cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መሰረተ ህይወት ሰ/ት/ቤት ❤️

"ይህ በደብረ መድሐኒት መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የመሰረተ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ቻናል ነው። በዚህ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ። መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካለዎት @narrrry @Yidna https://www.facebook.com/MHiwot2

Show more
Advertising posts
593Subscribers
-124 hours
+17 days
+1930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሆሳዕና በአርያም እንኳን አደረሳችሁ። የዛሬው የበዓል ውሎ በደብራችን በከፊሉ።
Show all...
ሆሳዕና በአርያም በዚህ ሰዓት ቤተክርስቲያን ያላችው ወንድምና እህቶቻችን የበዓሉን ድባብ በምስል አጋሩን።🙏
Show all...
አቤቱ ጌታ ሆይ፤ እንደ ኒቆዲሞስ ምስጢራትን በዓለማዊእይታ ከመመዘን የምታድነን መቼ ይሆን? በአንተ ፊትስከተናጋሪነት ወደ ትሑት አዳማጭነት የምንሸጋገረውስ መቼይሆን? ሌሎች ምን ይሉናል እያልን ከቀን ይልቅ ወደ አንተለመምጣት የምንወደው በሌሊት ነው፤ እርሱም ከሆነልን! አንተግን በቀን የመጡትን ብቻ ሳይሆን፤ ከአንተ ጋር በአደባባይእንዳይታይ በሌሊት ተደብቆ የመጣውን ኒቆዲሞስ ስንኳ ባዶእጁን ወደ መጣበት አልመለስከውም፤ አንተን ገንዞ እስከዘለዓለም “ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ” (ዮሴፍናኒቆዲሞስ ኢየሱስን ገነዙት) ተብሎ በቤተክርስቲያን አንደበትእንዲዜምለት አደረግህ እንጂ። እኛንም ‘አውቃለሁ’ ከሚል መታበይ አድነን። ባዶ እጅ ሆነን መጥነን፤ እንደ ኒቆዲሞስ ሙሉ እጅ ተቀብለን የምንሄድ እንድንሆንም ፈቃድህ ይሁንልን። መ/ር ፍሬሰንበት አድኃኖም የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የዕብራይስጥ ቋንቋ መምህር
Show all...
+• በሌሊት ለመማር የሄደው ሊቅ •+ ፀሐይ ሥራዋን ጨርሳ ቦታዋን ለሌሊቱ አስረክባለች። በቀን ትርምስምስ የሚሉት የእስራኤል ጎዳናዎች ዝምታ ሰፍኖባቸዋል። ሰዎችም ሌሊትን ለእረፍት የሰጠውን ፈጣሪ እያመሰገኑ ከድካማቸው ሊያርፉ ወደ መኝታቸው ገስግሰዋል። በዚህ ሰላማዊ ሌሊት ግን አንድ እንቅልፍ ያጣ ታላቅ የአይሁድ መምህር ነበር። ይህንን ሰው እንቅልፍ የከለከሉት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመለከታቸው ተዓምራት እና የሰማቸው ነገሮች ነበሩ። በአእምሮው ብዙ ጥያቄዎች ተፈጥረውበታል። ጌታችን በቀን ሲያስተምር ራሱ ሄዶ ቢሰማ፥ ጥያቄዎቹንም ቢጠይቅ፥ እጅግ ደስ ባለው ነበር። ይህንን ማድረግ ግን አልቻለም። ቀን ብዙ ሕዝብ ጌታን ይከተለዋልና፥ ሰዉ ሁሉ እያየው መማርና መጠየቁ ጣጣው ብዙ ሆነበት። “ታዋቂው የአይሁድ መምህር ከገሊላዊው ዘንድ ሊማር ሄደ” ብለው እንዳያዋርዱት፤ ባስ ካለ ደግሞ ከምኩራብ እንዳያባርሩት ፈራ። ጥያቄዎቹን ለራሱ እንዳያስቀራቸው ደግሞ የቀን ሰላሙንም ሆነ የሌሊት እንቅልፉን የሚነሱት ሆኑ። ብቸኛው አማራጭ ሰው ሁሉ በተኛበት እና ምስክር በሌለበት ተነስቶ መሄድ ነበር። ይህ አይሁድ መምህር በዚህ ውሳኔ ጸንቶ ተነሳና ጥያቄዎቹን እያሰላሰለ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ በሌሊት ጉዞ ጀመረ። ይህ በሌሊት ወደ ጌታችን የሄደው የአይሁድ መምህር ቅዱስ ያሬድ ሰባተኛውን የዐቢይ ጾም ሳምንት በስሙ የሰየመለት ኒቆዲሞስ ነው። ኒቆዲሞስ የአይሁድ ሊቅ እና መምህር ነበር።በእርግጥ እስራኤል ብዙ የኦሪት የሊቃውንት ያሉባት ሀገር ናት። ኒቆዲሞስ ግን በእስራኤላውያን ዘንድ ተራ ሊቅ ብቻ አልነበረም፤ በወቅቱ ‘ሳንሄድሪን’ ተብሎ የሚጠራው የአይሁድየሊቃውንት ጉባኤ አባልም ነበር እንጂ። እርሱ ሌሎች ሊቃውንት ከእርሱ ሊማሩ እና ሕግ ሊያመሳክሩ ወደ እርሱየሚሄዱለት ሊቅ የነበረ ቢሆንም፤ እርሱ ግን አለማወቁን አውቆ ከፍ ያለ ነገርን ለመማር ወደ ክርስቶስ ዘንድ በሌሊት መጣ።ሰዎች እርስ በእርስ እየተጋፉ ክርስቶስን ለማግኘት፣ መልኩንለማየት፣ ተዓምራት ሲሠራ ለመመልከት፣ ከትምህርቱንምለመስማት ይጎርፉ ነበር። ኒቆዲሞስ ግን ሰው በሌለበት ሌሊትበመሄድ ከክርስቶስ የጥበብ ውሃ እንደልቡ ማንም ሳይሻማውመቅዳት ቻለ። የጌታችንን እና የኒቆዲሞስን ውይይት በወቅቱ ከሩቅየተመለከተ ቢኖር በአንድ ቦታ ስለተገኙ ብቻ በመምህራንመካከል የሚደረግ ተራ ውይይት ሊመስለው ይችል ይሆናል።