ቴዲ አፍሮ teddy afro fans😘😘😘
Open in Telegram
->የቴዲ አድናቂዋች መናሀሪያ -> እዚህ ከኛጋ ለመሆን የሚያስ ፈልጋው መስፈርት ቴዲዬን መውዳድ ብቻ ->Hey everyone this channel gets the fans of tediy afro(king of 🎶🎶 )together one love
Show more7 370
Subscribers
No data24 hours
+127 days
+17330 days
Posts Archive
ተከታታይ የክረምት አኅዝቦታዊ ትምህርቱን በዩቲዩብ ገፃችን በቀጥታ ይከታተሉ
https://youtu.be/OfejW40Hd-k
Watch the Summer Public Lecture Series on our YouTube Channel
https://youtu.be/OfejW40Hd-k
#ESSS #SPLS
መጣና መጣና ደጁን ልንጠና
መጣና ባመቱ እንዴት ሰነበቱ
ክፈት በለው በሩን የንጉሱን*፪
ሙልሙል በላት ንግስቲቱን የቡሄውን
ሆያ ሆዬ ጉዴ ቴዲ ነው ኩራቴ...*፪
ሆያ ሆዬ......... ሆ
እዛማዶ.....ሆ
ነብር ይዘላል...ሆ
እዚህ ማዶ.....ሆ
አንበሳ ይዘላል.....ሆ
የኛማ ቴዲ.....ሆ
ፍቅርን ይዘምራል...
ሆያ ሆዬ ጉዴ ቴዲ ነው ኩራቴ....፪
ይሄ የማነው ቤት...."ሆ" የኮራ የደራ...."ሆ"
የቴዲ ነው ወይ...."ሆ" የዛ የቀብራራ...."ሆ"
እንደ ባሮ ውሃ ...."ሆ" ፀጥ ረጭ ያለው...."ሆ"
እንደ መቅደላ አቀበት..."ሆ" ክብሩ ያየለው...."ሆ"
የኛማ ቴዲ ...."ሆ" የዘመን ዘውድ አለው!
ሆያ ሆዬ ጉዴ ጨዋታ ነው ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያ ሆዬ ጉዴ ቴዲን ቴዲን ቴዲን ቴዲን ይላል ሆዴ..
ተው ጥራልኝ እና...ሆ አይኑን ልየው...ሆ
እንደ ሌት ኮከብ...ሆ የሚያበራው...ሆ
ከሩቅ ይስባል...ሆ የቴዲ ግርማው።
ክፈት በለው ተነሳ ያንን አንበሳ!...
ክፈት በለው ተነሳ ቴዲ ነው አንበሳ
ተው ስጠኝ እና ልሂድልህ
እንደ አረጀ ጅብ አልጭውብህ
ያረጀ ጅብስ ጮሆ ያባራል
እንደኔ ያለው ሺ አመት ይወድሃል!
ሆያ ሆዬ ጉዴ ብሯን ብሯን ብሯን ብሯን ይላል ሆዴ
ሆያ ሆዬ ነው የምንለው*፪
ኢትዮጵያ ሀገሬ ...."ሆ" ደስ ይበልሽ ...."ሆ"
ቡሄው በአልሽ ...."ሆ" ደረሰልሽ ...."ሆ"
አመት አውደ አመት ድግምና አመት ድግማና
የቴዲዬን ቤት ድገምና አመት ድገምና
ወርቅ አዝንብበት ድገምና አመት ድገምና
የነጭ ጤፍ ዘርፋፋ የወለዱት ይፋፋ
የነጭ ጤፍ ደግ ደግ የወለዱትም ይደግ
የገብስ እስር ዘለላ ቴዲን የጠላው ይጠላ
የጥንጅት ጢስ መአዛ የቴዲ ወዳጁ ይብዛ።
ክበር በሙዚቃ ንገስ በሀገር ማንም አይናገር
ክበር በክራር ክበር ጥፍ የጠላክ ይርገፍ።
@tediafrofans
@tediafrofans
ሰላም ኢትዮጵያውያን እስካሁን አርቲስቶች የጥበብ ሰዎች tiktikeሮች የሚሰጡንን challenge እየሰራን እንገኛለን አሁን ደግሞ ፈጣሪያችን (አምላካችን) አንድ challenge ሰጥቶናል እሱም ነሀሴን በመልካምነት የሚል challenge ሲሆን በውስጡ 3 packagጆችን ይዟል እነሱም
