cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አማን ኢብራሂም AMAN IBRAHIM’S PAGE

Advertising posts
450
Subscribers
No data24 hours
+37 days
+130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከኢስባል እንጠንቀቅ .mp31.28 MB
📣 የልጅዎ ስነ ልቦና ላይ ተፅዕኖ ያሳድራልና ልጅዎን ከሌሎች ጋር አያነፃፅሩ 7122 SMS | አስተውሎት ____ ✊ ወደ 7122 በ SMS  ok ቢልኩ ጠቃሚ እለታዊ መልዕክቶችን በ1 ብር ብቻ ያገኛሉ። ለወዳጆችዎ ያስተዋውቁን!
Show all...
የሸህ አህመድ የህልም ደብዳቤ የመስጂደነበዊ ኻዲም ሸህ አህመድ ያስተላለፉት ደብዳቤ እየተባለ የሚሰራጨውን መልእክት ብዙዎቻችን ከልጅነት ጀምሮ እናውቀዋለን። ‘መልእክቱን ያሰራጨ ኸይር ያገኛል፤ ችላ ያለው መአት ያገኘዋል’ በሚሉ የሀሰት ምሳሌዎችና ማስፈራሪያዎች ስለታጨቀ መልእክቱ በየጊዜው በስፋት ተሰራጭቶ እናገኘዋለን። በተለይም ከማህበራዊ ሚዲያዎች መስፋፋት በኃላ የስርጭቱ ይዘት በእጅጉ ጨምሯል። አያሌ ስህተቶች ያሉበት ይህ ደብዳቤ ተጨባጭነት የሌለውና የሙስሊሞችን አቂዳ የሚሸረሽር በመሆኑ ከማሰራጨት ልንቆጠብ ይገባል። የኢስላም ሊቃውንትም በውስጡ ያሉትን ግድፈቶች እና ቅጥፈቶች በመግለፅ ውሸትነቱን አስረድተዋል። የኡለማዎቻችንን መልእክት ያዘሉ አያያዥ ሊንኮችን ከታች አስቀምጫለው። የአላህ ፈቃድ ከሆነ ሀሳባቸውን ጠቅለል አድርጌ በሌላ ፅሁፍ አካፍላችኃለው። ለግዜው ስለይዘቱ ከአንድ ወንድም ፅሁፍ ቀንጨብ አድርጌ ጥቂት ልበላችሁ። 1ኛ፦ ደብዳቤው እንደሚለው የነቢያችን ሸፋዐ ትርኪ ምርኪ ያዘለ ወረቀት በማባዛት አይገኝም፡፡ ሸፋዐህ ከሚገኝባቸው መንገዶች መካከል፡- ሀ. ከኡመታቸው ውስጥ በአላህ አምልኮ ላይ ምንንም ማንንም ሳያጋራ በተውሒዱ ላይ ጸንቶ የሞተ፡፡ ሙስሊም ከአቢ ሁረይራህ የዘገበው ሐዲሥ ቁ 338 ለ. ከልቡ በኢኽላስ "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" ያለ ሰው፡፡ ቡኻሪይ ከአቢ ሁረይራህ የዘገበው ሐዲሥ ቁ 99 ሐ. ከአዛን በኋላ ያለውን ዱዓ ያደረገ ቡኻሪይ ከጃቢር ኢብኒ-ዐብዲላህ የዘገበው ሐዲሥ ቁ 614 اللَّهُمَّ رَبَّ هَذِهِ الدَّعْوَةِ التَّامَّةِ وَالصَّلَاةِ الْقَائِمَةِ آتِ مُحَمَّدًا الْوَسِيلَةَ وَالْفَضِيلَةَ وَابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا الَّذِي وَعَدْتَهُ መ. በሳቸው ሀገር በመዲና የኑሮም ይሁን ሌሎችን ችግሮችን በመቋቋም ጸንቶ የኖረና እዛው የሞተ ሙስሊም፡፡ ሙስሊም ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ የዘገበው ሐዲሥ ቁ 477 ሠ. የሱንና ሶላቶችን ማብዛት፡፡ ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ ሐዲሥ ቁ 16076 2ኛ፡- ወረቀቱን ያባዛ አንድ ሰው ብዙ ዕድሎች ገጠሙት ይላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በኢስላም ዕድል የሚባል ነገር የለም፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የሚከናውኑ ክስተቶች ሁሉ፤ አላህ ዘንድ ቀድሞ በታወቀው ለውሐል መሕፉዝ ላይ የተጻፉ አላህ በሻውና በፈቀደው መልኩ የሚከሰቱ የቀዷ ወል-ቀደር ውጤት ናቸው። እድል እና አጋጣሚ የሚባል ነገር የለም፡፡ ለመልካም እድል ምክንያት (ሰበብ) የሚሆኑ ነገሮዕን ለመጠቆም ካስፈለገ፤ አላህን መፍራት፡ ዝምድና መቀጠል፡ ሐላል ሪዝቅን ብቻ መከጀል እንጂ ወረቀት ኮፒ ማድረግ ዕድልን አያሰፋም፡፡ 3ኛ፡- ወረቀቱን ከማባዛት ችላ ያለው ሰውዬ በዚህ ሰበብ በዘጠነኛው ቀን ሞተ ይላል፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ የምትሞተው አላህ የወሰነላትን ምድራዊ ቆይታ ስትጨርስ ብቻ ነው (አሊ-ዒምራን 145) ሰዓቱ ሲደርስ ወደፊት ወደኋላ የለም!! ለመሆኑ ወረቀት ኮፒ አለማድረግ እንዴት ለሰውየው ሞት ምክንያት ይሆናል? ለመሆኑ ይሄ ወረቀት ደርሷችሁ ችላ ያላችሁት ወይንም ቀዳችሁ የጣላችሁ ወንድምና እህቶች የላችሁም? 4ኛ፡- ወረቁቱን ያሰራጨ ሰው ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቀውን ነገር ያያል፡፡ ኸይር ነገር የሚገኘው በአላህ ችሮታ ብቻ ነው። ወረቀትን በማሰራጨት የሚገኝ ዕድል ወይም የሚመጣ መአት የለም!! ሀሰትን ከማሰራጨት እንቆጠብ!! External links ☞ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) ምንጭ፡- አል-ኢስላሙ ሱአሉን ወጀዋብ ጥያቄ ቁ 31833 https://www.binbaz.org.sa/article/26 ☞ ሸይኽ ሷሊሕ አል-ፈውዛን http://www.alfawzan.af.org.sa/node/3736 ☞ ሸይኽ አብዱልአዚዝ አሰድሀን الوصية المكذوبة للشيخ عبد العزيز السدحان https://saaid.net/Minute/mm63.htm 🍂 Lies about a dream falsely attributed to the Watchman of the Prophet’s tomb https://islamqa.info/en/31833 ✍ አቡጁነይድ Aug 4, 2018 t.me/abujunaidpost
Show all...
09:47
Video unavailableShow in Telegram
📹 መውሊድ ኢስላማዊ በዓል ነውን? በነሲሓ ቲቪ  የቀረበ አጭር  ውይይት  🔗 Share Link https://t.me/abujunaidposts/514 ---------------- 📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች @abujunaidposts
Show all...
9.33 MB
"ከሴቶቻቹህ መካከል መጥፎዎቹ የሚገላለጡ ኩራተኞች እብሪተኞች የሆኑት ናቸዉ::"ረሱል(ﷺ) አላህ ይጠብቀን::
Show all...
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «በጁምዓ ሌሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ፣ በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድለታል።» ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ " ሐሰን " ብለውታል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የረሱል ስነ-ምግባር || ኡስታዝ አማን ኢብራሂም NesihaTv https://youtu.be/neZOUCnm6Ts ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!! Telegram፡ https://t.me/nesihatv YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCX2E30J71sKpnLQuGr7kt6w Facebook፡ facebook.com/nesihatv @nesihatv
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የሺዓና የአህሉሱና የዓሹራ ውሎ ✍ አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ ሙሀረም 12/ 1436 ዓ.ሒ ተፃፈ የዓሹራ ቀን፤ የፊዓአውንን ትእቢትና አምባገነነንነት ያከተመበትና ለሌሎችም መቀጣጫ የሆነበት፣ ነብዩላህ ሙሳም የተደሰቱበት ለአህሉሱና ታላቅ ትርጉም ያለው የድል ብስራት ቀን ነው። አህሉሱና ይህንን ቀን በአል አያደርጉትም። የተለየ ድግስም ሆነ አለባበስ የላቸውም። ሆኖም መልእክተኛው ﷺ በደነገጉት መሰረት ይፆሙታል፣ መልካም ተግባራትን ይፈፅሙበታል፣ ከአላህ ልዩ ምንዳን በመከጀልም በዒባዳ ያሳልፉታል። ሺዓዎች ግን ስለ ዓሹራ ቀን ሲያስቡ ሚታወሳቸው የታላቁ ሰሀቢይ የአሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ልጅ ሁሰይን የተገደሉበት ቀን መሆኑ ብቻ ነው። ሺዓዎች በዚህ ቀን ሀዘናቸውን ለመግለፅ እራሳቸውን የሚጎዱ ብዙ ነገሮችን በስፋት ይፈፅማሉ። ጭንቅላትንና ሌሎች አካሎቻቸውን በስለት መብጣትና ማድማት (ተጥቢር)፣ ፊታቸውን መደብደብ (ለጥም፣) እራስን በሰንሰለት መግረፍና ማንገላታት፣ በእንብርክክ መሄድ፣ ብዙዎችም ዘንድ ጥቁር መልበስና የለቅሶ ሙሾ ማውረድ ብሎም በራስ ላይ ኩነኔን መጥራት የተለመዱ የአሹራ ትእይንቶቻቸው ናቸው። በእጅጉ ይገርማል፤ ለኛ ለአህሉሱና ደስታን ሲያላብሰን፣ ተስፋን አሰንቆ ድልን ሲያበስረን፤ ለወንጀላችን ማርታን ለማግኘት ሩጫ ውስጥ ሲከተን፤ ለሺአዎች ግና፤ የሀዘን የዋይታ፣ የውድቀት የሽንፈት ማስታወሻ፣ የተስፋ ማጨለሚያ ነው!! ሁሰይን የነብዩ ﷺ የልጅ ልጅ በኢስላማዊ እውቀት ከመጠቁ ታላላቅ ሰሀቦች አንዱ ናቸው። በኢባዳ ብርቱ የተወዳጇ የመልእክተኛው ﷺ ልጅ የፋጢማ ረዲየላሁ አንሀ ልጅ ናቸው። ሆኖም... ቀሪውን በዚህ ሊንክ ያንብቡ http://clearfaith.blogspot.com/2015/10/blog-post.html?m=1 ------ 📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች @abujunaidposts
Show all...
አሹራ... ታሪክና እርምት 1) አሹራ... ታሪክና እርምት 1/4 በሁለት ጠረፎች መካከል https://youtu.be/WmK_NzcVYdg 2) አሹራ... ታሪክና እርምት 2/4 የሁሰይን መገደልና የሺዓዎች የቀብር አምልኮ https://youtu.be/xxSgqdIk5tQ 3) አሹራ... ታሪክና እርምት 3/4 || በሰሐቦች ጥላቻ ላይ የተመሰረተው የሺዓ እምነት https://youtu.be/2hmD6EfzNzQ 4) አሹራ... ታሪክና እርምት 4/4 ስለ አሹራና የሁሰይን መገደል የሺዓዎች ብዥታና መልሶቹ https://youtu.be/YAmqFXfp8rU ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!! @nesihatv
Show all...