cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ነሲሃ ሙስሊም ወጣቶች ክበብ Nesiha Muslim Youth Club

“አገርን በአደራ የሚረከብ ወጣት ከምንም በላይ በስነምግባርና በዕውቀት የታነፀ መሆን እንዳለበት እናምናለን!”

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
309
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዓረፋ‐ትልቁ የአላህ ቀን ============== ነገ ጠዋት ፀሀይ ስትፈነጥቅ አላህ የፈቀደላቸውና በምርጫው ከሌሎች የለያቸው ጥቂት ሑጃጅ የአላህ ባሮች ወደ ዐረፋ ሜዳ ያመራሉ። ዋነኛውን የሐጅ ስነስርዐት አካል "ዉቁፍን" ሊፈፅሙ።… በእርግጥ የተርዊያ ቀን የሚሰኘውን የዛሬውን ቀን ሚና ውስጥ በዒባዳና በዚክር አሳልፈዋል። : የዐረፋ ቀን ታላቁ የአላህ ቀን ነው። ኃጢኣት ይሰረዝበታል። በእለቱ ዱዓ ተቀባይነት ያገኛል። ከምንም ጊዜ በበለጠ የአላህ እዝነት ለባሮቹ ቅርብ ይሆናል። : የዐረፋ ቀን ዲን የተሟላበት ቀን ነው። በሙስሊሞች ላይ የአላህ ፀጋ የተፈፀመበት እለት ነው። የተውበት ቀን ነው። ምህረት የሚታደልበት ቀን ነው። ለአላህ የሚዋደቁበት የዱዓ ቀን ነው። የለቅሶና የተስፋ ቀን ነው። በርካታ ትሩፋቶቹ በሐዲስ ላይ ተጠቅሰዋል። በእለቱ መፈፀም ያለባቸው ተግባራት ተጠቁመዋል: ‐ : ⚀ የአመቱ ምርጥ ቀን ጃቢር [ረዐ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከቀናት ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ነው።» ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል። በሌላ ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከዐረፋ ቀን በላይ አላህ ዘንድ በላጭ የሆነ ቀን የለም። አላህ [በእዝነቱ] ወደ ቅርቡ ሰማይ ወርዳል። በሰማይ ፍጡራን ላይም በምድር ሰዎች [ልቅና] ይፎክራል።» : ⚁ መላኢካ የሚሰበሰብበት ቀን: የዐረፋ ቀንን ክብር ለማወቅ አላህ የማለበት ቀን መሆኑ ብቻ ይበቃል። አላህ እንዲህ ይላል: ‐ [وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ] «በተጣጅና በሚጣዱበትም፤ (እምላለሁ)፡፡» ከአቡሁረይራ [ረዐ] እንደተዘገበው: ‐ ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «[ሱረቱል ቡሩጅ ላይ] 'ወልየውሚል‐መውዑድ/በተቀጠረው ቀን' የተባለው የቂያማን ቀን ነው። አልየውሙል‐መሽሁድ/የሚጣዱበት ቀን ደግሞ የዐረፋ ቀን ነው። አልየውሙሽ‐ሻሂድ/የሚጣደው ቀን ደግሞ ጁሙዐ ቀን ነው።» ቲርሚዚ ዘግበውታል። ሱረቱል‐ፈጅር ላይም በድጋሚ አላህ የማለበት ቀን ነው። አላህ እንዲህ ይላል: ‐ [وَٱلشَّفْعِ وَٱلْوَتر] «በጥንዱም በነጠላውም።» በዚህ አንቀፅ አል‐ወትር/ነጠላ የተባለው የዐረፋ ቀን ነው። ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ [ረዐ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ጥንድ የተባለው [ዙልሒጃ 10 ወይም] የአድሓ ቀንን ነው። ነጠላ የተባለው የዐረፋ ቀን [ዙልሒጃ 9] ነው።» : ⚂ ዲን የተሟላበት ቀን: ቡኻሪና ሙስሊም ዑመር ኢብኑል ኸጣብን [ረዐ] ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት «አንድ አይሁድ ዑመርን እንዲህ አላቸው: «የሙእሚኖች አሚር ሆይ! በመፅሀፋችሁ ውስጥ ያለች አንዲት አንቀፅ አለች። በእኛ በአይሁዶች ላይ ወርዳ ቢሆን የወረደችበትን ቀን ዒድ አድርገን እንይዘው ነበር።» አለ። ዑመርም «የቷ አንቀፅ?» አሉ። ተከታይዋን አንቀፅ ጠቀሰላቸው: ‐ [اليوم أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَٰمَ دِينًا] «ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡» ዑመርም [ረዐ] እንዲህ አሉ: ‐ «ይህ የወረደበትን ቀን እና በነቢዩ [ﷺ] ላይ የወረደበትን ስፍራም አውቀነዋል። በጁሙዐ ቀን የዐረፋ ሜዳ ላይ ቆመው ሳለ የወረደ ነው።» : ዲን በዚያን ቀን ተሟላ የተባለው ሙስሊሞች ከዚያ በፊት ሐጅ አድርገው ስለማያውቁ ነው። ሐጅ ሲያደርጉ ዲኑ ያኔ ተሟላ። ምክንያቱም ሐጅ የኢስላም አንዱ መዐዘን ነው። በዚያን ዓመት ከሺርክ የፀዳው በኢብራሂም መንገድ ላይ የተመሰረተው የሐጅ ስነስርዐት ከነሙሉ ክብሩ ዳግም ተግባራዊ ተደርጓል። ዲኑም ሙሉ ማእዘናቱ ተሟልቷል። : ⚃ ምርጡ ዱዓ: የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «ምርጥ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔና ሌሎች ነቢያት ከተናገርነው ሁሉ ምርጡ ንግግር "ላኢላሀ ኢልለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሐምድ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር" የሚለው ቃል ነው።» ቲርሚዚ ዘግበውታል። በዐረፋ ቀን የአላህን እዝነት እና ምህረት ለማግኘት ዚክርና ዱዓ ማብዛት ያስፈልጋል። በተለይም «ላኢላሀ ኢልለላህ» የእለቱ ምርጥ ዚክር ነው። : ⚄ ጾም: የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የሚመጣውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል ብዬ አምናለሁ።» ሙስሊም ዘግበውታል : ⚅ የዒድ ቀን ነው: የዐረፋ ቀን የዒድ ቀን ነው። ሙስሊሞች ከሚኮሩባቸው የበዓል ቀናቶቻቸው መሀል ይመደባል። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የዐረፋ ቀን፣ የአድሐ ቀን እና የተሽሪቅ ቀናት ለሙስሊሞች የዒድ ቀናችን ናቸው። የመብልና የመጠጥ ቀናት ናቸው።» ቲርሚዚ እና አቡ ዳዉድ ዘግበውታል። : ⚆ የምህረት እና ከእሳት ነፃ የሚደረግበት: የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «አላህ ሰዎችን ከእሳት ነፃ የሚያደርግበት ከዐረፋ ቀን የበለጠ ቀን የለም። አላህ [በእዝነቱ] ወደ ምድር ይቀርባል። በመላኢካዎች ላይም ይፎክራል። 'እነዚህ ባሮቼ ከእኔ ውጪ ሌላን አይፈልጉም!' ይላል።» ሙስሊም ዘግበውታል። : በዚህ እለት ከእሳት ነፃ መሆንና የአላህን ምህረት ማግኘት የሚሻ ሰው በአላህ እዝነት ለመታየት የሚያበቁትን ተግባራት ይፈፅም። ከሁሉም የመጀመሪያው ስራ ደግሞ ከኃጢኣት ነፍሱን መጠበቅ ነው። ሌሎች ተግባራት ተከታዮቹ ናቸው: ① ጾም ከሐጀኛ በስተቀር ሌላው ሰው ይጾማል። የዚህ ቀን ጾም የሁለት ዓመታት ኃጢኣት ያስምራል።ተክ ② ተክቢራ ተክቢራ የእለቱ ዓርማ ነው። በተለይም ከሱብሒ ሶላት ጀምሮ ከማንኛውም ሶላት በኋላ ተክቢራ ይደረጋል። ③ ማንኛውም ዚክርና ዱዓእ ቁርኣን መቅራት፣ ሶለዋት ማድረግ፣ ተክቢራ፣ ተስቢሕ፣ ተህሊል፣ ኢስቲግፋር ማድረግ። አንዳንዴ ለብቻ ቆይቶም በጀመዐ ዱዓና ዚክር ማድረግ የእለቱ ድምቀት ነው። እለቱ ጥቂት ተሰርቶ ብዙ የሚገኝበት በመሆኑ እንጠቀምበት! ቤተሰቦቻችንን እናንቃ! የምናውቀውን ሁሉ እናነሳሳ! አላህ ተውፊቅ ይስጠን! https://t.me/fiqshafiyamh
Show all...
Tofik Bahiru

