cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

azyrot አዚሮት

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
161Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
አስከፊው ጥላ አድስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ህጻናት ተማሪወችን ሳይቀር በጎሳ በማሰለፍ ኦሮሞ የሆኑትን የኦሮሞ መዝሙር እንድዘምሩ ያደርጋሉ። ከኦሮሞ ውጭ ያሉ ብሄሮች ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር እያዘመሩና በጎሳ በጎሳ እየከፋፈሏቸው እንደሆነ ተሰምቷል። ይህ አካሄድ ልክ የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ከመካሄዱ ቀድም ብሎ የተደረገ ዝግጅት ነበር።
Show all...
ታሪክን አጣቅሶ የሀገራችንን ህብረተሰብ የሚያውቅ ወላድ እናቶች ምን ያህል እንደሚከበሩና እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው መገንዘብ አያቅተውም፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን የሰብአዊ መብት ህጎችም ሆኑ የሴቶች መብቶች በተለይም ለወላድ እናቶች ጥበቃ እንደሚያደርጉ ማንም የሚያውቀው ነው፡፡ ከአጠቃላይ ህጎችም በተለየ ኢትዮጵያ ፈርማና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማፀደቅ በህገ መንግስቱ አንቅፅ 9 ‹4› መሰረት የሀገሪቱ የህግ አካል ያደረገችው የተ.መ.ድ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አንቀፅ 6 አካል ጉዳተኛ ሴቶች ሰለሚጠበቁላቸው መብቶች ደንግጓል፡፡ ባህልንና ህጎችን ብቻ ሳይሆን ህሊናንም የሚደፈጥጥ ድርጊት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጌዶ ዞን ዲላ ከተማ ጪጩ ጤና ጣቢያ መፈፀሙ ተሰምቷል፡፡ በወላድ እናት ዓይንሥውር ወ/ሮ ስምረት ጥላሁን ላይ የተፈፀመው ዘግናኝ ደርጊት በአንዲት ግለሰብ ላይ ብቻ የተፈፀመ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሳይሆን በዚች ዓይነሥውር እናት በኩል በመላ ዓይነሥውራን ላይ የተፈፀመ አሰቃቂ ድርጊት ነው፡፡ በመሆኑም ማህበራችን አጥብቆ የሚያወግዘውና የሚኮንነው ድርጊት ብቻ ሳይሆን ምንም እንኳ የተወሰኑ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውና የዞኑ ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት አካላት ክትትል እያደረጉ መሆናቸውን ብንረዳም መጠየቅ ያለባቸው አካላት ከመጠየቅ እንዳይድኑ እስከመጨረሻው ድረስ ክትትላችንን እንቀጥላለን፡፡ የኢትዮጵያ ዓይነሥውራን ብሔራዊ ማህበር
Show all...
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁለት ዙር መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን÷ የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብም እንደየዙሩ የተለያየ ነው። በዚህ መሠረትም በመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች የሲቪክስ ትምህርት ፈተና ውጤት ያልተያዘ ሲሆን÷ ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ መሆኑን ተመላክቷል፡፡ ለመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 500፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 400 ተይዟል፡፡ ለሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ደግሞ ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 500 ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት መያዙ ተገልጿል፡፡
Show all...
የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያን አያውቃትም ወይ? * የትምህርት ሚኒስቴር የአገር ተስፋ የሆኑ ወጣቶችን መፃዒ እድል ባልተገባ ሁኔታ መዝጋቱ እጅግ አሳሳቢ ነው። ከዓመት በላይ በኮሮና ምክንያት ትምህርት ዘግታ በነበረች አገር፤ ሁለመናዋን የአገር አንድነትና የሕዝብን ደኅንነት በማስቀጠል ላይ አንጠልጥላ ስትማስን በነበረች አገር ውስጥ፤…በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት ወጣቶች ከደብተርና መጽሐፍ ይልቅ በወራሪ የሽብር ቡድኑ ስለተያዙ ከተሞችና ጋራዎች በማብሰልሰል ጭንቅ ጥብብ ሲሉባት በነበረች አገር፤…የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ተፈታኞች የጦር መሣሪያ አንግተው ላይ ታች ሲባዝኑ ባጅተው ጓደኞቻቸውን ቀብረው በሕይወት የተረፉት በሚሊታሪ ዩኒፎርም ለፈተና ተቀምጠው…እያለ…በሰላሙ ጊዜ ሆኖ የማያውቀውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥቡን ከፍ ማድረግ፦ 1) በወጣቶች ሕይወት መቀለድ ነው። 2) ወጣቶቻችን ታላላቆች ልዩነታቸውን በሰለጠነ መንገድ መፍታት ባለመቻላቸው፤ የታላላቆቹ ስንፍና ሰለባዎች እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው። 3) ወጣቶች የአገራቸውን አንድነት ለማስቀጠል የከፈሉትን ተሳትፎ የሚያኮስስ ነው። 4) የትምህርት ሚኒስቴር በፈተና ወቅት ችግር አልገጠመኝም፤ «ፈተናው በሰላም ተጠናቋል» የሚል መግለጫ ከሰጠ በኋላ የሲቪክስ ፈተና እንዳይያዝ የወሰነበት አግባብም ልክነት የጎደለውና ተጠየቅ ያለበት ነው። የአገራችሁ ነገ የሚያሳስባችሁ፤ በተለይም ወላጆች ጉዳዩን በዋዛ ሳታዩት እስከመጨረሻው ድረስ በመታገል፤ ትምህርት ሚኒስቴር የወሰነውን ውሳኔ ዳግም እንዲያጤን በምታደርጉት ሂደት በተገቢው ሁሉ ከወላጆችና ከተማሪዎች ጎን የምቆም መሆኑንም መግለጽ እፈልጋለሁ። 📝ክርስቲያን ታደለ
Show all...
ምነኛ መታደል ነው? ጫጫታው ግርግሩ፤ ሁካታው ሽብሩ፤ ረሃብ ቸነፈሩ፤ ስደት ስናይፐሩ፤ ቂም በቀል ነገሩ በመላባት በዚህች አለም ከማውራት ከመናገር ታቅቦ፤ ችሎ ማለፍን፤ መታገሥን በህይወት ተገንዝቦ መቆየት እውነት እንዴት ያለ ልብ ቢኖር ነው? በተኩላዎች ከተማ በግ፤ በእኩዮች በክፉዎች ዘመን ደግ ሆኖ ማረፍ እንዴት ያለ መመረጥ ነው? እንደ ሊቁና ቅዱሥ ዮሃንስ አፍወርቅ ቤቱን ወደ ገዳምነት የቀየረበትን እምነት መቀዳጀት፤ የማትጠፋውን የሰውነትን እሣት ምላስን ከርችሞ፤ ልሣንን ለጉሞ እንዲህ በአርምሞ ኖሮ ከምድራዊ ድካም ማረፍ ምነኛ መታደል ነው? እኮ ምነኛ መሠጠት? ተዘከረነ እግዚኦ አምላከ አቡነ መርቆሪዎሥ በውሥተ መንግስትከ! የአቡነ መርቆሪዎስ አምላክ ተለመነን! ቅዱሥነትዎ! ቡራኬዎ ከምትወዷት ሀገርዎ ከኢትዮጵያና ከልጅዎችዎ ከህዝቧ ጋር ትኑር! በረከትዎ አይለየን! በሀጢዓት ባህር ለተዘፈቅሁ ለእኔ ለወልደትንሣኤ ለከንቱውና ለከርታታው ልጅዎ ይለምኑልኝ! አሜን! (ሰላም ለተፈጥሮና ለፍጡራን በሙሉ ይሁን!) አያሌው ተስፋዬ. https://t.me/joinchat/RuPmDA5drDKAAwxd https://t.me/joinchat/L50fVzoeFhsxYjZk
Show all...
