cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

الفاروق

ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/joinchat/voYbxkO0KElmMjk0

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
181
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አቅል ላለው ሰው የሶፍይነት ማዕረግ ያላቸውና ሊሰጣቸው ከሚገቡ ሰዎች መካከል አንድኛው ሸክ ኑራድስ ናቸው እሳቸውም በግልፅ ዋሃብያ ካፊር መሆናቸውን ይናገራሉ አሏህን እንፍራ በሶፍያ ስም አንዋሽ አዳምጡ
Show all...
ش_نو_ر__أ_د_یس_مر_سا.aac7.22 MB
ሸክ ኑራድስ ወርቄዋ በሀቅ ላይ ነው የሞቱት ስለሙጀሲማ ምን አሉ ያዳምጡ
Show all...
4.90 KB
ሙ͟እ͟ሚ͟ን͟ ሁ͟ኑ͟! : «ሙእሚን እንደ ንብ ነው። ከበላች ጥሩውን ትበላለች። ጥሩን ትፀዳዳለች። ባረጀ እንጨት ላይ ብታርፍ እንኳን ደካማ ናትና አትሰብረውም። ሙእሚን እንደ የወርቅ ሽቦ ነው። ወናፍ አናፍተህ በእሳት ብታግለው ይቀላል። መልሰህ ብትመዝነው ግን ክብደቱ አይቀንስም።» አል‐ጃሚዑስ‐ሰጊር፥ ኢማም አል‐ሙናዊ (ረሒመሁላህ)። : ሙእሚን ሲባል በልሳኑ እና በልቡ ያመነ ብቻ አይደለም። በግብሩ እና በጠባዩም ያመነ ሰው ነው። ልቡ ንፁህ፤ ስነምግባሩም ያማረ ነው። ሙእሚን በንብ የተመሰለው ንብ ጥቅሟ ብዙ ወጪዋ ግን ትንሽ ስለሆነ ነው። «የደረቀ እንጨት ላይ ብታርፍ አትሰብረውም። በውሃ ላይ ብትወድቅ አታደፈርሰውም።» የተባለው ለዚህ ነው። ወሃከዘል‐ሙእሚን! : ሰይዲና ዐሊይ [ከር‐ረመላሁ ወጅሀሁ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «በዱንያ ስትኖሩ እንደ ንብ ሁኑ። አእዋፋት ሁሉ ደካማ እንደሆነች ያስባሉ። በሆዷ ውስጥ የያዘችውን ነገር ጥቅምና መድኃኒት አያውቁም።» : እንደ ንብ ሁኑ። እንድትኖር የታዘዘችበት ቦታ ላይ እንጂ አትኖርም። የጣፈጣትን ሁሉ አትበላም። የታዘዘችውን እንጂ አትቀምስም። አላህ እንዲህ አለ: ‐ «ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ (ሰዎች) ከሚሠሩትም (ቀፎ) ቤቶችን ያዢ፡፡ ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡» [ሱረቱን‐ነሕል] : የተፈቀደላት ምግብ ቢጣፍጥም ቢመርም ሌላን አትመኝም። በዚህ የተነሳ ከቀዳዳዋ የሚወጣው [ቆሻሻዋ] እንኳን ጣፈጠ፤ ፈውስም ሆነ። ሙእሚንም እንደዚሁ ነው። ጥሩውን እንጂ አይበላም። በጌታው ትእዛዝ እብጂ በደመነፍስ አይራመድም። በዚህ የተነሳ ውጩም ውስጡም ጥዑም ሆነ። ስለዚህ መልካም እንጂ አይሰራም፤ መልካም እንጂ አይናገርም። ልቡም ከማር ባላይ የጣፈጠ ነው፤ ክፉን አያስብም። : ጥሩን ያልበላ ጥሩን አይሰራም! ከሆዳችሁ ቀለብ በፊት የአእምሮኣችሁን ቀለብ ምረጡ! ወደ ቀልባችሁ የምትከቱትንም ለዩ! ስራችሁ ያምራል! ነገራችሁ ይጣፍጣል! : እንደ ንብ ሁኑ! ዱንያችሁ ያምራል! አኺራችሁ ይሳካል! ሙእሚን ሁኑ!… እንደ ሙእሚን ሁኑ!
Show all...
አዳቡል‐ኢስላም ——————— እቤትህ ስትገባ ወይም ከቤት ስትወጣ በሩን በሀይል አትግፋው። ራሱ በንፋስ ግፊት በሀይል እንዲዘጋም አትተወው። ይህ የምንኮራበት ዲናችን ኢስላም ካዘዘን ልስላሴ ጋር አይጣጣምም። ስለዚህ በእርጋታና በቀስታ ዝጋው። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «ልስላሴ በአንድ ነገር ላይ አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ። ጭካኔ በአንድ ነገር ላይ አይኖርም ያነወረው ቢሆን እንጂ።» : የወዳጅህ ቤት ስታንኳኳ «ማነው?» ከተባልክ «እገሌ ነኝ» በል፤ የምትታወቅበት ስምህን ጠቅሰህ። በድፍኑ «አንድ ሰው፣ እኔ፣ እንግዳ፣ ክፈቱት…» አትበል። እነዚህ ቃላት በር ላይ ቆሞ የሚያንኳኳውን ሰው ማንነት አይገልፁም። የሚከፍትልህ ሰው ዘንድ ድምፅህ የታወቀ መሆኑን አታስብ። አንዳንዴ ድምፅን ከድምፅ መለየት ያስቸግራል፤ የአንዳንድ ሰዊች ድምፅ ደግሞ ይመሳሰላል። ደግሞም እቤት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ድምፅህን ላያውቁ ይችላሉ፤ ማንነትህን ለመለየት ሊቸገሩ ይችላል። የሰዎች ጆሮ ድምፅን ሰምቶ በመለየት ላይ ሊሳሳት የሚችልበት ሁኔታም ሊኖር ይችላል። : ነቢዩ [ﷺ] ያንኳኳ ሰው ማንነቱን ሲጠየቅ «እኔ» ማለትን ከልክለዋል። ምክንያቱም «እኔ» ማለት ማንነትን አይገልፅም። ቡኻሪና ሙስሊም ከጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ [ረዐ] እንደዘገቡት እንዲህ ብለዋል: ‐ «የአላህ ነቢይ [ﷺ] ዘንድ መጣሁና በሩን አንኳኳሁ። "ማን ነው?" አሉ። "እኔ" አልኳቸው። ነቢዩ [ﷺ] "እኔ! እኔ!" አሉ፤ ንግግሬን ጠልተውት።» : ሶሐቦቹ ምን ጊዜም "ማን ነህ?" ሲባሉ የሚታወቁበት ስማቸውን ይጠቅሱ ነበር። ቡኻሪና ሙስሊም ከአቡዘር [ረضያሏሁ አንሁ] እንደዘገቡት: ‐ «በአንድ ቀን ሌሊት ከቤት ወጣሁ። የአላህ መልክተኛን [ﷺ] በመንገድ ላይ ለብቻቸው ሲሄዱ አገኘኋቸው። በጨረቃ ስር አብሬያቸው መሄድም ጀመርኩኝ። ከዚያም ወደኔ ዞሩና «ማነህ?» አሉ። «አቡዘር ነኝ።» አልኳቸው።» : «ሚን አዳቢል‐ኢስላም»፥ ሸይኽ ዐብዱል‐ፈታሕ አቡ ጉድ‐ዳህ
Show all...
የግጥሙ ደራሲ ☞ኡስታዝ_ሙሂቡ እና ☞ራዲያ በድሩ አቅራቢ እህት ራዲያ🕍 ኤዲት ኢብኑ ናፊዕ ክፍል ②ይ🀄️ጥላል ኢንሻ አሏህ @yedanawecuchannnneel
Show all...
አልቁድስ-mc.mp36.69 KB
العبادة بلا العلم كاكتابة على الماء «ያለ እውቀት የሚደረግ አምልኮት ከውሃ ላይ እንደመፃፍ ነው።» •በርግጥም እንደዚህ ተገጥሟል። ومن أعجب الأشياء أنك لاتدري وأنك لاتدري بأنك لاتدري የሚገርመው ነገር አንተ አለማወቅህ አለማወቅህም ምንም አልታወቀህ فإن كانت لاتدري ولم تك بالذي يسأل من يدري فكيف إذا تدري አዋቂ ካልጠየክ ከሆንክ አንተ እማታውቅ እንዴት ተብሎ ነው እውቀትን የምታውቅ تمام عمى طول السكوت وإنما شفاء العمى يوم تسأل من يدري ጅህልናን ማዘውተር በዝምታ ብዛት ለጅህልና አዋቂን መጠየቅ ፍቱን መድሀኒት
Show all...
#ረቢዐተ_ኢብኑ_ካዕብ አልአስለምይ!! እንዱህ ይላሉ፦ “እኔ ሁልጊዜ ለነቢዩ ﷺ ውዱእ የሚያደርጉበት ውሃና ሌላም የሚፈልጓቸውን ነገሮች ማታ ማታ አቀርብላቸው ነበር፡፡ አንድ እለት የአሏህ መሌእክተኛ (ﷺ) እንዱህ አሉኝ፡- “የምትፈልገውን ነገር ጠይቀኝ!” እኔም እንዱህ አልኳቸው፡-“እኔ ከእርስዎ ጋር በጀነት አብሬ መሆን ነው የምፈልገው፡፡” ነቢዩ (ﷺ) ይህን እንደሰሙ እንድህ አሉ፦ “ሌላስ የምትጠይቀኝ ነገር የለህም?” እኔም “ይህን ብቻ ነው የምፈልገው” አልኳቸው፡፡ ይህን እንደሰሙ እንድህ አሉኝ፡- “እንደዚያ ከሆነ ሱጁድ በማብዛት እርዳኝ፡፡” (ሙስሉም)
Show all...
#አስቸኳይ_መልእክት ሙስሊም የሆነ ሰው ሳያነብ እንዳያልፍ እንድሁም ሙስሊም ለሆኑ ሰወች ሸር እንድታደርጉት በአላህ ስም እጠይቃለሁ አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ 🗓እስኪ ዛሬ ሳልፈልግ ፓለቲካ ላወራ ነው ግዴታ ነገሮች ያስገድድና ስለፖለቲካ እናወራለን ላወራ የቻልኩት በዘር በፖለቲካ ስም ሙስሊም እየተጨፈጨፉ ነው አማራ ሞተ ተብሎ የሚገደሉት ግን ሙስሊሞች ናቸው ወለጋ ብንል መተከል ላይ ብንል አጣየ ሸዋሮቢት የመሳሰሉት ቦተወች ላይ የሚገደሉት ንብረታቸው የሚጠፋው መስጊዳቸው የሚቃጠለው ሙስሊሞች ናቸው እዚህ ላይ የአማራ ወይም የኦሮሞ ሞት አያሳስብህም እንዳትሉ እኔ የሰው ፍጡር እንድገደል አንሻም ለምንስ ይገደላል ግን ዋና አላማው ዘር ከዘር ማጣላትም ስም የሚገደሉት ሙስሊሞች ናቸው ስለዚህ ለራሳችን ለድናችን ለሉአላዊነታችን ለንብረታችን መታገል አለብን አሁን ላይ እስልምናን ለማጥፋት የተነሱ ፓርቲወች አሉ እነ ኢዜማ አብን እናት ፓርቲ እነዚህ እስልምናን ከስር መሰረቱ ለማጥፋት የተነሱ ፓርቲወች ናቸው ስለኢዜማ እናውራ የኢዜማ ሊቀመንበር የሆነው ብረሀኑ ነጋ ምን እንዳለ ታቃላችሁ ኢስላማዊ ባንክ የለም ሴት ሂጃብ አትለብስም የሚል አቋም አላቸው ይህ ፓርቲ ተመረጠ ማለት እኛ ሙስሊሞች ምን እንደምንሆን አስቡት ወደ አብን እንምጣ ከስሙ እንደምንረዳው ቀጥታ ምህፃረ ቃሉን ካየነው አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ነው ነገር ግን በስተጀርባ ሌላ ተልእኮ አለው አብን ምረጡ ሲባል ከሶስቱ ስላሴ አንዱ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ውስጥ የሆነውን አብ ማለት እግዚአብሔር ምረጥ ማለቱ ነው ባጠቃላይ ስለዚህ ፓርቲ ብናወራው አያልቅም በጥቅሉ ከሆሉም የበለጠ የኢስላም ፀር ነው አሁን ላይ የሀይማኖት ግጭቶችን የሚያስነሳና ሀይማኖት ን ከሀይማኖት እያጋጨ ዘርን ከዘር እያጋጨ ያለ እንደውም የሰሞኑን የአጣየና የሸዋ ሮቢት ጉዳይ ዋና አብን እንደሆነ ብዙ መረጃወች አሉ እንድሁም አጣየ ላይ ሲመታቸው የነበረው የአማራ ልዩ ሀይል ኦሮሞ የሆኑትን ሙስሊም የሆኑትን ኦሮሞና ሙስሊም ስለሆኑ ብቻ እየመረጠ ሲገድል የነበረ ነው ይህም የአብን ስራ ነው የአማራ ልዩ ሀይል ማለት አብን ነው ለምን ኦሮሞ ይሁን አማራ ለምን ይገደላል እንድሁም የሰሞኑ ሰልፍ ላይ ሰልፉን ሲመሩት የነበሩት አብን ናቸው መፈክሩ የሚያስጠላ ነበር የኦሮሚያ ልዩ ዞን ይፍረስ ምናምን እንድሁም ኮምቦልቻ ላይ መፈክሩ ኮምቦልቻ መካና መድና አደለችም ሙስሊም አይመራንም የሚል ነበር ይህንን ሲያደርጉ የነበሩት አብን ናቸው የአጣዬ፣ የከሚሴ በአጠቃላይ የወሎ ኦሮሞ አርሶ አደር የሚጮኽለት ሚዲያና አክቲቪስት ባይኖረውም እውነት አለው የምንለው በምክንያት ነው። ከገንዘባቸው፣ ከህይዎታቸውና ከዲናቸው ብቻቸውን ሲከላከሉ የሰነበቱ ጀግኖቻችን ናቸው ታሪካቸውን አንረሳም መጀመሪያ በሰርግ ላይ ግጭት ቀስቅሰዋል የመስጅድ ኢማም ገድለዋል አጣዬ ላይ ዐብደልሏህ የተባለ ሙስሊም ቤት አቃጥለዋል ሌላ የታጠቀ ኃይል አለ እየተባለ በፌስቡክና በሚዲያዎች የሚነዛው ወሬ ውሸት ነው ራሱ የአማራ ልዩ ሀይል አብን ነው ስለዚህ ይህ ፓርቲ ተመረጠ ማለት ለሙስሊሞች አስቡት ምን እንደሚሆን ወደ እናት ፓርቲ ስመጣ ከስሙ እንጀምር እናትን ምረጡ ሲል እናት ማሪያምን ነው ምልክታቸው እናት ልጅ አቅፋ ይመስላል ነገር ግን በስተጀርባ ሌላ ተልእኮ አለው እሱም ማሪያም እየሱስን አቅፋ ነው እጩወቹ በጠቅላላ ዳቆኖች ናቸው በየቤተክርስቲያኑ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው ያለው ይህንን ፓርቲ ስልጣን ላይ አውጥተው ክርስቲያን ሀይማኖት ብቻ እንድኖር ማድረግ ነው የሰሞኑ ሰልፍ ላይም ከኋላ ከአብን ጋ ሁነው ሲያስተባብሩ እና የራሳቸውን የፓለቲካ ስረአት በሰልፍ ስም ሲያራምዱ ነበር ስለዚህ ወንድሞቼ እንቃ ይህ ፓርቲ ስልጣን ላይ ወጣ ማለት ምን እንደሚፈጠር አስቡት ስለዚህ እኛ ሙስሊሞች ይህ ሁሉ እንድፈጠር መፍቀድ የለብንም በጣም ተኝተናል ተኝተን ሀይማኖታችን እስልምና አደጋ ላይ ወድቋል እንታገል አንድ እንሁን ከላይ ያሉት ፓርቲወች ስልጣን እንድይዙ አንፍቀድ ማውገዝ አለብን ምርጫ ካርድ አውጥተን ከነዚህ ውጭ ያለን ፓርቲ እንምረጥ ካልመረጥን እነዚህ ፓርቲወች ተመርጠው እንጨቆናለን ምርጫ ካርድ እኛ አላወጣንም ማለት እነሱ እንዳሸነፉ እድል መስጠትና ሀሳባቸው እንድሳካ ማድረግ ነው ስለዚህ እኛ ካርድ ማውጣት መምረጥ አለብን ባይጠቅመንም የማይጎዳንን መምረጥ የብልጦች ነው ስለዚህ አሁን ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ የሚባል ፓርቲ አለ ይህ ፓርቲ ከሌሎች የተሻለ ጥሩ አስተሳሰብ የያዘ ፓርቲ ነው በርግጥ ብዙሀኑ እጩወች ሙስሊሞች ናቸው ሊጠቅሙን እንጅ ሊጎዱን አይችሉም እንምረጣቸው ከሌሎች ለኛ የተሻለ ነው የዚህ ፓርቲ ሊቀመንበር አብዱል ቃድር አደም ይባላል ሙስሊም ነው ብዙወቹ እጩ ተወዳዳሪወች ሙስሊሞች ናቸው ለኛ ሙስሊሞች የተሻለ ነው መከፋፈልን የሚቃወም ስረአት ያለው ፍተሀዊ ፓርቲ ነው በምንችለው ለቤተሰቦቻችን እናሳምን እና ምልክቱ ብእር ነው እንምረጥ እስልምናችንን እናድን እንታገል ለባንዳወች አሳልፈን መስጠት የለብንም በጥቅሉ አማራ ክልል ላይ በርብርብ እስልምናን ለማጥፋት ተነስተዋል ጎንደር ላይ ሙስሊሞች መቀበሪያ አጥተው መስጊድ መስሪያ አጥተው እየተሰቃዩ ጥያቄያቸው ውድቅ ሁኖ ታፍነው ተረግጠው ተቀምጠዋል በተለያዩ ቦታወች በደል እየደረሰብንን ነው እኛ ሙስሊሞች በጣም ተኝተናል ይህ ሁሉ በደል የሚደርስብን ከኛ ሰው ስለሌለ ነው በምንችለው ለድናችን እንነሳ እንታገል 🔈እባካችሁ ይህንን መልእክት እዚህ ኢትዮጵያ ለሚኖሩ ሙስሊሞች እስልምናችን አደጋ ላይ ነው እንዳውቁት እንድታጋሩአቸው ስል በአላህ ስም እጠይቃለሁ
Show all...
① #ከሸዋል_6ቀናቶችን የፆመ አመቱን እንደፆመ ነው ረሱል ② #ለዒባዳ የጌዜ ገደብ የለው #በኡስታዝ ሀቢብ ኑሩ የሸዋል ፆም ኒያ #👇 نَوَيْتُ الصِّيَامَ يَوْم غَدٍ عَنْ سِتٍّ مِنْ شَوَّالٍ http://t.me/elmudinIslamicstudio
Show all...
2019_06_05 - 08_44_16 AM.mp31.27 MB
ከሸዋል ወር 6ቱን ቀናት ከመፆም አንዘናጋ!! ::::::::::::::::::: የአላህ መልካም ፈቃድና እዝነት ሆኖ የተከበረውን የረመዷን ወር በሰላም ፆመን ጨርሰናል። ታዲያ በህይወት እስካለን ድረስ አንድ መልካም ስራ ሰርተን ልንጠግብና ልንሰላች (ልንታክት) አይገባም!!። ከአንድ መልካም ተግባር ወደሌላ መልካም ተግባር መሸጋገር የዘውትር ልምዳችን ሊሆን ይገባል። አላህ (ተባረከ ወተዓላ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏል:- فَإِذَا فَرَغْتَ فَانصَبْ ۝ وَإِلَىٰ رَبِّكَ فَارْغَب «(አንዱን ስራ) በጨረስክም ጊዜ (ወደ ሌላ ስራ) ልፋ፡፡ (ቀጥል)፡፡ ወደ ጌታህም ብቻ ከጅል፡፡» አልሸርህ 7-8 እዚህች አለም ላይ እስካለን የአላህን እዝነት ከጅለን መልካም ስራ ሰርተን በጨረስን ቁጥር፣ ዳግም የአላህን እዝነት በመከጀል ወደ ሌላ መልካም ስራ ልንሻገር ይገባል!!። ይህ ከአንድ በብቸኛው አምላኩ አላህ አማኝ ከሆነ ሰው የሚጠበቅ ተግባር ነው። በመሆኑም የረመዷን ወርን ፆመን ስንጨርስ ከተከታዩ የሸዋል ወር 6ቱን ቀናት ብንፆም ምንዳው ልክ አመት ሙሉ እንደፆምን እንደሚታሰብልን የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተናግረዋል። ታዲያ ይህን የመሰለ ታላቅ ምንዳ ለማግኘት ወሩን ሙሉ ፆመን እንዴት የሸዋልን 6 ቀናት መፆም ይከብደናል?!፣ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም አስመልክተው አንዲህ ብለዋል። ከአቢ አዩብ አል-አንሷሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “የረመዷንን ወር የፆመ ሰው፣ ከዚያም ከሸዋል ስድስቱን ቀናት ያስከተለ ልክ አመቱን (ሙሉ) እንደፆመ ይሆንለታል።” [ሙስሊም፣ አቡዳውድ፣ ትርሚዚይ፣ ነሳኢይና ኢብን ማጀህ ዘግበውታል] ከሰውባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “ከፊጥር በኋላ ስድስቱን ቀን የፆመ ሰው አመቱን ማሟያ ይሆንለታል፣ በመልካም የመጣ ሰው ለእርሱ አስር አምሳያዋ አለው።” [ኢብን ማጀህ የዘገቡት ሲሆን ሀዲሱ ሶሂህ ነው።] ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሌላ ሀዲስ እንዲህ ብለዋል:- “ረመዷንን ፆሞ ከሸዋል ስድስቱን (ቀናት) የፆመ ሰው በእርግጥም አመቱን (ሙሉ) ፆሟል።” [ኢብን ሂባን በሶሂሃቸው ዘግበውታል።] አደራ! አንዘናጋ!! ከቻልን (ባረከላሁ ፊኩም) መዘናጋት እንዳይመጣ እንዲረዳን አከታትለን እንፁም።
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.