cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

❀ እውቀትን ፍለጋ ❀

Truth Never Update " Qur'an "

Show more
Advertising posts
479
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🌴❤️የጁመዓ ሱናዎች ለናፈቀው ብቻ ❤️🌴 ከናፈቀን በቤት ውስጥ የሚሰሩትን ሱናዎች አንስራ እስቲ #ኢንሻላህ አጅሩን በእኩል እናገኛለን 👇👇👇👇 1 ገላን መታጠብ። 2. ሽቶን መቀባባት (ለ ወንዶች) እና መዋብ። 3. ሲዋክን መጠቀም። 4. የክት ልብስ መልበስ። 5. በጊዜ መስጂድ መጓዝ። 6. በእግር እየተጓዙ ወደ መስጅድ መሄድ። 7. መስጂድ ከደረሱ በኋላ የሰዎችን ትከሻ በመረማመድ ሰዉን አለማስቸገር። 8. ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ተህየቱ መስጂድ መስገድ። 9. ኹጥባ ወደ የሚያደርገው ኢማም መዞርና እሱን እያዩ ኹጥባ ማድመጥ። 10. ኹጥባ በሚደረግበት ሰዓት ፀጥታን መላበስ። 11. ሰደቃን ማብዛት። 12. ከሀሙስ ማታ ጀምሮ እሰከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱ ከሕፍ መቅራት። 13. ድዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሰዓትን መጠባበቅ። 14. በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን በብዛት ማውረድ። #ያለ_ጁማዐ_ሰላት_ግን_ቀኑ_ሁሉ_ተዛባብን_እኮ! #ዛሬ_ጁማአ_ነው_እንዴ_ማለት_ጀመርረናል! 👉 #Share ማንን ገደለ መልካም ጁሙዓ Http://t.me/jenet8
Show all...

*የሉቅማን ምክሮች* ሃያልና አሸናፊው አላህ፣ ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ጥቅል የሆኑ ምክሮችን በመከሩበት አጋጣሚ ስለባህርይው ይነግረናል። ቁርኣን በሉቅማን ምዕራፍ ቁጥር 13 ላይ:- وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ “ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣኦትን) አታጋራ። ማጋራት ታላቅ በደል ነውና። ያለውን (አስታውስ)”  (ሉቅማን 31፤13) ሉቅማን ምክራቸውን የጀመሩት ከሁሉም የላቀና የከበደ የሆነውን እንዲሁም አጥብቆ ሊይዙት የሚገባ የሆነውን ሃያልና አሸናፊው አላህን ብቻ ማምለክ እንዳለበት ነው። ይህም የነገሩ ሁሉ ቁንጮና የኢስላም መሠረት ነው። ከዚያ የጥራትና የልዕልና ባለቤት የሆነውን አላህን ታላቅነቱን፣ በሁሉም ነገሮች ላይ ያለውን እውቀት፣ ያብራሩለታል፡- يَا بُنَيَّ إِنَّهَا إِن تَكُ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ فَتَكُن فِي صَخْرَةٍ أَوْ فِي السَّمَاوَاتِ أَوْ فِي الْأَرْضِ يَأْتِ بِهَا اللَّهُ ۚإِنَّ اللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٌ “(ሉቅማንም) ልጄ ሆይ! እሷ (ደጊቱም ሠናይቱም ሥራ) የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል ብትኾንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትኾን አላህ ያመጣታል። አላህ ሩህሩህ ውስጠ ዐዋቂ ነውና”(ሉቅማን31፤16) ከዚያም ሉቅማን ልጃቸውን ሃያልና አሸናፊው የሆነው አላህ ያዘዘውን ግዴታ እንዲወጣ ምክራቸውን ቀጥለው፣ ሶላት ላይ ቀጥ እንዲል፣ በመልካም እንዲያዝ፣ ከአፀያፊ ተግባር እንዲርቅ፣ በሚያጋጥሙት ችግሮች በትዕግስት እንዲወጣቸው ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፡- يَا بُنَيَّ أَقِمِ الصَّلَاةَ وَأْمُرْ بِالْمَعْرُوفِ وَانْهَ عَنِ الْمُنكَرِ وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ ۖ إِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ “ልጄ ሆይ! ሰላትን አስተካክለህ ስገድ፤ በበጎ ነገርም እዘዝ፤ ከሚጠላው ሁሉ ከልክል በሚያገኝህ መከራ ላይ ታገስ ይህ በምር ከሚይያዙ ነገሮች ነው” (ሉቅማን31፤17) ይህ ቁርኣናዊ መልዕክት አማኝ አንቀጹ ውስጥ የተወሱትን ተግባሮች የግዴታ መፈጸም እንዳለበት ጠቋሚ ነው። ዐብደላ ኢብኑ ዐባስ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና:- من حقيقة الإيمان الصبر على المكاره “ከእምነት የእውነትነት መገለጫ ውስጥ መካከል በሚጠሉት ነገር ላይ የሚደረግ ትዕግስት ነው” ይላሉ። አሁንም ሉቅማን ምክራቸውን በመቀጠል ልጃቸው ከአንዳንድ መጥፎ ባህሪያት መራቅ እንዳለበት እንዲህ ይመክሩታል፡- وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا ۖإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ “ጉንጭህንም (በኩራት) ከሠዎች አታዙር በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛና ሁሉ አይወድምና” (ሉቅማን31፤18)። በመጨረሻም እራሡን እንዲያስተናንስ፣ በአረማመዱ የኩራተኛ አካሄድን እንዳይሄድ፣ ድምጹን ዝግ እንዲያደርግ ይመክሩታል፡- وَاقْصِدْ فِي مَشْيِكَ وَاغْضُضْ مِن صَوْتِكَ ۚ إِنَّ أَنكَرَ الْأَصْوَاتِ لَصَوْتُ الْحَمِيرِ “በአካሄድህም መካከለኛ ኹን ከድምፅህም ዝቅ አድርግ ከድምጾች ሁሉ አስከፊው የእህዬች ድምጽ ነውና” (ሉቅማን፣ 19)። T..➳ telegram.me/jenet8 •┈┈• ❀°•🌹•°❀•┈┈•
Show all...
♥ ጀነት እንገናኝ ♥

ውድ የጀነት ተሳፋሪዎች : አጭር የጀነት መግቢያ መንገዶችን ይዘን አብረን ወደ ጀነት እና በቃ ጀነት እንገናኝ ። if jannah is Ur dream hold tight 2 Ur deen. ለጀነት ሰውን እንጋብዝ #share ለማንኛውም አስተያየት እና ሀሳብ ካላቹ በውስጥ ጣፍ ጣፍ ያድርጉልን ✍✍ @Remee @Romislamic_Bot

01:02
Video unavailableShow in Telegram
📌 ስለ ዘካ ወሳኝ ፈታዋና ማብራሪያዎች #ሼር በማድረግም ያጋሩ 🛑 የዘካን ገንዘብ ለወንድምና እህት መስጠት ይቻላል ወይ? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3805 🛑 ለሰው ያበደርኩት ገንዘብ እጄ ሳይገባ ዘካህ ማውጣት አለብኝ ወይ? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3819 🛑 ለኮንዶሚኒየም የሚቀጠብ ገንዘብ ዘካህ ይወጣበታል ወይ? መልስ https://t.me/ahmedin99/3806 🛑 የወር ደሞዝተኛ ዘካህ ግዴታ የሚሆንበት እንዴት ነው? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3807 🛑 የመቶ ሺህ ብር ካፒታል ያለው ሰው ዘካህ ማውጣት ይኖርበታል ወይ? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3818 🛑 ሰላት ለማይሰግድ ሰው ዘካን መስጠት ይቻላል ወይ? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3812 🛑 ዘካን ለመስጂድ ግንባታና ለመሳሰሉት መስጠት ይቻላልን? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3808 🛑 የሸቀጣቀጥ ስራ ላይ የተሰማራን እንዴት ነው ዘካህ የምናወጣው? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3809 🛑 ዘካህ የምናወጣው እጃችን ላይ ባለ ገንዘብ ብቻ ነው? ወይስ በመኖሪያ ቤታችንና በመኪናም ማውጣት ይኖርብናል? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3820 🛑 ድርጅቶች ውስጥ አክሲዮን ያለው ሰው ዘካህ ማውጣት አለበት ወይ? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3810 🛑 ለሆነ አላማ የተሰበሰበ ገንዘብ ዘካ ይመለከተዋል? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3811 🛑 ዘካ ማውጣት እያለበት እጁ ላይ ገንዘብ የሌለውን ሰው ምን ማድረግ ይኖርበታል? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3813 🛑 ሌሎች ሰዎች ጋር ንብረት ያለው ሰው ዘካውን እንዴት ማድረግ ይኖርበታል? መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3816 🛑 ለንግድ የቀረቡ ማንኛውንም ነገሮች የሚመለከት ዘካህ መልስ:- https://t.me/ahmedin99/3817
Show all...