en
Feedback
ትንቢተ ሕዝቅኤል 7

ትንቢተ ሕዝቅኤል 7

Open in Telegram

#ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። #ፍጻሜ መጥቶአል፥ ፍጻሜ መጥቶአል፥ ነቅቶብሻል፤ እነሆ፥ ደርሶአል። #በምድር የምትቀመጥ ሆይ፥ ተራህ ደርሶአል፥ ጊዜ መጥቶአል፥ ቀን ቀርቦአል፤ የሽብር ቀን ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም። #አሁን በቅርብ መዓቴን አፈስስብሻለሁ፥ ቍጣዬንም እፈጽምብሻለሁ፥ እንደ መንገድሽም መጠን እፈርድብሻለሁ፥ ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ። ትን.ሕዝ 7÷5-8

Show more
705
Subscribers
+124 hours
-37 days
-1030 days
Posts Archive
ቱርክ ኢስታንቡል https://youtu.be/40P1Dh_TIg0

❗️የኢራን ጦር በአሜሪካ ጦር ተመታ❗️ ባይደን በሶሪያ በሚገኙ የኢራን አብዮታዊ ዘብ የጦር ሠፈሮች እንዲመቱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ሲሉ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን አስታውቀዋል። "በዚህም
❗️የኢራን ጦር በአሜሪካ ጦር ተመታ❗️ ባይደን በሶሪያ በሚገኙ የኢራን አብዮታዊ ዘብ የጦር ሠፈሮች እንዲመቱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ሲሉ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን አስታውቀዋል። "በዚህም መሠረት ዛሬ በፕሬዚዳንት ባይደን መመሪያ የአሜሪካ ጦር የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ (IRGC) እና ተጓዳኝ ቡድኖች የሚጠቀሙባቸው ሁለት የጦሩ ሠፈሮች ላይ እራስን የመከላከል ጥቃት ተፈፅሟል" ሲል ፔንታጎን በድረ-ገጹ ላይ ተናግሯል። የአሜሪካ ጦር በሶሪያ የኢራን ኢላማዎች ላይ የፈፀመው ጥቃት ከፍልስጤም እና ከእስራኤል ግጭት ጋር በምንም መልኩ ግንኙነት እንደሌለው መምሪያው ገልጿል።

እስራኤል በትናንትናው እለት ብቻ በ1 ሺህ የጋዛ ኢላማዎች ላይ የአየር ድብደባ ፈጽማለች። በእስራኤል 900 ሰዎቸ በጋዛ ደግሞ 700 ፍልስጤማውያን እስካሁን በጦርነቱ ሞተዋል።

🇫🇷🇵🇸 የፈረንሳይ ፖሊስ በ #ሊዮን ፍልስጤምን ለመደገፍ በተደረገው ያልተፈቀደ በተባለው ሰልፍ ተሳታፊዎቹ ላይ አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙን BFMTV ዘግቧል። የአካባባው የመገናኛ ብዙኃን ባሰራጩት መረጃዎች መሠረት በርካታ ሰዎች በገብርኤል ፔሪ አደባባይ ተሰባስበው እንደነበር ተገልጿል። በተጨማሪም ፍልስጤምን ለመደገፍ በማድሪድ እና በለንደን ታላቅ ህዝባዊ ትዕይንት የተካሄደ ሲሆን የፓሪስ ነዋሪዎችም እስራኤልን ለመደገፍ ወደ አደባባይ ወጥተው እንደነበር ተነግሯል። Join us👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

ኢራን እና ሄዝቦላህ ካሚካዜ ድሮኖችን እና ሚሳይሎችን በሶሪያ ውስጥ በዳራ እና ኩኔይራ ግዛቶች ውስጥ ጨምሮ ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን በእስራኤል ወደተያዘው የጎላን ኮረብታዎች እየላኩ ነው። 🔻 "ከእናንተ ጋር ነን!" የኢራቅ ሚሊሻ አል-ሃሽድ አል-ሻቢ ለፍልስጤም ተዋጊዎች የተላከ መልእክት ! 🔻የኢራቅ ባድር ኮርፕስ ዋና ጸሃፊ ሃዲ አሚሪም “ዋሽንግተን በእስራኤል መንግስት እና ፍልስጤም መካከል በሚደረገው ጦርነት ጣልቃ ከገባች ሁሉንም የአሜሪካ ኢላማዎች እንመታለን” ሲሉ ዛቻ ሰንዝረዋል። 🔻 የየመን የሁቲ አማፂያን አሜሪካ ጣልቃ ከገባ ወደ ጦርነት እንገባለን ብለዋል። "በፍልስጤም ላይ የሚደረግ ማንኛውም ጣልቃ ገብነት ወደ ክልላዊ ጦርነት እንደሚያመራ አሜሪካን እናስጠነቅቃለን" ብለዋል መሀመድ አሊ አል-ሁቲ።

