cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቅ/ጊዬርጊስ saint george

ይህ የተከፈትው ለሳንጅዬ ወዳጆች?????????

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
508
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

❤️ዘመን ተሻጋሪ❤️ #እዮባ_ሳንጃው_አበባ ዘመን ተሻጋሪ ኢትዮጵያዊው አለ እስከዛሬ ጊዮርጊስ ህዝባዊው ከሱ ሌላ ማንስ ተረፈ ከጊዜው ጋር ሁሉም አለፈ ብዙ ቢሠራ ብዙ ቢታለም ወረፋ ሆኖ የማያልፍ የለም ግን የኛ ሳንጃው ወረት አይደለም ከትውልዱ ልብ አልተነጠለም የእኛ የናንተ የሷና የሱ ይቀባበላል የታሪክ ውርሱ ህፃን አዋቂው ሴቱና ወንዱ እምነት ሳይለየው ወይ የዘር ግንዱ በጊዮርጊስ ጉዳይ አንድ አቋም አለን ሳንነጋገር እንግባባለን ሳንጃው የህፃናት ሳንጃው የወጣት ክፉ አይንካው ቅንጣት ኦሆሆ አሃሃ ኦሆሆ አሃ ሳንጃው የክርስትያኑ ሳንጃው የሙስሊሙ ይብዛለት ሠላሙ ኦሆሆ አሃሃ ኦሆሆ አሃ #አዝማች ደጋፊው ለአርማው የታመነ ነው በማልያው ስር ሁሉም አንድ ነው ማንም አይኮራም-በዘር በሃይማኖት-በማንነቱ ሠው መሆኑ ነው-የደጋፊነት-ዋና መስፈርቱ ከየት ነው-ብሎ ቋንቋና ብሔር-ማን ይጠይቃል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት-ትንሽ ትልቁ-ስለኳስ ያውቃል ሳንጃው የድሃዎቹ ሳንጃው የሃብታሞቹ ለሁሉም ሠው ነው ምቹ ኦሆሆ አሃሃ ኦሆሆ አሃ ሳንጃው የተማሪው ሳንጃው የሠራተኛው ይኑርልን አርበኛው ኦሆሆ አሃሃ ኦሆሆ አሃ #እዮባ_ሳንጃው_አበባ መዝሙሮቹን ስለላክልን በቻናላችን ተከታታዮች ስም እናመሰግናለን ✌️ @SAINTGEORGESA
Show all...
ጊዮርጊሳዊው የጥበብ ማሽን ስራውን ቀጥሏል ! ዛሬ ደግሞ በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች የታጀበ፣ ወንበር የሚያስከዳ፣ ወገብ የሚፈትን፣ ወቅቱን ገላጭ ፅናትን አሳይ ስራ ይዞልን ብቅ ብሏል! ጊዮርጊስን . . . በተግባር የሚወደውን ክለብ ማገዝ የማይሰለቸው . . . ኢዮባ ሳንጃው አበባ! "በከፍታውም - ወይ በዝቅታው ልቤ ላይ ታስሯል - ማንም አይፈታው መልካሙን ጊዜ- እየተደሰትኩ ክፉውን ጊዜ - እየተጋፈጥኩ ብርቱ ፅናቴን ይዤ እጓዛለሁ ከሳንጅዬ ጎን ሁልጊዜም አለሁ አበባ አበባ ሳንጃው አበባ : ነበርኩኝ ትናንት - አለሁኝ ዛሬ ቢያሻኝ ጨፍሬ - ቢያሻኝ ዘምሬ ክብሬ ነውና - ከቶ አልጥለውም ስሙን ከአፌ ላይ - አልነጥለውም ንብረት የለኝም - የምኩራራበት ጉልበት የለኝም - የምመካበት ግን አፌን ሞልቼ ደረቴን ነፍቼ የማወራለት የምሳሳለት ከራሴ በላይ ክለብ አለኝ ከክለብም በላይ #_አበባ_አበባ #_ሳንጃው_አበባ" ------///----- ሁለተኛውም ዝማሬ ይዘቱ ይህን ይመስላል። " ዘመን ተሻጋሪ ኢትዮጵያዊው አለ እስከዛሬ ጊዮርጊስ ህዝባዊው ከሱ ሌላ ማንስ ተረፈ ከጊዜው ጋር ሁሉም አለፈ ብዙ ቢሠራ ብዙ ቢታለም ወረፋ ሆኖ የማያልፍ የለም ግን የኛ ሳንጃው ወረት አይደለም ከትውልዱ ልብ አልተነጠለም --- ህፃን አዋቂው ሴቱና ወንዱ እምነት ሳይለየው ወይ የዘር ግንዱ በጊዮርጊስ ጉዳይ አንድ አቋም አለን ሳንነጋገር እንግባባለን ሳንጃው የህፃናት ሳንጃው የወጣት ክፉ አይንካው ቅንጣት ኦሆሆ አሃሃ ኦሆሆ አሃ ሳንጃው የክርስትያኑ ሳንጃው የሙስሊሙ ይብዛለት ሠላሙ ኦሆሆ አሃሃ ኦሆሆ አሃ ደጋፊው ለአርማው የታመነ ነው በማልያው ስር ሁሉም አንድ ነው ማንም አይኮራም-በዘር በሃይማኖት-በማንነቱ ሠው መሆኑ ነው-የደጋፊነት-ዋና መስፈርቱ ከየት ነው-ብሎ ቋንቋና ብሔር-ማን ይጠይቃል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት-ትንሽ ትልቁ-ስለኳስ ያውቃል ሳንጃው የድሃዎቹ ሳንጃው የሃብታሞቹ ለሁሉም ሠው ነው ምቹ ኦሆሆ አሃሃ ኦሆሆ አሃ ሳንጃው የተማሪው ሳንጃው የሠራተኛው ይኑርልን አርበኛው ኦሆሆ አሃሃ ኦሆሆ አሃ ምሽት ይጠብቁ! ®kasstro sanjaw @saintgeorgesa
Show all...
ሚቾ ለ ኦርላንዶ ፓይሬትስ ያስተላለፋት የስንብት መልክት ቀጣይ ማረፊያቸዉ አልታወቀም ሆኖም ወደ ታላቁ ቅዱስ ጊዩርጊስ መመለሳቸዉ እድል ሰፊ ነዉ✌️
Show all...
የ2011 የተጫዋቾች ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ደሞዝ መጠን…  August 9, 2019  ዳዊት ፀሃዬ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ደሞዝ ጣርያን በመገደብ ዙርያ ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች በ2011 የከፈሉት ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ደሞዝ ይፋ ሆኗል። በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የክለብ ላይሰንሲንግ ማናጀር የሆኑት ተድላ ዳኛቸው ዛሬ ለቀረበው የውይይት አጀንዳ መነሻ የሆነ ጥናታዊ ፅሁፍ ባቀረቡበት ወቅት የተጫዋቾች ወቅታዊ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ደሞዝን ጠቅሰዋል። በጥናቱ መሰረት በ2011 የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ሦስቱ ከፍተኛ የሊግ እርከኖች የሚከፈለው አማካይ ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያ ይንን ይመስላል። *ፕሪምየር ሊግ -ዝቅተኛ – 43,000ብር -ከፍተኛ – 304, 000ብር *ከፍተኛ ሊግ -ዝቅተኛ – 5,000ብር -ከፍተኛ – 20,000ብር *በአንደኛ ሊግ -ዝቅተኛ – 2,500ብር -ከፍተኛ – 3,500ብር በ2011 የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለአንድ ተጫዋች የከፈሉት ከፍተኛና ዝቅተኛ ደሞዝ ደግሞ ይህንን ይመስላል። (ዝ-ዝቅተኛ / ከ-ከፍተኛ) ጅማ አባ ጅፋር፡ ዝ-15,000 ከ-304,000 ፋሲል ከነማ፡ ዝ-5000 ከ-189,000 ሲዳማ ቡና፡ ዝ-74,000 ከ-213,000 ሀዋሳ ከተማ: ዝ-150,000 ከ-166,000 ቅዱስ ጊዮርጊስ፡ ዝ-3,000 ከ-100,000 አዳማ ከተማ፡ ዝ-3000 ከ-228,000 መከላከያ፡ ዝ-3,100 ከ-182,000 ደደቢት፡ ዝ-10,000 ከ-25,000 ወላይታ ድቻ፡ ዝ-5,000 ከ-155,000 ድሬዳዋ ከተማ፡ ዝ-5000 ከ-175,000 ወልዋሎ፡ ዝ-15,000 ከ-166,000 መቐለ 70 እንደርታ፡ ዝ-73,000 ከ-190,000 ደቡብ ፖሊስ፡ ዝ-6,000 ከ-27,000 ስሁል ሽረ፡ ዝ-10,000 ከ-105,000 ባህር ዳር ከተማ፡ ዝ-45,000 ከ-151,000 *ኢትዮጵያ ቡና፡ በጥናቱ ማብራሪያ ወቅት አልተጠቀሰም። © ሶከር ኢትዮጵያ
Show all...
ናቶች ያሳያሉ። በአጠቃላይ የክልሎቹ የውስጥ ውድድሮች መዳከም አቅም ያላቸውን ተጫዋቾች እንዳይወጡ ያደረገ ይሉቅንም ክለቦች በጥቂት ተጫዋቾች እንዲሽከረከሩ ያድገ እና የሚወጣው በሚልየን የሚቆጠር ገንዘብ ለብክነት የተዳረገበት የሊግ አደረጃጀት እንዳለን ጥናቱ ያሳያል። ” በተጨማሪ ጥናቱን ያቀረቡት አቶ ገዛኸኝ ከፀጥታ እና ከደህንነት አኳያ የአሁን ያለው የሊግ አደረጃጀት ያለበትን ሁኔታ አብራርተዋል። ” እግርኳሱ የሰላም የወንድማማችነት መንፈስ የተላበሰ መሆኑ ቀርቶ የሀገር ስጋት እየሆነ መጥቷል። አሁን ያለው የስፖርታዊ ጨዋነት አይደለም። አንዳንድ ቦታ እንዳየነው በሜዳው አሸንፎ እንኳን በሰላም የማትወጣባቸው ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ነው። ይህንን ችግር ለመቆጣጠር ሲባል የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተባለ ስያሜው በገለልተኛ ሜዳ የሚደረጉ ጨዋታዎች እየተበራከቱ መጥተዋል። ለእነዚህ የፀጥታ ችግሮች መፈጠር ምክንያቱ የብሔር ክለቦች መብዛት እና የክለቦቹ ስያሜዎች እና አርማዎቹ ብሔር ተኮር መሆናቸው ነው። ሌላው የእግርኳስ ሙስና የጨዋታ ውጤት ማጭበርበር በስፋት ይታያሉ። ዳኛ መያዝ ፣ የጥቅም ግኑኝነት ሠንሰለት ፕሪምየር ሊግ ለመግባት እና ላለመውረድ እንዲሁም አሸናፊ ሆኖ ለማጠናቀቅ በስፋት የእግርኳስ ሙስና እየተንፀባራቅ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል።” ብለዋል። በተጨማሪም “በእግርኳስ መሠረተ ልማት ላይ ክለቦች ትኩረት ከማድረግ ይልቅ የሚያገኙትን ገንዘብ ለውድድር ብቻ እንዲያወጡ አድርጓል። በዚህ ምክንያት የታዳጊዎች አካዳሚ ፣ የእግርኳስ መሠረተ ልማት ላይ እንዳያተኩሩ አድርጓቸዋል። ይህም በብሔራዊ ቡድን ላይ ያሳደረውን ተፅእኖ (ውድቀት) አስከትሏል።” በሚል በቁጥራዊ መረጃዎች ቀርቧል። በአጠቃላይ ይህ የሊግ አደረጃጀት ብዙ ክፍተቶች ያለበት እና አዋጭ ባለመሆኑ አማራጭ የሊግ አደረጃጀት ማቅረብ ያስፈልገል። በማለት ጠቃሚ የሆነ ምክረ ሀሳብ በጥናቱ መሠረት ለጉባዔተኛው ቀርቧል። በዚህም መሠረት ተዟዙሮ መጫወትን በማስቀረት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉም የውስጥ ውድድሩን አጠናቆ የኢትዮጵያ ሻምፒዮን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማቅረብ ጥናታዊ ፁሁፋቸውን አጠናቀዋል። በመቀጠል በቀረበው ጥናት ውይይት ከመደረጉ በፊት የአአ አስተዳደር የከንቲባው ተወካይ አቶ ኃይለሰማዕት መርሐጥበብ እንደ አንድ የስፖርት ሳይንስ ባለሙያ ጥናቶች ጠቀሜታቸውን ገልፀው ” የኢትዮጵያ ስፖርት አሁን መዳን አለበት። ለዚህም የአዲስ አበባ ቡድኖች ምሳሌ መሆን አለባቹችሁ። ይህ ጥናትን መቶ በመቶ እስማማበታለው። መፍትሄ ማበጀት ካልቻልን በእኛ ሀገር ባለው የገንዘብ አወጣጥ ስርዓት ብዙ ብክነቶች ይመጣሉ። እግርኳሳችን የፖለቲካ ማንፀባረቂያ ሆኗል። ይህ መድረክ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡናን ከክለብ ባላንጣነት ወደ ኅብረት እና አንድነት ያመጣ መሆኑ ለአዲስ አበባ እና ለእግርኳሱ ትንሣኤ ነው።” ብለዋል። በቀረበው ጥናት ዙርያ ተጨማሪ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ በቀጣይ ምን መደረግ አለበት በሚለው ዙርያ የተለያዩ ሀሳቦች ቀርበዋል። በአንድ ወገን አብዛኛዎቹ የራሳችን ውድድር የምናደርግበት የሊግ ውድድር ይኑረን ሲሉ የኢትዮጵያ መድን እና ፌደራል ፖሊስ ተወካዮች ” በሀሳቡ ሙሉ ለሙሉ ተስማምተናል። ሆኖም ለአለቆቻችን አሳውቀን እንፈርማለን።” ያሉ ሲሆን አቶ አብነት ገብረመስቀል እና መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የመጨረሻ ጠንከር ያሉ መልክቶች አስተላልፈዋል። አቶ አብነት ” የአዲስ አበባ ክለቦች እስከ ዛሬ ድረስ በየክልሉ ስንሄድ ያልደረሰብን ዛቻ እና ድብደባ የለም። በአሁን ሰዓት የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከእኛ ጎን የቆመበት ጊዜ ስለሆነ እኛ አንድ መሆን አለብን። የእኛ አንድ አለመሆን ነው ምስቅልቅሉ የወጣ ስራ አስፈፃሚ መርጠን ዋጋ እየከፈለን ያለነው። ስለዚህ ይህ አሁን ያለው የውድድር ፎርማት ይቀየር። እንደ አዲስ አበባ አንድ ሆነን በራሳችን ውድድር እናካሂድ። በዚህ ምክንያት ጉሮሯቸው የሚዘጋ ጥቅማቸው የሚቀርባቸው ግለሰቦች የተለያየ ስም ሊሰጡን ይችላሉ። እኛ የፖለቲካ የብሔር እና ቡድኖች አይደለንም። ለሀገራችን ሰላም የሚጠቅመውን ነው እያሰብን ያለነው።” ብለዋል። መቶ አለቃ ፍቃደ በበኩላቸው ” ባለፉት ጊዜያት የተለያዩ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል። አሁን ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሰናል። እስከዛሬ በነበረው የሊግ ፎርማት የኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ ከፍተኛ ሀብት ያከበቱ ግለሰቦች ምን ዓይነት ሀብት እንዳፈሩ ከነመረጃው በጥናት የምናቀርበው ይሆናል። እነዚህ ግለሰቦች የራሳችንን ውድድር ስናካሄድ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስቀር በመሆኑ እኛን ለማዳከም በየቦታው እየተንቀሳቀሱ ነው። መዘግየታችን በጣም ነው የጎዳን። ቡናና ጊዮርጊስ ማሸነፍ ስላልቻሉ ነው ፎርማቱ ይቀየር የሚሉት ይሉናል። አሁን ደግሞ የልብ ልብ ተሰምቷቸው ቡናና ጊዮርጊስ የራሳቸውን ውድድር ብቻቸውን ያድርጉ እያሉ ይሳለቁብናል። አሁን ጉዳዩ የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያን እግርኳስ ከውድቀት፣ ከሞት ለማዳን ነው። ከዚህ በኃላ ለአንድ ቀን ማደር አንችልም። ይህን የመግቢያቢያ ሰነድ መፈረም አለብን ። ” ብለዋል። በመጨረሻም ከፌደራል ፖሊስ ክለብ በቀር በስብሰባው ላይ የተገኙ ክለቦች ለእግርኳሱ ዕድገትም ሆነ አላግባብ የሚወጡ የመንግስት የገንዘብ ወጪን ለማስቀረት በሚል ከ2012 ጀምሮ በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር በመሆን ለመወዳደር በጋራ ተስማምተው ተፈራርመዋል። ስምምነታቸውንም የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሚመለከተው አካላት በሙሉ እንዲያደርስ ወስነው ጉባዔው ተጠናቋል። © ሶከር ኢትዮጵያ @saintgeorgesa @saintgeorgesa
Show all...