1:ፈጣሪ የፈጠረን ምንም አይነት ጨካኝ ግዴለሽ ክፉ ብንሆንም እንኳን ለንፁ ነጭ ወረቀት ሀጥያትን ለማያቁት ህፃናት ልባችን ይራራል እናም ነገን ላያዩ የሚችሉ በህይወትና በሞት መሀል የሆኑ ያለ ሀጢያታቸው የሚሰቃዩትን በአፋቸው ከሳቅ ይልቅ እንባ የሞላቸውን በልብ ህመም የሚሰቃዩትን ልጆች ነገን እናሳያቸው እናም 1ኢትዮጽያዊ የሆነ ሰው ሀብታም ድሀ ሙስሊም ክርስቲያን አማራ ኦሮሞ ሳይን ፈጣሪ በፈጠረው ሰበዕዊነቱ ሰው መሆኑ ብቻ ይህንን እነዲያደርግ ያስገድደዎል:: ከነሐሴ 1-30 በቀን 1ብር ካርድ ወደ ልብ ህሙማን የስልክ እና የገንዘብ ማሰባሰቢያ አጭር ቁጥር 6710 ላይ ok ብሎ በመላክ ቤተሰብ ይሁኑ 1መልዕክት ሲላክ 1ብር ይቆርጥባቹሀል :: እንደው የነዛ ንፁህ ነጭ ወረቀት ሀጥያት የሌለባቸውን ፍጥረቶችን እንባ ለማበስ ይችን ትንሽ ነገር ማድረግ አቅቶን በሞት ስናጣቸው ህሊናችን ይጎዳል ከሰው ከመሆናችን ጋር እንጣላለን እናም ሀብታምም ድሀም ጋር በዚህ ሰዓት አኩል ያለቺን ይቺ 1ብር ናት እናም ይቺን 1ብር ለነዛ ልጆች በሚል መርሀ ግብር እንንቀሳቀስ :: ነገር ግን ይቺንም ያጣቹ በፀሎት በሀሳብ አግዙን::
2: ፈጣሪ ሲፈጥረን እኩል አድርጎ ነው:: ህይወት ግን ሚዛናዊ አይደለችም 1ኑን ሞልታ 1ኑን አጉድላበታለች እናም የሞላልን ልብስ አማረጠን የምንለብስ ቤታችን ቁምሳጥን በልብስ ሞልቶ የፈሰሰ አለን እናም ደጃችን ላይ ሰፈራችን ወይም ደግሞ አስፓልት ላይ ብርድ እየተመቱ የሚለምኑ ፈጣሪ ከኛ አንድ አድርጎ ህይወት ከኛ በታች ያረገቻቸውን ምስኪኖች ከቁምሳጥናችን የጠበበንን የማኖደውን ብዙ ጊዜ የለበስነውን ልብስ በነሐሴ ወር የነዚህ ምስኪኖች አውጥተን በማጋራት አብረናቸው ፎቶግራፍ በመነሳት እናስቀምጠው ልክ ነሐሴ 30 ሁላችንም ያንን ፎቶ የተለያዩ social mediaዎቻችን ላይ profile picture post story እናድርገው::
3: ሀገራችን ከበፊቱ ሰላሟ የደፈረሰ ማጣት የበዛባት ፍቅር መተሳሰብ የጠፋባት ጊዜ ላይ ደርሳለች ቢሆንም እንደ ዜጋ እንደ ኢትዮጵያዊነታችን የምናደርገው ቀላሉ እና ብቸኛ ነገር ፀሎት ነው :: እስኪ ሁላችንም ከነሐሴ 1-30 ባሉት ቀናት ጠዎት ስንነሳ ፈጣሪ ሀገራችንን ከክፉ ነገር ጠብቃት ብቻ ብለን እንተኛ እናም ጠዋት ደግሞ ስንነቃም እንደዛው እናድርግ :: ማሳሰቢያ የዚህ challenge አሸናፊ ለመሆን መሳተፍና challenjun መፈፀም ብቻ በቂ ነው:: ልክ እነዚህ challenጆች እንደፈፀምን ሽልማቱ የሚሆነው መስከረም 1 የዘመን መለወጫ እና አዲስ አመት ላይ ፈጣሪ በጤና በፍቅር በመስጠት በምናገኘው ደስታ ተከበን በመተሳሰብ በቤተሰባዊ አብሮነት እንዲሁም ደግሞ በኢትዮጵያዊነት ለዛች ቀን አድርሶ አዲስ ጥሩ እና በጎ አሳቢ ማንነት ይሰጠናል::
ለ10 ሰው በማጋራት(share) ሰባዊነቶን ያሳዩ¡!
🔊እኛ challenጁን ተቀላቅለናል እናንተስ
ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ከተሰኘው መጽሐፍ ከገጽ 204-206 ካለው የተወሰደ።
የምትሰማውን ሳይሆን የሚሰማህን ተከተል,!
ኢትዮጵያ የጀብድና መስዋዕትነት እንዲሁም የአሸናፊነት ምልክት እንጂ በምርኮ የምትበዘበዝ የተሸናፊዎች መገለጫ አይደለችም፡፡ ጀግኖቿ በህይወት እያሉም ሆነ በሞታቸው ውድቀትና ባርነትን ድል ነስተው፣ ሀገርና ህዝብን በነጻነት ያቆዩ ናቸው፡፡ በዘመን መፈራረቅ ውስጥ እነዚህ ታላላቅ ሰዎች ለሚወዱት ሀገርና ህዝብ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ከፍ አድርገው ህይወታቸውን ያለስስት ገብረዋል፡፡ እኒህ ከሀገርና ከህዝብ በፊት ራስን መስዋዕት ማድረግ የሚቀድማቸው ቀደምት አባቶቻችን እንዳለመታደል ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እሳት አመድን ወለደ እንደሚባለው ከላይ እስከ ታች የተሰገሰጉ ባለጊዜ ሹመኞች ባላጠለቁት ሱሪ፣ ባልነበሩበት የጦር ግንባር፣ የድል አጥቢያ ሽለላና ፉከራቸውን እያቀለጡ ሀገርን ለባንዳ፣ ህዝባቸውን ለባርነት አሳልፈው ሲሰጡ ይስተዋላል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመረማመጃ ምንጣፋቸውን አንስተው በባዶ እግር ጉዞ እሾህ ተጎዝጉዞ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ከኔ ጀመረች ባይ ተራማጆችን መመልከት የተለመደ ነገር እየሆነ መጥቷል፡፡ በሰላም ተኝቶ ለማደር ቀርቶ ቆሞ ለመራመድ እንኳን ከእግር በፊት ዋስትና የሆናቸውን የቀደሙት አባቶቻችንን ደምና አጥንት እየከሰሱና እያንኳሰሱ የተያይዞ ገደል ጉዟቸውን ተያይዘውታል፡፡ ይህ ጊዜ የሰጠው ባለ ጠባብ ቅል አዕምሮ የሰፊዋንና ታላቋን ሀገር ነባር ርስት ሸንሽኖ ህዝብን ለመበታተን በመጣደፍ ለሰይጣን ወዶ ገብነቱን በመፍቀድ ሽምጥ የሚጋለብ ፈረስነቱን ተያይዞታል፡፡ ልዩነት እየዘራ የሰው አንገት ያጭዳል፤ ጎተራና ገበታውም የአቤል ስጋና ደም ከሆነ ሰንብቷል፡፡
በዚህ መርህ አልባ የህይወት አዙሪት ቅኝት ብዙኀኑ የውሸት ገናናዎች በእውነት ተፈትነው ይወድቃሉ፡፡ ባለራዕዩ የጥበብ ሰው በአባቶች ቅን አመለካከትና በመንፈሳዊ ጸጋ ከዘመነ መሳፍንት አዙሪት ወጥታ እያበበች የነበረችውን ሀገር ትንሽዬ መንደር ያደረጓትን ሹማምንት በአደባባይ መታገሉ ከሞት በታች የሆነ ብዙ ዋጋ አስከፍሎታል፡፡ ይሁን እንጂ ከራሱ ዝና የቀደምት ሀገሩን ክብርና የህዝብ ነጻነት ለማስከበር ሞትም ቢመጣ ጽዋውን ሊጋተው ወስኖ ጉዞውን በመጀመሩ ምንም ዓይነት ፈተና ከጉዞው ሊያስቆመው አልቻለም፡፡
በጥቂት የሚቆጠር እድሜ ውስጥ ዋጋው ተለክቶ የማይታወቅ ዕልፍ ዘርፈ-ብዙ ስራ የሰራው ጥበበኛ የወገኖቹ የጸብ ጠብመንጃ ላይ በፍቅር ቁሞ የፈሰሰውን ደም ለማድረቅ፣ የተደፋውን ለማቅናት፣ የደረቀውን ለማለምለም ደፋ ቀና እያለ ሲታትር ውቡን የወጣትነት እድሜውን ለሀገሩ ገብሯል፡፡ ቴዲ ከብዙዎቹ የሚለየው የሚሰማውን ውስጡ የሚለውን፣ የሚሰሙትን፣ ጆሯቸውን የሰጡትን እንጂ በየመንገዱ የሚሰማውን አልተከተለም፡፡ ጥላቻን ጆሮው ሲሰማ ውስጡን ፍቅር ገባው፤ መከፋፈልን ጆሮው ሲሰማ አንድ መሆን ውስጡን ገዛው፤ የወደፊቱን ጭንቅ በጆሮው ሲሰማ ልቡ የወደፊቱ ብርሃን አየው፤ ያንንም ሲከተልና ሲያቀነቅን የኖረ የመልካም መሆን አርአያ ጀግና አርቲስት ነው፡፡
መጽሐፉን ከዚህ በታች በተጠቀሱት መደብሮች ማግኘት ይችላሉ።
✔️ስታዲየም ነጃ መጽሐፍ መደብር 0910990259
✔️ለገሀር በጋሻው መጽሐፍ መደብር 0911656729
✔️ለገሀር ማድያ ያሬድ መጽሐፍ መደብር 0913094097
✔️መሳለሚያ ሆናልያት ህንፃ ቢሮ ቁጥር 156 ተኬ ማን ፕሮሞሽን 0911518012 ወይም 0921935862
✔️አራት ኪሎ 0901197837
✔️ፒያሳ አምፒር ታረቀኝ መጽሐፍ መደብር 0983294565
ለበለጠ መረጃ 0975550865 ይደውሉልን።
ቴዎድሮስ እስኪ-ነግሥ /የቴዲ አፍሮ የህይወት ጉዞ/
"የሰው ልጅ በኖረበት በየትኛውም የዓለም ስፍራ፥ ባለጸጋ ሆነ ድሃ፣ አለቃ ሆነ ምንዝር በምድር በቆየባቸው ዘመናት የፈጸመው መልካምም ሆነ መጥፎ ተግባር በትውልዶች የህይወት ገጽ ውስጥ በአንዳች መልኩ መስፈሩ አይቀሬ ነው። በዚህ የህይወት ፍሰት ውስጥ ያለፈ ሁሉም ሰው ደግሞ የኋላ ዳና፣ የዛሬ አሻራ፣ የነገም ራዕይ አለው።"
እነሆ የክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የትላንት፣ ዛሬና ነገ መልክ፡፡
መጽሐፉን ከነገ ጀምሮ በነዚህ በታች በተጠቀሱት መደብሮች ማግኘት ይችላሉ።
✔️ስታዲየም ነጃ መጽሐፍ መደብር 0910990259
✔️ለገሀር በጋሻው መጽሐፍ መደብር 0911656729
✔️ለገሀር ማድያ ያሬድ መጽሐፍ መደብር 0913094097
✔️ሜክሲኮ ኤልያስ አምደ መጽሐፍ መደብር
✔️መሳለሚያ ሆናልያት ህንፃ ቢሮ ቁጥር 156 ተኬ ማን ፕሮሞሽን 0911518012 ወይም 0921935862
✔️አራት ኪሎ 0901197837
✔️ካዛንቺስ መላ ህንጻ ጦቢያ መጽሐፍ መደብር 0913108312
✔️ፒያሳ አፒር ታረቀኝ መጽሐፍ መደብር 0983294565
እንዲሁም በሁሉም የመጻፍ መደብሮች ያገኛሉ
ለበለጠ መረጃ 0975550865 ይደውሉልን
#የተረጋገጠ
https://t.me/Exodusmarket_bot?start=MDlhZ
አዲስ ሰዎችን በመጋበዝ ብር የምናገኝበት #Bot ተገኝቷል💯 ከሌሎቹ የሚለየው ክፍያ የሚፈፀመው በቴሌብር መሆኑ ነው!
ከዚህ ቦት ለሙከራ 20 ብር ሰርቼ ተቀብያለው 🙌 እናንተም Start ብላችሁ አሁኑኑ መስራት ደምሩ።
❎ ጓደኞችን ይጋብዙ እና ለእያንዳንዱ ጓደኛ 1 ETB ይቀበሉ !
📲ክፍያ Maximum በ24 ሰአት ውስጥ ይፈፀማል
🔰መጋበዣ ሊንክ
https://t.me/Exodusmarket_bot?start=MDlhZ
ቶሎ ተጠቀሙበት ✌️
