cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

ማኅቶት ማለት መብራት ነው ቶኔቶር ደግሞ የኢትዮጵያ የጥንት ስሟነው እናም ማኅቶተ ቶኔቶር ማለት የኢትዮጵያ መብራት ማለት ነው መብራቷ ደግሞ መካከሏን ገነት ዳሯን እሳት እያለች የምትጠብቃት የምትጸልይላት እምነቷ ቅድስት ተዋህዶ ጥንት የሌላት ጥንታዊት ዘመን የሌላት ዘመናዊት ናት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምሮ ነው አስተያየት ካለዎት @mahtotetonetor2 @mahtotetonetor1

Show more
Advertising posts
1 180
Subscribers
-124 hours
+67 days
+2130 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
#የትንሣኤው ሦስተኛ ቀን ቶማስ_ይባላል የትንሣኤ ሦስተኛው ዕለት ቶማስ ይባላል፡፡ ቶማስ ማለት ፀሐይ ማለት ሲሆን ፣ዲዲሞስ ማለት ደሞ መንታ ማለት ነው፡፡ ማመኑ በፀሐይ ፤መጠራጠሩ በመንታነት ይመሰላል፡፡ ቶማስ ሰዱቃዊ ነው ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን የለም ብለው ያምናሉ ቶማስም ሰዱቃዊ ስለሆነ ትንሣኤ ሙታንን የማይቀበል የማያምን ሰው ነበር፤ የጌታን ትንሣኤ ለመቀበል የተቸገረው አእምሮውን ገድሎት የነበረው ሰዱቃዊው ሀሳብ ስላልተለየው ነበር፡፡ ይሄ ብቻ ሳይሆን ጌታ አልዓዛርን ለማስነሣት ሐዋርያትን እንሂድ ሲላቸው "ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" ይላል ዮሐ 11፡16፡፡ የጌታችንን ከሞት መነሣት እርግጥ ሆኖ ሲያገኘው ግን የሞተው አእምሮው/ሀሳቡ ተነሥቷል ፤ "ጌታዬ አምላኬ" ብሎ ጠርቶ ሕያውነትን ተቀላቅሏል፡፡ "አንሥአኒ በትንሣኤከ፤ በትንሣኤህ አንሣኝ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ቶማስን በትንሣኤው አንሥቶታል፤ ስለዚህ የትንሣኤው 3ኛው ቀን ለቶማስ መታሰቢያ ሆኗል፡፡ ቶማስም ከ 3 ዓመት ትምህርት በኋላ ከጥርጥር ሞቱ ተነሥቷልና። ቶማስ ጠያቂ ነው፤ ያልገባውን ይጠይቃል፤ ማየት የፈለገውን ልየው ይላል፡፡ በዚህም ፍጥረታዊ ወይም ሳይንሳዊ ሰውን ይመስላል፤ ፍጥረታዊ ሰው ተነግሮት አያምንም፤ካልጨበጠ ካልዳሰሰ እውነትነቱን አይቀበልም ፦ " ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 2 : 14፡፡ ቶማስ የጌታችንን ድርጊቶች በጥርጣሬ ይመለከት የነበረ ሐዋርያ ነበር ፡፡ ለምሳሌ ጌታችን አልዓዛርን ለማስነሣት ሲሄድ ደስተኛ አለመሆኑን በሞት ስጋት ገልጾ ነበር፦ "ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" በማለት እንደተጻፈ፡፡ ዮሐ 11 : 16፡፡ በሌላ ጊዜም ቶማስ መንገዱን የጠየቀው ለዚህ ነበር፤ ያ መንገድ ወዴትና የት የሚወስድ ነው? የሚል ጥያቄ በውስጡ ይመላለስ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው፦ "ቶማስም። ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው" ዮሐ 14 : 5፡፡ በዚህ ሁሉ ጥያቄውና ጥርጥሩ ግን ጌታችን አንድም ቀን ሰልችቶት ተቆጥቶት ወይም በጥርጣሬ አትከተለኝ ብሎት አያውቅም ፤ ድካማችንን የሚያውቅ የሚሸከምልን አምላክ ነውና፤ ዛሬም ምንም ያህል ኃጢአት ብንሠራ ተጸጽተን በንስሐ ከተከተልነው አትከተሉኝ አይለንም፤ ከየትኛውም ክህደት ከየትኛውም ሃይማኖት ብንመለስ ወደ እውነተኛው ሃይማኖት ከገባን በኀላ አልፈልጋችሁም፡ውጡልኝ አይልም፤ "ወደኔ የመጣውን ወደ ውጪ አላወጣውም "ብሎናልና፤ ዮሐ 13፡32፡፡ ጌታችን ከሞት ከተነሣ በኀላ ለሁሉም ሲገለጥ ለቶማስ ግን አንድ ሳምንት ሙሉ አልተገለጠለትም ነበር፤ ቶማስም ጌታን በአካል ያዩት ሐዋርያት ሲነግሩት፦ • የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ • ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ • እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም" ይላቸው ነበር። ዮሐ 20 : 25፡፡ ጌታችን ይህንን ያደረገበት ምክንያትም፦ 1. ቶማስ በውስጡ መንፈሳዊ ቅናት እንዲያድርበት፤ ሁሉም ስለ ትንሣኤው ሲናገር እየሰማ እንዲጓጓ ነው፤ ይህ መጎምጀት ወደ ፍጹም መንፈሳዊነት ይመራልና፤ እኛም ዛሬ ለመንፈሳዊ ነገር ስንጓጓና ስንቸኩል እግዚአብሔርን እናገኘዋለን፤ በውስጣቸው የሚቀጣጠለው ፍቅረ እግዚአብሔር እርሱን ራሱን ይጠራዋል፤ ቀድሞም ለሞት ያደረሰው ፍቅር ነውና፡፡ 2. ጌታችን የአንዲት ነፍስ ጉዳይ ጉዳዩ እንደሆነ ያጠይቃል፡፡ የተገለጠው ለቶማስ ሲል ነበር ለሱም ሲባልም አስቀድሞ በሌለበት የተገለጠበት ፦ • ዕለት • ሰዓት • ቦታ • በተዘጋ ደጅ መግባቱ • ሰላምታው (ሰላም ለሁላችሁ ይሁን) • ሁኔታው /መልኩ አልተቀየረም፡፡ ቶማስ ባለበት የተገለጠበትና ሳይኖር የተገለጠበት ልዩነት ቢኖረው በመጀመሪያ ቀንና በስምንተኛ ቀን መሆኑ ብቻ ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየው ፦ • ለሰው ሁሉ ያለውን ክብር/ፍቅር/ግድ • ትንሣኤው እርግጥ መሆኑን • ፍጹም ቸርነቱን • መጀመሪያ ያዩትም መጨረሻ የሚያዩትም በአንድነት እንደሚወርሱት ያጠይቃል፡፡ የቶማስ የመጨረሻ እምነት፦ "ጌታዬ አምላኬም" ፤ዮሐ 20፡28፡፡ ይህ ቃል የመጨረሻው የእምነት ጥግ ቃል ነው፤ የምናምነው ይህን ነው ፤ የምንናገረው ይህን ነው፤ የምንሰብከው ይህንን ነው፤ ከዓለም የምንለየውም በዚህ ቃል ነው፡፡ ቶማስ ብዙ ቢጠይቅም፤ ቢጠራጠርም በመጨረሻ ግን "አምላኬ" ብሎ አመነ፤ ዛሬ "ኢየሱስን አምላክ " ብለው መጥራት የሚከብዳቸው ብዙዎች ናቸው፤ እኛ እንኳን የቶማስን ቃል የወንጌሉን ፍጥጥ ያለ እውነት ስንናገር ይጠሉናል፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድላቸው!!! ቶማስ ጌትነቱን አምላክነቱን ያመነው በመዳሰስና በማየት ከሆነ እኛስ ሳናይ እንዴት እናምናለን እንዳንል ጌታችን " ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው" በማለት ወሳኝ መልእክት አስቀምጦልናል፡፡ ዮሐ20 : 29፡፡ ወንጌላዊውም ታሪኩን ሲጠቀልለው፦ " ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል" በማለት ይህን አንብበን፤ ሰምተን ብቻ እንድናምን አስገንዝቦናል፡፡ ዮሐ 20 : 31፡፡ እኛም የቶማስን እጅ እጅ አድርገን ዳሰነዋል የሐዋርያትን ዓይን ዓይን አድርገን አይተነዋል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም "ክብሩን አየን.." እንዳለ አባ ሕርያቆስም " ከእርሱ ጋር በላን ጠጣን.." እንዳለ እኛም እንደ ቶማስ " ጌታችን አምላካችን" እንላለን!!!!! በዚህም እኛ "ብፁዓን ነን"!!! እንድናምነው የረዳን አምላካችን ይመስገን!!!! በበጎ ሥራም ደስ እንድናሰኘው ይርዳን!!! በረከተ ሐዋርያት ይደርብን!!! አሜን!!! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
5905Loading...
02
“ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም እምይዕዜሰ፤ ይህን ፤ ፍስሐ ወሠላም፡፡” መልካም የትንሣኤ ክርስቶስ ሲነሳ በራሳችን ምኞትና የሥጋ ፈቃድ እኛ እንዳንቀበር እንጠንቀቅ ! ዲ/ን ኤርምያስ @mahtotetonetor2
9812Loading...
03
ከእጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ገዳም ለዚህ ግሩፕ አባላት። ቀጥታ ቃላት ሳንጨምር ያሉንን ይኸው ~እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ ።ገንዘብ ወደ ገዳሙ አካውንት የምታስገቡ ሁሉ እኛ እሱ የሚያውቃችሁን የእናንተን ስም በጸሎት ሰዓት ለማንሳት አንደክምም ምንም እንኳን ኃጢአተኞች ብንሆንም እግዚአብሔር ይሰማናል ብለን እናምናለን ።የጥቂት እህቶችና ወንድሞች ስም ብቻ ነው የተላከልን የገንዘቡን መጠን ስንመለከት ብዙ ሰዎች እየተረባረቡ ነው በዚህም ከልብ እናመሰግናለን እግዚአብሔር ያክብርልን ።
1 0611Loading...
04
https://youtu.be/rlKB0bABiTM?si=vhtle6XvOri8xo8M
1 2648Loading...
05
የሕፃናት ሁሉ ተምሳሌት የስነ ምግባር ቀንድ ሕፃን ሐረገወይን እኛም የበኩላችንን እናድርግ 100,000 ብር እንድትሸለም እናድርግ ሕፃን ሐረገወይን ቀለሙ በ19:00ውስጥ 100,000,000 view
9042Loading...
06
በአል❌ በዓል✅ ትንሳኤ❌ ትንሣኤ✅
1 2672Loading...
07
Media files
1 3220Loading...
08
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እና ዮሐንስ ዘደማስቆ ሐዋርያው ጴጥሮስ ጌታ በዐረገ በዓመቱ (34 ዓ.ም.) ቅዱሱን እሳት በመቃብሩ ስፍራ ማየቱን ጽፈዋል። ይህ ተአምር አሁን እስካለንበት ዘመን የቀጠለ ሲሆን፣ ሁል ጊዜም በትንሣኤ በዓል ዋዜማ ቅዳሜ ቀን ይታያል። ስለዚህ የሚያስደንቅ ተአምር ብዙ የማያምኑ ሰዎች በራሳቸው መንገድ ለማጣራት ሞክረዋል። እስኪ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ታሪክ ላጫውታችሁ። በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ… ዕለቱ ቅዳሜ ጠዋት 4 ሰዓት የትንሣኤ ዋዜማ ነው። የእስራኤል አይሁድ ፖሊሶች እና የከተማዋ ከንቲባ  ይህ እሳት ይፈልቅበታል የተባለውን የጌታን መቃብር እውነትነት ማረጋገጥ ስለ ፈለጉ በውስጡ ለእሳቱ መነሣት ምክንያት የሚሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች ካሉ በሚል ለሁለት ሰዓታት ያህል ሦስት ጊዜ ጥብቅ ፍተሻ አደረጉ። ግን ምንም ሊያገኙ አልቻሉም። ቀጥሎም ሁለት መቃብሩን የሚጠብቁ ሙስሊሞችን በማምጣት ልክ የቀድሞዎቹ አይሁድ የጌታን መቃብር እንዳተሙ እነርሱም መቃብሩን ዘግተው በሰም እንዲያትሙት አደረጉ። ይህንም ተከትሎ በቦታው የነበሩ አረብ ክርስቲያኖች ቱርክ እስራኤልን በተቆጣጠረችበት በ13ኛው ክፍለ ዘመን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በየትኛውም ቦታ ቢሆን እንዳይዘምሩ የተከለከሉትን ቆየት ያለ ዝማሬ በኅብረት ከፍ ባለ ድምፅ መዘመር ጀመሩ። መዝሙሩም:- “እኛ ክርስቲያኖች ነን። ለብዙ መቶ ክፍለ ዘመናትም ክርስቲያኖች ነበርን። እስከ ዘላለምም እንዲሁ እንሆናለን፣ አሜን!” የሚል ነበር። እኩለ ቀንም ሲሆን የግሪኩና የአርሜንያው ፓትርያርክ፣ የግብፁ ሜትሮፖሊታንት እንዲሁም  ቀሳውስት እና ዲያቆናት ወደ ታተመው የክርስቶስ መቃብር መጡ። ከብዙ ጸሎት እና ምስጋናም በኋላ የታተመው የክርስቶስ መቃብር እንዲከፈት አደረጉ። ፓትርያርኩም ሞጣህቱን ብቻ አስቀርተው ከላይ የለበሱትን ልብሰ ተክህኖ በማውለቅ በክርስቶስ የዕድሜ ቁጥር ልክ ሦስት 33 ያልበሩ ሻማዎችን ይዘው ጨለማ ወደ ነበረው መቃብር ገቡ። ምእመናኑም ከውጭ ሆነው በአንድ ድምፅ ኪርያላይሶን (አቤቱ ይቅር በለን) እያሉ በመዘመር ይጠባበቁ ጀመር። ወደ ቅዱሱ መቃብር ገብተው የነበሩትም የግሪኩ ፓትርያርክ ያን በሰው ያልተቀጣጠለ እና የክርሰ‍ቶስን የትንሣኤ ብርሃን የሚያበሥረውን አምላካዊ እሳት ይዘው ብቅ አሉ። ይህን ጊዜ ጎልጎታ በእልልታ ተሞላች የቤተ ክርስቲያኑም ደወል በሐሴት ይደወል ጀመር። ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ እንኳን አደረሰን!!! ዲያቆን አቤል ካሳሁን
1 1834Loading...
09
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃኅ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ። (መዝ ፸፰፡፷፭/ ከውጭም ከሀገር ውስጥም በቀጥታ የደወላችሁ ቴክስትም ለእንኳን አደረሰህ መልእክታችሁ ባለመመለሴ ይቅርታ እየጠየቅሁ ለማኅቶተቶኔቶር አባላትና በዓለም ሁሉ ለምትገኙ አመሰግናለሁ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ !
1 2081Loading...
10
Media files
1 3470Loading...
11
አብረን ማኅሌት እንቁም ከሁሉ አስቀድሞ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል። "ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል። መልክአ ስዕል አይባልም። ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና ከአራቱ ወንጌላት 3ቱ ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል። ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭ ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤ ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤ ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ። አርያም፦ ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ  በትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ። ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ፤   ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤ ይገብሩ በዓለ ደመናት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። ምልጣን፦ ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን። አመላለስ፦ 'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪//፩/ ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/ ወረብ፦ ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/ እስመ ለዓለም፦ ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ። አመላለስ፦ ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/ ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/ ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ  ሰላም ይፃፋል ሰላም፦ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ ሰአሊ በእንቲአነ፤ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ፤ ያስተርኢ ኂሮቶ ላዕሌነ፤ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ። አመላለስ፦ ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/ ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፬/ ኪዳንን ከተደረሰ በኃላ መዝሙር በ፩፦ ሃሌ ሉያ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር፤ ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ፤ ወይወውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። አመላለስ፦ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ፤/2/ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ/4/ ሰላም ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ፤ ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት፤ ወኮርዕዎ ርእሶ በኅለት፤ ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት፤ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት። ከዚህ በኃላ ወደ ስርዓተ ቅዳሴ
1 2587Loading...
12
ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ
1 3192Loading...
13
ሁሉን የያዘውን ያዙት:ሁሉን የሚገዛውን አሰሩት የሕያው አምላክን ልጅ አሰሩት:በቁጣ ጎተቱት በፍቅር ተከተላቸው:በሚሸልተው ፊት እንደማይነገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት
1 5667Loading...
14
ዓርብ በ(ለ)ፈጠረው ዓርብ ተሰቀለ። ኦ ትዕግሥት ዘመጠነዝ ትግዕግሥት!!
1 7138Loading...
15
Media files
1 8031Loading...
16
የገጠሪቷ ቅድስት ቤተክርስቲያን ችግር የተረዳችሁ የሚያሳስባችሁም በትክክል ደራሽነታችሁን እያሳያችሁ መሆናችሁ በእውነት እጅግ ደስ ይላል እኔ በጣም አንዳንዶቻችሁ የምትልኩት ገንዘብ በትክክል መድረሱ አለመድረሱን ለሰከንድ እንኳን ሳትጠራጠሩ እየሰጣችሁ እየላካችሁ መሆኑ ስመለከት ሁልጊዜም የእምነታችሁ መጠን ይደንቀኛል ከትንሹ 10 ብር -55,000ብር የላካችሁ እንዳላችሁ የባንክ transaction የተላከልኝን ለማየት ችያለሁ።እግዚአብሔር ቤታችሁን በበረከት ይሙሉ ሰላምን ይስጣችሁ በጎደለ ይጨምርላችሁ በገዳሙ የምንሰራው ሥራ ሁሉ በሁላችሁም ስም አንድ የጋራ የሆነ ስም ሰይመን ለማስታወሻ ወደ ገዳሙ የመጣ ሰው ሁሉ ከዚህ የበረከት ሥራ አገልግሎት እንዲማርበት ቀጣዩ ትውልድ ማኅበራዊ ሚዲያን ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲጠቀምበት እንደ ምሳሌ እንዲሆን እንደምናደርግ ሙሉ ተስፋ አለኝ ።መድኃኒዓለም ሰላምን ይስጠን በየአላችሁበት ይጠብቃችሁ።
1 7821Loading...
17
Media files
1 5630Loading...
18
+ አትክልተኛ መስሏት ነበር + መግደላዊት ማርያም በዕለተ እሑድ ገና ጨለማ ሳለ ወደ ጌታ መቃብር ልትሔድ ተነሣች፡፡ እርግጥ ነው በጨለማ መውጣት ያውም ለሴት ልጅ የሚያስፈራት ቢሆንም ለዚህች ቅድስት ግን ከክርስቶስ ሞት በላይ ሌላ ጨለማ ገዝፎ ሊታያት አልቻለም፡፡ የሕይወትዋ ብርሃን በመቃብር ውስጥ አድሮአልና ሌላ ብርሃን ነግቶ መንገድ እንዲያሳያት አልጠበቀችም፡፡ ለሰው ሁሉ የሚያበራውን መብራት ክርስቶስን ከመቃብር ዕንቅብ በታች ካኖሩት ሦስት ቀን መሆኑ እንጂ የቀንና ሌሊቱ ልዩነት አልታወቃትም፡፡ በእርግጥም ሰባት አጋንንት ከላይዋ ላይ አውጥቶላት የነበረችን ሴት የቱ ጨለማ የቱ ጋኔን ሊያስፈራት ይችላል? ‹‹ፍቅር ፍጹም ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል››ና ጨለማውን ሳትፈራ ይህች ሴት እስኪነጋ ልቆይ ሳትል ወደ ጌታችን መቃብር ገሰገሰች፡፡ እንደጠበቀችው ግን ጌታችንን በመቃብር አላገኘችውም፡፡ በዚያ የለም፡፡ በመቃብር አለመገኘቱ ለእርስዋም ሆነ ለደቀ መዛሙርቱ ተስፋ የሚያስቆርጥ ኀዘን ላይ የሚጥላቸው ነገር ሆነ እንጂ ‹‹እነሣለሁ›› ማለቱን እንዲያስታውሱ ምክንያት አልሆናቸውም፡፡ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን እንኳን ጲላጦስ ፊት ቀርበው ‹‹ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ፡- ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን›› ብለው ነበር፡፡ (ማቴ. 27፡63) ሐዋርያቱና ማርያም መግደላዊት ግን መቃብሩ ባዶ ሆኖ ሲያዩ እንኳን ‹እነሣለሁ› እንዳለ ትዝ አላላቸውም፡፡ ስለዚህ የእምነት ጉድለታቸውም ደቀ መዛሙርቱን ‹‹እናንተ የማታስተውሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ›› ብሎ ፤ እርስዋን ደግሞ ‹‹አትንኪኝ›› ብሎ ገሠፆአቸዋል፡፡ (ሉቃ. 24፡25፣ ዮሐ. 20፡ 17) መግደላዊትዋ ጌታችንን በመቃብር ብታጣውም ‹በዚህ ከሌለማ ወደ ቤቴ ልሒድና ልረፍ› ከማለት ይልቅ በዚያው ቆማ ታለቅስ ጀመር፡፡ ከዚህ በኋላ በዕንባ በፈዘዙ ዓይኖችዋ ሁለት መላእክት ከመቃብሩ ግራና ቀኝ ሆነው ተቀምጠው አየች፡፡ ሳታስተውልም ‹‹ጌታዬን ወስደውታል›› አለቻቸው፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳብራራው) መላእክቱ ወደ ውጪ ሲያዩ ዓይናቸውን ተከትላ ዘወር ስትል ጌታችንን ቆሞ አየችው፡፡ ሆኖም አላወቀችውም፡፡ ‹‹ኢየሱስም አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሻለሽ ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት፡፡ እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሏት ፡- ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው›› (ዮሐ. 20፡15) ይህንን ተከትሎ ጌታችን ስላለማመንዋ ገሥፆአት ማንነቱን ገለጸላት፡፡ በዚህም ይህች ቅድስት ትንሣኤውን ከሰበኩ የጽዮን ልጆች አንዲትዋ ሆነች፡፡ የእስራኤልን ነጻ መውጣት የሙሴ እኅት ማርያም በከበሮ እንዳበሠረች ማርያምም የሰው ልጅን ነጻ መውጣት ያለ ከበሮ አወጀች፡፡ እርስዋን ብቻም ሳይሆን ሌሎች ሴቶችንም ዓርብ ዕለት እያለቀሱ ደረት እየመቱ ሞቱን በዕንባ አጅበዋልና እሑድ ዕለት የትንሣኤው ዜና አብሣሪዎች ለመሆን አበቃቸው፡፡ ሴት ልጅን ‹‹ደስ ይበልሽ›› በማለት የተጀመረው የአምላክ የማዳን ሥራም ሴት ልጅ ራስዋ ለሌሎች ‹‹ደስ ይበላችሁ›› ባይ እንድትሆን በማድረግ ተጠናቀቀ፡፡ ማርያም መግደላዊት ‹‹የአትክልት ጠባቂ መስሏት ነበርና ፡- ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው›› የሚለው ንግግር እንዲሁ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን ይህንን ቃል የተናገረችው ሳታውቀው ቢሆንም ንግግርዋ ግን ከስኅተትነቱ ይልቅ ቅኔነቱ የሚበልጥ ንግግር ነው፡፡ ‹‹አትክልተኛ መስሏት ነበር›› የሚለው ቃል ምንኛ ድንቅ ነው? አበው በትንቢተ ሕዝቅኤል 44ን ሲተረጉሙ ‹ከእውነት የሚሻል ስኅተት ከመግደል የሚሻል መሳት አለና›› ያሉት ይህንን ዓይነቱን ሳይሆን አይቀርም፡፡ ለመግደላዊት ማርያም ክርስቶስ አትክልተኛ መስሏት ነበር፡፡ ወይ ግሩም! ክርስቶስ በምድር በተመላለሰ ጊዜ ለሰዎች ‹ያልመሰላቸው› ምን ነገር አለ? እንደተወለደ ለአይሁድ ‹የዮሴፍ ልጅ መስሏቸው ነበር› ፣ ለሔሮድስ ደግሞ መንግሥቱን የሚቀናቀን ምድራዊ ንጉሥ መስሎት ነበር፡፡ ለኒቆዲሞስ ነቢይ መስሎት ነበር ፣ ለሳምራዊቷ ሴት ደግሞ መጀመሪያ ውኃ የሚለምን ተራ ሰው መሰላት ፣ በኋላ ደግሞ ነቢይ መስሎ ታይቷት ነበር፡፡ ክርስቶስ ለብዙዎ ያልመሰላቸው ምን አለ? ለግማሹ ኤልያስ ፣ ለአንዳንዱ ሙሴ ለሌላው ኢያሱ መሰለው፡፡ ለኤማሁስ ተጓዦች ‹መንገደኛ› ፣ ለሮም ወታደሮች ‹ወንጀለኛ› ፣ ለሔሮድስ መኳንንት ‹አስማተኛ› መስሏቸው ነበር፡፡ እኛ እርሱን እንድንመስል እርሱ እያንዳንዳችንን መስሎ ተሰደበ ተወቀሰ በመከራ ተሰቅሎ ሞተ፡፡ ዛሬ ደግሞ ለመግደላዊት ማርያም ‹‹አትክልተኛ›› መሰላት፡፡ ማርያም ሆይ በአንድ በኩልስ ልክ ብለሻል፡፡ ያየሽው እርሱ አትክልተኛ ነው፡፡ በእውነትስ አትክልተኛ ካልሆነ ‹‹አዳም ሆይ ወዴት ነህ›› እያለ በገነት ዛፎች መካከል ምን አመላለሰው? አንቺ አልተሳሳትሽም ‹‹ወይንን ተከልሁ አላፈራም ፣ ለወይኔ ያላደረግሁት ምን አለ? በእኔና በወይኔ መካከል ፍረዱ›› ብሎ የጠራን እርሱ አይደለምን? ‹‹ዘር ዘሪ ሊዘራ ወጣ ፣ ዘር ዘሪው እኔ ነኝ ፤ አጫጆቹ መላእክት ናቸው›› ብሎ በምሳሌ ያስተማረ እርሱ አይደለምን? ከዚህ በላይ አትክልተኛ ከየት ሊመጣ? ‹የወይን ሥፍራን ነበረችው ቅጥርም ቀጠረላት› በተባለችዋ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁላችንን ከአብ ጋር ላንነቀል የተከለን ፣ የጎኑን ውኃ እያጠጣን ፣ በመስቀሉ እየኮተኮተ የሚያሳድገን ‹‹ጳውሎስ ሲተክል አጵሎስ ሲያጠጣ ጌታ ያሳድግ ነበረ›› የተባለለት አትክልተኛ እርሱ አይደለምን? ሦስት ዓመት ተመላልሶ ፍሬ እያጣብን አዘነ እንጂ ፣ እሾኽና አሜከላ እያበቀልን አስመረርነው እንጂ እርሱስ ብርቱ አትክልተኛ ነበር ፤ ስለዚህ መግደላዊት ማርያም ሆይ አትክልተኛ ቢመስልሽም አልተሳሳትሽም፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ›› የሚለው ጥያቄም ቢሆን ከእውነታው አንጻር እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ጌታን በእርግጥ ከመቃብር ማን ወሰደው? ማንስ አስነሣው? ራሱ አይደለምን፡፡ ማርያም ‹አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ› አለችው፡፡ ማርያም ሆይ ጥያቄሽ ተገቢ ነው ፤ ብቻ አጥብቀሽ ጠይቂው ፤ የወሰደው እርሱ ራሱ ነው፡፡ ሥጋውን ከመቃብር ሕያው አድርጎ ነስነሥቶ የወሰደው ከፊትሽ ቆሟል፡፡ ማስረጃ ከፈለግሽ ‹‹ነፍሴን ደግሞ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም ፤ ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ›› ብሎ ሲናገር ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ሰምቶ ማስረጃ መዝግቦ ይዞበታል፡፡ አጥብቀሽ ያዢው! እንዳትለቂው! በፈቃዱ እንደሞተ ነፍሱንም ሊያኖራት ሥልጣን ያለው ከመቃብርም በሥልጣኑ የተነሣው እርሱ ነው፡፡ ማንም ወሰደው ሲሉ ብትሰሚ አትመኚ ፤ ኢየሱስን ከሙታን መካከል ወስዶ ሕያው ያደረገው ይኸው ከፊትሽ የቆመው አትክልተኛ ራሱ ኢየሱስ ነው፡፡ እግሮቹን ወድቀሽ ያዢ እንዳትለቂው ፤ ይህ አትክልተኛ ባዶ ያደረገው መቃብርን ብቻ እንዳይመስልሽ፡፡ ሲኦልን ብታዪ ምን ልትይ ነው? በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የራሱን መቃብር ባዶ ከማድረጉ በፊት የሲኦልን የብረት መወርወሪያ ሰባብሮ አእላፋት ነፍሳትን ዘርፎ ወደ ገነቱ ወርዶ ነበር፡፡ በዚያም ምርኮውን ሸሸገ፡፡ አሁን ደግሞ የቀረውን መቃብር ባዶ አድርጎት ቆሟልና እንዳትለቂው፡፡መግደላዊት ማርያም ሆይ ‹‹አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ››
2 06610Loading...
19
ጌታ የተገረፈው 6,666 ጊዜ ነው ለእድሜው ቁጥር (33) ሲካፈል 202 ጊዜ ይመጣል ...እድሜውን ሙሉ በዓመት 202 ጊዜ የተገረፈ ያህል መከራ ተቀብሏል !!! ቆዳው ከሰውነቱ እስኪነሳ ሥጋው እስኪያልቅ አጥንቱ እስከሚታይ ድረስ ተገርፏል!!! ሥጋው በጅራፍ ጫፍ እስኪበተን ደሙ ምድር ላይ እስኪረጭ ድረስ ተገርፏል!!! የኛ ጌታ!!! “ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።”   — ኢሳይያስ 53፥7 👉እኛ ግን እድሜ ዘመናችንን የአንዱን ግርፋት ስቃይ እንኳን በማሰብ መረዳት አልቻልንም😭 እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው @mahtotetonetor2
2 28521Loading...
20
ሕማም ለአንድ ሲሆን መከራ ስቃይ ማለት ነው ሕማማት ማለት ደግሞ መከራዎች ስቃያት ፀዋትወ መከራ/ ብዙ የመከራ የስቃይ ዓይነት ማለት ነው፡፡ ሕማማት በሁለት ተከፍሎ ይታያል 1. የሰው ልጆች ሕማማት 2. የጌታ ሕማማት ➊የሰው ልጆች ሕማማት፦ ይህ የሰው ልጆች ሕማማት የሚጀምረው አዳምና ሔዋን ዕፀበለስን በልተው ልጅነቱን ካጡበት ከክብርና ልብሰ ብርሃን ከተራቆቱበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ከዚህ በኀላ ያለው ጊዜ የፍርሃት የድንጋጤ የጭንቀት እና በማይሞላ ዓለም በምድረ ፋይድ/ምድረ ፍዳ የመቅበዝበዝ ሕይወት የተስተናገደበት ዘመን ነው፡፡ ይህም በሥጋ ሞትን በነፍስ የሞት ሞትን በሥጋ ወደ መቃብር በነፍስ ወደ ሲኦል መውረድን አስከትሏል፡፡ ሕማማት መባሉም የሰው ልጅ በሥጋ ብቻ ያይደለ በነፍስም በመንፈስም በስቃይ ጅራፍ እየተገረፈ የኖረባቸውን ድርብ ድርብርብ መከራዎችን ለመግለጥ ነው፡፡ ሕማማተ አዳም ከመርገሙ ጋር በዘር ተወርሷል መርገሙና የመርገሙ ውጤት ሞት ከእመቤታችን በስተቀር አዳም በኩር ለሆነለት ሥጋ ነፍስና መንፈስ ሁሉ ተላልፏል፤ መልኩን ይዘን ስንወለድ መርገሙንና ሞቱንም ወርሰን እንወለድ ነበር፡፡ በዚህ አካሄድ ሰው ሁሉ የስቃያቱ እኩል ተካፋይ ስለ ነበር ሀሉም ሕማማት ላይ ነበር፡፡ ➋ ሕማማተ ክርስቶስ፦ ለሕማማተ ክርስቶስ መነሻው የሰዎች ሕማማት ነው፡፡ ሕማማተ ክርስቶስ የሚጀምረው በበረት በመወለድ ነው • በቤተልሔም ብርድ • በግብፅ ስደት • በናዝሬት ድህነት • በኢየሩሳሌም ጾም ጸሎትና ስግደት • ረኀብና ጥም ድካምና እንግልት • የማይቋረጥ ትምሕርት • እኛ የማናውቀው ዝምታው ትካዜው ....ሁሉ ሕማማት ነው!!! ♥ከሌሎቹ ሕማማት የሚለየውና በቃላት ለመግለጥ ለማሰብም የሚከብደው ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ ማታ 3፡00 ጀምሮ እስከ ዓርብ 9፡00 ድረስ ያለው 18 ሰዓታትን የፈጀው ሕማማት ነው፡፡ ሊቃውንቱ እንደ ሥነ ፍጥረት ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ ብለው ቆጥረው 13 ሕማማተ መስቀል ብለው አስቀምጠዋል፡፡ ጌታችን 33 ዓመት ከ3 ወር በኖረበት ዓመት ሁሉ የሰውን ልጅ ሁሉ ሕማማት ተሸክሞ ነበር፡፡ መስቀል ላይም የሆነው ይሄ ነው... የከበደው መስቀሉ አልነበረም በመስቀሉ የእኛን ዕዳ ተሸክሞ ነበር ይወጋው የነበረው ችንካሩ ብቻ አልነበረም የእኛ ኃጢአት እስከ ውስጡ ዘልቆ እየወጋው ነበር በበደላችን እየደቀቀ ነበር በነውራችን እየተጨነቀ ነበር በመተላለፋችን እየቆሰለ ነበር ......ሕማማት ይሄ ነው!!! ነሥአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ ማለትም ይኸው ነው ሕማማታችንን እሱ ሲሸከምልን እኛ አረፍን!!! ☞ኢሳ 53 ሙሉው ይነበብ!!!☜ በዚህም ነጩን ወፍ ከራድዮንን ያስታውሷል! የበሽተኛውን በሽታ በአፉ እየመጠጠ ይወስድለታል ያን ጊዜ ወፉ/ከራድዮን፦ • ኃይሉን ያጣል ይደክማል ይልፈሰፈሳል • መልኩ ይጠቁራል • ብርድ ብርድ ይለዋል • ወደ አየር ወጥቶ 3 ሰዓት ፀሐይ ይሞቃል • ወደ ባሕር ገብቶ 3ቀንና ሌሊት ይቆያል • በ3ኛው ቀን ወደቀድሞው ነጭነቱ፤ኃይሉ ተመልሶ ከባሕር ይወጣል ☞ጌታም የእኛን ሕማማት መስቀል ላይ ከእያንዳንዳችን እየመጠጠ ተቀበለልን (ኢሳ 53፡6) ፤ በዚህ ጊዜም ፦ • ደከመ • ጠቆረ • ቃተተ • 3 ሰአት መስቀል ላይ ቆየ • 3 መዓልትና ሌሊት በመቃብር ቆይቶ በሦስተኛው ቀን በደላችንን የእኛን ሕማማት አራግፎ ተነሣ ....ወኀደገ ንዴተ ህላዌ ዘቀዳሚ ገብአ ወተመይጠ ውስተ ስብሐቲሁ ወክብሩ እንዲል ቅ.ዮሐ አፈ፤(የቀድሞውን አኗኗር ትቶ ወደ ፍጹም ክብሩ ተመለሰ፤ ጎድሎት ነበር ማለት አይደለም ትሕትናውን ማጠየቅ ነው፤ ፊል 2፡7) ዛሬ ቅድስት ቤተ ክርስታያናችን የብሉይ ኪዳን ሕማማት ከጌታ ሕማማት ጋር አስተባብራ ታስበዋለች፡፡ የተለመዱት የሐዲስ ኪዳን ሥርዓቶች የሚቋረጡት የአበውን ሕማማት ለማሰብ ነው! "ለከ ኃይል " እየተባለ የሚሰገደው ደግሞ ሕማማተ ክርስቶስን ለማዘከር ነው፡፡ ስግደታችንን ምኅላችንን ይቀበልልን!!! አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው @mahtotetonetor2
2 51333Loading...
21
እግዚአብሔር ያክብራችሁ ሰላምን ያድላችሁ EGUA D/MIHRET MEDIHANIALEM እጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን 🫴🫴አቢሲኒያ ባንክ 182395657 🫴🫴በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000273479744   
2 0220Loading...
22
#ሰሙነ_ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ። በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦ #ሰኞ #መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። #አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡- ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና። #ማክሰኞ #የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦ ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። #የትምህርት_ቀን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪። #ረቡዕ #ምክረ_አይሁድ_ይባላል፦ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። #የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል። #የእንባ_ቀን_ይባላል፡- ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። #ሐሙስ #ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። #የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። #ዓርብ #የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። #መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። #ቅዳሜ #ቀዳም_ስዑር_ትባላለች ፦ ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል። #ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። #ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡- ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል። ዲ.ን ኤርምያስ @mahtotetonetor1 @mahtotetonetor2 (ስምዐ ጽድቅ  መጋቢት ፳፻፪ ዓ.ም)
2 25022Loading...
23
ጥያቄ ፩) ፍትሕዎ ወአምጽዑ ሊተ••• ከየት ነው የሚመጡት የማን አህያ ነበሩ እነዚህ አህያዎች ለምን ታሰሩ ፣ፍቱና አምጡ ማለቱ ምን ለማለት ነው በእግረ ፀሐይ ፣በመላዕክት ጀርባ ፣በነፋስ ፣በደመና ተጭኖ መምጣት ይችላል ለምን አህያን መረጠ ፪) ቅጠል አነጠፉለት ይላል ለምን ትርጉሙ ምንድነው? @sekokaw ላይ መልሱን ይላኩልን !
1 8401Loading...
24
ማኅቶተ ቶኔቶር ፩: ከዘጠኙ ዐበይት የጌታችን በዓላት አንዱ "ሆሳዕና በአርያም" ማለት በአርያም /በሰማይ/ ያለ መድኃኒት ማለት ነው፡፡ ሆሳዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ሆሻአና" የሚል ሲሆን ትርጉሙም "እባክህ አሁን አድን" ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፡፡ መዝ.117፡25-26፡፡ የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት "ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም" በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሳዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ይህ ዕለት የጸበርት እሑድ /Palm Sunday/ ይባላል፡፡ ታሪካዊ አመጣጡ የመልካም ምኞትና የድል አድራጊነት መገለጫ ሆኖ ከደገኛው አባታችን ይስሐቅ ልደት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ይኸውም ሣራ የወላድነት ዕድሜዋን ጨርሳ ልማደ እንስት ከተቋረጠባት በኋላ ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ይስሐቅን በሰጣት ጊዜ ዘመዶችዋ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ የጎበኟትን አምላክ አመስግነዋል፡፡ እስራኤል ከአስከፊው የግብፃውያን አገዛዝ ተላቀው ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ የተሰማቸውን እጥፍ ድርብ ደስታ በገለጡ ጊዜ፣ እንዲሁም ዮዲት የተባለች ንግሥተ እስራኤል ሆሎፎርኒስ የተባለ አላዊ ንጉሥን ድል ባደረገች ጊዜ ቤተ እስራኤል እንደ ሰንደቅ ዓለማ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ አደባባይ ወጥተው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ በዘመነ ሐዲስም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከሲኦል ባርነት ነጻ ለማውጣት ወደ ዙፋን መስቀሉ /ሉቃ.22፤18/ በተጓዘ ጊዜ ሕፃናት እና አእሩግ ነጻ የሚወጡበት ቀን መድረሱን እነርሱ ሳያውቁ እግዚአብሔር ባወቀ ዘንባባ በመያዝ ዘምረዋል፡፡ እስራኤል ዘንባባ በመያዝ እንዳመሰገኑት እኛም አስራኤል ዘነፍስ ዕለቱን ዘንባባ /ጸበርት/ በግንባራችን በማሰር በዓሉን በየዓመቱ እያስታወስን እናከብራለን፡፡ በዚህ ዕለት ዘንባባ እየተባረከ ለሕዝቡ ይታደላል፡፡ ሕፃናትና አእሩግ "ለዳዊት ልጅ መድኃኒት መባል ይገባዋል" እያሉ ዘምረዋል፡፡ ይህ ሁሉ በአንድ ወገን የነበረው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ሲሆን በሌላ በኩል የነበረው አቀባበል ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነበር፡፡ ሥርዓተ ኦሪትን፣ ትንቢተ ነቢያትን በሚገባ እንከተላለን ይሉ የነበሩ ጸሐፍት ፈሪሳውያን "መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው" አሉት፡፡ ጌታችንም መልሶ "እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ" ሲል መልሶላቸዋል፡፡ ቅናት አቅላቸውን ያሳታቸው ፈሪሳውያንም የዋህ የሆነው ሕዝብ ምስጋና ወደ ጥላቻ እንዲለወጥ አድርገዋል፡፡ ከሁሉ የሚያሳዝነው በዕለተ ሆሳዕና እሑድ ዘንባባ ይዘው የዘመሩለትን ጌታ ዓርብ ላይ "ይሰቀል ዘንድ ይገባል" ብለዋል፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ በዚህም በነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ፡፡ "እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፣ በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡" ዘካ.9፡9፤ ማቴ.21፡4፤ ማር.11፡1-10፤ሉቃ.19፡28-40፤ ዮሐ.12፤15፡፡ ጌታችን በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እስራኤል ዘመነ ምሕረት ሲሆንላቸው አባቶቻቸው በአህያ ጀርባ ተቀምጠው ይታዩ ነበር፡፡ ጌታም እውነተኛ የኅሊና ሰላም ይዤላችሁ መጣሁ ሲለን በአህያ ጀርባ ወደ ቤተ መቅደስ ሕይወታችን ተጉዟል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተውአቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡ ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፤ ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡ የተምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡ የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡ ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፤ እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡ “የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ዘካ.9፡9 የሚለው የዘካርያስ ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ሕዝቡም ኢየሱስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ ከፊትና በኋላ ያሉት ደግሞ “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” እያሉ በታላቅ ድምፅ ይጮሁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በሕዝቡ እልልታና ደስታ ታጅቦ ሲገባ ተጠንቅቀው ይታዘቡትና ይመለከቱት የነበሩ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን ዝም እንዲያሰኛቸው ተናገሩት፡፡ እርሱም ሕዝቡ ዝም ቢል ድንጋዮች እንደሚጮኹ አስታወቃቸው፡፡ በጌታችን በዕለተ ልደቱ "በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል በምድር ሰላም ለሰው ሁሉ ይሁን" /ሉቃ.2፡13/ እያሉ የዘመሩለት የሰላም ባለቤት ነው፡፡ በመዋዕለ ትምህርቱም "ሰላሜን እሰጣችኋለሁ" /ዮሐ.14፡27/ ብሎ እንዳስተማረ ያን ሰላም የሚሰጥበትን ዕለት መቅረቡን ለማመልከት ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአህያ ጀርባ መቀመጡ ኅቡዕ ምሥጢር አለው፡፡ በአህያ ጀርባ የተቀመጠ ሰው ሌላውን አሳድዶ አይዝም፣ እርሱም ሮጦ አያመልጥም፡፡ በዚህም ጌታችን በእምነት ለሚፈልጉት የሚገኝ ቅርብ ሲሆን በእምነት ለማይፈልጉት ግን የማይገኝ
1 83112Loading...
25
🎤ሆሣዕና ምን ማለት ነው? የወይራ ዛፍና የዘንባባ ዝንጣፊ ምስጢራዊ ትርጓሜ ምንድነው ? ጌታ  በአህያ የመቀመጡን ምክንያቱን ለማወቅ        = ሆሣዕና ማለት መድኀኒት ማለት ነው ሆሣዕና የጌታችን የአምላካችን በዓል ነው ከጌታችን ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው። ✥  አንድም በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15 የዘንባባ ዝንጣፊ፡- ☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡- ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡- ☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና። ❖ ጌታችን አምላካችን ደቀ መዛሙርቱን  ወደ ፊታችው ባለው ሀገር ሂዱና አህያ ከውርጭላዋ ጋራ ታስራ ታገኛላችው ፈታችው እምጡልኝ  ምን ታደርጋላችው? የሚላቸው ሰው ካለ ጌታቸው ይፈልጋቸዋል በሉ ብሎ ላካቸው ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ እንዳዘዛቸው ሂደው ፈተው አመጡለት በዚያም የተሰበሰቡት ሁሉ በአህዮች ላይ ልብሳቸውን ጎዘጎዙለት ጌታችንም በሁለቱ  አህዮች ላይ ተቀመጠ 👉ከሌሎቹ እንስሳት አህዮችን መርጦ በአህዮች ተቀምጧል አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸውና። ❖የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች ዘሁል22÷28 ❖ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አህዮች ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን አሟሙቀውታል ቅዳሴ ማርያም ❖ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ለመግጽ ምሳሌ-    ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ  ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና ጌታችንም ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል። ❖ ትንቢቱን  ለመፈጸም ትንቢት-   አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው    ትሁትም  ሁኖ በእህያም በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈጸም ነው ዘካ 9÷1 ❖ምሥጢሩን ለመግለጽ ምሥጢር-   በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል ይህ እና ሌሎች ምስጢራትን ለመግለፅ ትንቢት ለመፈጸም አምላካችን በአህ። ❖ በዓለ  በሆሳዕና ጊዜ የጌታችን ትህትና    የምናስብበት እኔ ምሰሉ ስላለ በትህትና  እራሳችንን የምናኖርበት ።  በእላይ በሰማይ ኪሩቤል በፍርሃት መንበሩን የሚሸከሙት ቅዱሳን መላእክት ያለማቋረጥ የሚመሰግኑት በትህትና በአህያ ጀርባ የተቀመጠ በሕፃናት አንደበት የተመሰገን ቢታንያ ድንጋዮች የዘመሩለት የአምላካችን የጌታችን ክብረ በዓል በምናከብረበት ጊዜ የአምላካችን ትህትናውን በልባችን እያሰብ በተግባር እየገለጥ እንድንኖር አምላካችን ይርዳን ። ወስብሐት  ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ  ክቡር ። @mahtotetonetor2
2 71844Loading...
