cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የምርጫዬ ዕዉቀት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

የምርጫዬ እውቀት ፔጅ

Show more
Advertising posts
217
Subscribers
-7424 hours
-727 days
-6630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣የፍቅር፣እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
Show all...
ለሁሉም ክ/ከተማ CRRSA ጽ/ቤት አዲስ አበባ ጉዳዩ: የመምህራን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ምዝገባን ይመለከታል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመምህራን ልማት ጋር በተያያዘ በትምህርት ቢሮ በኩል የተለያዩ ፕሮግራሞችን ቀርፆ እየሰራ ይገኛል። በዚሁ መሰረት በነዋሪነት ያልተመዘገቡ መምህራንን ጥያቄ መመለስ ይቻል ዘንድ በተቋሙ ፀድቆና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር በተመዘገበው የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት ምዝገባ እና አገልግሎት አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 145/2016ዓ.ም አንቀፅ 34(7) ኤጀንሲው የሚቀርቡለትን አስተዳደራዊ ጉዳዮች አይቶ ለከተማው ነዋሪ ጥቅም ውሳኔ እንዲሰጥ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህ አሰራር ለመምህራን ልማት ጥቅም በልዩ ሁኔታ ተዘርግቷል። የመምህራን ምዝገባን በተመለከተ ** * መሸኛ ከክ/ሃገር አምጥተው በነዋሪነት ለመመዝገብ ጥያቄ የሚያቀርቡና አስመዝጋቢ ያላቸው አሰራርን ተከትሎ ለመንግስት ሰራተኛ በተቀመጠው አግባብ አገልግሎት ያገኛሉ። ይሁንና አስመዝጋቢ ኖሯቸው በተለያዩ ምክንያቶች መሸኛ ማቅረብ የማይችሉ በትምህርት ቤታቸው በሚላከው የመንግስት ሰራተኛ የቅጥር ቅፅ ኮፒ አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን በሶስት ወር የግዜ ገደብ ውስጥ መሸኛቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ይህንንም የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ተከታትሎ ያስፈፅማል። * መልቀቅያ ከክ/ሃገር አምጥተው በነዋሪነት ለመመዝገብ ጥያቄ የሚያቀርቡ ነገር ግን አስመዝጋቢ የሌላቸው በወረዳው ትምህርት ቤት በሚከፈተው የነዋሪነት ምዝገባ ቅፅ አገልግሎት የሚያገኙ ይሆናል። * መልቀቅያ ከክ/ሃገር በተለያዩ ምክንያቶች ማምጣት የማይችሉ እና አስመዝጋቢ የሌላቸው በትምህርት ቤቱ በሚላከው የመንግስት ሰራተኛ የቅጥር ቅፅ ኮፒ መረጃ አገልግሎቱን የሚያገኙ ሲሆን በሶስት ወር የግዜ ገደብ ውስጥ መልቀቅያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ይህንንም የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ተከታትሎ ያስፈፅማል። የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እና የትምህርት ቤቶች ተግባርን በተመለከተ **** * በቅድሚያ የትምህርት ቤቱን የህንፃ ይዞታ እና መሰል መረጃ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በፊርማው አረጋግጦ የነዋሪነት ቅፅ በወረዳው እንዲከፈት በደብዳቤ ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ጥያቄ ያቀርባል። የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤትም መረጃውን አረጋግጦ ለወረዳው CRRSA ጽ/ቤት የነዋሪነት ምዝገባ ቅፅ በትምህርት ቤቱ እንዲከፈት በደብዳቤ ጥያቄ የሚያቀርብ ሲሆን ምዝገባ ለሚያደርጉት መምህራንም የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር የግዴታ ውል በአሰራሩ መሰረት ቀርቦ የሚፈርም ይሆናል። * የትምህርት ጽ/ቤቱ በዚህ አሰራር የሚስተናገዱ መምህራንን ሙሉ መረጃ እና የቅጥር ቅፅ በትምህርት ቤቱ ሲቀርብለት መረጃዎችን አደራጅቶና ትክክለኛነታቸውን አረጋግጦ ምዝገባ እንዲያደርጉ ለሚመለከተው የወረዳ  የCRRSA ጽ/ቤት በአባሪ ጥያቄ ያቀርባል እንዲሁም * አጠቃላይ ስራዎችን ከወረዳው CRRSA ጽ/ቤት ጋር መገምገም። የክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊነት *** * በየወረዳው ያሉ ትምህርት ቤቶችን ለይቶ በደብዳቤ ለክ/ከተማው CRRSA ጽ/ቤት ማሳወቅ፣ * በወረዳ ጽ/ቤቶች በነዋሪነት የተመዘገቡ መምህራን መረጃ ማጥራት፣  ማረጋገጥ እንዲሁም መረጃዎቹን  በአግባቡ አደራጅቶ መያዝ፣ * አጠቃላይ ስራዎችን ከክ/ከተማው CRRSA ጽ/ቤት ጋር በየግዜው መገምገም። የትምህርት ቢሮ ሃላፊነት *** * በከተማው ያሉ ትምህርት ቤቶችን በደብዳቤ ለማዕከል CRRSA ማሳወቅ፣ * በወረዳ ጽ/ቤቶች በነዋሪነት የተመዘገቡ መምህራን መረጃ ማጥራት፣  ማረጋገጥ እንዲሁም አደራጅቶ በአግባቡ መያዝ፣ * አጠቃላይ ስራዎችን ከመምህራን ማህበር እና ከከተማው CRRSA ጋር በየግዜው መገምገም። ከዚህ ቀደም በተለያየ መልኩ ተከፍቶ የነበረ የት/ቤት ፋየል እንዲዘጋና እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል። በዚህ መልኩ ተመዝግበው አገልግሎት ሲያገኙ የነበሩ መምህራንም ወደ ተሻሻለው ወደዚህ አሰራር የሚገቡ ይሆናል። ማሳሰቢያ: ሃሰተኛ ማስረጃ ማቅረብ ወይም ዳያጠሩ ለተቋሙ ማስተላለፍ በወንጀል ያስጠይቃል። ይህ አሰራር ከሚያዚያ 24 2016ዓ/ም ጀምሮ የፀና ሲሆን ለሚመለከታቸው ሁሉ በቂ ኦረንቴሽን በመስጠት የኦዲት ስርዓትን ባማከለ መልኩ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንድታስፈፅሙ ኤጀንሲው ያሳስባል። ከሰላምታ ጋር ግልባጭ// * በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር * ለስራ-አስኪያጅ ጽ/ቤት * ለከንቲባ ጽ/ቤት * ለትምህርት ቢሮ አዲስ አበባ **** * ለሃላፊዎች * ለህግ ጉዳዮች ክፍል ሲ/ም/ነ/አ/ኤ ****
Show all...