ስለ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሐውልት! ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ፈረስ ላይ በግርማ ሞገስ ተቀምጠው የሚታየው ይህ ሐውልት፤ የተሰራው በልጃቸው ንግሥት ዘውዲቱ ጊዜ እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ይጠቅሳሉ። ንግሥቲቱ ሐውልቱን ያሠሩት የአባታቸው የአፄ ምኒልክ ማስታወሻ እንዲሆን በማሰብ ነው። ሐውልቱ ሁለት ነገሮችን ያመላክታል፤ እነርሱም ፀረ ቅኝ ግዛት ትግል እና የስልጣኔ ራእይ ናቸው። ሐውልቱ የተሰራው ከመዳብ ነው፤ የተቀረጸው ደግሞ በጀርመናዊው አርክቴክት ሃርትል ስፒንግለር ሲሆን፣ የተቀረፀው ጀርመን አገር ነው። ሐውልቱ በጀርመን አገር ተሠርቶ ከመጣ በኋላ የሚቆምበት ቦታ በዝግጅት ላይ እያለ ንግሥት ዘውዲቱ በድንገት መጋቢት 24 ቀን 1922 ዓ.ም. አረፉ። ነገር ግን የተጀመረውን ሥራ የንግሥቲቱን አልጋ የወረሱት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንዲጠናቀቅ በማድረግ፤ በንግሥናቸው በዓል ዋዜማ ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም. በታላቅ ክብር ተገልጧል። አፄ ምኒልክ በሐውልቱ ላይ የሚታዩት ካባ ለብሰውና በእጃቸው ደግሞ ጣምራ ጦር ይዘው ነው። ይጋልቡበት በነበረው በፈረሳቸው በ‹ዳኘው› ላይ ተቀምጠው የሚታይ ሲሆን፤ ‹ዳኘው› በመባል የሚታወቀው ይኸው ፈረስ የሚታየው ፊቱን ወደ ሰሜን አቅጣጫ መልሶ፣ በኋላ እግሮቹ ቆሞ እና የፊት እግሮቹን ወደላይ አንስቶ ነው። ፊቱን ወደ ሰሜን አቅጣጫ የመመለሱ ጉዳይ ጦርነቱ የተካሄደበት ቦታ በሰሜን ኢትዮጵያ አድዋ መሆኑን ለማስታወስ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። የአድዋ ጦርነት በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ በወራሪው የጣሊያን መንግሥትና በዳግማዊ አፄ ምኒልክ በሚመራው የኢትዮጵያ ጦር መሃከል የተካሄደ ጦርነት ሲሆን፣ ጦርነቱ በኢትዮጵያ አሸናፊነት በድል ተጠናቋል። የኢትዮጵያውያን ብሎም የአፍሪካውያን ኩራት ሆኖም ዛሬ ድረስ መዝለቁ እውን ነው። ሐውልቱ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በብዙ ዘርፍ ለአገር ትልልቅ ተግባራትን ያከናወኑ ንጉሥ በመሆናቸው ታላቅ ስራቸውን ለማንጸባረቅ የተቀረፀ እንደሆነ ይታወቃል። ጣሊያኖች ከአርባ ዓመታት በኋላ ዳግም ኢትዮጵያን በወረሩ ጊዜ ሐውልቱን አፍርሰው ቀብረውት የነበረ ቢሆንም፤ ከነፃነት በኋላ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሐውልት ከተቀበረበት ቦታ ወጥቶ እንደገና ታድሶና ተጠግኖ ቀድሞ በነበረበት ቦታ ሚያዝያ 27 ቀን 1934 ዓ.ም. እንዲቆም መደረጉን ከታሪክ መረዳት ይቻላል። (ሰላም ለተፈጥሮና ለፍጡራን በሙሉ ይሁን!) አያሌው ተስፋዬ. https://t.me/joinchat/RuPmDA5drDKAAwxd https://t.me/joinchat/L50fVzoeFhsxYjZk
Show all...
(ከትልቅ ወይም ከትንሽ ቢሆን መወለድ ሙያ አይደለም፤ ራስን ለታላቅ ታሪክ መውለድ ግን ሙያ ነው)። ይህ በአራዳ ጊዮርጊስ አደባባይ በሚገኘው ለአጤ ሚኒሊክ መታሰቢያነት በሚል በተዘጋጀው ሀውልት በእግርጌ በኩል የሰፈረው ድንቅ አባባልና ዘመናችንን የሚዋጅ የበሰለ ንግግር ነው. በብሄር ስም የተደራጃችሁ ፓርቲዎችና፤ ለብሔራችሁ፤ ለጎሳችሁ የምታደሉ፤ ታሪክ እንደሰራ ራሳችሁን የምታታልሉ ሰዎች ሰምታችኋል! (ከትልቅ ወይም ከትንሽ ቢሆን መወለድ ሙያ አይደለም፤ ራስን ለታላቅ ታሪክ መውለድ ግን ሙያ ነው)። የተናገረውን የሚያደርግ፤ ያደረገውን የማይናገር ትሁት ንጉስ ዳግማዊ እምዬ ምኒልክ. በክፋት ላሰበው፤ ቀፎው እንደ ተነካበት እንደ ንብ መንጋ የሚወር፤ ሲያሸንፍ፤ ሲረታ ድል አደረግሁ ብሎ የማይኮፈስ የማይንቀባረር፤ ምርኮኞቹን ደግ እንደሰሩ አብልቶ አጠጥቶ ወደ ሀገራቸው በክብር የሚሰድ፤ ግፍ ለፈጸሙ ምህረትን ይቅርታን ማድረግ የሚወድ፤ ለማንዴላ ስርዓትን ያስተማረ፤ ጥቁር ህዝቦችን ያቀራረበ ያፋቀረ ድንቅ መሪ. ያቆየኽልን ኢትዮጵያ ለዘለአለም በአንድነት በፍቅር፤ በህብረት በክብር፤ ከፍ ከፍ እንዳለች ትኑር! አያሌው ተስፋዬ ነኝ. (ሰላም ለተፈጥሮና ለፍጡራን በሙሉ ይሁን!). https://t.me/joinchat/RuPmDA5drDKAAwxd
Show all...
ወይ የዘንድሮ አድዋ! ወይ ድፍረት! ጣልያን እንኳን እንደዚህ አልደፈረችንም. እናንተዬ፤ ኦሮሚያን ልገንጥል እያሉ ሲወበሩ የነበሩ ወናጋም ኦነጎች መጀመሪያ ራሳቸውን ገንጥለው ነው ለካስ! ማል መናጋ፤ ትል ነበር እናቴ. ምን ይዘላብዳል፤ ለማለት. ፎኦኦኦኦኦ! ጉድ እኮ ነው! የሰማሁት በእውኔ ነው፤ ነው ወይስ በህልሜ፤ ጫካ ተወልዶ ያደገው፤ ቤቶፎቢያ ያለበት አራዊታም ቅንጭላት ቀጄላ መርዳሳ ጭራሽ ብሎ ብሎ አድዋን ያለ ሚኒሊክ እንድናስብ ፈለገ እንዴ! ኦነግን ያለ ታደሰ ብሩ፤ ያለ ዮሃንስ ለታ፤ ያለ ባሮ ቱምሳ ማሰብ ይቻለዋልን፤ መልሱን ለኦቦ ከጄላ ይቅርታ ቀጄላ ትቼዋለሁ. ጣልያን በገዛ ሀገሯ ለግራዚያኒ መታሰቢያ ሀውልት ለማቆም መንገድ ጀምራ ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን ሲያሰሙ ዳግም ሊገርፉን ነው እንዴ! በማለት ተንቦቅቡቀው ፕሮጀክቱን እንደተዉት የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው. ከመግለጫው በፊት ይህን ሊያስብ ይገባ ነበር. የቧልት ሚኒስትራችን አቶ ከጄላ መርዳሳ ቆም ብሎ ሊያስተውል በተገባው ነበር. ሻምበል አብዲሳ አጋ የኢትዮጵያ እንጂ የኦሮሚያ ጀግና አይደለም ለሚል ታሪክን በኩረጃ ተምሮ በኩረጃ ለሚያወራ ሰው ጆሮ መስጠትም አልነበረብንም! ክብረ በዓሉን ከአድዋ አደባባይ፤ ከቅዱስ ጊዮርጊሥ ቤተ-ክርሥቲያን ወደ አድዋ ድልድይ፤ ወደ ወንዝ ዳርቻ ወስዶ እንዲከበር ማድረግ ምን የሚሉት ነው፤ ዋቃ ጉራቻ፤ ሰግለን ቦረና እያለ በየዓመቱ ላልተፈታው ዲያቢሎስ ውሃ የሚረጨው አመሉ ብልጭ ብሎበት ይሆን፤ ነው ወይስ እኛ ተጃጅለንለት፤ እሺ ይሁን ብለን አድዋ ድልድይ ሄደን ስናከብር እሱ ደግሞ በጎን ሹልክ ብሎ የሚኒሊክን ሀውልት ሊያፈርሠው! የለም የለም የለም! አሁንም ጠቡ ከቅድሥት ቤተ-ክርሥቲያን፤ ከኦርቶዶክሥ ተዋህዶ ጋር እንደሆነ ፍንትው አድርጎ አሳይቷል! ይኼ እብሪቱ ግን የትም እንደማያደርሰው እሱም ያውቀዋል፤ እኛም እናውቀዋለን. የኢትዮጵያ ጥንታዊ የአርበኞች ማህበርን ግን ብራቮ! ቪቫ ብያለሁ. ወንዳታ! ወንድ ልጅ ቆረጠ ይሉሃል እንዲህ ነው. ፈሪ ሲያገኝ በአደባባይ ራሱን ዠግና አድርጎ ለሚኮፍሰው ለሚቆልለው ገለባ እንዲህ ማስተንፈስ ነው እንጂ! በእድሜ ትልቁ፤ በትምህርት ደረጃህ ትንሽ የሆንከው አቶ ኦቦ ክጀላ መርዳሳ ሆይ! እረፍ፤ ተጠንቀቅ፤ አድብ! ከምድር እስከ አርያም የተዘረጋችውን አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሠንደቅ ዓላማን ለብሠህ የመጣልህን ዝም ብለህ አትትፋ! በአንድ ወቅት ዶር ነጋሶ ጊዳዳን ቃለ መጠይቅ ሳደርግላቸው፤ ይቺ ሠንደቅ የኦርቶዶክስ ናት እንጂ የሌላው አይደለችም ብለውኝ ነበር. ምክንያቱም የኦነግና የሸኔ መስራች ስለነበሩ. እናማ ከአንተም የምጠብቀው አዲስና የተሻለ ነገር የለም! እንደዚያው ነው እንጂ! ለማንኛውም እንኳን ለ126ኛው የአድዋ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ! መልእክቱ ጣልያናዊውን ሚስተር ቀጄላን አይመለከትም! አያሌው ተስፋዬ ነኝ! ተጻፈ በ22/06/14 ዓ/ም.
Show all...
ከኢትዮጵያ የተዘረፉ የአብያተ ክርስቲያናት ቅርሶች በርካሽ ዋጋ በኢንተርኔት ለሽያጭ ቀርበዋል በጦርነቱ ወቅት ከበርካታ የትግራይ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ቅርሶች መዘረፋቸውን አረጋግጫለሁ" በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ተዘርፈው ከአገር ሳይወጡ እንዳልቀሩ የተገመቱ በርካታ የአብያተ ክርስቲያናት ጥንታዊ ቅርሶች ኢቤይ እና አማዞንን በመሳሰሉ የኢንተርኔት የመገበያያ መድረኮች ላይ እጅግ በርካሽ ዋጋ እየተሸጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከእነዚህ ቅርሶች ውስጥ ብዙዎቹ "ኢቤይ" በተሰኘው የኢንተርኔት ገበያ ላይ እንደቀረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ፣ በሃይማኖት ተቋማት ላይ ጥቃት መፈጸሙና ጥንታዊ ቅርሶች መዘረፋቸው መዘገቡ አይዘነጋም፡፡ ቢቢሲ ኒውስዴይ በጉዳዩ ዙርያ ያነጋገራቸው የቋንቋ ታሪክ ተመራማሪና በሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የድኅረ ዶክትሬት ተማሪ የሆኑት ዶ/ር ሐጎስ አብረሃ፤ በጦርነቱ ወቅት ከበርካታ የትግራይ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ቅርሶች መዘረፋቸውን አረጋግጫለሁ" ብለዋል፡፡ በወቅቱ ከተዘረፉት ቅርሶች አንዳንዶቹ ጥንታዊና እጅግ ብርቅዬ እንደነበሩ ዶ/ር ሐጎስ አስረድተዋል። ተመራማሪው ከኢትዮጵያ የተዘረፉት ቅርሶች በብዛት እየተሸጡ ያሉበት ዋጋ እጅግ ርካሽ የሚባል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ቅርሶቹ በዚህ ወቅት እንዴት ተዘርፈው ከአገር ሊወጡ እንደቻሉ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በሱዳንና ኬንያ በኩል ወጥተው ሊሆን እንደሚችል ግን ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በኢቤይ የኢንተርኔት የግብይት መድረክ ላይ ባለፉት ጥቂት ወራት በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ለሽያጭ ካቀረቡት ድርጅቶች መካከል ዎርሌይ ኢንተርፕራይስ ኢንተርናሽናል ኤልኤልሲ ይገኝበታል። ድርጅቱ ለገበያ ካቀረባቸው የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርጾች መካከል ከ15ኛው እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ በእጅ የተጻፈ ሃይማኖታዊ መጽሐፍ ይገኝበታል። በእንስሳት ቆዳ ላይ በግዕዝ ቋንቋ የተጻፈው ሃይማኖታዊ መጽሐፍ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም በ240 ዶላር ለገበያ ቀርቧል። ከ15ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ባሉት ዓመታት በግዕዝ ቋንቋ ሳይጻፍ አይቀርም የተባለለት መጽሐፍ ደግሞ በ1250 ዶላር ለሽያጭ ቀርቧል።
Show all...
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል 42ቱን መለየቱን የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ዛሬ አሳውቀዋል። አቶ ታገሰ ፥ ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች 632 የእጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቅረባቸውንና አብዛኛዎቹ ስራውን ለመስራት የሚያስችል ልምድና ዕውቀት ያላቸው መሆኑን መገንዘብ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ አዋጁ ለአፈ-ጉባኤውና ለአፈ-ጉባኤው ጽ/ቤት በሰጠው ስልጣን እንዲሁም በአዋጁ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ከቀረቡት 632 ዕጩዎች መካከል 42ቱ መለየታቸውን ተናግረዋል፡፡ በቀረቡ 42 ዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከአማካሪዎች ጋር ምክክር እየተደረገበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ሳምንት ደግሞ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ፣ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አመራር አካላት በሚገኙበት በዕጩዎች የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ ላይ ምክክር ተደርጎ ግብአት የሚሰበሰብ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ በማስከተልም በም/ቤቱ ድረ-ገጽና በማህበራዊ ሚዲያ የእጩዎችን ማንነት በመግለጽ በቂ ግብአት ከተሰበሰበ በኋላ ሰብሳቢና ም/ሰብሳቢን ጨምሮ 11ዱ ዕጩ ኮሚሽነሮች ለም/ቤቱ ቀርቦ ከፀደቀና ዕጩዎች ከተሰየሙ በኋላ ወደ ስራ እንደሚገባም ገልጸዋል።
Show all...
ጀነራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ 27 ግለሰቦች ሙሉ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ። በዚህም መሠረትም፡- 1/ አቶ ተፈራ ደርበው 2/ አቶ ደሴ ዳልኬ 3/ ዶክተር ስለሺ በቀለ 4/ ጄኔራል ባጫ ደበሌ 5/ ጄኔራል ሀሰን ኢበራሂም 6/ ወ/ሮ ሽትዬ ምናለ 7/ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ 8/ አቶ ረሻድ መሀመድ 9/ አምባሳደር ጀማል በከር 10/ አቶ ፈይሰል ኦሊይ 11/ አቶ ኢሳያስ ጎታ 12/ አቶ ፀጋአብ ክበበው 13/ አቶ ጣፋ ቱሉ 14/ ደክተር ገነት ተሾመ 15/ አቶ ዳባ ደበሌ 16/ አቶ ፍቃዱ በየነ የባሉሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት እንዲሁም 1/ አቶ አሳየ አለማየሁ 2/ አቶ ኃይላይ ብርሃነ 3/ አቶ አወል ወግሪስ 4/ ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት 5/ አቶ አንተነህ ታሪኩ 6/ አቶ አክሊሉ ከበደ 7/ አቶ ሰይድ መሐመድ 8/ አቶ ዮሴፍ ካሳዬ 9/ አቶ ዘላለም ብርሃን 1ዐ/ ወ/ሮ ፍርቱና ዲባኮ 11/ አቶ ወርቃለማሁ ደሰታ በአምባሳደርነት የተሾሙ መሆኑን ከፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
Show all...
