cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ertalepost ኤርታሌ ፖስት

Inbox @MarcusR17

Show more
EthiopiaAmharicThe category is not specified
Advertising posts
1 893
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ሲሸጡ የተገኙ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ 19 ሺ 200 ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላርን በኢትዮጵያ ብር እየቀየሩ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሥርቶ በ8 ዓመት ከ5 ወር እስራት እንዲቀጡ መደረጉን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ። ክርክሩን የመራው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 11ኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎት መሆኑ ተገልጿል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ሰደድ እሳት ተከሰተ በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በሚገኘው በአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ሰደድ እሳት መከሰቱን የቋራ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል ። የሰደድ እሳቱ በአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ በርሚል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሰሞኑን መከሰቱ ተነግሯል ። የተነሳው ሰደድ እሳት በቦታው ተገኝቶ መመልከት መቻሉን የቋራ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አ/ቶ ሲራጅ ሙሃመድ ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ። ሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር እየተደረገ ስላለው ሁኔታ ማወቅ ባይቻልም በቀጣይ ለብሔራዊ ፓርኩ ስጋት መሆኑ ተገልጿል ። የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ የህልውና ስጋት እንደገጠመው ከአሁን ቀደም ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል ። በፓርኩ ብርቅዬ እንስሳት የሆነውን ጥቁር ባለጋማ አንበሳን ጨምሮ ሌሎች የቱሪስት መዳረሻ መሆን የሚችሉ የዱር እንስሳት ያሉት ብሔራዊ ፓርክ እንደሆነ ይታወቃል ። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ በአፍሪካ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደምትገኝ ፕሬዝዳንት ባይደን ገለጹ አሜሪካ በአፍሪካ የጤና፣ መሰረተ ልማት፣ ንግድ እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደምትገኝ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ገለጹ፡፡ በዋሽንግተን ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የዩኤስ አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም አፍሪካን እንደ አኅጉር ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ለመንግስታት ከሚደረገው ድጋፍ በተጨማሪ በግል ንግድና ኢንቨስትመንት ላይ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ እያደረገች እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ በሚቀጥሉት 3 ዓመታት ውስጥ ከ15 ቢሊየን ዶላር በላይ ለግል ንግድና ኢንቨስትመንት የሚሆን ገንዘብ ወጪ ለማድረግ ማቀዳቸውን የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመላክቷል፡፡      
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጲያ በሚወጡበት ዙሪያ የሚነገረው መረጃ የጎንዮሽ ወሬ ነው ሲሉ አምባሳደር መለስ አለም ተናገሩ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በዛሬው እለት በውጭ ግንኙነት እና በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ረገድ ማብራሪያንና ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ እንዴት እንደሚወጡ ያለዉን አተገባበር በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የሚተገበር ነከዚህ ዉጪ የሚነገረዉ በሙሉ የጎንዮሽ ወሬ ነዉ ሲሉ መግለጻቸዉን ብስራት ሬዲዮ ከአምባሳደር መለሰ ሰምቷል፡፡ በሌላ በኩል አምባሳደሩ በሰጡት ማብራሪያ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ረገድ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ በማስመለስ ተግባር ከ 3 ሺህ በላይ ኡትዮጲያዉያንን ወደ ሀገር የማመለስ ስራ መተግበሩን ጠቁመዋል፡፡ከቀናት በፊትየዛምቢያ ፖሊስ የ27 ኢትዮጵያውያን አስከሬን በዛምቢያ ዋና ከተማ መገኘቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የፖሊስ ምርመራ እንደሚያመለክተው ከ20 እስከ 38 ዓመት የሆናቸው ወንዶች ንግዌሬ በተባለ አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች አስክሬናቸው ተጥሎ መገኘቱ ያመላክታል፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች እንደሆኑ እንደሚታመን የተነገረ ሲሆን አምባሳደር መለሰ በአሳዛኝ ሁኔታ  ህይወታቸዉ አልፎ  የተገኙ ኢትዮጲያዉያንን በተመለከተ የማጣራት ስራ ይከናወናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
Show all...
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሳሊቫን ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ በጦርነቱ ማቆም አተገባበር፣ በመንግሥት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ሥራዎች እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማደስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
Show all...
የፋይናንስ ደህንነት ዋዳ ዳሪክተር አቶ ቴድሮስ በቀለ ከነ ባለቤታቸው እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንንነት አስታዳደር የመረጃ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ኃላፊ አቶ ባህሩ ደምሴን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች ከ5ሚሊዮን ብር በላይ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ። በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎቹ 1ኛ የፋይናንስ ደህንነት ዋዳ ዳሪክተር አቶ ቴድሮስ በቀለ እና ባለቤታቸው ወ/ሮ እሩት አድማሱ÷ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንንነት አስታዳደር የመረጃ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ኃላፊ አቶ ባህሩ ደምሴን እንዲሁም የወ/ሮ ሩት እህት ወ/ሮ ቤቴሊዬም አድማሱ ናቸው። ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ተጠርጣሪዎቹ አቶ ቴድሮስ እና አቶ ባሀሩ በአገልግሎት ማዕከል ውስጥ የተሰጣቸውን ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም ከግብረአበሮቻቸው ጋር በጥቅም በመመሳጠር የሚሰሩበትን ድረጅት እና የባለሀብቶችን የስልክ ግንኙነት በመከታተልና በመጥለፍ መረጃ በመውሰድ ባለሀብቶች ገንዘብ እንዲከፍሉ በመጠየቅና ካልከፈሉ ደግሞ የፋይናንስ እቅስቃሴያቸው ከወንጀል ጋር ግንኙነት ያለው በማስመሰል የወንጀል ምርመራ እንዲደረግባቸው ለፖሊስ እንደሚሰጡባቸው በመግለጽና በማስፈራራት ጫና በመፍጠር ከበርካታ ሰዎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘቦ በመቀበል በሙስና ወንጀል መጠርጠራቸውን ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ገልጿል። በዚህ መልኩ ለጊዜው 5 ሚሊዮን ብር ተቀብለው ለግል ጥቅም ማዋላቸውን ጠቁሞ ማስረጃ መሰብሰቡን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስለው በመጠቀም በወንጀሉ ተካፋይ ናቸው ተብለው በተጠረጠሩት በአቶ ቴድሮስ በቀለ ባለቤት ሩት አድማሱና በ4ኛ ተጠርጣሪ የሩት እህት በሆነችው በወ/ሮ ቤቴሊዬም አድማሱ ስም ገቢ እንዲሆን እንደተደረገና እነዚህ ተጠርጣሪዎችም የወንጀል ተካፋይ በመሆን ገንዘቡን በጋራ በመደበቅ እና በመጠቀም መጠርጠራቸውንም አብራርቷል። በተጨማሪም 1ኛ ተጠርጣሪ በጥቅም ከተሳሰራቸው ግለሰቦች ጋር በመሆን ከዳንጓቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስልጣንን በመጠቀም ኮታና ቅድሚያ እንዲሰጣቸው በማድረግ ሲሚንቶ አውጥቶ እንዲሸጥ በማድረግ ወንጀል መጠርጠሩንም ፖሊስ ለችሎቱ አክሎ ገልጿል። በዚህ መልኩ እየተከናወነ ለሚገኘው ምርመራው ተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ እንዲያስችለው መርማሪ ፖሊስ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል። ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ ተብሎ በስር ማቆየት የግድ አይልም ሲሉ መከራከሪያ ነጥብ አንስተዋል። የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል። መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ በዋስ ቢወጡ ማስረጃ ሊያጠፋብን ይችላሉ ሲል ነዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል። የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ አዱኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ተጨማሪ ምርመራ ማስፈለጉን በማመን ለፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ፈቅዷል። ታሪክ አዱኛ
Show all...
“አፍሪካ፡ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት” በሚል መሪ ሀሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንት እና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙት ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ስታስጀምር፣ በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢልዮን ችግኞችን ለመትከል ማቀዷ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ ከታቀደው ግብ አልፋ በመላ ሀገሪቱ 25 ቢልዮን ችግኞች በመትከል የአራት ዓመት ዕቅዷን አሳክታለች። በዚህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለደን መልሶ ልማት ላደረገችው አስተዋጽዖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝታለች። #ertalepost Telegram t.me/ertalepost Twitter twitter.com/ErtaleP Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/ Instagram instagram.com/ertalepost youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሜሪካ ገብተዋል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በፓኪስታን በሰርጉ እለት ለባለቤቱ አህያ በስጦታ መልክ የሰጠዉ ባል መነጋገሪያ ሆኗል በፓኪስታን የሚገኙት ጥንዶች ቫሪሻ ጃቬድ ካን እና አዝላን ሻህ በቅርቡ የጋብቻ ስነስርዓታቸዉን ፈጽመዋል።ፓኪስታናዊው ሙሽራ በሠርጋቸው ቀን ለሙሽሪት የሰጠው ያልተለመደ ስጦታ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ቀልብ ስቧል። በሠርጉ ግብዣ ላይ አዝላን ሻህ ባለቤቱን አህያ በመስጠት አስገርሟል፡፡ የስጦታውን ምስል በኢንስታግራም በማጋራት ሻህ ልዩ ስጦታውን ያቀረበበትን ምክንያት አብራርቷል። " አህዮችን እንደምትወድ ሁልጊዜ አውቃለሁ ስለዚህ የሰጠኃት የሰርግ ስጦታ ይሁንልኝ" ሲል ጽፏል። ሙሽሪት ስጦታውን ካየች በኋላ በጣም መደሰቷን ተናግራለች፡፡ Via ዳጉ ጆርናል
Show all...