26
መሆኑን አስተምሯል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፀሐይ ዕድሜያችን ሳትጠልቅ በእምነት እንፈልገው፡፡ አሞጽ 4  የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፣ የተዋረደውንና የተሰበረውን ልብ አይንቅም፡፡ ኢሳ.66፡2፤ መዝ.50፡17፡፡ ጌታችን በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ስለሆነ የክብረ በዓሉ ምስጋና በዋዜማው ይጀመራል፡፡ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ካህናቱ በእምርት ዕለት በዓልነ፣ በታወቀ የበዓላችን ዕለት ከበሮ ምቱ በማለት የዋዜማውን ምስጋና ይጀምራሉ፡፡ የዋዜማው የምስጋና ቀለም እጅግ ሰፊ ስለሆነ በዚህ መዘርዘር አይቻልምና ከዋዜማው ፍጻሜ በኋላ ያለውን ሥርዓት እንመልከት፡- በሌሊተ የሆሳዕና ማኅሌት ከመቆሙ በፊት በካህኑ ተባርኮ በሰሙነ ሕማማት ሲነበብ ሲተረጎም የሚሰነብተው ግብረ ሕማማት የተባለው መጽሐፍ መነበብ ይጀምራል፡፡ ስቡሕ ወወዱስ ዘሣረር ኩሎ ዓለመ፣ ዓለምን ሁሉ ፈጠረ እግዚአብሔር ፍጹም የተመሰገነ ነው በሚለው የምስጋናዎች ሁል ርእስ የዕለቱ የማኅሌቱ ምስጋና በካህናትና በሊቃውንት ይጀመራል፡፡ ከዐቢይ ጾም መግቢያ ጀምሮ ማዕቀብ ተጥሎባቸው በዝምታ የሰነበቱት ከበሮና ጽናጽል የምስጋናው ባላድርሻዎች ይሆናሉ፡፡ በዚህ የተጀመረው ማኅሌት ሌሊቱን ሙሉ አድሮ መዝሙር በሚባለው . . . ምስጋና በኩል አድርጎ ሥርዓተ መወድስ ተደርጎ ሰላም በተባለ ምስጋና ይጠናቀቃል፡፡ ሥርዓተ ዑደት በሆሳዕና ሥርዓተ ማኅሌቱ ተፈጽሞ ሥርዓተ ቅዳሴው ከመጀመሩ በፊት እሰካሁን ከነበረው ሥርዓት ለየት ያለ ሆኖ እንመለከታለን፡፡ ይኸውም ሊቃውንቱ የዕለቱን ድጓ እየቃኙ እየመሩና እየተመሩ፣ ዲያቆኑ ከመዝሙር ዳዊት የዕለቱን በዓል የተመለከተ ምስባክ በዜማ እየሳመረ፣ ካህናቱም በዓሉን የተመለከተ ወንጌል በዐራቱም መዓዘን እያነበቡ ቤተ መቅደሱን አንድ ጊዜ ይዞሩታል፡፡ ለምሳሌ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ባለው በር ፊት ለፊት በመቆም መምህሩ አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ፣ ወደቤቱ እንገባ ዘንድ መንገዱን አሳዩን፡፡ የሚለውን ድጓ ይቃኛሉ ካህናቱ እየተከተሉ ያዜማሉ ዲያቆኑ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘየሐድር ውስተ ጽዮን፣ በጽዮን የሚገለጥ እግዚአብሔርን አመስግኑ እያለ ያዜማል፡፡ ካህኑም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 21፡ 1-13 ያለውን ኀይለ ቃል ያነባል፡፡ በዚህ ዓይነት መልክ በዐራቱም መዓዘነ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ዑደት ይፈጸማል፡፡ ይህን ሥርዓት ሊቃውንቱ ሲተረጉሙት አንደኛ ጌታችን በአህያ ውርንጫ ተጭኖ በሕፃናት አንደበት እየተመሰገነ ኢየሩሳሌም የገባበትን የምስጋና ጉዞ ለማመልክት ሲሆን ሁለተኛ ሕገ ወንጌል በዐራቱም ማዕዘነ ዓለም ለሕዝብና አሕዛብ መዳረሱን ለማመልከትና ሕዝብና አሕዛብ በሕገ ወንጌል አንድ አካል መሆናቸውን በገቢር ለማሳየት መሆኑን ያስተምራሉ፡፡ ሥርዓተ ቅዳሴ ዘሆሳዕና በዕለተ ሆሳዕና አሁንም የቅዳሴው አገባብ ሥርዓት ከሌሎች ዕለታት ለየት ያለ መሆኑን እንመለከታለን፡፡ ዲያቆናቱ ሕብስቱን በመሶበ ወርቅ ወይኑን በጽዋዕ ይዘው በምዕራብ በር በኩል ይቆማሉ፣ ሠራኢው ዲያቆን በዜማ አሰምቶ እርኅው ኆኅተ መኳንንት፣ አለቆች ደጆችን /በሮችን/ ክፈቱ ይላል፡፡ ካህኑም በመንጦላዕክት ውስጥ ሆኖ መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት ይህ የክብር ንጉሥ ማነው ብሎ ይጠይቃል ዲያቆኑም ይህ የኃያላን አምላክ እግዚአብሔር ነው ብሎ ይመልሳል፡፡ ዲያቆኑ ሦስት ጊዜ የክፈቱልኝ ጥያቄያዊ ዜማውን ካዜመ በኋላ ካህኑ ይባዕ ንጉሠ ስብሐት፣ የክብር ንጉሥ ይግባ ብሎ ፈቅዶለት ይገባል፡፡ መዝ. 23፡7 ይህንንም አበው እንደሚከተለው ያመሰጥሩታል፡፡ አንደኛ ቅዱስ ገብርኤልና ወላዲተ አምላክ በምሥጢረ ብስራት ጊዜ የተነጋገሩት እንደሆነና በመጨረሻም ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ፣ እንደቃልህ ይደረግልኝÂ ብላ መቀበሏን ሲያሳይ ሁለተኛው ፈያታይ ዘየማንና መልአከ ኪሩብ በማእከለ ገነት የተነጋገሩትን በድርጊት ለማሳየት መሆኑን ያስተምራሉ፡፡ ዋናው ምስጢር ግን ክርሰቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሊገባ ሲል ብዙዎቹ እንዲገባ መፍቀዳቸውን ያሳያል፡፡ እንደተለመደው ሥርዓተ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ እግዚእ ሕያዋን /የሕያዋን ጌታ/ የተሰኘው ጸሎት በካህናት ተደርሶ ለምእመናን ሥርዓተ ፍትሐት ይደረግላቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ሥርዓተ ፍትሐት ስለማይደረግ፡፡ በሰሙነ ሕማማት የማይከናወኑ ምሥጢራት በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡ ምእመናንም ተባርኮ የተሰጣቸውን የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ወደየቤታቸው ያመራሉ፡፡ የዘንባባው ምሥጢር የተጀመረው በታላቁ አባት በአብርሃም ነው፡፡ ኩፋ.13፡21 ይህን የአባታቸውን ሥርዓት አብነት አድርገው እስራኤል የኤርትራን ባሕር ሲሻገሩ፣ ዮዲት ድል ባደረገች ወቅት ዘንባባ እየያዙ እግዚአብሔርን አመስግነውታል፡፡ ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባም ሽማግሌዎችና ሕፃናት የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው እንደተቀበሉት እናነባለን፡፡ ሉቃ.12፡8 ኢትዮጵያውያን ምእመናንም ክርስቶስ የሰላም፣ የነጻነት፣ የድኅነት አምላክ መሆኑን ለመመስከር ዘንባባውን ይዘው ወደቤታቸው ይገባሉ፡፡ ዮሐ.14፡27 በእጃቸውም እንደቀለበት ያስሩታል፡፡ ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የሆነ ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ እንደተቀመጠ ሁሉ ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት ዛሬም ያድራል፤ የኅሊና ሰላምን ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ንስሐ ገብተን ጌታችንን ሆሳዕና በአርያም እያልን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ @mahtotetonetor2 በአጠቃላይ አህያ የተመረጠችበት ምክንያት ፩፦ ትንቢት ይፈፀም ዘንድ   ትንቢቱም "አንቺ የጽዮን ልጅ ዕጅግ ደስ ይበልሽ እነሆ ንጉስሽ ጻድቅና አዳኝ የሆነው ትሁትም ሆኖ በአህያዋ በአህያይቱ ግልገል ውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል"ዘካ 9÷9 ፪፦ ትህትና ለማስተማር ምክንያቱም አህያ የተናቀች ናትና አንድም የአለም ጥበብ እና ክብር በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነትና ውርደት መሆኑን ለማስረዳት። አለም የሚያደንቀው ትቶ አለም የናቀው ላይ ተቀመጠ ማለት ነው። ፫፦ እኔ የሰላም አምላክ ነኝ ሲል     አህይ የሰላም ምሳሌ ነች። በጥን ዘመን ነቢያት ትንቢት ሲናገሩ በአህያ ተቀምጠው ከመጡ የምስራች ሊናገሩ እንደሆነ በፈረስ ከመጡ ስለመቅሰፍት ወይም መዓት ትንቢት እንደማናገሩ ይታወቅ ነበር። ፬፦ በትሁት ልቦና አድሬ እኖራለሁ ሲለን ነው አህያ ብዙ ጫንከኝ ጎዳኸኝ ብላ ሳታማርር ራሷን ዝቅ አድርጋ አቅሟ በፈቀደ ሁሉ ባለቤቷን ታገለግላለቾ፡እኔም ራሱን ዝቅ አድርጎ በሚገዛልኝ ትሁት ሰው ልብ አድሬ እኖራለሁ ሲለን ነው። ህጻናት የዘንባባ ዝንጣፌ ይዘው የዘመሩበት ምክንያት ~ ዘንባባ በእስራኤላውያን ባህል የሰላም የደስታ ምልክት መሆኑን ስለሆነ (ነህ 8÷14) ~ዘንባባው የሚዋጋ እሾህ አለውና የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው።እግዚአብሔር ተዋጊ  ነው ዘፀ14÷14 ጠላታችን ሠይጣንን እንደ ሰም አቅልጦ እንደ ገል ገጥቅጦ ይጥልልናል ። ~ ዘንባባ የመለኮት ምሳሌ ነው። ዘንባባ ቢደርቅ እንኳን በእሳት ይለበለባል እንጂ አይነድም።የመለኮት ማንነትም ማንም ተመራምሮ አይደርስበትም። ህፃናቱ  አስቀድሞ ዳዊት "ከህፃናትና ከሚጠቡ ለራስህ ምስጋና አዘጋጀህ" መዝ 8÷2የሚለው ይፈጸም ዘንድ   ፈታችሁ አምጡ ማለቱ፦ _ አዳም ከዳቢሎስ እስራት የሚፈታበት ጌዜ መድረሱን ለማመልከት _ ለደቀ መዛሙርቱ የማሰርና የመፍታት ስልጣን መስጠቱን ሲያጠይቅ ነው። ማቴ 16÷18 ዮሐ20÷22 በአጠቃይ በእግዚአብሔር ቤት በትህትና በንጽህና በቅድስና መኖር እንደሚገባን ያስተምረናል።
2 05113Loading...
