cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Kahlil ጂብራን •

"ውበት የበለጠ ደምቆ የሚታየው . . . በሚመለከተው ዓይን ሳይሆን፥ ሊያየው በሚናፍቀው #ልብ ውስጥ ነው፡፡" / የሊባኖሱ ባለቅኔ. . .'ካህሊል ጅብራን' / • • • • • • • • • • ♥ ♥ ♥ The lovely poet KHALIL GIBRAN read more @tobiyan --------------- see more @tobiyan

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
928
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በዕውቀቱ ስዩም ህልም አለህ ይላሉ ራዕይ ያዘለ ኮከብ አለህ አሉ ትንቢት የታደለ ህልምህን ንገረኝ ኮከብህን አሳየኝ ተርጉሜው ልፅናና መነሻዬን ልወቅ መድረሻዬን ላጥና ባንተ ዕጣ ፈንታ ውስጥ ርስት አለኝና። _______________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
Show all...
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ምን ያህል ቢከፋ ምን ያህል ቢያሳምም፣ ለአላዘር መሞት የክርስቶስ እንባ በጉንጩ ሚዘምም፣ ፡ እንዴትስ ቢያንስ ነው እንዴትስ ቢጣጣል፣ በመግደል መሸነፍ እስከመቼ ድረስ ኖሮ ያልጠገበ በሞቱ ይቀጣል፣ ፡ ወረርሽኙ ሲነግስ ተጠንቀቁ ብለው የነተረኩኑ፣ ገዳይ ሲያሰፈስፍ ሜንጫ ሲሳልብን ስለምን ጨከኑ፣ ወይንስ ገዳይ መሸነፉ እንዲገባው ብለው ሟች ላይ ተዋገኑ፣ ፡ ምን ያህል ቢከፋ ምን ያህል ቢያሳምም፣ ለአላዘር መሞት የክርስቶስ እንባ በጉንጩ ሚዘምም፣ ፡ ሞትማ ህመም ነው የአምላክን እንባ ቋት የደነቆለ፣ ልቡን ያሳዘነ የወዳጁ በድን ስላቆለቆለ፣ አፈር ተምሶለት ባፈር ስለዋለ፣ ፡ እሱ ከታመመ እኔንማ እሰቡኝ፣ ማች ስቆጥር የምውል መግደል መሸነፍ ነው ብለው ከትበውኝ፡፡ ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
Show all...
በውቄ አልወጣም ተራራ ደመናን ልዳብሰ ቀስተ ደመናውን ቁልቁል ልቀለብስ አልዋስም እኔ ካቡነ ተክሌ ክንፍ ከያዕቆብ መሰላል፤ እኔ መውጣት ሳስብ ሰማዩ ዝቅ ይላል:: ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
Show all...
የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች 68. ሚካኤል ተው ተብት በኩፍር ሳትቀጣ ይበቃሃል የሚል ከአላህ አዋጅ መጣ እንዴት ያለች ንፋስ የሆነች ባላንጣ በጥፊ ብትመታው በአፍንጫው ደም መጣ ጉዞው ተቃረበ እሩሁ ልትወጣ:: 69. ጉግሣና ራስ ( ወ )ሎሌ፣ አጼ ዮሐንስ ሚካኤል፣ ምኒልክና አጼ ቴዎድሮስ ዘውዲቱና ፈረንጅ ተፈሪ ድረስ በብልሃት ገዟት አልጋው እንዳይፈርስ መጨረሻው ከፍቶ ጣሉት እንደርኩስ:: 70. የአላህን ትተው በውሻ የሚመሩ በሐበሻ መሬት ግፍን የሚሠሩ ቁመታቸው አጭር መልካቸው የሚያምሩ አይነግሡም ብላችሁ አትወዳደሩ ሃምሳ ዓመት ይነግሣል እግረ ውትርትሩ:: 7 1 .ባሕር ወዲያ ማዶ ዘር መጣ ሊጠቅም ግድግዳው የሚያምር በሽንጥ የሚጠቅም ቅጠሉ ለስላሳ ቁመቱ ረዣዥም እሱን ያልተከለ እንዴት ይለጅም ሸዋ በተለየ ያለሱ አይቆምም:: 72. ሥራቸው ባለጌ አህያ የሚበሉ ባሕር ወዲያ ማዶ ክፉ ሰዎች አሉ፣ ሐበሻን ለመውረር ሐሳብ ያስባሉ የኋላ የኋላ መምጣት ይመጣሉ አምስት ዓመት ገዝተው ወዲያው ይሄዳሉ:: 73. ድንጋይ ዱቄት አርገው መንገድ የሚያበጁ ገመድን ዘርግተው መብራት የሚያበጁ አህያ የሚያርዱ አሞራ የሚፈጁ መጡ እየተማሩ ሐበሻን ሊያበጁ ማማሩን አማረች ግን ብዙ ሰው ፈጁ:: 74. እግሩ እንደ ሙቀጫ የሚንከባለል ቢሄድ አይታክተው አቀበት ቁልቁል ጭቃ ካለው መንገድ መሄድ የማይችል ገደል የሚያንሸራትተው የሚንከባለል ይህንን የገዛ ካለፈው ምንም አይል:: 75. በገዛ እጁ ነድፎ ፈትሎ የሚሠራ ሰውን የሚያስገርም የሚሠራው ሥራ ልብሱ ተፈላጊ ሰውን የሚያኮራ ልብሱን ላይሸከሽክ አስተውሎ የሚሠራ በዚህ አይግረምህ ሌላ አለ የሚሠራ:: ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
Show all...
✍ መገንሽ በስውር ስትወርጂ ኖሮ ላፈር ገላሽ ከጥፋትሽ:ገኖ፣ አንቺን ሚጠጥትሽ ባል-ሰማ ነው አሉ፣ባል አወቀ ጭንቅሽ። 'ሰቢ ፯ ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ ከአባል የተላከ #yeneta #ሼር
Show all...
ሚስት-- ላንተ ስል ከአለም እንደምጣላ ታውቃለሃ? ባል-- ግንኮ ሁሌ ከኔ ጋር ነው ምትጣዪው ሚስት-- ምክያቱም የኔ ዓለም አንተ ነሃ፡፡ 😂❤️😂❤️😂❤️😂❤️😂❤️😂 ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
Show all...
🔰Online ስራ መስራት እንፈልጋለን ላላችሁ ይሄን⬇️ ቦት ተጠቀሙ፤ ሞክሬው ሰርቷል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://telegram.me/ask_anything_ethiopia_bot?start=i392939044 1⃣. ቦቱን Start በሉት። 2⃣. Join Channel የሚል ይመጣል #Join በሉት። 👉 @askAnythingEthiopia 👈 🔆ለተለያዩ ሰዎች በላካችሁ ቁጥር፤ በየአንዳንዱ ሰው 1ብር ይከፍላችኋል።✅ ❗️ቦት ውስጥ ከገባችሁ ብኋላ join channel የሚል አለ እሱን join ማለት አለባችሁ እንጂ ቦቱን ብቻ ስለተቀላቀላችሁ አይቆጥርላችሁም
Show all...
አንድ ነገር ላስቸግርህ? 🙏 ❇️ Online ስራ መስራት እንፈልጋለን🤔 ላላችሁ ይሄን⬇️ ቦት ተጠቀሙ፤ ሞክሬው ሰርቷል። 💡ስለ ቦቱ ቀለል አርጌ ለመንገር ያህል:- ከታች ያለውን ሊንክ ነህተሽ ሁለታችንም ትርፋማ እንሁን🤷‍♂️🤷‍♂️ የሚሰራው በመጀመሪያ ሊንኩን start ብለህ Ask Any Things bot ውስጥ ተቀላቀይ በመቀጠል invite ሚለወን በመንካት share ሚለወን እየነካህ በ 1 ሰው 50 ሳንቲም የከፈልሀል ጊዜው አሁን ነው::💁🏿‍♂ መርሳት የሌለብህ ነገር ግን👇 #bot_start_ብለህ_join_channel_ሚለውን_መንካት_ይኖርብሀል
Show all...
Start
Join channel
የህይወት ልጓም (Samuel Geda) 📄📄📄 አንድ የሥነ-ሕይወት (Biology) መምህር ለተማሪዎቹ፤ 'አባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ የሚለወጥበትን ዑደት' እያስተማራቸው ነው። ለጥቆም፤ "በሚቀጥሉት ሰዓታት ከአባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ የተቀየረው አካል፡ ከዕጭ-ሽፋኑ (cocoon) ውስጥ ለመውጣት ትግል የሚያደርግበት ጊዜ ነው፤ ሂደቱን ከመመልከት ውጪ ታዲያ ማንም ቢራቢሮውን ለመርዳት እንዳይሞክር!" ብሎ በማስጠንቀቅ፡ ተማሪዎቹን ጥሎ ከቤተ-ሙከራው ይወጣል። ተማሪዎቹም የሚሆነውን ለማየት በጉጉት ይጠባበቁ ጀመር፤ ልክ መምህሩ እንዳላቸውም ቢራቢሮው ከእጭ-ሽፋኑ (cocoon) ውስጥ ለመውጣት ይታገል ጀመር። ይሁንና ከተማሪዎቹ አንደኛው ልጅ የቢራቢሮውን ትግል ዐይቶ ያዝንና ከመምህሩ ትእዛዝ በተቃራኒ- ብራቢሮውን ከእጭ-ሽፋኑ ሊያወጣው ይወስናል። 'ትግሉን ባቀልለት' ሲልም የእጭ-ሽፋኑን ይሰብረዋል፤ ይሁንና እንደጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ከደቂቃዎች በኋላ ቢራቢሮው ይሞታል። ፧ መምህሩም የተማሪዎቹን ሁኔታ ሊያይ ሲመለስ የተፈጠረውን ነገር ይነግሩታል። ይህን ጊዜ መምህሩ የእጭ- ሽፋኑን ለሰበረው ተማሪ፡ ሁኔታውን ያስረዳው ጀመር፤ "ቢራቢሮውን የገደልከው እርሱን ለመርዳት በማሰብህ ነው፤ ምክንያቱም ከእጭ-ሽፋኑ ለመውጣት ትግል ማድረጉ፡ አንተ እንዳሰብከው ቢራቢሮውን የሚጎዳ ሳይሆን ለክንፉ ጥንካሬና እድገት የሚረዳው ነበር። ይህ የተፈጥሮ ህግ ነውና። አንተ ግን ትግሉን በማቋረጥህ ወይንም በመከልከልህ ምክንያት ቢራቢሮው ሊሞት ችሏል።" * * * ይህ ህግ በህይወታችንም ይሠራል። ከትግል ውጪ ወደ ህይወታችን የሚመጣ (ምንም ዐይነት) ስኬት የለም። አንዳንዴ ወላጆቻችን ከሃዘኔታ ስሜት ተነስተው የትግል ህይወትን ከኛ በማራቃቸው ጎድተውናል፡ እንዳንጠነክርና እንዳናድግም አድርገውናል። ብዙውን ጊዜ ትግል ምቹ ሜዳን ስለማይፈጥርልን አንወደውም። የምንፈልገው ስኬት ሁሉ ያለ ትግል ሰተት ብሎ እንዲመጣ ነው። ስኬቱን እንፈልጋለን ትግሉን ግን አንፈልገውም። ፧ አንድ ቢራቢሮ ቢራቢሮ ለመሆን-- ከእንቁላል ወደ እጭ (larva)፤ ከእጭ ወደ ሙሽሬ (pupa)፤ ከሙሽሬ ወደ አባጨጓሬ፤ ከአባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ፤ ከቢራቢሮነት መብረር እስከቻለባት ደቂቃና ሰአት ድረስ ያለውን *ትግል* ማለፍ የግድ ብሎታል። ልክ እንዲሁ፤ በህይወት ለማደግ/ለመለወጥ (ምንጊዜም) በትግል ውስጥ ማለፍን ይጠይቃል። ስኬት መፈለግህ ጤነኛና ብሩህ አእምሮ የመያዝህ ምልክት ነው። ይሁንና ስኬታማ ለመሆን ጥንካሬና እድገት የግድ ይሉሃል፤ እነርሱ የሚገኙት ደግሞ በትግል ውስጥ ነው። ይኸውልህ፤ የህይወት ትልቁ ልጓም ምንድነው ካልን- ትግል ነው። ነጻነት ያለው ሰው ለመሆን እንጂ ነጻ ለመሆን መፈለግ የለብንም። ፈጣሪም ቅርፅ የሚሰጠን በትግል ውስጥ እያቀለጠ ነው። ምናልባት ልጓም- እርምጃን የሚገታ፣ እረፍት የሚያሳጣ፣ ምቾት የሚነሳ፣ ገደብ የሚጥል፣ ከመንገድ የሚያስቀር፣... ሊመስል ይችላል። ይሁን እንጂ፤ ልጓሙ- ከግብ የሚያደርስ፣ የተገራ ማንነትን የሚያላብስ፤ ብቁና ስልጡን የሚያደርግ፣ ወደ ዓላማ-መርና መርኽ-ገዝ ህይወት (Self actualization/ realization) የሚያሳድግ፣ ጥንካሬን የሚሰጥ፣ ከሁሉ በላይ፡ ከራስ አልፎ ለሌላው የሚቆረስ ስብእና ባለቤት የሚያደርግ--ነው። ስለዚህ ትግል ማለት የስኬት ተቃራኒ ሳይሆን የስኬት አካል ነውና- ትልቁን የህይወት ልጓም- ትግልን አንጥላው! ሰናይ ዕለት! 📄📄📄 Credit to ፦ Samuel Geda 📖@thiolophy @thiolophy @thiolophy #ማንበብ_ምናልባት_ምናልባት_የተሻለ_ሰው_ሊያረግ_ይቻላል
Show all...
ፍልስፍና ምንድን ነው? ፨፨፨ ፍልስፍና ምንድን ነዉ? ተፈጥሮዉ ወይም ባህሪዉ ምንድነዉ? መልስ ከምናገኝባቸዉ መንገዶች አንዱ የቃሉን ማለትም የ"ፍልስፍና" ሥርወት (etymology) በመዳሰስ ነዉ። ፍልስፍና ከጽርእ ቋንቋ የተገኘ ነዉ፣ ፊሎሶፊያ የሁለት ቃላት ሕብረት ሲሆን፤ ፊልያ ማለት #ፍቅር፣ ሶፊያ ማለት ደግሞ #ጥበብ ነዉ፣ ስለዚህ ፍልስፍና ማለት የጥበብ ፍቅር ማለት ነዉ። ይሁን እንጂ ፍቅር ማለት ምንድነዉ? ጥበብስ? ፍቅር ማለት አካላዊ ያልሆነና በማንም ሠዉ ልትጭነዉ(impose) እና ልትማረዉ የማትችል ነገር ነዉ። ማፍቀር የእኔነት(ራስ) አንድ ገፅታ ነዉ። በራስ ብቻ ነዉ ሊኮተኮት፣ ሊጎለብትና ሊጠነክር የሚችለዉ። ፍቅር መሠረታዊ ዝንባሌ ነዉ፣ ወይም እኔነት ወደ ህልዉ የሆነዉ ነገር የሚያነጣጥርበት ነዉ። እንዲሁም እኔነትን እዉን በማድረግ ፕሮጀክት ላይ በጣም መሠረታዊ ጥንተ ነገር (element)ነዉ። ፧ ጥበብም አካላዊ ያልሆነ እንደ ፍቅር ከራስ ወይም ከእኔነት ጋር የተያያዘ ነዉ። ልክ እንደ ሣንቲም ሁለት መሠረታዊ ገጽታዎች አሉት። በአንደኛዉ ገጽታ በሁሉም የሕይወት አቅጣጫዎች ምክንያታዊ ባሕሪ ሲሆን፤ ለሰዉ ልጅ በትክክል ጥሩ የሆነና በትክክል መጥፎ የመግለጽ ወይም የመወሰን አቅም ነው። ፍልስፍና እና መፈላሰፍ የሃይማኖትና ባህል ፀጋዎችን የሚፈታተን አለፍ ሲልም የሚቃረን ነው የሚል እምነት ቀኖናዊ ጭፍንነት አሊያም ገራገርነት(naivete) ከመሆን አልፎ በሙግታዊ አመክንዮ ሲደገፍ አልታየምም። አግባብ ባለው መንገድ እስከተከናወነ ድረስ የፍልስፍና ጥናት ከመንፈሳዊ እድገታችን ጎን ለጎን "የራስን" እዉቀታችን፣ ዉስንነታችንና አቅማችንን በማወቅ ሂደት ላይ አጋዥ ነው። ይህን እዉቀት ከራሳችን ከ"ዉስጥ" የሚፈልቅ እንጂ ከእኛ "ዉጭ" የሚገኝ አይደለም። ፧ እኛ የምናድግ ፍጡሮች ነን። በቀጣይ የመሆን ሂደት ላይ ያለን - ቢያንስ ለማርጀት! ግን ደግሞ በተስፈኝነት ወደተሻለ በመሆን ሂደት ላይ ነን፣ የበለጠ ለመማር፣ የበለጠ ክህሎት ለመደለብ፣ የበለጠ ለመብሰል ብልህ ለመሆን። ፨፨፨ ምንጭ ፦ (የፍልስፍና መግቢያ ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ) Credit to ፦ ፈቲያ @thiolophy @thiolophy @thiolophy #ማንበብ_ምናልባት_ምናልባት_የተሻለ_ሰው_ሊያረግ_ይቻላል
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.