en
Feedback
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Channel የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 14 386 subscribers, ranking 6 113 in the Religion & Spirituality category and 2 343 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 14 386 subscribers.

According to the latest data from 25 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 531 over the last 30 days and by 20 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 28.42%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects N/A% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 085 views. Within the first day, a publication typically gains 0 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 33.

📝 Description and content policy

Channel description not provided.

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 26 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

14 386
Subscribers
+2024 hours
+1147 days
+53130 days
Posts Archive
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መጋቢት ፩ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

"ጾማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ ፣ የተራቡት ሲደገፉ ፣ ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡"                ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ 2016 ዓ.ም ዐቢይ ጾምን አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል። መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ሁሉ የምትገኙ ምእመናንና ምእመናት ልጆቻችን በሙሉ!!! እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት የጾመ ኢየሱስ ሱባኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ! “ወእምዝ ኃደጎ ዲያብሎስ ወናሁ መጽኡ መላእክት ይትለአክዎ፡- ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ትቶት ሄደ፤ እነሆም ያገለግሉት ዘንድ መላእክት መጡ›› (ማቴ ፬፲፩)፡፡ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ተመሥጦ የምንጾመው ጾም፣ ጾመ ኢየሱስ ተብሎ የሚታወቀው ነው፡፡ ይህ ጾም በጥንት ጊዜ ሰው በኃጢአት የወደቀበትን ምክንያት፣ እንደዚሁም ሰው ኃጢአትንና ዲያብሎስን እንዴት እንደሚያሸንፍ ጌታችን እኛን ያስተማረበት ጾም ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ መጽሐፏ እንደምታስተምረን፣ ኃጢአትና ዲያብሎስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፤ ይህም ማለት ዲያብሎስ ባለበት ኃጢአት አለ ፤ ኃጢአት ባለበትም ዲያብሎስ አለ ማለት ነው፤ እነዚህ ሁለቱ የሚለያዩ አይደሉም፤ የመጨረሻ ግባቸው ደግሞ ሰውን መጣል ነው፡፡ዲያብሎስ የሰውን ደካማ ዝንባሌ ወይም በሆነ ነገር መጐምጀትን በሰው ሲመለከት ያንኑ የጐመጀበትን ክፉ ምኞት እንዲፈጽም፣ በረቂቅ የሰው ኅሊና ውስጥ ገብቶ በከፍተኛ ደረጃ ይገፋፋል፤ ሰውም በራሱ የመጐምጀት ዝንባሌና በዲያብሎስ ግፊት ለመንፈሳዊ ሕይወቱ ጐጂ የሆነውን ድርጊት ይፈጽማል ፤ ቀጥሎም ድርጊቱ በእግዚአብሔር ፊት በደል ይሆንና ከእግዚአብሔር ይለየዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ከተለየ ደግሞ ዘለዓለማዊ ሕይወትንና ክብርን ጨምሮ ብዙ መልካም ነገርን ያጣል፤ ኃጢአት የሚባለውም ይህ ነው፤ በቀደሙት አባትና እናት ማለትም በአዳምና ሔዋን የተከሠተው ነገርም ይኸው ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ኃጢአትን በጽድቅ፣ ዲያብሎስን በጾም በማሸነፍ የአሸናፊነትን መንገድ ሊያሳየን የመጣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአዳምና በሔዋን የተፈጸመው ውድቀት እንዴት እንደሚቀለበስ በዚህ ጾም አስተምሮናል፡፡ ጌታችን ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ፤ ዲያብሎስም መራቡን አይቶ ይጐመጅልኛል ብሎ በምግብ ፈተነው፡፡ የጌታችን መልስ ግን ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ የሚል ነበረ፣ በተመሳሳይም በፍቅረ ንዋይና በአምልኮ ባዕድ ፈተነው የጌታ መልስ ግን በተቃራኒው ነበረ፡፡ ዲያብሎስ በሦስቱም የማስጐምጃ ፈተናዎች ጌታ ሊሸነፍለት ካለመቻሉም በላይ "አንተ ሰይጣን ከኋላዬ ሂድ" ብሎ ሲገሥጸው ተሸንፎ ትቶት ሂዶአል በአሸናፊነቱ የተደሰቱ መላእክትም ወዲያውኑ መጥተው በክብረ አምልኮ አገለገሉት፤ በዚህ ድርጊት የምንመለከተው እውነታ ቀዳማይ አዳምን ባሸነፈበት ስልት ዳግማይ አዳም ክርስቶስን ለመጣል ዲያብሎስ የሄደበትን ርቀት በአንድ በኩል ስናይ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዳግማይ አዳም ክርስቶስ የቀዳማይ አዳም ተሸናፊነትና ውድቀት ለመቀልበስ ያሳየውን ጥብዓት እናያለን፡፡ በዚህም የቀደመው ውድቀት በኋለኛው አሸናፊነት ሙሉ በሙሉ ተቀልብሶ፣ ዲያብሎስ ጓዙን ጠቅልሎና ተስፋ ተስፋ ቆርጦ መሄዱን እናስተውላለን። የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን የአሸናፊነትን መንገድ በቃልና በተግባር አስተምሮናል፤ አሳይቶናልም፤ ይህንም ያደረገው እሱ አሸንፎልናል እያልን ለመኵራራት ሳይሆን፣ በእሱ ኃይል እየታገዝንና እሱ ባሸነፈበት ስልት እየተጠቀምን እንድናሸንፈው ነው፡፡ ሰይጣን የሚሸነፍበት ስልት በሌላ ሳይሆን፤ ሥጋዊ መጐምጀትን ከአእምሮአችን አውጥተን በመወርወር ነው፡፡ ሥጋችን በፍቅረ ንዋይ፣ በሥልጣን፣ በዝሙት እንደዚሁም በተለያዩ ሥጋዊ ምኞቶች ሊጐመጅ ይችላል፤ ያን ጊዜ ሰይጣን እነሱን እንድንፈጽም ሊገፋፋን ከበኋላችን እንደቆመ እናስብና "አንተ ሰይጣን ከኋላዬ ሃድ” እንበለው፡፡ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር ያስጐመጁን ነገሮችን ከኅሊናችን አውጥተን በመጣል እሱን ማሸነፍ አለብን፤ በዚህ ጊዜ ሰይጣን ይሸሻል፤ መላእክትም ወደኛ መጥተው ይረዱናል፣ ይጠብቁናል፤ ያግዙናል፣ ያድኑናል፡፡ ዲያብሎስ የሰዎችን የመጐምጀት ዝንባሌን ተከትሎ በመገፋፋት ዛሬም ዓለማችንን ለከፋ ውድቀት እየዳረጋት ነው፣ ሀገራችንን ጨምሮ በየአካባቢው የሚቀሰቀሱት አለመግባባቶችና ግጭቶች መንሥኤያቸው ከመጐምጀት ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ ግማሹ በሥልጣን፣ ግማሹ በሀብት፥ ግማሹ በራስ ወዳድነት፣ ግማሹ ደግሞ የበላይ ለመሆን በሚል እሳቤ የሰው ኅሊና በክፉ ምኞት ይጐመጅና በዲያብሎስ ገፋፊነት ወደ ተግባራዊ ጥፋት ይገባል፡ በውጤቱም ሰው ይጎዳል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ጾም ማለት እህልንና የእንስሳት ውጤቶችን ከመመገብ መከልከል ብቻ አይደለም፣ የእንስሳት ውጤት የሆኑትን ላለመመገብ ከምንወስነው በላይ እኩያት ፍትወታትንና ኃጣውእን ላለማስተናገድ በቁርጥ መወሰን ይጠበቅብናል፡፡ ስንጾም መገዳደልን፤ መጣላትን መለያየትን፤ መገፋፋትን በሆነ ነገር መጐምጀትን እርም ብለን በመተው ዲያብሎስን የምናሸንፍበት የአሸናፊነት ኅሊና መላበስ አለብን፣ ከክፉ ኅሊና እና ተግባር የተለየን ያህል በአንጻሩ ደግሞ በጎ ነገርን ለመስራት በእጅጉ መበርታት ይጠበቅብናል፡፡ ዲያብሎስ ተስፋ ቆርጦ የሚሸሸው ይቅር ይቅር ስንባባል፤ ለሰላምና ለአንድነት፣ ለፍቅርና ለስምምነት ስንቆም ነው! ከዚህም ጋር በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ጸያፍ የሆነው ግብረ ኃጢአት በዚህች ምድር እንዳይፈጸም ማኅበረ ሰባችን በተጠንቀቅ ሲቆም ነው፤ እንደዚሁም ደም መፋሰስ፣ አለመተማመንና በሴት ልጆቻችን የሚደርስው አካላዊ፣ መንፈሳዊና ሞራላዊ ጥቃት ሲቆም ነው፡፡ ጾማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ፣ ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡ ይህ ዓይነት መልካም ሥነ ምግባር በእያንዳንዱ የማኅበረሰብ አእምሮ ቦታ አግኝቶ ሲተገበር ትክክለኛውን ጾም ጾምን ማለት እንችላለን፣ ዲያብሎስም በእርግጠኝነት በዚህ ይሸነፋል፤ የሰው ጣዕመ ሕይወትም በዚህ ይለመልማል! ምድሪቱም በእግዚአብሔር በረከት ትሞላለች፡፡ ይህን ቅዱስ ተግባር በወርኃ ጾሙ በደንብ እንድንተገብረው ለመላው ኢትዮጵያውያን በተለይም ለኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ መንፈሳዊና አባታዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በመጨረሻም በሀገራችን ረሃብ የሚያጠቃቸው ወገኖች በበዙበት በአሁኑ ወቅት ፤ ሳንመጸውት ጾምን ጾምን ማለት ማጣፈጫ ወጥ የሌለው ምግብ መመገብ ማለት ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የቁርስ በጀቱን ለተራቡ ወገኖች በመለገስ ወገኖቹን በረሃብ ከመሞት እንዲታደግ ወቅታዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ መልካም የጾም ወቅት ያድርግልን! እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን፡፡

ዘወረደ "ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም!" ዮሐ 3፡13 እንኳን ለጾመ ሁዳዴ በሰላም አደረሳችሁ! ጾሙ የዲያብሎስ ድል መንሻ የኃጢአት መደምሰሻ ያድርግልን! የሰንበት ትምህርት
ዘወረደ "ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም!" ዮሐ 3፡13 እንኳን ለጾመ ሁዳዴ በሰላም አደረሳችሁ! ጾሙ የዲያብሎስ ድል መንሻ የኃጢአት መደምሰሻ ያድርግልን! የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

"እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።" መዝ 33፡8 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube
"እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።" መዝ 33፡8 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

እመ ምዑዝ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ https://www.tiktok.com/t/ZTLR3qkaK/

"አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።" መዝ 50፡1 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️YouTu
"አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።" መዝ 50፡1 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

"አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ የአፌንም ቃል አድምጥ!" መዝ 53፡2 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️YouTube 👇 https://www.youtub
"አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ የአፌንም ቃል አድምጥ!" መዝ 53፡2 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

የመጀመርያው መንፈቀ ዓመት ፈተና በጉራጌ ሀገረ ስብከት የወልቂጤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተስፋ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ተሰጠ። የካቲት 27/6/2016 ዓ.ም (የሰንበት ትምህርት ቤቶ
+9
የመጀመርያው መንፈቀ ዓመት ፈተና በጉራጌ ሀገረ ስብከት የወልቂጤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተስፋ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ተሰጠ። የካቲት 27/6/2016 ዓ.ም (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) በወልቂጤ ከተማ የሚገኘው ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ተስፋ ሕይወት ሰ/ት/ቤት በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ሲያስተምራቸው የነበሩ ከአንደኛ ክፍል እስከ አሥራ ሁለተኛ ያሉ ተማሪዎችን የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የማጠቃለያ ፈተና አስፈተነ። ፈተናው የተከናወነው ከየካቲት 23-24 ሲሆን ሁሉም ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን ተነግሯል። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube @eotc-gssu 👉 Facebook @EOTC.GSSU 👉 Telegram @SSUGlobal 👉 Tiktok @eotc_gssu

"እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን።" የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️YouTube 👇 https://www
"እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን።" የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። https://www.tiktok.com/t/ZTLdVHjfe/

"አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።" 2 ዜና 7፡16 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ
"አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።" 2 ዜና 7፡16 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu