cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Anatoni external audit and consultancy worker🙏

All about bussines ethiopia for our support we gave Telegram support by our telebirr account 0963160399

Show more
Advertising posts
479
Subscribers
No data24 hours
+47 days
+2430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

[ Album ] በመንግስት የልማት ድርጅቶች ላይ በተደረጉ የሪፎርም ስራዎች የገቢ አቅማቸውን ማሳደግ እንደተቻለ ተገለጸ ታህሳስ 2/2016 - የገንዘብ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የሶስት ወራት አፈጻጸም በተካሄደበት ወቅት እንደተገለፀው በመንግስት ልማት ድርጅቶች ላይ በተደረጉ የሪፎርም ስራዎች የገቢ አቅማቸው ማሳደግ እንደተቻለ ተገለጸ፡፡ በመድረኩ ላይ እንደተጠቀሰው የሩብ ዓመት በጥቅል የሀገር ምርት፣ በነፍስ ወከፍ ገቢ፣ በገቢ ረገድና ሌሎችም የኢኮኖሚ መሻሻል አመላካቾች ዕድገት ታይቷል ተብሏል፡፡ የሩብ ዓመቱ የመንግስት ወጪ 123.8 ቢሊዮን የተመዘገበ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ያጋጠመ የ34.3 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት በሀገር ውስጥ ምንጮች መሸፈኑ ተጠቅሷል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት ከልማት አጋሮች ጋር በቅንጅት በመሰራቱ የውጭ ሃብት ግኝት ከማሳደግ ባሻገር የበጀት ጉድለታችንን መሽፈን ችለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ታክስ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ጋር ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የፋይናንስ አስተዳደሩን ማጠናከር እና ማዘመን እንደሚገባ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡ የገንዘብ ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ በመንግስት ልማት ድርጅቶች በሆኑት በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት፣በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣በኢትዮ-ቴሌኮም እና በመሳሰሉ የመንግስት የልማት ተቋማት በተደረጉ የሪፎርም ስራዎች የገቢ አቅማቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሩ የመንግስትን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ባሰቀመጡበት ወቅት እንደተናገሩት የገቢ አሰባሰብ ለማሰደግ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመሆን በቅንጅት እንደሚስራ አሰረድተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ተግባራዊ በሚደረገበት ወቅት የገንዘብ ሚኒስቴር ድጋፍ እንደሚያደረግ ተናግረዋል፡፡
Show all...
dear our channel member we lost our number till release contact number 0937445158 Anatoni🙏🙏🙏
Show all...
👍 1
#ለሆቴሎች
Show all...
👍 1