«አላህ መልካም ነገርን የፈለገለት ሰው በዲን ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖረው ያደርገዋል።» ነቢዩ ﷺ ይህ በተውፊቅ ባህሩ እየተዘጋጁ የሚቀርቡ ተከታታይ ኢስላማዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ቻናል ነው። ትምህርቶቹ በፅሁፍ፣ በቪዲዮ እና በኦዲዮ ይቀርባሉ። ይከታተሉን፤ መልክቶቻችንን ለወዳጆችዎ ያጋሩልን!

ዐረፋ❤ በዚህ ቀን የሚደረግ ዱዓ በአላህ ፍቃድ ተመላሽ አይሆንም። አላህ ዱዓዎችን የሚቀበልበት ቀን ነው። ጭንቀት ፣ ሀጃ ፣ ምኞት ያላችሁ ሁሉ ዛሬን በዱዓ ሳትቦዝኑ አሳልፉ ቀደምቶች እንዲህ ይላሉ፦ 『በአረፋ ቀን የምናደርገው ዱዓ ተቀባይነት ስለመሆኑ የማንጠራጠር በመሆናችን ሀጃችንን ለዚያ ቀን እናቆይ ነበር።』 እንዲሁም ከቀደምት ደጋግ ታላላቅ ሰዎች አንዱ እንዲህ ይላሉ ፦ 『በአላህ እምላለሁ በአረፋ ቀን ዱዓ አድርጌ አላውቅም ሌላ አረፋ ከመምጣቱ በፊት አላህን የጠየቅኩት ሀጃዬ ሙሉ ለሙሉ ተፈፅሞልኝ ያገኘሁት ቢሆን እንጂ።』
Show all...
ﺍﻟْﺤَﺞُّ ﺃَﺷْﻬُﺮٌ ﻣَّﻌْﻠُﻮﻣَﺎﺕٌ ﻓَﻤَﻦ ﻓَﺮَﺽَ ﻓِﻴﻬِﻦَّ ﺍﻟْﺤَﺞَّ ﻓَﻠَﺎ ﺭَﻓَﺚَ ﻭَﻟَﺎ ﻓُﺴُﻮﻕَ ﻭَﻟَﺎ ﺟِﺪَﺍﻝَ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺤَﺞِّ ‏[ ٢ :١٩٧ ] “ሐጅ (ጊዜያቱ) የታወቁ ወሮች ናቸው። በእነርሱም ውስጥ ሐጅን (እንዲሠራ) ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም።”(አል-በቀራህ 2፤ 197)
Show all...