cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"

Show more
Advertising posts
16 219
Subscribers
+224 hours
+217 days
+20030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰው እንዴት የሕይወትን መንገድ ይጓዛል የሚለው ጥያቄ ነው ልዩነቱን የሚያመጣው። ሕይወት የእውነት ጉዳይ ስትሆን፣ ጥያቄው እንዴት በሕይወት መንገድ ላይ ትክክለኛውን አካሄድ እንሄዳለን ነው የሚሆነው፡፡ የሕይወትን መንገድ በእውነት የሚጓዝ ተጓዥ፣ መንገዱ የት ነው ብሎ አይጠይቅም፤ ይልቁንም እንዴት እንደሚጓዝ ይጠይቃል እንጂ፡፡ ሆኖም ግን ሁሉ ነገር የሚወሰነው መንገዱ ሲገኝ ይመስል፣ ትዕግስት የለሾች እንዲሁ ዝም ብለው መንገዱ የት እንዳለ በመጠየቅ ይሄንን ወሳኝ ጥያቄ ማዳፈናቸውን ከቁብ አይቆጥሩትም፡፡ መንገዱ የት ነው ያለው? ብሎ በመጠየቅ ራሱን ሊያሞኝ ፈቅዷል፡፡ ይሄንን የሕይወት መንገድ እንዴት እንደምንጓዘው ይጠይቀናል፡፡ ህላዌ ሞት እንደሆነ፥ ሞትስ ለዘርዓ - ብእሲ ኹሉ ህላዌ እንደ ኾነ ማን ያውቃል? እኛ ስንኖር ሞት አይኖርም። ሞት ሲመጣ እኛ እንደሌለን ደግሞ እናውቃለን። ሕልውና በቁስ ይጀምራል ቢባል መዋሸት ይሆናል? ቤባንያ በኾነ በኩል ድጋሜ ከጽርዐውያን እንዲህ ይባልለታል። በመጀመሪያ ምንም አልነበረም፤ ስለዚህም 'ምንም' ኖረ። በመኖሩ ግን በፍጹም ሊታወቅ አልተቻለውም ነበረ፡፡ምክንያቱም ምንም ነበርና። ሊታወቅ የማይቻለው "ምንም" ግን በመኖሩ ታወቀ። የታወቀው እርሱ ግን ከቶም ሊገለጥ አይችልም። ምክንያቱም "ምንም" ነውና። ቤባንያም ይመልሳል «ሰው ነን ያልን፣ በምንም ውስጥ የተመላለስን ምንም ሆነን ተገኘን። ምንም! ምንም! ይገባሃል? አንዲት ጥበብ ህያው ያስመሰለችን ምንም ነን!» (ገፅ፥216) መቅበዝበዛችን ፥ አንዱንም አለማድማታችን ርዕሱ ለእኛ የተገባ እንደኾነ ያሳይብናልና... በራሳችን ስቀን መንገድ ኾነን እንቀራለን። ___ © Khalid Yohannes
Show all...
🔥 2
በዚህም የኢኪዩ አመላካችነትና መሪነት ሁሉም ነገር ለኒናካዋ የሚታይ ብሩህ መንገድ ኾኖ ታየው። ኒናካዋም ፈገግ አለ። በዝግታም ለዘላለም አሸለበ። ከላይ በጠቀስነው ታሪክ ውስጥ ለህይወት የሚሆን ምን አይነት ተጨባጭ ነገር አለ? ምንም። እነዚህ 'ሩቅ ምስራቆች የማያቀሉብን የሕይወት ዳገት የለም። የአንድ ግለሰብ በህይወት እና ሞት መካከል ያለን ቅፅበት "የሕይወት ታሪክ" አድርገው ሊያስተምሩን ሲነሱ ማን ተሟገታቸው? አንድ ወዳጄ ከ'ዚህች ግራ ገብ የብልጭታ ታሪክ የገባውን ሲገልጽልኝ "በህይወት ውስጥ ጠቃሚው ነገር መንገዱ ሳይሆን ሂያጁ ራሱ ነው። በመምጣት እና መሄድ ውስጥ ‘ባለቤቱ’ ይረሳል" አለኝ። ጥሩ ነው፤ ግን እንደዚያ መኖር ይዘለቃል? እና [...] ከዚህ ጋ አያይዤ ቤባንያን ይዣት ስዞር ሳንከላውሳት ከረምኩ። መጀመሪያ እንዳልኩት ገጸባሕርያቱ ተመሣሣይ እጣዬን የያዙ ስለመሠለኝ። ከሰው ጋ ላወራባት ከጠረጴዛ እሰይማታለሁ። ከተሰየመችበት ከወዳጆቼ እንዳዳመጥነው "ቤባንያ በአንድ በኩሏ የቡድሒስት የመንገድ አተላለም ያለባት መፅሐፍ ትመስላለች" የሚሉኝ ወዳጆች አንደኛኞቹ ናቸው። አቶ መፍትሔ(ቤባንያ ውስጥ የሚገኝ ገጸ-ባሕርይ) ከነበረበት ሕይወት የነፃበትና የፀደቀበትን የመከራ መንገድ፥ እንዲኹም መዳረሻ የሆነውን "ምንምነት" ይጠቅሳሉ። ተሐድሶ ያልተካኼደበትን የቡድሒስት አካኼድ... ማለትም "ከምንምነት ወደ ምንምነት" የምትል የሒንዱ ሕይወት መፈከር ነው ግቡ የሚሉኝም አሉ። "ምንምነት" የሚል የመዳረሻ ስያሜ ግዱ ነው ለመፍትሔ? አይመስለኝም። Randomness ይታይበታል « ስያሜ የመነሻና የመድረሻ መለኪያ ቦታ አይደለም? ለፍለጋ የተነሣ ስያሜ ምን ይፈይድለታል?» ይልቅ አካባቢውን እዩት 'ውበት ፈስሶበታል' ከሰባቱ ሰማያት፣ ከእሳት፣ ከመሬት፣ ከነፋስ፣ ከውሃ፣ ከቅዱሳን መላዕክት፣ ከጨለማና ከጠፈር በኋላ የተፈጠሩ ሁሉ እዚህ ዓይንን ደስ እንዳሰኙ አሉ...» (ገፅ 206) እኔን ከዛ ይልቅ መንገዱን የመራው ኞኞ ወደ ምንምነት በማድረሱ "እሰይ ተበቀልኩት ይላል? ወይስ አሁንም በፅድቅ ሕይወቱ ያዝናል?" የሚለው እንዲሁ እንደ 'ሊትሬቸር' መዳረሻ አጓጊና ለሌላ ፅሑፍ የሚነሽጥ ይመስለኛል። መፍትሔ ወዶና ፈቅዶ ስለወጣው ሞት ማሰብ አግባብ አይደለም? ( የ'ቤባንያ' ዓለም የሚፈቅድልን ሰዋሰዉ፤ "የሞተው ሞት" ሳይኾን የወጣው ሞት የሚል ነው ) « ከተለከፍንበት የእድሜ አዙሪት የምንላቀቀው መቼ ነው? ልቤን በዕድሜ ሙሉነት የምሸነፈው?» የመፍትሔ የመጀመሪያ ጥያቄ አያይ! የእጓለ ገብረ ዮሐንስ "በተዋሕዶ ከበረ" ትውረት አሊያ ኀልዮት በሥነ ፅሑፍ ውስጥ ነፍስ ስትዘራ የምትይዘው መልክ ይኸው ነው የሚሉም እንዲኹ። «ማስረጃችሁን?» ብንላቸው የሰልፍ ሪፍሌክሲቪቲ ወይም ሰልፍ ቢጌቲንግ አተራረክ ስልቱን የመረጠበትን ምክንያት እናሥስ ነው የሚሉት። « ሰልፍ ሪፍሌክሲቪቲ ወይም ሜታፊክሽን የመምረጡ መንገድ ከትረካዎቻችንና 'ሚጣለውን ጥለን የሚነሳውን አንጠልጥለን በሚል 'Postmodernist Approaches to ethiopian Identity' ቅኝት ያመላልሰናል። ለምንድነው የአፍሪካ የድህረ ዘመናዊ አስተሳሰብ አቀንቃኞች፤ ይልቁንም በዓለማየሁ ገላጋይ መፃሕፍት ላይ ያለፈውን ሙሉ በሙሉ በማጥፋት የማይጀምሩት? (እንደ ወጉ ድኅረዘመናይነት ሙሉ የባሕል አፍራሽነት ባሕርይ ስላለው) መሳይ ከበደ(ፕ/ር) በአጭሩ የሚሉት ይኼንን ነው «...for them the negative accounts of the past is an active cause of the present. paralysis of Africans. Indeed, degrading descriptions of Africa’s past have induced Africans to secretly accept their inferiority vis-à-vis theWest.Some such withdrawal of self-confidence and sense of ambition has, in turn, persuaded Africans to admit that no other option exists for them than dependency and imitativeness » ❨Africa'S quest for a philosophy of decolonization; P.137-38❩ Self reflexivity የሚባል አካኼድ ከሥነፅሑፉ ባሻገር በሥነ-ማኅበረሰብ(sociology) እና ሥነ-ሰብ( anthropology) ያለውን ቦታ እንድናይ ይጋብዛሉ። ቤባንያ ደግሞ በሴቲንግ(መቼትና፥ ድባብ) በኩል ያረፈችበት ሸኖን፥ መፍትሔ ኢኮኖሚክስ ላይ የሚወረውራቸው ጉዳዮች፥ በትዕምርት(symbol) ደረጃ ወክሎ የመጣው ማንነት'identiy'ና፥ ቤባንያ 'ታሪክ' የሚባልን ጉዳይ ወካይ፥ በመልክም በስጋም የተዛመዷት ከበደ ሚካኤል፥ ባለቤቷ ኞኞና ከሰንቦካ ወንዝ አውጥተው ያተረፉት(ገፅ 73) የሚታይባቸውን የሞራል ልዕልና እይ ነው የሚሉን። "የሃገራችን ሰዎች አንሳ ለሞራል ልዕልና? ሁሌ ከውጪ ካልቀላቀልን አይታያችሁም ኣ?!" "አብረኸትን ተመልከት። የጋሽ ይማምን ስርዓት በራሷ መንገድ አፍርሳ ትገነባለች(ገፅ23)። አባ ገልገሎ(ኮርማ ብሩ) ስምና የቤቱን ሁሉ አቀማመጥ ይለዋውጣል(ገፅ 39)። የመጡት ሁሉ በስርዓታቸውና በታሪካቸው መሠረት ይቀርጹታል(ገፅ 26፥ 27እና 31)። ይኼ ሰው ማነኝ የሚል ቀውሱን መለሰባቸው?በፍጹም...» እንደውም ለመፍትሔ እንዲኽ ያለ ተቃውሞ የሚለው ፦ «"ከእኛ የተገኘ ዕውቀት ደሞ እነሆ” አጎነበሰ፣ ብርድ ልብሱን ጠቅልሎ ከወገቡ ጋር የተቋጠረውን ፈትቶ ወደ በርሜሉ ውስጥ ወረወረ፡፡ “እስኪ ልነሳና እንዝርቴን ላስላው፣ ምን ያቦዝነዋል ፈትሎ `ሚያድር ስው::" ፈገግ ብሎ እያየኝ። “ለእንደዚህ ያለ ማህበረሰብ፤ ገመናውን በመሸፋፈን የሺህ ዓመታት ልምድ ላለው ህዝብ ስድብህን ወደ ኋላ ደብቆ አክብሮት በማሳየት የሚያገለማ ጥንጣን ህብረተሰብ ፈትሎ ሚያድር ያስፈልገዋል፡፡ የውርደት መሠረት ላይ ኩራትን ለገነባ ሰው ከስድብ ሌላ መፍትሔ ስራይ አለው?... የለውም!! አንተ ያላፈርከው ለምንድነው? የመሸፋፈን ባህላችን ስላልገላለጠህ ነው? ከዚህ ጊዜ በኋላ የነበርክበትን ህይወት ሳትፀየፍ እንዴት እንዳለ ተቀላቀልከው? ከየት መጣሁ ብለህ እንዴት አትጠይቅም?...” » (ቤባንያ፥ ገፅ ፷፬) ጣልቃ ገብነቱን በ Jaques lecan ሳይኮአናሊስስ በኩል የሚፈታ ነው የሚሉኝም እንዲሁ አንድ ሦስት አልጠፉም። "በ 'Matheme' የሌካን ቀመር በኩል የሚፍታታ ማንነት ነው መፍትሔ የሚባል ገጸባሕርይ" ይላሉ። ብዙ አይዋጥልኝም። እነዚህ ሁሉ ታይቶ እንደሚጠፋ ስሜት በኻሊድ ውስጥ የታዩ ናቸው። (አንድ ቀን ሳይጠፉ እናናዝዛቸዋለን) የሚዋጥልኝ ይኼ ነው ቅድሚያ በአበው ንግርት፤ ከያሕያ ሱርዋርዲ ቃል እንጀምራለን። Love's Alchemy'ን ገልጠን ከውስጡ ስንኞች በሌጣው እንመዛለን። "በመንገድ ሳላችሁ በዛፉ ላይ፥ በሳሩ ላይ የምትቀቡት ጠረን የሂደትና የጥበብ ዱካችሁ ነውና እንዳታጡት ተጠንቀቁ። በአደንና ጉዞም ላይ ሳላችሁ እንዳትስቱ ለእያንዳንዷ ኢምንት ነገር መጨነቁን አትተዉ። እኩይ ወይም ሰናይ ለመባል ይበቃሉና። እናንተ ተጓዦች ናችሁ እናንተ መንገዱን ናችሁ እናንተ መድረሻውን ናችሁ፡፡ ወደራሳችሁ በምታደርጉት ጉዞ መንገዱ እንዳይጠፋችሁ ተጠንቀቁ..."
Show all...
👍 2
⎡...መንገድ ያጣ ሁሉ መንገድ ኾኖ ሲቀር...⎦ ❝ መቼ ነው ልባችንን የዕድሜ ሙሉነት የሚረታው? ከተለከፍንበት አዙሪት የሚላቀቀው? ❞ (ቤባንያ ገፅ፥፲፪) ___ አንዳንዴ የራሴን ገፀባሕርይ "ኻሊድ"ን፥ የክሪስቶፈር ኖላንን ገፀባሕርይ 'Leonard moans' እና የዓለማየሁ ገላጋይን ገፀባሕርይ 'መፍትሔ' በአንድ የሕይወት መስመር ውስጥ አገኘዋለኹ። Memento ላይ የሚታይ የጊዜ መሳከር፥ እኔን በሌላ አቅጣጫ እንዳጋጠመኝ እንዲኹ፤ የዓለማየሁ ገላጋይን "መፍትሔ"ም ሰው ጊዜን በሚረዳበት ስሜቱ በኩል ከማስተላለፍ ይልቅ እንደአማልክቱ በትዝታ ውስጥ ትዝታ እየደራረበና፥ የጊዜን ሕግ እያሳከረ ሪትሙን ለማግኘት ጥቂት የተቸገረ ገጸባሕርያት በምድር ውስጥ እንገኛለን። አዲስ አበባን 'ርቄያት ከሔድኩ ከጊዜያት በኋላ ስመለስ... ሳላርፍ ቀጥታ ፒያሳ ከዚያም ወደ አራት ኪሎ የእግር መንገድ ማድረግ ፈልጌ ሄድኩኝ። የማየው ግራ አጋባኝ። በሱለይማን ዘመን ተኝቶ በዘከርያ ዘመን እንደነቃው ኡዘይር(እዝራ) ያክል ነበር የዘመን ክፍተቱ የተሰማኝ። የዚኽን ጊዜ፥ እኔም እንደ'መፍትሔ'ና ሊዎናርድ ኹሉ "How am I supposed to feel, when I can't feel time?" ማለት አማረኝ። የተፈጠረብኝን ስሜት ማጋራት እሳት በገለባ፣ እፍ ብሎ የማንደድን ያክል ደካማ ሙክርታ እንደሆነ ይገባኛል። ሲጀመርም በዞርኩባትና በበላሁባት ከተማ ጥቂት ጊዜያት መራቅ ነው መቶ አመታትን የሚያክል ገደል የተፈጠረብኝ? አጃዒብ! በወጣትነት ዘመን ድርግም የምትል ተስፋ ከዚህች ከተማ የሚፈለፈልበትን ቦታ ያየሁ መሠለኝ። ቁጭ ተብሎ የሚታሰብ ሐሳብ ፥ ትዝ የሚል የቀን ውሎ፥ ካለን መንፈስ ተለካክቶ የሚያስደንቅ ኪነ-ሕንፃ፥ የሚውጠነጠንና የሚሸጋገር 'አርት' ማየት ዘበት ይመስል ነበር። "ከምንም በላይ ትልቁ ጠንቅ — እራስን ማጣት፥ ከራስ ጋ መጠፋፋት ነው። በሕይወታችን ውስጥ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረና እንዳልሆንን ያህል በጣም በጸጥታ ውስጥ ሊከሰት ይችላል። ሌላ ምንም አይነት ነገርን ማጣት ፡ እንዲህ በጸጥታ ሊገለጥ አይችልም— ማንኛውም። ክናድህን፥ እግርህን፥ ሚስትህን፥ ወዘተርፈ ... በእርግጠኝነት መታየቱና መታወቁ አይቀርም — እራስን መሰረቅ ሲቀር። ሶረን ኪርክጋርድ 'The Sickness Unto Death' እንዲኽ ቢለኝም፤ ምንምነትን መቀዳጀት ኩሏዊ መሆን መቻል ነው። ጠንካራን መሰረት ይዘህ ወደ አርያም ለምዘግዘግ ከሻህ ታዲያ፣ 'አልቦ' አፈር ላይ ዘርህን ዘርተህ፥ ስርህን በረዥሙ መስደድ እንደሚኖርብህ አትዘንጋ።(ግዴታዊ ቃና አለው)ኦቦ Nietzsche ; በኸርቪን ዲ ያሎም¹ በኩል "when Nietzsche wept በኩል ይቃረነኛል። በጊዜው የኖርኩባትን ከተማ ሳይ የተሰማኝ ራስን ማጣት ነበር። ሰዎች ግን ይኽ ማጣት "ለበጎና ለምልዐት መንደርደር ነው" ይሉኝ ነበር። ቆይቼ አደራጅቼ ለማሰብ ሞከርኩ። ወደ ምንምነት መሄድ ራስን ለማጣት ተመራጩ መንገድ ነው። ሁሉን የሆነ አንድ ራሱን ይሰዋል። አንድ ራሱን ፡ ለሁሉ በመሰዊያው ያቀረበ መኖሩ ምን ይጠቅመዋል?... ሰው ግን ተፈጥሮ ከሰጠው ውጪ ራሱን ዳግም ለመፍጠር የሚሽቀዳደም መሆኑ — መልከኛ፥ ልዩ፥ ያልተሟላና የማይሞላ ፤ ግን መቼውንም ወደ ባዶነት የማያሽቆለቁል ያደረገዋል (ሕያውነቱ እስከተረጋገጠ ድረስ)። ራስን ዳግም በመፍጠር ውስጥ ፈለግን ማሰሥ እንጂ ባዶነትና ራስን ማግኘት ቦታ የላቸውም። በዚህ ውስጥ ራስ "ለሌላ ይሰ'ጣል" እንጂ ለሁሉ ባለመሆኑ ሁለቱንም ፍኖቶች ይሸሻል። ❨ለሌላ ግን ለማን ይሰጣል ራስ?❩ ወደ ጥንታዊዉ የአዳም እና ሄዋን ሀጢአት ታሪክ ወስደን ልናስተውለው እንችላለን፡፡(የክርስትናን ታሪክ ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነው) አዳም እና ሄዋን ምንም ተጨማሪ እውቀትም ሆነ ለውጥ በማያሻው አለም ውስጥ ነበር የሚኖሩት ይባላል፡፡ ምርጫ የሚባልን ነገር practically አያውቁትም፡፡ ምኞትም ሆነ ህልም፣ ስቃይም ሆነ ደስታ ጉድለት ስላልነበረባቸው አያስፈልጋቸውም፡፡ እንደ እንስሳ ነበሩ፡፡ ሀጢአት የመስራት አቅም ግን ነበራቸው፡፡ …እውቀትን ለማወቅ የሚያስችል አእምሮ፤ ወሲባዊ ተራክቦን መፈፀሚያ ደግሞ የመራቢያ አካላት ከሀጢአቱ በኋላ ሳይሆን ከመጀመሪያው እነዚህ አቅሞች በተፈጥሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሀጢአት እንዳይሰሩ የሚፈልገው ፈጣሪያቸው ሀጢአትን መስሪያ ግን ከመጀመሪያው ፈጥሮ ሰጥቷቸዋል፡፡ which is Freedom of the will. እንግዲህ የመጀመሪያው እውቀት ፍሬዋን ከመብላት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፤ እንደ ኦሪት ዘልደት ሐተታ፡፡ በፊት የማያስፈልገውን ነገር ለመፈለግ… የምርጫ ብቃቱን ተጠቀመ፡፡ አንድ የቤተክርስቲያን መምህር ያካሄዱት መፈንቅለ አምላክ ነበር ብሎ ይገልጸዋል- አሪፍ ነው። እንደ አምላክ ለመሆን ወይንም እንደ ራሱ ለራሱ መሆን ፈልጎ ሳይችል ቀረ..."ሰው መሆን ክቡር" ትላለች ጂጂ የሰውን ከንቱነት እያወቀች። እውቀት ራስን በራስ ሳይሆን ራስን ከውጫዊው ተፈጥሮ ጋር በማስተሳሰር የሚገኝ ነው፡፡ ይህም ለሳርተር “ኮንሽስነስ” ይባላል።ይህም እውቀት ባዶነት ይባላል።ይህ የኤግዚዝቴንሻሊዝም ፍልስፍና … በውድቅት ዘመን የወጣ በመሆኑ ከነበረበት ዘመን ጋር ብዙ ትስስር ይኖረዋል፡፡ ጦርነቱ፥ አብዮቱ፥ ስቃዩ ... የ'ነዚህ ሁሉ የዘመን መንፈስ ገላጭ ነው፡፡ ሞቶ እየሰራ ወይንም እየኖረ የሚመስለውን የሳይንስ፣ የሀይማኖት፣ የስነ ምግባር … ባህል ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ለባህል መነሳትም ሆነ መውደቅ አስተዋፅኦ የሚያደርገው ሰው ነው፡፡ ምክንያቱም ባህል ራሱ ከእውነታ ውስጥ የሚገልፀው ስለ ሰው እውነት ብቻ ነው፡፡ የፍልስፍና ሞት አልያም የሞት ፍልስፍና … ስለ ባህል ህይወት የሚገልፅ ግለ-ታሪክ ነው፡፡ እና ግለ ታሪኩ ሲጣፍ በሰዒድ መሕዲ እንዲህ ይዘለሳል በስሜ ውርስ አለኝ ...! ለውሃል መህፉዝ ላይ የተጻፈ ፣ 'ማይሰረዝ ቀድር ፥ ለቋሚ ኹሉ የተረፈ፤ [ ከሕይወት ማድጋ ጠብታ .. ሕያው እስትንፋስን መጥለቅ፣ በአላህ ቀለም ተጽፎ ፣ ወደ መድ ፍጻሜ መዝለቅ፣ «መኖር እና መሞት» ] ነው ውርሱ። ስሄድ ...! መንገድ ...! ስኖር እስከ ህቅታዬ ስቆጥር፣ ስቆም... ¡ ትግል ¿! ስወድቅ አኺሬን በለህድ ሳጥር፣ (አ በ ቃ ኹ !) ሞቼ ነቃኹ ፥ ቋሚው ቀረ !¡ መቃብሬ ራስ'ጌ ላይ ፥ አንድ ሀረግ ሰፈረ «ኖሮ ተረስቶ ነበር ሲያልፍ በድኑ ታፈረ» ። ታዲያ ሰሞኑን ይኽን እውነት በሚያፍታታ ጨዋታ ተለክፌ ቀረኹ። ከለከፉኝ ጠይም ጨዋታዎች ደግሞ አንዱ የኒናካዋና የዜኑ መምህር አጭር ምልልስ አንዱ ነው። ኒናካዋ የሚባል የሩቅ ምስራቅ ሰው አለ አሉ። ከ"አለ" ይልቅ "ነበረ" እንበል እንጂ፤ በህይወት እና ሞት መካከል እያጣጣረ ባለበት ጊዜ የተነገረበት፥ የተተረተበት በመኾኑ። እና ነፍሱን ይማረውና ኒናካዋ ከመሞቱ ቀደም ብሎ የዜኑ መምህር ኢኪዩ ሊጎበኘው ሄዶ ‘ልመራህና ልረዳህ እችላለሁ?’ ይለዋል። የዜኑ መነኩሴ (እንዴት ያለ ደፋር መነኩሴ ነው ጃል?!) «ወዲህ የመጣሁት ብቻዬን ነው። የምሄደውም ብቻዬን ነው። እኔን ሊረዳ የሚችል ምን ነገር ይኖርሃል?» ግራ መጋባት ፊቱ ላይ አለ። ኢኪዩም እንዲህ አለ « የምትመጣ እና የምትሄድ መሆንህን ካመንክማ በእርግጥም ግራ ተጋብተሃል። መሄድ እና መምጣት የሌለበት አንድ መንገድ ላመላክትህ...»
Show all...
👍 1🔥 1