የእሽሙር ማህበር (JOINT VENTURE) የእሽሙር ማህበር ምንነት የእሸሙር ማህበር በአዲሱ የንግድ ህግ ከተካተቱ ሰባት የንግድ ማህበር አይነቶች አንዱ ሲሆን ማህበሩ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸው በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት የሚያቋቁሙት በሦስተኛ ወገኖች የማይታወቅና የሕግ ሰውነት የሌለው የንግድ ማህበር እንደሆነ በንግድ ህጉ አንቀፅ 234 ስር ተደንግጓል፡፡ ይሁንና የማህበሩ መኖር በሦስተኛ ወገኖች ከታወቀ ጊዜ አንስቶ ማህበሩ ከእነዚህ ወገኖች ጋር በሚኖረው ግንኙነት እንደ ህብረት ሽርክና ማህበር ይቆጠራል፡፡ የእሽሙር ማህበር ከሌሎች የንግድ ማህበራት ከሚለዩት ባህርያት የንግድ ማህበሮች የማስመዝገብ ሥርዓቶች በዚህ ማህበር ላይ ተፈጻሚ የማይሆን መሆኑ ነው፡፡ የእሽሙር ማህበር ባህርያት የእሽሙር ማህበር መመስረት አንደኛ ሸሪክ ያለው ነገር ግን ሌላኛው ሸሪክ የሌለውን ጠንካራ ጎን ለመጋራት ያስችላል፡፡ ለምሳሌ እውቅና እና መልካም ስም ያለው የንግድ ስም (Brand Name ) ካለው የንግድ ማህበር ጋር ሽርክና የገባ ካንፓኒ ከመልካም ስሙ ተጠቃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ሁለት ሸሪኮች ያሏቸውን ጠንካራ ሀብት (የገንዘብ፣ የእውቀት፣ የቴክኖሎጂ እና የመሳሰሉትን) በማቀናጀት የተሻለ ውጤታማ የሆነ ማህበር ይመሰርታሉ፡፡ የሚከተሉት የእሽሙር ማኅበር ልዩ ባህሪያት ተብለው ሊወሰዱ ይችላሉ፡- 1. ህጋዊ ሰዉነት የሌለዉ ስለመሆኑ የእሽሙር የሽርክና ማኅበር ህጋዊ ሰዉነት የለዉም ሲባል በሸሪኮች መካከል ያለዉ ግንኙነት ተራ ዉል ግንኙነት ነዉ ማለት ነዉ፡፡ በመሆኑም ሸሪኮቹ የአንድ ተቋም አባላት ሳይሆኑ ተራ ዉል ተዋዋይ ወገኖች ናቸዉ፡፡ ይልቁን ህጋዊ ሰዉነት ስለሌለዉ የንግዱ ስራ የሚሰራዉ በሸሪኮቹ ስም ነዉ፡፡ ስለሆነም እያንዳንዱ ሸሪክ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ሲዋዋል፣ ዉሉን ሲፈጽም ወዘተ… በራሱ ስም ነዉ፡፡ ይህም የሚሆነዉ የሽርክና ማኅበሩ ለሶስተኛ ወገኖች ስውር ስለሆነ ነዉ፡፡ የእሽሙር ማኅብር ህጋዊ ሰዉነት ስለሌለዉ ሸሪኮቹ የሚያዋጡት ገንዘብ እና ሀብት የማኅበሩ ሊሆን አይችልም፡፡ በመሆኑም በንግድ ህጉ ቁጥር 236/2 ስር እንደተደነገገው ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር እያንዳንዱ ሸሪክ ያዋጣው ንብረት ባለቤት ነዉ፡፡ 2. ለሶስተኛ ወገኖች የማይታወቅ መሆኑ ለሶስተኛ ወገኖች አለመታወቁ (ድብቅ መሆኑ) ያለመመዝገቡ ውጤት ነዉ፡፡ የሕግ ሰዉነት ስለማይኖረዉ እንዲመዘገብ አይደረግም፡፡ ካልተመዘገበ ደግሞ ለህዝብ የሚታወቅበት መንገድ አይኖርም ማለት ነዉ፡፡ እዚህ ላይ የእሽሙር ሽርክና ማኅበር ድብቅነት የመመዝገብ ግዴታ ካለመኖሩ ብቻ የመነጨ ሳይሆን ይልቁንም በህጉ ታዉቆ እና ታስቦበት የተደነገገ ነዉ፡፡ አሰራሩም ያልተለመደ እና ግራ አጋቢ ቢመስልም በሌሎችም አገሮች የተለመደ እንጂ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ ያለ አይደለም፡፡ 3. ቅንጅት መፍጠር (Creates Synergy) የእሽሙር ማህበር በሁለት ወይም ከሁለት በላይ በሆኑ ማህበራት መካከል ሲመሰረት አንደኛው ሸሪክ የሌላኛውን ባህርይ ለመጠቀም ያስችለዋል (extract the qualities of each other)፡፡ እንዲሁም አንዳቸው ያንዳቸውን ጥቅም ለመጋራት ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ከፍተኛ ጥንካሬ ያለው ቅንጅት መፍጠር ይችላሉ ማለት ነው( a joint venture to generate synergies between them for a greater good)፡፡ይህም በተዘዋዋሪ ትልቅ ካፒታልን ለመፍጠር የሚያስችላቸው ሲሆን ወጪያቸውንም እንዲቀንሱ ይረዳቸዋል፡፡ 4. ስጋት/አደጋን መጋራት (Risk and Rewards can be Shared) የእሽሙር ማህበር በአንድ ሀገር ውስጥ ባሉ ድርጅቶች ወይም በተለያዩ ሀገሮች ባሉ ድርጅቶች መካከል ሊደረግ የሚችል ሽርክና በመሆኑ በእነዚህ ሀገሮች ሊኖሩ የሚችሉ የባህል ልዩነቶች (diversifications in culture)፣ የቴክኖሊጂ፣ የመልከዓ መድር አቀማመጥ ጥቅምና ጉዳት (geographical advantage and disadvantage)፣ የተደራሽ ደንበኝ (target audience) ሁኔታዎች በማህበሩ ላይ ሊፈጥር የሚችለው ተፅዕኖ ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ በመሆኑም በሸሪኮች መካከል የሚደረግ ስምምነት የአደጋ ስጋቶችን እና ጥቅሞች ለመጋራት ያስችላቸዋል፡፡ 5. የተለየ ህግ አለመኖር (No Separate Laws) የእሽሙር ማህበር የሕግ ሰውነት የሌለው የንግድ ማህበር በመሆኑ ማህበሩን የሚያስተዳድር የተለየ ሕግ አይኖርም፡፡ እንዲሁም ይህን ማህበር በተለየ ሁኔታ የሚያስተዳድር አካልም የለም(no separate governing body which regulates the activities of the joint venture.)፡፡ የእሽሙር ማህበር ጥቅሞች (advantages of a Joint Venture) 1. የምጣኔ ሀብትን ማሳደግ (Economies of Scale) የእሽሙር ማህበር ሸሪኮች ወይም ድርጅቶች ሀብታቸውን ወይም ካፒታላቸውን በማጣመር ስለሚቋቋሙ ህብረት መመስረታቸው ውስን አቅማቸውን ለማሳደግ ይረዳቸዋል፡፡ 2. አዲስ ገበያ መድረስ እና የአውታረ መረቦችን ስርጭት (Access to New Markets and Distribution Networks) አንድ ድርጅት ከሌላ ድርጅት ጋር የእሽሙር ማህበር ስምምነት ሲያደርግ አንደኛው የሌላኛውን የገበያ እድል የመጠቀም እና የማሳደግ አጋጣሚን ይፈጥርለታል፡፡ ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ካንፓኒ ከህንድ ካንፓኒ ጋር የእሽሙር ማህበር ስምምነት ቢያደርግ በህንድ ውስጥ የሚኖርን ሰፊ፣ የተለያየ የመግዛት ፍላጎት እና አቀም ያለውን ገበያ የመድረስ ጥቅም ያገኛል ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የህንድ ካንፓኒም በአሜሪካ ውስጥ የሚገኝን ጥሩ የመክፈል አቅም ያለውን ገበያ መቀላቀል ይችላል ማለት ነው፡፡ 3. ፈጠራን ማሳደግ (Innovation) የእሽሙር ማህበር ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ከቴክኖሎጂ አንጻር ለማሻሻል እድልን ይፈጥራል፡፡ በመሆኑም የቴክኖሎጂ መሻሻል እና የፈጠራ ስራዎች ማደግ የተሻሉ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ውጤታማ በሆነ ዋጋ( efficient cost) ለማቅረብ ያስችላል፡፡ አለም አቀፍ ድርጅቶች አዳዲስ ምርቶችን በቅናሽ ዋጋ በተሻለ ጥራት እንዲያቀርቡ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ 4. የማምረቻ ወጪን ማሳነስ (Low Cost of Production) ሁለት እና ከሁለት በላይ ሸሪኮች ሲጣመሩ ውጤታማ በሆነ ዋጋ ምርትን ለደንበኞች ማድረስ አንዱ አላማቸው ነው፡፡ ይህም የሚሆነው የማምረቻ ዋጋን መቀነስ ሲቻል ነው፡፡ በመሆኑም የማምረቻ ዋጋን በጋራ በመቀነስ የተሻለ ምርት እና አገልግሎትን ለደንበኞች ያቀርባሉ፡፡ የእሽሙር ማህበር ጉዳት (Disadvantages of a Joint Venture) 1. ግልፅ ያለሆነ አላማ፡- ሸሪኮች በእሽሙር ማኅበር ሲጣመሩ አላማቸውን በጣም ግልፅ በሆነ ሁኔታ የማያስቀምጡበት አጋጣሚ በርካታ ነው፡፡ እንዲሁም የማህበሩ አላማ ለሁሉም የማህበሩ አባላት በአግባቡ ላይገለፅላቸው ይችላል፡፡ በመምሪያው ህ/ማ/ማ/ስ/ሂ
Show all...