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ! የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለስድስት ወር ተደንግጎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ወሰነ።ምክር ቤቱ ዛሬ ረቡዕ ጥር 18 ቀን 2014 ዓም ባካሄደው ስብስባ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተፈጻሚነት ጊዜ እንዲያጥር ያደረገው አዋጁን ማውጣት “የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ በመሆኑና ስጋቱን በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ ውሳኔውን ማስተላለፉን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
Show all...
ቅዱስ ሲኖዶሱ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ላይ ሊያደርገው የነበረው ስብሰባ ተራዘመ! ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባጋጠመቸው የጤና እክል ምክንያት ስብሰባው ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተገለጸ። ቅዱስነታቸው፣ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ላይ በሌሉበት ሁኔታ ጉባኤውን ማካሔድ ስለማይቻል የቅዱስ ፓትርያርኩ ጤና እስከሚመለስ ድረስ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን የቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል። [Addis Maleda
Show all...
መስቀል ዐደባባይ በሕግም፣ በታሪክም፣ በስምም፣ በካርታም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ ነው። አዳነች አቤቤ ግን ይኽን ክደው እና ዘርፈው የሁሉም ግብር ከፋይ ነው ብለው ቀሰቀሱብን። ተደበደብን፣ ታሰርን የመርዝ ጭስ በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ተተኮሰ። ዕጣነ አሮን በሚታጠንበት መቅደስ የመርዝ ጭስ ታጠንን።
Show all...
የዐዲስ አበባ ፖሊስ መስመር አትለፍ! የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ማዋከባቸውን ቀጥለዋል። የማኅበራት ኅብረቱን ተወካዮች ነገ ጧት በአስቸኳይ ቢሮዬ መጥታችሁ አናግሩኝ በማለት የከተማው ፖሊስ ኮሚሽነር ቀጭን ትእዛዝ አይሉት ጥሪ አስተላልፈዋል። በቦሌ መድኃኔዓለም የተጠራው ጉባኤም አሳስቦታል። በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ለመሰብሰብ የማንንም ባለሥልጣን ፈቃድ ቤተ ክርስቲያን አትጠይቅም። ስለዚህ መንግሥት እና ባለሥልጣናት አድቡ። መቆራረጫችንን በገዛ እጃችሁ አታፋጥኑት። ኦርቶዶክሳዊው ላይ አምርራችሁ የምትወጡትን ነገር መለስ ብላችሁ አስቡበት።
Show all...
ስለ #ፊልድ_ማርሻል ወታደራዊ ማዕረግ: ★★★★★ . አሁን አሁን "ፊልድ ማርሻል" ማዕረግ ባለ #አምስት_ኮከብ ደረጃ እንደሆነ ይቆጠራል። በአለም ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ አገራት በወታደራዊ ማዕረግ የመጨረሻው የማዕረግ ደረጃ የሆነውን ፊልድ ማርሻል የተባለውን ማዕረግ በጦርነት ተሳትፎ ጀብዱ ለሰሩ ለጀግኖቻቸው ሰጥተዋል፡፡ ታዲያ ከእነዚህ ውስጥ 7 የሚሆኑት ፊልድ ማርሻሎች አፍሪካዊያን ናቸው፡፡ ከነዚህ መሀል፦ . 1. #ኢትዮጵያ፦ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጥቅምት 23 ቀን 1923 እስከ መስከረም 2 ቀን1967 ዓ.ም ድረስ የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩት ፓን አፍሪካኒስቱ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የመጀመሪያው የአገራችን ፊልድ ማርሻል ነበሩ፡፡ ማዕረጉንም ያገኙት እ.አ.አ በጃኑዋሪ 20 1865 ከወቅቱ የብሪታኒያ ንግሥት ነበር፡፡ . 2. #ኮንጎ፦ የቀድሞዋን ዛየር የአሁኗን ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክን እ.አ.አ ከ1965 እስከ 1997 ድረስ የመሯት ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ እ.አ.አ በሰኔ 17 1983 ራሳቸውን በራሳቸው ፊልድ ማርሻል ብለው የሰየሙ ሲሆን ትእዛዙ የተፈረመው በወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር በነበሩት ጀነራል ሊኩሊያ ቦሎንጎ ነበር፡፡ . 3. #ኡጋንዳ፦ ሌላው አፍሪካዊ ፊልድ ማርሻል ደግሞ ኡጋንዳን እ.አ.አ ከ1971 ጀምሮ እስከ 1979 ድረስ ለ28 አመታት በፈላጭ ቆራጭነት ሆነው በፕሬዘዳንትነት ያስተዳደሯት ኢዲ አሚን ዳዳ ነበሩ፡፡ አሚን እ.አ.አ በ1946 የብሪታኒያ ቅኝ አገዛዝ ስርዓትን በመቀላቀል በሶማሊያ እና በኬኒያ ማገልገል ጀመሩ። የተዋጣላቸው ጦረኛ ነበሩ ተብሎላቸዋል፡፡ ታዲያ ይህ ጦረኝነታቸው የኋላ የኋላ የኡጋንዳ መሪነትን እንዲጨብጡ ዋነኛውን ሚና መጫወቱ አልቀረም። ከቅኝ አገዛዝ ማክተም በኋላ አሚን በኡጋንዳ ጦር ሰራዊት ውስጥ የሜጀር ጄነራልነትን ማዕረግ አገኙ። የኋላ የኋላ እ.አ.አ በ1971 መፈንቅለ መንግስት አካሂደው አገሪቷን በእጃቸው አስገቡ፡፡ ቆየት ብለው ደግሞ ከዚህ በኋላ ፊልድ ማርሻል ነኝ ብለው ራሳቸውን ሾመ፡፡ . 4. #ግብፅ፦ ሌላኛዋ አፍሪካዊ ፊልድ ማርሻል ጎረቤት አገር ግብጽን እ.አ.አ ከ2014 እስከ 2020 ድረስ በፕሬዘዳንትነት የመሩት ጄነራል አብዱልፈታህ አልሲሲ ሲሆኑ የፊልድ ማርሻልነት ማዕረጉን ያገኙት እ.አ.አ በፌቡሯሪ 1 2014 ነበር፡፡ በግብጽ የፊልድ ማርሻልነት ማዕረግን ያገኙ አል ሲሲ ብቻ አልነበሩም፡፡ የረዥም ጊዜ የግብጽ ገዢ የነበሩት ሆስኒ ሙባረክን መውደቅ ተክተሎ ግብፅን ያስተዳደረው የቀድሞ ወታደራዊ ምክር ቤት መሪ የነበሩት እንዲሁም የአገሪቷ መከላከያ ምኒስትርን በበላይት ለ21 አመታት የመሩት መሀመድ ሁሴን ታንታዊ እ.አ.አ በ1993 የፊልድ ማርሻልነት ማዕረግን በእጃቸው ማስገባት ችለዋል፡፡ . 5. #ሱዳን፦ ሱዳንም ለአፍሪካ አንድ ፊልድ ማርሻልን አበርክታለች፡፡ እ.አ.አ ከኦክቶበር 16 1993 እስከ አፕሪል 11 2019 ድረስ የሱዳን ፕሬዘዳንት የነበሩት ኦማር አልበሽር በሱዳን ታሪክ ብቸኛው ፊልድ ማርሻል ናቸው፡፡ . 6. በአገራችን ታሪክ ሁለተኛው የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ለኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ለጄነራል ብርሃኑ ጁላ በታህሳስ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ተበርክቷል፡፡ ምንጭ፦ ሰዋሰው
Show all...
