cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓቱን የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረባት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።

Show more
Advertising posts
711Subscribers
No data24 hours
-57 days
-2130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ፈጣሪ አለልን !🙏 ፈጣሪ አይተውም ቀን አለው እየሆነ ስላለው ስለሚሆነው ስለሆነውም ሁሉ የእርሱ መልካም ፍቃድ ከጎናችን ነው ትቶን የማያውቅ መቼም አይተወንም ! የተባረከ ቀን 😍
Show all...
🌺 ሃሌ ሉያ አንተ ሰው ሆይ ¯¯¯¯¯ ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ (4) ቡሄ መድረሱን ሰምተሃል ወይ ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ መስማቱንማ ሰምቼ ነበር ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ ከዚያ ቢያደርሰኝ ልዑል እግዚአብሔር ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ •••• እናቴ ሆይ............ሆ ይህን ባየሻ ..........ሆ በቁርማ ዳቦ ........ሆ ሲጥለኝ ውሻ........ሆ ደጓ ጫማዋን ......ሆ አውልቃዋለች.......ሆ ውሃ ሲጠማ.........ሆ አጠጥታዋለች......ሆ የስዋ ውዳሴ .......ሆ ሆኖኛል ውይን ...ሆ ዘሬም ብዘምር ....ሆ እኖራለሁኝ .........ሆ ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4) •••• በእምነት እንውጣ .ሆ ከተራራው ላይ......ሆ ይታይ ብርሃኑ........ሆ ክብሩ ኤልሻዳይ....ሆ ሙሴን እንጠይቅ...ሆ የጥንቱን ነገር .......ሆ ምን እንደሚለው ...ሆ ጌታን ሲያናግር......ሆ ድምጹን እንስማ ....ሆ እንደ ትሁትነቱ.......ሆ እንቀበለው ..........ሳ እኛም በትሩን .......ሆ ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (2) ተቁኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2) •••• ተራራውማ ..........ሆ ነውና አምሳል.......ሆ ለቤተ ክርስቲያን...ሆ መንበረ ልዑል......ሆ ወጥተን እንጠይቅ.ሆ ኤልያስን ..............ሆ እንድንዳስሰው......ሆ ጸጓራር ክንዱን.....ሆ ሰማይ በትለጉም...ሆ ባህር ቢከፍል.......ሆ እሳት ብታወርድ....ሆ ጠላትም ቢርድ.....ሆ በሰረገላ ..............ሆ የተነጠከው.........ሆ ይህ ሁሉ ክብር ....ሆ በማን ስልጣን ነው..ሆ ለሁላችን መልካም ነው በዚህ መኖር(4) •••• የእመብርሃን .........ሆ የምዬ ልጅ............ሆ ተጥሎ ላይቀር .....ሆ ተረስቶ ደጅ...........ሆ ሰአሊ ለነ .............ሆ ባለበት አፉ...........ሆ የጭንቁን እለት......ሆ ተሰብሮ ሰልፉ.......ሆ እንዳባቶቹ ...........ሆ ቅኔን ተቀኘ...........ሆ ድንግል ስትረዳው....ሆ አይኑ ስላየ..............ሆ ተፈስሂ ደብረ ታቦር (2) ተፈስሂ አርሙኒየም (2) ባንቺ ላይ ታየ እግዚአብሔር ተፈስሂ አርሙንየም •••• ሙሴ ስላለ ............ሆ መና ያውርዳል........ሆ ቅዱስ ኤልያስ.........ሆ ስጋ ያመጣል..........ሆ ዮሃንስንም............ሆ ጌታ ይወዳል.........ሆ መድኃኒታችን........ሆ ፈውስ ይሆነናል.....ሆ በዚህ እንድንኖር ...ሆ ዳሱን ጥለናል .....ሆ ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4) •••• አባቴም ቤት..........ሆ አለኝ ለከት............ሆ እናቴም ቤት .........ሆ አለኝ ለከት...,........ሆ ፍልሰታ ስትሆን....ሆ የቆምኩባት...........ሆ በድብረ ታቦር ......ሆ ያጌጥኩባት...........ሆ ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ(2) ተቀኙለት  በልልታ ላዳኙ ጌታ(2) •••• አመት አውዳመት "ድገምና" አመት "ድገምና" ያባብዬን ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና" ይግባ በረከት "ድገምና" አመት "ድገምና" የማምዬ ቤት "ድገምና"  አመት "ድገምና" ይትረፍረፍ በእውነት "ድገምና" አመት "ድገምና" ነሩ በሀይማኖት ጽኑ በጸሎት  በተዋህዶ ቤት(4) •••• የሰማይ ሰራዊት "በእምነት" ያድርጋችሁ "አሜን" አማኑኤል በጸጋ "በእምነት" ያኑራችሁ "አሜን" ከስጋ ወደሙ "በእምነት" ያድላችሁ "አሜን" ዘርን እደ አብርሃም "በእምነት" ያብዛላችሁ "አሜን" ይባረክ በእግዚአብሔር በእምነት ዘመናችሁ  "አሜን"/2/ እድሜና ጤናውን በእምነት ያድላችሁ "አሜን" (2) •••• መዝሙር በዘማሪ ይገረም ደጄኔ •••• ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
Show all...
