cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

tobiyatewahdo 7 (ጦቢያ ተዋህዶ7 )

አስተውሉ! ሃይማኖት ያለምግባር ምግባርም ያለ ሃይማኖት አያድንም! ሃይማኖትስ ለአጋንንትም አላቸው በጎ ምግባር የላቸውምና አይድኑም። ( አጋንንትኒ የአምኑ ቦቱ ወይደነግጹ እንዳለ ) ያዕ 2 :19 @tobiyatewahdo

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
263
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥🌦🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧 #የዛሬ ሳምንት ወይም #ሰኔ 14/2012 ዓ.ም የሚታየው ቀለበታማ የፀሐይ ግርዶሽ ዝርዝር ግርዶሹ የሚታይባቸውን ከተማዎች፡ የሚጀምርበት ሰአት፤የሚያበቃበትና ምን አይነት የአየር ጸባይ እንደሚሆን እንዲሁም ፀሐይ የምትሸፈንበት መጠን በመቶኛ (በፐርሰንት ተቀምጧል) ለሁሉም ሼር አድረጉት በተለይ በገጠሩ ክፍል ያሉ ሰዎችን ይህ ግርዶሽ ከመጀመሩ በፊት ልናሳውቅ ይገባል፡፡ መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ! የተለያዩ መረጃዎችን በመዝገበ ተዋህዶ ወኦርቶዶክስ የምናቀርብ ይሆናል፡፡ ..........❐❏ 💚💛❤️ ❐❏...... ═════ •『 ♡ 』• ═════ 👉 @tewahedo123 👈 👉 @tewahedo123 👈 👉 @tewahedo123 👈 ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━━ ※※※※ @tewahedo123 ※※※※ እንድንበዛ #ሼር እናድርገው እንድንበዛ #ሼር እናድርገው #share 💚💛❤️ #share #share 💚💛❤️ #share
Show all...
..........❐❏ 💚💛❤️ ❐❏...... ═════ •『 ♡ 』• ═════ 👉 @tewahedo123 👈 👉 @tewahedo123 👈 👉 @tewahedo123 👈 ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━━ ※※※※ @tewahedo123 ※※※※ #share 💚💛❤️ #share #share 💚💛❤️ #share
Show all...
✝ሰኔ እና ሰኞ ገጠመ!✝ ☞እነሆ ሰኔ ገባ! "ምክር ለወዳጅ . . . (ለሚሰማም ሁሉ)" ☞ፖለቲካና ሐይቅ አንድ ናቸው፡፡ ከመግባትህ በፊት ዋና ስለመቻልህ እርግጠኛ ሁን፡፡ ☞ዋና መቻል ብቻውንም አይበቃህም፡፡ ለምን ትለኝ እንደሆን ሐይቅ (ፖለቲካ) ውስጥ መስጠም ብቻ ሳይሆን አዞን፡ አንበሪን በመሰሉ አራዊት መበላትም አለና፡፡ ☞ስለዚህ ዋና ሳትችል፡ ከአራዊቱም ማምለጫ ቀዳዳ (መሸሸጊያ ጓዳ) እንዳለ እርግጠኛ ሳትሆን እዋኛለሁ (እፖለትካለሁ) አትበል፡፡ ☞እንቢ ካልክ ምርጫው ያንተ ነው፡፡ እኔ ግን እንድትጸልይ እመክርሃለሁ፡፡ "" ሰኔና ሰኞን አንድ አያድርግብህ! (ምርቃት ነው!) በርግጥ ከርሞ (በ2012) ሊሆን ነው መሰለኝ፡፡ "" ☞የተባረከውን ወር ይስጠን! Dn Yordanos Abebe
Show all...
Dn Yordanos Abebe (ገብሩ ለቅዱስ ዳዊት) †✝† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †✝† =>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: +በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት:: +ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች:: +ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች:: +የአምላክ እናቱ *እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች:: *ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች:: *የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች:: *የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች:: *የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች:: *እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች:: +ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ:: +አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና:: =>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ? 1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7) 2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል): ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና:: 3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1) 4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ:: 5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: 6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና 7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው:: =>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን:: =>ግንቦት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ 2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ 3.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት 4.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ) 3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም 5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ 6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ 7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል) 8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) =>+"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7) ✝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝
Show all...
Ke Zekere kedusan kalkidan: ልጋብዛቹ ††† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ ††† ††† ደብረ ምጥማቅ ††† =>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች:: +ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ: +ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር:: +ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች:: +በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል:: +እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው:: +የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር:: +እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች:: ††† አባ መርትያኖስ ††† =>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር:: +አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው:: ††† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: ††† =>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ) 2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት) 3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ 4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ =>ወርኀዊ በዓላት 1.አበው ጎርጎርዮሳት 2.አቡነ ምዕመነ ድንግል 3.አቡነ አምደ ሥላሴ =>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17) ወስብሐት ለእግዚአብሔር @tobiyatewahdo @tobiyatewahdo
Show all...
++[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ] አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ]፦ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ ጋስጫ ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ "ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ አባ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ:: ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና ቅዱስ ዑራኤልን አስከትላ መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው ተሠወረችው:: ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው: መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር አርባ አንድ ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ናቸው) @tewahedo123 #share #share #share #share
Show all...
#Share_our_channel #Share_our_channel #Share_our_channel http://t.me/tewahedo123
Show all...
መዝገበ ተዋህዶ ወኦርቶዶክስ

"ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን" 2ኛ ቆሮ 2:14 በዚህም ቻናል የቤተክርስቲያን አባቶች ምእመናንን ያጸኑበትንና ያጽናኑበትን ፁሁፍችን እንለቃለን። እግዚአብሔር ሃይማኖታችን:ሀገራችን:እንዲሁም ምዕመናንን ይጠብቅልን።ለማንኛውም አስተያየትና ጥቆማ @i_am_tewahedo በዚህ ሊንክ ማድረስ ይቻላል።

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.