የጀግናው እሸቴ ሞገስና ልጁ ይታገሱ እሸቴ የቀብር ሥነ ሥርዓት በሸዋሮቢት ተካሄደ የጀግኖቹ አስከሬን ከመኖሪያ ቤታቸው በአካባቢው ማኅበረሰብ፣ በፋኖ፣ በሚሊሻ፣ በልዩ ኀይልና የመንግስት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ታጅቦ በሸዋሮቢት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የቀብር ስነ ስርአታቸው ተፈፅሟል።
Show all...
የትናንት ምሽቱ የፕ/ት ኢሳያስ ቃለ ምልልስ ላይ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች በአማርኛ :: - ደብረፂዮንን በሁመራ ለምን ለጦርነት እየተዘጋጁ እንደሆነ ጠየኩት። - ህወሓት በኤርትራ ውስጥ ከ100 በላይ ቦታዎች ላይ ኢላማ ለማድረግ ማቀዱን የሚያሳይ ማስረጃ አለን። - የህወሓት ጀብዱ የተሳሳተ ስሌት ነበር። - በህዳር 2020 የመጀመሪያ ሳምንት ከ5000 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች የኤርትራን ድንበር አቋርጠዋል። - የኢትዮጵያ ጦር ከመቀሌ ይወጣል ብለን አልጠበቅንም። - የህወሓት አመራር ከስልጣን መውጣቱን እንኳን አልጠበቀም። የውጭ አካላት የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ እንዲወጣ ግፊት ያደርጉ ነበር። - ማንኛውም ጤነኛ ወታደራዊ አመራር ያለ ሎጂስቲክስ እስከ ኮምቦልቻ እና ደሴ ድረስ ሊገባ ባልደፈረ ነበር። - የህወሓት የውጭ ሃይሎች በጦርነቱ ውጤት አልረኩም። - ወያኔ በኤርትራ ላይ ያደረሰው ጉዳት ከኃይለሥላሴና ከመንግስቱ ኃ/ማርያም የከፋ ነው። - የትግራይ የነጻነት ሪፐብሊክ የለም፣ አይሆንምም። - ወያኔ የኢትዮጵያን የተረቀቀውን ሕገ መንግሥት ከማንም በፊት እንዳነብ ሰጠኝ። ሕገ መንግሥቱ ለኢትዮጵያ አደገኛ ነበር፣ እናም ቅሬታዬን አንስቻለሁ። - ከብሄር ፌደራሊዝም ፖሊሲ የበለጠ አደጋ የለም። - አገሪቱ አንድ ካልሆነ ለውጭ አገሮች በሉዓላዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ቀላል ነው። - ባለፉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ አንድነት ለኒዮ-ቅኝ ገዢ አገሮች ትምህርት ሆኖ ቆይቷል። - የአሜሪካን ህዝብ እና መንግስትን መለየት አለብን። በአለም አቀፍ ደረጃ ውድመትን የሚፈጥሩት መቶኛ ከአሜሪካ ህዝብ 0.1% እንኳን አይደለም። - በአሁኑ ጊዜ በዩኤስኤ ውስጥ የተሰራ የለም. ሁሉም ነገር በቻይና የተሰራ ነው. - ቻይና ሩብ የአሜሪካ ዕዳ አለባት። ዩኤስኤ በኢኮኖሚ ኃያል አገር ናት የሚለው ግምት የተሳሳተ ነው። - ስማቸው እንጂ ኢጋድ ወይም AU የሉም። የግል ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች አበላሽተውታል። - ቻይና ምዕራባውያንን አንቀሳቅሳለች። ምዕራባውያን አገሮች ሩሲያንና ቻይናን መያዝ አልቻሉም። - በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ ዓለም ለበጎ ነገር የተለየ ይሆናል. - የዓለም ልዕለ ኃያል መንግሥት እንደ ኤርትራ ትንሿን አገር ለስምንት ዓመታት እንዴት ማዕቀብ ይጥላል? ይህ በእነርሱ በኩል ተስፋ መቁረጥ ነው, እኛ ለመሾም ፈቃደኛ ባለመሆኑ. - የአሜሪካ ልዑክ ሥራ ለአገሮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማዘዝ ነው። - ሽብርተኝነት የተፈጠረው ‘በነሱ’ ነው። - ባለፈው አመት ሲሰራጭ የነበረው 40% ዶላር በህገ ወጥ መንገድ በአሜሪካ ታትሟል። -በአሜሪካ መንግስት ላይ 'immunity' ፈጥረናል። - የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፖሊሲዎች እና 'የዓለም ስርዓት' የጫካ ህግ ናቸው. ተሃድሶ ተከልክሏል። - ኤርትራን ሰይጣናዊ ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው። - የአፍጋኒስታን ሰዎች ለምን ይሰቃያሉ? - በተሞክሮአችን ምክንያት የዩኤስን ማዕቀብ መቃወም እና ማቆየት እንችላለን። - የሰማንያ አመታት ታሪካችን ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ነው። የእነሱ ሰላም እና ብልጽግና ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው. - በኢትዮጵያ ላይ የደረሰው አስከፊው ነገር ወያነ ነው። - ኤርትራና ኢትዮጵያ ግንኙነታቸውን ያጠናክራሉ። - ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ ዘላቂ ሰላምና አንድነት እንዲኖር የጎሳ ፌደራሊዝምን ማሻሻል ወይም ማስወገድ አለባት። - ህወሀት ለተጋሩ ከአማራ ያነሱ መሆናቸውን በመንገር ጥላቻን እየዘራ ነበር። -የመጀመሪያው ወያነ አስተሳሰብ ከሁለተኛው እና ከአሁኑ ወያነ የተለየ ነበር። - ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት የሚሰቃዩት ተጋሩ ናቸው። - አሁን በሱዳን ያለው መጥፎው የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት ነው። Translated by Paulos
Show all...
በትላንትናው እለት የማዕረግ እድገት ያገኙ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ዝርዝር የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሿሚ 1. ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለልቻ የጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች 1. ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰ አስረስ 2. ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ቡታ 3. ሌ/ጀነራል ሐሰን ኢብራሂም ሙሳ 4. ሌ/ጀነራል ጌታቸው ጉዲና ሰልባና የሌ/ጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች 1. ሜ/ጀነራል አለምሸት ደግፌ ባልቻ 2. ሜ/ጀነራል አጫሉ ሸለመ መረጋ 3. ሜ/ጀነራል ጥጋቡ ይልማ ወንድምሁነኝ 4. ሜ/ጀነራል መሐመድ ተሰማ ገረመው 5. ሜ/ጀነራል አብዱራህማን እስማዔል አሎ 6. ሜ/ጀነራል በላይ ስዩም አከለ 7. ሜ/ጀነራል ዘውዱ በላይ ማለፊያ 8. ሜ/ጀነራል መሰለ መሰረት ተገኝ 9. ሜ/ጀነራል ሹማ አብደታ ህካ 10. ሜ/ጀነራል ብርሀኑ በቀለ በዳዳ 11. ሜ/ጀነራል አሰፋ ቸኮለ እንዳለው 12. ሜ/ጀነራል ደሳለኝ ተሾመ አብተው 13. ሜ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ ለሙ 14. ሜ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ ኛጳ የሜ/ጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች 1. ብ/ጀነራል አማረ ገብሩ ሀይሉ 2. ብ/ጀነራል ኢተፋ ራጋ ሜኮ 3. ብ/ጀነራል ተስፋዬ ወ/ማሪያም ሀብቱ 4. ብ/ጀነራል አዳምነህ መንግስቴ ገብሬ 5. ብ/ጀነራል አብዱ ከድር ከልዩ 6. ብ/ጀነራል ሙላቱ ጀልዱ ዋቅጅራ 7. ብ/ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ ካህሱ 8. ብ/ጀነራል ግርማ ከበበው ቱፋ 9. ብ/ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን በርሄ 10. ብ/ጀነራል አድማሱ አለሙ ወ/ሰንበት 11. ብ/ጀነራል ታገሰ ላምባሞ ድምቦሬ 12. ብ/ጀነራል ፍቃዱ ጸጋየ እምሩ 13. ብ/ጀነራል አለማየሁ ወልዴ ጅሎ 14. ብ/ጀነራል ሰለሞን ቦጋለ መኮንን 15. ብ/ጀነራል ሻምበል ፈረደ ውቤ 16. ብ/ጀነራል ግዛው ኡማ አብዲ 17. ብ/ጀነራል ደምሰው አመኑ ፋፋ 18. ብ/ጀነራል ጀማል መሃመድ ይማም 19. ብ/ጀነራል አለሙ አየነ ዘሩ 20. ብ/ጀነራል ሰይድ ትኩዬ አበጋዝ 21. ብ/ጀነራል አብድሮ ከድር በናታ 22. ብ/ጀነራል ናስር አባዲጋ አባዲኮ 23. ብ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌው አለሙ 24. ብ/ጀነራል ነገሪ ቶሊና ጉደር የብ/ጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች 1. ኮ/ል ሙሉ ሞገስ መኮንን 2. ኮ/ል ደረጀ ደመቀ ማሞ 3. ኮ/ል ተሾመ ይመር አበጋዝ 4. ኮ/ል ያዴታ አመንቴ ገላን 5. ኮ/ል አዱኛ ዴሬሳ ሆሬሳ 6. ኮ/ል ሹመት ጠለለው እንዳሻው 7. ኮ/ል ደስታ ተመስገን አራጋው 8. ኮ/ል ደርቤ መኩሪያ አዲሱ 9. ኮ/ል አበበ ዋቅሹም ተሬሳ 10. ኮ/ል እሸቱ አስማማው አስፋው 11. ኮ/ል አበባው ሰይድ ይመር 12. ኮ/ል ተመቸው ተስፋዬ አበራ 13. ኮ/ል አማረ ባህታ በርሄ 14. ኮ/ል ጌታቸው አሊ መሃመድ 15. ኮ/ል ማርየ በየነ አስናቀ 16. ኮ/ል ካሳ ደምሌ አቡነህ 17. ኮ/ል ሻምበል በየነ ንጉሴ 18. ኮ/ል አምሳሉ ኩምሳ ሮሮ 19. ኮ/ል ተሾመ አናጋው አያና 20. ኮ/ል ተመስገን ማሎሬ ግዶሬ 21. ኮ/ል ገዛኽኝ ፍቃዱ በቀለ 22. ኮ/ል ጀማል ሻሌ ዱሌ 23. ኮ/ል ከማል አቢሶ እንተሌ 24. ኮ/ል ጀማል ቱፊሳ ጭቃቂ 25. ኮ/ል በስፋት ፈንቴ ተገኝ 26. ኮ/ል ሃይሉ መኮንን ምስክር 27. ኮ/ል አዲሱ መሐመድ ፀዳል 28. ኮ/ል ማርየ ምትኩ አለሙ 29. ኮ/ል ናስር አህመድ እራስ 30. ኮ/ል ጌታሁን ካሳዬ ሳህሉ 31. ኮ/ል አበባው መንግስቴ ሰራጨ 32. ኮ/ል አብርሀም ሞሶሳ ጋጀ 33. ኮ/ል ንጉሴ ሚዔሶ ጅባ 34. ኮ/ል ተስፋየ ከፍያለው አስፋው 35. ኮ/ል ታየ አለማየሁ ገዛኽኝ 36. ኮ/ል አዘዘው መኮንን አበራ 37. ኮ/ል ዱሬሳ ደገፋ ኤኙኒ 38. ኮ/ል እሸቴ አራጌ ሞገስ 39. ኮ/ል ወርቅነህ ጉዴታ ደበሉ 40. ኮ/ል ሶፊያን ሸክመሀመድ ከሊፋ 41. ኮ/ል መሀመድ ሁሴን እንድሪስ 42. ኮ/ል ሰይፈ ኢንጊ ጉራሮ 43. ኮ/ል ሁሉአገርሽ ድረስ እንዳሻው 44. ኮ/ል መካሽ ጀምበሬ አምባው 45. ኮ/ል ዝናቡ አባቦር አባጊሳ 46. ኮ/ል ሞሲሳ ቶሎሳ ገርባ 47. ኮ/ል እሸቱ መንግስቱ መንገሻ 48. ኮ/ል እርቃሎ ዱካቶ ጋጌ 49. ኮ/ል ዋለልኝ ታደሰ አዛል 50. ኮ/ል ተስፋዬ ለገሰ ዲያና 51. ኮ/ል ጌታቸው ሀብታሙ ቸኮል 52. ኮ/ል ሐሺም መሐመድ ጭቆላ 53. ኮ/ል ከበደ ገላው ጅማማ 54. ኮ/ል መላኩ ገላነህ ዘለቀ 55. ኮ/ል ተክሉ ሁርሳ ጅንካ 56. ኮ/ል ሐሽም ኢብራሂም አዋሌ 57. ኮ/ል በላይ አየለ ማሞ 58. ኮ/ል ሀብታሙ ምህረቴ በየነ Via EPA
Show all...
ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ** በነገራችን ላይ የእነእስክንድር ነጋንና የእነጃዋርን ከእስር ነጻ መሆን በሰማሁና ስሜቴን በዚሁ ገጼ ላይ ባጋራሁ ጊዜ የእነስብሃት ነጋን መፈታት የተመለከተ አንዳችም ያወኩት ነገር አልነበረም። እውነት ለመናገር ጽሁፉን ካጋራሁ በኋላ ዘግይቶ የእነስብሃት ነጋን ከእስር ነጻ መሆን እንደሰማሁ ድብልቅልቅ ባለ ስሜት ውስጥ ለሰዓታት ቆየሁኝ። የእነእስክንድርን ነጻ መሆን ስጠብቀው የነበረ በመሆኑ በአወንታዊ መልኩ ድጋፌን ገልጬ መንግስትን አበጀህ ብዬአለሁ። የእነስብሃት መፈታት ግን ከጉሮሮዬ አልወርድ ብሎ ተናነቀኝ። ግራ ተጋብቼ ከራሴ ጋር ዝግ ስብሰባ ተቀመጥኩ። መንግስት የህወሀት ሰዎችን ከእነ እስክንድር ነጋ ጋር በአንድ ቀን፣ በአንድ ዓይነት መግለጪያ ነጻ እንዲሆኑ ያደረገበት ምክንያት ፈጽሞ አልገባኝም። ለተወሰኑ ሰዓታት ስለሆነው ነገር ለማሰብ እንኳን አቅም አጥቼ ቆየሁ። በእርግጥ የአሜሪካንን ቀጣይ ስትራቴጂ በተመለከተ ከመንግስት አንድ ከፍተኛ አመራር የሰማሁት መረጃ አስደንግጦኛል። ነገሮችን ፍጹም ጥንቃቄና እርጋታ ባለው አካሄድ ካልያዝነው ስሜታችንና እልሃችንን ብቻ እያዳመጥን የምንዘልቅ ከሆነ ወደፊት የኢትዮጵያ ጉዳይ ከምናስበው በላይ ውስብስብና የከፋ እንደሚሆን ይሰማኛል። አሜሪካ የቻይናንና የሩሲያን የተጠናከረ እንቅስቃሴ ለማኮላሸት ትግራይ ክልልን ዲፋክቶ ስቴት በማድረግ የቀጠናውን የጂኦ ፖለቲካ አቅጣጫ ልትዘውረው እቅዱ እንዳላት ፍንጭ መታየቱን ከዚሁ ሁነኛ የመንግስት ባለስልጣን መረጃውን አግኝቼአለሁ። የቻይና እጆች አፍሪካ ቀንድ ላይ በሰፊው እየተዘረጉ መምጣቻው አሜሪካን ትግራይ ክልልን እንደመያዣ ተጠቅማ በዲፋክቶ ስቴት አድርጋ አከባቢውን እንዳሻት ለመቆጣጠር አዲስ ዓይነት ዘመቻ ልትጀምር እያኮበኮበች መሆኗን ነው ከባለስልጣኑ የሰማሁት። አልሸባብን ከሽብርተኝነት መዝገብ ላይ ስሙን በመሰረዝ አጋር ሃይል ሆኖ የሚመጣበትንና አሜሪካን በቀጠናው ላይ የሚኖራትን የበላይነት እንዲያስጠብቅላት እንደምትፈልግ ከወዲሁ የጀመረችው እንቅስቃሴ እንዳለም ተሰምቷል። በእርግጥ የእነስብሃት ነጻ እንዲሆኑ የተደረገበት ሁኔታና አውድ ስሜትን በሀዘን ያኮማትረዋል። እንደማንኛውም ህወሀትን አምርሮ እንደታገለ ሰው የዚህ ወንጀለኛና ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን አመራሮች በየትኛውም ፖለቲካዊ ስሌት ከእስር ነጻ እንዲሆኑ መደረጉን በአወንታዊ ስሜት ልቀበለው የምችል አይደለሁም። ነገር ግን መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ ለምን ደረሰ? የህዝብን ስሜት እንደሚጎዳው እያወቀ ለምን አደረገው? የህወሀት ሀይል ገስግሶ ደሴን ተሻግሮ ደብረብርሃን ጫፍ በደረሰ ጊዜ እንኳን ያላደረገውን አሁን በአሸናፊነት ስነልቦና ላይ ሆኖ ህወሀትን ጠራርጎ ካስወጣና ወታደራዊና ፖለቲካዊ የበላይነትን ከያዘ በኋላ እንዲህ ዓይነት እርምጃ የወሰደው ምን ፈልጎ ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን በሰከነ ሁኔታ መወያየትና ማሰብ ይፈልጋል። የደረሰብንን መከራ እያሰላን፣ በደላችንን እየቆጠርን በእልህና ቁጣ ውስጥ ብቻ ሆነን ፍርድ የምንሰጥ ከሆነ ለስሜታችን ልክ ልንሆን እንችላለን። እንደሀገር ግን ያልጠበቅነው ሌላ አደጋ መከሰቱ የማይቀር ነው። እስቲ ለምን መንግስት እነስብሃትን ነጻ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው እስኪነግረን በትዕግስት አንጠብቅም? የራሳችንን እልህና ቁጭት ዋጥ አድርገን እይታችንን ከቀጠናው አጠቃላይ ጂኦፖለቲካል ፍጥጫ አንጻር ሰፋ አድርገነው እንፈትሸው። በተረፈ በእነስብሃት መፈታት እኔም የእግር ጥፍሬ ድረስ ድንጋጤ ያነዘረኝ መሆኑን መደበቅ አልፈልግም። በጥሞናና በእርጋታ ነገሮችን ለማየት እድል መስጠቱን ግን መርጬአለሁ። #ኢትዮጵያ #Ethiopia
Show all...
ከፍትህ ሚኒስቴር ክሳቸው ተቋርጦ በተፈቱ እስረኞች ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ መንግስት የተወሰኑ እስረኞችን ክስ በማቋረጥ ከእስር መፍታቱ የአገራዊ ምክክሩን አካታችነት እና ሰብአዊነትና ርህራሄን ታሳቢ ያደረገ ውሳኔ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ። ከፖለቲካ ልሂቃን አልፈው ወደ ማህበረሰቡ እየተንጸባረቁ ያሉ ያለመግባባት ችግሮችን በአገራዊ ምክክር ከስር መሰረቱ ለመመፍታት በመደበኛ ፍትህ ብቻ ሳይሆን በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ እልባት መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል። የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፤ መንግስት በትናንትናው እለት የተወሰኑ እስረኞችን መፍታቱን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸውም በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው የተያዙ እስረኞችን በመፍታት ሂደት 'ምህረት' የሚደረገው በሕግ አውጭ አካል ሲሆን ይቅርታ ደግሞ በይቅርታ ቦርድ ጥያቄ መሰረት በአገሪቷ ፕሬዝዳንት በኩል የሚፈፀም መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም በትናንትናው እለት መንግስት ይፋ ያደረገው እስረኞችን የመፍታት እርምጃ ምህረትም ሆነ ይቅርታ ሳይሆን በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ላይ ያለን ጉዳይ ክስ የማቋረጥ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል። የክስ ማቋረጥ ውሳኔው የተወሰነው በሶስት መዝገቦች ሲሆን ሁሉቱ መዝገቦች በአቶ ጃዋር መሃመድና በአቶ እስክንድር ነጋ ስም ያሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በሁለቱ መዝገቦችን ክስ የማቋረጥ ውሳኔ ሁለቱ ግለሰቦች በርካታ ተከታይ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች በመሆናቸው ለአገራዊ ምክክር መድረኩ አካታችነትና አሳታፊነት የሚኖረውን ፋይዳ ታሳቢ ማድረጉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። 'አገራዊ ምክክር በአንድ አገር ከብዙ ዘማናት አንድ ጊዜ የሚደረግ ነው' ያሉት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያም እስካሁን ሁሉን አካታች አገራዊ ምክክር ተካሂዶ እንደማያውቅ ገልጸዋል። በዚህም እስረኞችን የመፍታት ውሳኔው 'ሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፌበታለሁ' የሚለው አሳታፊና አካታችና ቅቡልነት ያለው የምክክር መድረክ እንዲሆን ለማስቻል መንግስት የሄደበት እርቀት ስለመሆኑ አንስተዋል። በሶስተኛ የክስ መዝገብ ደግሞ በእነ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ስም የተካተቱ ስድስት ግለሰቦች ከጤና ችግርና ከዕድሜ መግፋት አንጻር ጉዳያቸው ታይቶ ለሰብዓዊነትና ለርህራሄ ሲባል ከእስር እንዲፈቱ መደረጉን አብራርተዋል። በመዝገቡ የተካተቱ ተከሳሾች ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራር የሰጡ ግለሰቦቦች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ስድስት ግለሰቦች የአሸባሪው ቡድን ስራ አስፈጻሚ አባል ያልነበሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በክስ መዝገቡ የተካተቱ ሌሎች ተከሳሾች የክስ ሂደቱ ግን ይቀጥላል ብለዋል። አገር መልከ ብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ስትገባ ችግሮቹን ለመፍታት በመደበኛ የፍትሕ ስርዓቱ መሰረት መፍትሄ ስለማያገኙ የሽግግርና የተሃድሶ ፍትህ ተመራጭ የሚደረግበት አውድ እንዳለ ጠቅሰዋል።በዚህም በኢትዮጵያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ የአገር ህልውና ለማስጠበቅ በኢትዮጵያ ከመደበኛው ፍትህ ስርዓት ይልቅ በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ እልባት መስጠት ተገቢነት እንደለው ገልጸዋል። በኢትዮጵያ አገራዊ መግባባትና መስማማት የሚያስፈልጋቸው በርካታ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እስካሁን የተደረገ ሁሉን አቀፍ አገራዊ ምክክር አለመኖሩን ያስታወሱት ሚኒስትሩ ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ መሆኑን ተናግረዋል። አገራዊ ችግሮች ከፖለቲካ ልሂቃኑ አልፈው በማህበረሰቡ ዘንድ እየተንጸባረቁ በመሆኑ አገራዊ ቀውሱ ወደ ትውልድ እንዳይሻገር በበቀል ፍትህ ሳይሆን በምክክርና በውይይት መፈጸም የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ብለዋል። ባለፉት ሶሰት ዓመታትም ሆነ ቀደም ሲል ባጋጠሙ የመብት ጥሰቶች የአገር ህልውና ታሳቢ ባደረገ መልኩ በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ መፈትሄ መስጠት እንደሚገባ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል ነው ያሉት። በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ላይ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረገው አቶ ስብሐት ነጋ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር፣ አቶ ኪሮስ ሐጎስ፣ አቶ ጃዋር መሐመድና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ እንዲሁም አቶ እስክንድር ነጋና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ መሆኑ ይታወቃል። ኢዜአ
Show all...
