cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ግጻዌ ወመዝሙር (Gitsawe)

የየእለቱን የቅዳሴ ሰዓት የመልእክታት እና የወንጌል ምንባብ እና ትክክለኛው ምስባክ በደብረ ዓባይ ዜማ ከነምልክቱ የሚቀርብበት ቻናል። ለማንኛውም አስተያየት @YKAZW ይጠቀሙ። https://t.me/joinchat/AAAAAEYf9w2sDdXH1khWWQ

Show more
Advertising posts
1 078
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን መልካም ክብረ በዓል። ካራ ቆሬ ረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
Show all...
✔️🔔ማሳሰቢያ፦ ሰሞኑን ብዙ ሰው የቴሌግራም አካውንቱን እየተዘረፈ ነው። በተለያዩ የቴሌ ግራም ቻናል ሲዘዋወሩ የምናያቸው አጫጭር ሊንኮች የቴሌግራም አካውንታችሁን ለማበላሸት ስለሚዳርጉት ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ እንኳን ቢሆን ሊንኮቹ የተላኩት የሚልኩላችሁ እነርሱ አይደሉምና የሚላከውን ሊንክ አትንኩት። ምንክያቱም ሊንኮቹን ስትነኩ እናንተ የምታስተዳድሯቸውን አካውንቶቻችሁን ግሩፖቻችሁን ቻናላችሁን በተጨማሪም ከሰዎች ጋር Text ያደረጋችሁትን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፉት እና እንደ አዲስ የቴሌግራም አካውንት እንድትከፍቱ ትዕዛዝ ሊሰጣችሁ ይችላል።  ስለዚህ ከእነዚህን ጠላፊዎች/ሃከሮች ሴራ ለመዳን የሚላክላችሁን ሊንክ አለመንካት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው። በተጨማሪም ከጠላፊዎች  አካውንታችሁን ለማዳን በምታስታውሱት PASSWORD ከቴሌግራም ሴቲንግ ውስጥ "TWO STEP VERIFICATION" የሚለውን ON  አድርጋችሁ አካውንታችሁን ጠብቁ። https//t.me/Gamel_Media
Show all...
ጋሜል Media

✍️ "ጋሜል" ማለት "እግዚአብሔር ሊመረመር የማይቻል ግሩም ድንቅ ነው።" ማለት ነው። ✍️ ✍️ "ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር።" ✍️ ✍️ "Gamel" means "God is wonderful beyond measure." ✍️ መዝሙረ ዳዊት (Psalm) 118÷7 Youtube -

https://www.youtube.com/channel/UCHxwszkxLPFCFKAOf1WtaDw

👍 1
" ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል " - ቅዱስነታቸው ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በትግራይ ክልል በተካሔደው ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች እየተከናወነ ያለውን የኀዘን ሥነ ሥርዓት በማስመለክት አባታዊ የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ። ከቅዱስነታቸው መልዕክት የተወሰደ ፦ " ዛሬ በትግራይ ክልል እየተዘከሩ ስላሉ ወገኖች በእጅጉ ማዘናችንን እንገልጣለን ። ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ የነበረ ቢሆንም ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል። ዛሬ በትግራይ ክልል የማይለቀስበት ቤት የለም። የተሰዉት ልጆቻችን በሕይወተ ሥጋ ኖረው ቢሆን ብዙ ታሪክ መሥራት ይችሉ የነበረ ቢሆንም እነዚህ የቤተሰብና የቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የሀገር ተስፋዎች በእሸት በመቅረታቸው በኀዘን በተሰበረ ልብ ሁነን ለነፍሳቸው ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንዲሰጥልን እንጸልያለን። በኀዘን የተጎዳችሁ አባቶችና እናቶችም ይህ ቢሆን ኖሮ እያላችሁ ራሳችሁን እንዳትጎዱ፤ የእናንተ መጎሳቆል የሞቱትን ቀና አያደርግምና ልባችሁን እንድታበረቱ እናሳስባለን ምክንያቱም መቃብር መጨረሻችን ያልሆነ የትንሣኤ ሕዝብ ነን፡፡ በምድር ላይ ስንኖር ማንም ለራሱ መከራን አያቅድምና የታቀዱ ቀኖችንም ለማለፍ ሕገ ተፈጥሮ አይፈቅድልንምና በሆነውና በሚሆነው ነገር ሁሉ ' እንደ ፈቃድህ ይሁን ' እያሉ ልብን ማሳረፍ ይገባል በማለት እንመክራለን፡፡ " (ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል) @Gamel_Media
Show all...
1
05:51
Video unavailableShow in Telegram
18.68 MB
Photo unavailableShow in Telegram
የረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እሑድ ነሐሴ 28 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ያከብራል። እርስዎም የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የምስረታ በዓል አብረውን ያከብሩ ዘንድ ተጋብዘዋል። አድራሻ: - አዲስ አበባ, ካራ ቆሬ, በረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት እና ስብከተ ወንጌል ሁለገብ አዳራሽ።
Show all...
1
Photo unavailableShow in Telegram
1
+++እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ+++ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ፡፡ ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው፡፡ ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ዘንድ ተቀምጦ አየው፡፡ የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት፡፡ ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት፤ የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ፡፡ ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፅዋት ሁሉም አዘነበሉ፤ መላእክት፤ የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት፡፡ አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወረቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት፡፡ በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኃላ በልጆችዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች፡፡ ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ፤ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው፡፡ እርሱም እንዳየ እንደሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንዳሳረጓት ነገራቸው፡፡ ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ፡፡ ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር የአንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ፡፡ እነሆ እኔ እርስዋን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው፡፡ ይህንንም ብሎ ከእርሳቸው ዘንድ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው፡፡ አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሳየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በጾም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን፡፡ በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ፤ የነሐሴ ወር እንደዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው፡፡ በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት፡፡ እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዔ ካህን ሆነ፡፡ እስጢፋኖስም አዘጋጀ፤ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ፡፡ ሁሉም ሐዋርያት በመሰዊያው ዙሪያ ቆሙ፤ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡ ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው፡፡ ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን  እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት፡፡ በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰበኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው፡፡ መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ፡፡ የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለቸው ልጄ ሆይ እነሆ በዓይኖቻቸውም አዩ፤ በጆሮዎቻቸውም ሰሙ፤ በእጆቻቸው ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ድንቆች ሥራዎችን አዩ፡፡ እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ፡፡ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል፡፡ እርሷ ስለ እኛ ወደተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለች፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን፡፡ በረከቷም ሐዋርያት በሰበሰበዋት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን፡፡ ምንጭ፡-ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ
Show all...
1