cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ገድለ ቅዱሳን

@Gedelat ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡ በአድራሻችን ✍ @Mnfesawi_bot

Show more
Advertising posts
6 670
Subscribers
-324 hours
-17 days
+4930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

                        †                         🕊  💖        †   †   †       💖  🕊 [         በፍቅር ፍርሃት የለም !        ] 🕊 ❝ አንዴ የእግዚአብሔርን ፍቅር ከቀመስንና በፍቅሩ መመላለስ ከጀመርን ፈቃዳችን ሁሉ የጌታን ፍርድ ቀን በናፍቆት መጠባበቅ ይሆናል፡፡ በትእግስትና በፍጹም ተአምኖ ሁነን፡፡ ምክንያቱም በዚህ ዓለም ስንኖር ምሳሌውን የምንከተል ነንና፡፡ ከሚመጣው ዓለም ከርስቱ ተካፋዮች ነን፡፡ እምነታችንን በእግዚአብሔር ፍርሃት መጀመራችን መልካም ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም የጌታን የፍርድ ቀን የምንፈራ እንሆናለንና፡፡ ጠላታችን ሰይጣንን ለመዋጋት ንቁ እንሆናለን፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር እና የወንድሞቻችን ፍቅር እየወደድን በመጣን ቁጥር የሠርጉን ቀን በናፍቆት የምንጠባበቅ እንሆናለን፡፡ ልክ ንጽሕት ድንግል ተጊጣ አምራ የሙሽራዋን ቀን እንደምትጠባበቅ እምነት ፍቅርና ተስፋን ተሞልተን የጌታን ቀን ናፍቆት የምንጠባበቅ እንሆናለን፡፡ ፍቅር በልባችን ውስጥ ሲነግሥ ፍርሃት ቦታውን ይለቃል፡፡ በመጀመሪያ ፍጹም የሆነ ፍቅር እርሱም ፍርሃትን በልቡናህ አስወግዶ የሚያስወጣ በር መኖሩን ተመልከት፡፡ መርምርም። ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላልና የአማኝ ሰው ፍጹምነት ፍቅር ነው። ❞ ❝ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም። ፍርሃት ቅጣት አለውና። የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። ❞ [ ፩ዮሐ.፬፥፲፰ ]                  †                        [ 💖  ከጾማችን ማግሥት  💖  ] [ 🕊 በአበው ቅዱሳን 🕊 ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Show all...
                        †                         🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 ❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞ ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  ❝  ቤተክርስቲያንን በደሙ ተቤዣት  ❞  ] ❝ [ ኃጢአት የሚደመሰስባት እንድትሆን ጽዮን [ መጠጊያ የሆነች ወይም የምትባል ] ቤተክርስቲያንን በደሙ ተቤዣት [ ቤዛ ሆናት ወይም ገዛት ] ፣ ከጎኑ በፈሰሰው ውኃም አጠመቃት ፣ በዕጸ መስቀሉም ቀደሳት። ❞ [ ድጓ ዘፋሲካ ] [       እናታችን ቤተክርስቲያን !      ] ❝ መሓሪው አምላክ በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ዓለም ደስታችን ፍጹም ይሆንልን ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ሲል ቅድስት ቤተ ክርስቲያኑን በደሙ መሠረታት፡፡ ስለዚህ ከኃጢአት ሥርየት የምናገኝበትን ጸጋ ታጎናጽፈናለች፡፡ ትቀድሰናለች፡፡ ታስታርቀናለች፡፡ ሰማያዊ በረከትንም ታድለናለች፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሮች ዘወትር የተከፈቱ ናቸውና ወደ እርስዋ እንፋጠን፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ከነገርናት ሸክማችንን ሁሉ ትሸከምልናለች፡፡ ልባችን በደስታና በቅድስና እንዲመላ ታደርጋለች፡፡  ❞  [ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ] 🕊 [  💖  ነገረ ትንሣኤ - ፪ -  💖  ] 🕊 [ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ] †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Show all...
1
4
🕊 †   🕊   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡   🕊   † ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ግንቦት ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 🕊 †  ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ †  🕊 በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሐዋርያት ቀጥሎ የቅዱስ አትናቴዎስን ያሕል ስለ ሃይማኖት የተዋጋ ቅዱስ ፈልጐ ማግኘት አይቻልም:: †  ቅዱስ አትናቴዎስ ማን ነው ? ቅዱስ አትናቴዎስ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዘመነ ሰማዕታት መጠናቀቂያ በ፫፻ [300] አካባቢ ፪፻፺፮ (296) እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው:: ወላጆቹ አረማውያን በመሆናቸው ክርስትናን አልተማረም ነበር:: ሕጻን እያለ ለጭዋታ ከቤቱ ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተ:: ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት:: አትናቴዎስም ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ ብሏቸው እሺ ስላሉት ሕጻናቱ ዕጣ ተጣጣሉ:: ላንዱ ቄስ: ላንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያርክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕጻናት ይሰግዱለት ጀመር:: በአጋጣሚ ሕጻናቱ ይሕንን ሁሉ ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ እለ እስክንድሮስ በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕጻኑ አትናቴዎስ ትንቢት ተናገረለት:: ከዚያም የአትናቴዎስ አባቱ ሲሞት ሊቀ ዻዻሳቱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ: የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ሁሉ በልቡናው ላይ ቀረጸበት:: ከዚሕ በኋላ ዲቁናን ሹሞ አስተምር አለው:: ምንም ሕጻን ቢሆንም ከሊቅነቱ: ከአመላለሱና ከአንደበቱ ጣፋጭነት የተነሳ የሰማው ሁሉ ይደነቅ ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ አድራለችና:: ቅዱስ አትናቴዎስ ሊቀ ዲቁና በተሾመ ወራት አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን በመረበሹ ኒቅያ ላይ ፫፻፲፰ [318] ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡ ጸሐፊ አድርገው ሾሙት:: በጊዜውም በዕድሜ የስንት ጊዜ ትልቁ የሚሆነውን አርዮስን ተከራክሮ ምላሽ አሳጣው:: †  ቅዱስ አትናቴዎስ ከሊቃውንቱ ጋር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ መሠከረ:: ጸሎተ ሃይማኖትንም ያረቀቀው እርሱ ነው:: ከዚሕ በኋላ የእስክንድርያ [የግብፅ] ፳ [20] ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ:: ቤተ ክርስቲያንን በመልካም እረኝነት ለ፵፰ [48] ዓመታት ሲመግብ ብዙ መከራዎችን ተቀበለ:: ለ፭ [5] ጊዜ ከመንበሩ አፈናቅለው ወደ በርሃ ሲያግዙት በስደት ከ፲፭ [15] ዓመታት በላይ አሳልፏል:: በተሰደደባቸው ቦታዎች መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን አሳምኗል:: በጎቹ እንዳይባዝኑበት ደግሞ በጦማር [በደብዳቤ] ይጠብቃቸው ነበር:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናገኘው ቃለ ሃይማኖት በዚሕ ዘመን የተጻፈ ነው:: በወቅቱ የነበረው ንጉሥ [ትንሹ ቆስጠንጢኖስ] የአባቱን [ታላቁ ቆስጠንጢኖስን] ዕረፍት ተከትሎ ነገሠ:: ወዲያውም አርዮሳዊ መናፍቅ ሆነ:: ሃይማኖታቸው የቀና አባቶችንም ያሳድድ ገባ:: ከአበው ቅዱሳን መካከል ግንየዚህ መከራ ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አንትናቴዎስ ነበር:: በተለይ አንድ ጊዜ ንጉሡ ቅዱሱን ወደ በርሃ አግዞ: መናፍቅ ዻዻስ በግብጽ ሹሞ: ብዙ ክርስቲያኖችን በግፍ ሲያስገድል: ቅዱሱን ለ፮ [6] ዓመታት አሰቃየው:: የወገኖቹ [የልጆቹን] ስቃይ የሰማው ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በድፍረት ወደ ቤተ መንግስት ገብቶ ተናገረው:: ፪ [2] አማራጭን አቅርቦ "ወይ ግደለኝና እንደ አባቶቼ ሰማዕት ልሁን: ካልሆነ ግን ወደ መንጐቼ [ምዕመናን] መልሰኝ" አለው:: መናፍቁ ንጉሥም ቢገድለው ብጥብጥ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ በስልት ሊያጠፋው ወሰነ:: ቀዛፊ: መቅዘፊያ: ምግብና ውሃ በሌላት ጀልባ ውስጥ ከቶም ሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ጣለው:: ድንገት ግን ከሰማይ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ወረደ:: ሚካኤልና ገብርኤል ባሕሩን እየቀዘፍ: ሌሎች መላእክት እየመገቡት በዚህች ቀን እስክንድርያ [ግብጽ] አድርሰውት ተሠውረዋል:: ሕዝቡም በታላቅ ሐሴት እየዘመሩ አባታቸውን ተቀብለውታል:: ሐዋርያዊው ቅዱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋግቶ: ብዙ ስቃይንም ተቀብሎ በ፫፻፹፫ [373] ዓ/ም አካባቢ አርፏል:: ቤተ ክስርቲያን ፦ - "ሊቀ ሊቃውንት: - ርዕሰ ሊቃውንት: - የቤተ ክርስቲያን - [ የምዕመናን ] ሐኪም [ Doctor of the Church ]: - ሐዋርያዊ" ብላ ታከብረዋለች:: አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሊቁ በረከት አይለየን:: በምልጃውም ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን:: 🕊 [ † ግንቦት ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፪. የባሕታውያን አለቃ ታላቁ አባ ሲኖዳ [ጽንሰቱ] ፫. ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ [ሃብቱን: ንብረቱን: ልብሱን ሳይቀር መጽውቶ ራቁቱን የተገኘ ደግ ሰው ነው] ፬. አባ ሐርስዮስ ገዳማዊ [ †  ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ሥሉስ ቅዱስ [አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ] ፪. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ፫. አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን አለቃ] ፬. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት ፭. አባ ባውላ ገዳማዊ ፮. ቅዱስ አግናጥዮስ [ለአንበሳ የተሰጠ] " ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዐን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩ ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና። " [ማቴ.፭፥፲] (5:10) [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Show all...