲ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚዎችም፣ ጠቅላዩ ብቻ ሳይሆኑ ተጠቅላይ ፖለቲከኞች የየራሳቸውን ድርሻ ያነሳሉ። ጠቅላዩ የልቀቅ ጥያቄ ከዚህ ቀደም ሲቀርብላቸው 'አብረን እንልቀቅ ነው የሚባለው' ባሉት ላይ የተወሰነ ሀቅ አላቸው። አዎ፤ እኔም እላለሁ እናንት በጎጥ ፖለቲካ የቆረባችሁ፣ ጥላቻና በቀልን በውስጣችሁ ያነገሳችሁ፣ በስልጣን፣ በገንዘብ፣ በሞራልም ጭምር የሞሰናችሁና የከሰራችሁ፣ በግራም በቀኝም የተሰለፋችሁ ፖለቲከኝነት የጨነገፈባችሁ ሰዎች ይህን ሕዝብ ተፋቱት፣ የሥልጣን ጥማችሁን ገታ አድርጉና ወደሚመጥናችሁ ሙያ ግቡ፣ አገሪቱ ወደ ሌላ ዙር እልቂትና ትርምስ ሳትገባ፣ የመበታተን አደጋም ሳይገጥማት በፊት የተረጋጋ የፖለቲካ አውድ ለመፍጠር ሥልጣን አይደለም አገርም መልቀቅ ካለባችሁ ልቀቁ። የልቀቅ አለቅም ነገር ሲነሳ በልጅነቴ አንዲት የመንደራችን ሰው የሴጣን ልክፍት የሚባል ነገር ይዟት የተፈጠረው ነገር ትዝ አለኝ። ሴትየዋ ትጮሃለች፣ ዙሪያዋን መንደርተኛው ከቧታል። አንድ ሦስት ጎረምሶች እላዩዋ ላይ ሰፍረው እጅግሯን ጠርንፈው በመያዝ እንዳትወራጭ አድርገዋታል። ቄሱ ዳዊታቸውን ከደገሙ በኋላ መስቀላቸውን ግንባሯ ላይ አድርገው ሴጣኑን ልቃት ይላሉ። በሴትየዋ አንደበት የሚናገረው ሴጣንም አለቃትም ይላል እየደጋገመ። በዚህ አይነት ምልልስ ብዙ ከተቆየ በኋላ ምሱን ጠርቶ ለቅቄያለሁ አለ። ሴትየዋው ወደ ጤናም እሷነቷ ተመለሰች። ተረጋግተታም ቁጭ አለች። ለምን እንደሆን እንጃ በአንድ በኩል የሚያስጓራት ሴጣን፣ በሌላ በኩል ሰውነቷ እስኪደቅ ድረስ ያለ የሌለ ጉልበታቸውን በመጠቀም እላይዋ ላይ የሰፈሩባት ወጠምሻ ጎረምሶች፣ ከዛም የቄሱ ከድብደባ ያልተናነሰ በመስቀል እና በጠበል ግንባሯን እየደጋገሙ የሚወቅሯት ሴትዮ ኢትዮጵያ መስላ ታየችኝ። ለምን እንደሆነ እንጃ አለቅም፣ እለቃለሁ፣ ምሴን ስጡኝ፣ ለቀቅኳት እያለ በሴትዮዋ አንደበተት የሚናገረው ሴየይጣን በቀነጨሩትና በጨነገፉት ፖለቲከኞች ተመስሎ ታየኝ። ለምን እንደሆነ እንጃ።🤔 መልካም ቅዳሜ!
Show all...
