cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

ከመ/ገ/ጽ/ቅ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰንበት ት/ቤት ጋር በመሆን ☞ ዘወትር ረቡዕ ከ10:00 - 11:30 ☞ በመ/ገ/ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት አዳራሽ መንፈሳዊ ትምህርት የምንማማር ሲሆን ይህንን የተማሪዎች ጊቢ ጉባኤ አገልግሎት ለማጠናከር የተከፈተ የቴሌግራም ማኅበር ነው። @YeGibi_Gubae ✞ ኢንኅድግ ማኅበረነ ✞ አንድነታችንን አንተው

Show more
Advertising posts
1 635
Subscribers
-224 hours
+27 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰላም እንዴት አመሻቹ እንደሚታወቀው በ አሁኑ ረቡዕ ማለትም 14/09/16 ነገረ ክርስቶስን የሚያመለክት ቃለ መጠይቅ ነው እና ለእርሱ የሚሆኑ ጥያቄዎች እስከ ነገ(ሰኞ) ማታ ድረስ በ @bek1913 ከተማሪው ሰብስባቹም ሆነ ከራሳችሁ ሀሳብ እንድትልኩ ስል በ ልዑል እግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ
Show all...
👍 2 1
🔴አዲስ የትንሣኤ መዝሙር"ዛሬስ ትልቅ ደስታ ለእኛ ሆነልን"በዘማሪ ዲ/ን ያሬድ ንጉሤ https://youtube.com/watch?v=8_5FGMqGWoQ&si=kWvJMxOuiwGKRtm-
Show all...
🔴አዲስ የትንሣኤ መዝሙር"ዛሬስ ትልቅ ደስታ ለእኛ ሆነልን"በዘማሪ ዲ/ን ያሬድ ንጉሤ

👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
🕯 ዝክረ ቅዱስ ጊዮርጊስ 🕯         🎯      ቅዳሜ ግንቦት 3 2016 ዓ.ም.      🕰           ከ 6:00 - 8:00      🏤        በሰንበት ት/ቤቱ ሕንጻ    ሁላችንም ከጓደኞቻችን ጋር እንድንገኝ ስንል በአክብሮት በአክብሮት እንጠይቃለን። "ፍቅር ያጌብረኒ ከመእንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" የቅዱሳንን ዜና እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል።                           ✍አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ማኅበራችንን አንተው! @StGeorge_Gibi_Gubae በሰዓታችን እንገኝ!
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
++++++++++++++++++++++
የትንሣኤ ልዩ ጉባኤ
++++++++++++++++++++++ 📅ቀን  ረቡዕ ሚያዚያ 30/2016  ⌚ሰዓት 10:00-11:30 በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ   ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ የካቴድራል፣ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ ◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈ ያወቅነውን በማሳወቅ የበኩላችንን እንወጣ               share & join @StGeorge_Gibi_Gubae ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @YeGibi_Gubae ላይ ያናግሩን
Show all...
👍 2👏 1
ቀጤማ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ ዓዋዲ/ እየመቱ “ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ” የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቀጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቀጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ሲወስዱት በራሱ ላይ የእሾህ አክሊል  የደፉበት መሆኑን የሚያስታውስ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቀጤማ ተሸክመው፣ ቃጭል ሲያቃጭሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡        «ቄጠማ»፣ ለጥፋት ውሃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደሆነ ሁሉ በሐዲስ ኪዳንም በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ ስትል ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የሆነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሚያቃጥለው ዋዕየ ሲኦል /የሲኦል ቃጠሎ/ ወደ ልምላሜ ገነት ጥንተ ማኅደራቸው መመለሳቸውን በዚህ አኳኋን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም! "ያለ ደዌና ያለ ሕማም፥ ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ!" https://t.me/LetsknowtheEOTC https://t.me/StGeorge_Gibi_Gubae
Show all...
ተዋሕዶን እንወቅ።

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ሥረይ ለነ ኩሎ አበሳነ ኢታብአነ ውስተ መንሱት እግዚኦ አድህነነ እምዕለት እኪት ወባልሀነ ውስተ መንሡት። ✝በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ✝ የየእለቱን ስንክሳር፥ ውዳሴ ማርያም፥ ፀሎተ አርጋኖን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ የጻድቃንና የሰማእታትን ገድል፥ የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፥ የድሮ እና አዳዲስ መዝሙራትን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይቀላቀሉን።

🕊 2👍 1 1
#ቀዳም_ሥዑር ዕለተ ቅዳሜ እግዚአብሔር የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር የሚሄዱትን እና በክንፍ የሚበሩትን በባሕር የሚዋኙትን እንስሳትን በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈበት ዕለት ነች፡፡ ይህች የመጀመሪያው ቅዳሜ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት ናት። እግዚአብሔር ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ ስላረፈበት ሰንበት ዐባይ /ታላቋ ሰንበት/ ትባላለች። ታላቋን ሰንበት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት ታዟል(ዘፍ.፩፣፫)፡፡ ዕለተ ቀዳሚት /ሰንበት ዐባይ/ በዘመነ ሐዲስም የተለየ የደኅነት ሥራ ተከናውኖባታል፡፡ ጥንት ሥነ ፍጥረትን በመፍጠር ዕረፍት እንደ ተደረገባት ሁሉ የፍጥረት ሁሉ ቁንጮ የሆነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው ቸሩ መድኃኔዓለም በመቃብር ዐርፎባታል፡፡ ይኽች ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሰ መቃብር ዐርፎ የዋለባት ዕለት በመሆኗ «ቀዳሜ ስዑር » ትሰኛለች፡፡ ስዑር ቀዳሜ የተባለችው በዓመት አንድ ቀን ስለ ምትጾም ነው፡፡ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያምም ሆነች ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንሥተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውሃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረው አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡ ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ በቅብብሎሽ ከዘመናችን በደረሰው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በኀዘን፣ በጾምና በጸሎት ዕለቷ እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆች የተቻላቸው ሐሙስ ማታ ቀምሰው ከዓርብ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውሃ ሳይቀምሱ ያድራሉ። ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው ቅዳሜን በመጾም ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ በዚህ ዕለት ከሰኞ ከሆሣዕና ማግሥት ጀምረው እስከ ስቅለተ ዓርብ ድረስ በስግደት እና በጾም ያሳለፉ ምእመናን በዕለተ ቅዳሜ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ «ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፡-በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ» የምሥራች እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምእመናን ቄጠማ ይታደላል፤ ቄጠማው የምሥራች ምልክት ነው፡፡ ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖኅ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ሆነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውሃ ጠፍተዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዟቸው ከገባው እንስሳት መካከል የ ጥፋት ውሃን መጉደል ዓይታ እንድትነግረው ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ሰዷት ነበር። እርሷም በአፏ ቄጠማ  ይዛ ትመልሳለች (ዘፍ.9፣1-29)፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውሃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል፡፡ https://t.me/LetsknowtheEOTC https://t.me/StGeorge_Gibi_Gubae
Show all...
የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

ከመ/ገ/ጽ/ቅ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰንበት ት/ቤት ጋር በመሆን ☞ ዘወትር ረቡዕ ከ10:00 - 11:30 ☞ በመ/ገ/ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት አዳራሽ መንፈሳዊ ትምህርት የምንማማር ሲሆን ይህንን የተማሪዎች ጊቢ ጉባኤ አገልግሎት ለማጠናከር የተከፈተ የቴሌግራም ማኅበር ነው። @YeGibi_Gubae ✞ ኢንኅድግ ማኅበረነ ✞ አንድነታችንን አንተው

👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ፍቅርም እንደዚህ ነው ስለ ዐርብ ዕለት መስማትም መናገርም ማሰብም ጭምር ምን ያህል እንደሚከብድ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በቅዳሴው እንደገለጸው ዕለተ ዐርብን ማሰብ ይከብዳል። ዐርብ ከቀናት ሁሉ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ልዩ ቀን ናት። የሰው ልጅ የተፈጠረባት፣ ከገነት የወጣባት፣ ወደ ገነትም የተመለሰባት ይህች ልዩ ዐርብ ናት። ፍቅሩ እንደ ሰው ፍቅር ያይደለ ጌታችን ልጆቹ በተድላ ገነት ይመላለሱ ዘንድ በዛሬው ዕለት በመከራ መንገድ ተመላለሰ። የሰው ልጅ ከእስራቱ ነጻ ይወጣ ዘንድ እርሱ የታሰረበት፣ የሰው ልጅ የዳነ ይባል ዘንድ የሕማም ሰው የተባለበት፣ የሰው ልጅ በገነት መንግሥተ ሰማያት ያመሰግን ዘንድ እርሱ በምድር የተሰደበበት ቀን ነው። ክርስቶስ ለሰው ልጅ ያደረገውን ዘርዝሮ መጨረስ አይደለም ለመጀመር ይከብዳልና አንድ ጥያቄ ራሳችንን እንጠይቅ - እኛ ስለ ክርስቶስ የተቀበልነው መከራ ምንድን ነው? ስለ ክርስትናችንስ የተሸከምነው መስቀል ምንድን ነው? ይህንን ባናደርግ ክርስቶስ በቊጣው ከሚቀጣን ይልቅ በፍቅሩ የሚቀጣን ይበልጥብናል። እና ለአንተ ብዬ ጎኔን የተወጋሁ ስለ እኔ ብለህ ኃጢአትን አትተውምን? እኔ ለአንቺ ብዬ የተቸነከርኩ ስለ እኔ ብለሽ ትእዛዜን አትጠብቂምን? ቢለን መልስ ይኖረን ይሆን? እየገደልንህ እየወጋንህ የወደድከን ሆይ! ዕለት ዕለት ፍቅርህንና የከፈልክልንን ዋጋ እናስብ ዘንድ ማስተዋሉን አድለን!
Show all...
13👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
++++++++++++++++++++++
የሕማማት ልዩ ጉባኤ
++++++++++++++++++++++ 📅ቀን  ረቡዕ ሚያዚያ 16/2016  ⌚ሰዓት 10:00-11:30 በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ   ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ የካቴድራል፣ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ ◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈ ያወቅነውን በማሳወቅ የበኩላችንን እንወጣ               share & join @StGeorge_Gibi_Gubae ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @YeGibi_Gubae ላይ ያናግሩን
Show all...
🙏 2👍 1
​​🌷እንኳን አደረሳችሁ ለዐቢይ ጾም ሰባተኛው ሰንበት
              🌷ኒቆዲሞስ🌷 ➡️ የዐቢይ ጾም ሰባተኛው ሳምንት ኒቆዲሞ ይባላል። ስያሜውን ያገኘው እውነተኛ እውቀትንና ሕይወትን ፈልጎ ነገር ግን ምድራዊ ሥልጣኑን በአይሁድ ሸንጎ እንዳይነጠቅ ፈርቶ በሌሊት ወደ ጌታ  እየሄደ ይማር ከነበረው ከአይሁድ አለቃ ከኒቆዲሞስ ነው።
➡️ ዳግም ልደትን በተመለከተ ኒቆዲሞስ የጠየቀው ጥያቄና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመለሰው መልስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ላይ በሰፊው ተብራርቶ ተጽፏል።
➡️ ኒቆዲሞስ በፍርሃት ተውጦ እየተደበቀ በሌሊት ብቻ ኢየሱስ ክርስቶስን ሲከተለው የነበረ ሲሆን በኋላ በቃሉ ተመስጦና በፍጹም ፍቅሩ ተስቦ በድፍረት ተከትሎታል። የኢየሩሳሌም ሸንጎ ኢየሱስን ሊከሰው ሲፈልግ ኒቆዲሞስ ግን መከሰስ እንደሌለበት በድፍረት ሲመሰክር እናየዋለን (ዮሐ 7፥45-52)።
➡️ በተጨማሪም ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለ በኋላም ሌሎች ደቀ መዛሙርት በፍርሃት ተውጠው ሲሸሹ እርሱ ለመግነዝ የሚሆን   መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ በድፍረት በቦታው ሲገኝም እንመለከተዋለን (ዮሐ 19፥39)።
➡️ የዘለዓለም ሕይወትን መውረስ የሚፈልግ ሁሉ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ መወለድ እንዳለበት የዮሐንስ ወንጌል ምዕ 3 ያስተምረናል።
➡️ ክርስቶስ ” ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው ” ብሏል። የመጀመሪያው ልደት ከእናትና አባት ከሥጋ መወለድ ሲሆን ዳግም ልደት ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ የመወለድ ሚሥጢር ነው። ይህ ደግሞ በሰው ኃይል ሳይሆን በእግዚአብሔር ኃይል ነው የሚሆነው።
➡️ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ያስተማረው ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚገኝበት ዳግም ልደት ለእኛም ጭምር የተነገረ መሆኑን ከልብ ልናስተውል ይገባል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል  ሕያውና  ዘለዓለማዊ ነው።
➡️ ጠቅለል ባለ መልኩ ” ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው” (1ኛ ጢሞ 1፥15) ብሎ ሐዋርያው እንደተናገረው ክርስቶስ የከፈለልንን የደም ዋጋ ከልብ በማመንና ዘወትር ያለማቋረጥ ፍቅሩንና ቤዛነቱን በማሰብ በፍርሃትና በሌሊት ሳይሆን በፍጹም እምነትና በብርሃን  ልንከተለው ይገባል።
➡️ የዳግም ልደት ዋናው ጽንሰ ሃሳብም ለምድራዊው ሥልጣንና ሀብት ቅድሚያ በመስጠት በሥጋ ልደት ጸንቶ መኖር ሳይሆን ለዘለዓለማዊ ሕይወት ቅድሚያ በመስጠት ዳግም ከመንፈስ ቅዱስ  በመወለድ ሰማያዊ ዜግነትን ማግኘት ነው።
✍ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው የጸጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ሚሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!
Show all...
👍 5🙏 2
ረቡዕ ሚያዚያ 9/2016 ዓ.ም   የካቴድራል፣ ቅ/ማርያምና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ጊቢ ጉባኤ የ2016ዓ.ም.          Join and share👇    @StGeorgeGibi_Gubae
Show all...