የግጥም ምሽት በቴሌግራም
Open in Telegram
ይህ ቻናል ከተለያዩ መጽሐፍት የተቀነጨቡ ግጥሞች የሚቀርቡበት እንዲሁም ወርሃዊ የግጥም ውድድሮች የሚካሄዱበት ነው ግጥም ለምትወዱ ሁሉ...የራሳችሁን ሙከራም የምታቀርቡበት ነው ለማንኛውም አስታየት @Nirvana134 እንዲሁም @simba23 ላይ አለን ፧ @yegetem32
Show more5 931
Subscribers
No data24 hours
-87 days
-4030 days
Posts Archive
5 931
Repost from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
የክብ.....ካብ
"""""""''''''''''''''""
እንጀራችን ክቡ፥
ዕድላችን ክቡ፥
መንገዳችን ክቡ...
በመከበብ ዕጣ፥ዕድል ተለውሶ፤
ከቶ አይደርስም ያሉት
እየተቃበዘ ይመጣል መልሶ...
በል ስራህን መርምር
አላማህን መትር እጆችህን አጥና፤
አርምጃህ ሀቅ ይሁን
ከሰው ጫንቃ ውረድ ውልህ ይሁን ቀና...
ዕቅድህን እየው...
ዕቅድህን እየው
አይምሮህን ቃኘው
በማጥ አትዳክር ህልም አለምህ ጠቦ፤
ህይወት አዙሪት ነው
የግፍ እንባ እንደ እባብ ይመጣል ተስቦ...
ተው
ተው እስቲ እረፍ
ነፍስያህን በእውነት ግረፍ
አትድንም
አትተርፍም
ከህዝብ ዕንባ ከሰው ደም ጦስ፤
ቢታጠብስ መቼ ፀዳ
ከኢየሱስ ደም ያ ጲላጦስ?
አፅዳ...
ፈትግ....
አንፃ ሀሳብህ ህሊናህን ቃኘው፤
ባሰብከው ልክ ነው
የሰማይ ቤት ዕዳህ ፍርድህ የሚዳኘው....
አስብ አለምህን
አስብ ህይወትህን
አስብ እምነትህን
አስብ...
አስብ...
አስብ...
ከመኖርህ ጉድጓድ መልካምነት ሰብስብ...!
ሸፍን ገመናህን
ህሊናህን ገንባ በፍቅር ምሰሶ፤
የክብ ነው ነፍስህ
የሰራኸው ሁሉ ይደርሳል መልሶ!
#አስብ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
@HAKiKA1
5 931
Repost from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
ሽውርር ተስፋ
"""""""""""""""""
ያለፈው ክፋት ነው
የሚመጣው እንጃ፤
ዛሬን መዳከር ነው
የሀገሬው ፍርጃ...
ትላንትም ግፍ ነበር
የህይወት ልቅምቅም፤
ከገር ፊታችን ላይ
እንባን የሚያስለቅም...
ይመሻል?..... አናውቅም
ይነጋል?.....አናውቅም፤
ተስፋችን ቢቀበር
አይገርምም አይደንቅም፤
አሁን ሰላም ካለ
ነገን አ'ናፍቅም...
.
እንግዲህ
.
ልቦናህን መርምር
እርምጃህ ቀስ በቀስ፤
ልቦናሽን እዪ
መንገድሽን ቀነስ፤
የቂም ሾተል ይዞ
"ነገን አንጋ" ብሎ
በፀሎት ጌታ ፊት የምን ማለቃቀስ?
አንቅረው ሴራህን
ሽልሽን አራግፊ ክፋት ይጨናገፍ፤
ይህንን አርጎ ነው
ለአዲስ ንጋት ጀንበር አጥብቆ መንሰፍሰፍ...
.
አልያማ
.
በሆድ ክፉ አርግዞ
የነገር ሽል ይዞ
ከነፍስና ስጋ ሳይጠፋ በቅጡ፤
ለፍቅርና ሰላም
በህልም ቅዠት አድረው
በተስፋ ዓለም ላይ ነገን ቢቋምጡ፤
የነገ ቀን ነግቶ
ማርያም ማርያም ቢባል የሰይጣን ነው ምጡ፤
ስህተት ነው ንጋቱ...!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
@HAKiKA1
5 931
Repost from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
የቆጥ ውበት
"""""""""""""""
ከውበትሽ፥
ከስብዕናሽ፥
ቅልውጥ ሄጄ ስስቀመቀም፤
ነግሰሽብኝ፥
ከልቤ ላይ፥
ማርከሻሽን ከምን ልልቀም...?
የአንጀት ደዌ
ልክፍት ነው
መወደድሽ ውስጥ ይንጣል፤
ሚቆጠቁጥ፥
የሰማይ ቆጥ፥
ሽቅብ ላይ ነው ልብሽ አይጣል፤
የሾህ ብቃይ፥
ሊሆን ስቃይ፥
በውበትሽ ጅራፍ ቀጣን፤
በአንቺ ሚዛን
ሲወዳደር
ክፉ አይደለም ከቶ ሰይጣን..!
አጃኢብ ነው
ፍቅርሽ ሲጥል
አይፎክርም... አያቅራራ፤
ማስታገሻ
ከቶ የለም
ሲፈጥርሽም እፁብ ስራ፤
ስንቱ አዳም
ለአንቺነትሽ እሱነቱን እየሰዋ፤
የብብቱን ክብር ጣለ
.....ለውበትሽ ሲንጠራራ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
@HAKiKA1