....እንጨምር ... "ተባረኪ ችግሩ አላዛር ከታሪክ ዉጭ ሆኖ ነው የሚያየኝ ። እኔ ደግሞ ታሪክ ልስራ እየለፋሁ ነው ። ጊዜዬን ለጭቁን ህዝቦች ነፃ መውጣት መስጠት ነበረብኝ ። ለምወደው ድርጅቴ መስጠት ነበረብኝ “ አዳም ፣ 242 ) :: በመሆኑም አላዛር ለተባረኪ የማይደፍር “ ፈሪ” ወይም የማይገባው “ ደደብ “ ወይም “ ከግል ስሜቱ መውጣት የከበደው ራስ ወዳድ ነው”( መረቅ ፣ 240 ) “ አማን በአዕምሮዬ መጣ :: አላዛር የሆነ ሴታ ሴት መሰለኝ። የሆነ ያልወለደኝ እማማ :: ጡት ባያጠባኝም የሆነ የወለደኝ ምንትስ። የምወደውን ልጅ ስሮጥና ስሸሽ አስታውሼው ፣ ስረጋጋ ፣ በዝምታ በልቤ እንዲህ አልኩት ፣ ማዘሬ ነህ ምንድነህ ?” (መረቅ ፣ 248) ። በላካናውያን እሳቤ ተፈጥሯዊው እውነት ትራውማ ነው እንጂ በትዕምርታዊ እርከን ዉስጥ ያለ ነገር አይደለም :: ለዚህም ነው ፋንታሲ ይህንን ትራውማ ለማከም ለሚደረገውን ጥረት መድረክ ሆኖ ብቅ የሚለው( fantasy is a setup ):: ይህ የእሷ እጣ ፈንታ ብቻ አይደለም ፤ በዘመኑ የነበሩ ወጣቶች ጣጣ ነው፤ ይህም ወጣቶቹ የወል ልቦናን ገንብተው የወል እርካታን ለመገንባትና ለማግኘት የሚዳክሩት ፣ በዢዤክ እሳቤ (Collective jouissance) ዉስጥ የሚታይ ነው :: ስሎቬኒያዊው ስሎቮን ዢዤክ እንዲህ ይላል፦ Nationalism thus becomes ‘the privileged domain of the eruption of enjoyment into the social field.’ The ‘national Cause’ is then cleverly related to Lacan’s concept of ‘the Thing’, which is closely linked with the concept of jouissance; it is itself a materialization of jouissance. እንደውም ብሔርተኝት ፣ ፋሺዝም ፣ ናዚዝምና ሌሎችም በዚህ በ Collective jouissance ውስጥ የሚታዩ ናቸዉ ይላል :: ይህም በረቀቀ መንገድ የሌሎችን ወሲባዊ እርካታን ቀንብበው ለዓላማቸው የሚያውሉ ደስታ ስራቂዎች (ብልጦች) አሉ ይለናል :- "What is at stake in ethnic tensions is always the possession of the national Thing: the ‘other’ wants to steal our enjoyment (by ruining our ‘way of life’) and/or it has access to some secret, perverse enjoyment. In short, what gets on our nerves, what really bothers us about the ‘other,’ is the peculiar way he organizes his enjoyment. In short, what gets on our nerves, what really bothers us about the ‘other,’ is the peculiar way he organizes his enjoyment. ( Slavoj Žižek ፥ 22 ) " ይህንን ሃሳብ በሜሎስ ነቅናቂ እሳቤ እናጠናክረው : “ ወሲብ ትልቅ ጉልበት ነው የወሲብን ስልጣን ወጣቶች ልብ ውስጥ እንይወጣ አድርገህ አምቀህ ለጫጫታ ትጠቀምበታለህ ። በየአቅጣጫው ታፍነውና አንድ የፖለቲካ መውጫ ብቻ ቀዳዳ ካበጀህለት ባሪያ አገኘህ ማለት ነው “ (መረቅ፥162) እዚህ ጋር በተለይ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ፣ መረቅና የስንብት ቀለማት ረቂቅ በሆኑ የስነ ልቦና ፤ የታሪክ፣ የፖለቲካ ፣ የማህበረሰብ እሳቤዎችና እጅግ በላቀ እና በተዋጣለት ኪነጥበባዊ አለም ውስጥ የተሰሩ ናቸው :: በመሆኑ እነዚህ ብሉይ (Classic ) ስራዎች በላካንያን እሳቤ በዋነኛነት በ " fantasy Structure ፣ desire እና Collective Jouissance " ውስጥ ለመተንተን ሁነኛ ማዕቀፎች መሆን ይችላሉ። ይህም አዳም ረቂቅ ፈላስፋና አሳቢ፣ ጥልቅ አንባቢና የተዋጣለት ደራሲ መሆኑን ከስራዎቹ መረዳት ይቻላል :: *** ይህ ፅሁፍ ይድነቃቸው ሰለሞን (Ph.D) ለኢትዮጲስ ጋዜጣ ፣ ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በወጣው ፅሁፍ ገፋፊነት ምክንያት የተፃፈ ነው ። በዚህም የእሱ ፅሁፍ የተሳሳታቸውን ወሳኝ ጉዳዮች ለማረም ያለመ ነው። ለዚህም ሲባል የእሱን ቴክስቶች (ከመረቅ የወሰዳቸውን ተጠቅሜያለሁ) ለንፅፅር እዲመች :: ለተጨማሪ ንባብ ምክንያት ስለሆንከኝ ምስጋና ይድረስህ :: © Teshale Kebede Bedriya
Show all...
