cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Show more
Advertising posts
4 138Subscribers
-324 hours
-127 days
-3830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የማኅበሩ አባል መሆን የምትፈልጉ ኦርቶዶክሳውያን ወንድም እህቶቻችን ይኸን ፎርም በመሙላት አባል መሆን ትችላላችሁ https://docs.google.com/forms/d/1LnRCOLLvC80rbdC-GjYgyEBVnYcUYJBcdFoBKu5ho7Q/edit#responses
Show all...
የማኅበረ መዓዛ ሃይማኖት የአባልነት መሙያ ቅጽ

ሙሉ ስም

ይኸ ቤተክርስቲያን የት ይገኛል ስሙንና ቦታውን ጻፉ
Show all...
አቤቱ ___ብትጠባበቅ አቤቱ ከፊትህ ማን ይቆማልAnonymous voting
  • ምሕረት
  • ኃጢአትን
  • ፍርድን
  • ቃል
0 votes
3
ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን እንዴት አደራችሁ ወንድም እህቶቻችን ህብረታችን እጅግ ያስቀናል በ ትንሽ ቀናት ዉስጥ እጣን ጧፍ ሻማ ለ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ አስገብተናል ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን🙏🙏🙏 8 ኪሎ እጣን 7 ፓኮ ሻማ 4 ፍሬ ባለ ቀለሙ ሻማ 4 ኪሎ ዘቢብ 3 ሙሉ ጧፍ የአምስቱ ልዑካን ልብሰ ተክህኖ አምላከ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የተመሰገ ይሁን
Show all...
ኒቆዲሞስ የዐብይ ሰባተኛ ሰንበት !! ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ ፩–፪) በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር ”አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሳ መርምርና እይ“ አሉት እንጂ አልተቀበሉትም። ዮሐ ፯፥፵፰–፶፪። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ”ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ። ዮሐ ፲፱፥፴፱። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል። የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ­ የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ ዮሃ ፫፤፪ ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው በሌሊት ወደ ጌታ እየሄደ ይማር ነበር ኒቆዲሞስ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ ? ፩/ ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ስማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴ ከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል ብሎ ነው እኛስ ዛሬ የዘላለም ህይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃል ብትህትና መማር ሲገባን ለምድራዊ ክብር ብለን በቀን ጊዜያችን መማር ያልቻልን ስንቶቻችን ነን ስለዚህ ቀን ጊዜአችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል። ‹ ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና › ዮሃ ፱፤፬ ፪/ .ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር እኛስ ዛሬ ልባችን የተረዳውን እውነት በግልጥ እንዳንፈጽም በፍራቻ በይሉኝታ የምንሰውር ስንቶቻችን ነን ‹ፍጹምፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና› ፩ዮሃ ፬፤፲፰ ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል። ፫/ ኒቆዲሞስ ከቀን ልብ ይልቅ የሌሊት ልብ የተካተተ ስለሆነ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር የሰማነው ቅዱስ ቃል በህይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብⶀል ‹ በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው› ማቴ ፲፫፡፳፫
Show all...
👍 2
ስለ ቅድስት አርሴማ ስለ ቅድስት በርባራ ስለ ቅድስት ሉሲያ ስለ ቅድስት ኡሊያና ስለ ቅድስት ካትሪን ስለ ቅድስት ኬርያኬ ታሪክ  ተዘጋጁ ተብሎ ነበር  በዝምታ ይሆን ? ቅን ልብ ይኑረን ለመማር ለማወቅ እንፈልግ
Show all...
"እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው" ኦሪት ዘፍጥረት 30÷30 ቅድስት ቤተክርስቲያን  ልጆቼ እርዱኝ ትላለች። የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅዱሳን      ዋጋቸው 1 ኪሎ እጣን                         600 ብር 2ኪሎ ዘቢብ 900 ብር   እነዚህን በመርዳት  ስማችንን በሰማይ በሕይወት መዝገብ እናስመዝግብ አንድ ጧፍ ለእኛ 5 ብር ነው ለገጠር ቤተክርስቲያን ግን የአንድ ቀን ቅዳሴ ማስቀደሻ ነው ። እናስብበት   በውስጥ ማናገር የምትፈልጉ ማናገር ትችላላችሁ ቅን ልብ ይኑረን
Show all...
የጨለማውን ግርማ ገፎ ብርሃንን ላሳየን የድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይሁን
Show all...