እውነታው ግን እንዲህ አይደለም። ክርስቶስ የሌሊት ፈጣሪ፤ ኒቆዲሞስ ደግሞ የሌሊት ተማሪ ነበሩና። በእድሜም ኒቆዲሞስበልጦ ይታይ ይሆናል። እውነቱ ግን ክርስቶስ እድሜየማይቆጠርለት የጊዜ አስገኝ፤ ኒቆዲሞስ ግን በጊዜ ቀንበርውስጥ እያረጀ የሚገኝ አንድ መምህር መሆኑ ነው። ሁለቱም‘መምህር’ መባላቸው እኩል እንደሚያደርጋቸው የሚያስብምአይጠፋም። እውነታው ግን ክርስቶስ የራሷ የጥበብ ፈጣሪ፤ ኒቆዲሞስ ደግሞ ጥበብን ለማግኘት የሚታክት ተማሪመሆናቸው ነበር። ባለቅኔውም “ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ፥ ኦኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የዐቢ” በማለት፥ ጣት ከጣት እንደሚበልጥ ሁሉ፥ መምህር የተባለውም ኒቆዲሞስ ከእርሱ እጅግ ለሚበለጥ ጌታችን መስገዱን አመስጥሮ የተናገረው ለዚህ ነው። በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደምናነበው ከሆነ፥ ኒቆዲሞስበክርስቶስ ፊት ሲቀርብ ያስቀደመው እውቀቱን ነበር። የጌታንተዓምራት መመልከቱን ከተናገረ በኋላ “መምህር ሆነህከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን” (ዮሐ 3:2) በማለት አዋቂነቱን በክርስቶስ ፊት ለማስመስከር ፈለገ።የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ የሆነውን ጌታ ‘መምህር’ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ተናገረ። በቀንም ሆነ በሌሊት ወደ እርሱ የሚመጡትን የማይገፋ ጌታ ግን ‘መምህር ብቻ እንዴት ትለኛለህ?’ በማለት አልገሰጸውም። እንዲያውም በከሳሾቹ ፊትዝምታን የመረጠ ጌታ፤ ለኒቆዲሞስ ግን የልቡን መልካም መሻትአይቶ ምስጢረ ጥምቀትን ገለጠለት። “እውነት እውነትእልሃለሁ፤ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርንመንግስት ሊያይ አይችልም።” (ዮሐ 3:1) በማለትምሰማያዊውን ምስጢር ከፊቱ አቀረበለት። እውቀትንበማስቀደም ከክርስቶስ ፊት ለመቅረብ የሚከረው ኒቆዲሞስ፤ አወቅሁት ያለው ሁሉ በጌታ ፊት ምንም እንዳልሆነየተገነዘበው ከዚህ ጀምሮ ነበር። ንግግራቸው እየገፋ ሲሄድምየኒቆዲሞስ ንግግሮች እያጠሩ፤ የጌታም ንግግሮች እየረዘሙሄዱ። ምሑሩ ኒቆዲሞስ አውቃለሁ ብሎ እንዳልጀመረ ሁሉ“እንዴት ሊሆን ይችላል?” ብሎ እየጠየቀ ምላሽ የሚያዳምጥትሑት ተማሪ ሆነ። ኒቆዲሞስ የክርስቶስን መልሶች ለመስማት በትሕትናከእርሱ ዘንድ ቢሄድም፤ መልሶቹን የሚመዝነው ግን እርሱ‘አውቀዋለሁ’ ከሚላቸው ዓለማዊ እይታዎች አንጻር ነበር።የዳግም ውልደት ምስጢር ሲነገረውም የመዘነው እርሱከሚያውቀው ከእናት ማኅጸን ከሚገኝ ውልደት ጋር ነበር።በእርግጥ መንፈሳዊውን እውቀት በዓለማዊ ዕይታ ሲመዝን ኒቆዲሞስ የመጀመሪያው ሰው አልነበረም። እናታችን ሣራእንደምትወልድ በሰማች ጊዜ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወትይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል።” (ዘፍ 18:12) ብላስቃ ነበር። ይህንን ያደረገችው የእግዚአብሔርን ሥራበዓለማዊ ሥርዓት ስለመዘነች ነበር። ካህኑ ዘካርያስምእንደሚወልድ ሲነገረው “እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋአርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ?” (ሉቃ 1:18) በማለትየጥርጣሬን መልስ የሰጠው የእግዚአብሔርን ተስፋ በዓለማዊዓይን ተመልክቶ ነበር። በክርስቶስ ፊት አዋቂ ሆኖ ለመታየት የሚሞክር ሁሉአላዋቂነቱ ይገለጥበታል። እመቤታችን “ገዥዎችንከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል” (ሉቃ1:52) ስትል ስለ ትሕትና ምስጢር የነገረችን ለዚሁ ነው። “ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” (ዮሐ 3፡5) የሚለውን ምስጢረ ጥምቀትን ያረገዘ ስንኝ መገንዘብ ከብዶት ሲጨነቅ የተመለከተው ጌታ፥ ሰማያዊ ምስጢራትን በዓለማዊ እይታእየተመለከተ ለተቸገረው ኒቆዲሞስ “አንተ የእስራኤል መምህርስትሆን ይህንን አታውቅም?” (ዮሐ 3:10) በማለት ውዳሴምተግሳጽም በአንዴ ቸረው። ከዚህ በኋላ ኒቆዲሞስጥያቄዎቹንም ሳይቀር አቁሞ የጥበብ ምንጭ የሆነውን ጌታማዳመጥ ብቻ ጀመረ። የሕይወታችን አካሄድ ካስተዋልነው ሲበዛ የኒቆዲሞስንይመስላል። እኛ መንገዳችንን ሁሉ ቀይሰን ስናበቃ ወደ ጌታየምንሄደው ለውሳኔ አፈጻጸም ነው። እኛ እቅድ አውጪእንሆንና እርሱን የእቅዳችን አጽዳቂ እናደርገዋለን። ይህሲተረጎም በክርስቶስ ፊት ቀርቦ እንደ ኒቆዲሞስ “እናውቃለን”ብሎ እንደማለት ነው። በክርስቶስ ፊት ተናጋሪዎች እንጂአዳማጮች መሆን አንፈልግም። ጌታ ክርስቶስ ግን ቸርና ሰውንወዳጅ ነውና፤ ተናጋሪ ሆነን ቀርበን ስንኳ አዳማጭነትንያስተምረናል። “ይህን አድርግልኝ” ከማለት “እንደ ፈቃድህይሁንልኝ” ወደ ማለት ቀስ በቀስ ያሸጋግረናል። ጌታችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብሎ ሄዶባዶውን የሚቀር የለም። ኒቆዲሞስም ቢሆን እርሱን ብሎ ሄዶሰማያዊ ምስጢርን ተቀበለ። የጌታችንን የከበረ ሰውነትበከርቤና እሬት ቅልቅል እንዲያውም በሽቶ እንደ አይሁድአገናነዝ ለመገነዝም የታደለ ሆነ። ይህ ብቻም አይደለም - በቤተክርስቲያን ቅዱስ ትውፊት መሠረት ከሁለቱ የኤማሁስመንገደኞች (ሉቃ 24፡13-35) አንዱ ኒቆዲሞስ ነበር። ጌታመጻሕፍትን ተርጉሞለት በመጨረሻም የትንሣኤውን አጥርቶ ለማየት የበቃ ሆኗል።
Show all...
‹‹ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው››  ቅዱስ  ያሬድ          ሚያዚያ ፬፤፳፻፲፮ ዓመተ ምሕረት   ከማንም አስቀድሞ አገልግሎት ለአምላካችን እግዚአብሔር ይገባል፤ በጥንተ ተፈጥሮ በመጀመሪያው ቀን የተፈጠሩት መላእክት ፈጣሪያቸውን ዘወትር ያለማቋረጥ ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያሉ እንደሚያመሰግኑት ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመጽሐፈ አክሲማሮስ ገልጾልናል፡፡ (አክሲማሮስ ዘእሑድ) በዕለተ ዓርብ ሰው ሲፈጠር እንደ መላእክቱ የፈጠረውን ጌታውን እንዲያመሰግን፣ እንዲያገለግል እንዲሁም ስሙን እንዲቀድስና ክቡርን እንዲወርስ በመሆኑም የቀደመ ሰው አዳምም አምላኩን እያመሰገነና በገነትም በጸሎት እየተጋ ኖሯል፡፡         በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት ተመዝግቦ እንደምናገኘው ጥንተ ጠላት ዲያብሎስ አምላኩን ለማመስገን ባለመፍቀዱ ተረግሞ ወደ ምድር ከተጣለ በኋላ የሰውን ዘር በተለያዩ መንገዶች በማሳት፣ ከቀናው መንገድና ከጽድቁ ጎዳና በማስወጣት ፈጣሪያቸውን እንዳያገለግሉ ያደርጋል፡፡ (ዘፍ.፩-፰፣ አክሲማሮስ ዘዓርብ)      ይህ በእርግጥ አስከፊና አሳዛኝ ቢሆንም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት  ‹‹በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ›› በማለት እንደ ነገራቸው ምንም እንኳን ጠላታችን መከራ አጽንቶና ተስፋ አስቆርጦ ብኩንና ከንቱ ሊያደርገን ቢጥርም መከራውን አልፈን፣ ሥቃያችንን ተቋቁመንና ችግራችን ተወጥተን በመልካም አገልግሎት ወደ አምላካችን መንግሥት መግባት ይቻለናል፡፡ (ዮሐ.፲፮፥፴፫)   መልካም አገልግሎት ለእግዚአብሔር አምላክ በሰውነታችን በበጎነታችን፣ በቅንነታችን፣ በትሕትናችን፣ በዕውቀታችንና በጉልበታችን የምናቅርበው የጸሎት፣ የጾም፣ የምጽዋት፣ የትሩፋትና የፍቅር አገልግሎት ነው፡፡ አምላካችንን ከማመስገን በተጨማሪ ዘወትር እርሱን በመፍራት በዕለት ኑሮአችን ልናስበውና ልናገለግለው ይገባል፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ሰው በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስት ቢሆን ክፋትና ኃጢአት ከመሥራት ርቆ ይኖራልና፡፡ በቅንነትና በትሕትና የተሞላ የማኅበራዊ ሕይወትም ይኖረዋልና፡፡ ለሌሎች ሰዎችም መልካም ከማድረግ አይቦዝንም፡፡ ከዚህም አልፎ ተርፎ ባካበተው የመንፈሳዊ እና ዓለማዊ ዕውቀት እንዲሁም ባለው ጉልበት አምላኩን ዘወትር ያገለግላል፤ ይህም ተግባሩ ለጌታው የታመነ ታማኝና ቸር አገልጋይ ያሰኘዋል፡፡     በመጽሐፍ ቅዱስ የሐዲስ ኪዳን ክፍል ወንጌል ላይ ቅዱስ ማቴዎስ የጻፈውን አንድ ታሪክ እናንሣ፤ ‹‹አንድ ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ባለጸጋ ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤  ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት፣ ለአንዱ ሁለት፣ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድር ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።››   ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው። አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ “ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት” አለ። ጌታውም “መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው።   ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ “ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት” አለ። ጌታውም “መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው።   አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ “ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ” አለ። ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ “አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁበት እንዳጭድ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፤ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት፤ ዐሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳን ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።›› (ማቴ.፳፭፥፲፬-፴)   ባለ ጸጋ የተባለው ጌታችን ነው፡፡ መክሊት የተባለው ደግሞ ከአምላካችን የተጠን የተለያዩ የአገልግሎት ጸጋዎች ናቸው፡፡ በታማኝነት ያገለገሉት ሰዎች ምሳሌ በምድራዊ ሕይወታቸው በተሰጣቸው ጸጋ በትጋት አምላካቸውን አገልግለው በመልካም ዕረፍት ገነት የገቡት ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፤ መክሊቱን የቀበረው ሰነፍ አገልጋይ ደግሞ በተሰጣቸው ጸጋ በታማኝነት ማገልገል  ሲገባቸው ያላገለገሉ ሰዎች ምሳሌ ነው፡፡   ጌታቸው ሊቆጣጠራቸው የመምጣቱ ነገር ጌታችን በዕለተ ምጽአት ለፍርድ ሲመጣ ለሁሉም በሠራው ሥራ መጠን ዋጋ ለመስጠት እንደሚመጣ የሚያመለክት ነው፡፡ ያገለገሉትን ታማኝ አገልጋየችም ለእያንዳንዱ  ‹‹ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!››  ማለቱ ታማኝ አገልጋዮች መንግሥተ ሰማያትን እንደሚወርሱ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ሰነፉ አገልጋይ ወደ ጨለማና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ቦታ መወርወሩም ኀጥአን ወደ ገሃነመ እሳት መጣላቸውን የሚያሳይ ነው፡፡   ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው›› በማለት የተናገረው ይህን የወንጌል እውነት የሚገልጽ ነው፡፡ ታማኝነትና ቸርነት ለአገልግሎታችን እጅጉን አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ታማኝ መሆን ያለ ጥርጥርና በፍጹም እውነት ለአምላካችን መገዛት፣ መታዘዝና መኖር እንዲሁም በሕጉ መኖር ነው፡፡ ይህም ለእርሱ ታምነን ያለ ሐሰት፣ ያለ ስርቆት፣ ያለ አመንዝራነት እና ያለ ክህደት ወዘተ. እንድንኖር ይረዳናል፡፡ በተሰጠንም ክሂሎት፣ ተሰጥኦና ትሩፋት ማገልገል ያስችለናል፡፡ በአንደበታችን እንድናመሰግናው፣ በእጆቻችን አጨብጭበን፣ በጣቶቻችን በገና ደርድረንና መሰንቆ መትተን እንድንዘምርለት፣ በጉልበታችን እንድንሰግድለት በልባችን እንድናፈቅረው አስተምሮናል፡፡      ቸር በመሆን ለሌሎች በለጋስነት ካለን ነገር በመስጠትና በማካፈል መኖርን አሳይቶናል፡፡ አንድ ዳቦ ያለው ግማሹን ለሌላው እንዲያካፈል፣ ሁለት ልብስ ወይም ጫማ ያለው ለሌለው እንዲሰጥ፣ ከማዕዳችን ለተራቡ እንድናበላ፣ ከማድጋችን ለተጠሙ እንድናጠጣ፣ ለተቸገሩትና ላዘኑት ቸርነት በማድረግ እንድናስተዛዝን፣ የታመሙትን እንድናስታምም የአምላካችን ቅዱስ ቃል ያዘናል፡፡ እኛም እንደ መልካም ልጆቹ ለእርሱ በመታዘዝ ታማኝና ቸር አገልጋይ እንሁን!   የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነትና ረድኤት አይለየን፤ አሜን!    
Show all...
👍 2
   ገብርኄር! Who is faithful servant?   ቸር አገልጋይ ማን ነው??   A good service is what we serve by our personhood, goodness, sincerity, humility, knowledge and energy in prayer, fasting, alms giving, deeds of benevolence and love.  Humans in addition to praising the Lord, needs to live daily in trepidation of God to serve Him. A human with trepidation of God, afar from harm and sin and become good person. He/she will also have a social life filled with sincerity and humility; Does not also desists from doing righteous for others. Moreover, with the spiritual and carnal knowledge as well as the energy, serve the Lord. This is known as a faithful and generous servant. Let us mention one story in scripted in the Holy Bible, in Matthew’s gospel (25:14-30).....read...    
Show all...
አንባብያን ሆይ! በመፃጉዕ ቦታ እኛ ብንሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልትድኑ ትወዳላችሁን? ብሎ ቢጠይቀን መልሳችን ምን ይሆን? ለራሳችን፣ ለማኅበረሰባችንና ለሀገራችን መለኮታዊውን ፈውስ በእውነት እንመኛለን ይሆን? ይህ ጥያቄ ከአካላዊው ድኅነት በዘለለ ለአእምሯዊ፣ ለስሜታዊና ለመንፈሳዊ ማንነታች ፈውስን መሻታችንን በጥልቀት ይመለከታል። እውነት ፈውስን እንፈልጋለን? ፍትሐዊነት የሰፈነበት፣ አቀመ ደካሞች መጠጊያ የሚያገኙበት፣ የተበደሉ የሚካሱበት ማኅበረሰብንስ እንናፍቃለን? ++++ ድኅነት ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቦቻችን፣ ለጎረቤቶቻችን፣ ለኅብረተሰባችን ብሎም ለሀገራችን ጭምር መሆኑን "ብቻ" በሌለበት የኦርቶዶክሳዊነት ትርጉም ውስጥ የምንረዳው እውነታ ሲሆን ልክ እንደ መፃጉዕ በእምነት ሆነን አዎ ጌታ ሆይ መዳን እንፈልጋለን ብለን ፈቀዳችንን በቅንነት ብንገልጽና አሳልፈን ብንሰጥ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ይገለጣል። አዎ አባት ሆይ ሕመምተኞች ነንና ፈውስህን እንፈልጋለን! ሊቁ አውግስጢኖስ “እምነት ያላየኸውን ማመን ነው፣ የእምነት ሽልማት ደግሞ ያመንከውን ማየት ነው”[2] ብሎ እንደጻፈ። እኛ በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት መልካም ነገርን ፈውስን ለተጠማችው ምድራችን ተስፋ እንድናደርግ ያደርገናል። ይህንም በፍጹም እምነት ተስፋ ያደረግነው መልካም ነገር ሊቁ እንዳለው የእምነታችን ሽልማት ሆኖ የምናገኝው ሲሆን ነገር ግን ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ እንዳስተማረን እምነት ያለ ሥራ የሞተ መሆኑን ቆም ብለን ማጤን ይገባናል። ++++ ‘ልባቸው የቆሰሉትን ይፈውሳል ፡ ሕማማቸውንም ይጠግናል’ መዝ ፻፵፯፥፫ ++++ 3. የጌታችን የኢየሱ ክርስቶስ ፈውስ (ዮሐ ፭፥፰) ‘ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ’ በዚህ ቁጥር ላይ የምናገኘው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ከላይ ለጠይቅነው ፈውስን የመሻት ጥያቄ የተሰጠ ታላቅ ምላሽ ነው። የጌታችን ትዕዛዝ የሻትነውን መልካም ነገር ለማግኘት ከምናደርገው ጥያቄና ጥረት ጋር በእጅጉ የሚስማማ ነው። ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በአልጋ ላይ የነበረው መፃጉዕ እንደተነሳ በዘመናት ስቃይ ውስጥ የምንገኝ እኛና ማኅበረሰባችንም በእርሱ መለኮታዊ ኃይል እንነሳለን። ይኸውም የመነሳት፣ አልጋን ተሸክሞ የመሄድና የመለወጥ ሂደት በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በእውነተኛው ሐዋርያዊ ሥልጣነ ክህነት በሚከናወኑ በቅዱሳን ምስጢራት አማካኝነት የሚፈጸም ነው፡፡ በምሥጢረ ጥምቅት ንጽሕናን ገንዘብ እናደረጋለን ይኸውም ከጥላቻ ከመለያየትና ከመገፋፋት አውጥቶ አንድ የክርስቶስ አካል ያደርገናል። ቅዱስ ቁርባንም ዘወትር በክርስቶስ አካልነት ውስጥ እንድንሆን በማድረግ በአንድነትና በአብሮነት ያስተሳስረናል። ምሥጢረ ቀንዲልም ቁስላችንን ይጠግናል ከተኛንበትም አልጋ ያነሳናል። ሌሎችም ቅዱሳት ምሥጢራት ከክብር ወደ ክብር እንድናድግ ይረዱናል። በመሆኑም አንዲት ጥምቀትን የተጠመቅን ከአንድ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የተቀበልን ኦርቶዶክሳውያን በኅብረት በመመላለስ ለህዝባችንና ለሀገራችን መፍትሄዎች መሆን ይገባናል። ++++ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ስለ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ባስተማረው ትምህርቱ “እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ የሕይወት ውኃ ምንጭ ይሆንላታል ወደ ዘላለም ሕይወትም የሚመራ የሕይወት ውኃ ምንጭ ይሆናል” [3] በማለት የቅዱሳት ምሥጢራትን ጥልቅ ትርጉም ይነግረናል። ቅዱሳት ምሥጢራት መንፈሳዊ ዕድገትና ለውጥ በማምጣት ያለምንም ልዩነትና አድልዎ ስለ እግዚአብሔር ልጆች ክብር፣ እኩልነትና ለውጥ በአንድነት እንድንቆም ይመሩናል። በቤተሳይዳ የመጠመቂያ ሥፍራ የተከናወነውን ተአምራዊ ፈውስ ስናስብ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የሰጠው መለኮታዊ ትእዛዝ አካላዊ ፈውስን ብቻ ሳይሆን ከመንፈሳዊውና ከሥነልቦናዊ እሥራትም ነፃ የመውጣትን ጥሪ ያካተተ መሆኑን እንገነዘባለን። ይህንንም ጥሪ ተከትለን ፍትሐዊነት እንደ ወንዝ የሚፈስባት ሁሉም በነጻነትና በክብር የሚራመደባትን ምድር ለመገንባት በጋራ መሥራት ይገባናል። ++++ ውድ የእግዚአብሔር ልጆች በዚህ ሳምንት እያሰብነው ያለው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የፈውስ ተአምራት ከመፃጉዕ ግለሰባዊ ማንነት በዘለለ በዘመናችን እኛን፣ ማኅበረሰባችንና ሀገራችንን የሚያጠቃልል ሰፊና ጥልቅ ትርጓሜ እንዳለው እናስተውል። እንደ ሀገር፣ ማኅበረሰብና ግለሰብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራትና ድንቅ ነገር እንደሚያስፈልገን እንመን። ለሚያጋጥሙን የተለያዩ ህመሞቻችን ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛና ዘላቂ ፈውስ በፍጹም ማግኘት አንችልም። በሀገራችን ውስጥ ከተፈጠረው የመለያየት፣ የመቃቃርና የኢ-ፍትሐዊነት ህመም ድኅነትን እናገኝ ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፈውስ የሚያስፈልገን ሲሆን የሚከፋፍሉንን እንቅፋቶች አስወግደን አንድ መሆን የምንችለው በእሱ ጸጋ ብቻ ነው። እኛም እንደ ግለሰብ ከብዙ መከራዎች፣ ፍርሃቶችና ጥርጣሬዎች ጋር ትግል ላይ እንደሆንን ይታወቃል። ይህም ትግላችን አብቅቶ ፍጽም ምሉዕነት ያለውን ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፈውስ ያስፈልገናል። በዚህም ውስጥ እርሱ በመንገዳችን ሁሉ ከእኛ ጋር አብሮ እንዲጓዝ ፈተናዎቻችንን በእምነትና በድፍረት የምንጋፈጠበትን ኃይል እንዲሰጠን በፍጹም ትህትና በጾምና በጸሎት እንትጋ። ++++ ‘የጠፋውን እፈልጋለሁ የባዘነውንም እመልሳለሁ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አጸናለሁ` ሕዝ ፴፬፥፲፮ ++++ የተወደድሽ የድኅነታችን ምክንያት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የመከራችንን ጥልቀትና የልባችንን የመፈወስና የመዳንን ምኞት አድምጠሽ የአንቺን የእምነት፣ የትህትና እና የእግዚአብሔርን ፈቃድ መታዘዘ እንድንከተል ጸጋውን ይሰጠን ዘንድ በልጅሽ ፊት አማልጅን። ++++ የሰማይ አባት ሆይ ጸሎታችንን ሰምተህ ለሀገራችን፣ ለአህጉራችንና ለዓለማችን የአንተ የፈውስና የጸጋ መሳሪያዎች እንሆን ዘንድ ጸጋህን ስጠን። በነገር ሁሉ ፈቃድህን እንድንፈልግ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም፣ የቅዱሳን እና የምእመናን ሁሉ ጸሎት የብርታትና የመጽናናት ምንጭ ይሁንልን። በአንድ ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱም ጋር ትክክል በሆነ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን!   መ/ር ቃለአብ መዝገቡ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የፈተናዎች ማስተባበሪያና ክትትል ክፍል ዋና ኃላፊ መጋቢት ፳፩ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ++++⁑⁑⁑++++ ማጣቀሻ መጻሕፍት 1.Chrysostom, John. In Evangelium S. Matthaei, homily 50:3–4, pp 58, 508–509 2.Church, D. (1999). Seeing is Believing!. Nursing times, 95(32), 53. 3. Schaff, P. (Ed.). (1980). Nicene & Post-Nicene Series 2 Vol 7: Cyril Of Jerusalem: Catechetical Lectures, Gregory Of Naziansum: Orations, Sermons, Letters, Prolegomena. A&C Black.
Show all...
👍 1
"ተንሥእ ወንሣእ ዐራተከ ወሑር ፤ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ" ዮሐንስ ፭፥፰  ፈውሳችን ከወዴት ነው? ከምኩራብ በመቀጠል የምናገኘው የዐቢይ ጾም አራተኛው ሳምንት 'መፃጉዕ' ተብሎ ይጠራል። ይህ ሳምንት ነባቤ መለኮት ተብሎ በሚጠራው የመለኮትን ነገር በምልዓት ባስተማረው በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ከቁጥር ፩ ጀምሮ እስከ ፲፭ ድረስ በተጻፈልን መሠረት ጌታችን አምላችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በጠና ደዌ ተይዞ ከአልጋው መነሳት ተስኖት በብዙ ጭንቀትና ሐዘን ውስጥ ሆኖ በቤተ ሳይዳ ፈውስን ይጠባበቅ የነበረውን ሕመምተኛ መፈወሱን መነሻ በማድረግ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምጻሞችን ስለማንጻቱ፣ ጎባጦችን ስለማቅናቱ፣ ሽባዎችን ስለመተርተሩ፣ በአጠቃላይ ለብዙ ሕመምተኞች ፈውስን ስለ መስጠቱ ፣ ስለማዳኑና ስለ ድንቅ ተአምራቱ የሚዘመርበት ፣ የሚሰብክበት ፣ የሚዘከርበትና ቅድስት ቤተክርስቲያን ዓለምን ሁሉ የምታስተምርበት ሳምንት ነው። ++++ በዚህ የዐቢይ ጾም ሳምንት ፈውስን በተጠሙ ሰዎች በተጨናነቀነው በኢየሩሳሌም መሐል በጥንታዊ ሕንፃዎች መካከል በብዙ መከራና ተስፋ የተሞላ የቤተ ሳይዳ የሕመምተኞች የመጠመቂያ ሥፍራን እናስታውሳለን። ለረጅም ዘመናት ፈውስን ለማግኘት ብዙ አቅመ ደካሞችና ፈውስን የተጠሙ ሕመምተኞች በዚህ ሥፍራ ተስብስበዋል። በቤተ ሳይዳ የቆየ የፈውስ ታሪክ ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ሳይዳ የመጠመቂያ ገንዳ አጠገብ ለረዥም ዘመናት ፈውስን ተጠምቶ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ባናወጠው ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚጥለው አስታማሚ አጥቶ አንድ ቀን ድኅነትን አገኛለሁ በሚል ተስፋ በሥፍራው በበሽታ የሚማቅቀውን ሕመምተኛ እንዳገኘው በቅዱስ ወንጌል ላይ እንመለከታለን። ++++ ይህ ግንኙነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድራዊ ሕይወታችን ለተገለልነው፣ ለተረሳነውና ለተጨቆነው ያለውን ገደብ የለሽ መለኮታዊ ፍቅርና ርኅራኄ ፣ ሥጋንም ነፍስንም የመፈወስ የማይመረመር መለኮታዊ ሥልጣኑንና በጨለማ ውስጥ የሚያበራ የተስፋችን ብርሃን እንደሆነ የምናስተውልበት ጥልቅ ማስታወሻችን ነው። ይህንንም የተቀደሰ የቅዱስ ወንጌል ምንባብ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምሪት ውስጥ ሆነን ስናሰላስለው ሁሌም አዲስ በሆነው ዘመን በማይሸረው መልእክቱ ውስጥ በሃይማኖት፣ በተቀደሰው የክርስትና ትውፊት የከበረችውንና በጽናት የተሞላችውን ምድራችንን ኢትዮጵያን እናስተውልበታለን። 1.የሕመምተኞች ሁኔታ (ዮሐ ፭፥፪-፭) ኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።  አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር። በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበር። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተከትለን ራሳችን በቤተ ሳይዳ መካከል ስናደርግ ልክ በቤተ ሳይዳ እንደነበረው የታመመው ሰው ብዙ ህመምን ፣ መከራን ፣ ስቃይንና ጉዳትን ተሸክመው በትግል ውስጥ ያሉ ነገር ግን የተረሱ ሰዎችን በምድራችን ላይ እናስተውላለን። በምድራችን ላይ ያለው እልቂት ፣ ሥር የሰደደ ድህነትና ሥራ አጥነት ፣ የመሠረተ ልማት አለመሟላት ፣ የህክምና ቁሳቁስ እጥረትና በአጠቃላይ የማኅበራዊ ፍትሕ መታጣት ብዙዎች ፈውስን እዲሹ ነገር ግን በረዳት ማጣት በአልጋቸው ላይ ሆነው እንዲማቅቁ አድርጓቸዋል። ++++ በዚህ የመጽሐፍ ክፍል ላይ የተገለጠው ሁኔታ በዘመኑ በኅብረተሰቡ ውስጥ የነበሩ ሥር የሰደዱ ሥርዓታዊ ኢፍትሐዊ ሁኔታዎችን የሚያንጸባርቅ ነው። ዓይነ ስውራን በመንገዳቸው ላይ እንደሚሰናከሉ፣ አካል ጉዳተኞችም ሊቋቋሟቸው የማይችሏቸው መሰናክሎች እንደሚገጥሟቸው፣ ሌሎችም በሥርዓት አድልዎ በድህነትና በኋላቀርነት ወጥመድ ውስጥ እንደሚቆዩ ሁሉ በዘመናችንም ኢኮኖሚያዊ፣ ትምህርታዊ፣ ማኅበራዊና በመሳሰሉ ሁኔታዎች በተያያዘ በበዙ ኢፍትሐዊ ድርጊቶች ጋር ዕለት ዕለት መታገላችንና በመከራ አዙሪት ውስጥ መዘፈቃችን  የተለመደ ሆኗል። ኢፍትሐዊ በሆነው የሀብት ክፍፍል ወይም ሠርቶ ለመለወጥ እኩል ዕድል በማጣት ምክንያት ዛሬም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ግለሰቦችና ቤተሰቦች ለኑሯቸው የሚያስፈልጋቸውን መሠረታዊ ፍላጎት እንኳን ለሟሟላት ሲቸገሩ እናስተውላለን። በትምህርት መስኩም ቢሆን ልጆች የትምህርት ዕድል በማጣት እምቅ አቅምና ችሎታቸውን እንዳያወጡ እነሱም በዛው ተመሳሳይ የሕይወት አዙሪት ውስጥ እንዲቀጥሉ እያደረጋቸው ነው። ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ሳይዳ በመገኘት ያስተማረው ተግባራዊ ነገረ መለኮት ከንፈርን ከመምጠጥና ርኅራሄን ከማሳየት በዘለለ  እጆቻችን የወደቁትን እንዲያነሱ፣ አንደበታችን ለማኅበራዊ ፍትሕ እንዲሟገት፣ ከተረሱት ጋር የሚሆን ለግፍና ለሥቃይ ቦታ የሌለው አእምሮን ገንዘብ አድርገን ወደ ተግባር እንድንገባና ጌታችንን እንድንመስል ጥሪ የሚያስተላልፍ ነው። ++++ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም የክርስቶስን አካል ማክበርና ከፍ ከፍ ማደረግ ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ እርቃኑን በሚሆንበት ጊዜ ፈጸመህ ችላ አትበለው። በብርድ ዕርቃኑን ሆኖ በውጪ ሳለ ቸል ካልከው እንግዲያውስ በቤተመቅደስ ሐር ተጎናጽፎ ስትመለከተውም ክብርን አትስጠው። ተርቤ አላበላችሁኝም ያለው ይህ የሐዲስ ኪዳን ሥጋዬ ነው ብሎም የተናገረው እርሱ ነው። ከእነዚህ ለወንድሞቼ ለአንዱ እንኳን ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ብሎ ያስተማረህ ጌታ ቅዱስ ደሙ በወርቅ ጽዋ ሞልቶ ሳለ ወንድምህ ግን በረሃብ ቢሞት መልካም ነውን? አስቀድመህ የወንድምህን ረሀብ አስታግስ ከዛም በተረፈው መቅደስህን ማስጌጥ ትችላለህ።`[1] በማለት ለህመምተኞችና በተለያየ ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች በመድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልንመስለው እንደሚገባ እጅግ ልብን በሚነኩ ቃላት ተግባራዊ ጥሪን ያስተላልፋል። በዚህ ቅዱስ የዐብይ ጾም ሳምንት የምናስበውን መፃጉን ስናሰላስል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ጥሪ ተከትለን ከተረሱት፣ ከተገለሉት፣ ከተገፉትና ከተጨነቁት ጎን በመቆምና በመካከላችንም ታናሹን በማገልገል የክርስቶስን ማንነት በማክበር እርሱን ለመምሰል የተሰጠንን የተቀደሰ አደራ ለመፈጸም እንትጋ።   2. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥያቄ፦ ፈውስን መሻት (ዮሐ ፭፥፮) ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ። ልትድን ትወዳለህን? አለው። በዚህ ክፍል ላይ የምናገኘው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥያቄ መከራና ተስፋ በመቁረጥ እንደ ዓለት ባደደረው ልብ ውስጥ ዘልቆ የሚገባ መሆኑን እናስተውላለን። የጌታችን ጥያቄ የእምነትና የፍላጎት ጥያቄ ነው።
Show all...