cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Show more
Advertising posts
4 137
Subscribers
No data24 hours
+67 days
-2930 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
Media files
580Loading...
02
ረቡዕ –አልዓዛር አልዓዛር ክርስቶስ ያስነሣው የማርያምና የማርታ ወንድም ነው፤ የስሙም ትርጓሜ እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፲፩፥፯-፵፰)፤ አልዓዛር የሞተው መጋቢት ፲፯ ነበር፡፡ እህቶቹም ክርስቶስ እንዲመጣ መልእክት ልከውበት ነበር፤ ክርስቶስ ግን በ፬ኛው ቀን ማለትም  መጋቢት ፳ መጥቶ ከሞት አስነሥቶታል፤(ዮሐ.፲፩፥፵፬)፡፡ ፋሲካውንም በወዳጁ በአልዓዛር ቤት ያከብር ዘንድ  ከቀደ መዛሙርቱ ጴጥሮስንና ዮሐንስን አስቀድሞ ላከ፤ ከዚያም በአልዓዛር ቤት ሆኖ የሐዲስ ኪዳንን ሥርዓት ምሥጢረ ቁርባንን ሰርቶ ለደቀ መዛሙርቱ አሳያቸው፤ አልዓዛር ከተነሣ በኋላ በሐዋርያት ኤጲስ ቆጶስነት ተሸሞ ፵ ዓመት አገልግሎ ግንቦት ፳፯ ቀን ዐርፏል (ስንክሳር ግንቦት ፳፯)፡፡    ወስብሐት ለእግዚአብሔር https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw #ሼር
880Loading...
03
ማክሰኞ ቶማስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ትንሣኤው ሐዋርያት ተሰብስበው በነበረበት በዝግ ቤት ገብቶ ሲገለጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ ሐዋርያትም የጌታችንን ከሙታን ተለይቶ መነሣት ቢነግሩት ‹‹እኔ ሳላይ አላምንም›› አላቸው፡፡ በሚቀጥለው ሳምንትም ጌታችን ቶማስ በተገኘበት በድጋሜ  ተገለጠላቸው፡፡ ጌታችንም ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን ‹‹ጣትህን ወደዚህ አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን›› ብሎ በጦር የተወጋ ጎኑን ፥ በችንካር  የተቸነከረ እጁንና እግሩን እንዲዳስሰው በማድረግ ትንሣኤውን  አረጋገጠለት፡፡ ቶማስም ሲዳስሰው እጅ ከእሳት እንደገባ ጅማት ስለተኮማተረ ‹‹ጌታዬ አምላኬም›› ብሎ መሰከረ፡፡  በኋላ ግን ፈውሶታል፤ ኢየሱስም ‹‹ስለ አየኸኝ አምነሀል ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዐን ናቸው›› አለው፡፡  ምንም አንኳን ድርጊቱ የተፈጸመው በዳግም ትንሣኤ ቢሆንም የሐዋርያው መታሰቢያ ሆኖ ዕለተ ማክሰኞ ‹ቶማስ› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ (ዮሐ. ፳ ፥ ፳፬ -፴) ወስብሐት ለእግዚአብሔር
2816Loading...
04
Media files
2102Loading...
05
ሰኞ ማዕዶት ማዕዶት ማለት (ዐደወ-ተሻገረ) ከሚል የግእዝ ግስ የተወረሰ ሲሆን በጥሬው "መሻገር" ማለት ነው:: ይሕም በደመ ክርስቶስ ተቀድሰን: በትንሳኤውም ድኅነት ተደርጐልን መከራን: መርገምን: የኃጢአትን ባሕር: አንድም ባሕረ እሳትን መሻገራችንን ያመለክታል:: +ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ *ከባርነት ወደ ነጻነት *ከጨለማ ወደ ብርሃን *ከሞት ወደ ሕይወት *ከኃጢአት ወደ ጽድቅ *ከሲዖል ወደ ገነት *ከገሐነመ እሳት ወደ መንግስተ ሰማያት አዳምንና እኛን ልጆቹን አሸጋግሮናል:: +አባታችን አዳምና ልጆቹ ከሲዖል የወጡት በዕለተ ዐርብ በሠርክ ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚሕ ዕለት እዲታሰብ ታዛለች:: +ጌታችን ምርኮን ማርኮ: ጥጦስ መንገድ ጠራጊ ሆኖለት ወደ ገነት ሲያስገባቸው ለድንግል ማርያም አሳይቷታል:: እመ አምላክም በፍጹም ልቧ ደስ ተሰኝታለች:: አዳምና ልጆቹ እመቤታችንን ከላይ ሆነው እጅ ነስተዋታል:: እርሷ የድኅነታቸው ምክንያት ናትና:: =>አማናዊው ብርሃን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጨለማችንን በምሕረቱ ያብራልን:: =>+"+ ክርስቶስም እኮ ስለ ሰው ኃጢአት አንድ ጊዜ ሞቶአል:: ኃጢአት የሌለበት ክርስቶስ ጻድቁ ስለ እኛ ሞተ:: ስለ ኃጢአታችን እኛን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ:: በሥጋ ሞተ: በመንፈስ ግን ሕያው ነው:: ነፍሳቸው ታስራ ወደ ነበረችበት ሔደ:: ቀድሞ ክደውት ለነበሩት ነጻነትን ሰበከላቸው:: +"+ (1ጴጥ. 3:18)
3156Loading...