⁽⁽ የፈሲታ ተቆጢታ ⁾⁾ የትግራይ ልሒቃን ነገር ፡ ከሆነው ሁሉ ወዲያ ተመልሰህ የሁኔታ ባዘቶ ውስጥ ገብተህ ላለመወሽከት ነገሮችን ለመተው ብትቆርጥም፣ ነገሮችን በአወንታ ለመመልከት እና ከትናንት የተማረ አካሔድ ብትፈልግም እንደፈለከው አይሆንም። ከ'መፍሳት' አልፎ 'መቆጣት' የሚያስከትል ፡ "የፈሲታ ተቆጢታ" አይነት ነገር ይገጥምሃል። 1) ከጦርነቱ በፊት የነበሩ ጦርነቶች ("The wars before the war") በወጉ አለመተንተንና አለመዘርዘር ያስከተለው የተረክ መሸፋፈን አለ። በዚህ የተነሳ እንዲያው ፡ ቁጭ ባሉበት ጦርነት የወረደባቸው እያስመሰሉ ሒደቶችን ያልገመገመን ወገን ለማሳሳት ይሞከራል። በዚያ ጦርነት ቅድመ-ሒደቶችና ዋዜማዎች የነበሩት ፉከራዎች፣ ሽለላዎች፣ ማን-አሕሎኝነት፣ ወዘተ ምን እንዲያመጡ ነበር? የሚል የምር ምርመራ የለም። "የማንወጣው ነገር የለንም- ዘይድይቦ ነገር የለን" ሲባል ፣ .... "ኢትዮጵያ ያለወያኔ አይሆንላትም ፣ "ወያኔ ማረን" እንዲባል፣ "ሰላምና ልማት በወያኔ ጊዜ ቀረ" እንዲባል፣.. " የብልፅግናን ማሕበራዊ መሠረት ለመናድ "አማራውን ማስቆጣት" በሚል በመላው ኢትዮጵያ ፡ የአማራን የዘር ጭፍጨፋና ቀውስን ስፖንሠር ያደረጉ ሰዎች፣ ተመልሰው ተጎጂና ተጠቂ እኛ ብቻ ነን አሉ። እንደእውነቱ አማራ ወያኔን ለመዋጋት ጥቅምት 24'ን መጠበቅ አያስፈልገውም ነበር። 2) "የአብይን ቡድን በኃይል ማስወገጃው ጊዜ ፣ ነገ ወይ በኋላ ሳይሆን አሁን ነው፤ ሰዓቱ፣ ደቂቃውና ሰከንዱ አሁን ነው። ጊዜ የለም። " ብለው ተንትነው፣ በተዘጋጁበትና በከፈቱት ጦርነት ፥ ኢሳያስን አስወግደን የትግራይ አጋር መንግስት እናቁም ብለው ባሴሩበት ለተከተለው ጣጣ ባለቤት ሊፈልጉለት ይፈጋሉ። መሓላ የፈፀሙበትን ሰንደቅ አላማና ሕገመንግስት ክደው እና የአገር ሠራዊት በብሔር አደራጅተውና አስኮብልለው ሲያበቁ አገራቸውን የወጉ ሰዎች፣ ይቅርታ ተጠያቂ ሆነው መጡ። መብረቃዊ ጥቃት አደረስን እንዳልተባለ፤ " የሠራዊቱን ጥቃት 'ሱቅ' በሉ" እየተባለ እንዳልተቀለደበት ፣ "እንደአባቶቻችሁ..." እየተባለ ሲፎክር እንዳልነበረ፡ የብቻ ተጠቂነት እና ይቅርታ ወግ ይተረተራል ። መብረቅህስ!? የ'preemptive attack ዲስኩርህ እንዴት ወደዚህ አመጣህ!? የሚላቸው የለም። 3) ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገር ተጠቃ ብሎ በሁሉም መስክ ጦርነቱን ደግፏል። ሁሉም ቢታገላቸውም ፥ ኢሳያስን አስወግደን፡ ሲሆን የትግርኛ ተናጋሪዎች ሪፐብሊክ እንመሠርታለን ብለው በድሕረ-2010 የተከተሉት የአስመራ ፖሊሲ የወለደው የሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት ቢመጣም ፣ እነሱ ያደጉበት ኦሬንቴሽን ነውና "ጠላታችን አማራ ነው" ብለው አማራን ተበቀሉት። የባለ 5 ዞኗ ትግራይ መሪዎች ፥ የአማራን 8 ዞኖች ተቆጣጥረው 'ሆነብን' ያሉትን ሁሉ ግፍ ፈፀሙበት። በነገራችን ላይ ሻዕቢያ ምንም ቢያደርግ ፣ የቱንም ግዛታቸውን ቢቆጣጠር ስለእሱ አይደለም ወጋቸው። ነገራቸው ስለአማራ ነው። አማራ እንጂ ሻዕቢያ መሬት ያዘብን አይሉም። በጉልበት እናስመልሳለን የሚሉት የሻዕቢያ ይዞታ ብዙ አትሰማም። ከእንግዲህ አይመልሰውና! የአማራ ልጅ ደም የፈሰሰበት ባድመ በኤርትራ መያዝ አይደለም ጭንቀታቸው። የሠራ-አካላቸው ስለአማራ ነው። They reconstructed an Amhara enemity! የፖለቲካቸው thesis እሱ ነው። ልደቱ አያሌው እንዳለው ፡ "የትግሬ ልሒቅ በአማራ ላይ ዐይነ ጥላ አለበት"ና ነው። 4- ሙስሊሙም ፣ ፕሮቴስታንቱም ሌላውም "ለአገር ብለህ ቁም" ተብሎ ባራመደው አቋም ልዩነት ባይኖረውም፡ ለእነሱ ጠላት አማራ አለበት ብለው የሚያስቡትን ኦርቶዶክስን ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊም ተቋም ወይ ፕሮቴስታንቱ 'ይቅርታ ይበል ወይ አንቀላቀልህም' ብሎ እንዲነሳ አይቀሰቅሱትም። እዚያ ግድም አማራን አያገኙትም። የአማራን 8 ዞኖች ውድመት ለመጠገን ያልበጀተው ሲኖዶስ፡ ለትግራይ በጀት ቢይዝም፣ አማራን ይቅርታ ያላለው ሲኖዶስ ትግራይን ይቅርታ ቢልም፡ 'ይቅርታው አነሰን' ብለው ሲጮሁ ተመለከትኩ። የሲኖዶሱ መሪ፣ የቤተ-እምነቷ ፓትርያሪክ የትግራይ ሰው ቢሆኑም ፡ ጠላት ሲያደርጉ የምታያቸው አማራዎችን መርጠው ነው። ነባር ኦሬንቴሽን ነው። "የአማራ ከሆነ ነገር፥ ለትግራይ የሚመጣ በጎ ነገር የለንም" ብለው ጥርስ የነቀሉ ናቸውና ነው። ከኦርቶዶክስ አይደለም ፀባቸው ከአማራ ኦርቶዶክሶች ነው። ሲኖዶሱ ይበተን የሚሉት ፡ 'አማራን ያሳንስልናል፣ ያጠቃልናል' ብለው በማለም ነው። ከጋራ ውድመታችን ለማትረፍ እየሠራ ብዙ ስለጎዳን አካል በጋራ የምናስብበት ፣ ከእልህና ስሜት የምንወጣበት ጊዜ እንዲኖር ፅኑ ፍላጎቴ ነው። ስንቴ እንበለጥ ⁉ ግን የዚህ ልሒቅ ነገር ለmanipulation እጅግ ምቹና ዝግጁ በመሆኑ ለሌላ ውድመት ሌላ ዛቻና ፉከራ ይዟል። ሌላ እልህ፣ ሌላ በቀል፡ አዝሎ ኤርትራንም፣ አማራንም፣ ቀጠናውንም ለመንከስ ይዶልታል!! በእልቂት permanent minority መሆንን የማረጋገጥ ጥድፊያ ላይ ነው !! ትግራይ ፈጣሪ ይሁንሽ !!
Show all...
👍 1
አፈሩ ይቅለለውና ዶ/ር ፀሐይ ጀምበሩ የዲያስፖራውን ፖለቲካዊ ተሳትፎ፡ ⁽⁽የረጅም ርቀት ብሔርተኝነት⁾⁾ በሚል ፅፎበታል። የአማራ ዲያስፖራ ባለፉት 30 ዓመታት የከሠሩ የፖለቲካ ቡድኖችን በመደገፍ ገንዘቡን ጊዜውንና ጉልበቱን አባክኗል። ግንቦት-7ን እና ብርሃኑ ነጋን በመደገፍ ያጠፋው ሀብት ቀላል አይደለም። አሁን ከዚያ መሠል ሁኔታ ወጥቶ አማራን የመታደግ እና የማጠናከር ሥራ ውስጥ መግባቱ ትልቅ ነገር ነው። ያኛው ጥቂት ንቅሎች ብቻ የሚባዝኑበት ሠፈር ሆኗል። ስለሆነም ጥሩ ጅምሮችና ቀሪ የቤት ሥራዎች አሉ። 1) መደራጀት ፥ ዲያስፖራው በአንድ ረገዱ ጉዳዮቹን በአደረጃጀት ለመመለስ እየሠራ መሆኑ መልካም ነው። በርከት ያሉ ዲያስፖራው በመኖሪያ አካባቢው የሚመክርባቸውን ማሕበራት መመሥረቱን ቀጥሏል። እስራኤል አካባቢ ደግሞ ከፍ የማድረግ ምልክቶች አሉ። ወደ ጋራ አሰባሳቢ ተቋምነት ለማምጣት እና የጋራ አቋሞችን በጋራ ድምፅ ለማሰማት የጀመራቸው ንቆናቄዎችም መልካም ናቸው። የሚቀድመው የራስህን ወገን፡ በጋራ ጉዳይ ማሰለፍ ነው። ጥሩ ጅምር ነው፥ ነገር ግን የግል ኢጎዎችን በማስወገድ የበለጠ መተባበርና በጋራ መቆም ይጠይቃል !! አንተ መደራጀት ሳትችል በአፈና ውስጥና በድሕነት ውስጥ ያለው እንዲደራጅ መጠበቅ ልክ አይመጣም። 2) ወደአዳራሽ ምክክር ፥ ዲያስፖራችን ጉዳዩቹን በየአዳራሹ እየመከረ መሆኑ ጥሩ እድገት ነው። በባዶ ከመጮህ ይልቅ አሁን የአማራ ዲያስፖራ ነገሩን ወደ አዳራሽ ምክክር ወስዶታል። ይሔ በሳምንት ውስጥ ሳይሰማ የማይታለፍ ጉዳይ ሆኗል ‼ አሁን የማይሰባሰብ እና የማይመክር የአማራ ኮሚዩኒቲ የለም። ይጠናከር! ሳይንሳዊ ይሁን !! 3) ስርዓታዊ ጫና ማድረግ ፥ በኢትዮጵያ ያለውን ሥርዓት ለመታገል በተለይ የ #RerouteRemmittence ዘመቻ ጫናው ተጨባጭ ነው። ሌሎች ብዙ ጫና መፍጠሪያ መንገዶች አሉና እነሱ ላይ ሰፊ የቤት ሥራ አለ። 4) ቀሪ የቤት ሥራዎች ፥ ➙ የተፅዕኖ ፈጣሪ አገራትንና ግለሰቦችን በማስገንዘብ ረገድ የበለጠ ጠንካራ ሥራ ይፈልጋል። ➙ የረጅም አመት አሉታዊ ትርክትን የመስበር እና ቀጠናዊ አወንታዊ ሚናችንን የማሳወቅ ጉዳይ በመሆኑ ብርቱ ሥራ ይፈልጋል!! ➙ ወደአለምአቀፍ ተቋማት እና ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ አማራዎችን የመሳብና የማሳተፍ ሥራ በስፋት ይፈልጋል። አምባ ወደ እውቀት ተኮር ፖለቲካዊ ተዋስኦዎች አጠንክሮ በመግባት አመታዊ የእውቀት ጉባኤዎችን ማከናወን መጀመር አለበት። ➙ የውጭው ከበረታ የአገር ውስጡን መከታተልና መጫን ይችላል። deliver ለሚያደርግ ብቻ ውጤት ተኮር ድጋፍ በማድረግ ወገኑን ማገዝ ይችላል።
Show all...
👍 3