cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

All in one

Astronomy Astrology Astrophysics History Religion ለአስተያየት እና እንዲለቀቅ የምትፈልጉት ካለ @B12514

Show more
Advertising posts
192
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

# ፆመ_ነብያት_መቼ_ይገባል ? ለምንስ_እንፆማለን? ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም #ሐሙስ ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 በዕለተ ይፈታል። ይህ ማለት የዘንድሮ የገና ፆም ቅበላ እስከ ማክሰኞነው ከረቡዕ ጀምሮ የፍስክ ምግቦች አይበሉም። ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው። ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው። => ይህ ፆም፣ ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል። # ፆመ_ድህነት የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው። # ፆመ_ማርያም የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል። # ፆመ_አዳም የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡ # ፆመ_ፊሊጶስ የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ # ፆመ_ስብከት የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡ ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን። ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ_ድንግል ወለመስቀሉ_ክቡር
Show all...
​​#ሕዳር_ሚካኤል ! #እንኳን_ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #በዓለ_ሲመት_በሠላም_አደረሰን ! በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (ሕዳር 12) (አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE_SHARE_SHARE ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡) ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡ በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡
Show all...
አውሬ ሁሌም አውሬነቱ አይለቀውም ! በቪዲዮ ላይ ያለው ግለሰብ አንበሳውን እራሱ ነው ያሳደገው ! እንደድል ሆኖ ሰውየው ህይወቱ ተርፏል !
Show all...
12.mp42.63 MB
ህዳር ሚካኤል እና ህዳር ሲታጠን/የህዳር በሽታ/ ።========================== በዚህች ቀን የሰማይ ሰራዊት ሁሉ አለቃቸው መልአከ ምክሩ የምክሩ አበጋዝ ይለዋል የቅድስት ሥላሴ መንጦላእትን የሚከፍትና የሚዘጋ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ቀን ነው። . በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡ ተያይዞም በዕለቱ የህዳር ሲታጠን ታሪክ ይነሳል፤ . አፍሪካን የጎዳው ከባዱ የእንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ በአገራችን ከህዳር 7 እስከ ህዳር 20 ቀን 1911 ዓ.ም ለአስራ አራት ቀናት ገደማ የቆየ ነበረ በሽታው በህዳር ወር የተከሰተ በመሆኑ ህዝቡ የህዳር በሽታ እያለ ጠራው :፡ . ብላቴን ጌታ መርስዔ ሀዘን ወልደቂርቆስ የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ በተሰኘው መጽሀፋቸው እንዳሰፈሩት፤ ወረርሽኙ እስከ አርባ ሺህ ኢትዮጵያዊንን ለሞት ዳርጓል፤ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ዘጠኝ ሺህ ዜጎች በበሽታው ሞተዋል፡፡ . በተለይም ህዳር 12 ቀን 1911 ዓ.ም በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሞቱበት በመሆኑ በቀኑ የጽዳት ዘመቻ እንዲደረግ በአዋጅ ተነግሮ ስለነበር፣ ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ይህ ነገር እንደባህል ተወስዶ በየዓመቱ ህዳር 12 ቀን የጽዳት ዘመቻ ይደረግ ጀመር፤ ይህም በተለምዶ ህዳር ሲታጠን የምንለው ነው፡፡ . ከበዓሉ ረድኤት ያሳትፈን አገራችንን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን አሜን።
Show all...
#እንኳን_አደረሳቹሁ_የተዋህዶ_ልጆች እመቤታችን ከልጇ ከወዷጇ ከጌታችን ጋር ከስደት ወደሀገሯ የተመለሰችበት ቀን ነው ይህም ቀን ቁስቋም ተብሎ ተሰይሟል። ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት እንደሆነ ደብረ ታቦር ማለትም የታቦር ተራራ ማለት እንደሆነ ደብረ ሲና ማለት የሲና ተራራ ማለት እንደሆነ። ደብረ ሊባኖስ ማለትም የሊባኖስ ተራራ ማለት እንደሆነ። ደብረ ቁስቋም ማለት የቁስቋም ተራራ ማለት ነው ጌታችን ታምራት በሰራባቸው ተራራዎች በአሉ በተራራዎች ተሰይሞ ይከበራል። ▪ቁስቋምም እመቤታችን ከስደት ስትመለስ ከልጇ ከጌታችን ከፃድቁ ከዮሴፍ ከቅድስት ሰሎሜ ጋራ ያረፈችበት ተራራ ነው ። ▪ስለዚህ በአሉ ቁስቋም ተብሎ ይከበራል። እመቤታችን ከልጇ ጋራ 42 ወር ተሰዳ በግብፅ ከኖረች በሇላ አሳዳጃው ሄሮድስ ሰለሞተ ወደሀገራ እንድትመለስ መልአኩ ለዮሴፍ ነግሮት ሲመለሱ በዚህ ተራራ ላይ አርፈዋል። ▪በዚም ተራራ ላይ ቅዱሳን መላእክት ክንፋቸውን ዘርግተው በእመቤታችን እና በጌታችን ላይ ረበዋል ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ~ዮም ፀለሉ መላእክት ላእለ ማርያም ወላእለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም~ ብሎ እንደተናገራው በዚህ ተራራ መላእክት ረበው ዘምረውበታል አመስግነውበታል ▪እመቤታችን ተአምራት ባደረገችበት ዕለትና ተራራ ተሰይሞ በአለ ክብሯ ይከበራል። ▪ስለዚህ ቁስቋም ማለት ማርያም ማለት አይደለም እመቤታችን ያረፈችበት ተራራ ነው እንጂ ▪ልደታ በአታ ኪዳነ ምህረት ፍልሰታ ማለትም ማርያም ማለት ሳይሆን ልዩ ልዩ ታሪኳ የተከናወነበት ቀን ነው ▪ልደታ ብለን የምናከብረው የተወለደችበትን ቀን ነው ▪በአታ ብለን የምናከብረው ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን ነው ▪ኪዳነ ምህረት ብለን የምናከብረው የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበትን ቀን ነው ፍልሰታ ብለን የምናከብረው ተነስታ ሥጋዋ ወደሰማይ በእርገት የፈለሰበትን ቀን ነው
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ7 ሚልዮን በላይ አህዮች በመያዝ China እና Pakistan በማስከተል አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሀገራችን ከአለም ሀገራት ብዙ አህዮች የሚገኙባት ሀገር ናት🥇🥇🥇
Show all...
✍ " ብርጭቆ ለመስበር አንድ ድንጋይ ይበቃል፡፡ 👉እንዲሁ አንድ የሳሳ ልብ💔 ለመስበር አንድ አረፍተ ነገር ይበቃል፡፡ 👌ከመናገርህ በፊት ያነሳኸውን ቃል በአእምሮህ ላይ አስቀምጥና መዝነው፡፡ 👉የሚሰብር ከሆነ ጣለው፡፡ ❤️የሚጠግን ከሆነ ተናገረው፡፡ "                                             መልካም ቀን
Show all...
​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞ ✞ ጥቅምት ፳፯ (27) ✞ ✞✞✞ እንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል:: ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: 7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: +በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: 11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው:: ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም:: በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል:: © ዝክረ ቅዱሳን
Show all...
#መድሃኒአለም ማለት የአለም ሁሉ መድሃኒት ማለት ነዉ ስጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ለኛ ሲል ህይወቱን የሰጠ ፨ አሮንና ልጆቹን ....... ለክህነት የመረጠ ፨ ኤልያስን ....... በአዉሎ ነፋስ የነጠቀ ፨ እዮብን ....... በባእድ ሀገር ከፍ ከፍ ያደረገ ፨ ሎጥን ........ ከእሳት ያወጣ ፨ ለሳምሶን ........ ሀይልን የሰጠ ፨ አዛርያን አናንያን ሚሳኤልን ....... ከእሳት የታደገ ፨ ጥበብና ማስተዋልን ....... ለሰለሞን የሰጠ ፨ ያዕቆብን ....... በመንገዱ የጠበቀ እና የባረከ ፨ እስራኤልን ....... ከግብፅ ባርነት ያወጣ ፨ ለሙሴ ....... ጽላት የሰጠ ለኪሩቤል ላይ የተቀመጠ ክብሩንም የገለጠ ስጦታዉ የማያልቅበት #ቸሩ_መድሃኒአለም_ይክበር _ይመስገን_አሜን /፫/ #መድኃኒአለም _የገዢዎች ሁሉ ገዢ #መድኃኒአለም ____ የነገስታት ሁሉ ንጉስ #መድኃኒአለም ____ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ነዉ ኃይሌን ጉልበቴን ታድሳለህ ቀና ቀና እንድል ታደርጋለህ መድኃኒአለም መድኃኒቴ መ ____ መሃሪ ይቅር ባይ አምላክ ድ ____ ድካሜን ተመልከት ስለዉ ተበርክኬ ኃ ____ ኃያላት የማይችሉህ የኃያላን ኃያል ነ ____ ነፍሴ ትልኃለች ጌታዬ ይረዳኛል አ ____ አለምን ለማዳን መስቀል ላይ የዋለ ለ ____ ለዘላለም ፍቅር ነህ ሁሌ የማትቀየር ም ____ ምህረትህ የበዛ #የድንግል_ማርያም_ልጅ_ቸሩ_መድኃኒአለም_አንተ_ነ ህ_አባቴ !! ቸሩ መድኃኒአለም በያላቹሁበት ይጠብቃችሁ ወጥቶ ከመቅረት ከድንገተኛ አደጋ ይጠብቃችሁ አሜን/፫/ የሚያኖረን ሰዉ ሳይሆን የአለም መድኃኒት የሆነዉ ለእኛ ሲል የእሾህ አክሊል የደፈዉ ቸሩ መድኃኒአለም ነዉ። ቸሩ መድኃኒአለም ሃገራችን ይጠብቅልን የዲያብሌስ ስራ እጅግ ተስፋፍቶብን የሰዉኛ ዘይቤዉ ከእኛ ዘንድ ጠፍቶብን ምግባራችን ከፍቶ ትዛዝህን ሽረን ..... በበደል ጨቂተን ዉስጣችን ሲያነባ ካንተ ተሰዉረን ለሰዉ ልጅ ነዉና ደምህ የፈሰሰዉ በምህረት እጆችህ እንባችን አብሰዉ ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ጥንት ለነበረ አሁንም ላለ ኋላም የሚኖር ስሙ የተመሰገን ይሁን አሜን ፫
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#አስደናቂ_እውነታዎች 👉በፍሎሪዳ ከተማ ውስጥ አንዲት የ17 ዓመት ልጃገረድ ከጥር 4/1966 እስከ ሰኔ 8/1966 በተከታታይ ያለ ምንም ማቋረጥ አስነጥሷት የአለም መነጋገሪያ ሆና ነበር 😂😂
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.