06
✞ ትንሣኤከ ለእለ አመነ ✞ ትንሳኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ከፈኑ ዲቤነ /2/        የትንሳኤው በጎል የሰው ልጆች ሂወት ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== የሲኦል መውጊያዋ ፍላፅው ተነስቷል የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነብሳቱን በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== ማርያም መቅደላዊት የጠራሽ በስምሽ በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ መላዕክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል የነገራችሁን እዩተሰ ተፈፅሟል በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== የሞት ሐይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አሌንታ እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው በትንሳኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== ለትንሳኤው ልጆች ለምናምን ለኛ ብርሐንን ላከልን ላይጨልም ዳግመኛ እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ❖ @meazahaymanot❖   ❖ @meazahaymanot ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
3183Loading...
07
***        እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም               አደረሰን! አደረሳችሁ! “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይዕዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሠላም፤ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ዲያብሎስን አሰረው፤ አዳምን ነጻ አወጣው፡፡ ሰላም! ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ኾነ፡፡
3246Loading...
08
Media files
50Loading...
09
Media files
3382Loading...
10
Media files
3122Loading...
11
#ምልጣን ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንሥአ #ክርስቶስ እሙታን : ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ : አማን ተንሥአ እምነ ሙታን። ድምጽ 🗣🔊 ዲያቆን ፍቅረ አብ ምንጭ :ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል @meazahaymanot
10Loading...
12
#ምስባክ ዘትንሣኤ (ዘማሕሌት) መዝ 77÷65 ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ። ድምጽ 🗣🔊ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል ወቲዩብ @meazahaymanot
10Loading...
13
Media files
10Loading...
14
Media files
10Loading...
15
Media files
10Loading...
16
Media files
10Loading...
17
ሥርዓተ ማኅሌት ዘበዓለ #ትንሣኤ ደወል እንደተደወለ ከሁሉ አስቀድሞ ነቢያት ከዛሙ ሙሉ የዮሐንስ ወንጌል ይነበባል! ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል። "ተፈሥሂ #ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል : መልክዐ ስዕል ግን ዛሬን ጨምሮ እስከ በዓለ ፶ ፍጻሜ ድረስ አይባልም። ከእላይ አለላቹ ፈልጉ ወደ እላይ ለቅቄላችኋለሁ! ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል : ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና አራቱም ወንጌላት ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል። ይ.ዲ #ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭ ወተንሥአ #እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ። #አርያም ሃሌ ሉያ #ለአብ : ሃሌ ሉያ #ለወልድ : ሃሌ ሉያ #ወለመንፈስ_ቅዱስ : ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ ትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ ዛቲ #ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ። ሃሌ ሉያ #ለአብ : ሃሌ ሉያ #ለወልድ : ሃሌ ሉያ #ወለመንፈስ_ቅዱስ : ይገብሩ በዓለ ደመናት : ወምድርኒ ትገብር #ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። #ምልጣን ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንሥአ #ክርስቶስ እሙታን : ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ : አማን ተንሥአ እምነ ሙታን። አመላለስ፦ 'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪//፩/ ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/ ወረብ፦ ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/ #እስመ_ለዓለም ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ። አመላለስ፦ ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/ ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/ ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ "ይእቲ #ማርያም" የሚለው የኪዳን መግቢያ ይዘመማል ፣ ይመረገዳል። አመላለስ፦ ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ/፬/ #መዝሙር ትትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር : ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ : ወይበውኡ አድባር ወአውግር : ወኲሉ ዕፀወ ገዳም : ወዮምሰ አባይ ፍሥሃ በሰማያት : ወምድርኒ ትገብር #ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። አመላለስ፦ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ፤/2/ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ/4/ #ሰላም ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ : ተካፈሉ አልባሲሁ : ሐራ ሰገራት ወኮርዕዎ ርእሶ በሐሰት : ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት : ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት : ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት ለአሕዛብ ወለበሐውርት። አዘጋጅ ✍#ዲያቆን ፍቅረ አብ https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw #subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 💛 @meazahaymanot   💚 💛 @meazahaymanot    💚 💛 @meazahaymanot  💚 💙💙💙💙💙💙💙💙💙      🙏join👍
3183Loading...
18
https://youtu.be/sBdqfj2u034?si=PDfA6bVxEgcLwXHB
3151Loading...
19
ቀዳም ስዑር ቅዳሜ፡– ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር  ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡   ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡   የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ ምእመናን ሆይ፣ በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓተ መላእክት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የዕለታቱን ክብርና ስያሜ ከማወቅና ከመረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃይማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡       እንበለ ደዌ ወሕማም    እንበለ ፃማ ወድካም   አመ ከመ ዮም   ያብጽሐኒ ያብጽሐክሙ ለብርሃነ ትንሳኤ  እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም
4125Loading...
20
Media files
3616Loading...
21
ኦ ዘጥዑመ ሞተ በሥጋ ኦ ዘጥዑመ ሞተ በሥጋ https://youtu.be/E2i9BlYYdVU?si=ZCLIsFQT1xFNxdvj
4121Loading...
22
ጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ሐሙሰ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ስያሜ ያለው ነው፡፡ ይህም ምክንያቱ በዕለቱ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የተገለጠበት ስለሆነ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህን በሚዘክር ሁኔታ ታስበዋለች፡፡ ምን ተፈጸመ? በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ እለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡ ሌላው በዚህ ዕለት የተፈጸመው ተገባር ሕጽበተ እግር ነው፡፡ወንጌሉ እንዲህ ይላል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ዐሳብ ካገባ በኋላ ኢየሱስ ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡”�/ዮሐ.13፥1-10/ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ሊከላከል ሞከረ፤ ጌታችን እንዲህ አለው “እኔ የማደርገውን አሁን አንተ አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው” /ዮሐ.13፥10/፡፡ ጴጥሮስ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም ባለው ጊዜ የጌታችን መልስ ይህ ነበር “ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም”� በዚህም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶሰ አንድ ደቀ መዛሙርቱን ሥርዓተ ጥምቀት ፈጸመ ሁለተኛ በቃል ያስተማረውን ትኅትና በተግባር ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሮል፡፡ “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሁት ነኝና” እንዲል /ማቴ. 11፥29/፡፡ ይህንም ሲፈጽም አሳልፎ ሊሰጠው ያለውን የአስቆሮቱን ይሁዳ አለየውም፡፡ ሌላው በዚህ ዕለት ይሁዳ አሳልፌ እንደሚሰጠው ተናገረ በዚህም ማንነቱን ጭምር ለይቶ ነገራቸው፡፡ እንዲህም ብሎ “እጁን በወጭቱ ያጠለቀው እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ነው” በዚህ ዕለትም የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ የተቀበለልን የእኛን ሥጋ የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፥36-46፣ ዮሐ.17/   ጸሎተ ሐሙስ ስያሜዎች የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይለምን የነበረን ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፤36-46፣ ዮሐ.17/ በዚህም ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሕጽበተ እግር ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ወንጌሉ እንደሚል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ዐሳብ ካገባ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡” /ማቴ.26፥27/  የምሥጢር ቀን በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዮ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ የምሥጢር ቀን ይባላል፡፡ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ የሆነውን የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት የመሠረተበት ነው፡፡ ቀድሞ የነበረውን መስዋዕተ ኦሪት ሽሮ የሐዲስ ኪዳን ደምና ሥጋውን ፈትቶ ስላቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡ /ሉቃ.22፥20/ የነጻነት ሐሙስ በመብል ያጣውን ክብር በመብል የመለሰበት ዕለት በመሆኑ   ጌታችን በሰጠን ሥልጣን  ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡ የትንሣኤውን ብርሃን ለማየት ያብቃን አሜን!!
