cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መጻሕፍት PDF book

For any comment 🔥 @kalebma

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
180
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

<<… ስግብግብ ሀሳብ በአእምሮአችሁ ውስጥ እያለፈ ከሆነ፣ እንዲያልፍ ፍቀዱለት፤ ብስጭት እያለፈ ከሆነም ይለፍ፣ ምን የሚያገባችሁ ነገር አለ? ደግሞስ ማን ሆናችሁ ነው ጣልቃ የምትገቡት? ለምንስ ነው ከአእምሯችሁ ጋር በሀይል የምትጎዳኙት? ለምን ' እኔ ስግብግብ ነኝ፣ እኔ ተበሳጭቻለሁ.....' ብላችሁ ማሰብ ትጀምራላችሁ? በአእምሯችሁ ውስጥ እያለፈ ያለው አንድ የብስጭት ሀሳብ ብቻ ነው። ሀሳቡ ይለፍ፣ እናንተ ደግሞ አስተውላችሁ ተመልከቱት! >> ፨፨፨ ምንጭ ፦ " ብርሃነ ኅሊና...ገጽ 62 " ትርጉም ፦ አና ፍራንክ @eth_tibeb
Show all...
🖤🖤🖤ከታላቅ ከታናሽ🖤🖤🖤 ' ከሽንጡ ከሻኛ አራት ኪሎ በልተው አትፆምም ወይ ቢሉኝ ባዶ ሆዴን መጥተው ሩብ ኪሎ ስጋ አጥታ ፆም ላልያዘች ነብሴ ስንኝ ቋጠርኩላት በራበው መንፈሴ እኔ ምልሽ ለራት ያልነው ፍስክ ራብ እያበሰረ ከምኔው ተፈቶ ከምኔው ታሰረ ሳይይዙ ላይለቁ ሳያስር ላይፈታ ልፁም አልፁም ብለን ላፍ ብናመነታ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ‼️ እኔና ቤቴ ግን .... ኑሮ ጨክኖብን ዋጋ ተጭኖብን ፍየል ዱር እንስሳ በግ ሲመስለን አውሬ ሸኾናው ክፍት ነው ወይፈን እና በሬ በሚል የወል ሀሳብ በጋራ ተስማምተን ቁርጥ እርኩስ አስባልን ጥብሱን አስገዝተን እኔና ቤቴ ግን .... ስጋ ስንል ስጋት በለውጥ ታድሎን አመት እንፆማለን መፆም ማን ከልክሎን ኩነኔ ሳንሰራ ፃድቅም ሳንባል በገነት መካከል በሲኦልም መሀል እንዳንባል ሀጢያን እንዳንባል ፍፁም ምን በልተን እንግደፍ ምኑን ትተን እንፁም ከታላቅ ከታናሽ ከሽንጥ ከሻኛ አራት ኪሎ በልተው አትፆምም ወይ ቢሉኝ ባዶ ሆዴን መጥተው ሩብ ኪሎ ስጋ አጥታ ፆም ላልያዘች ነብሴ ስንኝ ቋጠርኩላት በራበው መንፈሴ ተቀበይ..... ተቀበይ ነብሴ ሆይ ገጠምኩልሽ ላንቺ የአለም ሀጢያት ፈርተሽ ስጋን ብትሰለቺ በዚህች ፆመኛ ሀገር አሳሪ ነው ፈቺ remhai @eth_tibeb
Show all...
💫"ከአንገት በላይ ያለውን ስትመግብ እሱ ደግሞ ከአንገት በታች ያለውን በደምብ አርጎ ይመግብልሀል" ይለናል ዚግዚግላር የተባለ ደራሲ። ለሆዳችን አስበን አሪፍና ንፁህ ምግብ እንደምንበላው ሁሉ ለአይምሮአችንም መልካም ሀሳቦችን ምርጥ አመለካከቶችን እያሳደድን መመገብ አለብን። የሆድ ምግብ ጤናና ትንፋሻችንን ያቆይልናል የአይምሮ ምግብ ደግሞ መድረሻችንን ይወስነዋል። ለመጨረሻ ጊዜ የበላኸው መቼ ነው ብዬ ብጠይቅህ የፈለገ ቢሆን ከሳምንት ወይ ከ 2 ቀን በፊት አትለኝም፤ ለመጨረሻ ጊዜ ያነበብከው መቼ ነው? ብዬህ ግን ጥያቄውን ለመመለስ ጊዜ ከፈጀህ ያለህበት ሁኔታ ከባድ ነው። ወዳጄ አስብበት! @eth_tibeb
Show all...
🦅ንስር አሞራ እስከ ሰባ ዓመት በሕይዎት የመኖር ጸጋ ተሠጦታል፡፡ ነገር ግን ይህን 70 ዓመት የዕድሜ ፀጋን አጣጥሞ ለመኖር አርባኛ ዓመቱ ላይ በሕይዎቱ ወሳኝ የሚባል ውሳኔን ማሳለፍ ይጠበቅበታል፡፡ ይኸውም ንስሩ አርባኛ ዓመት ዕድሜው ላይ እነዛ እረዥምና እንደልብ የሚተጣጠፉት ጥፍሮቹ እንደ እነጨት ይገራሉ፡፡ ስል የነበረው ማቁርቱም ወደ አንገቱ ይታጠፍና ምግቡን አንድኖ እንዳይዝ ያግደዋል፡፡ የገረጀፉት ላባዎቹም ከደረቱ ላይ ተጣብቀው የመብረር ስራውን አስቸጋሪ ያደርጉበታል፡፡ በዚህ ወቅት ንስሩ ሁለት ወሳኝ አማራጮች ይጠብቁታል፡፡ አንድም ሞትን አሜን ብሎ መቀበል ወይም ደግሞ አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት ሚፈጅን ፈታኝ የለውጥ ሂደት ማካሄድን፡፡ በለውጡ ሂደት ለማለፍ ከወሰነ ቀጣዮችን ተግባራት መፈጸም ይጀምራል፡፡ በመጀመሪያ ንስሩ ከፍ ብሎ ከወጣ ተራራ አለት ላይ ይቀመጥና የታጠፈውን ማንቁርቱንና ጥፍሮቹን ከአለቱ ጋር ደጋግሞ በመምታት ወልቀው እንዲወድቅ ያደርጋል፡፡ የገረረውና የታጠፈውን ማንቁርት እንዲሁም ጥፍሮቹን አውልቆ ከጣለ በኋላ ከስር የወጣው ሙሽራ ማንቁርትና ጥፍር እስኪጠነክር ድረስ ለቀናቶች ይታገሰዋል፡፡ ማቁርቱና ጥፍሮቹ ከጠነከሩ በኋላ ቀጣይ የሚጠብቀው ተግባር የደረቁትና ከደረቱ ጋር ተጣብቀው ከመብረር ያገዱተን ላባዎች እየነጨ በማራገፍ በአዲስ እንዲተኩ ማድረግ ነው፡፡ ይህን እልህ አስጨራሽና አንድመቶ ሃምሳ ቀናት ወይም አመስት ወራት የፈጀውን የለውጥ ጉዞ ካካሄደ በኋላ ዳግም ውልደቱን የሚያበስር ቀጣይ ሰላሳዎቹን ዓመታትም በትኩስ ኃይል መኖር የሚያስችል ለውጥ አደረገ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታም የዳግም ውልደቱን በረራ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ይጀምራል፡፡ በህይወት አሸናፊ ለመሆን እልህ አስጨራሹን ህይወትን ውጣ ውረድ ለውጥ ሂደት መታገስ ማለፍ ይጠይቃል፡፡ @eth_tibeb
Show all...