ሰበር ዜና እነእስክንድር ነጋና ጃዋር መሐመድን ጨምሮ በእስር ላይ የነበሩ የፖለቲካ መሪዎች ተፈቱ ታኅሣሥ 29/2014 (ዋልታ) መንግሥት በእነ እስክንድር ነጋና ጃዋር ሲራጅ መሐመድ መዝገብ የተከፈቱትን ክሶች እንዲቋረጡ መወሰኑን ተከትሎ እስረኞቹ ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ ሆኗል፡፡ ከእሥር በምሕረት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው 1. አቶ ስብሐት ነጋ 2. ወሮ ቅዱሳን ነጋ 3. አቶ ዓባይ ወልዱ 4. አቶ አባዲ ዘሙ 5. ወሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር አቶ ኪሮስ ሐጎስ 6. አቶ ጁሐር መሐመድና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ 7. አቶ እስክንድር ነጋና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ
Show all...
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የፈለግንውን መሳሪያ መሻሻጥ እንችላለን። ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የፈለግነው የጋራ ስምምነት እናደርጋለን። የኢትዮጵያን መንግስት ግን ይሄንን አድርግ ይሄንን ስራ ብለን አናዝም። አገሪቱ አለም ላይ ሀገረ መንግስት ሳይመሰረት በፊት ቀድማ መንግስት ያላት በራሷ ፖሊሲ እራሷን ያስተዳደረች አገር ናት። ከዚች አገር ጋር ስለ ስረአተ መንግስት ስለ ውስጥ ጉዳይ ገብተን ይሄንን ፈፅሙ በዚህ ሁኔታ ቀጥሉ ከዚህ አገር ጋር ተጣሉ አንልም። የአገሪቱ ታሪክ እንደዛ አይፈቅድም። ቱርክም የዚህ አይነት ፖሊሲ የላትም። እንኳን ለኢትዮጵያ ለብዙ ትንንሽ አገሮች የኛን ጥቅም ጎደተው የነሱ ጥቅም እንዲከበር ነው አድርገን ነው ስምምነት ላይ የምንደርሰው። ለምን ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት አደረጉ መሳሪያ ሸጡ እያሉ የሚወቅሱ አገሮች አሉ። እኛ ህጋዊ የአገሪቱ መንግስት ጋር ነው ስምምነት ያደረግነው ይህ ማንኛውም መንግስት የሚያደርገው የሚደበቅ ነገር የለለው ነው። የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ጥሰን በጀት ወይም በወታደር የሰው አገር ሄደን አልደበደብንም። እኛ አፍሪካ ላይ ያለንን አካሄድ ስም ለማጠልሸት የሚፈልጉ አገሮች ትናንትም ዛሬም የሰው አገር ሉአላዊነት እየሰጣሱ ከተሞችን በማውደም፣ ህዝቦችን መባፈናቀል በመግደል አገር በመዝረፍ የሚታወቁ አገሮች ናቸው። ስለዚህ እኛ ከኢትዮጵያ ጋር የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ማንኛውንም ስምምነት ስናደርግ የእነሱን ፍቃድ መጠየቅ የለብንም። ወደፊት ኢትዮጵያ የቱርክ ጠንካራ ወዳጇ እንድትሆን እየሰራን ነው። መንግስታችን በጦርነቱ የወደሙ መሰረተ ልማቶችና የህዝብ መገልገያ ተቋሞች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ኢትዮጵያን ለማገዝ እየሰራ ነው። አፍሪካ ውስጥ ሰፊ የኢንቨስትመንት እና የሰው ሀብት ካላቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚ አገር ናት። ወደፊት ይሄንን ሀብት ተጠቅማ ከኛ ጋር አብረን ለመስራት ትኩረት ሰተን እየሰራ ነው። አገሪቱ በማንኛውም መንገድ ከቱርክ ጋር ጥቅማችንንና ጥቅሟን አስከብራ እሰራለሁ ካለች በአፍሪካ የቱርክ ተመራጭ አገር አድርገን ወስደን እንሰራለን። ከቱርክ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ የተወሰደ ኢራቅ አረቢክ የዘገበው ! @ሱሌማን_አብደላ
Show all...
ሰበር ዜና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ ****************** የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ። የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ በ13 ተቃውሞና አንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አዋጅ 1265/2014 ሆኖ በአብላጫ ድምፅ ነው የፀደቀው። ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በጋራ እንዲመክሩና ብሔራዊ መግባባትን እንዲፈጥሩ ለማስቻል በሚል ከዓመታት በፊት ጀምሮ ሲጠየቅ የነበረውን አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋም ጉዳይ ከመጋቢት 2010 በኋላ እንደአዲስ የተደራጀው መንግሥት በምርጫ ማግሥት ይህንኑ እውን ለማድረግ ቃል ገብቶ እንደነበር ይታወሳል።
Show all...
ኤድና ሞል ሲኒማ ከ13 ዓመታት አገልግሎት በኋላ ተዘግቷል። ለተመሳሳይ ዓመታት በሕንፃው አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ጌም ሴንተርም ስራ አቁሟል። ሁሉም ተከራዮች እስከ ጥር 2፣ 2014 ድረስ እንዲለቁ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን የድርጅቱ ሰራተኞችም ቢሯቸው ታሽጎ ያለ ክፍያ ተባረዋል። ይህንን ያደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ንብረቱን ኢስት ስቲል ለተሰኘው የቻይና ድርጅት እያስተላለፈ መሆኑ ይፋ አድርጓል። የኤድና ሞል ባለቤት ተክለብርሃን አምባዬ የተበደሩት ብድር በወቅቱ ባለመክፈላቸው ባንኩ ድርጅቱን በሐራጅ ለቻይናው ኩባንያ በ810 ሚሊየን ብር መሸጡ ይታወሳል።
Show all...
) የደቡብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስና የፀረ አፓርታይድ ታጋዩ ዴዝሞንድ ቱቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡   ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡   ዴዝሞንድ ቱቱ በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓትን ለማስወገድ ባደረጉት ትግል በፈረንጆቹ በ1984 የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡  
Show all...
ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ አረፈ! ታዋቂው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ በ53 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የቅርብ ቤተሰቦቹ ለቢቢሲ ገለጹ።ተስፋዬ ገብረአብ ለወራት በህመም ላይ የቆየ ሲሆን ኬንያ ዋና ከተማ ውስጥ ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ነው አርብ ከሰዓት በኋላ ታኅሣሥ 15/2014 ዓ.ም ነው ያረፈው።
Show all...
ህወሃት ኤርትራ ላይ ወረራ ፈፅሟል። ኢሳያስ አፈወርቂም ጦራቸው እርምጃ እንዲወስድ ትእዛዝ ሰጥተዋል። (ተስፋዬ ጥበቡ)
Show all...
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ይሄንን አሸባሪ ታግሎ የማስወገድ አቅምና ችሎታው አለው። ድጋፍና እርዳታ በአስፈለገ ጊዜም የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ከክልሉ ሕዝብ ጎን ይቆማል። የማንኛውም ውሳኔያችን መርሕ ኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ድል እንድትጎናጸፍ ማስቻል ነው፤ ግዛታዊ አንድነታችን የሚጠበቅበትና በዘላቂነት ኢትዮጵያ አሸናፊ የምትሆንበትን መንገድ መቀየስ ነው። ከእንግዲህ አሸባሪው ኃይል በቃዠ ቁጥር የፈለገውን የሚያደርግበት ሁኔታ የለም። የለም ስንል አይፈልግም ወይም አይሞክርም ማለታችን አይደለም። ነገር ግን እንደ ከዚህ በፊቱ አንድነታችን ጠብቀን እስከቆምን ድረስ መቼም ቢሆን ኢትዮጵያ አትሸነፍም፡፡ የኢትዮጵያ ድል መሠረቱ የጠላት ድክመት ሳይሆን የእኛ ብርታትና ትብብር መሆኑን አውቀን፣ ይበልጥ አንድነታችንን አጠንክረን መቆም ይገባናል፡፡ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ታህሳስ 15፣ 2014 ዓ.ም
Show all...