👍 5
የላካኒያን ሳይኮአናሊሲስ እና መረቅ *** በእርግጥ "መረቅ " በኪነ ጥበብ ምትሃት ፣ በእሳቤ ጥራትና በፍልስፍናው ጥልቀት በከባዱ የሚያነቃንቅ ብሉይ ስራ ነው። እውቁ ፈረንሳዊው የሳይኮአናሊሲስ ጠበብት ዣክ ላካን፣ ሳይኮአናሊሲስ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረ ፈላስፋ ነው። ፍሩድን በጥልቀት ያጠናና በስራዎቹም ሥነ - ፅሁፍን ፣ ፊልም ፣ ፖለቲካና በማህበረሰብ ጥናት ላይ ተጽዕኖውን ማሳረፍ የቻለ አሳቢ ነው። እንደ ላካን እሳቤ "ሰው '' በዋናነት የህይውት ዘይቤው የተበጀውና መንገዱን የተቀየሰለት ቋንቋን መጠቀም ከጀመረበት ቅፅበት ጀምሮ በሚገነባው ኢ-ንቁ የአዕምሮው ክፍል ነው :: ይህም “Unconscious mind is structured like a language” ይላል። የላካንያን ኢንቁ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ትዕምርቶችና መዋቅሮች ማከናወኛ (ሚዲየም፣ ስቴጅ ) ጭምር ነው። በዋናነት አንድ ህፃናን ከተወለደ በኋላ ራሱን የሚያውቀው በእናቱ ጡት አማካይነት ነው። በዚህ ጊዜ ጨቅላው እራሱን መለየት አይችልም፤ ይልቁን ፍፁም እርሱነቱንና አካባቢውን ማገናዘብ ባልቻለበትና እራሱን በእናቱ የመስለባቸውን ደረጃዎች ያልፋል :: ጨቅላው ከእናቱ ጡት እንደተነጠል ( ከ6 እስከ 18 ወራት ያለውን ጊዜ ይሸፍናል) የእኔነት ምስሉን መቅረጽ ይጀምራል። የእናቱ አንድ አካል እንዳልሆነም ይረዳል። ይህን ego form የሚያደርግበት እርከን ላካን Imaginary order ሲል ሰይሞታል። ይህን imaginary order በማለፍ በትዕምርትና በቋንቋ ወደተዋቀረው ስርዓት ውስጥ የሚገባው ጨቅላው እናቱም ብትሆን ከሙሉ እሱነቱ የተነጠለች (M)Other እንደሆነች ይረዳል። ሕጻኑም የደስታና የእርካታ ምንጩን ትቶ በማህበረሰቡ አስቀድሞ ወደተሰሩት ፍላጎቶች ፊቱን ያዞራል። (unreplaceable lack ) በሌላ አገላለጽ ህፃኑ ተፈጥሯዊ ፍላጎቱ ፋንታሲ ወደ ፋንታሲ ሽግግር ያደርጋል :: በዚህም ህጻኑ ከተፈጥሯዊ እሱነቱ ወጥቶ በቋንቋና በትምዕርት ወደ ተዋቀረው ስርዓት ውስጥ ይገባል። ይህንን የቋንቋ ስርዓት በአርስቶትል አባባል ... “Automation:-Signifiers of the signifiers) ነው። ይህም ተፈጥሮኣዊ እሱነቱና እርካታውን ሙሉ በሙሉ የሚያጣበትና የሌሎች ፍላጎት (desires of the Other) ለተፈጥሯዊው ፍላጎቱ አማራጭ ሆኖ የሚመጣበት ነው ። ስለዚህ የላካንያን ሳይኮአናሊሲስ መሰረት የሆኑት ሶስቱ እርከኖች ማለትም Imaginary፣ Symbolic እና Real order፣ ለትዕምርታዊ ዓለም ተገዢ ይሆናሉ፡፡ በዚህም ተፈጥራዊ እውነት (real ) ሙሉ በሙሉ በቋንቋ ስለ ማይወከል ከቋንቋ ውጪ ይሆናሉ ፤ ይህንን ለካን ( Symbolic castration) ይለዋላል :: በዚህ በቋንቋ የሚመራው ግለሰብ እነዚህን ጉዳዮች በሌላ ማህበሰባዊ እውነታ (social reality) ይተካሉ :: ስለዚህም ተፈጥራዊው እውነት እና እርካታው (enjoyment) ፣ ስነ-ልቦናዊ ምስቅልቅሎሽ ( trauma) በመሆን ወደሌላ ምናባዊ አለም ወይም ፋንታሲ ሽግግር (transference) ያደርጋሉ። በዚህም ተፈጥራዊ እውነታ እና እርካታ ፋንታሲ ውስጥ ይገባሉ :: በዚህም መሰረት መረቅን በላካን ለማንበብ የተደረገውን ጥረት እንይ ፦ "ከሁሉ ለመሸሽ የምችል ዓይነት ወደ አማን ደረት ተጣበቅሁ ። አማን ጓደኛዬ ነው ፣ ጓደኛዬ ነበር፣ እና ምን አለበት? አይኖቼን ገርበብ አድርጌ አላዛርን አስባለሁ። አላዛር አ አይኖቹን ጨፍኖ እየተልቆሰቆሰ ሲያቅፈኝ። በፀሃያማ ቀን በቀስታ ታኮኝ ሲቆም ። በሃሳቤ እዛና እዛ ስቀባዥር አማን አናቴን ሲስመኝ ሰማሁት :: አላዛርን ማለም አቆምኩ :: ግራ በመጋባት ምልክት ቀና ብዬ አየሁት :: ቀና ብዬ እያየሁት ሳለሁ ሳልጠብቀው አፌ ላይ ሙሉ በሙሉ ሳመኝ ። በፍጥነት ከእቅፉ ተላቀቅሁና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቆም ብዬ ጃኬቴንና ሱሪዬ አስተካከልኩ። “ የት ነው? “አለኝ “ቤት ለመሄድ ነበር “ተራዬ እንዳልሆነ አውቃለሁ ” መኪና የለም ::ትንሽ ረጋ በይ :: ተራሽ ገና ነው” የምመልሰው አልነበረኝም ..... ይህ ሁነት በመጋቢት 1969 ተባረኪ የወጣቶች ሊግ ሰላማዊ ሰልፍ በተደረገበት ሌሊት ነው። በመጀመሪያ ተባረኪ ሰላማዊ ሰልፉን ለመሳተፍ ፈርታ ስታመነታ ነበር ። ሆኖም ፍራቻዋን ለትግል አጋሯ አማን (የእሷም ፣ የአላዘርም አብሮ አደግ) በቁንጽል ወይም በዝርዝር አትነግረውም፡፡ “ ፈሪው ወዳጄ አላዛር በልቤ ጥርጣሬ አስገብቶ ሳይሆን ይቀራል ፤ ለአማን ልነግረው አልደፈርኩም ። ግን ደግሞ የጠላቴን አይን እያየሁ ግንባሩ ላይ መጮህ እፈልጋለሁ ...” (መረቅ ፥ 246።) ከትዕምርታዊ ስርዓት ይልቅ ፣ ነገሩን በቀጥታ ለማየት ከፈለግን ተፈጥሯዊው ፍላጎት እንደሆነ እንረዳለን ። ነገር ግን ይህ ተፈጥሯዊ ፍላጎት ለማግኘት ለአማን የሚቻል አይደለም ፤ ይህም የአማን ፍላጎት ወደ ፋንታሲ ውስጥ ተሻጋሪ ይሆናል ። በመሆኑም አማን ተባረኪ የዓላዛር ፍቅረኛ መሆኗ እያወቀ እሷን ከመመኘት አላገደውም፤ ይህም ተፈጥሯዊ ፍላጐቱ ለማርካት የነበረውን ማንኛውም አጋጣሚ ከመሞከር ወደኋላ አላለም ፤ ይህም ተባረኪ በአማን አዕምሮ ውስጥ የምትንሳፈፍ ለተፈጥሮኣዊ ፍላጎቱ መልስ ሰጪ ናትና ። እዚህ ጋር የስሎቮን ዢዤክን ሀሳብ ላምጣ ፦ "For a Man ,the relationship with a women is possible only in as much as she fits his formula " ይላል :: ለዚህም አካላዊ ባይሆንም በፖለቲካው መድረክ የነበራቸው ግንኙነት ለዚህ ወሲባዊ ፍላጎት ልዋጭ ሆኖ መቅረቡን እናያለን። እንዲህ ትላለች ቴቤ ፦ " ....አማንን ሩካቤ ስጋ እምቢ ብላውም ባማረ መልክ በፖለቲካ ተራክበናል። እኔ እንደማልረሳው እሱም አይረሳኝም " ትላለች (መረቅ፥293 )። ..ሌላ እንጥቀስ ... ” የስላማዊ ሰልፉ ማግስት በመሽሽ ላይ እያለሁ ፣ ትዝ ያለኝ ብቸኛ እናቴና አላዛር ነበሩ። ለብቻዬ በኮሮኮንች ላይ እየተወለካከፍኩ ስሮጥ የከበበኝ ጨለማ ማሃል የታወሱኝ እማማና አላዛር ነበሩ። ፍቅር ከዋናው አላማዬ በላይ የሚንሳፈፍ ጉድ የለዉም (መረቅ ፥ 246)” እዚህ ጋር ተባረኪ ፣ እናቷና ዓላዛር ተያይዘው የመጡት ሁለቱም ለተፈጥሯዊ ፍላጎቷ መገኛ ቢሆኑም የነበረችው በትርክት ውስጥ ስለሆነ አታገኛቸውም ። ምክንያቱም ትዕምርታዊ አለም ተፈጥሮኣዊ እዉነት (real ) እርካታ ( jouissance) በቋንቋ አይወከሉም ፤ ይህም እንዴት ወደ ፋንታሲ ሽግግር እንደሚደርግ ከላይ አይተናል ። ይህንን ክፍተት በፋንታሲ ከተያዘ በኋላ ለሌሎች ፍላጐት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ፤ በዘመኑ የነበረው ፋንታሲ ውስጥ መጫወት የሚችል ርዕዮት ዓለም ደግሞ ማርክሲዝምና ሌኒንዝም ነው፡ ፡ በመሆኑም የማርክስ ርዕዮት ዓለም የእናቷና የዓላዛር ተቀናቃኝ ሆኖ ይመጣል ። ዢዤክ እንደሚለው (fantasy is narative) ፋንታሲ ትርክት በመሆኑ በወቅቱ የነበረው የማርክሲስም ርዕዮተ አለም አዕምሮዋን መቆጣጠር መቻሉና አዕምሮዋ ውስጥ ያለዉ የፋንታሲ መዋቅር ወዲህ በእናቷና ዓላዛር እሳቤ ወዲያ በርዕዮተ ዓለሙ ለሁለት ተከፍሎ እናያለን።
Show all...
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሐነ ትንሳዔው አደረሳችሁ። በዓሉ የሠለም፣ የጤና፣ የፍቅር እንዲሆን ከመጻሕፍት ዓለም - Book Shelf ይመኛል።
Show all...
👍 5
ትዝ ይላቹሀል? Phsyics እና Maths ላይ የነበሩ solve አርጉ ምንባላቸው problems? እና ደሞ እነዛ የMaths ረዣዥም equations? The value of 'x' ፍለጋ ብዙ ወረቀት እኮ ነው የጨረስነው። አንድ መስመር ጥያቄ ተሰጥቶን 2 ባዶ ወረቀት ለመልስ ሲያስከትሉልን የነበረው ጭንቀት አረሳውም። ከelementary እስከ ዩኒቨርሲቲ maths በጣም ከባድ ትምህርት ነው። ብዙ ለፍተን . .አጥንተን ነው የምንሰራው። ነገ Maths ነው ፈተናው ሲባል ሌሊቱ ይለያል. .እንቅልፍ አይታሰብም ነበር። ዛሬ ላይ ሆኜ ያን ሁሉ ትግል ሳስብ ቆጨኝ። ያን ሁሉ አቅሜን ያዋልኩበት ልፋት አሁን ላይ ትምህርት ጨርሼ ህይወትን ለብቻዬ ስጋፈጣት ምንም ጥቅሙ አልታይ አለኝ። ዛሬ ህይወት በብዙ አቅጣጫ ትፈትናለች። The value of 'X'ን ስለመፈለግ ያን ሁሉ ከምንማር አሁን ለሚገጥሙን ፈተናዎች መፍትሄ ፍለጋ ብንማር ምን ነበረበት? እንዲሁ በምኞት ሀሳብ ስሞላ እነዛን በስንት ጥረት የሸመደድኳቸውን equations ተጠቅሜ የአሁን ውጣውረዴን መፍታት ያምረኛል። በነዛ word problems ውስጥ ዛሬ የሚገጥመኝ የህይወት እንቅፋት ተተንትኖ ከነ አሰራሩ ተፅፎበት በነበር ብዬ እጓጓለሁ። አሁን የሚገጥመን የሴትነት ፈተና ፣ የትዳር ችግር ፣ ድብርት ፣ ብቸኝነት ፣ አምኖ መካድ ፣ የልብ ስብራት ፣ ስራ ማጣት ፣ ራስን መጥላት በየትኛው equation ነው solve ሚደረገው? እኚህን ቻሌንጆች በየትኛው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ነው የተማርነው? አልተማርንም! ዛሬ ብዙ የህይወት ገፃችንን ቢወስድም ለትምህርት የሰጠነውን ያህል ቦታ ተሰጥቶት ግን አላወቅነውም። ትምህርት አያስፈልግም አልልም። ነገር ግን ያን ያህል ሁሉን ረስተን አቅማችንን invest ልናደርግበት አይገባም። አሁን ባለንበት ሁኔታ የተማርነው እውቀት አብዛኛው የሚጠፋ ነው። የሚቀረውን ደሞ ለሆነ ድርጅት ግብዐት ሆነን በመስራት ብንጠቀመው ነው (እሱም ከተገኘ)። ከስራ ውጪ ግን ብዙውን የህይወት መንገዳችንን ሚይዝ ከተለያዩ ሰዎች ጋ መኖር ፣ ትዳር ፣ እናትነት ፣ አባትነት አለ። ቀላል አይደሉም....እስክንኖርባቸው አዲስ ናቸው። ማወቅ ፣ መዘጋጀት ፣ መጠንከር አለብን። ሁሌ ደሞ አልጋ በአልጋ አይሆኑም ማጣት ፣ መውደቅ ፣ መሰበር ይኖራቸዋል. .ለዚህስ ከማደጋችን ጋ ሚመጣ እውቀት መኖር የለበትም? ስንት ልጅ ነው ደህና ወላጅ ኖሮት እንዲህ አይነት ስለ ህይወት ትምህርት የሚያገኘው? . .አላውቅም! ግን በቃ ትምህርት የሰጠነው እድሜ አይገባውም። እሱ ላይ ብቻ መደገፍ የለብንም. .አላማችን ሊሆን አይገባም። ከልጅነት ጀምሮ ከትምህርት ጎን ለጎን ራሳችንን ምንሰራበት ህይወት ሊኖረን ይገባል። ውስጣችን ያለውን አቅም ፣ የተፈጠርንለትን አላማ ነው ማጠንከር ያለብን። እንጂማ ትምህርት ብቸኛ መንገዳችን ከሆነ 12 ላይ ወይም ዩኒቨርሲቲ ላይ ሲያልቅ ራሳችንን በማጣት እንጎዳለን። ወዴት እንደምንሄድ ሲጠፋን...ህይወታችንን በምን ማስቀጠል እንደምንችል ግራ ሲገባን አጉል አወዳደቅ እንወድቃለን። ማንፈልገውን ትምህርት በብዙ ፈተና ተምረን. .የሚገባን ቀርቶ የሚያኖረንን ስራ እንኳን ስናጣ አናሳዝንም? ለመኖር ፣ ላለመወቀስ ፣ ላለመውደቅ ብለን እንደገና ማንፈልገው ፣ ሰው ያሰመረልን መንገድ ላይ መሄድ ደሞ ይታክታል። ስለ ነገኣቹ . .ስለ ህይወታቹ አስቡ. .አላማችሁን ለዩና እሱን ዋና መንገዳቹ አድርጉት. .ራሳቹ ላይ ስሩ! ስኬት በትምህርት ብቻ አይደለም! © Nejat Hussen
Show all...
👍 7 2