27
በመንዝ ዘብር ገብርኤል የሚታወቁት በታላቁ የቀለም ቀንድ ወላዴ አእላፍ ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ መ/ምሕረት የኔታ አክሊሉ ወ/ማርያም ሰኔ 29/2012 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ የተጣለለትና በሞላሌ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ግንቦት 1/2016 ዓ.ም በድምቀት ይመረቀል። የበረከቱ ተካፍይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።
1 9486Loading...
28
ሰው በጎ ተናግሮ በጎ ነገርን አይፈጽመውም ክፉ ተናግሮ ክፉ ለማድረግ ግን ይፋጠናል ። ቀሲስ ብርሃኑ ዘቤተ ጎርጎርዮስ በዓርብ ጉባኤ ፲፰/፰/፳፻፲፯
2 0664Loading...
29
አይዞህ እንደ ዳዊት ሊያነግሥህ ሲፈልግ ጎልያድን የሚያህል ችግር ይሰጥሃል።
2 2806Loading...
30
“ዓርብ ለፈጠረው ዓርብ ተሰቀለ። መልኩ ለጠፋ፣ ውበቱ ለረገፈ ዓለም መልክና ውበት ደም ግባት ሆነለት።” ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
2 5328Loading...
31
Media files
1 4960Loading...
32
አስተምረኝ ጸዳልህ ግሩም፣ ክብርህ ትልቅ፣ ፍቅርህ ድንቅ የሆነ ፤ ሙት ለሆንኩት ሕይወትን የዘራህ ጌታዬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አመሰግናለሁ። ፍቅርህ መሸሻዬ፣ ክንድህ አቅሜ ፣እቅፍህ መሸሸጊያዬ ሆኖልኝ የማይታለፈውን አልፍኩ። የማይጀመረውን ፈጸምኩ። የማይወጣውን ወጣሁ ተመስገንልኝ። ታላቁን ሽንፈቴን በድል የለወጥክህ ሹመት አክሊሌ አንተ ነህ። ዘለዓለማዊ የምትሆን አምላኬ ሆይ እውቀት ያልኩት መና ሆኖ ፣ጥበብ ያልኩት ከንቱ ሆኖ ልቤ ቆስሎብኛል። ዘለዓለምን አስተምረህ ዘመኔን አለምልም። የፈጸምኩ መስሎኝ ስጀምር፣ የጸናው ምስልኝ ስናወጥ  እንድፈፅም አድርገህ አስተምረኝ እንድፀና አድርገህ አበርታኝ። ጌታዬ ሆይ እንደ ልብህ አልሆንኩምና እንደ ልቤ እየሆንኩ ነው። እንደ ሃሳብህ አልሆንኩምና እንደ ሀሳቤ እየፈረጅኩ ነው። እንደ ፍቃድ አልሆንኩምና እንደ ፍቃዴ አየተጓዝኩ ነው። እባክህ ከዚህ ጥም ቃጠሎ በቃልህ ትምህርት አርካኝ።በሆሳዕና አጅቤህ በቀራንዬ የማልሸሸው አንተ ስታስምረኝ ነው ።  ዕለት ዕለት በኃጢአት አንተን ከመስቀል የምድነው እንተ ስታስተምረኝ ነው። እንደ ኒቆዲሞስ አንተን ከመስቀል ላይ ለማውረድ የምታደለው አንተ ስታስተምረኝ ነው ። በቃልህ ብርሃን ጨለማ ኑሮዬን አብራው።ቅጥ አልባ ውድቀቴን አርመው። ለዝና የሚያደለው ልቤ ለፍቅርህ  ይደንግጥ። አስተምረህ ልቤን በፍቅርህ ማርከው። እየበደልኩ በጥፋቴ እንዳልኖር አስተምረኝ።በሰጠኸኝ ቀን ውስጥ ቀኔን የምኖር ብሆንም ፣ ቸርነትህ በዝቶ በነውርና በአመጽ ብዳክርም አንተ ብቻ አስምረኝ ከእንግዲህ የዓለም አልሆንም። ዘለዓለማዊው ቃልህ ዘለዓለሜ ነው። የዛሬ ትህምርትህ የዓመት ቀለቤ ነውና እባክህ እንደ ኒቆዲሞስ እኔንም አስተምረኝ። በማላፍርበት ደግነትህ ለዘለዓለሙ አሜን ። ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ @mahtotetonetor2
2 84411Loading...
33
የሀገር መከላከያ ዩኒፎርም(መለዮ) ለብሰህ በወጡንቻማ ፓስተሮች ነቢያቶች ነን ባዮች ቸርች ሄደህ በካራቴ በጠረባ ተብለህ ተደብድበህ መውደቅ እና የመከላከያን ክብር ማዋረድ ምንም ችግር የለውም። በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በምስጋና መገኘት ግን ነውር ነው ያሳስራል ማለት በየትኛው እውነት ትክክለኛ ፍርድ ነው ያስብላል???
2 3973Loading...
34
https://youtu.be/zRsRm66sXNI?si=XKkQis-wApk3BZlk
3 0372Loading...
35
Media files
2 8114Loading...
36
ማኅቶተ ቶኔቶር ፩: +++ የኒቆዲሞስ ክርስትና +++       ኒቆዲሞስ የሚለው ስም በዮሐንስ ወንጌል ብቻ ከተጻፉ ስሞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የዚህን ሰው ስም ባነሣበት ሥፍራ ሁሉ ‹አስቀድሞ በሌሊት የመጣው› የምትል ቅጽል ያስቀድማል፡፡ ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ ነው፡፡ በሀብቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ባለጸጋ ፣ በሹመቱ የአይሁድ ሸንጎ /synagogue/ አባል ፣ በትምህርቱ ደግሞ ጌታችን ራሱ እንደመሰከረለት ‹የእስራኤል መምህር› የሆነና አዋቂ ነው፡፡ የአይሁድ አለቃ ፣ የእስራኤል መምህር ኒቆዲሞስ ጌታችን ራሱ ለብቻቸው በቃል ምልልስ እያናገረ ጥያቄያቸውን እየመለሰ ካስተማራቸው ጥቂት ዕድለኛ ሰዎች አንዱም ነው፡፡ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅነት ያገኘንበትን ምሥጢረ ጥምቀት በጥልቀት እና በዝርዝር የተማረው የመጀመሪያው ሰውም ኒቆዲሞስ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ጌታችን ጥምቀትን በተግባር ሲመሠርት የዓይን ምስክር እንደነበረ ሁሉ ጥምቀት በትምህርት ስትመሠረት ደግሞ የዓይን ምስክሩ ኒቆዲሞስ ነው፡፡ በትምህርቱ መካከልም ባቀረበው ጥያቄ ‹ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ ስለ መወለድ› ጌታችን በምሳሌ አድርጎ ያስተማረው ሲሆን አላምን ብሎ ‹እንዴት ሊሆን ይችላል?› ብሎ ሲከራከር ደግሞ ገሥጾታል፡፡ ዛሬም ድረስ ኒቆዲሞስ መልስ ከተሠጣቸው በኋላ የሚነታረኩ ተከራካሪዎች ምሳሌ ሆኖ በሊቃውንት ይጠቀሳል፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያምን የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት በሙሉ ልብ በመቀበሏ በምናመሰግናት ጊዜም ‹እንደ ዘካርያስ ሳትጠራጠሪ እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ ቃሉን የተቀበልሽ› እያልን መሆኑ ይህን እውነታ ያጎላዋል፡፡ ኒቆዲሞስ ወደ ክርስትና ከመጣበት መንገድ ጀምረን በዮሐንስ ወንጌል ስንከተለው ቀስ በቀስ እያደገ የመጣ የመንፈሳዊነት ደረጃን እናገኛለን፡፡ የኒቆዲሞስ ክርስትና እንደ ወጣኒ (ጀማሪ) እንደ ማዕከላዊና እንደ ፍጹም በሦስት ደረጃዎች ላይ የሚታይ ሕይወት ሆኖ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ እንደሚከተለው እንመልከተው፡፡ ወጣኒው (ጀማሪው) ኒቆዲሞስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ሳለ ያደረገውን ተአምር ተመልክተው ብዙ ሰዎች በስሙ አምነው ነበር፡፡ ያ ወቅት ጌታችን በቃና ዘገሊላ ሠርግ ቤት ውኃን ወይን ያደረገበትና ፣ በቤተ መቅደስ ይሸጡ ይለውጡ የነበሩትን ገሥጾ ያስወጣበት ነበር፡፡ ይህንን ምልክት ተከትለው ካመኑበት ብዙ ሰዎች አንዱ ታዲያ ኒቆዲሞስ ነበር፡፡ ይህ ሰው በጌታችን ቢያምንም ባመነበት ወቅት እምነቱን በልቡ ብቻ ይዞ አቆይቶ ነበር፡፡ ከዚያም በአሳቻ ሰዓት በማታ ወደ ጌታችን መጣና ‹መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን› አለው፡፡ ኒቆዲሞስ ጌታችንን እግዚአብሔር በረድኤቱ ተአምራትን እንዲያደርጉ ከሚያስችላቸው ጻድቃን እና ነቢያት ለይቶ አላየውም ነበር፡፡ ንግግሩም ከእርሱ ጋር ምልክቱን አይተው አምነው ከነበሩት ሰዎች ቁጥር መሆኑን በሚያሳይ መንገድ ‹እናውቃለን› የሚል የብዙዎች ወኪልነት ንግግር ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር እንግዲህ አምላካችን በዝርዝር ያስተማረው፡፡ ኒቆዲሞስን እንዲህ በሌሊት ያስመጣው ምንድር ነበር? ክርስቶስን በቀን በአደባባይ ሊያናግረው አይችልም ነበር? እሱ እንደሆነ በሔደበት መንገድ የሚለቀቅለት የአይሁድ አለቃ ነውና ጌታችንን ለማግኘት ሰዎች አገዱኝ ሊል አይችልም፡፡ ይህ እንግዲህ የኒቆዲሞስ የመጀመሪያው የክርስትና ደረጃ ነበር፡፡ እሱ አምላካችንን ስላደረገው ተአምር ሊያደንቀው ፈልጓል ‹እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው› ብሎ አመስግኖታል ፤ ሊከተለው ግን አልፈለገም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከጌታችን ጋር ሆኖ ሰዎች እንዲያዩት አልፈለገም፡፡ የጌታ ተከታይ ፣ ደቀመዝሙር ሆኖ መታሰብ አልፈለገም ፣ ጉዳዩ ክብሩን የሚነካበት መሰለው፡፡ የተማረ ነውና ‹ገና ይማራል እንዴ› ብለው እንዳይንቁት ለክብሩ ሳሳ ፣ በዚያ ላይ ደግሞ ጌታችን በአይሁድ ሹማምንት ዓይን የተናቀ ነበር፡፡ እርሱ ‹ግንበኞች እንደናቁት ድንጋይ› ነበር፡፡ ‹‹የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።›› ይላል ነቢዩ፡፡ /ኢሳ. ፶፫፥፫/ ታዲያ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ መታየት በዚያን ወቅት የሚያስከብር ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህ ፈራ ተባ እያለ በጨለማ መጣ፡፡ ወደ ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚመጣ ሰው አንዱ ፈተናው ይኼ ነው፡፡ ክርስትናችን በሰዎች ፊት የታወቀ እንዲሆን ፈቃደኞች የማንሆን ብዙዎች ነን፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሰው ተብሎ ላለመታየት የሚሸሹ ብዙዎች ናቸው፡፡ ማዕተብ ማድረግ ፣ በቤተ ክርስቲያን አጠገብ ሲያልፉ መሳለም ፣ በአበው ትውፊት ጽዋዕ መጠጣት ወዘተ ማድረግ የሚከብዳቸው የሚጨነቁና የሚያፍሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ በሚሠሩበት መሥሪያ ቤት አካባቢ ስለ ሃይማኖታቸው ባይታወቅ የሚመርጡ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔዳቸው ባይሰማ ደስ የሚላቸው ኒቆዲሞሶች ብዙኃን ናቸው፡፡ የኒቆዲሞስ ችግር በክርስትናው ማፈሩ ብቻ አልነበረም፡፡ ክርስትና የሚያመጣበትን መዘዝ መፍራቱም ጭምር ነው፡፡ አይሁድ ‹‹እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኩራብ ይውጣ›› የሚል ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡ (ዮሐ. ፱፥፳፪) በዚህ ሕግ ምክንያት በጌታችን አምነው እንኳን ስለ እርሱ ለመመስከር የሚፈሩ ብዙዎች ነበሩ፡፡ ‹‹ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ነገር ግን ከምኵራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና።›› (ዮሐ. ፲፪፥፵፪) ኒቆዲሞስ ወደ ጌታ መጥቶ መማሩ እንዲታወቅ ያልፈለገውም ለዚህ ነበር፡፡ ለክርስትናው ምንም ዓይነት ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ለማድነቅ እንጂ መከራን ለመቀበል አልተዘጋጀም፡፡ ይህ ዓይነቱ ችግር ሌላው የክርስቲያናዊ ሕይወት ፈተና ነው፡፡ ሐዋርያው የክርስትናችንን ዓላማ ሲገልጥ ‹‹ስለ እርሱ ደግሞ መከራን ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፡፡›› ብሏል፡፡ (ፊል. ፩፥፳፱) ብዙዎቻችን ክርስትናችንን እንፈልገዋለን ፤ ሆኖም በክርስትናችን ምክንያት ቅንጣት መከራ እንኳን እንዲነካን አንፈልግም፡፡ በእግዚአብሔር በማመን ውስጥ ፈተናም አለ፡፡ ራሳችንን በእውነት ክርስቲያን ነኝ ብለን ለመጠየቅ ብንፈልግ አብረን መጠየቅ ያለብን በእውነት መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ወይ ማለት ጋር ነው፡፡ በእግዚአብሔር በማመናችን ምክንያት ምን የከፈልነው ዋጋ አለ? ለእርሱ ብለን የተውነው ነገር ምንድን ነው? ለእሱስ ብለን ያጣነው ነገር ይኖር ይሆን? ምንም ነገር ከሌለ ክርስትናችን ገና ያልጠነከረ ነው ማለት ነው፡፡ ማዕከላዊው ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊያንና የካህናት አለቆች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዘውት እንዲመጡ ሎሌዎች ላኩአቸው፡፡ እነዚህ ሎሌዎች ጌታችንን ይዘው እንዲመጡ ቢላኩም በጌታችን ጣዕመ ትምህርት ተደንቀው ተመስጠው ሲማሩ ውለው ባዶ እጃቸውን ተመለሱ፡፡ አይሁድ ‹ያላመጣችሁት ስለ ምንድን ነው?›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹‹እንደዚህ ሰው ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም›› ብለው መለሱ፡፡ ይህን ጊዜ አይሁድ ተቆጥተው ሎሌዎቹን ‹‹እናንተ ደግሞ ሳታችሁ? ከአለቆች ወይም ከፈሪሳውያን መካከል በእርሱ ያመነ ሰው የለም፡፡ ሕዝቡም ያመነበት ሕግ የማያውቅ ርጉም ስለሆነ ነው›› ብለው ገሠጹአቸው፡፡ እናንተ ያመናችሁት
1 92112Loading...
37
ባለማወቃችሁ ነው ፤ ከእኛ ከአዋቂዎቹ ማን በእሱ አመነ? ብለው ሊያሸማቅቋቸው ሞከሩ፡፡ ይህን ሁሉ ሲሆን የማታው ተማሪ የአይሁድ መምህር ኒቆዲሞስ እዚያ ቆሞ ነበር፡፡ ከአለቆች መካከል በጌታ ያመነ የለም ሲባል እየሰማ ነው፡፡ አሁን ክርስትናው ልትፈተን ነው፡፡ ደፍሮ እኔ አምኜአለሁ ብሎ መናገር ባይችልም ፈራ ተባ እያለ እንዲህ አለ ‹‹ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው።›› እነሱ በተናገሩት ብቻ ለምን ትፈርዳላችሁ? እሱን ሳትሰሙ መፍረድ ተገቢ ነው ወይ? ማለቱ ነበር፡፡ አይሁድ እንደ ሎሌዎቹ ሁሉ ኒቆዲሞስን ማቃለል እንዳይችሉ የተከበረ መምህር ሆነባቸው፡፡ ስለዚህ ‹‹አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ አሉት። እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ሄደ።›› ጌታችን ከገሊላ ናዝሬት መምጣቱን በመጥቀስ መሲህ ከገሊላ አይነሣም ብለው ሊያስተባብሉ ሞከሩ፡፡ ይህ ግራ መጋባት በሐዋርያው ናትናኤልም የታየ ነበር እርሱ ‹‹ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?›› ብሎ የጠየቀው መሲሁ ከይሁዳ ቤተ ልሔም እንደሚነሣ የተነገረውን ትንቢት በማየት ነበር፡፡ ጌታችን የተወለደው ከቤተ ልሔም ነው ያደገው ግን በገሊላ ናዝሬት በመሆኑ ነው ይኼ ሁሉ ውዥንብር፡፡ ኒቆዲሞስ ክርስትናውን በሌሊት ፈርቶ ጀመረ፡፡ አሁን ሙሉ በሙሉ ክርስቲያን ነኝ ብሎ መመስከርና መግለጥ ባይችልም ቢያንስ አይሁድ ከአለቆች ማን በእርሱ አመነ? ብለው ሲዘብቱ ቢያንስ ድምፁን ለማሰማት ሞከረ፡፡ በጥያቄ አስጨንቆም በዚያች ዕለት ስብሰባውን በተነው፡፡     ፍጹማዊው ኒቆዲሞስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል መከራ ዓለምን የማዳን ሥራውን ፈጸመ፡፡ በዚህ የመከራ ወቅት በዋለበት የዋሉ ባደረበት ያደሩ ደቀ መዛሙርቱ ከዮሐንስ በቀር በፍርሃት ተበተኑ፡፡ ነፍሱን ከሥጋው ተለይቶ ከመስቀሉ ሲወርድም አንድም ሐዋርያ አብሮት አልነበረም፡፡ በዚህ ወቅት ኒቆዲሞስ እንደ ቀድሞው ሌሊት እስኪሆን አልጠበቀም፡፡ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ ከአርማትያው ዮሴፍ ጋር ሆነው የጌታችንን ሥጋ ወሰዱ፡፡ እንደ አይሁድ የአገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት፡፡ ሲገንዙት እያለቀሱ ነበር ‹‹ሞትከኑ መንሥኤሆሙ ለሙታን ፤ ደከምከኑ መጽንኤሆሙ ለድኩማን›› ‹‹ሙታንን የምታስነሣ ሆይ ሞትክን? ደካሞችን የምታጸናቸው ሆይ ደከምክን?›› እያሉ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ጌታችን በመለኮቱ ሕያው እንደመሆኑ አነጋገራቸው፡፡ በነገራቸው መሠረት ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት…›› የሚለውን በኪዳን ወቅት የምናደርሰውን ዓለም አቀፋዊ ጸሎት እያደረሱ ገነዙት፡፡ ኒቆዲሞስ ሲፈራ ፣ ቀስ እያለ ሲናገር የነበረውን ክርስትናውን በአደባባይ ገለጠ፡፡ ‹‹ልቡ ለጻድቅ ውኩል ከመ አንበሳ›› ‹‹ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ሳይፈራ ይኖራል ›› እንዲል ጠቢቡ በጌታ የደረሰ መከራ ቢደርስብኝ ሳይል ሥጋውን ተሸክሞ ገነዘ፡፡ ከምኩራብ ያስወጡኛል ብሎ የፈራው ኒቆዲሞስ ቤተ ክርስቲያን እንዳለች ስለተረዳ በድፍረት ክርስትናውን መሰከረ፡፡ ከሦስቱ የኒቆዲሞስ ክርስትና ደረጃዎች እኛ በየትኛው ላይ ነን? ስለ ሃይማኖታችንስ በየትኛው ደረጃ እንመሰክራለን፡፡ በጨለማ ነው? ፈራ ተባ እያልን ነው ? ወይንስ ያለ ፍርሃት? ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ @mahtotetonetor1 @mahtotetonetor2
3 0479Loading...
38
https://youtu.be/TyoHNL9djPg?si=qOOmU5fLWIIFAXNq
2 1522Loading...
39
https://youtu.be/q6UjqtqbQ4E?si=IcH-9GaPis_AQSPI
2 3020Loading...
40
           "የዘላለም አምላክ" ◾️ ዘዳ 33፥26 በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ፡ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው" ተራሮች ሳይወለዱ፥      ምድርም፡ አለምም ሳይሰሩ   መላዕክት እልል ሳይሉ፥    ሳይዘምሩ "ያኔ" እና "እዛ"፥       የሚባሉ ነገሮች ሳያኖሩ   ዘላለም አንተ ነህ ኦ፥    ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ለፀሐይ እና ጨረቃ ፥     ለእርሱ የዘላለም ብርሃን ሆንከው! ➻ @mahtotetonetor2
2 4520Loading...
