cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከመፅሀፍት ዓለም 📖 📚books world 📖📚

የተለያዩ ሀገር በቀልና የባህር ማዶ መፅሀፎች የሚገኙበት ገፅ ሲሆን ገፁን ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፉት 📚📚

Show more
Advertising posts
1 766
Subscribers
+1124 hours
+447 days
+17030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የፍቅረኞቻችሁን ስም ክንዳችሁ ላይ መነቀስኮ በራሱ ችግር አይደለም! ከመነቀሳችሁ በፊት ግን ይችን አዳምጡኝ! ብዙ ሰው ከተነቀሳችሁ በኋላ ብትለያዩ ምናምን ይላል ... እኔ እሱ አያሳስበኝም! ችግሩ ስታረጁ ታቱው አንዳንድ የትርጉም ለውጥ ሊያመጣ ይችላል! ለምሳሌ አባባ ሳህሌ ወጣት በነበሩበት ዘመን ውጥርጥር ያለ ጡንቻቸው ላይ የራሳቸውንና የባለቤታቸውን ስም ተነቀሱ! "ሳህሌ ፣ ያርበድብዱ " እንደውም የተረፈው ቦታ ላይ ጦርና ጋሻ ጨመሩበት! እያረጁ ጡንቻቸው ሲሟሽሽ ግን ከሚስታቸው ስም የተወሰኑ ፊደላት በቆዳቸው ሽብሽባት ውስጥ እየገቡ ተደበቁ ! እና የቀሩት ፊደሎች ሲነበቡ ትንሽ የባለጌ አይነት ሆኑ (ያው ትገምታላችሁ) ...🤔 የባሰው ነገር ደግሞ የተነቀሱት ጋሻ ቆዳቸውን ተከትሎ ወደታች ታጠፈና የተንጠለጠሉ ሁለት ፍሬዎች መሠለ ! በዛ ላይ ከላይ ጦሩ አለ..."ኧረ ወዲያ ሸፈን ያርጉት አንቱ ሰው አማረብኝ ብለው ነው? ሆሆ በስተርጅና " ይላሉ ሚስቲቱ ባዮት ቁጥር እፍረት ባንዣበበት ፊት! "ምን ሆነ "ብለው ቆዳቸውን ሳብ አድርገው ሲያዪት የተደበቁት ፊደላት ይወጡና ይስተካከላል ፤ ሲለቁት ይባልጋል! እንዲቹ ሲጨቃጨቁ ይውላሉ😂! አሌክስ አብርሃም
Show all...
😁 7
ውድ የዚህ ገፅ ተከታዮች እንደምን ሰነበታችሁ!? በእናንተ ጥያቄ መሰረት ፍቅር እስከመቃብርን በትረካ እያቀረብንላችሁ ነው። ሌላ በትረካ እንዲቀርብ የምትፈልጉት መፅሀፍ ካለ መጠዬቅ ትችላላችሁ!
Show all...
👍 2
ይህ ሰው በወጣትነቱ ነው ጫካ የገባው ምናልባትም ጫካ ገብቶ በትግሉ ውጤት የሀገር መሪ መሆን የቻለ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስተርም ነው፡፡ መለስ ከታጋይነቱ ጎን ለጎን አሰላሳይ፣ አንባቢና ጨዋታ አዋቂ ነው፡፡ የአዳም ስሚዝ፣ ሙራይ ሮዝባርድና የሚኬል ማሽለር ስራዎችን እድሜው ሐያዎቹ መጀመሪያ ላይ እያለ ነው ያነበባቸው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአለም ኢኮኖሚክ ፎረም እውቀቱ የተገለጠባቸው መድረኮች ናቸው፡፡ የአክሱም ሐውልት መመለስና የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ በአዲስ አበባ መቅረቱ የዲፕሎማሲ እውቀቱ ውጤት ናቸው፡፡ የህዳሴ ግድብ ደግሞ ስሙን ከመቃብር በላይ ያስቀረው ፕሮጀክቱ ነው፡፡ መለስ ጨዋታ አዋቂም ነበር፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው "የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው ይህ ደግሞ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አደጋ ነው" ሲሉ ላቀረቡት ጥያቄ የመለስ ዜናዊ መልስ እንዲህ የሚል ነበር "የሀገሪቱ የድህነት ምንጭ ህዝቡ 75 ወይም 80 ሚሊየን መድረሱ ነው ብዬ አልወስድም ምክንያቱም ሰው ሲወለድ ሆድ ብቻ አይደለም ይዞ የሚወለደው እጅና እግርም ይወለዳል፤ እጅ ይሰራል እግር ይሰራል ከዛ ሆድ ይበላል ስለዚህ ዋናው ጉዳይ ሆዱ ብቻ የሚሰራን ግለሰብ እጅና እግሩ እንዲሰራ ማድረጉ ነው" ከአንድ የፓርላማ አባል ቅርሶችን ስለመጠበቅ ቀርቦላቸው ለነበረው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ "ቤተመንግስት የምንገለገልባቸው በሐይለስላሴ ዘመን የተገዙ መርሴዲስ መኪኖች ነበሩ፤ ቅርስ ስለሆኑ ለሀገራችን መልካም ስም ያመጣሉ ብለን ስንጠቀምባቸው ቆየን በኋላ ግን ከቦሌ የሚመጡ እንግዶችን ይዘው ወደቤተመንግስት ሲመጡ ሒልተን ሆቴል አካባቢ ዳገቱ እየከበዳቸው መቆም ጀመሩ፤ እንዳንቀይራቸው ቅርስ ናቸው እንዳንጠቀምባቸው ከሒልተን ማለፍ አቃታቸው ምን እናድርግ?" የሚል ነበር ለማንኛውም በህይወት ቢኖሩ ዛሬ ልደታቸው ነበር፡፡ እስኪ ስለመለስ ዜናዊ ትውስታችሁን አጋሩን፡፡
Show all...
ፍቅር እስከ መቃብር ክፍል አስራ ሁለት (12)
Show all...
👍 2
ፍቅር እስከ መቃብር ክፍል አስራ አንድ (11)
Show all...
ፍቅር እስከ መቃብር ክፍል አስር (10)
Show all...
ፍቅር እስከ መቃብር ክፍል ዘጠኝ (9)
Show all...