cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Hiwoti❣️ Tube❤️

Ewukt talakoan takbralech

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
199Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Respect 🙏
Show all...
የአለም እውነታወች ------------------------------------// ✍ የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ፀልይ ፡፡ ✍ የውሻ ቡችላ እየተሸጠ ሰውን ግን በነጻ የሚፈልገው ሲታጣ ዘመኑ መክፋቱን አንተም አብረህ መክፍትህን እወቀው ፡፡ ✍ ስለ ብርቅየ እንስሳት ብዙዎች እያለቀሱ ይናገራሉ በምግብ እጥረት ስለሚሞቱት ህጻናት ግን ቃል አይናገሩም ፡፡ ✍ ስለ ጠፈር ሳይንስ ብዙ ይወራል (ይሰራል) የምድር ኑሮ ግን ሲተራመስ ያስተዋለ የለም ፡፡ ✍ ስለ ወደቁ ሐውልቶች ብዙ ይባላል በየ ጎዳናው ዳር ስለወደቁት ምስኪን ህጻናት ግን ምንም አይባልም ፡፡ ✍ የለማኝ ገቢ ይጠናል ይታወቃል የ ባለ ስልጣናት ስርቆት ግን ታይቶ እንዳልታየ ይታለፋል ፡፡ ✍ ስለ አየር መበከል ዓለም በሙሉ ይጮሃል ስለሰው ልጆች መርከስ ግን ዝም ይባላል ፡፡ ✍ ውሾች እና ድመቶች አልጋህ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድክ ድሆች ግን የግቢህ ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ ባለመፍቀድህ የፈጣሪህን ምህረት ጠይቅ ፡፡ ✍ የፈጣሪ ስዕል እያልክ ስትስም ራሱ ፈጣሪ አክብሮ የፈጠረውን ሰውን ግን ረግጠህ በማለፍህ የወጣልህ አስመሳይ መሆንህን እወቀው ፡፡ ✍ ከዚህ አፍ እና ልብ ከተለያዩበት ቲያትረኛ ማንነትህ ፈጥነህ ውጣ ፡፡ ☞☞ ሰዎች ሆይ የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ፡፡ @ethiohane
Show all...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 ✍ያንተ የሆነችን ሴት አታስለቅስ፤ ምክንያቱም እምባዋን የሚጠርጉ ሌሎች አሉና✍ #ሴት፡ ምን ለማለት ፈልገህ ነው? #ወንድ፡ ግንኙነታችን ማቋረጥ እንዳለብን አስቢያለው #ሴት፡ ለምን? #ወንድ፡ አላቅም፤ ብዙም ደስተኛ አይደለውም፤ ይቅርታ ግን ከፈለግሽ ንፁ ጓደኛማቾች መሆን እንችላለን። #ሴት፡ እየቀለድክ መሆን አለበት። #ወንድ፡ በጣም አዝናለው፤ ባንቺ ምክንያት አይደለም፤ በእራሴ ምክንያት ነው፤ ነገሮችን ካለምንም ችግርና ፈቃድ ማድረግ እፈልጋለው፤ ለፍቅር ህይወት ዝግጁ አይደለውም። #ሴት፡ ግን እኮ እንደ ምታፈቅረኝ ነግረከኛል፤ እነዛን ሁሉ ቃልኪዳኖች ገብተህልኛል፤ እንድቀርብህ አድርገኸኛል፤ ሁሉ ነገሬን ሰጥቼካለው፡፡ እንዴት ይሄን ታደርግብኛለክ? #ሴት፡ ሌላ ሴት አለች አይደል? ግልፁን ንገረኝ! #ወንድ፡ ማንም የለም፤ በቃ በቻዬን መሆን ፈልጌ ነው፤ አስደሳች ግዜ ነበር ያሳለፍነው፡፡ #ሴት ፡ በጣም መጥፎ ሰው ነክ፤ ሁለተኛ እንዳታናግረኝ። በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ሴቷ online ስትገባ ወንዱ ከሌላ ሴት ጋር ፎቶ post አድርጎ ተመለከተች፡፡ "ሌላ ሴት እንዳለች ገምቼ ነበር፤ በጣም ውሸታም ነክ" ብላ txt አረገችለት፡፡ ግን ምላሽ አላገኘችም፡፡ ቀኖች መቁጠራቸውን ቀጠሉ እሷም ያለማቋረጥ ስለሱ ታስብ ነበር። በስተመጨረሻ "በጣም ናፍቀኸኛል፤ እባክህ ዳግም እናውራ" በማለት txt አረገችለት፡፡ አሁንም ምላሽ የለም፡፡ አሁንም በህይወቱ ምን አዲስ ነገር እንደተፈጠረ ለማወቅ የልጁን Social media በየቀኑ ትመለከታለች። አሁንም ታፈቅረዋለች ቢሆንም እሱን እረስታ ወደፊት መሄድ እንዳለባት ታቃለች፤ ነገር ግን መቁረጥ አልቻለችም፡፡ #ሴት፡ " ሁሉም ነገር አንተ ጋር ሰላም እንደሆነ ተስፋ አደርጋለው፤ ሲመችህ txt አርግልኝ፤ ንፁ ጓደኞች እንድንሆን እየሞከርኩ ነው፡፡" ነገር ግን አሁንም ከወንዱ ምንም ምላሽ የለም፡፡ በሳምንታት ውስጥ ከአዲሷ ልጅ ጋር ፍቅረኛሞች መሆኑን አረጋገጠች፡፡ በዚህ ግዜ ሁሉም ነገር ቆረጠላት፤ እንደተዋሸች፣ እንደተከዳች፣ እንደተጠላች ተሰማት፡፡ እናም ለመቁረጥ ወሰነች፡፡ ከተወሰኑ ግዚያት በኀላ ሙሉ በሙሉ ለእሱ የነበራትን ስሜት አውጥታ መጣል ቻለች፡፡ ከሌላ ደስ ከሚል ሰው ጋር ፍቅር ጀመረች፡፡ አንድ ቀን ከአዲሱ ፍቅረኛዋ ጋር ፎቶ post አደረገች፡፡ #ወንድ፡ "ሰላም እንዴት ነሽ? አንቺ ጋር ሁሉም ሰላም ነበር ብዬ ተስፋ አደርጋለው፤ ነፃ ስትሆኝ txt አርጊልኝ፤ ናፍቀሽኛል ወጣ ብለን እንጨዋወታለን፡፡ txtuን አየችው፤ ከሌላ ወንድ ጋር ስላያት ብቻ ትኩረት ለመስጠትና እንደሚያስብላት ለመምሰል መሞከሩ አሳቃት፡፡ ይህን ያደረገው በመቅናቱና በእሷ ከተካት ሴት ጋር ደስተኛ ባለመሆኑ ብቻ እንደሆነ አውቃለች፤ ለዛም ነው ዳግም ሊያወራት የሞከረው፡፡ #ጭብጥ my brother በእጅህ ያለው ነገር ከእጅህ ሳይወጣ መውደድና ማድነቅን እወቅበት፤ ወርቁን በመዳፍህ ይዘህ ሳለ ነሀሱን ፍለጋ አትኳትን፤ መልካም ቀን             ይቀላቀሉን ለ አስተያየትዎ 👉 @ethiohane
Show all...
#ስለ_ጊዜ ኒዉዬርክ ከካሊፎርኒያ በ 3 ሰዓት ትቀድማለች ነገር ግን ይህ ካሊፎርኒያን ቀርፋፋ አያደርጋትም ምክንያቱም የራሷ ጊዜ አላትና ፡፡ አንዳንድ ሰዉ በ22 አመቱ ይመረቃል ነገር ግን አሪፍ ስራ ለመያዝ 5 አመት ይፈጅበታል። አንዳንዱ በ25 አመቱ የድርጅት ሃላፊ ሆኖ በ50 አመቱ ሲምት ሌላዉ በ50 ዓመቱ ሃላፊ ሁኖ እስከ 90 ዓመት ይኖራል። ኦባማ በ55 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጨረሰ ነገር ግን ትራምፕ በ70 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጀመረ! ይሄ ትራምፕን ኅላ ቀር አያደርገዉም። ጊዜ በሕይወታችን ወሳኝ ነገር ነዉ ፡፡ ፈጣሪ በግዜዉ ሁሉን ነገር ዉብ ያደርጋል ፡፡ ስለዚህ.... ከሁሉ በኋላ የቀረን ወይም ወደፊት የቀደምን አይምሰለን ሁሉም ሰዉ የራሱ የሆነ የኑሮ ሩጫና የተፈጠረበት አላማ አለዉ! ሁላችንም የራሳችን የሆነ የጊዜ ክልል አለን @ethiohane
Show all...
✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔ እርግጠኛ ነኝ ይህን ጽሁፍ ካነበባችሁ በኋላ የሚሰማችሁ የመንፈስ እርካታን ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያቅትም። አጭር ጽሁፍ ነች ትነበብ ✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔ በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጎድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ በራሷ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣምም መጮህ ጀመረች፡፡ ባለቤቱም አህያዋን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለተ አልቻለም፡፡ አህያዋም ብዙ ያገለገለችና ያረጀች ስለሆነች እንዲሁም ሌሎች እንስሳትም ወደ ጉድጓዱ እንዳይገብበት በማሰብ ጉድጓዱ ውስጥ ሊቀብራት ወሰነ፡፡ ጎረቤቶቹንም አስተባብሮ ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ፡፡ አህያዋ ይህን ስትመለከት እየቀበራት መሆኑነ ተረዳችና በሰቀቀን አለቀሰች፡፡ይሁን እንጂ አህያዋ አፈር ሲደፋባት አንድ ነገር ታደርግ ጀመር፡፡ አፈሩ በተደፋባት ቁጥር አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ጀመር፡፡በተደጋጋሚ ከሚደፋባት አፈር ላይ መቆምም ትጀምራለች፡፡በሂደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች ከፍ እያለች በመጨረሻም ጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መውጣት ቻለች፡፡በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ሰዎች በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡ ሰው ያስባል እግዚአብሔር ይፈፅማል!!!!!!! ከእግዚአብሔር አይምጣ እንጂ ከሰው የመጣ እሱ ይመልሰዋል !!!!!! አሜን !!!!!!!!!! ! ካነበብኩት! «ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ» @ethiohane
Show all...
በጥዋት ተነስተህ አትበሳጭ፣ባለፈው ነገር አትማረር፣አትናደድ ይልቁም ዛሬ ለተሰጠህ ህይወት ፈጣሪህን አመስግን። በህይወት መኖርህ በራሱ ትልቅ ተስፋ ነው። አንተ ጥረትህን ቀጥል ፈጣሪ ሁሉን በጊዜው ያደርጋል። ☞እንዳትረሳ ፦ ስለሌለክ ነገሮች እያሰብክ ፈጣሪን አታማር ይልቁንም ስላለክ ብዙ ነገሮች በማሰብ ደስ ይበልክ ፈጣሪንም አመስግን። ➖➖➖መልካም ቀን➖➖➖        @ethiohane
Show all...
📚ለበጎ ነው አንድ ሰው በባህር ብቻውን በጀልባ እየተጓዘ በማዕበል ተመታና ጀልባው ተሰባብራ በባህሩ ውስጥ ሰጠመች። ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል። ምግቡን ዓሳ አያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ። አንድ ቀን ለምግብ የሚሆነው አሳ ሊያጠምድ ባህሩ ዳርቻ ላይ መንጠቆውን ይዞ ለረጅም ሰአት እየጠበቀ እያለ በድንገት ጭስ ሸተተው። ዞር ብሎ ሲያይ ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው። እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት አልቻለም። ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል፤ አለቀሰ፤ ፈጣሪውን ወቀሰ፤ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ብቻዬን ጥለኸኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለኸኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራኋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለህ ብሎ አማረረ። ከደቂቃዎች በኃላ አንድ ድምፅ ሰማ፤ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ፤ ተደሰተ። የመርከቡ ሰዎች መጥተው ጭነው ወሰዱት። ከዚያም የመርከቡን ሰዎች ጠየቃቸው! እንዴት አገኛቹኝ? እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት አገኛቹኝ? አላቸው። መርከበኞቹም "እኛማ በዛኛው በኩል ዞረን እየሄድን ነበር። ከዚህ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰዉ ይኖራል ብለን መጣን፤" አንተን አገኘን አሉት። አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃዬ ልታውጣኝ ፈልገህ ነው ትንሿ ጎጆዬን ያፈረስከው፤ ወደ ትልቁ ቤቴ ልትውሰደኝ ነው አለ። አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣና ሲበላሽብን ሰውንም ፈጣሪንም ስናማርር እንኖራለን። ግን ካጣነው እና ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን። በችግራችን ጊዜ መጠጋት ያለብንን ፈጣሪያችን እንረሳዋለን። ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪ የሆነውን አምላክ እንወቅሳለን። ወዳጄ ሆይ ሁሌም ቢሆን በማንኛውም መጥፎ አጋጣሚ ውስጥ ሆነንም መልካም ነገሮችን ማሰብና በፈጠረን አምላክ ተስፋ ማድረግን ልማድ እድርገው፡፡ @ethiohane @ethiohane @ethiohane @ethiohane
Show all...
ኩባያው ባዶ ሲሆን ነው መቅዳት የምትጀምረው የዛሬ ርእስ በውሀ የተሞላ ኩባያ ውስጥ ማንም ውሀ መጨመር አይችልም፡፡ በውድቀት በሽንፈት በሞራል ውድቀት በትናንት ታሪክ ፀፀት በተሞላ የአይምሮ ኩባያ ውስጥም ማንም ሀኪም ማንም አዋቂ ማንም ወዳጅ ዘመድ ፍቅረኛ ደስታን ሊጨምር አይችልም፡፡ ንፁህ ውሀ መቅዳት ከፈለክ መጀመሪያ ኩባያው ባዶ መሆኑን አረጋግጥ፡፡ ምናልባት የትላንት ህይወትህ ግሳንግስ ወይም በስደት ስለኖርክ ወይም እነከሌ የያዙት አንተ ጋር ስለሌለ በቅናት በፀፀት ኩባያህን ሞልተኸዋት ታዲያ ፈጣሪ የመፅናናትን የብርታትን የስኬትን ውሀ የት ይቅዳልህ? ውድ አንባቢዬ የትም እንዴትም ሆነህ አንብበኝ ይህንን እውነት እፅፍልሀለው ጀበና ቢገነፍል እራሱን ነው የሚያቆሽሸው ህይወትን ሁሌ ብታማርራት ተበሳጭተህ እራስህን ከህይወት ገፅ ብትገነጥል እራስህን ነው የምትጎዳው፡፡ ስለዚህ ኩባያህን ዛሬ አሁን እያት የያዝክባትን ሁሉ ድፋ ይህንን ፅሁፍ አንብበህ ስትጨርስ ያለምክንያት ፈገግ በል፡፡ ትችላለህ ጥርሳቸውን ለምግብ መፍጫነት ብቻ ከሚጠቀሙ ሰዎች ተለየህ ማለት ነው፡፡ ጀግናና ሚስማር ሲመቱት ይጠብቃል እንደሚባለው ሁሉ አንተም ችግር ስደት ወሬ ተስፋ መቁረጥ ሲመቱህ የበለጠ እየጠበክ ተስፋ አስቆርጣቸው፡፡አይዞህ መሆን የፈለከውን ህልምህን ዛሬ ጀምረው በተስፋ ተስፋን የሰጠ የታመነ ነው!! በቅንነት አምላክህን ጠይቀው ይሰጥሀል፡፡ መልካም ምሽት ሚስትህን እንደራስህ ምትውርዳት ወደክ ኣይደለም የፈጣሪ ህግም ጭምር ነው አንድ ሰውዬ ፂሙን በጣም ያሳድጋል ግን ታጥቦት አያውቅም የሚበላው ምግብ ፍርፋሪ የሚጠጣው መጠጥ እንጥብጣቢ ፂሙ ውስጥ እየገባ ይጠራቀማል ግን አይታጠብም ። እና አንድ ቀን መሽተት ጀመረ ሰውየውም አፍንጫውን ይዞ ከቤት ወጣ ውጭውም ይሸታል በቃ አካባቢያችን ተበክሎአል ብሎ ሌላ ሰፈር ሄደ ይሸተዋል ካፌ ገባ ጭራሽ የካፌውም ሰዎች አፍንጫቸውን ይዘዋል በጣም ተገርሞ ወደቤቱ ተመለሰ ሽታው ግን ሊጠፋለት አልቻለም መጨረሻ በቃ አለማችን #ገምቶአል ብሎ ተቀመጠ * ** ****, ምነው ስለግማት ፃፍሽ እንዳትሉኝ። እኛ ሰዎች እራሳችን ላይ ያለውን ችግር ማየት አንችልም ይባስ ብለን እኛ ለፈጠርነው ችግር ሌሎችን ተጠያቂ እናደርጋለን ትልቅ መስታወት ፊት ቆመን እራሳችንን ሳይሆን ሌሎችን እናያለን 👉እስኪ እራሳችንን እንይ የሌሎች ሰዎች ውድቀትን የሌሎችን ሰንፍና የሌሎችን ድካም አናውራ እራሳችን የተሸከምነውን ከኛ አልፎ ለሌሎች ችግር የሆነውን የራሳችንን ስህተት እናቅና ይሄ ሰውዬ ፊቱን ነበር መታጠብ የነበረበት እራሱ በፈጠረው ቆሻሻ ሌሎቹን ማሽተቱ ሳያንስ ችግሩንም የሌሎች አደረገው 👉እራሳችንን እንመልከት ። ፍቅሪ ይስዕር ፍቅር ያሸንፋል ማፍቀርህ እግጠኛ ብቻ ሁን https://t.me/Ethiohane
Show all...
Hiwoti❣️ Tube @@💣

Ewukt talakoan takbralech