#ገብርኤል_ሀያል ገብርኤል ሀያል መላከ ሰላም መላከ ብስራት የምታወጣ የእግዚአብሔርን ህዝብ ከሚነድ እሳት ፍቅርህ ተስሉዋል በልባችን ፊትህ ቆመናል ባርከን ብለን የፅናታቸው ዝናው ሲሰማ ከዚያች ቢያብሎን ከሞት ከተማ ህፃናት ሳሉ በራ እምነታቸው ቁመህ ተገኘህ መሀከላቸው አዝ ውሀው ሲዘልል ቢያስደነግጥም በጋኖቹም ውስጥ ቢነዋወጥም ፀንተው ዘመሩ ልጅና እናቱ አንተ ስትደርስ ከዚያ ከሳቱ አዝ ቂርቆስም ፀና ሞትን ሳይፈራ አንተ ስላለህ ከነርሱ ጋራ አትፍሪ አላት ስለምን ትፍራ አምነው ድል ነሱት ያንን መከራ አዝ~~ እኔም አምናለው አድነኝ ብዬ ቆመህ አማልደኝ ከቸር ጌታዬ ክፉውን ዘመን የማልፍበት ፅናትን ስጠኝ ድል ልንሳበት
Show all...
እንደ ሶስቱ ህፃናት ቂርቆስ በረታ በእቶን እሳት ውስጥ ገባ እናቱንም መራት ወደ ገነት የሶስት ዓመት ሕፃን ቂርቆስ ሰማዕት እኛ ልጆቹ ምልጃውን አምነን ጌታን አክብሮ ለሰበሰበን በማሕቶት በጸዳል ያየው በሠረገላ ስጋው ያረገው ቂርቆስ(3) ሕፃን አማልደን እኛን ልጆችህን(2) አንጌቤናዊው በሮም ከተማ በሕፃን አንደበት ድምፅህ ተሰማ መልክና ውበትህ ቂርቆስ ደም ግባትህ በንጉሱ ፊት አንተን ሊያስወድድህ ልጅ እንድትሆነው ንግስናን ሰጥቶ ለጣዖት ስገድ ብሎ ማለደ ቂርቆስ ከፈጣሪዬ ቂርቆስ ከአምላኬ በቀር ቂርቆስ አትስገድ ተብሎ ቂርቆስ ተጽፎ ነበር ቂርቆስ ብለህ ነገርከው ቂርቆስ ለእስክንድርዮስ ቂርቆስ በሕፃን አንደበት ቂርቆስ ወንጌልን ሰበክ ቂርቆስ ቂርቆስ (3) ሕፃን አማልደን እኛን ልጆችህን(2) አትፍሪ አልካት እናትህን ነጎድጓድ ድምጹ ሲያርድ ልቧን ጸለይክ ወደ አምላክ በቅን ልቦና ያበረታት ዘንድ ቀና አልክና ፍሬው ያለ ግንድ እንዴት ይሆናል አንተም አበርታት ልቧም ይጸናል ቂርቆስ የእናትህን ቂርቆስ ጣቶቿን ይዘህ ቂርቆስ እየመራሃት ቂርቆስ ገባህ ወደ እሳት ቂርቆስ ለእናትህም ቂርቆስ አባት ሆነሃት ቂርቆስ እሳቱ ሳይሆን ቂርቆስ ገነትም ታያት ቂርቆስ ቂርቆስ (3) ሕፃን አማልደን እኛን ልጆችህን(2) የራማው መልዓክ ገብርኤል መጣ ከእቶን እሳት አንተን ሊያወጣ ከጸጉርህ ጫፎች ሳይቃጠሉ ገብርኤል ገባ ከነበልባሉ ነጎድጓድ ዲኑ ስለ በረደ ንጉስ አፈረ ልብሱን ቀደደ ቂርቆስ በእምነት ጽናት ቂርቆስ ያንተ ብርታት ቂርቆስ ዛሬም ያበራል ቂርቆስ በእኛ ሕይወት ቂርቆስ በቃልኪዳንህ ቂርቆስ በፍቅርህ ቂርቆስ እንኖራለን ቂርቆስ በአንተ ቤተ መቅደስ ቂርቆስ ቂርቆስ (3) ሕፃን አማልደን እኛን ልጆችህን(2) ብላቴናው የሶስት ዓመቱ ሆነ ሰማዕት ቂርቆስ ከእነ እናቱ በሮም ከተማ ደምህ ሲፈስ አንገትህን ሰጥተህ እንደ ጳውሎስ ደም እና ውሃ ፈሰሰ ወጣ ቃሉን በእምነት ፈጽመህ ጸናህ ቂርቆስ በጥር 15 ቂርቆስ በማለዳው ቂርቆስ ስጋህ አረፈ ቂርቆስ በሰረገላው ቂርቆስ ረሀብ ጥማቱ ቂርቆስ ክፉ ቁራኛ ቂርቆስ እንዳይደርስብን ቂርቆስ ለመንክ ለእኛ ቂርቆስ
Show all...
