en
Feedback
አሽከርካሪ ተሸከርካሪ መረጃ ዴስክ/Driver Vehicle Information Desk 🚓🚑

አሽከርካሪ ተሸከርካሪ መረጃ ዴስክ/Driver Vehicle Information Desk 🚓🚑

Open in Telegram
705
Subscribers
-224 hours
+97 days
+5230 days
Posts Archive
አንድ መኪና ከመግዛቶ በፊት የብድር ዕግድ እንዳለበት እና እንዳሌለበት በብሔራዊ ባንክ ዌብሳይት ማረጋገጥ እንደምትችሉ ታውቃላችሁ።

‎የትራፊክ ደንብ መተላለፍ በእስራት እንደሚያስቀጣ ሰም‎ተዋል❓❗️ ‎⚠️⚠️⚠️ ‎ተጠያቅነቱም በአዲሱ የመንገድ ትራንስፖርት የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 መሠረት በአሽከርካሪውና በባለንብረት ላይ የተጣሉ ግዴታዎችን አለመፈጸምና በ1996ቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ መሰረት ነዉ። ‎ ‎ይህም የትራፍክ ደንብ መተላለፍ ጥፋቶች ከ3 ወር እስከ 15 ዓመት ድረስ በቀላልና በፅኑ እስራት እንዲሁም እስከ 15ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ ሊያስቀጣ ይችላል። ‎ ‎🔴 የትራፊክ ደንብ መተላለፍ በእስራትና በገንዘብ ቅጣት ብቻ ሳይሆን የቅጣት ነጥብ ሪከርድ እንዲመዘገብበትና ከአሽከርካሪነት እግድ ልያስከትል ይችላል። ‎ ‎✅ #በትራፊክ_ደንብ_መተላለፍ ምክንያት የትራፊክ ክስ ቻርጅ አልፈርምም ወይም አልቀበልም ማለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 438 መሰረት ‎ ‎በሥልጣን ላይ ያለን የመንግሥት ሠራተኛ ሥራ ማደናቀፍ ወይም ትዕዛዝ አለማክበር ፣ የመተባበር ግደታ መጣስ በመባል እስከ 5 ዓመት ቀላል እስራት ያስከትላል። ‎ ‎✅ #የትራፊክ_ደንብ_ተላልፎ አምባጓሮ መፍጠር ፦ ድርጊቱ የትራፊክ ደንብ መጣስንና መንገድ ላይ ጠብ (አምባጓሮ) ማንሳትን በአንድነት ያካተተ ከሆነ፣ ግለሰቡ ‎ ‎በአንቀጽ 572 እና በ 577 መሰረት ከ3ወር እስከ 3 ዓመት እስራትና በትራፊክ ደንብም በተደራራቢነት ሊቀጣ ይችላል ። ‎ ‎በአምባጓሮዉ ከባድ ጉዳት ወይም ሞት ያስከተለ እንደሆኔ ቅጣቱ በሌሎች ድንጋጌዎች መሰረት ይጨምር ይችላል። ‎ ‎✅ #ሕጋዊ_ሥልጣን_ላለው የመንግሥት ሠራተኛ (የትራፊክ ፖሊስ) የመንጃ ፈቃድ ፣ የተሽከርካሪ መታወቂያ (ሊብሬ) ወይም ሌላ የሚፈለጉ መረጃዎችን አልሰጥም ወይም አላሳይም በማለት ሥራውን እንዳይሠራ ‎ ‎በኃይል በማስገደድ ለመጠቀም በመዛት ከሞከረ ጉዳዩ ወደ ከባድ ወንጀል ተቀይሮ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 441 መሠረት ከ3 ዓመት እስከ 5 ዓመት ጽኑ እስራት ልያስቀጣ ይችላል። ‎ ‎✅ #የትራፊክ_ደንብ_ባለማክበር በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረስ (በቸልተኝነት ሰውን መግደል) በሰዉ አካል ወይም በጤና ላይ ‎ ‎ ጉዳት ማድረስ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 543 አንቀጽ 559 መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 15 ዓመት እስራትና በብር እስከ 15 ሺ ብር መቀጮ ልያስቀጣ ይችላል። ‎ ‎#ማጠቃለያ፦ አሽከርካሪዎች! ለሕግ ብቻ ሳይሆን ለህሊና መታዘዝ ያስፈልጋል ፣ ከአስከፊዉ አደጋና ወንጀል ራስህንና ሌላዉን ተከላክሎ ማሽከርከር ያስፈልጋል፣ ‎ ‎የትራፊክ ደንብን በማክበር በምንም ግዜ በጥንቃቄና በእርጋታ ያሽከርክሩ። የትራፊክ አደጋ አካል ያጎድላል!፣ሕይወት ይቀጥፋል! ፣ንብረት ያወድማል::

እባኮትን በኃላፊነት ያሽከርክሩ❗️ ገፃችንን Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ኃሳብ አስተያየት ይስጡን 📡📡📡📡📡 ለበለጠ መረጃ ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ Telegram 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/vehicleinformation Facebook 👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/AADVInfoCenter Tiktok 👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@aadvlca