#የትንሣኤው ሦስተኛ ቀን ቶማስ_ይባላል የትንሣኤ ሦስተኛው ዕለት ቶማስ ይባላል፡፡ ቶማስ ማለት ፀሐይ ማለት ሲሆን ፣ዲዲሞስ ማለት ደሞ መንታ ማለት ነው፡፡ ማመኑ በፀሐይ ፤መጠራጠሩ በመንታነት ይመሰላል፡፡ ቶማስ ሰዱቃዊ ነው ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን የለም ብለው ያምናሉ ቶማስም ሰዱቃዊ ስለሆነ ትንሣኤ ሙታንን የማይቀበል የማያምን ሰው ነበር፤ የጌታን ትንሣኤ ለመቀበል የተቸገረው አእምሮውን ገድሎት የነበረው ሰዱቃዊው ሀሳብ ስላልተለየው ነበር፡፡ ይሄ ብቻ ሳይሆን ጌታ አልዓዛርን ለማስነሣት ሐዋርያትን እንሂድ ሲላቸው "ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" ይላል ዮሐ 11፡16፡፡ የጌታችንን ከሞት መነሣት እርግጥ ሆኖ ሲያገኘው ግን የሞተው አእምሮው/ሀሳቡ ተነሥቷል ፤ "ጌታዬ አምላኬ" ብሎ ጠርቶ ሕያውነትን ተቀላቅሏል፡፡ "አንሥአኒ በትንሣኤከ፤ በትንሣኤህ አንሣኝ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ቶማስን በትንሣኤው አንሥቶታል፤ ስለዚህ የትንሣኤው 3ኛው ቀን ለቶማስ መታሰቢያ ሆኗል፡፡ ቶማስም ከ 3 ዓመት ትምህርት በኋላ ከጥርጥር ሞቱ ተነሥቷልና። ቶማስ ጠያቂ ነው፤ ያልገባውን ይጠይቃል፤ ማየት የፈለገውን ልየው ይላል፡፡ በዚህም ፍጥረታዊ ወይም ሳይንሳዊ ሰውን ይመስላል፤ ፍጥረታዊ ሰው ተነግሮት አያምንም፤ካልጨበጠ ካልዳሰሰ እውነትነቱን አይቀበልም ፦ " ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 2 : 14፡፡ ቶማስ የጌታችንን ድርጊቶች በጥርጣሬ ይመለከት የነበረ ሐዋርያ ነበር ፡፡ ለምሳሌ ጌታችን አልዓዛርን ለማስነሣት ሲሄድ ደስተኛ አለመሆኑን በሞት ስጋት ገልጾ ነበር፦ "ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" በማለት እንደተጻፈ፡፡ ዮሐ 11 : 16፡፡ በሌላ ጊዜም ቶማስ መንገዱን የጠየቀው ለዚህ ነበር፤ ያ መንገድ ወዴትና የት የሚወስድ ነው? የሚል ጥያቄ በውስጡ ይመላለስ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው፦ "ቶማስም። ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው" ዮሐ 14 : 5፡፡ በዚህ ሁሉ ጥያቄውና ጥርጥሩ ግን ጌታችን አንድም ቀን ሰልችቶት ተቆጥቶት ወይም በጥርጣሬ አትከተለኝ ብሎት አያውቅም ፤ ድካማችንን የሚያውቅ የሚሸከምልን አምላክ ነውና፤ ዛሬም ምንም ያህል ኃጢአት ብንሠራ ተጸጽተን በንስሐ ከተከተልነው አትከተሉኝ አይለንም፤ ከየትኛውም ክህደት ከየትኛውም ሃይማኖት ብንመለስ ወደ እውነተኛው ሃይማኖት ከገባን በኀላ አልፈልጋችሁም፡ውጡልኝ አይልም፤ "ወደኔ የመጣውን ወደ ውጪ አላወጣውም "ብሎናልና፤ ዮሐ 13፡32፡፡ ጌታችን ከሞት ከተነሣ በኀላ ለሁሉም ሲገለጥ ለቶማስ ግን አንድ ሳምንት ሙሉ አልተገለጠለትም ነበር፤ ቶማስም ጌታን በአካል ያዩት ሐዋርያት ሲነግሩት፦ • የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ • ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ • እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም" ይላቸው ነበር። ዮሐ 20 : 25፡፡ ጌታችን ይህንን ያደረገበት ምክንያትም፦ 1. ቶማስ በውስጡ መንፈሳዊ ቅናት እንዲያድርበት፤ ሁሉም ስለ ትንሣኤው ሲናገር እየሰማ እንዲጓጓ ነው፤ ይህ መጎምጀት ወደ ፍጹም መንፈሳዊነት ይመራልና፤ እኛም ዛሬ ለመንፈሳዊ ነገር ስንጓጓና ስንቸኩል እግዚአብሔርን እናገኘዋለን፤ በውስጣቸው የሚቀጣጠለው ፍቅረ እግዚአብሔር እርሱን ራሱን ይጠራዋል፤ ቀድሞም ለሞት ያደረሰው ፍቅር ነውና፡፡ 2. ጌታችን የአንዲት ነፍስ ጉዳይ ጉዳዩ እንደሆነ ያጠይቃል፡፡ የተገለጠው ለቶማስ ሲል ነበር ለሱም ሲባልም አስቀድሞ በሌለበት የተገለጠበት ፦ • ዕለት • ሰዓት • ቦታ • በተዘጋ ደጅ መግባቱ • ሰላምታው (ሰላም ለሁላችሁ ይሁን) • ሁኔታው /መልኩ አልተቀየረም፡፡ ቶማስ ባለበት የተገለጠበትና ሳይኖር የተገለጠበት ልዩነት ቢኖረው በመጀመሪያ ቀንና በስምንተኛ ቀን መሆኑ ብቻ ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየው ፦ • ለሰው ሁሉ ያለውን ክብር/ፍቅር/ግድ • ትንሣኤው እርግጥ መሆኑን • ፍጹም ቸርነቱን • መጀመሪያ ያዩትም መጨረሻ የሚያዩትም በአንድነት እንደሚወርሱት ያጠይቃል፡፡ የቶማስ የመጨረሻ እምነት፦ "ጌታዬ አምላኬም" ፤ዮሐ 20፡28፡፡ ይህ ቃል የመጨረሻው የእምነት ጥግ ቃል ነው፤ የምናምነው ይህን ነው ፤ የምንናገረው ይህን ነው፤ የምንሰብከው ይህንን ነው፤ ከዓለም የምንለየውም በዚህ ቃል ነው፡፡ ቶማስ ብዙ ቢጠይቅም፤ ቢጠራጠርም በመጨረሻ ግን "አምላኬ" ብሎ አመነ፤ ዛሬ "ኢየሱስን አምላክ " ብለው መጥራት የሚከብዳቸው ብዙዎች ናቸው፤ እኛ እንኳን የቶማስን ቃል የወንጌሉን ፍጥጥ ያለ እውነት ስንናገር ይጠሉናል፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድላቸው!!! ቶማስ ጌትነቱን አምላክነቱን ያመነው በመዳሰስና በማየት ከሆነ እኛስ ሳናይ እንዴት እናምናለን እንዳንል ጌታችን " ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው" በማለት ወሳኝ መልእክት አስቀምጦልናል፡፡ ዮሐ20 : 29፡፡ ወንጌላዊውም ታሪኩን ሲጠቀልለው፦ " ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል" በማለት ይህን አንብበን፤ ሰምተን ብቻ እንድናምን አስገንዝቦናል፡፡ ዮሐ 20 : 31፡፡ እኛም የቶማስን እጅ እጅ አድርገን ዳሰነዋል የሐዋርያትን ዓይን ዓይን አድርገን አይተነዋል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም "ክብሩን አየን.." እንዳለ አባ ሕርያቆስም " ከእርሱ ጋር በላን ጠጣን.." እንዳለ እኛም እንደ ቶማስ " ጌታችን አምላካችን" እንላለን!!!!! በዚህም እኛ "ብፁዓን ነን"!!! እንድናምነው የረዳን አምላካችን ይመስገን!!!! በበጎ ሥራም ደስ እንድናሰኘው ይርዳን!!! በረከተ ሐዋርያት ይደርብን!!! አሜን!!! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
Show all...
“ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም እምይዕዜሰ፤ ይህን ፤ ፍስሐ ወሠላም፡፡” መልካም የትንሣኤ ክርስቶስ ሲነሳ በራሳችን ምኞትና የሥጋ ፈቃድ እኛ እንዳንቀበር እንጠንቀቅ ! ዲ/ን ኤርምያስ @mahtotetonetor2
Show all...
ከእጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ገዳም ለዚህ ግሩፕ አባላት። ቀጥታ ቃላት ሳንጨምር ያሉንን ይኸው ~እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ ።ገንዘብ ወደ ገዳሙ አካውንት የምታስገቡ ሁሉ እኛ እሱ የሚያውቃችሁን የእናንተን ስም በጸሎት ሰዓት ለማንሳት አንደክምም ምንም እንኳን ኃጢአተኞች ብንሆንም እግዚአብሔር ይሰማናል ብለን እናምናለን ።የጥቂት እህቶችና ወንድሞች ስም ብቻ ነው የተላከልን የገንዘቡን መጠን ስንመለከት ብዙ ሰዎች እየተረባረቡ ነው በዚህም ከልብ እናመሰግናለን እግዚአብሔር ያክብርልን ።
Show all...
የሕፃናት ሁሉ ተምሳሌት የስነ ምግባር ቀንድ ሕፃን ሐረገወይን እኛም የበኩላችንን እናድርግ 100,000 ብር እንድትሸለም እናድርግ ሕፃን ሐረገወይን ቀለሙ በ19:00ውስጥ 100,000,000 view
Show all...
በአል❌ በዓል✅ ትንሳኤ❌ ትንሣኤ✅
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እና ዮሐንስ ዘደማስቆ ሐዋርያው ጴጥሮስ ጌታ በዐረገ በዓመቱ (34 ዓ.ም.) ቅዱሱን እሳት በመቃብሩ ስፍራ ማየቱን ጽፈዋል። ይህ ተአምር አሁን እስካለንበት ዘመን የቀጠለ ሲሆን፣ ሁል ጊዜም በትንሣኤ በዓል ዋዜማ ቅዳሜ ቀን ይታያል። ስለዚህ የሚያስደንቅ ተአምር ብዙ የማያምኑ ሰዎች በራሳቸው መንገድ ለማጣራት ሞክረዋል። እስኪ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ታሪክ ላጫውታችሁ። በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ… ዕለቱ ቅዳሜ ጠዋት 4 ሰዓት የትንሣኤ ዋዜማ ነው። የእስራኤል አይሁድ ፖሊሶች እና የከተማዋ ከንቲባ  ይህ እሳት ይፈልቅበታል የተባለውን የጌታን መቃብር እውነትነት ማረጋገጥ ስለ ፈለጉ በውስጡ ለእሳቱ መነሣት ምክንያት የሚሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች ካሉ በሚል ለሁለት ሰዓታት ያህል ሦስት ጊዜ ጥብቅ ፍተሻ አደረጉ። ግን ምንም ሊያገኙ አልቻሉም። ቀጥሎም ሁለት መቃብሩን የሚጠብቁ ሙስሊሞችን በማምጣት ልክ የቀድሞዎቹ አይሁድ የጌታን መቃብር እንዳተሙ እነርሱም መቃብሩን ዘግተው በሰም እንዲያትሙት አደረጉ። ይህንም ተከትሎ በቦታው የነበሩ አረብ ክርስቲያኖች ቱርክ እስራኤልን በተቆጣጠረችበት በ13ኛው ክፍለ ዘመን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በየትኛውም ቦታ ቢሆን እንዳይዘምሩ የተከለከሉትን ቆየት ያለ ዝማሬ በኅብረት ከፍ ባለ ድምፅ መዘመር ጀመሩ። መዝሙሩም:- “እኛ ክርስቲያኖች ነን። ለብዙ መቶ ክፍለ ዘመናትም ክርስቲያኖች ነበርን። እስከ ዘላለምም እንዲሁ እንሆናለን፣ አሜን!” የሚል ነበር። እኩለ ቀንም ሲሆን የግሪኩና የአርሜንያው ፓትርያርክ፣ የግብፁ ሜትሮፖሊታንት እንዲሁም  ቀሳውስት እና ዲያቆናት ወደ ታተመው የክርስቶስ መቃብር መጡ። ከብዙ ጸሎት እና ምስጋናም በኋላ የታተመው የክርስቶስ መቃብር እንዲከፈት አደረጉ። ፓትርያርኩም ሞጣህቱን ብቻ አስቀርተው ከላይ የለበሱትን ልብሰ ተክህኖ በማውለቅ በክርስቶስ የዕድሜ ቁጥር ልክ ሦስት 33 ያልበሩ ሻማዎችን ይዘው ጨለማ ወደ ነበረው መቃብር ገቡ። ምእመናኑም ከውጭ ሆነው በአንድ ድምፅ ኪርያላይሶን (አቤቱ ይቅር በለን) እያሉ በመዘመር ይጠባበቁ ጀመር። ወደ ቅዱሱ መቃብር ገብተው የነበሩትም የግሪኩ ፓትርያርክ ያን በሰው ያልተቀጣጠለ እና የክርሰ‍ቶስን የትንሣኤ ብርሃን የሚያበሥረውን አምላካዊ እሳት ይዘው ብቅ አሉ። ይህን ጊዜ ጎልጎታ በእልልታ ተሞላች የቤተ ክርስቲያኑም ደወል በሐሴት ይደወል ጀመር። ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ እንኳን አደረሰን!!! ዲያቆን አቤል ካሳሁን
Show all...
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃኅ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ። (መዝ ፸፰፡፷፭/ ከውጭም ከሀገር ውስጥም በቀጥታ የደወላችሁ ቴክስትም ለእንኳን አደረሰህ መልእክታችሁ ባለመመለሴ ይቅርታ እየጠየቅሁ ለማኅቶተቶኔቶር አባላትና በዓለም ሁሉ ለምትገኙ አመሰግናለሁ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ !
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram