cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ምጥን ቅመም (Mitin Kimem)

እያሳሳቁ ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ጽሁፎችን እናደርሶታለን። https://t.me/joinchat/AAAAAEW4c6a4s66UQCzegg

Show more
Advertising posts
999
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✔️🔔ማሳሰቢያ፦ ሰሞኑን ብዙ ሰው የቴሌግራም አካውንቱን እየተዘረፈ ነው። በተለያዩ የቴሌ ግራም ቻናል ሲዘዋወሩ የምናያቸው አጫጭር ሊንኮች የቴሌግራም አካውንታችሁን ለማበላሸት ስለሚዳርጉት ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ እንኳን ቢሆን ሊንኮቹ የተላኩት የሚልኩላችሁ እነርሱ አይደሉምና የሚላከውን ሊንክ አትንኩት። ምንክያቱም ሊንኮቹን ስትነኩ እናንተ የምታስተዳድሯቸውን አካውንቶቻችሁን ግሩፖቻችሁን ቻናላችሁን በተጨማሪም ከሰዎች ጋር Text ያደረጋችሁትን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፉት እና እንደ አዲስ የቴሌግራም አካውንት እንድትከፍቱ ትዕዛዝ ሊሰጣችሁ ይችላል።  ስለዚህ ከእነዚህን ጠላፊዎች/ሃከሮች ሴራ ለመዳን የሚላክላችሁን ሊንክ አለመንካት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው። በተጨማሪም ከጠላፊዎች  አካውንታችሁን ለማዳን በምታስታውሱት PASSWORD ከቴሌግራም ሴቲንግ ውስጥ "TWO STEP VERIFICATION" የሚለውን ON  አድርጋችሁ አካውንታችሁን ጠብቁ። https//t.me/Gamel_Media
Show all...
ጋሜል Media

✍️ "ጋሜል" ማለት "እግዚአብሔር ሊመረመር የማይቻል ግሩም ድንቅ ነው።" ማለት ነው። ✍️ ✍️ "ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር።" ✍️ ✍️ "Gamel" means "God is wonderful beyond measure." ✍️ መዝሙረ ዳዊት (Psalm) 118÷7 Youtube -

https://www.youtube.com/channel/UCHxwszkxLPFCFKAOf1WtaDw

" ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል " - ቅዱስነታቸው ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በትግራይ ክልል በተካሔደው ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች እየተከናወነ ያለውን የኀዘን ሥነ ሥርዓት በማስመለክት አባታዊ የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ። ከቅዱስነታቸው መልዕክት የተወሰደ ፦ " ዛሬ በትግራይ ክልል እየተዘከሩ ስላሉ ወገኖች በእጅጉ ማዘናችንን እንገልጣለን ። ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ የነበረ ቢሆንም ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል። ዛሬ በትግራይ ክልል የማይለቀስበት ቤት የለም። የተሰዉት ልጆቻችን በሕይወተ ሥጋ ኖረው ቢሆን ብዙ ታሪክ መሥራት ይችሉ የነበረ ቢሆንም እነዚህ የቤተሰብና የቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የሀገር ተስፋዎች በእሸት በመቅረታቸው በኀዘን በተሰበረ ልብ ሁነን ለነፍሳቸው ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንዲሰጥልን እንጸልያለን። በኀዘን የተጎዳችሁ አባቶችና እናቶችም ይህ ቢሆን ኖሮ እያላችሁ ራሳችሁን እንዳትጎዱ፤ የእናንተ መጎሳቆል የሞቱትን ቀና አያደርግምና ልባችሁን እንድታበረቱ እናሳስባለን ምክንያቱም መቃብር መጨረሻችን ያልሆነ የትንሣኤ ሕዝብ ነን፡፡ በምድር ላይ ስንኖር ማንም ለራሱ መከራን አያቅድምና የታቀዱ ቀኖችንም ለማለፍ ሕገ ተፈጥሮ አይፈቅድልንምና በሆነውና በሚሆነው ነገር ሁሉ ' እንደ ፈቃድህ ይሁን ' እያሉ ልብን ማሳረፍ ይገባል በማለት እንመክራለን፡፡ " (ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል) @Gamel_Media
Show all...
📖 📖 📖 አንዳንድ ሰዎች እጅግ የጠለቀ ኀዘንና መቆርቆር ውስጥ ሲገቡ “እግዚአብሔር ትቶኛል! ፤ የእሥራኤል አምላክ ረስቶኛል!” ብለው ሲያማርሩ እሰማቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ነቢዩ እንዲህ ከሚሉ ሰዎች ጋር ክርክር አለው፡፡ “በውኑ ሴት ከማኅፀኗ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃኗን ልትረሳ ትችላለችን?” በማለት ይጠይቃቸዋል (ኢሳ.49፡14)፡፡ ይህም ማለት ሴቷ ከማኅፀኗ የተወለደው ልጇን ትረሳ ዘንድ እንደማይቻላት ሁሉ እግዚአብሔርም ሰውን ይረሳ ዘንድ ባሕርይው አይደለም እያላቸው ነው፡፡          ነቢዩ ይህን ምሳሌና ማነጻጸርያ አንሥቶ ክርክር መግጠም የፈለገው እያንዳንዷ እናት ለልጇ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቅ ነው፡፡ ሆኖም ይህን ያህል የምናንቆለጳጵሰው የእናት ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ሲነጻጸር ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው “አዎን እርሷ ልጇን ትረሳ ይሆናል ፤ እኔ ግን አልረሳሽም… ይላል እግዚአብሔር” በማለት የሚቀጥለው፡፡ እንግዲህ የአምላካችን ፍቅር እንደምን የበዛ እንደሆነ ታስተውላላችሁን?        እንግዲያውስ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አባት ለልጆቹ እንዲያዝን እንዲራራ እንደዚህም ሁሉ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ይራራለቸዋል።” ብሎ እንደተናገረ “እግዚአብሔር ረስቶኛል! ፤ የእሥራኤል አምላክ ትቶኛል!” የሚል ማንም አይገኝ። (መዝ.102፡13)፡ ጆሮን የፈጠረ እርሱ ይሰማል ፤ ዐይንን የፈጠረ እርሱ ያያል፡፡ እግዚአብሔር በእጁ መዳፍ የቀረጻቸው ልጆቹን አይረሳም፡፡ ✍ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ https://t.me/Gamel_Media
Show all...
ጋሜል Media

✍️ "ጋሜል" ማለት "እግዚአብሔር ሊመረመር የማይቻል ግሩም ድንቅ ነው።" ማለት ነው። ✍️ ✍️ "ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር።" ✍️ ✍️ "Gamel" means "God is wonderful beyond measure." ✍️ መዝሙረ ዳዊት (Psalm) 118÷7 ለማንኛውም አስተያየት @DN_YKAZ

https://t.me/Gamel_Media

05:51
Video unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እሑድ ነሐሴ 28 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ያከብራል። እርስዎም የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የምስረታ በዓል አብረውን ያከብሩ ዘንድ ተጋብዘዋል። አድራሻ: - አዲስ አበባ, ካራ ቆሬ, በረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት እና ስብከተ ወንጌል ሁለገብ አዳራሽ።
Show all...
#መልእክተ_ቅዱስ_ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!! በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ እግዚአብሔር አምላካችን በይቅርታውና በምሕረቱ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመተ ምሕረት የድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ:: “ወእምኵሉስ ዘይቀድም ተፋቀሩ በበይናቲክሙ በምልአ ልብክሙ እስመ ተፋቅሮ' ይደፍኖን ወይደመስሶን ለኵሎን ኃጣውእ!" (ከሁሉ አስቀድሞ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ፣ መፋቀር ሁሉንም ዓይነተ ኃጢአት ይሸፍናልና ይደመስሳልምና (፩ ጴጥ.፬-፰) ሁላችንም እንደምናውቀው የቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ መሠረትና ጣርያ ወለልና ግድግዳ በፍቅርና በፍቅር ብቻ የተገነባ ነው፡ ፍቅር እግዚአብሔር ዓለምን ያዳነበት መድኃኒት ነው፣ ፍቅር የጥላቻና የመለያየት ግንብን ንዶ ይቅርታንና አንድነትን የሚገነባ ጠንካራ ዓለት ነው፣ ፍቅር መጽናናትንና ደስታን የሚያፈራ ጣፋጭ ተክል ነው፤ በፍቅር ለፍቅር የሚደረግ ሁሉ ፍሥሐን እንጂ ጸጸትን አያስከትልም በመሆኑም በሰብአዊ ድክመት ምክንያት ሰዎች ፍቅርን ሙሉ በሙሉ በሚፈለገው ደረጃ ባንጠብቀውም በዓለማዊም ሆነ በመፈንሳዊ ሕይወት ከፍቅር የበለጠ ጠቃሚ ነገር የለም ፍቅር የማይሻርና ለዘላለሙ ጸንቶ የሚኖር እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተመዘግቦአል፤ ምክንያቱም ፍቅር ከሞት በኋላም ቢሆን በእግዚአብሔር መንግሥት ይቀጥላልና ነው ዛሬ የሚጀመረው የድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታም በፍቅር ለፍቅር የተፈጸመ ነው፣ ይኸውም ቅዱሳን ሐዋርያት የድንግል ማርያምን የማረፊያ ቦታ ለማየት ሲሉ የጾሙት ጾም ነው! ቅዱሳን ሐዋርያት የገለፁት ፍቅረ ድንግል ማርያምን ብቻ ሳይሆን ያረፈችበትንም ቦታ ጭምር ያመለከተ ነበረ፤ ይህ ሊሆን የቻለው ከልብ የሆነ እውነተኛ ፍቅር በሐዋርያት ዘንድ ስለነበረ ነው፡፡ እኛም ዛሬ የምንጾመው ይህንን የማርያም ጾም እንደ አበው ሐዋርያት ፍቅረ ድንግል ማርያም በልባችን ውስጥ ተተክሎ ስላለ ነው፤ እግዚአብሔር በፍቅርና በሃይማኖት የሚቀርብለትን ሁሉ ይቀበላልና የሐዋርያትን ጾምና ጸሎት ተቀበሎ ጥያቄአቸውን መልሶአል። ዛሬም ይህንን ጾም የምንጾመው እግዚአብሔር ጾማችንን ተቀብሎ የልባችንን መሻት ይፈጽምልናል ብለን ነው ፣ በፍቅርና በሃይማኖት አስክ ጾምን ደግሞ እግዚአብሔር ይቀበለናል፤ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! እንደ እግዚአብሔር ቃልም እንደ አባቶቻችን ትውፊትም የጾመ ፍልሰታ ጾም ሲጾም የበደለ ይቅርታ ጠይቆ፣ ተገቢውንም ካሣ ከፍሎ፣ ቂም በቀሉን አሰርዞ፣ ፍቅርን መሥርቶ ነበረ የተበደለም በበኩሉ ዕርቅን አውርዶ፣ ይቅርታን ሰጥቶ የእእምሮ ማለስለሻና ማስረሻ የሆነውን ካሣውን ተቀብሎ ተሙንና በቀሉን ከአእምሮው አውጥቶና አጽድቶ፤ ለእግዚአብሔር ስል ከልቤ ይቅር ብያለሁ ብሎ፣ ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ በፍቅር ይታረቃል በዚህ ሁኔታ ፍጹምና ልባዊ ፍቅር ተይዞ ሲጾም ሁሉም ዓይነተ : ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ይደመሰስለታል ፤ እግዚአብሔርም ይቅርታ ጠያቂውንም፣ ይቅርታ ሰጪውንም አሸማጋዩንም ይባርካል፤ ማኅበረ ሰቡም በዚህ ቅዱስና ሃይማኖታዊ ባህልና ትውፊት ተጠብቆ ለብዙ ዘመናት አንድነቱንና ሃይማኖቱን ወንድማማችነቱንና ነጻነቱን አስጠብቆ እስከ ዛሬ ደርሶአል | ይህ ለሀገራችን ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔር በረከት ነበረ፣ ይህ እውነተኛ በረከት በአሁኑ ጊዜ ቸል በመባሉ ፈተናችን በዝቶአል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሰው በኃጢአት ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ ጥልና መገዳደል በየትኛውም ጊዜ፤ በየትኛውም ሀገር በየትኛውም ማኅበረ ሰብ ይከሠታል፤ ዛሬም በሀገራችን በተፈጠረው አለመግባባት ከባድ ችግር ተፈጥሮአል የሚያስገርመው ነገር ቢኖር እንዴት እንደባህላችንና እምነታችን በቀላሉ በዕርቅና በይቅርታ ማስተካከል አቃተን የሚለው ነው፡ የዘመናችን ልዩ ነገር ይህ ነው ለዚህም ብዙ የተለያየ ምክንያት ሊኖረው ይችላል፣ በሃይማኖት ዓይን ሲታይ ግን ለእግዚአብሔር ቃል የምንሰጠው ክብር በእጅጉ ስለተቀነሰ ነው የሚል ሆኖ ይገኛል፣ ይህ ዝንባሌ አሁን ላለውም ሆነ ለሚመጣው ትውልድ አደገኛ ስለሆነ የኦርቶዶክስ ሕዝበ ክርስቲያንም ሆነ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን በጥልቀት ሊያጤኑትና ሊያርሙት ይገባል። የተወደዳችሁ የመንፈስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናንት | ሽማግሌ የሀገር በረከት ነው፤ አስታራቂ ሽማግሌ የችግር ሐኪምና ፈዋሽ ነው፣ የፍቅርና የተግባቦት መሐንዲስም ነው፤ በእግዚአብሔርም የሚያስታርቁ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው” ተብሎ ውዳሴ ተችሮአቸዋል፣ እነዚህን ሽማግሌዎች ተጠቅመን ችግሮቻችንን መፍታት ጊዜው የሚጠይቀው አስገዳጅ ጉዳይ ሆኖአል፤ ሁሉም ታየ፤ ሁሉም ተሞከረ፣ ዘላቂ መፍትሔ ሲያመጣ ግን አልታየም፤ እንዲያውም ችግሩ ወደ ሃይማኖት ተዛምቶ ቤተ ክርስቲያንም የገፈቱ ቀማሽ ለመሆን ተገዳለች፡፡ በተጨባጭ እንደሚታውቀው ሕዝብንና ሃይማኖትን ነጣጥሎ ሰላምን ማረጋገጥ ከቶውኑ ሊታሰብ አይችልም ምክንያቱም ሕዝብ የሃይማኖቱ ቤተሰብ ነው፤ ሃይማኖቱም በሕዝቡ መንፈስ ውስጥ ነግሦ የሚኖር መለኮታዊ ኃይል ነውና፣ ከዚህ አንጻር “ወልድ ሲነካ አብ ይነካ" እንደሚባለው ሕዝቡ ሲነካ ሃይማኖቱ ይነካል፣ ሃይማኖቱ ሲነካ ደግሞ ሕዝቡ ይነካል፤ በመሆኑም በተካሄደው ግጭት ብዙ ነገሮች መመሳቀላቸው የማይካድ ቢሆንም ችግሩ በዕርቅና በካሣ በይቅርታና በመተው ካልተዘጋ ለማንም ስለማይበጅ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ለዕርቅ ዝግጁ እንዲሆነ፣ የበደሉም እንዲክሱ የሀገር ሽማግሌዎችም የማስታረቅ ስራን በሐቅ በገለልተኝነትና ዕንባን በሚያደርቅ ስልት እንዲሸመግሉ መንግሥትም የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የገጠመንን ፈተና ሁሉ ሊያቀልልንና ሊያስወግድልን የሚችል እግዚአብሔር ስለሆነ፤ በዚህ የጾመ ማርያም ወቅት ምእመናን በተመሥጦና በንሥሐ ሕይወት ለእግዚአብሔር በመንበርከክ ስለ ሰላምና ፍቅር እንዲማፀኑ፣ ካላቸውም በረከት ለተራቡትና ለተፈናቀሉት እንዲለግሱ ሁሉም ወገኖች በሆነው በመጨረሻም ነገር ይብቃን ብለው ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲቀርቡ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ መልካም የጾመ ማርያም ሱባዔ ያድርግልን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን !!! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም.
Show all...