አትፈላሰፉ ማለት በጥልቀት አታስቡ ማለት ነው! (እ.ብ.ይ.) ዓለም በክፉ አስተሳሰብ ልትወድም እየተንደረደረች ነው፡፡ ሕይወት ጥድፊያ ነው፡፡ ኑሮ ድካም ብቻ ሆኗል፡፡ እዚህም እዚያም ግፊያ ነው፡፡ መተረማመሱ፣ መረጋገጡ፣ መገፈታተሩ የሁላችንም ባህሪ ሆኗል፡፡ ተጠባብቆ ጉዞ፣ ተቻችሎ ኑሮ ቀርቷል፡፡ ሩጫው ወዴት እንደሆነ አይታወቅም፡፡ አካሄዱን ቆም ብሎ የሚያስብ፣ ሃሳቡን የሚመረምር፣ ሰውነቱን የሚፈላሰፍ ብዙ የለም፡፡ ማንም ማንንም አይምርም፡፡ ጥቅሙን ለማግኘት ሲል የማይደረገውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ የሕይወት ግቡ በሀብት ማሸብረቅ፣ ሆዱን መሙላት፣ የሚያምር ልብስ መልበስ፣ ቁስ መሰብሰብ፣ በቅንጡ መኪና መሽከርከር፣ በዘናጭ መኖሪያ ቤት ውስጥ መኖር ብቻ ነው፡፡ በሚያምር መንፈስ፣ ደስ በሚያሰኝ አኗኗር፣ ልብን በሚያረካ ምግባርና ተግባር፣ በዕውቀትና በጥበብ ያሸበረቀ ጎጆ ውስጥ ለመኖር የሚሻ ሰው መንምኗል፡፡ ፍላጎቱ ሆድ ብቻ ነው፡፡ ፖለቲካውም የሆድ ነው፡፡ ለጭንቅላቱ የሚያስብ፤ ለነፍሱ የሚቆረቆር፣ ለመንፈሱ የቆመ ጠፍቷል፡፡ ሰውነትህን የምታውቀው፣ የተፈጠርክበትን ዓለማ የምትገነዘበው፣ የውስጡን ዓለምህን የምትረዳው በጥበብ ባህር መንሳፈፍ፣ በሃሳብ መፈላሰፍ፣ በዕውቀት መራቀቅ፤ በእውነት ውቅያኖስ መጥለቅ ስትችል ነው፡፡ ከሆድህ ከፍ ብለህ ማሰብ ስትጀምር ሰው በምግብ ብቻ እንደማይኖር ትረዳለህ፡፡ መንፈስህ ሲዘምን፣ ነፍስህን ስታነቃ በነፃ ሃሳብ ትሰለጥናለህ፤ በገዛ ራስህ ፍላጎት የባርነት ሸምቀቆ ውስጥ አትገባም፡፡ ነፍስያህን ከቆሸሸው ዓለም ነፃ የምታወጣት ከሆድ አስተሳሰብ ርቀህ ከፍ ብለህ ስትበር ነው፡፡ ዓለሙንና በዓለሙ ውስጥ ያለውን በሃሳብ ከፍ ብለህ፣ በዕውቀት ረቅቀህ፣ በጥበብ ክንፍ በርረህ በእውነት ሰማይ ላይ ሆነህ እንደወፍ (Birds eye view) ከላይ ወደታች ዓለሙን ስትመለከተው ብዙ ዕውቀት ትጨብጣለህ፡፡ አስተዋይና ታዛቢ አዕምሮ ይኖርሃል፡፡ ሃሳብ የሚመስሉ ነገር ግን ገና በደንብ ያልታሰቡ ድፍንና ጥሬ ሃሳቦች ታገኛለህ፡፡ ያልበሰሉ መብሰል የሚቀራቸው አመለካከቶች ፍጥጥ ብለው ዓይንህ ውስጥ ይገባሉ፡፡ መወቀጥ፣ መሰልቀጥ፣ መደለዝ የሚቀራቸው አስተሳሰቦች ዓለሙን ወደኋላ እየጎተቱት እንደሆነ ትረዳለህ፡፡ አዎ ስትፈላሰፍ፣ በሃሳብ ባህር ስትቀዝፍ፣ በጥበብ ውቅያኖስ ስትወራጭ፣ በምክንያታዊ አስተሳሰብ ከፍ ስትል፣ በመንፈሳዊ ዕውቀት ስትረቅቅ ዓለሙ ያንስብሃል፡፡ ሳታውቀው ከዓለሙ መንገድ ከመንጋው መስመር ትወጣለህ፡፡ መንገድህ መንገዳቸው አይሆንም፡፡ ጎዳናቸው ይቀፍሃል፡፡ የማስመሰል ዱካቸው ያስጠላሃል፡፡ ራስን ከመሆን ይልቅ ሌላውን ለመምሰል የሚደረገው ግርግር ትርጉሙ ከንቱ እንደሆነ ትደርስበታለህ፡፡ የመኖር ትርጉሙ ይምታታብሃል፡፡ የሆድ ፖለቲካ ባነወረው ዓለም መኖር ይሰለችሃል፡፡ ከአንገት በታች ለሆነ አምሮት ብቻ ሰው ባሪያ ሲሆን ስታይ ምነው የዚህ ትውልድ አባል ባልሆንኩ ትላለህ፡፡ አንዳንድ ሰው ለየት ባለ አስተሳሰብ ሃሳብህን ስታንፀባርቅ አትፈላስፍብኝ ተው ይልሃል፡፡ መፈላሰፍ እውነትን መፈለግ እንደሆነ አይገባውም፡፡ በሃሳብ ምርምር ውስጥ መሆን በሌላው ላይ መቃናጣት አይደለም፡፡ ገና ለየት ያለ የፍልስፍና ሃሳብ ስታነሳ የሚደክማቸው ብዙ ናቸው፡፡ ጥያቄ ስትጠይቅ ደሞ ጀመረህ ብለው ሃሳብህን ያስቆሙሃል፡፡ ፍልስፍናን ሳያውቁት የሰለቻቸው የቅርብህ ሰዎች ሺ ናቸው፡፡ ፍልስፍና በጥሞና ማሰብ ነው፡፡ መፈላሰፍ ሃሳብን፣ ራስን፣ ዓለሙን መመርመር ነው፡፡ የመጣንበትንና የቆምንበትን አስተሳሰብ ወዴት እየወሰደን እንደሆነ ቆም ብሎ ማሰብ አሁኗዊ ሁኔታችንንና ትናንትናችንን ለመረዳት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ መፈላሰፍ አይሰለችምም አያሰላችምም። ይልቁንስ አዕምሮን በአዲስ ሃሳብ ያነቃቃል። አዕምሮ እንዳይተኛ ዘወትር የንቃት ክኒኑ የሆነውን ፍልስፍናን መዋጥ ይገባዋል። አትፈላሰፉ ማለት በጥልቀት አታስቡ ማለት ነው። ማሰብን መከልከል ወንጀል ነው። እንዲያስብ፣ እንዲፈላሰፍ፣ እንዲመራመር፣ እንዲጠይቅ የተፈጠረን አዕምሮ አትፈላሰፍ ማለት ምግብ መከልከል ማለት ነው። ሰውን አትብላ እንደማትለው ሁሉ አትፈላሰፍ አትለውም። ባይሆን ለጤናህ የሚስማማህን መርጠህ ብላ ልትለው ትችላለህ። መርጦ መፈላሰፍ አንድ ነገር ነውና። አንድ የግሪክ ፈላስፋ ፡- ‹‹ጢም ፈላስፋ አያደርግም! (A beard doesn’t make a philosopher)›› ይላል፡፡ እውነት ነው! ልብስ ሰውን ሰው እንደማያደርገው ሁሉ ጢም ማሳደግ፣ ፀጉር ማስረዘምም ፈላስፋነትን አይሰራም፡፡ ሰውን ሰው የሚያደርገው አስተሳሰቡና ግብሩ ነው፡፡ ፈላስፋንም ፈላስፋ የሚያስብለው በሃሳቡ ሲረቅቅ፣ በዕውቀቱ ሲመጥቅ ነው፡፡ ሃሳባቸውን ያሳደጉ፣ አመለካከታቸውን ያስረዘሙ እንጂ ፀጉራቸውንና ፂማቸውን ብቻ ያስረዘሙ ፈላስፋ መሆን አይችሉም፡፡ በልብስና በቁስ ፈላስፋ የሚመስሉ ነገር ግን በሃሳባቸው ከፍ ያላሉ በየቦታው፣ በየመንገዱ ጎዳናውን ሞልተውታል፡፡ መፅሐፍ ማንበብ የሚችሉ ነገር ግን ራሳቸውን ማንበብ የማይችሉ ፈላስፋ-መሳዮች (Pseudo-philosophers) ብዙ ናቸው፡፡ ወዳጄ ሆይ .... በሃሳብ ሰማይ ብረር፣ በጥበብ ውቅያኖስ ጥለቅ፣ በእውነት ዓለም ላይ ምጠቅ፡፡ እስኪበቃህ ድረስ ተፈላሰፍ፡፡ እስከምትችለው ድረስ ራስህንም፣ ዓለምህንም፣ የሚታየውንም፣ የማይታየውንም ዓለም መርምር፡፡ መፈላሰፍህ በቃላት ብቻ ለመራቀቅ አይሁን፡፡ ለመምሰል የሆነ ፍልስፍና ዋጋ የለውም፤ እንደውም ከራስህ ጋር ያጠፋፋሃል፡፡ ፍልስፍናህ ሰውነትህን ለማግኘት፣ መንፈስህን ለማዘመን፣ አዲስ ሃሳብ ለመስራት፣ አንተነትህን ከፍ ለማድረግ ይሁን! አትፈላሰፍብን የሚልህን አትስማ! የምትፈላሰፈው ጨለማህን ለመግፈፍ፣ ድንቁርናህን ለማውደም፣ እውነትን በእጅህ ለማድረግ፣ የጥበብ ጥምህን ለመቁረጥ፣ ራስህን በራስህ ለመምራት፤ በስሜትህ ላይ የበላይ አለቃ ለመሆን መሆኑን ተረዳ! አራት ነጥብ!! --------- በጥልቀት አስቡ እንጂ! አትፈላሰፉ አትበሉ፤ ይልቁንስ... በሃሳብ ምጠቁ፤ በዕውቀት ተራቀቁ፤ ተፈላሰፉ በሉ፣ እውነትን መሻት ነው፤ ጥበብን ማፍቀር ነው፤ የመፈላሰፍ ውሉ፡፡ ዓለሙን መረዳት፤ ራስን ማወቅ ነው፤ የፈላስፋ ጎሉ፡፡ @eth_tibeb
Show all...
"እንደ ሞተ ሰው ሁን" ❖ ከወንድሞች አንዱ ወደ አባ መቃርዬስ መጥቶ " አባክህ ለህይወቴ የሚሆን መመርያ ስጠኝ" አለው ፡፡ አባ መቃርዬስም ያንን ወንድም ወደ መቃብር ሂድና በሙታን ላይ ክፋ ነገር አድርግባቸው፡፡ ብሎ ላከው ሰውየውም በሙታኑ ላይ ድንጋይ በመወርወርና በመሳደብ የተላከውን ፈፅሞ መጣ ፡፡ " አባ መቃርዮስም ምን አሉህ ? ሲል ጠየቀው " ያም ወንድም "ምንም አላሉኝም " ብሎ መለሰ ፡፡ በነጋታውም ተመልሰህ ናና አመስግናቸው አለው፡፡ በነጋታውም ያ ወንድም ወደ መቃብሩ ስፋራ ተጉዞ ሙታኑን " ሐዋርያ ፣ ቅዱሳን ፣ጻድቃን ፣ እያለ አመሠገናቸውና ተመለሰ ፡፡ መቃርዮስም " ምን መለሱልህ አለው" ምንም አለ ፡፡" መቃርዮስም " ስትሰድባቸው ፣በድንጋይ ስትመታቸው ፣ ስታመሰግናቸውም ፣ ስታወድሳቸው ፣ ምንም አልመለሱልህም ፡፡ አንተም ለነፋስህ ድህነት ከፈለግክ እንደ "ሞተ ሰው ሆነህ ኑር" ፡፡ ሰዎች ክፋ ቢያደርጉብህም ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ አለው ፡፡፡ ወዳጄ ሆይ የታላቁን አባት ምክር ልብ አልክን ? የሚሰድብህንና ድንጋይ የሚወረውርብህን እንዴት ማለፋ እንዳለብህ ተማርክ ? የሚያመሰግኑህንና የሚያወድሱህን እንዴት መቀበል እንዳለብህ አስተዋልክ ? ☞ ቀልብህን የሚቀሙህን ብዙ ሰዳቢዎች አሉብህ ፡፡ የሚያስጎነብሱህ ብዙ ድንጋይ ወርዋርዎች አሉብህ ፡፡ ☞ አንዱ ድህነትህን እያነሳ ያሸማቅቅሀል ፤ሀብት የሌለህና ገንዘብ መቁጠር ያልቻልከው የማትረባ ስለሆንክ ብቻ እንሆነ በማሰብ ያሳንስሀል ☞ በምግባርህ የሞትህ እንደሆንክ እየጮኸ ይነግርሀል ☞ ሃይማኖትህና ኢትዮጲያዊነትህ ለድህነት አስተዋፅኦ እንዳደረገና ማንነትህ ራሱ የተዋረደ እንደሆነ በመንገር ተፈጥሮህን " ንቀህ "አርቴፋሻል እንድትሆን ኦርጅናልነትህን አርክሰህ ፌክ እንድትሆን ይሰብክሃል፡፡ ☞ በዘር ገመድ ተብትበው ከወንድምህ ጋር የሚያናቁሩህ ሃይማኖትህንና ሰብአዊነትህ ሳይቀር በዘረኝነት ሰፌድ የሚያበጥሩ ድንጋይ ወርዋርዎችን እንዴት ይሆን ያለፋካቸው ፡፡ ☞ ጾምህን የሚያንቋሽሹ ፣ ሱባኤህን የሚረብሹ ፣ ጸበል መጠጣትህን ፤እምነት መቀባትህን የሚያንሻፋፉ ፤እግዚአብሔር በሞተ ነገር ላይ ታሪክ እንደሚሰራ ስትነግራቸው የሚስቁ ፤ በሰማይ ህይወት አለ ስትላቸው በሙት አምራቸው የሚሳለቁ ፤ይልቅ ዓለምህን ቅጭ ጊዜህን ተጠቀምበት የሚሉ አለማውያንና ማንነትህን ለማርከስ ማንነታቸውን ለማንገስ የሚወረውሩት ጥቁር ድንጋይ አቁስሎህ ይሆን ???? ወዳጄ ሆይ ታላቁ አባት እንዲህ ይልሃል ለስጋውያን ለስሌታውያን እንደ ሞተ ሰው ሁን !!!! ☞ ደግሞስ ገና ልትሰራ የምትችለውን ገና በልዑልነትህ ንጉስ ብለውህ ገና በወጣትነትህ ጻዲቅ አድርገውህ ገና በተማሪነትህ ረብኒ ብለውህ ዳዴህን ሳትጨርስ የአትሌትነት ማዕረግን ሰጥተውህ በዲያብሎስ መዝሙር ከፋ ከፋ በጣሙን ከፋ ከፋ ሗላ ስትወድቅ አጥንትህ እንዳይተርፋ ሰቅለው በአፋጢምህ የሚደፋህን አድር ባዮችና ህሊና ቢሶች እንዴት አልፈሀቸው ይሆን ? ለእነርሱም ወሬ መንኩሰህ እንደ ሞተ ሰው ሆንክን ?? ☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ትዳር አለህ ፡፡ ☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ህይወት አለህ ☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታጠነክረው ወዳጅነት አለህ ☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምትሰራው እልፋ ስራ አለህ ፡፡ ✞ ደግሜ ደግሜ እልሃለሁ የታላቁን አባት ቃል ተውሼ ለእነዚህ እንደሞተ ሰው ሁን!!!! ✍ እንደ ሞተ ሰው ሁን እንጂ ሙት ሁን አልተባልክም ፤ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ በግብርህ ሕያው ሁን እንጂ ሙት አትሁን፡፡ " ሀዋርያው እንዳለው አንተ ለዚህች አለም ሙትባት ይህች አለምም በአንተ ዘንድ የሞተች ትሁን ፡፡፡ "" እንደሞተ ሰው ሁን """ ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠ © ዘሕሊና የተወሰደ @eth_tibeb
Show all...
💫'ተማሪ ካለ አስተማሪ የትም ቦታ አለ'። በቃ በእያንዳንዱ ቀን የምናሳልፋቸው ውሎዎች እንደ ትምህርት ከተማርንባቸው ከኛ በላይ የሚፈልገውን የሚያሳካ የለም። ማህተመ ጋንዲ 'ነገ እንደሚሞት ሰው መኖር አለብህ፤ ዘላለም እንደሚኖር ሰው ደግሞ መማር አለብህ' ይላል። @eth_tibeb
Show all...
💫"ሁሉን ካጣ ጤነኛ ሰውና ሁሉን እንዳገኘ ከሚያምነው እብድ የቱ እድለኛ ነው?" "አንዲት ሴት የምታፈቅረውን ሰው ባለማግኘቷ የተነሳ ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ብትገባና ሀዘኗ ወደ አእምሮ መታወክ ቢወስዳት የመጨረሻው እጣ ፈንታዋ በማበድ ቢገባደድ ብለን እናስብ። ይህቺ ሴት ካበደች በኋላ ያንን የምትመኘውን ሰው እንዳገኘች እያሰበች በፍሰሀ ተሞላች ብለን እናስብ. .......ለዚህች ሴት የትኛው ዓለም ይሻላታል?" ክራራዊ ህይወት ገፅ 85 @eth_tibeb
Show all...
🌗"ትጋት የተስፋ ልጅ ናት።" 🌗 "ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው በሕይወቴ ውስጥ መልካም ነገሮች ወይም ስኬት ብዬ ከማስባቸው ውስጥ ማስተርስ ዲግሪዬ ወይም ዶክትሬት ዲግሪዬ አይደለም፡፡ ልጆቼ፡ ትዳሬ፡ ቤቴ ናቸው! በሕይወቴ ትልቁ ቁም ነገር ትልቁ ስኬት እነርሱ ናቸው! እናም አሁን ሳስበው የተጓዝኩበት የሕይወቴ አቅጣጫ ትክክል ነበር፡፡ አካሒዴም በእኔ ምኞት እና መምህሬ ባሰበልኝ ሳይሆን ፈጣሪ በመረጠልኝ ስለነበር በጎ መሆኑን የኋላ ኋላ ተገንዝቢያለው፡፡ 🌙እናም በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳን ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው፡፡ ሕይወት ጠመዝማዛም ብትሆን ውብና ተስፋን የተሞላች ናት! በዚህ ዓለም ሁሉም ነገር አበቃ አከተመ! ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል! የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር ዙሪያችን! ጭው ያለ በርሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሪያለው፡፡ 🌗ዕድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜም ቢሆን እንኳን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም፡፡ ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛ እና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና! " 🗞ከሰበዝ መጽሃፍ የተመዘዘ/ገጽ 97/ @eth_tibeb
Show all...
💫"ሁሉም ነገር መጨረሻው ላይ ያማረ ነው፤ ካላማረ ግን ገና መጨረሻው ጋር አልደረስክም ማለት ነው" ይለናል ዕውቁ ዘፋኝ ጆን ሌነን። እንዴት ደስ የሚል ቃል ነው?! ፍፃሜው ካላማረ እንዳታቆም ወዳጄ! @eth_tibeb
Show all...