👍 1
የቴምብር ቀረጥ የክፍያ ሁኔታዎች  •  የሚከፈለው የቴምብር  ቀረጥ  ከብር 50.00 በታች  በሚሆንበት ጊዜ  ክፍያ ተገቢውን ዋጋ የያዘውን ቴምብር በመለጠፍ ይፈጸማል ፡፡ •  የሰነዱ ዓይነትና ሁኔታ ለየት ያለ አሠራርን  ሲጠይቅ  የታክስ ባለሥልጣኑ  በሚሰጠው አቅጣጫ /መመሪያ መሠረት ቴምብር ከመለጠፍ በሌላ መንገድ ቀረጡ አንዲከፈል ሊያደርግ ይችላል ፡፡ •  የተምብር  ቀረጥ  በተለጠፈበት ሰነድ የሚሠራ ወይም የሚቀበል ስው በዚህ ቴምብር  ሁለተኛ እንዳይሰራ ተደርጎ  ይሠረዛል ፡፡ •  ቴምብሩ ታክስ ባለሥልጣኑ በሚወስነው መሠረት ካልተሰረዘ ሰነዱ ቴምብር እንዳልተለጠፈበት ይቆጠራል ፡፡  •  በንብረት ባለቤትነት መመዚገቢያ ሰነድ ላይ የሚከፈለው የቴምብር ቀረጥ ልክ የሚሰላው አንድ ሰው ከሌላ ሰው በተላለፈለት ወይም በህግ መሠረት  የንብረት ባለቤትነት ምዝገባ በሚፈጸምበት ንብረት ላይ አንደኛው የጋራ ባለቤት ያለውን ድርሻ ለሌላው የጋራ ባለቤት ወይም የጋራ ባለቤት ላልሆነ ማንኛውም ሰው ሲያስተላፍ ለንብረቱ ባለቤትነት መመዚገቢያ ሠነድ ላይ የሚከፈለው የቴምብር ቀረጥ የሚተሰበው በንብረቱ ሙሉ ዋጋ ላይ ሳይሆን በተላለፈው ድርሻ ላይ ብቻ ነው ፡፡ በጋራ ባለቤትነት በተያዘ ንብረት ላይ የጋራ ባለሀብቶች የሚኖራቸውን መብትና ግዴታ የሚወሰነው የጋራ ሀብትን የሚያቋቋመው ውል ወይም ኑዛዜ ስለሆነ እያንዳንዱ ባለ ሀብት ስላለው ድርሻ መቅረብ ያለበት ማሰረጃ በንብረቱ ላይ የጋራ ሀብትን ያቋቋመ ውል ወይም ኑዛዜ ነው፡፡ ውሉን ወይም ኑዛዜውን የእያንዳንዱ ባለሀብት ድርሻ የማይለያይ ሲሆን እያዳንዱ የጋራ ባለሀብት በንብረቱ ላይ እኩል ድርሻ እንዳለው ይገመታል ፡፡ •  የጨረታ ማሰከበሪያ ወይም የውል ማስከበሪያ ( በጨረታ ያሸነፈው ሰው መ/ቤቱ የሚፈልገውን ውጤት እንዲያገኝ የሚያስችለውን ተግባር ለማከናወን የሚገደድብትን ውል ሲፈርም የውል መስከበሪያ ደግሞ ተዋዋዩ በውሉ የገባውን ግዴታ በአግባቡ ሲፈጽም ቀሪ የሚሆኑና ተጫራቹ  ወይም ተዋዋዩ ለመ/ቤቱ የሚገባቸው የገንዘብ ዋስትና ግዴታዎች) የሚጠይቅ ሰው ዋስትናውን የሚሰጠው በሰነድ ከሆነ በቴምብር ቀረጥ አዋጅ አንቀጽ 2(2) መሠረት ሰነዱ ማገቻ ስለሆነ ከአዋጁ ጋር በተያያዘ  ሠንጠረዥ ተመን መሠረት ቀረጡ ይከፈልበታል ፡፡  •  ባንኮች የሚፈጽሙት የብድር መያዣ ውል የክልል መስተዳደሮች በሚያስፈጽሙት ሰነድ ውስጥ ይካተታልን ተብሎ ጥያቄ የሚነሳበት ሁኔታ ያለ በመሆኑ እንደሚታወቀው ባንክ ለብድር መያዧነት የሚጠቀምበት ሰነድ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ከተበዳሪው ንብረት ጋር በተያያዘ በክልሎች ማዘጋጀ ቤት ከሚቋቋም የማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ጋር አብሮ እንዲያያዝ መደረግ ያለበት በመሆኑ ክልሎች የብድር መያዣ ውልን ለማስፈጸም የሚችሉበት የህግ አግባብ ያለ በመሆኑ ባንኮች የሚፈጽሟቸው የብድር መያዧ ውል ሰነዶችን በተመለከተ ክልሎች በማዘጋጃ ቤታቸው በኩል የሚያስፈጽሙት ተግባር በመኖሩ ፤ ክልሎች በሚያስፈጽሙት ሰነድ ላይ ደግሞ የቴምብር ቀረጡን መሰብሰብ ያለባቸው ክልሎች ስለሆኑ ባንኮች በብድር መያዣ  ሰነድ ላይ የሚሰበሰብበት 1 % የቴምብር ቀረጥ የክልሎቹ ገቢ ይሆናል ማለት ነው ፡፡ •  በቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁ.110/90 አንቀጽ 3 (12) የቴምብር ቀረጥ  ከሚከፈልባቸው መካከል የንብረት ባለቤትነት ማስመዝገቢያ ሰነድ (document of Title to properity) እንደሆነ ተደንግጓል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመጠሪያ ስያሜ ለውጥ ቢያደርግ የሦስተኛ ወገኖችን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ለውጡን ህግ በሚጠይቀው መሠረት ማስታወቂያ አወጥቶ ስሙ እንዲስተካከል ከማድረግ ውጭ ማህበሩንና ንብረቶቹን እንደገና የማስመዝገብ ውጤት እንዲኖረው በንግድ ህግ ቁጥር 114 (ለ) ፤ 224 እና 118    ( በቅደም ተከተል ሲነበቡ) ተመልክቷል፡፡ በመሠረቱ የቴምብር ቀረጥ በባህሪው በሰነድና ሰነድ ከማስፈጸም ጋር ተያይዞ የሚከፈል ታክስ ነው፡፡ በአኳያው የሥም ለውጥ ማድረግ ስሙን ከማረም ወይም ከማስተካከል ውጭ በሥም ለዋጩ ላይ የተለየ ግዴታ የሚያመጣ ፤ ለተፈጥሮም ሆነ ለህጋዊ ሰው ከተረጋገጠበት መብቶች መካከል የፈለገውን ሥም ከመጠቀም መብት የፈለገውን ሥም ከመጠቀም መብት ጋር የተያየዘ ሆኖ ይገኛል፡፡ ስለሆነም አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚጠራበትን ስያሜ በመለወጡ ብቻ የንብረት ባለቤትነትና ማስመዝገቢያ የቴምብር ቀረጥ በድጋሚ አንዲከፍል መጠየቅ አይጠበቅም፡፡
Show all...
👍 1
#NBE
Show all...
👍 1
"The Aysha Wind Power Project will be implemented with strong government-to-government support by AMEA Power, a prominent private sector player," said Ahmed Shide, Minister of Finance of Ethiopia. Abebe Gebrchiwot of the PPP Directorate added, "This project represents a major stride in our journey towards increasing clean energy production, providing sustainable electricity to our people, and driving economic growth and job creation in the region." The signing of this agreement with AMEA POWTR marks significant milestone. It demonstrates the Ministry of Finance's determination to attract private investments in the energy sector and increase the share of renewable energy in Ethiopia's power mix
Show all...
1