4875Loading...
23
ረቡዕ ምክረ አይሁድ ይባላል፦የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል።ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው።ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ 22÷1-6 ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡-ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ 26÷6-7 የመዓዛ ቀን ይባላል። የእንባ ቀን ይባላል፡-ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር 14÷9 የእንባ ቀን ይባላል። መልካም ሰሞነ ሕማማት
4916Loading...
24
Media files
4860Loading...
25
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ ማቴ.21÷23-25፤ ማር.11÷27፣ ሉቃ.20÷1-8፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡ ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ በአንድ አገር የንግድ ቦታን የሚያጸድቅ መንግሥት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡት ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አልመለሰም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሷል፡፡ “በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ፤ በማን ሥልጣን ነው ይህን የምታደርገው?” ነበር ያሉት፡፡ በራሴ ሥልጣን ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡ ጌታችን እኩይ የሆነውን የፈሪሳውያንን አሳብ በመረዳት “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር ሲል” ጠይቋቸዋል፡፡ ከሰማይ ያልነው እንደ ሆነ ለምን አላመናችሁበትም ይለናል÷ ከሰው ያልነው ከሆነ ሕዝቡ ይጣላናል፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ከዚህ የተነሣ ያቀረቡት የፈተና ጥያቄ ግቡን ሳይመታ ከሽፎባቸዋል፡፡ ማቴ.21÷25፤ ማር.11÷27-30፤ ሉቃ.20÷1-8፡፡ ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡፡ ለብርሃነ ትንሣኤው አምላካችን በሰላም ያድርሰን፡፡ ይቆየን፡፡
4963Loading...
26
Media files
4371Loading...
27
. ዕለተ ሰኑይ ሀ. አንጽሖተ ቤተ መቅደስ፡- በዚች ዕለት መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፡፡ በዚያም በደረሰ ጊዜ ቤተ መቅደሱ የጸሎት የመሥዋዕት ቤት መሆኑ ቀርቶ የንግድ ቤት ሆኖ ቢያገኘው ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው ገርፎም አስወጣቸው፡፡ ይኸውም የእርሱ ቤተ መቅደስ የሆነውን ሰውነታችንን ኃጢአት ሰፍኖበት ቢያገኘው ራሱ ተገርፎ ተገፍፎ መከራ መስቀልንም ሁሉ ተቀብሎ ከሰውነታችን ኃጢአትን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ (ሉቃ.፲፱፥፵፮)   ለ. መርገመ በለስ፡- ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግስቱ ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፤ በመንገድም ሲያልፍ ቅጠል ያላት በለስን ከሩቁ ተመለከተ፡፡ ወደ በለሲቱም በቀረበ ጊዜ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ያንጊዜም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር›› ሲል በለሲቱን ረገማት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ይህንን ሰሙት፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት በለሲቱ የተረገመችባት ቀን ናትና መርገመ በለስ ተብላ ትጠራለች፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩-፲፬) በዚህ አገላለጽ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ስትሆን ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባር ነው፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈልጎ አላገኘባቸውም፡፡ እስራኤል፦ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም ዘር መባልን እንጂ የአብርሃምን ሥራ በመሥራት በምግባር በሃይማኖት ጸንተው መኖር አይፈልጉምና ደግ ሰው አልተገኘባቸውም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡፡ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛትም አማናዊ ድኅነትን የምታሰጥ ሆና አላገኛትም፡፡ ይሁን እንጂ በእርሷ ድኅነት ባይገኝባትም ‹‹ኦሪትና ነቢያትን ከመፈጸም በቀር ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ›› በማለት ሕገ ኦሪትን ፈጽሟታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በለስ የተባለች ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አግኝቷታል፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በአንቺ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ሲል ነው፡፡ በለሲቱ ስትረገም ፈጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ያገኘን በደል በእርሱ እንደጠፋልን ለመግለጽ ነው፡፡ መልካም ሰሞነ ሕማማት
5502Loading...
28
Media files
5554Loading...
29
ኦ ዘጥዑመ ሞተ በሥጋ ኦ ዘጥዑመ ሞተ በሥጋ https://youtu.be/E2i9BlYYdVU?si=ZCLIsFQT1xFNxdvj
5033Loading...
30
ስለማኅበሩ ሐሳብ አስተያየት ከአላችሁ በውስጥም ሆነ በዚሁ ጻፉልን
4430Loading...
31
Media files
4961Loading...
32
Media files
4991Loading...
33
Media files
4310Loading...
34
✞ ሆሣዕናችን ጌታ ኢየሱስ ✞ የሰላም ንጉሥ በአህያ ላይ በኢየሩሳሌም ታየ ፀሐይ ደዌን ሊሸከም ሊያድለን ፈውስ ሆሣዕናችን ጌታ ኢየሱስ ዘንባባን ይዘው በእጃቸው ቅኔን ሊዘራ ልሳናቸው የምስጋና አምላክ በእልልታ ኢየሩሳሌም ገባ ጌታ /አዝ = = = = = ጽዮን ከተማ ተደሰተች ንጉሥ ሲመጣ በዓይኗ እያየች ድኀነትሽ ቀርቧል ሰላምሽ ሐሴት አድርጊ በሕዝብሽ   /አዝ = = = = = የኪሩቤልን ድንቅ ሥራ ታየች አህያ ስትሰራ ዙፋን ሆናለች ለንጉሡ ከውርንጫ ጋር በመቅደሱ   /አዝ = = = = = ከፊት ሲቀድሙ ሲከተሉ በምስጋና ቃል እልል ሲሉ አነጠፋለት ልብስን በምድር ለአንተ ይገባል ሲሉ ክብር   /አዝ = = = = = ድንጋይ ጀመረ ቅኔ መዝሙር እንደ መላእክት ሲሰጥ ክብር ከየት አገኘው አንደበትን ብሎ የጮኸው አሁን አድን   /አዝ = = = = = ከፊት ሲቀድሙ ሲከተሉ በምስጋና ቃል እልል ሲሉ አነጠፋለት ልብስን በምድር ለአንተ ይገባል ሲሉ ክብር 👉ሊቀመዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
4732Loading...
35
Media files
4482Loading...
36
https://vm.tiktok.com/ZMMgUHpGm/
5211Loading...
37
የማኅበሩ አባል መሆን የምትፈልጉ ኦርቶዶክሳውያን ወንድም እህቶቻችን ይኸን ፎርም በመሙላት አባል መሆን ትችላላችሁ https://docs.google.com/forms/d/1LnRCOLLvC80rbdC-GjYgyEBVnYcUYJBcdFoBKu5ho7Q/edit#responses
4850Loading...
38
ይኸ ቤተክርስቲያን የት ይገኛል ስሙንና ቦታውን ጻፉ
5931Loading...
39
Media files
7211Loading...
ረቡዕ –አልዓዛር አልዓዛር ክርስቶስ ያስነሣው የማርያምና የማርታ ወንድም ነው፤ የስሙም ትርጓሜ እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፲፩፥፯-፵፰)፤ አልዓዛር የሞተው መጋቢት ፲፯ ነበር፡፡ እህቶቹም ክርስቶስ እንዲመጣ መልእክት ልከውበት ነበር፤ ክርስቶስ ግን በ፬ኛው ቀን ማለትም  መጋቢት ፳ መጥቶ ከሞት አስነሥቶታል፤(ዮሐ.፲፩፥፵፬)፡፡ ፋሲካውንም በወዳጁ በአልዓዛር ቤት ያከብር ዘንድ  ከቀደ መዛሙርቱ ጴጥሮስንና ዮሐንስን አስቀድሞ ላከ፤ ከዚያም በአልዓዛር ቤት ሆኖ የሐዲስ ኪዳንን ሥርዓት ምሥጢረ ቁርባንን ሰርቶ ለደቀ መዛሙርቱ አሳያቸው፤ አልዓዛር ከተነሣ በኋላ በሐዋርያት ኤጲስ ቆጶስነት ተሸሞ ፵ ዓመት አገልግሎ ግንቦት ፳፯ ቀን ዐርፏል (ስንክሳር ግንቦት ፳፯)፡፡    ወስብሐት ለእግዚአብሔር https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw #ሼር
Show all...
ማክሰኞ ቶማስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ትንሣኤው ሐዋርያት ተሰብስበው በነበረበት በዝግ ቤት ገብቶ ሲገለጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ ሐዋርያትም የጌታችንን ከሙታን ተለይቶ መነሣት ቢነግሩት ‹‹እኔ ሳላይ አላምንም›› አላቸው፡፡ በሚቀጥለው ሳምንትም ጌታችን ቶማስ በተገኘበት በድጋሜ  ተገለጠላቸው፡፡ ጌታችንም ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን ‹‹ጣትህን ወደዚህ አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን›› ብሎ በጦር የተወጋ ጎኑን ፥ በችንካር  የተቸነከረ እጁንና እግሩን እንዲዳስሰው በማድረግ ትንሣኤውን  አረጋገጠለት፡፡ ቶማስም ሲዳስሰው እጅ ከእሳት እንደገባ ጅማት ስለተኮማተረ ‹‹ጌታዬ አምላኬም›› ብሎ መሰከረ፡፡  በኋላ ግን ፈውሶታል፤ ኢየሱስም ‹‹ስለ አየኸኝ አምነሀል ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዐን ናቸው›› አለው፡፡  ምንም አንኳን ድርጊቱ የተፈጸመው በዳግም ትንሣኤ ቢሆንም የሐዋርያው መታሰቢያ ሆኖ ዕለተ ማክሰኞ ‹ቶማስ› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ (ዮሐ. ፳ ፥ ፳፬ -፴) ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Show all...
👍 4
ሰኞ ማዕዶት ማዕዶት ማለት (ዐደወ-ተሻገረ) ከሚል የግእዝ ግስ የተወረሰ ሲሆን በጥሬው "መሻገር" ማለት ነው:: ይሕም በደመ ክርስቶስ ተቀድሰን: በትንሳኤውም ድኅነት ተደርጐልን መከራን: መርገምን: የኃጢአትን ባሕር: አንድም ባሕረ እሳትን መሻገራችንን ያመለክታል:: +ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ *ከባርነት ወደ ነጻነት *ከጨለማ ወደ ብርሃን *ከሞት ወደ ሕይወት *ከኃጢአት ወደ ጽድቅ *ከሲዖል ወደ ገነት *ከገሐነመ እሳት ወደ መንግስተ ሰማያት አዳምንና እኛን ልጆቹን አሸጋግሮናል:: +አባታችን አዳምና ልጆቹ ከሲዖል የወጡት በዕለተ ዐርብ በሠርክ ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚሕ ዕለት እዲታሰብ ታዛለች:: +ጌታችን ምርኮን ማርኮ: ጥጦስ መንገድ ጠራጊ ሆኖለት ወደ ገነት ሲያስገባቸው ለድንግል ማርያም አሳይቷታል:: እመ አምላክም በፍጹም ልቧ ደስ ተሰኝታለች:: አዳምና ልጆቹ እመቤታችንን ከላይ ሆነው እጅ ነስተዋታል:: እርሷ የድኅነታቸው ምክንያት ናትና:: =>አማናዊው ብርሃን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጨለማችንን በምሕረቱ ያብራልን:: =>+"+ ክርስቶስም እኮ ስለ ሰው ኃጢአት አንድ ጊዜ ሞቶአል:: ኃጢአት የሌለበት ክርስቶስ ጻድቁ ስለ እኛ ሞተ:: ስለ ኃጢአታችን እኛን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ:: በሥጋ ሞተ: በመንፈስ ግን ሕያው ነው:: ነፍሳቸው ታስራ ወደ ነበረችበት ሔደ:: ቀድሞ ክደውት ለነበሩት ነጻነትን ሰበከላቸው:: +"+ (1ጴጥ. 3:18)
Show all...
✞ ትንሣኤከ ለእለ አመነ ✞ ትንሳኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ከፈኑ ዲቤነ /2/        የትንሳኤው በጎል የሰው ልጆች ሂወት ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== የሲኦል መውጊያዋ ፍላፅው ተነስቷል የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነብሳቱን በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== ማርያም መቅደላዊት የጠራሽ በስምሽ በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ መላዕክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል የነገራችሁን እዩተሰ ተፈፅሟል በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== የሞት ሐይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አሌንታ እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው በትንሳኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== ለትንሳኤው ልጆች ለምናምን ለኛ ብርሐንን ላከልን ላይጨልም ዳግመኛ እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ❖ @meazahaymanot❖   ❖ @meazahaymanot ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram