cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Eyorica Sound and Qouets

በዚ ቻናል ቆየት ያሉ የ #ሀገር ውስጥና የ ውጭ ዘፈኖች በkb . .. ... .... ..... ....... እንዲሁም #ጥቅሶችን ያገኛሉ ኣሁኑኑ ይቀላቀሉን Join as 👇👇👇 @eyoric @eyoric @eyoric For any comment @Ab_sha

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
187Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Conditioned Mind "It is not because things are difficult that we do not dare; it is because we do not dare that things are difficult." - Seneca --- በሕንድ መንደሮች ውስጥ ሲዘዋወር የቆየ አንድ እንግዳ ሰው ነዋሪዎቹ ዝሆኖቻቸውን የሚጠብቁበት መንገድ ግራ አጋብቶታል... እጅግ ግዙፍ የሚባሉ ዝሆኖች በቀላሉ ሊበጠሱ በሚችሉ ገመዶች ታስረው በጸጥታ የመቆማቸው ምስጢር እውነትም እንቆቅልሽ ነበር... 'እንዴት ሊሆን ይችላል?'... ግራ መጋባቱ እየቀጠለ ሲሄድ ወደ አንድ የዝሆኖች አሰልጣኝ ዘንድ ቀርቦ 'ይህን እንዴት ማድረግ ቻላችሁ?... ዝሆኖች በምድር ላይ በጉልበታቸው ተስተካካይ የሌላቸው ፍጥረታት መሆናቸው ይታወቃል... በዚህ ሰላላ ገመድ ታስረው እንዲቆዩ ያደረጋቸው ምስጢር ምንድነው?...' ሲል ጠየቀ... 'ደህና...' አለ ዝሆኖችን የሚገራው ሰው... በእንግዳው ሰው ጥያቄ አንዳችም መገረም ሳያሳይ... 'በዚህ ገመድ መታሰር የሚጀምሩት ከደረጁ.. ጉልበት ካበጁ በኋላ አይደለም... ገና ግልገል ሳሉ ነው... በዚያ የማለዳ ዕድሜ አሁን የምታየው ገመድ እነርሱን አስሮ ለመቆየት በቂ ነበር... እየቆዩ ሲሄዱ ገመዱን የሚበጥስ አቅም ቢፈጥሩም በልጅነታቸው የታተመባቸው እምነት ግን ዛሬም ገመዱን መበጠስ እንደማይችሉ ይነግራቸዋል'... ሰውየው በጥበባቸው ተገረመ... ግዙፉን ዝሆን ለማሰር ግዙፍ ሰንሰለት አላስፈለጋቸውም... አስተሳሰባቸውን የሚያስር የማለዳ ልማድ በቂ ነበር... ነገሩ ሰንሰለት ካሰረው ልማድ ያሰረው ነው... 'ልማድ ከብረት ይጠነክራልና' ሼክስፒር እንዳለው... የኑረት ውበት በየደረሱበት መጠየቅ... የሰውነት ከፍታም በየመዳረሻው መርቀቅ ቢሆንም ከተነገረው ዘሎ 'ለምንና እንዴት' ለማይል አዕምሮ የነበረን ማስጠበቅ እንጂ 'አዲስ ነገር' ማፍለቅ አይሆንለትም... የኑረት ስኬትም ሆነ ውድቀት በእምነትህ ልክ ይገነባል... ቡድሃ "All that we are is the result of what we have thought. The mind is everything. What we think we become. " የሚለውን ቃል በትምህርቱ መጀመሪያ ላይ ያስቀመጠው ለዚሁ ነበር... የምታምናቸውን ነገሮች ለምን እንዳመንካቸው ጠይቀህ ታውቃለህ?... የተቀበልካቸውን እሳቤዎች ልክነት በ'እንዴት' ዓይን መዝነህ ታውቃለህ?... የነገሩህን መጽሐፍትና ያስተማሩህን አንደበቶች መርምረህ ታውቃለህ?... እርግጠኛ ስለሆንክባቸው ጉዳዮች ቢያንስ ለራስህ በታማኝነት የምታቀርበው መልስ አለህ?... ወይስ እንደ ግዙፉ ዝሆን በሰላላ የአስተሳሰብ ወደሮ ታብተሃል?... መጠየቅስ አድክሞህ ይሆን?... Wynn Bullock የተባለ ሰው... "If you stop searching, you stop living, because then you're dwelling in the past. If you're not reaching forward to any growth or future, you might as well be dead." ብሎ ነበር... ሶቅራጥስ በበኩሉ "The unexamined life is not worth living" ብሏል... ከማለዳ ውልደት እስከ ውድቅት ህልፈት የምትሳበው ኑረት ሁለንተናዋ በጠነከረ ልማድ የተቀየደ ነው... ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ የትወናዋን አካሄድ የሚወስንላት መራሔ ተውኔት ልማድ ወይም እምነት ይባላል... የምታምነውን ነው የምትሆነው... ግና.. የማለዳ እምነትህ ረፋድ ላይ... የረፋድ እሳቤህ ቀትር ላይ... የቀትር ግንዛቤህ በተሲዓት... የተሲዓት እውነትህ በምሽት ካልተመረመረ ከልማድ እስረኛነትህ ሳትፈታ ውድቅትህ ይመጣል... "The world is a prison and we are the prisoners.Dig a hole in the prison wall and let yourself out." ይልሃል ሩሚ... 'ተለምዷል' የሚልህ ሰው ሲበዛ ጠርጥር... ቅኝት ነው... 'ምንም ማድረግ አይቻልም' ካለህ ተቃኝቷል በቃ... 'ያለ ነው'... 'ባሕል ነው'... 'አሰራር ነው'... 'እከሌ የሚባል ሰው ወይም መጽሐፍ ላይ ሰፍሯል'... ወዘተረፈዎች የቅኝት መገለጫዎች ናቸው... እዚህ መንደር ውስጥ 'ለምን' ባይ የተገኘለት የእብደት ታፔላ ይለጠፍለታል... ዕድሜ ልኩን ጥርሱን ሳያጸዳ የኖረ ሰው ለተወሰኑ ቀናት ብሩሽ ተጠቅሞ በመተዉ የአፉን ሽታ ቢያስተውል ሊል የሚችለው አንድ ነገር 'የጥርስ ሳሙና አፍ ያሸታል' ነው... ብሩሽ ከመጠቀሙ በፊት ሽታውን ተላምዶት ስለቆየ 'አፍህ ይሸታል' ቢሉት አይቀበልም ነበር... ብሩሹ ካለመደው ንጽህና በኋላ ግን የትኛውንም ሽታ መረዳት ይጀምራል... ተለማምዶ እስኪዘነጋው ድረስ... ጠረን እንድትለይ የሚረዱህን 'ብሩሾች' ስንቴ 'ያሸታሉ' ብለህ ጣልክ?... ስንቴስ ወደ ቀደመ ሽታህ ተመለስክ?... ኒቼ በተወልን ድንቅ መስመር የማያልቀውን እንጨርስ... "If you have a 'why' to live by, you can live with any 'how'." የ'ለምን' እና 'እንዴት' ድፍረት ይስጠን!! ደምስ ሰይፉ
Show all...
#LaLiga መልካም የዓድዋ ድል ቀን ለኢትዮጵያዊያን ወዳጆቻችን እንመኛለን!
Show all...
Watch "Ali and abreham shalaye" on YouTube https://youtu.be/uNMuIXHzaqw 👆👆👆👆👆👆 Subscribe our channel please
Show all...
Ali and abreham shalaye

