en
Feedback
አነቃቂ ሀሳቦች በፍጹም ፍሰሀ/Fitsum Fiseha /

አነቃቂ ሀሳቦች በፍጹም ፍሰሀ/Fitsum Fiseha /

Open in Telegram

ካልቆምክ ትደርሳለህ 🚶‍♂️🚶‍♂️🚶‍♀️🚶‍♀️

Show more
449
Subscribers
+324 hours
+137 days
+5930 days
Posts Archive
ሰላም ወዳጆች 👋 ዛሬ “የመልቀቅ ቀን ነው” በህይወት ውስጥ አንዳንድ ነገሮችን አስፈላጊውን ዋጋ ከፍሎ አጥብቆ መያዝ ተገቢ ሲሆን አንዳንድ ነገሮችን ደግሞ ጨክኖ መልቀቅ ያስፈል ጋል። የሚያስፈልግና
ሰላም ወዳጆች 👋 ዛሬ “የመልቀቅ ቀን ነው” በህይወት ውስጥ አንዳንድ ነገሮችን አስፈላጊውን ዋጋ ከፍሎ አጥብቆ መያዝ ተገቢ ሲሆን አንዳንድ ነገሮችን ደግሞ ጨክኖ መልቀቅ ያስፈል ጋል። የሚያስፈልግና የሚጠቅመንን በመግፈት የማይረባን ሲጎትቱ መኖር ትልቁ ኪሳራ ነው። ትልቁ ትርፍ ደግሞ የማይበጅን ነገር በጊዜ መልቀቅና የሚጠቅምን ነገር ከወዲሁ አጥብቆ መያዝ ነው። 1- መልቅ/መተው ያለብን -ማማረር -ስግብግብነትን -ቁጣ -ቂም -ጥላቻ -ንቀት -ጉራ/ከኔ ወዲያ ላሳር/ -ስርቆት -ዝሙት -ሀሜት -መፍረድ -ስንፍና 2-መያዝ/ማጥበቅ -ማመስገን -ደግነት -ሰላም -ይቅርታ -ፍቅር -ማክበር -ሀቀኝነት -ታማኝነት -በግልፅ መናገር -ማገዝ/መርዳት -እርጋታ -ትጋት ለመቀበል መልቀቅ ያስፈልጋል። እስኪ ዛሬ ሚሞሪ ሞልተው የሚያጨናንቁንን ሰብስበን ያስቀመጥናቸውን ውስጣዊ ሲስተማችንን ያጨናነቁ ፈይሎችን እናጥፈ።

“በከረመ እውቀት አዲስ ችግር መግጠም አያዋጣም “ ” አዲስ ነገር መማር ” በየቀኑ አዲስ ነገር መማር የሚችል በየቀኑ ማደግ ይችላል። በከረመ እውቀትና መረዳት አዲስ ውጤት አይመጣም።አዲስ ነገር ማወ
“በከረመ እውቀት አዲስ ችግር መግጠም አያዋጣም “ ” አዲስ ነገር መማር ” በየቀኑ አዲስ ነገር መማር የሚችል በየቀኑ ማደግ ይችላል። በከረመ እውቀትና መረዳት አዲስ ውጤት አይመጣም።አዲስ ነገር ማወቅ አእምሯችንን በማንቃት ውስጣዊ አሰራራችንን ያድሳል። በቀን ውስጥ 20 ደቂቃ በመመደብ ስለምንሰራው ስራ ፣ስለጤናችን ፣ስለቤተሰብ ህይወት ፣ስለመንፈሳዊ ህይወት ፣ቋንቋችንን ለማሻሻል ፣ስለ ማርኬቲንግ እና ስለ ሌሎችም ጉዳዮች እራሳችንን አዲስ ነገር በማስተማር በየቀኑ ማደግ እንችላለን። መጥረቢያ ሲሞረድ በፍጥነት እና በቀላሉ እንደሚቆርጥ ሁሉ ሰውም በአዲስ እውቀት እራሱን ሲሞርድ ውጤታማ ይሆናል። በየቀኑ በመማር ያለማወቃችንን መጠን እንቀንስ ። መልካም ቀን 🙏

👉ተሳክቷል 👏👏👏 እዚህ ሆኖ ለሚያይ ሰው ብርታትን እሚያጋባ ፣እምነትን የሚያፀና ልብን ቀጥ የሚያደርግ እርብርብ ነው። አንድ 1000,000 ዶላር ሊሞላ ጥቂት በቀረ ጊዜ በለሊት ቁጭ ብድግ እያ
+2
👉ተሳክቷል 👏👏👏 እዚህ ሆኖ ለሚያይ ሰው ብርታትን እሚያጋባ ፣እምነትን የሚያፀና ልብን ቀጥ የሚያደርግ እርብርብ ነው። አንድ 1000,000 ዶላር ሊሞላ ጥቂት በቀረ ጊዜ በለሊት ቁጭ ብድግ እያልን ነው ያየነው ። እኔ እንደዚህ የተሰማኝ እነዛ ጀግና እህትና ወንድሞች ምን ይሰማቸው ፣እንዴትስ ይደሰቱ ይሆን ?ተመስገን 👏 እግዚሀብሄር ፈቅዶ የመጀመሪያው ሳምንት እቅድ ተሳክቷል። ለአንድ ሳምንት ያለእረፍት ያገለገላችሁ ፣ሳትሰስቱ የሰጣችሁ ከናንተ ተምረናል አበርትታችሁናል።ተባረኩ። አሁንም በቀረው ጊዜ ሳንደክም ሳንሰለች ገንዘብ በመስጠት ስርጭቱን ሼር በማድረግ ላልደረሳቸው እንዲደርስ በማድረግ ከበረከቱ እንካፈል። ይህን ያደረገ ልኡል እግዚሀብሄር የተመሰገነ ይሁን።

👉Strength doesn’t come from what you can do. It comes from overcoming the things you once thought you couldn’t.
👉Strength doesn’t come from what you can do. It comes from overcoming the things you once thought you couldn’t.

👉ወደ ፊት የምንሄድበት ትልቁ ምክንያት የምንቆምበት ምክንያት አለመኖሩ ነው። መቆም የቆምክበትን ቦታ ብቻ እድል እንድትጠቀም ያደርግሀል፣መራመድ ደግሞ የማታውቀውን አዲስ እድል ወደ አንተ ያመጣል።ስ
+9
👉ወደ ፊት የምንሄድበት ትልቁ ምክንያት የምንቆምበት ምክንያት አለመኖሩ ነው። መቆም የቆምክበትን ቦታ ብቻ እድል እንድትጠቀም ያደርግሀል፣መራመድ ደግሞ የማታውቀውን አዲስ እድል ወደ አንተ ያመጣል።ስትቆም ባለህበት ታረጃለህ ወይም እንዳረጀህ ይሰማሀል። ወደ ፊት ስትሄድ መጀመሪያ ትደክማለህ ከዛ ትታደሳለህ ብሎም ትጠነክራለህ። አንድ ቦታ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ስር ይሰጠን ነበር።ስለዚህም ወደፉት የምንሄድበት ትልቁ ምክንያት የምንቆምበት ምክንያት አለመኖሩ ነው። እግዚሀብሄር ይመስገን 3ኛ ዙር ስልጠናችን እንዲህ ተጀምሯል መቀላቀል የምትፈልጉ በ0972727384 ደውሉ☎️ ….

👉 ሰምላኩን ማየት የሚፈልግ ? ሰዉየው 10 ግራም ወርቅ ሰጥተህው ካልተደሰት አምስት ግራም ብትጨምርለት ሊደሰት አይችልም።ምክንያቱም ችግሩ ከወርቁ ሳይሆን ከሰውየው የማጣጣም ችግር ነው። ማጣጣም ካልቻልክ ምግቡ ቢቀየርም ቢጨመርም ልዮነት አይፈጥርም፣ልዮነት የሚፈጥረው ምላስህ ሲድን ነው። ወዳጄ ህይወትን ማጣጣም ከተቸገርክ ይህን ልብ በል ምግብ በምላስ እንደሚጣጣመው ሁሉ ህይወትን ማጣጣም የሚቻለውም በምስጋና ነው።አመስጋኝ ካልሆንክ ምንም ቢሰጠህ አይበቃህም። የምንኖርበት አለም ዋና ስራ ደግሞ ምስጋናን መቀማት ነው። እስከ አሁን የተደረገለትን ማየት ያልቻለ ከአሁን በሀኀላ የሚደረግለት ለማየት ይቸገራል።አይኑም ልቡም ታውሯል። አምላኩ ውድ የሆኑ የማይተኩ በረከቶችን ሰጥቶት ፣ስንቱን ፈተና አሻግሮ እዚህ አድርሶት የምስጋና ህይወት ለመኖር የሚሰንፍ እሱ በረከቱን እንዳያይ በአለም የተጋርደ ነው። አለም የምታመሰግንበት ምክንያት እንድታይ አይፈልግም ምክንያቶችን ደርድሮ ካለህና ከተደረገልህ ይልቅ የሌለህ ብዙ እንደሆነ አጉሉቶ በማሳየት ቀስ እያለ ሰላምህን ፣ደስታህን እና እርጋታህን ይነጥቅሀል ከዛ አንተ እራስህ አማራሪና ተስፈ የቆረጠ ሰው ትሆናለህ። ልብ በል አለም የምስጋናህን ገመድ ከበጠሰ በኀላ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ለፈለገው አላማ የሚጠቀምህ መጫወቻ ያደርግህል ። ከዛማ ምን ልበልህ በጤናህ አትደሰትም ፣በመንጋቱ አትደሰትም ፣በመተንፈስህ አትደሰትም ፣ መራመድ በመቻልህ አትደሰትም፣ ማየት በመቻልህ አትደሰትም፣ በትዳርህ አትደሰትም ፣በልጆችህ አትደሰትም ፣በስራህ አትደሰትም ፣በጎደኞችህ አትደሰትም ………….ምክንያቱም አለም ያለህን እንዳታይ ጋርዶሀል። አምላካችንን ማስደሰት ፣ውስጣዊ ሰላም ማግኘት እና አለምን ማሸነፍ የምንችለው በምስጋና ህይወት ነው።ጠዋት አመስግኖ ሲያማርሩ መዋል ሳይሆን ከጠዋት እስከ ማታ በምስጋና መኖር ያልተነገረለት ፍትሁን መድሀኒት ነው። የምስጋና ህይወት የሚኖር ሰው አምላኩን ማየት ይችላል።ምክንያቱም የተደረገለትን ማየት የቻለ ፣ነገም የሚደረግለትን ማየት ስለሚችል አምላኩ ዛሬ ያደረገለትን አይቶ ያመሰገነ ነገም ሲያደርግለት የአምላኩን እጅ ማየት ይችላል። አምላኩን ማየት የሚፈልግ ያመስግን🙏 ሁሉም ቀን የምስጋና ቀን ነው 🙏

👉ዛሬ ምግብህን እንደመድሀኒት በጥንቃቄ ካልተመገብክ ነገ መድሀኒት እንደምግብ መብላትህ አይቀርም ። ልብ በል አሁን ትኩረት ያልሰጠህው ጤና ብዙ ሰዎች አልጋ ላይ ተኝተው የሚናፍቁት በረከት ነው:: አእምሮን እና ሰውነትን መንከባከብ ለጤናማ ህይወት እጅግ አስፈላጊ ነው። የአካልን ጤንነት መጠበቅ በርካታ ጥቅሞች አሉት ከምግባ እንጀምር 🏃🏻‍♂️🏃🏻‍♂️🏃🏻‍♂️ 1- ሰው የሚበላውን ይመስላል እንዲሉ ጤማ አመጋገብ ስርአት ማዳበር በቂ ጉልበት ማግኘት እንድንችል እና የበለጠ ብቁና ቀልጣፈ እንድንሆን ያደርጋል ሀ-ቢያንስ በቀን ውስጥ አንድ ጊዜ አትክልት ብቻ መመገብ ለ-በቂ ውሀ መጠጣት ከ1 ሊትር በላይ ሐ-አልኮል መጠጦችን ከመጠቀም መቆጠበ መ-በመጠን መመገብ ጤናማ የአመጋገብ ስርአት በራሱ ለአካል እንደ መድሀኒት ሆኖ እንደሚያገለግል ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ይህን ማድረግ ካልቻልን ውስጣዊዉ ስርአታችን ለመመራመርና እና ለመፍጠር ሊያውለው የሚገባውን ሀይል እና ትኩረት ያለ አግባብ ያስገባነውን ምግብ ለማሰተዳደር እና ጤና የሚነሱትን ምግቦች ለማስወገድ በሚያደርገው ግብ ግብ ያባክነዋል።በልቶ መና ማለት ይህ ነው😁 በአጭሩ ለመግለፅ እኛ እምንበላውን አለመምሰል አንችልም። ለማሳሌ የማይመቸንን ምግብ ስንበላ ጨጓራችን እንዴት እንደሚሆን ማየት በቂ ነው።በጨጓራ መታወክ ምክንያት ሙሉ ሰውነት ጤና ያጣል። “””” አስተውል ዛሬ ምግብህን እንደ መድሀኒት በጥንቃቄ ካልተመገብክ ነገ መድሀኒት እንደምግብ መብላትህ አይቀርም ።””””” ስለዚህ ወዳጆች በልቶ መና እንዳንሆን ሳይረፍድ አሁኑኑ እንወስን። ጤና ከሌለ ሁሉም የለም። መልካም ቀን 🙏

👉የሀብታሞቹ ምክር ሁለት የምድራችን ቁንጮ ባለሀብቶች ቢልጌት እና ዋረንቡፌት በአንድ አጋጣሚ አንድ ፕሮግራም ላይ ተገናኝተው በሻይ ሰአት ሲጫወቱ አንድ የታወቀ ጋዜጠኛ ጠጋ ብሎ ሰላምታ ከሰጣቸው በኀላ እናንተ ሁለታችሁ የአለም ቁጥር አንድ ሀብታሞች ናችሁ። አንድ ምክር ብቻ ምከሩ ብትባሉ ምንትመክራላችሁ ብሎ ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቃቸው ። ሁለቱ ቱባ ባለሀብቶች እምብዛም ሳይቸገሩ ልክ እንደተመካከረ ሰው በአንድ ቃል “Focus “ሲሉ መለሱ።ይህ ሁኔታ ለአንድ ሳምንት የሚዲያዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ልክነው እኔም ስኬታማ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንድ ብቻ ምረጥ ብባል ትኩረትን እመርጣለሁ። ትኩረት በሌለበት በሌላ በየትኛውም ጥበብ ውጤታማ መሆን አይቻልም ።ትኩረታችሁን የወሰደ ህይወታችሁን ይወስዳል። የማተኮር ብልህነት ስለትኩረት ማወቅ ፣ትኩረት ልንሰጠው የሚገባንን ጉዳይ መለየት ፣ለዛ ጉዳይ ጥራት ያለው ትኩረት መስጠት እና የሰጠነውን ትኩረት በቂ ለሆነ ጊዜ ሳይበተን ማቆየትን የሚያካትት ብልህነት ነው። 👉ዛሬ የምናደርገው 1-ትኩረት የሚፈልጉ “A” ጉዳዮች መለየት ትኩረታችንን እነዚህ ጉዳዮች ላይ ብቻ ማነጣጠር ፣ 2-ትኩረታችሁን የሚበተ‍ኑ ውስጣዊና ውጫዊ ጉዳዮች መከታተል ፣ 3-ትኩረታችሁ ተበትኖ በሀሳባችሁ ሌላ ቦታ ሄዳችሁ ወይንም ሳታስቡት የጀመራችሁትን ሳትጨርሱ ሌላ ስራውስጥ ገብታችሁ እራሳችሁን ካገኛችሁት(ሞባይል መነካካት) ፈገግ ብላችሁ በፍጥነት ትኩረትን መሰብሰብና የተጀመረውን መጨረስ። 4-ትኩረት የሚበትኑ (distractions)አስቀድሞ ከአከባቢ ማራቅ ።ሞባይል ሳይለንት ማድረግ ወይም ለሌላ ሰው መስጠት የመሳሰሉትን እርምጃዊች መውሰድ። 5-ለ45 ደቂቃ እየሰሩ 15 ደቂቃ በማረፍ ወይም ለ90 ደቂቃ እየሰሩ 30 ደቂቃ በማረፍ የትኩረትን ጥራት መጨመር።ያለእረፍት መስራት የትኩረትን ጥራት በመቀንስ ውጤትን ይቀንሳል። 6-የምናከናውነው ነገር የሚያልቅበትን ጊዜ መወሰን፣በዛው መሰረት ጀምሮ መጨረስ፣ 7- በአንድ ጊዜ አንድ ነገር ብቻ መስራት ።በአንድ ጊዜ ሁለትና ሶስት ነገር መስራት አይመከርም። 8- በትኩረት መኖርና መሰራት የሚፈጥረውን ልዮነትና የሚሰጠውን ጥቅም ማጣጣም እና እራስን ማበረታታት።

ሰላም ወዳጆች እንደምን አደራችሁ 🙏 ዛሬ ቀኑ “የዲሲፕሊን ነው” ዲሲፕሊን ማለት አቅደን የጀመርነውን ጉዳይ ደስ ቢለንም ባይለንም፣ ቢመቸንም ባይመቸንም የማድረግ ብቃት ነው።ይህ የስኬታማ ሰዎች በሀ
ሰላም ወዳጆች እንደምን አደራችሁ 🙏 ዛሬ ቀኑ “የዲሲፕሊን ነው” ዲሲፕሊን ማለት አቅደን የጀመርነውን ጉዳይ ደስ ቢለንም ባይለንም፣ ቢመቸንም ባይመቸንም የማድረግ ብቃት ነው።ይህ የስኬታማ ሰዎች በሀሪ ነው። የስኬት ህግ የመቀጠል ህግ ለው ፥ውስጣዊ እና ውጫዊ ሁኔታዎች የሚፈጥሩትን ጫና ተቋቁሞ በሙሉ ልብ መቀጠል። ሰኞ የጀመርነውን የመፈፀም ብቃት በከፍተኛ ዲሲፕሊን መቀጠል አለበት ።ለመቀጠል ደግሞ ቁርጠኝነት እና ዲሲፕሊን ያስፈልጋል።ከቆረጥን ይህን የማድረግ አቅም ደግሞ ውስጣችን አለ። መልካም ቀን 🙏