#KBG እስራኤል 🇲🇱የፍልስጤም Vs እስራኤል ጦርነት ትንበያ ========= #ሰውየው ቭላድሚር ቮልፎቪች ዚሪኖቭስኪ ይባላሉ። (እ.አ.አ ከሚያዚያ 25 - 1946 እስከ ሚያዚያ 6 ቀን 2022 ድረስ በህይወት የኖሩ አርበኛ ነበሩ) እ.ኤ.አ. በ1992 በተመሰረተው የፖለቲካ ፓርቲ ከ1993 እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ ያገለገሉ የሩሲያ የቀኝ ክንፍ ፖፕሊስት ፖለቲከኛ እና የሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኦፍ ሩሲያ (LDPR) መሪ ነበሩ። ትውልዳቸው በቀድሞዋ የሶቪየት ህብረት በካዛኪስታን ግዛት ዛሬ ላይ አልማቲ በተባለችው ከተማ ሲሆን ከሞስኮ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት የተመረቁ እንዲሁም የ3ኛ-4ኛ-5ኛ ደረጃ የአባት አገር ራሺያ የክብር ሜዳሊያ ተሸላሚ - ሌሎችም በርካታ ክብር የተጎናፀፉ በሳል ፖለቲከኛ ነበሩ - እንዲያውም የአገሪቱ የበላይ ም/ቤት ምክትል ሊቀመንበር በመሆንም አገልግለዋል። በ2018 በሩስያ በነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም ፑቲንን የተፎካከሩ ዕጩ እስከመሆን ደርሰው ነበር። እኚህን ሰው ዛሬ ላይ ድንገት ለምን አነሳናቸው ? (ያለምንም ማወላወል ከ2 ዓመታት በፊት ቀጣዩን በመናገራቸው) «እ.ኤ.አ 2024 ከመግባቱ ጥቂት ቀደም ብሎ በመካከለኛው ምስራቅ የማይበርድ ታላቅ ግጭት ይነሳል። ሁሉም በዩክሬን ምን እየተደረገ እንደነበር እንኳ በቀላሉ ይረሳል - ምክንያቱም ኢራን ታላቅ ወጀብን ታሰነሳለች። ኢራን ማለት ደሞ ሰሜን ኮሪያን ወይም ቬትናምን ወይንም ደሞ ኮሶቮን አይደለችምና - በነዚያ ቀጠናዎች በጣም አሰቃቂ የሆኑ ክስተቶች ይፈጸማሉ - ልብ አድርጉልኝ ፡ እየተናገርኩ ያለሁት 3ኛውና የመጨረሻው የዓለማችን ጦርነትና የመጥፊያችን እልቂት እንዴት ዘው ብሎ እንሚገባ ነው» ቭላድሚር ቮልፎቪች ዚሪኖቭስኪ (በመጋቢት 2013 ዓ.ም የዛሬ 2ዓመት ገደማ በሶልዬቮቭ የቀጥታ ስርጭት ላይ ከተናገሩት የተወሰደ ነው)

🔥🇮🇱 የእስራኤል የራሃት ፖሊስ አዛዥ ዛሬ ከፍልስጤማውያን ጋር በተፈጠረው ግጭት መገደላቸው ተዘገበ። Join👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp
🔥🇮🇱 የእስራኤል የራሃት ፖሊስ አዛዥ ዛሬ ከፍልስጤማውያን ጋር በተፈጠረው ግጭት መገደላቸው ተዘገበ። Join👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሌላኛው ገጽታ❗ የግብፅ ጦር የ2ኛውና 3ኛው ብርጌድ ሠራዊት ከፍተኛ የውጊያ ዝግጁነት እያደረጉ ሲሆን በእስራኤል ድንበር ላይ የደህንነት እርምጃዎች መውሰድ ጀምረዋል የሚሉ መረጃዎች ወጥተዋል። የሠራዊቱ የተለያዩ ክፍሎች ከካይሮ እና አሌክሳንድሪያ ወደ ሲና ባሕረ ገብ መሬት እየተላኩ ነው ተብሏል። እስራኤል በበኩሏ በግብፅ ውስጥ ላለው የውጥረት መባባስ ምላሽ እየሰጠች እንዳለች እና በሌላ በኩል ደሞ #ቴል_አቪቭ <በአካባቢው ወታደራዊ ውጥረት መፈጠሩ እስራኤልን ለማዘናጋት የተደረገ ሙከራ ነው> በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብታለች - መባሉን ዘገባዎች ጠቁመዋል። የእስራኤል ጦር ከብዙ ስፍራዎች ሸሽቷል - ሸሽቷል ብቻም ሳይሆን በርካታ ታንኮቹን (ያውም #መርካቫ የተባሉትን) ለሃማስ ጦር ትቶ - #ሃምቪ የተባሉትን የታጠቁ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎቹን ፣ የጦር ትጥቅ መጋዘኖቹን ሁሉ ከነመሳሪያዎቻቸው ለሃማስ ጦር ትቶላቸው ስፍራውን ለቅቆ ወጥቷል። በአሁኑ ሰዓት አሰቃቂ ቪዲዮዎች የመረጃ መረቦችን እያጨናነቁት ይገኛሉ። ሃማስ ከእስራኤል ጦር የማረካቸውን የጦር ትጥቆች አስመልክቶ በርካታ ቪዲዮዎች ተሰራጭተዋል - ጥቂትና የመረጥናቸውን ተመልከቷቸው። እነሆ ጋበዝን ! Join us 👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

❗️ሃማስ በእስራኤል ላይ ባካሄደውና {የብረት ሰይፍ - Iron Swords} ሲል በጠራው ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት IDF ወታደሮቹን ወደ ሌላ ቦታ እንዳዛወረ የሚያሳይ ቪዲዮ አሳትሟል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሌላኛው የእስራኤል ጠላት #ሂዝቦላህ እስራኤልን ለማጥቃት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑን እንዳስታወቀና እንቅስቃሴ መጀመሩን አስመልክቶ የአካባቢው ሚዲያዎች ዘግበዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ወታደሮች ወደ ሰሜናዊ እስራኤል ለመግባት በሞከሩት የሂዝቦላህ ተዋጊዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል ሲል እየሩሳሌም ፖስት ዘግቧል። በተጨማሪም ኔታንያሁ ከባይደን ጋር ውይይት ማድረጋቸው የተነገረ ሲሆን ኔታንያሁ ባይደን ላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነው እስራኤል የምታሸንፍበት ረጅምና ብርቱ ዘመቻ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል። Join👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

ዛሬ በደቡብ እስራኤል የተከሰቱት ክስተቶች በአንድ የግንባሩ ዘርፍ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የመከላከያ ሰራዊቱን ሙሉ ሽንፈትን ያከናነበ ነበር ከማለት ውጭ ሌላ ነገር ሊባል አይችልም። በጥቂት ሰአታት ውስጥ የተማረኩት እና የተገደሉት የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር እ.አ.አ በ1973 ከዮም ኪፑር ጦርነት በኋላ ያልታየ መሆኑ ተነግሯል። የአማፂው ቡድን ተዋጊዎች ከእስራኤል ጦር አንፃር በጣም ትንሽ ሲሆኑ ፍጹም የታጠቁ እና የሰለጠኑ የሰራዊት ክፍሎችን ለማሸነፍና ስፍራዎቹን ለመቆጣጠር የነበራቸው ፍጥነት እጅግ አስገራሚ ሆኗል:: እስራኤል ምንም እንኳን ለእንደዚህ ዓይነቱ ትንሽ ቡድን የሚሆን ልዩ ወታደራዊ ኃይል ቢኖራትም ወደ አስደንጋጭ ጦርነት በዚህ ፍጥነት መሸጋገሯ ግን ሙሉ በሙሉ ተኝታ ነበር አስብሏል። እስራኤልን ህዝብ የከፋፈለው የፖለቲካ ሽኩቻ ፣ የቀደሙት ዘመን ወታደራዊ ድሎቿ እና የነበራት በራስ የመተማመን መንፈስ በአሁኑ አጋጣሚ ቴልአቪቭ ሁኔታውን በትክክል እንድትገመግም አልፈቀደላትም ፣ ይህም " ለIDF የቀን ጨለማ ” እንዲፈጠርበት ምክንያት ሆኗል ። የፍልስጤማውያኑን ጥንካሬ ለመገመት አያዳግትም። በእርግጥ ነው IDF ወደ አእምሮው ተመልሶ በጋዛ ውስጥ መዘዘኛ ኦፕሬሽን ማካሄዱ አይቀርም። ነገር ግን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በጦር መሳሪያዎችና በሰዎች ላይ ለአስርት ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ ኪሳራ ደርሶበታል። ዓለምን ሁሉ ሲያስደምም የኖረው #መርካቫ የውጊያ ታንክ በርካሽ የሰው አልባ አውሮፕላን ሲወድም ታይቷል። በአጠቃላይ ግን እስራኤል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዘመን በፊት ወደነበረበችበት የሲኦል ዞን ውስጥ እየገባችና ግዛቶቿም ከሠራዊቱ ስልጣን ቁጥጥር የወጡ በመሆን የመንግስትን የመኖር ያለመኖር ህልውና የተፈታተነ አጋጣሚ ውስጥ ገብታለች። @MayalInfoWorld

"ጦርነቱን ለማሸነፍ ሁሉም እስራኤላውያን እንድትተባበሩ ጥሪ አቀርባለሁ - ከዛሬ ጀምሮ እስራኤል በጦርነት ውስጥ ናት። 📍የመጀመሪያው አላማችን አካባቢውን ሰርጎ ከገባ የጠላት ሃይል ማጽዳት እና ጥቃት የደረሰባቸውን ክልሎች ፀጥታና ሰላም ማስፈን ነው። 📍ሁለተኛው ግብ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የሚገኘው ጠላት ከፍተኛ ዋጋ ያለው ቅጣት ማግኘቱ ነው። 📍ሦስተኛው ዓላማ ማንኛውም 3ኛ አካል ወደዚህ ጦርነት በመቀላቀል ስህተት እንዳይሠራ ሌሎች መድረኮችን ማጠናከር ነው›› ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በቴል አቪቭ በተካሄደ የካቢኔ ስብሰባ ላይ የተናገሩት Join👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

#𝘽𝙍𝙀𝘼𝙆𝙄𝙉𝙂 💥❗ዙሩ ከረረ❗💥 ኢራን ፍልስጤሞች በእስራኤል ውስጥ የጀመሩትን የአል-አቅሳን ኦፕሬሽን ትደግፋለች ሲሉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒ አማካሪ ጄኔራል ራሂም ሳፋቪ ተና
#𝘽𝙍𝙀𝘼𝙆𝙄𝙉𝙂 💥❗ዙሩ ከረረ❗💥 ኢራን ፍልስጤሞች በእስራኤል ውስጥ የጀመሩትን የአል-አቅሳን ኦፕሬሽን ትደግፋለች ሲሉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒ አማካሪ ጄኔራል ራሂም ሳፋቪ ተናገሩ። Join👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

#𝘽𝙍𝙀𝘼𝙆𝙄𝙉𝙂 እስራኤላዊው ብርጋዴር ጀነራል ንምሩድ ኣሎኒ በሐማስ ቁጥጥር ስር መግባታቸው ተረጋገጠ !

🇫🇷 ማክሮን በእስራኤል ላይ የፍልስጤም ታጣቂዎች ያደረሱትን ጥቃት አውግዘዋል። 🇩🇪 የጀርመን ባለስልጣናት በእስራኤል የፍልስጤም አክራሪዎችን እንቅስቃሴ አውግዘዋል። 🇭🇺 ሃንጋሪ በእስራኤል ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት በማውገዝ እስራኤል ራስን የመከላከል መብቷ የተጠበቀ ነው ስትል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ገልፃለች። 🇹🇷 ተርኪዬ- ኤርዶጋን በእስራኤል ግጭት ላይ ያሉ ወገኖች ሁኔታውን እንዲያባብሱ ሳይሆን እንዲቆጣጠሩ አሳስበዋል። 🇬🇪 ጆርጂያ - ወንድም ህዝብ እስራኤልን ይደግፋል - የጆርጂያ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ 🇮🇷 ኢራን "የጽዮናውያን አገዛዝ እየሞተ ነው" - አያቶላ ካሜኒ በ X

🇫🇷 ማክሮን በእስራኤል ላይ የፍልስጤም ታጣቂዎች ያደረሱትን ጥቃት አውግዘዋል። 🇩🇪 የጀርመን ባለስልጣናት በእስራኤል የፍልስጤም አክራሪዎችን እንቅስቃሴ አውግዘዋል። 🇭🇺 ሃንጋሪ በእስራኤል
🇫🇷 ማክሮን በእስራኤል ላይ የፍልስጤም ታጣቂዎች ያደረሱትን ጥቃት አውግዘዋል። 🇩🇪 የጀርመን ባለስልጣናት በእስራኤል የፍልስጤም አክራሪዎችን እንቅስቃሴ አውግዘዋል። 🇭🇺 ሃንጋሪ በእስራኤል ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት በማውገዝ እስራኤል ራስን የመከላከል መብቷ የተጠበቀ ነው ስትል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ገልፃለች። 🇹🇷 ተርኪዬ- ኤርዶጋን በእስራኤል ግጭት ላይ ያሉ ወገኖች ሁኔታውን እንዲያባብሱ ሳይሆን እንዲቆጣጠሩ አሳስበዋል። 🇬🇪 ጆርጂያ - ወንድም ህዝብ እስራኤልን ይደግፋል - የጆርጂያ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ 🇮🇷 ኢራን "የጽዮናውያን አገዛዝ እየሞተ ነው" - አያቶላ ካሜኒ በ X Join👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y