cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አል ኢህሳን ኢሥላሚክ ቻናል

በጎ ተግባርን እንያዝ እንማማር ♥♥♥♥ እንዋደድ ነገ በአርሽ ጥላ ስር እንዲያካለን አል ኢህሳን የሙስሊሞች ጀመዐ

Show more
Ethiopia8 517The language is not specifiedReligion & Spirituality70 447
Advertising posts
422
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሂሳብ ይቅር ~ ትዳራችንን አደጋ ላይ ከሚጥሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሂሳብ ነው። አዎ ሂሳብ ብዙ ትዳር አናግቷል። ብዙ ቤተሰብ በጥብጧል። ብዙ ጓደኝነትን አደፈርሷል። ሂሳብና አብሮነት ብዙም አይጣጣሙም። የማወራው የገንዘብ ሂሳብ አይደለም። የነገር ሂሳብ እንጂ። "ምን ሲደረግ እንዲህ ተብየ?!" ማለት። ሰዎች ነን፣ ደካማ ፍጥረቶች። ጓደኛችን ላይ፣ የትዳር አጋራችን ላይ ለሚፈጥረው ነገር ደንታ ሳይኖረን የወረወርነው ቃል ስንት ልብ ያቆስላል?! ትኩረት ሳንሰጥ እንደዋዛ ከምንጥላቸው ቃላት ስንቴ የወላጆቻችንን ቅስም ሰብረናል? በሚያሳዝንና በሚያሳፍር ሁኔታ ስንት የቅርብ ሰዋችንን እናማለንኮ! ቦታ በምንሰጠው ጓደኛችን፣ ክፉ ደጉን አብሮ ባሳለፈ የትዳር አጋር በተሰነዘረ ቃል አቂመን ቅርበታችን ወይም ጥምረታችን የፈረሰ ስንቶች ነን? የነገር ሂሳብ በጥብቅ እያወራረዱ ሰላማዊ አብሮነትን ማስቀጠል ከባድ ነገር ነው። ብልጠት ሰው ጋር አያኗኑርም። "አህያን ሲጭኑ ሶስት ሆኖ፣ ከሰው ጋር ሲኖሩ ሞኝ ሆኖ" ይባላል። በዚች ምድር ላይ ከትዳር አጋር፣ ከጓደኞች ጋር አጉል ብልጥ ከሚሆን ይልቅ የዋህና ገራገር ሰው የተሻለ የልብ ሰላም አለው። አውዛዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:- "ሰላም አስር ክፍሎች አሉት። ከነዚህ ውስጥ ዘጠኙ የሚገኙት በሌሎች የሚሰነዘርብንን ጥፋት እንዳላዩ ሆኖ በማለፍ ውስጥ ነው።" ከቅርብ ሰው በተሰነዘሩ መጥፎ ቃላት ምክንያት ሊፈርስ ያዘመመን ትዳር፣ ወይም ሊበላሽ በቋፍ ያለን ጓደኝነት በይቅር ባይነት፣ በሆደ ሰፊነት በማለፍ ከአደጋ የታደገን እንዲሁም መልካም ግንኙነትን ያስቀጠለን ሰው አላህ አብዝቶ ይመንዳው። በዱንያም በኣኺራም ያስደስተው። ኣሚን። በድጋሚ የተለጠፈ = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

በጨለማ ተጓዦችን… አበስራቸው‼ ======================== ✍ ምናልባትም ቀን ላይ ላብ ጠብ በሚያደርግ የጉልበት ሥራ ላይ አሳልፈህ ይሆናል፣ ናላን በሚያዞር የጭንቅላት ሥራ ተወጥረህ ይሆናል፣ በጠዋት የወጣህ ወደ ቤትህ የምትገባው አምሽተህ ይሆናል፣ ርቦህ ደክሞህ መጥተህ ትንሽ አረፍ እንዳልክ የፈጅር ሶላት ይደርስና በዙሪያህ ባሉ መስጂዶች «ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ነው፣ ኑ ወደ ሶላት፣ ኑ ፈላሕ ወደምትወጡበት መንገድ…» የሚል የጌታህን ጥሪ በአላህ ባሮች አንደበት ትሰማለህ። ያኔ ነፍስህ በእንቅልፍ ሰመመን ውስጥ ሆና ከላይህ ላይ ያለውን ብርድልብስ አሽቀንጥረህ፣ ያንን ጣፋጭ እንቅልፍ ትተህ ለጌታህ ትዕዛዝ ምላሽ ለመስጠት ትነሳለህ ወይንስ «ቆይ ትንሽ እንቅልፌ ይውጣልኝና እነሳለሁ!» በሚል ሽንገላ ባልሰማ ጸጥ ብለህ ጸሐይ ሲወጣ መስገድ?  መቼም ከናካቴው አለመስገድ ይኖራል ብዬ አላስብም። አላህ ይጠብቀንና! ፈጅር ላይ ከዚያ ደክሞህ ካገኘኸው ጣፋጭ እንቅልፍ ለመነሳት እነዚህ 3 ሐዲሦች በቂ ናቸውና ላስታውስህ ወደድኩ። ♣ ①ኛ) ለአንተ ገና ሳያዩህ በትካዜ የናፈቁህና  ሁሌም የሚቆረቆሩልህ አዛኙ ነቢይ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ (بشرِّ المشائينَ في الظلمِ إلى المساجدِ، بالنورِ التامِّ يومَ القيامةِ) «በጨለማ ወደ መስጂድ ተጓዦችን የውመ-ል-ቂያማህ በሙሉ ኑር (ብርሃን) አበስራቸው።» [ጃሚዑ-ስ'ሶጚር: 2129፣ ሶሒሕ አቡ ዳውድ: 561] • √ ያኔ የውመል ቂያማህ ሁሉም ሰው በጭንቅ ውስጥ ሆኖ፣ ታላላቅ ነቢያትና የአላህ መልዕክተኞች ﷺ ሳይቀሩ «ነፍሴ ነፍሴ» በሚሉበት ቀን፣ ከፊሉ ሰው በጸሐይዋ ንዳድ ላቡ እስከ አፍንጫው ድረስ ሲያሰምጠው፣ ወደየት ልሽሽ፥ ወደየት ልግባ በሚልበት የጭንቅ ቀን… «ሙሉ በሆነ ኑር» ከመበሰር የበለጠ ምን መታደል አለና ነው ፈጅር ሶላት ላይ የምትዘናጋው? ይሄን ብስራት የነገረህ እኮ ተራ ሰው ሳይሆን የሁሉም ፈጣሪና ባለቤት የሆነው አላህ የላካቸው ውድ ነቢይ ﷺ ናቸው። በል ተነስ! * ②) ነቢይህ ﷺ እንዲህም ብለዋል፦ (مَن صَلَّى الصُّبحَ فَهُوَ فِي ذِمَّةِ اللَّهِ…) «ሱብሒን (የፈጅር ሶላትን) የሰገደ ሰው በአላህ ጥበቃ ስር ነው።» [ሙስሊም: 657] • √ እና እንደ ሙስሊም በአላህ ጥበቃ ስር ከመዋል የበለጠ ምን መታደል አለና ነው የምንዘናጋው? አላህ በጥላው ስር ካዋለህ አንተን የሚዳፈር ሁሉ ጥላውን እንደተዳፈረ ነውና የሚከላከልልህ አላህ ነው። ምክንያቱም ራስህን ለርሱ ሰጥተሃልና! ያ ሊጎዳህ ያለ ሁሉ ከአላህ በታች የሆነ አንድ ተራ ፍጡር ነውና በጥበቡ አደብ ያሲዘዋል። • √ አዕመሽ እንዳስተላለፈው በአንድ ወቅት ሳሊም (የዐብደ-ል'ሏህ ኢብኑ ዑመር ልጅ) ከሐጃጅ አጠገብ ቆሞ ነበርና (ያው ሐጃጅ ኢብኑ ዩሱፍ እንደምታውቁት…) አንዱ በአጠገቡ ሲያልፍ አየና ሐጃጅ ለሳሊም "የዚህን ሰው አንገት በሰይፍ ቅላው!" ብሎ አዘዘው። ሳሊምም የታዘዘውን ለመፈጸም ሰይፉን እንዳነሳ… ለሰውየው «ፈጅርን ሰግደሃል?» አለው። አንገቱ ሊቀ'ላ የነበረው ሰውየም «አዎ» ሲል መለሰ። ሳሊምም «በል! እንዳሻህ ጉዞህን ቀጥል!» አለውና ወደ ሐጃጅ ተመልሶ ይዞት የነበረውን ሰይፍ ጣለው። ሐጃጅም ለሳሊም «አንገቱን ቀላኸው?» ብሎ ጠየቀው። ሳሊምም «በጭራሽ» አለው። ሐጃጅም «ለምን?» አለው። ሳሊምም «እኔ አባቴ (ዐብደ-ል'ሏህን ማለቱ ነው) ነቢዩ ﷺ "የጠዋትን (የፈጅርን ሶላት) የሰገደ ሰው እስከ ምሽት ድረስ በአላህ ጥበቃ ስር ነው!" ብለዋል ሲል ሰምቸዋለሁ።» ብሎ መለሰለት። «በአላህ ጥበቃ ስር ያለን ሰው አልዳፈርም!» ማለቱ ነው። • √ ታላቁ የዘመናችን ዐሊም ኢብኑ ዑሠይሚንም ይሄን ሐዲሥ አስመልክተው በሪያዽ ሸርሓቸው ላይ ትንታኔያቸውን ሲያሰፍሩ እንዲህ ብለዋል፦ " في هذا دليل على أنه يجب احترام المسلمين الذي صدَّقوا إسلامهم بصلاة الفجر ؛ لأن صلاة الفجر لا يصليها إلا مؤمن ، وأنه لا يجوز لأحد أن يعتدي عليهم) «ይህ እነዚያን በፈጅር ሶላት እስልምናቸውን ያረጋገጡ ሙስሊሞችን ማክበር እንደሚገባ ማሳያ ነው። ምክንያቱም የፈጅር ሶላትን ሙእሚን እንጂ አይሰግዳትም። ስለሆነም ማንኛውም ሰው ድንበር ሊያልፍባቸው አይገባም።» [ሸርሕ ሪያዹ-ስ'ሷሊሒን: 1/591] • ምንም እንኳ እስልምናችን በማንም ንጹሐን ላይ ድንበር ማለፍን ቢከለክልም፤ ጭራሽ በእንዲህ አይነት ባሮቹ ላይ ድንበር ማለፍን ደግሞ የክልከላ ጥግን ከልክሏል። * ③ኛ) ሐቢቢ! የፈጅርን ሶላት ፈርዱን መስጂድ ሂዶ መስገድ፤ አይደለም ፈርዱን መስገድ ሱን'ናውን መስገድ ብቻውን ያለውን ደረጃ አልሰማህም? ወይንስ ሰምተህ መተግበር ተሳነህ? ውዱ ነቢያችን ﷺ ምን እንዳሉ ልንገርህ፦ ሐዲሡን ያስተላለፈችው ራሷ ባለቤታቸው እናታችን ዓኢሻህ (እውተኛዋ የእውነተኛ ልጅ) ናት - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና። ውዱ ነቢይ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ (ركعتَا الفجرِ خيرٌ من الدُّنيا وما فيها))، «የፈጅር 2 ረከዓዎች (ሱንናዎቹ)፤ ከዱንያና በውስጧ ካለው ይበልጣሉ።» [ሙስሊም: 725] وقال أيضًا እንዲህም ብለዋል ﷺ፦  ((لهُما أحبُّ إليَّ من الدُّنيا جميعًا) «እነርሱ ለኔ ከዱንያ ሁሉ የተወደዱ ናቸው።» • አስበው! ዱንያ ላይ ስንት ገንዘብና ስንት ስልጣን አለ? በየሃገራቱ ያሉ ውብና ሃብታም መንደሮችን፣ ዘመናዊ መኪኖችንና መኖሪያ ቤቶችን፣ የቅንጦት መዝናኛዎችን… ስንቱን ልዘርዝርልህ። ስታየው የሚያስቀና ስንትና ስንት ነገር አለ። «እኛም ከነዚህ ጋር እኩል እዚህች ዓለም ላይ እየኖርን ነው?» የሚያስብሉ ስንትና ስንት ቅንጡ ኑሮዎች አሉ? ግን ምን ዋጋ አለው? የፈጅርን እንኳን ፈርዱን ሱ-ን'ናውን መስገድህ ብቻ ከዚህ ሁሉ ይበልጣል። የሱን'ናው ትሩፋት እንዲህ ከሆነ ፈርዱ ምን ቢሆን ነው በአላህ! ኧረ! ያ አኺ! ተነስ እንነሳና ፈጅርን እንስገድ! ደግሞ ለዚህች ለማትሞላና ብትሞላ እንኳ ነገ ጥለናት ለምንሄዳት ዱንያ ብለን ይሄን ሁሉ ትሩፋት እናስመልጥ እንደ?  ትንሽ ደቂቃ እኮ ናት ሐቢቢ! 24 ደቂቃ እንኳ ላትሞላ ትችላለች! ታዲያ እንደት ከ24 ሰዓቱ ውስጥ 24 ደቂቃ ለጌታህ ትዕዛዝ ምላሽ ለመስጠት አጣህ? የተፈጠርከው እርሱን ለመገዛት ሆኖ ሳለ ሙሉ ጊዜህን መስጠት ባትችል እንኳ 24 ደቂቃ መስጠት ተሳነህ? አስበው! 24 ደቂቃ በስንት እንደምታልፍ! ከጓደኛህ ጋ ሻይ ቡና እንበል ብለህ ስንት ሰዓታት ነው የምታሳልፈው? ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ስንት ሰዓት ነው የምታሳልፈው? ኳስ… ገለመሌ እያልክ ምን ያክል ሰዓት ነው የምታሳልፈው? ታዲያ የባለዚሁ ሰው እንደት ይህቺን ታክል ደቂቃ ለሶላት መስጠት ከበደህ? ኧረ! ተው ሐቢቢ ተው! ብልጥ ሁን! የላ! ፈጅር አዛን ሲል ወደ መስጂድ! የምን እየሰሙ መሟዘዝ! የምን አላርም አለመቅጠር ወይም የቀጠሩትን ማጥፋት! አላህ ያግራልን! ውዶች አንዘናጋ! የፈጅርና የዒሻእ ሶላት ለሙናፊቆች ለማስመሰል እንኳ የማይመቹ የአማኝነት ማረጋገጫ ናቸውና እንበርታ።  * ለሌሎችም የፈጅር መስገድ መነሳሳት ሰበብ ከሆንን (ለአንድም ሰው ቢሆን) መልዕክቱን እናድርሳቸው። || ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ ========= ኖቬምበር 26, 2023 ♠ t.me/MuradTadesse ummalife.com/MuradTadesse fb.com/MuradTadesse X.com/MuradTadesse
Show all...
ነቢዩን የመውደድ ጥግ ቢስሚላህ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ አሰላሙዐለይኩም ውዶች፣ ሙስሊሞችየሆንን  ሁሉ ነቢዩ ሙሐመድን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንወዳለን ብለን እናምናለን የውዴታችን መጨረሻ መለኪያው የት ድረስ ነው? ? ከማንም ከምንም በላይ ከራሳችንም ነፍስ በላይ እርሳቸውን እንወዳለን? ? መልሱ እነሆ በራሳቸው አፍ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡“ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ አንዳችሁ አመነ አይባልም እኔን ከወላጁና ከልጁ በበለጠ ሁኔታ እስካልወደደ ድረስ።” /ቡኻሪ የዘገበው / የሀዲሱ የአማርኛ ትርጉም ደረሳው አፕ / በመሆኑም ነቢያችንን መውደድ እኔ በህይወቴ ባገኛቸው ከራሴ ነፍስ አብልጬ እወዳቸዋለሁ ፣እርሳቸው የሚጎዳ አደጋ ቢቃጣባቸው  መጀመሪያ ማረፍ ያለበት በኔ ላይ ነው።ለእሳቸው ህይወቴን  አሳልፌ እስከ መስጠት ድረስ የእርሳቸው ውዴታ ይገለጣል። የመውደድህ ጥግ እኔ እያለሁ ማንኛውንም አደጋ ተጋፍጬ እከላከላለሁ ፣ህይወቴ እስከ ማለፍ ድረስም ቢሆን  ለእሳቸው ዘብ እቆማለሁ ማለትንና መፈፀምን ያካትታል። ።አለበለዚያ ግን ሙእሚንነቱ የተሟላ አይሆንም። ለዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ያሉትም ይ ህንኑ መመዘኛ ነው። ቡኻሪ ሐዲስ ቁጥር 6632 ይመልከቱ ። እርሳቸው ካለፉ በኋላ ደግሞ ለዲናቸው ልዕልና መታገልና ዘብ መቆም፣ ሱናቸውን በመከተል ያደርጉዋቸው የነበሩ የሱና ተግባራትን  ህያው ማድረግና ክብራቸውን ማስጠበቅን ያካትታል። ወላሁ አዕለም። አላህ ሆይ የእርሳቸውን ውዴታ ወፍቀን በቂያም ቀን ሸፈዓቸውን ግጠመን አንተ ከአዛኞች ሁሉ አዛኝ ነህና። ወሰላም ኑረዲን ጀማል  07/03/2016 https://t.me/alfelah09
Show all...
በሰላት ውስጥ  ወደ ሰማይ ማየት  ሁክም ቢስሚላህ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ አሰላሙ ዐለይኩም ውዶች ፣ ነቢዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም  ሰጋጆች በሰላት ውስጥ ሆነው በዱዓእ ወቅት ወደ ሰማይ ማየትን እንደሚከተለው   ዛቻ አዘል ክልከላ  አድርገዋል። عن ابي هريرة رضي الله عنه  قل قل رسول الله ‏ لَيَنْتَهِيَنَّ أَقْوَامٌ عَنْ رَفْعِهِمْ أَبْصَارَهُمْ عِنْدَ الدُّعَاءِ فِي الصَّلاَةِ إِلَى السَّمَاءِ أَوْ لَتُخْطَفَنَّ أَبْصَارُهُمْ ‏ አቡ ሑረይራ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፣ ሰዎች በሰላታቸው ውስጥ ዱዓ በሚደረግበት ወቅት ዐይናቸውን ወደ ሰማይ ከማንጋጠጥ ይከልከሉ አሊያ ማያዎቻቸውን ከመነጠቅ  (ይጠንቀቁ)።   /ሙስሊም የዘገቡት  ሐዲስ ቁጥር 429/ እና ወንድም እህቶች በግልም ይሁን በጀመዓ ስንሰግድ በተራዊህ ሰላት ቁኑት ላይ እንዲሁም በዘወትር የለይል ሰላቶች ቁኑት ወይም በልዩ ወቅታዊ ኩነቶች ኢማሞች ዱዓ ሲያደርጉ  ከእውቀት ማነስና በነሻጣ ገብተን ፊታችንን ወደ ሰማይ የምናንጋጥጥ ከሆንን ልንጠነቀቅ ይገባናል። አላህ ሆይ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ዒባዳ እንድንፈፅም እርዳን ። ወሰለም ወሰሊላሁመ ወሰለመ ዐላ ነቢዪና ወቁድወቲና ሙሐመድ። ኑረዲን ጀማል 06/03/2016 https://t.me/alfelah09 አድ ና ሼር በማድረግ ሊላሂ ብላችሁ  ተባበሩ
Show all...
እናቱን እወዳለሁ የሚል ብቻ ሳያነብ እንዳያልፍ ✅✅የእናት ሐቅ✅✅✅ 1- ☞ድምፅክን ከድምጿ ከፍ አታርግ 2-☞አጉል ክርክር አትከራከራት 3☞-እሷ ሳትጨርስ አትናገር 4-☞በስሟ አትጥራት 5-☞እንቅልፏ ሳትጨርስ አትቀስቅሳት 6-☞ለምክንያት ካልሆነ በቀር ከፊት ተፊቷ አትቅደም 7-☞ባርያ ለጌታው እንደሚተናነስ ሁሉ ተናነስላት 8-☞ጠርታ ሳትጨርስ "አቤት" በላት 9-☞ከቤት ወጥተህ አትዘግይባት 10-☞በእይታህ አታፍጥጥባት 11-☞በንግግርህ አትጋፈጣት 12-☞በንግግሯ አትዘንባት 13-☞መላዋንና ሐሳቧን አታናንቅ 14-☞ሲጨንቃት አማክራት 15-ሲቸግራት እርዳት 16-☞ስትታመም አሳክማት 17-☞ስትታረዝ አልብሳት 18-☞ጉዳይዋ ሁሉ ጉዳዬ ነው በል 19-☞እቅድ ሐሳቧን ተካፈል 20-☞የስጋ ዘመዶቿን ቀጥል 22☞-ወዳጆቿን ውደድላት 23-☞ከእርግማኗ ተጠንቀቅ 24-☞እሷን ከማስከፋት ፈፅሞ ራቅ 25☞-ቀስ ብለህ አስረዳት 26-☞በሚገባት አነጋገርና ቋንቋ አነጋግራት 27-☞ከዱዓዋ ፈልግ 28-☞ለምርቃቷ ተሽቀዳደም 29-☞አላማህን አትደብቃት 30-☞እሷ ሳትቀመጥ አትቀመጥ 🌺🌸🌺🌸🌺🌸🌺🌸🌺🌸🌺🌸🌺🌸 https://t.me/TEBRAKEE https://t.me/httssshtt
Show all...
አላህን መዘከር ፈድል ቢስሚላህ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ "አላህን ማስታወስ በለጭ ነው" ብሎናል አላህ በቁርአኑ። ከፈርድ ስራዎች ባሻገር ካሉ የዒባዳ ስራዎች አላህን መዘከር  ከሚጠቀሱ ትላልቅ ዒባዳዎች አንዱ ነው። አላህን በቀንም በሌትም መዘከር ፣ ማወደስ ከበላጭ ስራዎች  ውስጥ ነው። የዚክር ታላቅነትንና የሚያስገኘውን ምንዳ አስመልክቶ ነቢዩ የሚከተለውን ሀዲስ ተናግረዋል። ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ)፦ “ከሥራችሁ ሁሉ ብላጭ ይሆነ፥ ወርቅና ብር ከምትለግሱ የተሻለ ምንዳ የሚያስገኝላችሁና ከጠላት ጋር ተገናኝታችሁ አንገታችሁን ከመሞሻለቅ የበለጠ ሥራ ልጠቁማችሁን?” በማለት ጠየቁ። “አዎ” አሏቸው። “አላህን ማውሳት” በማለት መለሱ። (ቲርሙዝይና ኢብን ማጀህ) አላህ ሆይ ከዛኪር ባሮችህ ደብልቀን ሼር አድ በማድረግ ዳእዋውን እናዳርስ https://t.me/alfelah09
Show all...
ቅናት  የተወገዘ ነው ከ ..... በቀር ቢስሚላህ  አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ ውዶች ቅናት በሰው ልጅ ዕለታዊ ህይወት የመከሰት ተግባር ሆኗል።አላህን ከሚፈሩና ከሚብቃቁ ባሮች በቀር።ያለውም የሌ ውምሴቱም ወንዱም፣ሸይኹም ይሁኑ  ምሁሩም ወይም ያልተማረውም ። ሸይጣን አባት አደምን ዐለይሂ ሰላምና  እናት ሐዋን አላህ ለአደም በሰጠው ከፍ ያለ ደረጃ በመቅናትና በመመቅኘት የተከለከሉትን ዛፍ እንዲበሉ  አሳሳታቸው ፣ከጀነትም እንዲወጡ አስፈረደባቸው። አሁንም የሰው ልጅ ይህን እኩይ ባህሪ ነፍሲያውን በመቆጣጠር  እስካልተዋጋ፣ ድረስ እስመገዳደል ሊያደርስ የሚችል  ጥፋትን ይፈፅማል።ጎትጓቹ ደግሞ ሰይፉን አስልቶ ይጠብቃል። በኢስላም ክፉ ቅናቶች የተወገዙ ናቸው። የተፈዱ ሁለት ቅናቶች ሲቀሩ ። እነዚህም ፣ አላህ ለሰውየው/ ለሴትየዋ   የሚሰጣቸው ሁለት ሽልማቶች በመልካም ኒያና ያማረ ተግባር ላይ  ካዋላቸው እውቀትና ሀብት ናቸው። በዚህ ረገድ በዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ አላህ ስራውን ይውደድለትና ባስተላለፈልን ሰሂህ ሐዲስ  ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም  እንዲህ ብለዋል። - ‹‹ቅናት በሁለት ነገር ላይ ብቻ (ይፈቀዳል)፡፡ አላህ ገንዘብ የሰጠው ሆኖ ሳለ ገንዘቡን በሐቅ ላይ በሚያውል ሰው እና አላህ ጥበብን (ዕውቀትን) ሰጥቶት በርሷ የሚፈርድና የሚያስተምር በሆነ ሰው፡፡››   (ቡኻሪ ዘግበወታል) አላህ  ሆይ የመልካም ባህሪያት  ባለቤቶች አድርገን። ወሰላም ኑረዲን ጀማል 30/02/2016 ወሰሊላሁመ ወሰለመ ዐላ ነቢዪና ሙሐመድ https://t.me/alfelah09
Show all...
ወለድን ራቁ በአላህ የተረገመ ተግባር ነውና ቢስሚላህ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ አሰላሙ ዐከይኩም ውዶች ፣ ከጉድለት የጠራው አላህ አራጣ /ወለድ የተከለከለ ሀራም ተግባር መሆኑን አስመልክቶ እንዱህ ይላል ٱلَّذِينَ يَأْكُلُونَ ٱلرِّبَوٰا۟ لَا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ ٱلَّذِى يَتَخَبَّطُهُ ٱلشَّيْطَٰنُ مِنَ ٱلْمَسِّ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا ٱلْبَيْعُ مِثْلُ ٱلرِّبَوٰا۟ ۗ وَأَحَلَّ ٱللَّهُ ٱلْبَيْعَ وَحَرَّمَ ٱلرِّبَوٰا۟ ۚ فَمَن جَآءَهُۥ مَوْعِظَةٌۭ مِّن رَّبِّهِۦ فَٱنتَهَىٰ فَلَهُۥ مَا سَلَفَ وَأَمْرُهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ وَمَنْ عَادَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ እነዚያ አራጣን የሚበሉ ያ ሰይጣን ከመንካቱ የተነሳ የሚጥለው ሰው (ከአውድቁ) እንደሚነሳ ብጤ እንጅ (ከመቃብራቸው) አይነሱም፡፡ ይህ እነርሱ መሸጥ የአራጣ ብጤ ብቻ ነው በማለታቸው ነው፡፡ ግን መሸጥን አላህ ፈቅዷል፡፡ አራጣንም እርም አድርጓል፡፡ ከጌታውም ግሳጼ የመጣለትና የተከለከለ ሰው ለርሱ (ከመከልከሉ በፊት) ያለፈው አለው፡፡ ነገሩም ወደ አላህ ነው፤ (አራጣን ወደ መብላት) የተመለሰም ሰው እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ ቁርአን የላም ምእራፍ 2 :275
Show all...
AMHARIC QURAN PRO - Apps on Google Play

The Noble Quran with Amharic Translation for Ethiopian muslim

ወንድምህን በዳይም ይሁን ተበዳይ እርዳው ቢስሚላህ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ አሰላሙ ዐለይኩም ውዶች፣ ሰው አምሳያውን ሰው የስጋ ወንድሙምይሁን የኢስላም ወንድሙን ወይም ባዳን ሰው እንዲያም ሲል የማያወቀውንም መንገደኛ ሊበድል ይችላል። ራስ ወዳድነት በሰው ውስጥ የተተከለች ትልቅ መርቃዥ መረዘኛ በሽታ ነች ።ከዚያም ወደምቀኝነትና ግድያ ሁሉ ልታመራ የምትችል የህይወት ቫይረስ ናት። መድሀኒትዋ  አላህን በመፍራት ነፍሲያን ሸይጣንን መቆጣጠር  ፣ተውበት ፣ዱዓ እና ሌሎችም ወደ መልካምነት የተዘበሉ ተግባራት ናቸው።በአላህ ፈቃድ። አልፎ ከመጣና ወንድም ወንድሙን ሲበድል ካገጠመህ፣ካየህ  ደግሞ "وعنه قال‏:‏ قال رسول الله صلى الله عليه وسلم‏:‏ “انصر أخاك ظالمًا أو مظلومًا” فقال رجل‏:‏ يا رسول الله أنصره إذا كان مظلومًا أرأيت إن كان ظالمًا كيف أنصره‏؟‏ قال‏:‏ ‏"‏تحجزه -أو تمنعه- من الظلم فإن ذلك نصره” ‏(‌‏(‏رواه البخاري‏)‌‏)‌‏.‏" ከአነስ ረዲየላሁ ዐንሁ በተላለፈልን ሐዲስ ነቢዩ  ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም " ወንድምህን በዳይም ይሁን ተበዳይ እርዳው አሉ።" አንድ ሰው እንዲህ አለ። አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ ተበዳዩን ልርዳውነገር ግን በዳዩን እንዴት እረዳዋለሁ?  በማለት ጠየቃቸው ። እርሳቸውም  "ከበደሉ ታቅበዋለህ ወይም ትከለክለዋለህ።ያ ተግባርህ እርሱን መርዳት ነው  አሉት።" ቡኻሪ የዘገቡት ወንድሞች,እህቶች   !!! በገዛ ሀገራቸው አየተገደሉናእተተባረሩ ላሉ ንፁሀን የገዛ ሙስሊም ወንድሞቻችንን ቢያንስ በትልቁ አላህ ስም በ ዱዓ እናግዛቸው አላሁመ እንሱርሁም ነስረን ሻፊያ ወካፊያ አላህ ሆይ የተበደሉ የገዛ ወንድሞቻችንን ነስራቸው ። ያናሲሩ፣ያዐዚዙ የወሊዩ መሳኪን እህዚም አዱዊከ ወዐዱዊህም ወሰለላሁመ ወሰለመ ዐላ ነቢዪና ሙሐመድ ኑረዲን ጀማል 29/02/2016 https://t.me/alfelah09
Show all...
ሳይሰገድ የተረሳ ሰላት  ማካካሻ ቢስሚላህ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ አሰላሙ ዐለይኩም አላህ በቁርአኑ ለነቢዩ ሙሳና ለተከታዮቻቸው ሰላትን ያዘዛቸው ለምን እንደሆነ ሲገልፅ  እንዲህ ይላል *ሱራህ 20, አያህ 14* إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ «እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ ። " ቁርአን ምእራፍ  ጠ ሀ  20:14 በአርካኑል ኢስላም በየአንድ ሰው ሙስሊምነት መመዘኛው ሰላት መስገድን ግዴታው መሆኑን አምኖ ሲሰግድ ነው። አላህ በቁርአን  ሰላት ክፉ የሆኑ ና የተጠሉ ተግባራትን እንዳይፈፅም ትከለክላለች ይለናል ። በመሆኑም ሰላት በጊዜዋ በስርዓትዋ ልትሰገድ ይገባል። ሳይሰግድ በመርሳት ሰላት ወቅት ያለፈበት  ው ልክ እንዳስታወሰው ይስገድ። ነቢዩ እንዲህ ብለዋል ። :-!አነስ ኢብን ማሊክ (ረድየሏሁ ዐንሁ/ሃ) እንዳወሱት ነቢዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሶላት ረስቶ ያልሰገደ ሰው ልክ እንዳስታወሰ ይስገዳት፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ ማካካሻ የላትም፡- ‹‹እኔ አላህ እኔ ነኝ፤ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፤ ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡›› ቡኻሪ ዘግበውታል አላህ ትክክለኘ ሰጋጆች ያድርገን ኑረዲን ጀማል  28/02/2016 https://t.me/alfelah09
Show all...