cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

BBC Amharic

ወቅታዊ መረጃ ማቅረብ ቀዳሚ አላማው ነው ።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
128
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በህዳሴ ግድቡ አካባቢ ያለው የኢትዮጵያ የአየር ክልል ለበረራ ዝግ መደረጉ ተገለጸ!‼️ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ወሰንየለህ ሁነኛው (ኮሎኔል) ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በሚገነባበት ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ የአየር ክልል ከማንኛውም ዓይነት የበረራ እንቅስቃሴ ዝግ እንዲሆን፣ ከሚመለከታቸው የደኅንነት አካላት ጋር በመወያየት ክልከላ ተጥሎበታል። በመሆኑም የንግድ ወይም የመንገደኞች ማጓጓዣ አውሮፕላኖችም ሆኑ ሌሎች ዓይነት የበረራ እንቅስቃሴዎች፣ ግድቡ በሚገኝበት አካባቢ መከናወን እንደማይችሉ ገልጸዋል። ይህ ቢሆንም የሚመለከተው አካል በሚሰጠው ልዩ ፈቃድ ብቻ በተከለከለው የአየር ክልል በረራ እንዲደረግ ሊፈቀድ እንደሚችል አስረድተዋል።  የአገርን ደኅንነት ለማረጋገጥ እንዲህ ዓይነት ክልከላዎችን መጣል በዓለም አቀፍ አሠራር የተለመደ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኢትዮጵያም የግድቡን ደኅንነት ለማረጋገጥ ሰትል ይህንን ክልከላ መጣሏን ገልጸዋል። #Share_በማድረግ_ለሌሎች_ያጋሩ #አስተያዬት_ወይም_ጥቆማ_ካለዎት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @PaaaaactBot Join_ለማድረግ👇👇👇👇👇 @dagandro
Show all...
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሰኔ 22/2012 ዓ/ም - መስከረም 8/2013 ብቻ እስከ 150 ሰዎች መገደላቸውን 3 ፓርቲዎች አሳውቀዋል! በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሱት ፦ - የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) - የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ - የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ ነፃነትና ንቅናቄ ለሰላም እና ዴሞክራሲ ድርጅት ከሰኔ 22/2012 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 8/2013 ዓ/ም ድረስ በጉባ፣ ወንበራና ቡለን ወረዳዎች በታጣቂዎች እና በፀጥታ አካላት በተወሰዱ እርምጃዎች እስከ 150 ሰዎች መሞታቸውን ከ50 በላይ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው በጥናት ማረጋገጣቸውን ለ 'አዲስ ማለዳ' ጋዜጣ አሳውቀዋል። ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ (መስከረም 16) @dagandro @dagandro
Show all...
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን መቀበል ከመጀመራቸው አስቀድሞ የተቋማቱ ዝግጁነት እንደሚረጋገጥ ተገልጿል! የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በጅማ ዩኒቨርስቲ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተከታዩን ብለዋል፦ - ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መች ይከፈቱ  የሚለው ትክክለኛ መልስ እያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ በWHO መለኪያ መስፈርት መሰረት ደረጃውን ጠብቆ በተዘጋጀ ዝርዝር በጥልቀት የዝግጅት መጠኑ ተፈትሾ ዝግጁ ሲሆን ብቻ ነው። በዚያ መሰረት የተቋማት ዝግጅት ይፈተሻል። በዳሰሳውም መሰረት መቀበል እንደሚችሉ ፍቃድ ይሰጣል። - ቅድሚያ ለተመራቂዎች በመስጠት ተማሪዎችን በመከፋፈል በትንሽ ቁጥር ይጀመራል፡፡ ይህም ከሚታዩ ነገሮች ትምህርት እየተወሰደ የተማሪ ቁጥር ለመጨመር እድል ይሰጣል። ዝርዝር አፈጻጸሙ በምን እንደሚመራ ከጤና ሚኒስቴር  ጋር በመሆን ፕሮቶኮል ይዘጋጃል። - የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማጓጓዝ ሂደት ውስጥ ችግር እንዳያጋጥም ከትራንስፖርት ሚኒስቴርና ጤና ሚኒስቴር  ጋር በትብብር ይሰራበታል። - ዩኒቨርስቲዎች ከአሁኑ ተማሪዎች መልሶ ለመቀበል የሚያስችል እቅድ አዘጋጅተው ከአስተዳደር ሰራተኞች እና መምህራን ጋር በመወያየት የጋራ ሊያደርጉ ይገባል። - አንድ ብሎክ ወይም አንድ ካምፓስ ኮቪድ-19 ቢያጋጥም ምን ይደረጋል ከሚለው ጀምሮ በዝርዝር መስራት እና እያንዳንዱ እቅድ ያለተማሪዎች እገዛ ተፈፃሚ ስለማይሆን ወደተማሪዎች ለማስረፅ መስራት የግድ ይላል። - የመከላከያ ቁሳቁሶችን አስመልክቶ ደግሞ የትኞቹ በዩኒቨርስቲዎች ይቅረቡ የትኞቹ በተማሪዎች ይሟሉ የሚለውን ከተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተለይቶ መወሰን አስፈላጊ ነው። (MoSHE-Dr Samuel Kifle) @dagandro @dagandro
Show all...
ትምህርትን እንደ መነገጃ የሚቆጥሩ የግል ትምህርት ቤቶች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የትምህርት ሚኒስቴር አስጠንቅቋል!‼️ የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ሙያውን አክብረው የሚሰሩ የግል ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ሁሉ ትምህርትን እንደ ሸቀጥ የሚቆጥሩ የግል ትምህርት ቤቶችም አጋጥመውናል ብለዋል። መንግስት የወሰነውን የነፃ ዝውውር ወደ ጎን በመተው የትምህርት ክፍያ ካልከፈላችሁ ወደ ቀጣዩ ክፍል አትዛወሩም የሚሉ የግል ትምህርት ቤቶች እንዳሉ አጋጥሞናል ነው ያሉት። ትምህርት ቤቶች ቀድመው ሲያስከፈሉ ከነበረው የአከፋፈል ስርዓት ውጪ አዲስ የአካፋፈል ስርዓት ሲከተሉ የተገኙ እንዳሉም አንስተዋል። በዚህ ተግባር ውስጥ የተገኙ ትምህርት ቤቶች እስከ መዘጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል። የትምህርት ቤቶቹ አስተዳደሮች ቢወስኑ እንኳ የተማሪ ወላጆች ማህበር ያልተስማማበት ክፍያም ሆነ አከፋፈል ተቀባይነት የለውም። አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ደግሞ የወላጅ ማህበር አባላትን ልጆቻችሁን እናባርራለን የሚል ማስፈራሪያም እያደረሱባቸው ስለመሆኑ ተሰምቷል። @dagandro @dagandro
Show all...
#COVID19Ethiopia ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,221 የላብራቶሪ ምርመራ 602 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 553 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 67,515 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,072 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 27,638 ደርሷል። @dagandro @dagandro
Show all...
- ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በአግባቡ መከናወናቸው የሚያረጋግጥ ግብረ ኃይል በየትምህርት ቤቶቹ ሊቋቋም እንደሚገባ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል። - የሰዎችን ቁጥር በመመጠን እና የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መስፈርቶችን በመተግበር ስብሰባ ፣ ሲኒማ ፣ ቲያትር ፣ የስፖርት ዝግጅቶች ፣ ማህበራዊና ሐይማኖታዊ በዓላት፣ የአደባባይ በዓላት፣ ሊፈቀዱ እንደሚገባ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። - ጤና ሚኒስቴር በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ በመላ ሀገሪቱ አስገዳጅ ሊሆን ይገባል ብሏል። (ኢቲቪ) @dagandro @dagandro
Show all...
ተራዝሞ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ አሁን ላይ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ማካሄድ እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክረ ሀሳብ አቅርቧል። በጤና ሚኒስቴር በቀረበው መክረ ሀሳብ ላይ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየት እየሰጡ ሲሆን፥ የምክር ቤት አባላቱ ከተወያዩበት በኋላ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። @dagandro @dagandro
Show all...
በኢትዮጵያ በ10 ቢሊዮን ዶላር 25 ጊጋ ዋት ተጨማሪ ኃይል ለማመንጨት ፍላጎት እንዳለው ፎርቲስኪው የተባለ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር 25 ጊጋ ዋት ተጨማሪ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ውይይት ፎርቲስኪው ከተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር አካሂዷል። ድርጅቱ 15 ጊጋ ዋት ከውኃና 10 ጊጋ ዋት ከጂኦ ተርማል ለማመንጨት እና 10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ እንደሚፈልግ አስታውቋል። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ይህ ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ነው ሲሉ ገልጸዋል። እ.አ.አ. በ2030 ኢትዮጵያ ለዜጎቿ መቶ በመቶ ኃይል ለማቅረብ ያቀደች በመሆኑ ይህ ውይይትና የድርጅቱ ተነሳሽነት ጠቀሜታ ያለው ነው ብለዋል። ፎርቲስኪው የተሰኘው የዓለም አቀፍ ድርጅት በአውስትራሊያ በጊኒና በሌሎችም ሃገራት ተመሳሳይ ሥራ በመሥራት ውጤታማ እንደነበር ገልጸው በኢትዮጵያ 25 ጊጋ ዋት ሃይል ለማመንጨት ያላቸውን ፍላጎት ለሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል። ፎርቲስኪው በማዕድን፣ በማዳበሪያ፣ በኃይል ማመንጨት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በሌሎችም ሥራዎች ላይ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለውም ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። @dagandro @dagandro
Show all...
የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል! በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረጋጋት የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ በግጭት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ25 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ሰሞነኛ ጉዳዮችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ተከታዩን ብለዋል ፦ - በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች አቅም በላይ አልነበረም ሊከሰትም አይገባው ነበር። - ችግሩ በተፈጠረበት ሰዓት መከላከያ የራሱ ተልዕኮ ላይ ነበር ሠራዊቱ ወደ ስፍራው በማቅናት የአከባቢውን ሰላምና ደህንነት የማስከበር ስራ በጀግንነት ተሰርቷል። - መከላከያ ከገባ በኋላ በአጥፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰዱ አሁን በክልሉ ያለው ሁኔታ ወደ ቀድሞ ሰላማዊና መረጋጋት እንቅስቃሴ ተመልሷል። - በማህበራዊ ሚዲያዎች “መካላከያ ቀድሞ ወደ ስፍራው አልደረሰም” በሚል እየተናፈሰ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው። - በክልሎች የፀጥታ ችግሮች ሲከሰቱ የማረጋጋት ግዴታ በዋናነት የክልልና የወረዳ የጸጥታ ኃይል ነው መከላከያ የራሱ ግዳጆች ቢኖሩትም ከክልሎቹ አቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥም አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። - በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መከላከያ ግዳጅ እንደተሰጠው ከ150 ኪሎ ሜትር ውስጥ 50 ኪሎ ሜትሩን በእግሩ በመጓዝ በታጣቂዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ወስዷል። (ኢቲቪ) @dagandro @dagandro
Show all...
በትግራይ ክልል ምርጫ ባይቶና አንድ ወንበር ማግኘቱ መገለፁ ይታወሳል ፣ ዛሬ ፓርቲው በሰጠው መግለጫ ወንበሩን ሊረከብበት የሚያስችል የሕገ አግባብ አለመኖሩ ገልጿል፡፡ ባይቶና በምርጫው ያገኘው 93,945 ድምፅ አንድ ወንበር ሊያስገኝለት የሚችል ሕጋዊ የቁጥር ስሌት አለመኖሩን ፣ ይልቁንስ የቀረው አንድ ወንበር ለህወሓት እንደሚገባ ፓርቲው ጠቁሟል፡፡ ከዚህ ውጭ ባይቶና በምርጫው ሂደት በርካታ ሕገ-ወጥ ተግባራት መፈፀማቸውን ጠቅሶ አውግዟል። - በምርጫው ዕለት የባይቶና ታዛቢዎች በፖሊስ ከምርጫ ጣብያዎች እንዲወጡ ተደርጓል፣ - እጩዎች ታስረዋል፣ ዛቻ ደርሷቸዋል፤ - ህዝብ አማራጭ ፓርቲ እንዳይመርጥ በገዢው ፓርቲ ታችኛው መዋቅር ማስፈራራት ተፈፅሟል፣ - ለምረጡኝ ቅስቀሳ የተከራያቸው መኪና ባለቤቶች ታስረዋል የሚሉና ሌሎች ቅሬታዎች ከባይቶና ተነስተዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ችግር መካከል ባይቶና ፓርቲ ቀላል የማይባል ድምፅ ማግኘቱ እና "የመጪው ግዜ ፓርቲ" መሆኑ አሳይቷ ሲሉ የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ ክንፈገብርኤል ገብረዮሐንስ መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል። @dagandro @dagandro
Show all...