#የመኪና_ቁልፍ_አሰራር የተሽከርካሪ Ignition Switch (የመኪና ቁልፍ) ብዙውን ጊዜ LOCK → ACC → ON → START የሚሉ ደረጃዎች አሉት። እያንዳንዱ ደረጃ የተለየ የኤሌክትሪክ ስርዓት ያነቃል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 1. 🔒 LOCK — መቆለፊያ ጥቅሙ: መኪናውን ከማቆም በኋላ ለመቆለፍ እና ቁልፉን ለማውጣት የሚያስችል ደረጃ ነው። 🔹አሰራሩ: 🔹ሞተሩ ይጠፋል። 🔹አብዛኛዎቹ የመኪና ኤሌክትሪክ ሲስተሞች ይቋረጣሉ። 🔹ቁልፉ ሊወጣ ይችላል። 🔹በብዙ መኪናዎች Steering Wheel ሊቆለፍ ይችላል። ማስታወሻ: መኪናው በመንቀሳቀስ ላይ እያለ LOCK ላይ ማድረግ አደገኛ ነው። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 2. 🔌 ACC — Accessory ACC ማለት Accessory ማለት ነው። ጥቅሙ: ሞተሩን ሳያስነሳ አንዳንድ የመኪና ኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን ለማስኬድ ይጠቅማል። በACC ላይ ሊሰሩ የሚችሉት: 🎵 Radio / Audio 📱 የስልክ ቻርጀር 💡 አንዳንድ የውስጥ መብራቶች 🖥️ አንዳንድ Display/Infotainment systems ነገር ግን: ሞተሩ አይሰራም። ስለዚህ ለረጅም ጊዜ ACC ላይ መተው ባትሪውን ሊያሳንስ ይችላል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 3. ⚡ ON — Ignition ON ጥቅሙ: የመኪናውን ዋና የኤሌክትሪክ ሲስተም ለማንቃት ይጠቅማል። አሰራሩ: 🔹Dashboard ይነሳል። 🔹ECU/ECM ይነሳል። 🔹Fuel system እና ሌሎች የመኪና ሲስተሞች ይነቃሉ። 🔹የWarning Lights መብራቶች ይታያሉ። 🔹መኪናው ለመነሳት ዝግጁ ይሆናል። አስፈላጊ: ON ላይ መሆን ማለት ሞተሩ ተነስቷል ማለት አይደለም። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 4. 🚗 START — ሞተር ማስነሻ ጥቅሙ: ሞተሩን ለማስነሳት የሚጠቅም የመጨረሻ ደረጃ ነው። አሰራሩ: 1.ቁልፉን START አቅጣጫ ሲያዞሩ፣ Starter Motor ኃይል ያገኛል። 2.Starter Motor የሞተርን Crankshaft ያሽከረክራል። 3.ECU የFuel Injection እና Ignition/Combustion ሂደትን ያስተባብራል። 4.ሞተሩ ሲነሳ፣ ቁልፉን መልቀቅ አለብዎት። 5.ቁልፉ በራሱ START → ON ይመለሳል። ⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰ 🔄 በአጭር LOCK → ACC → ON → START → ON LOCK: መኪናው ተዘግቷል ⬇️ ACC: አንዳንድ Accessories ይሰራሉ ⬇️ ON: ዋና የመኪና ኤሌክትሪክ ሲስተሞች ይነሳሉ ⬇️ START: Starter Motor ሞተሩን ያስነሳል ⬇️ ON: ሞተሩ ከተነሳ በኋላ ቁልፉ ወደ ON ይመለሳል። ማስታወሻ: በአዳዲስ መኪኖች የቁልፍ ስርዓቱ በPush Start Button ሊተካ ይችላል፤ ነገር ግን ACC, ON, START የሚሉት የስርዓት ተግባራት በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው። ገፃችንን Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ኃሳብ አስተያየት ይስጡን 📡📡📡📡📡 ለበለጠ መረጃ ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ Telegram 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/vehicleinformation Facebook 👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/AADVInfoCenter Tiktok 👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@aadvlca

#ጥንቃቄ_ያድርጉ❗️ ከቆሙ ተሽከርካሪዎች ላይ የሰሌዳ ስርቆት ሲፈፅም የነበረ ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ ተያዘ፡፡ ***** አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ/ም (#አዲስ_ፖሊስ)፦ተጠርጣሪ አየነው ፈጠነ የሰሌዳ ስርቆት ድርጊቱን የፈፀመው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አትሌቶች መንደር አካባቢ ነው። በክፍለ ከተማው በተለያዩ ቦታዎች ግለሰቦች ተሽከርካሪዎቻቸውን አቁመው በሚሄዱበት ወቅት እንቅስቃሴዎቻቸውን በመከታተል ሰሌዳዎችን በመፍታት የሳፋሪ ኮም ስልክ ቁጥሩን በወረቀት ፅፎ በመለጠፍ ከአካባቢው በቅርብ ርቀት በመሆን ሲደወልለት ገንዘብ መክፈል እንዳለባቸው ካልከፈሉ ወንጀል እንደሚፈፅምበት እያስፈራራ ከ5ሺህ ብር እስከ 7ሺህ ብር እየተቀበለ እንደሆነ የግል ተበዳዮች በጎሮ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ባመለከቱት መሰረት በምርመራ ክፍሉ ክትትል መጀመሩ ተገልጿል። በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የጎሮ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በግልፅ እና በስውር ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪው ግለሰብ እንደለመደው የሰዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል መንገድ ዳር እና የመኖሪያ ቤት በር አካባቢ የቆሙ ተሽከርካሪዎችን ሰሌዳ በመፍታት  ላይ ሳለ እጅ ከፍንጅ ሊያዝም ችሏል፡፡ ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ባደረገው የምርመራ  ማስፋት ተግባር እና  በመኖሪያ ቤቱ ባደረገው ፍተሻ ተጨማሪ ሰሌዳዎችን በማግኘቱ የምርመራ መዝገቡን በማደራጀት ክስ ተመስርቶበት በማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል። ህብረተሰቡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሰሌዳ እየፈቱ ስልክ እያስቀመጡ የወንጀል ተግባር እየፈፀሙ ያሉ ግለሰቦች በመኖራቸው ጥንቃቄ በማድረግ የፓርኪንግ ጥበቃ ባለበት በማቆም እንዲሁም ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲገኝ ለአቅራቢያቸው ፖሊስ መምሪያ ጥቆማ በመስጠት የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ሊተባበሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በመልዕክቱ አሳስቧል። መረጃው #Addisababapolice ገፃችንን Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ኃሳብ አስተያየት ይስጡን 📡📡📡📡📡 ለበለጠ መረጃ ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ Telegram 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/vehicleinformation Facebook 👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/AADVInfoCenter Tiktok 👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@aadvlca

#ከፍጥነት_በላይ_መንዳት_የሚያስከትላቸው_አደጋዎች❗️ አንድ አሽከርካሪ በተፈቀደው ፍጥነት መንዳት የራሱን፣ የተሳፋሪዎችን እና የሌሎችን መንገድ ተጠቃሚዎች ሕይወት ይጠብቃል። ከፍጥነት በላይ መጓዝ የሚያስከትላቸው አደጋዎች፦ 1.የትራፊክ አደጋ ዕድል ይጨምራል። 2.የብሬክ ርቀት ይረዝማል፤ በአፋጣኝ ማቆም ይከብዳል። 3.የተሽከርካሪ መቆጣጠር ይቀንሳል፤ በመታጠፊያና በእርጥብ መንገድ መኪናው ሊያንሸራትት ይችላል። 4.የሞት እና ከባድ ጉዳት አደጋ ይጨምራል። 5.እግረኞችንና ብስክሌተኞችን የመግጨት እድል ይጨምራል። 6.የንብረት ጉዳት ያስከትላል፤ መኪና፣መንገድ እና ሌሎች ንብረቶች ሊጎዱ ይችላሉ። 7.የነዳጅ ፍጆታ ይጨምራል። 8.የጎማና የብሬክ መበላሸት ይፋጠናል። 9.የሕግ ቅጣት ሊያስከትል ይችላል፤ ቅጣት፣ ፈቃድ እገዳ ወይም ሌሎች እርምጃዎች። 10.በድንገተኛ ሁኔታ ውሳኔ ለመስጠት የሚያገኙት ጊዜ ይቀንሳል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 በማሽከርከር ወቅት መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች 1.የተፈቀደውን የፍጥነት ገደብ ያክብሩ። 2.የደህንነት ቀበቶ (Seat Belt) ሁልጊዜ ያድርጉ። 3.ስልክ አይጠቀሙ፤ መልዕክት አይጻፉ። ከፊት ከሚሄደው ተሽከርካሪ በቂ ርቀት ይጠብቁ። 4.የትራፊክ ምልክቶችንና መብራቶችን ያክብሩ። 5.አልኮል ወይም አደንዛዥ ዕፅ በተጠቀሙበት ሁኔታ አያሽከርክሩ። 6.ድካም ወይም እንቅልፍ ሲሰማዎት አያሽከርክሩ። 7.የመኪናውን ብሬክ፣ ጎማ፣ መብራትና ውሃ/ኩላንት በየጊዜው ይመርምሩ። 8.በዝናብ፣ ጭጋግ ወይም በሌሊት ፍጥነትን ይቀንሱ። 9.የአቅጣጫ ምልክት (Indicator) በትክክል ይጠቀሙ። 10.መስተዋቶችን በተደጋጋሚ ይመልከቱ። እግረኞችን፣ ብስክሌተኞችንና 11.ሞተርሳይክሎችን በተለይ ይጠንቀቁ። 12.ሁልጊዜ ትኩረትዎን መንገዱ ላይ ያድርጉ። የዛሬው መልዕክታችን❗️ "ፍጥነት ጊዜን ሊቆጥብ ይችላል፤ ነገር ግን ሕይወትን ሊያጠፋ ይችላል። በጥንቃቄ ያሽከርክሩ፤ ሕይወትዎንና የሌሎችን ሕይወት ይጠብቁ።" ገፃችንን Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ኃሳብ አስተያየት ይስጡን 📡📡📡📡📡 ለበለጠ መረጃ ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ Telegram 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/vehicleinformation Facebook 👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/AADVInfoCenter Tiktok 👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@aadvlca