❖ ወዳጅ_ነህ_ለሁሉ ❖ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ ዛሬም ቆመሀል በኪዳንህ ላሉ ክንፍህን ዘርጋ ሚካኤል ቅደም ከፊቴ ምራኝ መንገዴን እንዳይመሽ ልድረስ ካባቴ እንዴት ይገፋል ጎዳናው ካላንተ እርዳታ ጥሜን ቁረጠው በበትርህ ጭንጫውን ምታው (2) ተጠመጠመ ጠላቴ በእሳት ሰንሰለት የጌታ መልአክ ሚካኤል በሰይፍ ወድቆበት የለም ከቦታው ስመለስ አጥቼዋለው የሚረዳኝን ተሹሞ አይቼዋለው (2) ከመቃብሩ ድንጋዩን አንከባለሀል ስለረዳኸዉ ዳንኤል እጅግ ወዶሀል ይነዋወፃል ባህሩ አንተ ስትመጣ እግዚአብሄር ይንገስ ዳቢሎስ መድረሻ ይጣ (2) አለኝ ትዝታ በቤትህ ከልጅነቴ ስትሳሳልኝ እያየው ፀንቷል ጉልበቴ ልዘምር እንጂ ላመስግን ታላቁን ጌታ አንተን የሰጠኝ ጠባቂ በቀን በማታ (2)
Show all...
ጾመ ሐዋርያት 📖ጾመ ሐዋርያት በወርኃ ሰኔ ስለሚጾም በምእመናን ዘንድ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፤ ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማትም አንዱ ነው፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ 📖ይህም ጾም ከበዓለ ኀምሳ በኋላ የሚጾም ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ቅዱሳን ሐዋርያት በጸሎት ይተጉ ወደ ነበረበት ቤት በመሄድ ደቀመዛሙርቱን ይዟቸው ከቤት በመውጣት መንገድ ጀመረ፡፡ እርሱ ከፊት እየመራቸው እነርሱ እየተከተሉት ወደ ረጅሙና በረጃጅም ዛፎች ወደ ተሞላው ደብረ ዘይት ተራራ ይዟቸው ወጣ፡፡ ይህንንም እየነገራቸው ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ፤ከፍ አለ፡፡ ነጭ የሆነች ብሩህ ደመናም አምላካችንን ተቀበለችው፡፡ከዓይናቸውም እየራቀ፤ከእይታቸው በርቀት ሳይሆን በርኅቀት ተሰወረባቸው፡፡ሐዋርያትም ኢየሱስ ክርስቶስን በጣም ይወዱት ስለነበር ሲለያቸው አዝነው አተኩረው ሰማዩን ለረጅም ሰዓት ተመለከቱ፡፡ ድንገትም ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ቅዱሳን መላእክት በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው፡፡መላእክትም ሐዋርያትን እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል፡፡ ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል›› አሏቸው፤ (ሐዋ. ፩፥፰-፲፩)፡፡ ሐዋርያትም የመላእክትን ማረጋጊያ ቃል ከሰሙ በኋላ በኢየሩሳሌም ወደ ምትገኘው ቤተ መቅደስ በመሄድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸው እስኪፈጸም ድረስ ቀን ከሌሊት በአንድነት ሆነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከመካከላቸው አድርገው በጾምና በጸሎት እየተጉ ቆዩ፡፡ 📖የጾመ ሐዋርያት የጊዜ ቀመር ሥሌት በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት›› (ማቴ.፱፥፲፬)። ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ያንጊዜም ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፭)፡፡ 📖እኔ ሳለሁ አይጾሙም ማለቱ እርሱ ካልሞተና ካላረገ፤ መንፈስ ቅዱስም ካልተሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት ጾመው ድል መንሳት ስለማይቻላቸው ነው፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው ሐዋርያት ጾመው ጸልየው ድል ያደረጉትን ዓለም እኛም የምናሸንፍበት ኃይል እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን አምላከ ሐዋርያት ተለመነን እያልን ለመማጸን ነው፡፡ 📖ይህን ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን አብዛኛው ምእመን ‹‹የቄስ ጾም›› ነው በማለት ከጾሙ ሽሽት ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተክርስትያንን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ መስተካከል ይገባዋል፡፡ 🙏🏽ሐዋርያትን አብነት በማድረግ ጾመን በረከትን ልናተርፍ ይገባናል፡፡🙏🏽 የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን ሐዋርያት በረከት የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎት እና ምልጃ አይለየን፡፡
Show all...
12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና በእንተ እግዝእትነ ማርያም። በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት የኃጥያት ማሠሪያ ይፍታችሁ ሲል ፲፪ [12] ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና ፲፪ [12] ደግሞ በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላል። ካህናትና ምዕመናን በሙሉ በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህንኑ ፲፪ [12] ጊዜ እንላለን። ➥እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት፦ አቤቱ ክርሰቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርሰቶስ ማረን ማለት ነው። ➥አስራ ሁለት ጊዜ እግዚኦ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሌሊቱ 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሠራነው ኃጥያት ለሃያአራቱ ፳፬ [24ቱ] ሰዓት ምሕረትን እናገኝ ዘንድ ነው። ሌላው አሥራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት ፦ ➥፩ኛ. በስመ ሥላሴ ነው። በእያንዳንዱ ፊደል አ ብ ወድ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪ ➥፪ኛ. የድኃነታችን ምክንያት በሆነችው በእመቤታችን ስም ፊደል ቅ ድ ስ ት ድ ን ግ ል ማ ር ያ ም ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪ ➥አቆጣጠሩም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደታች ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት [በትንሿ] ጣት ወደላይ ነው። ➥ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፦ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን። ➥ መሐል ጣት ወደላይ ፦ ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን ➥ በቀለበት ጣት ወደታች ስንቆጥር፦ ለፍርድ መምጣቱን በትንሿ ጣት ወደላይ ስንወጣ፦ ደግሞ ሁላችንን በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው። ➥ በእንተ እግዝእትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ፦ ከትንሽ ጣት ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደላይ ይፈፀማል። ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳየን ምስጢር ነው። ምን ከመጽሐፈ አሚን ወሥርዓት የተወሰደ በመምህር ዘበነ ለማ የተፃፈ ገፅ 238 ሙሉ መጽሐፉ ከላይ በpdf ተቀምጧል ትምህርቱን ለሌሎች እናካፍል ‼️ አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾 https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg ➮ከወደዱት ያጋሩ share & join 🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻  @Orthodox_Addis_mezmur @orthodox_spiritual_poems @Eotc_Books_By_Pdf @Lesangeez128 🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
Show all...
✝✝እንኳን ለዐብይ ጾም አደረሳችሁ/አደረሰን።✝✝ ✝እንደ አምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ከ7ቱ አጽዋማት መካከል የሆነውን ይህንን ታላቅ ጾም እንድንጾም ፈቃዱ ሆኖ ዕድሜን ለንሰሐ ስለሰጠን ልናመሰግን ይገባል። ✝ተወዳጆች ሆይ ይህ የጾም ወቅት ከሌሎች የጾም ጊዜያት ለየት ያለ ማለትም በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በሀገራችን በኢትዮጵያ ላይ ትልቅ አደጋ መጋረጡ ሲለሚታወቅ ይህ ፈተና የሚጠፋው በጾምና ጸሎት መሆኑን አውቀን ልንጠቀምበት የሚገባ ወቅት ስለሆነ ሁላችንም በንሰሐ ተጎብኝተን የምንፈጽመው ሊሆን ይገባል። ✝ሌላው በጾሙ ጥያቄዎቻችን መልስ የሚያገኙበት፣ የቅድስት ቤተ ክርሰቲያናችን አንድነት የሚመለስበትና የሀገራችን ሠላም የሚረጋገጥበት እንዲሆን ሁላችንም በጸሎት የምንበረታበት እንዲሆን ሁላችንም ልንተጋ ይገባል። ✝በመጨረሻም ከውድቀታችን ተነስተን፣ ወደ አባቶቻችን ካህናት ቀርበን ለመንፈሳዊው አገልግሎት ከፊት ይልቅ የምንተጋበት ጾም ይሆንልን ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው። ✝መዋለ ጾሙን በሠላም ያስጀመረን አምላክ ሁላችንንም በሠላም አስፈጽሞ ለብርሃነ ትንሣኤው በሠላም ያድርሰን።✝
Show all...
ቤተክርስቲያን ጥቁር ልብስ እንዲለበስ ጥሪ አቀረበች! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለ3 ቀናት ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አስተላልፏል። ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን ተብሏል። መረጃውን ለ10 ሰው #ሼር በማድረግ የአባቶችን አደራ እንወጣ!
Show all...