Created by VideoShow:http://videoshowapp.com/free

ልብ የሚነካ ታሪክ... _ባርባራ እና _ስቴፈን አንድ ቀን አንድ ሽማግሌ ታካሚ ሰው ከነርሷ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሁንም አሁንም ይቁነጠነጡ ነበር፡፡ አሁንም አሁንም ደጋግመው ሰዓታቸውን ያያሉ፡፡ ነርሷ ገረማትና ረጋ ብለው ሕክምናቸውን እንዲከታተሉ ነገረቻቸው፡፡ ሃሳቧን ተቀብለው ለጥቂት ሰኮንዶች ረጋ ቢሉም አሁንም የቀደመ ነገራቸው ተመለሰ፡፡ «ለምንድን ነው ይህንን ያህል ያልተረጋጉት? ያጋጠመዎ ችግር አለ?» አለቻቸው፡፡ «ፈጽሞ፤ ምንም ዓይነት ችግር አላጋጠመኝም» «ታድያ ለምን ይቁነጠነጣሉ፤ መረጋጋትኮ አልቻሉም» አለቻቸው፡፡ «ይቅርታ» አሉና አንገታቸውን ደፋ አደረጉ፡፡ ነገር ግን ወዲያውኑ ሰዓታቸውን ደግመው ተመለከቱት፡፡ «ሐኪሙን ለማግኘት የቸኮሉበት ምክንያት አለ?» አለቻቸው ነርሷ የሰውዬው ሁኔታ እንግዳ ሆኖባት፡፡ «አዎ፤ በቶሎ እርሳቸው ጋር ቀርቤ ብጨርስ ጥሩ ነው» አሏት፡፡ «ሌላ ሐኪም ጋር ቀጠሮ ይዘዋል» አለቻቸው፡፡ «ፈጽሞ፤ ሌላ ሐኪም ጋርስ ቀጠሮ የለኝም» አሉ ታካሚው፡፡ «ታድያ ወዴት ለመሄድ ነው ይህንን ያህል የቸኮሉት፡፡» «ከባለቤቴ ጋር አምስት ሰዓት ላይ ቀጠሮ አለኝ» አሉ ታካሚው፡፡ «ኦ፤ ከባለቤትዎ ጋር ከሆነማ ነገሩ ቀላል ነው፤ ማስረዳትም ይችላሉ፤ ባለቤትዎም ቢሆኑኮ የርስዎን ታክመው መዳን ይፈልጉታል፡፡ እናም እባክዎ አሁን በቂ ጊዜ ስለ ሌለዎ ይደውሉላቸውና አንድ አሥራ አምስት ደቂቃ እንደሚያረፍዱ ይንገሯቸው» አለች ነፍሷ እፎይታ እየተሰማት፡፡ «ባለቤቴ ጋር መደወል አልችልም፡፡ እርሷ ብደውልላትም መደወሌን አታውቅም፤ መደወሌንም አታስታውስም» አሉ በኀዘን ስሜት፡፡ «እንዴ ለምን?» አለች ነርሷ አሁን እንደገና ግራ እየተጋባች፡፡ «እርሷ ታምማለች፡፡ ያለችውም በአረጋውያን መጦርያ ነው፡፡ ሁሉንም ነገር አታስታውሰውም፡፡ አልዛይመር የተባለው በሽታ በጣም አጥቅቷታል፡፡» አሉና ታካሚው ሰዓታቸውን ተመለከቱ፡፡ «ታድያ በዚህ ዓይነት እርስዎንስ ያስታውሱዎታል እንዴ?» አለች ነርሷ በተሰበረ ልብ፡፡ «የኔ ልጅ እርሷኮ እኔንም አታስታውሰኝም፡፡ ፈጽማ ረስታኛለች» አሉ ታካሚው፡፡ «ማንነትዎን አያስታውሱዎትም፤ አያውቁዎትም ማለት ነው?» «አዎ አታውቀኝም፡፡ የምታስታውሰው ነገርም የላትም፤ ፈጽማ ረስታኛለች፤ የምገዛላትን፤ የማደርግላትን ነገር ሁሉ ረስታዋለች፡፡ እኔ አሁን ማን እንደሆንኩ አታውቅም» «ታድያ እንደዚህ የማያስታውሱዎ ከሆነ ለምን ቸኮሉ?» ለእርሳቸውኮ አምስት ሰዓትም ሆነ ሰባት ሰዓት ያው ነው፡፡ በሉ ቀስ ብለው ሕክምናዎን ጨርሰው ይሂዱ» አለች ነርሷ ነገሩን በማቅለል፡፡ «የለም የኔ ልጅ፤ እንደዚያ አይደለም፡፡ እኔ እርሷጋ ዘወትር እሑድ በአምስት ሰዓት መሄድን አስለምጃለሁ፡፡ ከርሷ ጋር በዚህ ሰዓት ቀጠሮ አለኝ፡፡ ብታውቀውም ባታውቀውም፤ ብታስታውሰውም ባታስታውሰውም ቀጠሮዬ ግን አይቀርም፡፡ ዋናው ነገር የርሷ ማስታወስ አይደለም ልጄ፤ የኔ ማክበር ነው፡፡ ይህ ለእኔ እና ለእርሷ ፍቅር ከሚከፈሉት መሥዋዕትነቶች አንዱ ነው፡፡ እርሷ አታውቀኝም፤ እኔ ግን አውቃታለሁ፡፡ ትናንት እንደዚህ አልነበረችም፡፡ እኔ የትናንትናዋን ሚስቴን ነው የማስታውሰው፡፡ ስለዚህ በሰዓቱ መሄድ አለብኝ፡፡ «ያኔ አታዬኝም፤ አትሰማብኝም ብዬ ምንም ነገር ተደብቄያት አድርጌ አላውቅም ነበር፡፡ ዛሬም አታውቅም ብዬ ምንም ነገር ላደርግ አልፈልግም፡፡ በሰው አለማወቅ መጠቀም ይበልጥ አላዋቂነት ነው ልጄ፡፡» «ለመሆኑ ካላስታወሱዎት አሁን ሂደው ምን ያደርጋሉ?» አለች ነርሷ የኒህን አስገራሚ ሰው የኑሮ ምሥጢር ለማወቅ ጓጉታ፡፡ «ልብሷን እቀይርላታለሁ፤ የቤቷን አበባ እቀይራለሁ፡፡ ወደ ውጭ አወጣትና ብታስታው ሰውም ባታስታውሰውም ዝም ብዬ በዚህ ሳምንት የሆነውን ነገር አወራታለሁ፤ ያለፈውን ትዝታ እያነሣሁ አጫውታታለሁ፡፡ ብትስቅም፣ ባትስቅም አንዳንድ ጊዜ ቀልድ እነግራታለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አጫጭር ታሪኮችን አነብላታለሁ፡፡ ይህ ሁሉ ድሮ ደኅና እያለች የማደርግላት ነው፡፡ አንዳችም አላጓድልባትም፡፡ አየሽ ልጄ፣ እኔ ያኔ ስንጋባ ቃል የገባሁት ለሚስቴ እንዲህ እና እንዲያ አደርግላታለሁ ብዬ እንጂ እርሷ እንዲህ እና እንዲያ ታደርግልኛለች ብዬ አይደለም፡፡ ይህንን ቃል የገባችው እርሷ ናት፡፡ እርሷ ደግሞ እስከ ምትችል ድረስ ይህንን ነገር አክብራ ፈጽማለች፡፡ አሁን ግን አትችልም፡፡ እኔ ግን ቃል የገባሁትን መፈጸም እችላለሁ፡፡ ስለዚህ ለምን አስቀርባታለሁ፡፡ አንቺ ለምን የራስሽን አታደርጊም? ያንቺን ጥሩነት እና መጥፎነት ለምን ሰዎች ይወስኑልሻል? አንቺ ራስሽ መወሰን አትችይም?» «አምስት ደቂቃዎን ብቻ ልውሰድብዎት፤ ይህንን ሁሉ እንደሚያደርጉላቸው ውለታዎን የማያስቡልዎ ከሆነ፤ ከርሳቸውም አንዳች ምላሽ የማያገኙ ከሆነ፤ ምን ይሁነኝ ብለው ይደክማሉ?» አለች ነርሷ አገጯን በመዳፏ ደግፋ፡፡ «እኔ ለሚስቴ አንዳች ነገር የማደርገው ውለታ ፍለጋ ብዬ አይደለም፡፡ የኔ ደስታ ሳደርግ እንጂ ሲደረግልኝ የሚገኝ አይደለም፤ በመስጠት እንጂ በመቀበል አይገኝም፤ በመሞት እንጂ በመግደል አይገኝም፤ እኛ አብረን ለመኖር ተስማማን፤ ቃል ገባን እንጂ፤ በደኅንነታችን ጊዜ ብቻ አብረን ለመሥራት ኮንትራት አልተፈራረምንም፡፡ ለኔ በደጉ ጊዜም ሚስቴ፣ ናት በክፉው ጊዜም ሚስቴ ናት፡፡ ሳትታመምም ሚስቴ ናት፤ ታምማም ሚስቴ ናት፡፡ ሌላው ቀርቶ ስትሞትም ሚስቴ ናት፡፡ እርሷ ብታልፍም እኔ ግን ትዝታዋን አግብቼው እቀጥላለሁ፡፡ ከዚያም ደግሞ በሞት እከተላታለሁ፡፡ ስለሚቀጥለው ዓለም አላውቅም፡፡ ከቻልኩ ግን እዚያም ብትሆን ሚስቴ ናት፡፡ እኔ ባልዋ ስሆን ለርሷ የባልነት ግዴታዬን ለማድረግ እንጂ ከርሷ ለመቀበል አይደለም፡፡ እርሷም የርሷን ለማድረግ እንጂ ከኔ ለመቀበል አይደለም፡፡ ልጄ ከሰጡሽ ተቀበይ እንጂ ለመቀበል ግን ስትይ ግን አትስጭ፡፡ አሁን ይብቃኝና እባክሽን ሐኪሙ ጋር ቶሎ አገናኝኝና ልሂድ፡፡» አሉ ታካሚው አሁንም ሰዓታቸውን እያዩ፡፡ ነርሷ ተገረመች፡፡ «ካላስቸገርኩዎ እባክዎን የባለቤትዎን ስም ይንገሩኝ» አለች ነርሷ በሶፍት ዓይኖቿን እየጠረገች፡፡ «ባለቤቴ ባርባራ ትባላለች፤ የኔ ከመዝገቡ ላይ አለልሽ» አሏት፡፡ «አዎ ሚስተር ስቴፈን» አለችና ማወቋን ገለጠችላቸው፡፡ ቀዳሚው ታካሚ ከሐኪሙ ጋ ለመውጣት ሲዘገዩ እኒህኛው ታካሚ ተነሡና ሄዱ፡፡ «እባክዎን ቆዩ» ለማለት ነርሷ ልብ አልቀረላትም፡፡ ነርሷ ፈቃድ ወሰደችና ለአሥራ አምስት ቀናት ያህል ቤቷ ተቀመጠች፡፡ እኒያ አረጋዊ ታካሚ የነገሯትን ነገር ደግማ ደጋግማ አምሰለሰለችው፡፡ በእርሳቸው ሕይወት ውስጥ ያለውን መመርያ መረመረችው፡፡ ከራስዋም ጋር ለማዛመድ ሞከረች፡፡ በአሥራ አምስተኛው ቀን አንድ ሃሳብ መጣላት፡፡ ሰዎች በራሳቸው ተነሣሽነት ከማንም ዋጋ እና ውለታ ሳይጠብቁ በጎ ነገርን እንዲያደርጉ የሚያበረታታ፤ የሚያስተባብር እና የሚያስተምር ተቋም መመሥረት፡፡ እጅግ ብዙ ሰዎችን በዚህ ዓላማ ያሰለፈ አንድ ትልቅ ተቋም መሠረተች «ባርባራ እና ስቴፈን» ይባላል፡፡ ልብ ይስጠን ማስተዋልን ያድለን እራሳችንን ምናይበት መስታወት ይሁነን ልባዊ ለጋስ ያድርገን ላሳብ አስታያታቹ ሁሌም እዚህ ላይ ያድርሱን 👉@Ab-chu @Eyoric @Eyoric @Eyoric ምንጭ:-በዳንኤል ክብረት ከ 11 አመት በፊት በሱ ብሎግ ለይ ሼር የተደረገ
Show all...
​​#​​ይነበብ ..📑 : : ፡ ፡ ❤️በጣም የሚዋደዱ ባልና ሚስት ድንገት በማይታወቅ ምክንያት በማሃላቸው ባለመግባባት የተነሳ ግጭት ይፈጠራል... ባል ይናደድና ይደበድባታል፤ ሚስት በጣም ታዝንና ታለቅሳለች ባል ትቷት ወደ መኝታ ቤት ይገባና ይተኛል፤ ሚስት ትንሽ ካሰበች በኋላ ወደ መኝታ ቤት ገብታ ትተኛለች፤ ሲነጋ ባል ከተኛበት ሲነቃ በጣም ደንግጦ ስቅስቅ እያለ ማልቀስ ይጀምራል...ሚስት ጥቅልል ብላበት አቅፋው ተኝታ ነበር፤ ለቅሶውን ሰምታ ትነቃለች እንዲም ትለዋለች እንዳስለቀስከኝ አስለቀስኩ ብድሬን መለስኩ ብላ እየሳቀች ሳመችው.... እሱም በጣም ተደስቶ አቅፎ ሳማት.....እሳትን በውሃ እንጂ በእሳት አታጠፋውምና።......... @Eyoric @Eyoric @Eyoric
Show all...

❂✿የዋህ ማለት ሀይል የሌለው ማለት አደለም ✿❂ የዋህነት ማለት ክፋትን በክፉ ለመመለስ ሙሉ ሀይል ይዞ ነገር ግን ሀይል ለክፋት ላለመጠቀምና እራስን መግዛት ማለት ነዉ።የዋህ ማለት ሞኝ ማለት ሳይሆን ሀይል እንዳለዉ እያወቀ ሀይሉን ለክፋት ሳይሆን ለመልካምነት ብቻ ለመጠቀም የወሰነ እራሱን የሚገዛ ማለት ነዉ፡፡ በየዋህነት ዉስጥ ደሞ ጥሩነት ወይም መልካምነት አለ።መልካምነት እንደወጥ ማጣፈጫ ጨዉ ማለት ናት ማንም ሰዉ በዉስጡ መልካምነት ሳይኖረዉ ደስተኛ መሆን፡መርካት፡ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፡ጤናማ መሆን አይችልም።ምክንያቱም መልካምነት ሀገር የለዉም ድንበር የለዉም ጥቁር ነጭ አይልም በነፃ አገልግሎት ወገንን ማስደሰት ሁል ጊዜ ለሰዉ በመስጠት በማድረግ እንጂ ዉለታ የማይጠብቅ እራስ ወዳድነት የማይሰማዉ ልዩ ነዉ መልካምነት።የሚገርመዉ መልካምነት ሁሌ በመስጠት በማድረግ የሚረካ ሲሆን ትርፉም የህሊና ሰላም ደስታ ፍቅር ጤና ብቻ ብዙ ነገር እናገኝበታለን ። @Eyoric @Eyoric @Eyoric
Show all...
💕 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷✏️

♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤ ➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤ ➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤ ➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟 ҒϴᏞᏞϴᏔ ϴΝ ҒᎪᏟᎬᏴϴϴᏦ =

https://www.facebook.com/fikrenbegtm

ᶠᵒʳ ᵃⁿʸ ᵖʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ = +251916898399 = T.me/Abate_Hiwote

♥️♡+:。.。 ... ..........➲........... 。.。:+♡♥️ ጥፋቶች ሁሉ በቅጣት አይታረሙም;- ጥበብ እጅግ_ያስፈልገናል‼ ምን አይነት? ታሪክ ነዉ....ይነበብ !! ፨በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ልጅ የመጀመሪያ ደረጀ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዉና፦ ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ አስተማሪውን "#አስታወስከኝ_ወይ?" ይለዋል። አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "#ይቅርታ_አላስታውስህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" አለው፤ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "#3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ሄዶ ይናገራል አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፍታችንን ወዴ ግድግዳ አዙረን እንድንቆም አዘዝከን። በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤የሚገባበትን አጠሁ። አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ሲሰድበኝ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርግቴን ሲሰሙ 😔 👌👌👌👌 በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ በቃ መጥፎ ዜናው ሊነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ። 👌👌👌👌 ፍተሻውም ስያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደ የቦታችሁ ተመለሱ አልከን። እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ። በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር። በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠራ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤አንተም ምንም ብለሃኝ አታውቅም። እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬ እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው። አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው። አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ #ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!"አለው። በህይወታችን ለሚናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ #ጥበብ_ያስፈልገናል‼ እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ...ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙምና 🙏 @Eyoric @Eyoric @Eyoric
Show all...
💕 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷✏️

♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤ ➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤ ➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤ ➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟 ҒϴᏞᏞϴᏔ ϴΝ ҒᎪᏟᎬᏴϴϴᏦ =

https://www.facebook.com/fikrenbegtm

ᶠᵒʳ ᵃⁿʸ ᵖʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ = +251916898399 = T.me/Abate_Hiwote

True love vs fake love 👌👌😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂 @Eyoric
Show all...
@Eyoric @Eyoric " JOIN "🦋
Show all...