#ይህን_ያውቁ_ኖሯል? ኩላንት ምንድነው? ጥቅሙስ? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ኩላንትምንድነው(Coolant) በመኪና ማቀዝቀዣ ስርዓት ውስጥ የሚጠቀም ልዩ ፈሳሽ ነው። ከሞተሩ ሙቀትን ይወስዳል፣ ወደ ራዲያተሩ ያደርሰዋል እና እዚያ ሙቀቱን ያስወጣል። እንዲሁም ሞተሩን ከመቀዝቀዝ፣ ከመሞቅ እና ከዝገት ይጠብቃል። What is Coolant? Coolant is a special liquid used in a vehicle's cooling system. It absorbs heat from the engine and carries it to the radiator, where the heat is released. It also prevents the engine from freezing, overheating, and rusting. 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 Types of Coolant IAT (Green): For older vehicles; needs replacement every 2–3 years. OAT (Orange/Red): For modern vehicles; lasts 5 years or more. HOAT (Yellow/Blue/Pink): Hybrid coolant; offers long life and better corrosion protection. IAT (አረንጓዴ): ለአሮጌ መኪናዎች፤ በ2–3 ዓመት ይቀየራል። OAT (ብርቱካናማ/ቀይ): ለዘመናዊ መኪናዎች፤ 5 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ይቆያል። HOAT (ቢጫ/ሰማያዊ/ሮዝ): የተቀላቀለ ኩላንት፤ ረጅም ጊዜ የሚቆይ እና ከዝገት ጥሩ ጥበቃ ይሰጣል። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 Benefits of Each Coolant Color ✅Green Good for older engines and copper/brass radiators. ለአሮጌ ሞተሮችና ራዲያተሮች ተስማሚ ነው። ✅Orange Long-life coolant with excellent rust protection. ረጅም ጊዜ የሚቆይ እና ከዝገት ጥሩ ጥበቃ ይሰጣል። ✅Red High-temperature protection for modern engines. ለዘመናዊ ሞተሮች ከፍተኛ የሙቀት ጥበቃ ይሰጣል። ✅Blue Excellent corrosion protection and long service life. ከዝገት በጣም ጥሩ ጥበቃ እና ረጅም የአገልግሎት ዘመን አለው። ✅Pink Long-lasting, commonly used in Japanese vehicles. ረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ በጃፓን መኪናዎች ብዙ ጊዜ ይጠቀማል። ✅Yellow Hybrid coolant suitable for many modern vehicles. ለብዙ ዘመናዊ መኪናዎች የሚስማማ ድብልቅ ኩላንት ነው። Note / ማስታወሻ: የኩላንት ቀለም ብቻ ዓይነቱን አይወስንም፤ አምራቾች የተለያዩ ቀለሞችን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ሁልጊዜ የመኪናውን መመሪያ ይመልከቱ። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 How Coolant Works The water pump circulates coolant through the engine. The coolant absorbs heat from the engine. Hot coolant flows to the radiator. Air passing through the radiator cools the coolant. The cooled coolant returns to the engine, and the cycle repeats. የውሃ ፓምፕ ኩላንቱን በሞተሩ ውስጥ ያዘዋውራል። ኩላንቱ የሞተሩን ሙቀት ይወስዳል። የሞቀው ኩላንት ወደ ራዲያተሩ ይሄዳል። በራዲያተሩ የሚያልፈው አየር ኩላንቱን ያቀዘቅዛል። የቀዘቀዘው ኩላንት ወደ ሞተሩ ይመለሳል እና ዑደቱ ይቀጥላል። 🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺 Coolant vs Water (Comparison) Coolant A special liquid made for engine cooling. ለሞተር ማቀዝቀዣ በተለይ የተሰራ ፈሳሽ ነው:: ውሃ Ordinary water used for cooling in emergencies. ተራ ውሃ ሲሆን በአስቸኳይ ጊዜ ብቻ ሊጠቀም ይችላል። Which is Better? የቱ የተሻለ ነው? Coolant is much better than water because it cools the engine, prevents rust, protects against freezing and overheating, and lubricates the cooling system. Water should only be used temporarily in an emergency. ኩላንት ከውሃ በጣም የተሻለ ነው። ሞተሩን ያቀዘቅዛል፣ ከዝገት ይጠብቃል፣ ከመቀዝቀዝና ከመሞቅ ይከላከላል፣ እንዲሁም የውሃ ፓምፕን ይቀባል። ውሃ ደግሞ በአስቸኳይ ጊዜ ብቻ ለጊዜው መጠቀም ይመከራል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ስለዚህ ለተሽከርካሪዎ አምራቹ ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት ኩላንት በአግባቡ ይጠቀሙ። ገፃችንን Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ኃሳብ አስተያየት ይስጡን 📡📡📡📡📡 ለበለጠ መረጃ ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ Telegram 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/vehicleinformation Facebook 👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/AADVInfoCenter Tiktok 👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@aadvlca

#የሲዳማ_ክልል እና የሐዋሳ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች #በውቢቷ_ቦሌ_አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሄዱ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 የሲዳማ ክልል እና የሐዋሳ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ በአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ውቢቷ ቦሌ የተሞክሮ ማዕከል በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል። የጉብኝቱ ዓላማ በተቋሙ የተተገበሩ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቶችን በመመልከት ልምድ መቅሰምና በክልሉ ለመተግበር የሚያስችሉ ልምዶችን ማግኘት ነበር። በልምድ ልውውጡ ወቅት ተሳታፊዎቹ በተቋሙ የተተገበሩ የአገልግሎት ማሻሻያ ሥርዓቶችን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እና የሥራ አፈፃፀም ልምዶችን በተግባር በመመልከት ልምድ ቀስመዋል። 🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺 1. ፈጣንና ቀልጣፋ የተገልጋይ አገልግሎት አሰጣጥ በተቋሙ የተዘረጋው ፈጣን የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት እና ዘመናዊ የወረፋ አስተዳደር (Queue Management System) በመጠቀም ተገልጋዮች ረጅም ጊዜ ሳይጠብቁ በአጭር ጊዜ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል። ይህ አሰራር የጊዜ ብክነትን በመቀነስ፣ የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ እና የተቋሙን የአገልግሎት ቅልጥፍና በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 2. የተሽከርካሪና የአሽከርካሪ ፋይሎችን በዘመናዊ E-File System ማስተዳደር በተቋሙ የሚገኙ ከ120 ሺህ በላይ የተሽከርካሪ ፋይሎች እና ከ90 ሺህ በላይ የአሽከርካሪ ፋይሎች በዘመናዊ ዲጂታል E-File System እየተተዳደሩ መሆናቸው ተመልክቷል። ይህ ሥርዓት መረጃን በፍጥነት ለማግኘት፣ የመረጃ ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ የወረቀት አጠቃቀምን ለመቀነስ እና የመረጃ ግልጽነትና ተደራሽነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 3. ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎት መስጠት በተቋሙ ውስጥ የተዘረጉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች አገልግሎቱን ፈጣን፣ ትክክለኛ እና ግልጽ እንዲሆን አስችለዋል። ከእነዚህ ቴክኖሎጂዎች መካከል፦ Integrated Vehicle Management System Industrial Endoscope Declaration Verification System (C-Number) TIN Registration System Document Authentication System እና ሌሎች ተመሳሳይ ዲጂታል ሲስተሞች በሥራ ላይ ውለዋል። እነዚህ ሲስተሞች የሰው ስህተትን በመቀነስ፣ የሥራ ቅልጥፍናን በማሳደግ፣ የመረጃ ትክክለኛነትን በማረጋገጥ እና የተገልጋዮችን እምነት በማጠናከር ጉልህ ሚና መጫወታቸው ተገልጿል። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 4. ወቅታዊ የተሽከርካሪ ግምት አሰራር ተሳታፊዎቹ በተቋሙ የሚተገበረውን ወቅታዊ የተሽከርካሪ ግምት አሰራር በተግባር ተመልክተዋል። ይህ ሥርዓት ተሽከርካሪዎች በትክክለኛ፣ ፍትሃዊ እና ግልጽ መንገድ እንዲገመቱ የሚያስችል ሲሆን፣ በመንግስትና በተገልጋዮች መካከል ያለውን መተማመን በማጠናከር እና የአገልግሎት ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል። በመርሃ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች እና የውቢቷ ቦሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ_ታዬ_ዲባባ ተገኝተው፣ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለው ትብብር በስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ድጋፍ እና በቀጣይ የልምድ ልውውጦች እንዲጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። በመጨረሻም የሲዳማ ክልል እና የሐዋሳ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ውቢቷ ቦሌ የተሞክሮ ማዕከል ለክልሎች የተሳካ የልምድ ማስፋፊያ ማዕከል መሆኑን በማረጋገጥ፣ እንዲህ ዓይነቱ የልምድ ልውውጥ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው የመንግስት አገልግሎት ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል። #ውቢቷ_ቦሌ_አሽከርካሪና_ተሽከርካሪ_ባለስልጣን

የተሽከርካሪ አግልግሎት ለውጥ ለማድረግ ፡-
የተሽከርካሪ አግልግሎት ለውጥ ለማድረግ ፡-

#የተመዘገቡ_ውጤቶች_ተጠናክረው_ይቀጥላሉ:: ውጤት ያስመዘገብንባቸውን መንገዶች አጠናክረን እንቀጥላለን :- #አቶ_ዘገዬ_በላይነህ #ዋና_ሥራ_አስኪያጅ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የ90 ቀን እና የ2019
+9
#የተመዘገቡ_ውጤቶች_ተጠናክረው_ይቀጥላሉ:: ውጤት ያስመዘገብንባቸውን መንገዶች አጠናክረን እንቀጥላለን :- #አቶ_ዘገዬ_በላይነህ #ዋና_ሥራ_አስኪያጅ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የ90 ቀን እና የ2019 በጀት ዓመት የሐምሌ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ከጠቅላላ ካውንስል አባላት ጋር ገመገመ። በግምገማ መድረኩ በዚህ ወር እና በ90 ቀን ዕቅድ ለመፈጸም የታቀዱ ተግባራት አብዛኞቹ ከዕቅድ በላይ የተከናወኑ መሆኑ ተገልጿል። አገልግሎቱን የሚያቀሉ፣ ለተገልጋዩ እርካታ መሻሻል ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ዕቅዶች አጠናቆ መፈጸም፣ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ መደገፍ፣ ምቹ የሥራ አካባቢን መፍጠር፣ የአረንጓዴ አሻራ እና የሰው ተኮር ሥራዎች አፈጻጸም በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በሪፖርት ቀርቧል። በሪፖርቱ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል። "እስካሁን በነበሩ ሥራዎቻችን ውጤት ያስመዘገብንባቸውን አሰራሮችና መንገዶች አጠናክረን በመቀጠል ለተገልጋዩ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ማላቅ ይገባል" ሲሉ የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ #አቶ_ዘገዬ_በላይነህ የመድረኩን ማጠቃለያና የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል። ገፃችንን Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ኃሳብ አስተያየት ይስጡን 📡📡📡📡📡 ለበለጠ መረጃ ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ Telegram 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/vehicleinformation Facebook 👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/AADVInfoCenter Tiktok 👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@aadvlca

#ይህን_ያውቁ_ኖሯል❗️ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 🔹#ዲፈረንሻል (Differential) 🔹 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 1. ዲፈረንሻል ምንድን ነው? ዲፈረንሻል በተሽከርካሪ የኃይል ማስተላለፊያ (Drivetrain) ሥርዓት ውስጥ የሚገኝ ዋና ክፍል ሲሆን፣ ከጊርቦክስ የሚመጣውን ኃይል ወደ ጎማዎች ያስተላልፋል። ተሽከርካሪው ሲታጠፍ የግራና የቀኝ ጎማዎች በተለያየ ፍጥነት እንዲዞሩ ያደርጋል። ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 2. የዲፈረንሻል ተግባር (Functions) 🔹ኃይልን ከጊርቦክስ ወደ ጎማዎች ማስተላለፍ። 🔹ተሽከርካሪው ሲታጠፍ ጎማዎች በተለያየ ፍጥነት እንዲሽከረከሩ ማድረግ። 🔹የሞተር ጉልበት (Torque) በሁለቱም ጎማዎች ላይ ማከፋፈል። 🔹የጎማ መጎተትን መቀነስ። 🔹የተሽከርካሪውን መረጋጋትና መቆጣጠር ማሻሻል። ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 3. የዲፈረንሻል ጥቅሞች (Uses/Advantages) 🔺ለስላሳ መታጠፍን ያስችላል። 🔺የጎማ ዕድሜን ያራዝማል። 🔺የኃይል ማስተላለፍን ያሻሽላል። 🔺በአስቸጋሪ መንገድ ላይ የመንዳት ብቃትን ያሳድጋል። 🔺የተሽከርካሪውን ደህንነት ያጠናክራል። ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 4. የዲፈረንሻል አይነቶች (Types) 1️⃣ክፍት ዲፈረንሻል (Open Differential) – በአብዛኛዎቹ መኪናዎች የሚገኝ። 2️⃣የተገደበ መንሸራተት ዲፈረንሻል (Limited Slip Differential - LSD) – መንሸራተትን ይቀንሳል። 3️⃣የሚቆለፍ ዲፈረንሻል (Locking Differential) – በጭቃና በከባድ መንገድ ላይ ይጠቅማል። 4️⃣ቶርሰን ዲፈረንሻል (Torsen Differential) – ኃይልን በራሱ ያከፋፍላል። 5️⃣ኤሌክትሮኒክ ዲፈረንሻል (Electronic Differential) – በኤሌክትሮኒክ መቆጣጠሪያ የሚሰራ። ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 5. የዲፈረንሻል ዋና ክፍሎች 🔺ዲፈረንሻል ኬዝ (Housing) 🔺ሪንግ ጊር (Ring Gear) 🔺ፒኒዮን ጊር (Pinion Gear) 🔺ሳይድ ጊር (Side Gear) 🔺ስፓይደር ጊር (Spider Gear) 🔺ቤሪንግ (Bearing) 🔺የዘይት ማህተም (Oil Seal) ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 6. የዲፈረንሻል ችግሮች (Problems) 1️⃣የዘይት መፍሰስ። 2️⃣ያልተለመደ ድምጽ (ጩኸት ወይም ግጭት)። 3️⃣የጊር መልበስ። 4️⃣የቤሪንግ መበላሸት። 5️⃣የዘይት እጥረት። 6️⃣መንቀጥቀጥ ወይም ንዝረት። ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 7. የዲፈረንሻል ጥገና (Maintenance) 1️⃣የዲፈረንሻል ዘይትን በተወሰነ ጊዜ መቀየር። 2️⃣የዘይት መጠን እና ጥራት መመርመር። 3️⃣የዘይት መፍሰስ መፈተሽ። 4️⃣የቤሪንግና የጊር ሁኔታ መመርመር። 5️⃣ያልተለመደ ድምጽ ከተሰማ በፍጥነት ማስተካከል። የሚመከረውን የዲፈረንሻል ዘይት መጠቀም። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 8. የዲፈረንሻል ጥሩ አጠቃቀም 🔺ከባድ ጭነት ከአቅሙ በላይ አለመጫን። 🔺በከፍተኛ ፍጥነት አስቸጋሪ መታጠፍን መቀነስ። 🔺በየጊዜው ቴክኒካል ምርመራ ማድረግ። 🔺የሚመከረውን የሰርቪስ ጊዜ መከተል። ⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰ ዲፈረንሻል የተሽከርካሪ ኃይል ማስተላለፊያ ሥርዓት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ክፍል ነው። ጎማዎች በተለያየ ፍጥነት እንዲዞሩ በማድረግ መኪናው በደህና እና በቀላሉ እንዲንቀሳቀስ ይረዳል። መደበኛ ጥገና በማድረግ የዲፈረንሻሉን ዕድሜ ማራዘምና የጥገና ወጪን መቀነስ ይቻላል። መልካም ጊዜ ገፃችንን Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ኃሳብ አስተያየት ይስጡን 📡📡📡📡📡 ለበለጠ መረጃ ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ Telegram 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/vehicleinformation Facebook 👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/AADVInfoCenter Tiktok 👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@aadvlca

#_እንዲታወቅ፡-- የደንብ 557/2016 ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ አስኪጸድቅ የትራፊክ ጉዳት ካደረሱ አሽከርካሪዎች ውጪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ማገድ ለጊዘው እንዲቆም ተደረገ (ት/ማ/ባ ነሀሴ/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራፊክ ማጅመንት ባለሰልጣን የደንብ ተላላፊዎችን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መቀበልም ሆነ ሰሌዳ መፍታት ሳያስፈልግ የዲጂታል የትራፊክ ቁጥጥር እና ቅጣት ማስፈጸሚያ ሲስተም ስርዓት በመዘርጋት የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጣር የወጣውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016 የቅጣት አወሳሰንን እየተገበረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከደንቡ ተግባር ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በደንብ መተላላፍ የነጥብ ጣሪያ ደርሰው የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫቸው ታግዶ የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስዱና እና ነጥባቸው ሳይሞላም አስቀድሞ ስልጠና ወስደው ነጥብ የሚቀንስላቸው ደንብ ተላላፊዎች በደንቡ አንቀፅ 96 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 ላይ በሁለቱም የእውቅና ክህሎት ስልጠና ወስደው የወሰዱበትን ማረጋጋጫ ሲያቀርቡ እግዱ እንደሚነሳ ይደነግጋል፡፤ ይሁን እንጂ ከአፈጻጸም አንጻር ይኸው አገራዊ ደንብ /በሌሎች ክልሎች ተግባራዊ ባለመደረጉ እና በአዲስ አበባ ከተማ በሚያሽከረክሩ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ብቻ መተግበሩ በደንብ ተላላፊዎች ዘንድ የፍትሀዊነት ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል፡፡ ባለሰልጣን መ/ቤቱም ይህንኑ የፍትሀዊነት ጥያቄ ለመንገድ ደህንነት ፈንድ አገልግሎት ባሳወቀው መሰረት አና ተቋሙም ችግሩን በመረዳት በቀን 23/11/2018 በቁጥር 1904/18 በተጻፈ ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቶበታል፡፡ በምላሹም ከደንብ ትግበራ ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ደንብ ተላላፊዎች የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዳቸው ታግዶ የተሀድሶ ስልጠና የሚያገኙበትን ሂደት የተሳካ ለማድረግ መመሪያ ሲዘጋጅ መቆየቱን አመላክቷል፡፡ እንዲሁም መመሪያውም ያለበትን ሂደቶች አልፎ በአሁኑ ወቅት ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩንና በሌሎች ክልሎችም ወጥ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት ሲባል ለጊዜው የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃዱን የማገዱ ተግባር አንዲዘገይ በማለት አሳውቋል ፡፡ በመሆኑም የደንብ መተላለፉ የገንዘብ ቅጣቶቹ እንደተጠበቁ ሆነው ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው ጸድቆ እስኪላክ ድረስ የትራፊክ ጉዳት ካደረሱ አሽከርካሪዎች ውጪ ለጊዜው በነጥብ እና በቆይታ /ሳይከፍል 6 ወር የቆየ/ ከዚህ በፊት የታገዱትም ሆነ በቀጣይ የሚታገድ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ መቆሙን እንገልጻለን፡፡ ክእግዱ መቆም በስተቀር ደንብ ተላላፊዎች ያሉባቸውን የቅጣት ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን