cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

👑blue_vibe🙃

የደበረው😫 ኑሮ የመረረው 😫 ካለ እኛን በመቀላቀል ቀንዎትን ብሩህ ያርጉ። የኛ ዋና አላማ #Removing ድብርት ነው። ከተቀላቀሉን በኃላ ጥርስዎት አይከደንም #የቀልዶች ስብስብ😂😂 #quote🤔 #music🎧 #movies🎬 #vine📼 #funny pics 📸 +#ለጓደኛዋ HBD🎂 ለማለት or አስተያየት ካሎት 👉 @miku_20👈 . share share @feta_belu

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
301
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

I can't wait to hate my daughter's boyfriend for no reason.
Show all...
❤️የልቤ ትርታ❤️ # ክፍል_ሀያ ምርጦቼ የዚህን ቻናል ቤተሰብ አባላት እንዲጨምር የናንተ ድጋፍ ያስፈልገናል ለዛሬ አንድ ነገር ጀባ ልበላችሁ በተቻላችሁ መጠን የምታነቡትን ታሪክ ቢያንስ ለአንድ ሰው ወይም ግሩፕ ላይ ሼር ያድርጉ፡፡ ስንበዛ እናምራለን! ከሁለት_አመት_በኅላ .........የመቅደስና የጌዲዮ ትውውቅ ድፍን ሶስት አመት ሊሞላው አንድ ሳምንት ብቻ ነው የቀረው አሁን አመቱ አዲስ ነው የረፍት ጊዜያቸውን ጨርሰው መቅደስ ያራተኛ አመት ጌዲዮ ደግሞ ያምስተኛ አመት ትምህርታቸውን ለመቀጠል ነገ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ ይጓዛሉ በተለይ ለጌዲዮ ይህ አመት ልዩ ነው ዛሬ ላይ እንዲቆም በትምርቱ ገፍቶ ሰው የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ከፈጣሪ በታች መሰላል የሆነችውን የናቱን አደራ የሚወጣበት ተመርቆም ለቁም ነገር የሚበቃበት ልዩ አመት ነው እንኳን ለናቱ እንኳን እራሱ መቅደስም የዚህን አመት መጨረሻ ናፍቃለች ደወለችለት ....ሄሎ ጌዲ ወዬ ፍቅር እንዴት ነህልኝ እግዚያብሄር ይመስገን ደናነኝ አንቺ እንዴት ነሽ እማ ደናነኝ አንተ ግን እያመመህ ነዋ አለችው አረ ደናነኝ ደሞ ደናነኝ ትላለሀ ቅድም እኮ ስደውል ማዘር አንስተው እንዳመመህ ነግረኛል ውይ መቅዲ እማን አታውቂያትም እና ነው እራሴንም ስል እኮ ነው አቋረጠችው በቃ እራስ ምታት ላንተ በሽታ አይደለማ ለማንኛውም ነገ መናህሪያ እንደደረስክ ደውልልኝ አባዬ አደርሳችኋለሁ ብሎኛል ለሊት ስለምትነሳ አሁን ተኛ አለችው እሺ ደናደሪልኝ እንደደረስኩ እደውልልሻለሁ እሺ ቻው። .......በንጋታውም ልክ እንዳለችው ተያይዘው ባባቷ መኪና ተያይዘው ጅማ ገቡ አባቷም ምሳ ጋብዞ ግቢ አድርሷቸው ወደአ.አ ተመለሰ.......መቅደስና ጌዲዮ ግቢ እንደገቡ ከሁሉም ጓደኞቻቸው ጋር ተገናኙ ወይና ብርሀን ሰአዳ በለጠው ሌሎቹም ተሰባሰቡና ቡና ለመጠጣት ሻንጣዎቻቸውን አሳርፈው ወጡ....... በለጠው በጓጓው ልቡ እናንተ የተገናኛችሁበትን ሶስተኛ አመት እንዴት ነው የምታከብሩት አላቸው መቅደስም እንዳምናው ነዋ አለችው በቃ ይቀወጣል አላት ብርሀንም ሙድ ስትዪዝበት የሰውንማ ለማሞቅ አንደኛ ነህ ግን ያንተ መቼ ነው ስትለው ሁሉም ሳቁበት እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ ባንድ ሳምንት አንድ ሴት እቀይራለሁ ታዲያ እኔ ለየትኛዋ ፓርቲ ላዘጋጅ ስታዪኝ ከበርቴ ቱጃር መሰልኩሽ እንዴ ጌዲዮም ቀጠለና አንድ መያዝ ነዋ አለው ወይ አንድ ትቀልዳለህ መሰል እንደዛ ሲል ሰአዳ ወሬ ቀይር አለችው ከዛም ትንሽ እንደተዝናኑም ጌዲዮ አመመው ብዙም ሳይዝናኑ ወዲያው ወደግቢ ተመለሱ።...... ........ሶስተኛ አመት የትውውቅ ልደታቸውንም በደመቀ መልኩ እያከበሩት ሳለ ዛሬም ጌዲዮ አመመው ቢሆንም እስኪነቃ ጠብቀው ሻማቸውን አብርተው ሲደሰቱ ነው ያደሩት ቢሆንም ግን መቅደስ የፍቅረኛዋ ነገር እያሳሰባት ነው ጭራሽ እንቅልፍ አልወሰዳትም ጌዲዮ ሲነቃ እንቅልፍ አልያዛትም መቅዲ ምን ሆንሽብኝ ለምን አተኚም ሲላት እንቅልፌ ስላልመጣ ነው አንተ ተኛ አለችው ፊቷ ተቀያይሮ ስለነበር ጌዲዮ ወዲያው አወቀባት ምን እያሰብሽ ነው ስለኔ ነዋ አላት አዎ ስላንተ ቆይ እስከመቼ ነው እንዲህ በሽታህን ተሸክመህ የምትኖረው መቅዲዬ እሺ ምን ላርግ ምን ላርግ አትበለኝ ይኸው ሀኪም ቤት ለመሄድ አይደል እንዴ ዛሬ ነገ እያልክ ስንት ጊዜ የሆነክ መቅዲ ብሄድም ምንም ለውጥ አይኖረውም እኮ እንዴት አወክ መቅዲዬ የኔ በሽታኮ አትጨርሰው ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ልትለኝ ነዋ አዎ ደሞኮ ሰዎች ሲያወሩ እንደሰማሁት ከሆነ እጀ ሰብ ነው ይባላል አረ ጌዲ እንደተማረ አስብ ለስሙ ነው እንዴ አራት አመት ሙሉ አገር አቀፍ ውጤት አሸንፈህ የተሸለምከው ለነገሩ ጌዲ ሀሳቧን እንድትቀይር እንጂ በንደዚህ አይነት ነገር አያምንም .....መቅዲዬ ምንም አልሆንም ደሞ ፀበል እየሄድኩ አይደል ይሻለኛል ጌዲ ልታባብለኝ አትሞክር እኔ እንቅልፍህም ያስፈራኛል እንባ ባይኗ ሞልቶ ፈሰሰ ደግሞ የትኛው ፀበል ነው ሀኪም የሚከለክለው ሁሌ ይሻለኛል ትላለህ ግን እያባሰብህ ነው ጌዲ አንተን ካጣን እኔም ሆንኩ እናትህ አንድ ቀን አናድርም መቅደስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ጌዲም ሊያስቀይሳት ፈልጎ ማታ ወድቄ አሳፈርኩሻ አላት መቅደስ ባንዴ አራስ ነብር ሆነች ባለ በሌለ አቅሟም በጥፊ ሞላችለት ለመናገር ተስኗት ትንፋሿ ተቆራረጠ ጌዲዮም ጉንጩን ይዞ እየሳቀ አረ እየቀለድኩ ነው አመረርሽ እኮ ሲላት በንዴት ደረቱን እየወቀረች እኔ ጨንቆኛል አንተ ትቀልዳለክ ጌዲዩ በፍቅር የሚመቱትን ሁለት እጆቿን ግጥም አርጎ ይዞ አቀፋት መቅደስ ይበልጥ አለቀሰች የምታጣው የምታጣው እየመሰላት ነው ጌዲዮም ሁኔታዋ ግራ ገብቶት አረ በቃ አንቺ ደስ ካለሽ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ እኔዳለን አላት እስኪ ማሪያምን በል አለችው በንባና በሳቅ መሀል ሆና ማሪያምን እኔዳለን ብሎ አባበላትና አቅፏት ተኙ።.......... .......መቅደስ ከጌዲዮ ቀድማ ነቃች ሻውር ወስዳ ለባብሳ ስትጨርስ ልትቀሰቅሰው ጌዲ አለችው መልስ አልሰጣትም አሁንም ተጣራች ዝም አላት አንተ ጌዲ ተነስ ሰአት እረፍዷል ግቢ ክላስ መግባት አለብን አለችው አሁንም መልስ አልሰጣትም ክው አለች ከወንበሯም ተነስታ ወዳልጋው አመራች በጆቿም እየደበደበች ብጠራውም ሊሰማት አልቻለም እንደበረዶ ቀለጠች ሰውነቷ ደነዘዘ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋ ጌዲ ጌዲ ደጋግማ እየተጣራች አቤት በለኝ አለች ጌዲዮ ግን....... #ክፍል21 ቶሎ እንዲቀጥል......👍 Join @feta_belu 👈
Show all...
❤️የልቤ ትርታ❤️ ክፍል 19 .........መቅደስና ጌዲዮን መናፈሻው ውስጥ ተቃቅፈው ለብዙ ሰአት አልወጡም መቅደስ የቆሰለውን ፊቱን እየደባበሰች አይን አይኑን ታየዋለች እሱ ግን የወይንሸት ነገር አሳስቦታል በርግጥ መቅደስም በውስጧ እየተመላለሰችባት ነው ቡሀላም ጌዲ አለችው እሱም ወዬ መቅዲ ሲላት ትላንት ስታገት እኮ ወይንሸትም አብራ ታግታላቸ በዛ ላይ እስካሁን አልመጣችም እኔ ፈራሁ አለችው ወይና ስልክ ደውላም እንደነገረችው ቡሀላም መረጃ አቀብላ እንዳስፈታችው ለማንም እንዳይናገር በራሷ በመቅደስ ነው ያስማለችው ....ለምን አትደውዪላትም አላት አረ ብዙ ሞክረናል ስልኳ ዝግ ነው አሁንም ሞክሪ ከፍታው ይሆናል አላት ስልኳን አውጥታ ደወለች ዝግ ነው ደግማ ደጋግማ ሞከረች ቢያንስ አስሮ ከሞከረች ቡሀላ ጠራ መቅደስ ከተቀመጠችበት ተነሳች ጌዲዮን በተስፋ ያዳምጣት ጀመር ስልኩ ተነሳ ሄሎ....ሄሎ....ሄሎ. ....ወይና የት ነሽ አለቻት ወይናም በሚቆራረጠው ድምጿ ከክሊኒክ እየወጣች ቢሄንም እዚሁ ነኝ እየመጣሁ ነው አለቻት መቅደስም ግን ደናነሽ ስትላት አዎ ብላ ዋሸቻት ከ15 ደቂቃ ቡሀላም ግቢ እንደምትመጣ ነገረቻትና ስልኩን ዘጋችው ጌዲዮም ችግር አለ አላት መቅደስም ድምጿ ጥሩ አይደለም ግን ደናነኝ ብላኛለች አለችው በቃ አትፍሪ ደና ትሆናለች ዶርም ሄጄ ልብሴን ቀያይሬ እመጣለሁ ሲላት ወይና እየመጣች ስለሆነ እኔ እዚሁ እጠብቅሀለሁ አለችው ግንባሯን ስሟት ሄደ። ..........ባለቻት ደቂቃ ወይና ግቢ ገባች መቅደስ ስታያት ደነገጠች ፊቷ ድልዝ ብልዝ ብሎ አልኮን ተቀብቷል አይኗ ገብቷል ጉንጯ ደግሞ አብጧል ጭራሽ ያቺ ቀበጧን ወይንሸት አትመስልም መቅደስ አቅፋ ምን እንደሆነች ጠየቀቻት ወይና ግን መልሷ ምንም አልሆንኩም ነበረ ብዙ ለመነቻት ፍንክች ዮናስ ነው አይደል ዝም መቅደስ ተናደደች እንዴ ፊትሽ እንደዚህ ባንዲራ መስሎ የምንብምንም አልሆንኩም ነው አለቻት ወይና አይኗ ግንባ ሞላ መቅዲ ይሄ ይገባኛል እንደውም እንደኔ በደል ሲያንሰኝ ነው አለቻት መቅደስ ግራ ገብቷት የተፈጠረውን እንድትነግራት ባባቷ ስም ለመነቻት እሷም ቤተክርስቲያ ሄደው እንደምትነግራት ቃል ገብታ ይዛት ሄደች...... .......ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እንደገቡ ከጥላ ስር ቁጭ አሉ ወይና ከመጀመሪያ ቀን አንስቶ እስከዛሬ ያረገቻትን በንባ ጎርፍ እየታጠበች ነገረቻት ይህን ሁሉ ያረገችውም አባቷን ለማሳከም እንደሆነ እናም በግዚያብሄር ስም ይቅርታ እንድታደርግላት ከግሯ ተንበርክካ ለመነቻት መቅደስ ግን የሰማችውን ማመን ስለተሳናት ቃል ሳተነፍስ ጥላት እየተጣደፈች ወጣች አጋጣሚ ሆኖ የለቱ ጉባኤ የስብከት ፕሮግራም ላይ ደርሶ ነበር የስብከቱም ቃል ይቅር እንዳልኳችሁ ይቅር ተባባሉ ነው መቅደስ ይህን ቃል ስትሰማ ቆም ብላ አሰበች ቢሆንም ስጋዊ መንፈሷ እልህ አሲዟት መንገዷን ቀጠለች ቀጥታም ዶርም ገብታ ማንንም ሳታናግር ተጠቅልላ ተኛች ወይናም ትንሽ ቆይታ ከኋላዋ መጣች ሰአዳና ብርሀን ደነገጡ አንቺ በአላህ ምን ሆነሽ ነው አለቻት ሰአዳ ብርሀንም ቀጥላ አረ ምን ጉድ ነው በማሪያም መቅደስ ነይ እያት ብላ ልትቀሰቅሳት ስትል እንደተኛ ሰው ዝም አለቻት ወይናም ምንም አልሆንኩም አታስቡ ደናነኝ ብላ እሷም ተኛች ሁለቱም እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ሲገላበጡ አደሩ ጠዋትም........ .........መቅደስ ተነስታ ጌዲዮ ጋር ሄደች ተያይዘውም ካፌ ገቡ ምን ሄነሽ ነው ማታ ስደውል ስልክሽን ያላነሳሽው አላት እሷም ዝም አለችው ፊቷ ልክ አልነበረም መቅዲ ምን ተፈጠረ ትክክል አይደለሽም አላት እሷም አዎ አይደለሁም እንዴ ምን ሆንሽብኝ አላት እሷም የተፈጠረው ነገረችው እሱም እንዴ ታዲያ ይቅርታ ሳታረጊላት መጣሽ አላት ጌዲ ከበደኝ በሷ የተነሳ እኮ እኔና አንተም ተለያይተን ትምህርታችንንም አጥተን ነበር። አለችው ጌዲ ፈገግ ብሎ መቅዲ እውነተኛ ፍቅር ይፈተናል በርግጥ አጥፍታለች ግን እኛ ከተፃፈልን ውጪ አልኖርንም አንኖርምም አንዳንዶቻችን የሌላውን ብርሀን ስላጨለምን የኛ ይበልጥ ይበራል ብለን እናስባለን ግን ተሳስተናል ከምንም በላይ ግን ጥፋተኝነትን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ ትልቅ ጥበብ ነው ይቅርታንም መቀበል መሸነፍ ሳይሆን ትልቅ ብልህነት ነው ሰው ሆኖ የማይሳሳት የለም ፍቅራችንን ገደል ልትጨምረው ብትሞክርም ከገደሉ የመለሰችውም እሷ ነች አላት ግን ይህን የተናገረው እንዳትናገር ያለችውንም የነገረቻት መስሎት ነበር መቅደስ ቀበል አርጋ እንዴት ነው ከገደል የመለሰችው አላት እንዴ የዛቀን ማታ ስልክ ባትደውልልኝ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስበሽዋል በዛላይስ እኔን ለማስፈታት ካገቱሽ ልጆች መረጃ ለመሰብሰብ አንሶላ እስከመጋፈፍ እራሷን ለመስዋት ማቅረቧ ይቅርታን ሊያስደርግላት አይችልም መቅደስ ጭንቅላቷን ያዘች ቆይ ለምን አልነገረችኝም ስትል ጌዲ ደንግጦ አልነገረችሽም እንዴ አላት አዎ ብላ ከመቀመጫዋ ተነስታ ቡሀላ እንገናኛለን ብላው እየሮጠች ሄደች...... .......ዶርም ስትገባ ወይና እያለቀሰች ለመሄድ ሻንጣዋን እያዘጋጀች ነበር መቅደስም ተቆጥታ የት ልትሄጂ ነው አለቻት ወይናም አባቴ ሰው ያስፈልገዋል ልሂድለት አለቻት መቅደስም ውሸትሽን ነው ይቅርታ ስላላረኩልሽ ነዋ አለቻት ወይናን ባታረጊልኝም አልፈርድብሽም ስትላት መቅደስ ጥምጥም ብላ አቀፈቻትና ይቅርታዋን እንደተቀበለቻት ነገረቻት ወይና በደስታ ጮቤ እረገጠች ትልቅ ሸክም ቀለለላት.......... ......ከዚህ ቡሀላ ወይና ከመቅደስና ከጌዲዮ ጋር በመተባበር ዮናስን ለፍርድ የሚያበቁ መረጃዎችን ሰበሰቡ ለምሳሌ ሴቶችን ለሹገር ዳዲዬች እንደሚሸጥ አደንዛዥ እፆችን ግቢ ድረስ እንደሚያዘዋውር ሌሎችም ከዛም ከጅማ ዩኒቨርስቲ ግቢ ተባረረ በመቀጠልም በፍርድ ቤት ሶስት አመት ተፈረደበት....... ...... ከዚህን ጊዜ በፍቅራቸው ማህል የገባና ከፍተኛ ክፍተት የፈጠረ ሰው የለም ያመቱ መጨረሻ ላይ ማለትም ትምህርት ሲዘጋ ጌዲዮ መቅደስን ወሎ ድረስ ወስዶ ከናቱ ጋር አስተዋወቃት እናቱም ልክ እንደኔ ሆነሽ ልጄን ተንከባከቢልኝ ብለው አደራ ሰጧት መቅደስም ብትሆን ያለምንም ፍርሀት ቤተሰቦቿ ጋር ወስዳ አስተዋወቀችው ከዛም ሁሉም ቤተሰቦቿ በተሰበሰቡበት በሽታው ተነስቶበት ወደቀ የሚገርመው ግን አንድም ሰው አልተቃወማትም እንደውም ኮሩባት ልጃችን ገንዘብ ቤት መኪና መልክ ቁመና ዝና ሳትል ፍቅርን መረጠች ብለው ልክ እንደጌዲዮ እናት የመቅደስም ቤተሰቦች መረቋቸው እህት ወንድሞቿም ቷናሻችን ብትሆኚም ሁሌ አርአያችን ነሽ ብለው ተራ በተራ እያቀፉ ሳሟት።.. ያው በሽታው ሲብስበት ፀበል ይዛው እየሄደች ታስታምመዋለች እናም በዚህ መልኩ ጌዲዮና መቅደስ ድፍን ሌላ ሁለት አመት በፍቅር ዘለቁ ከሁለት አመት ቡሀላ ምን ሊፈጠር ይችል ይሆን አብረን የምናየው ይሆናል....... #ክፍል_ሀያ ይቀጥላል ......... Join @feta_belu
Show all...
❤️የልቤ ትርታ❤️ #ክፍል 18 .. ........መቅደስን ጓደኞቿ ወስደው ካስተኟት ቡሀላ በንጋታው ቢያንስ ከቀኑ ስድስ ሰአት ድረስ አልነቃችም ነበር ጓደኞቿም እጆቿንና እራሱዋን ይዘው እየጠበቋት ነው ቢሆንም አሁንም አልነቃችም ከዛም ሰአቱ ብዙ አጠንጥኖ ስምን ሰአት አካባቢ ነቃች ስትነቃ ሁሉም ነጭ ሆነባት ቀስ እያለም ጓደኞቿን አየቻቸው በስማቸውም ጠርታ እንዴት እንደመጣች ጠየቀቻቸው ስላስታወሰቻቸው በደስታ ዘለሉ የተፈጠረውን ግን ወዲያው ሊነግሯት አልፈለጉምሽ ግን እየቆየች ስትመጣ ትላንት እስከማደንዘዣው መርፌ የሄነው ትዝ አላት ባይኖቿም ፈልጋ ስታጣት ወይንሸትስ አለቻቸው እነሱም ስላላወቁ ከትላንት ጀምሮ አላየናትም አሉዋት....... መቅደስ ቁጭ ብድግ አለች ምን አርገዋት ይሆን ብላ አሰበች ባይኗ እንባ ሞላ በርግጥ አፍነው ምን አረጉኝ ብላም ተጨነቀች ይበልጥ ግን የወይንሸት ነገር አሳሰባት እነብርሀንም ምን እንደተፈጠረ ጠየቋት እሷም የምታስታውሰውን ብቻ ነገረቻቸው እነሱም ካፈኗችሁ የምታስታውሺው አለ ብለው ጠየቋት ምንም እንዳላየቻቸው ነገረቻቸው........ ......ሰአዳና ብርሀንም እርስ በርስ ተያይተው ይህን ያረገው ዮናስ መሆኑን ተረዱ......መቅደስም ፈጠን ብላ ለወይና እንድረስላት አለች ስልኳንም አንስታ ወደ ጌዲዮ ልትደውል አስባ ስልኳን ስትፈልግ አጣችው ሰአዳ ነበረች የደበቀችው መቅደስም የጠፋ መስሏት ብርሀን ስልክሽን ስጪኝ ጌዲ ጋር ልደውል አለቻት ብርሀንም ቻርጅ ዘግቷል አለቻት እሺ ሰአዳ አለች እሷም ምንም ሳንቲም የለውም አለቻት ኮልሚ ባክስ መልሳ ሰአደ በማፈር ስሜት አራቴ ስለላኩበት አይልክም አለች መቅደስ አይታባቸው የማታውቀው የመረበሽና የማይሆን ምክንያታቸው ግራ አጋባት ወዲያው በቃ ተዉት ዶርሙ እሄዳለሁ ብላ ስትነሳ ሁለቱም ጮኸው አስቀመጧት መቅደስ ይበልጥ ተንቀጠቀጠች ምን እንደተፈጠረ እንዲነግሯት ለመነቻቸው አጋጣሚም ሆኖ ስልኳን ከብርሀን ትራስ ስር አየችው.......... ከዚ በላይ ሊዋሹዋት ስላልቻሉ ከመጀመሪያ ጀምሮ እየተቀረፀ ሼር የተደረገላቸውን ቪዲዮ ተራ በተራ አሳዩዋት .......መቅደስ የወጉዋት መርፌ እንደዛ እንዳረጋት ትረዳች ግን የኔ የምትለው ዮናስ ይሄንን ማድረጉ ሰው ማመን ቀብሮ ነው የሚባለው ተረት እውነት ነው አስባላት ወዲያውም ለባብሳ ጌዲዮ ወደታሰረበት ሄዳ ሁኔታውን አስረዳች በርግጥ ፖሊሶቹ አጭበርባሪ ቢሏትም ከግቢም ቢያስወጧት ወዲያው ወይንሸት ተሸፋፍና ይህንን ሁሉ ያደረገው ዮናስ ስለመሆኑ መረጃ ይዛ መጣች ወዲያውም ፈቱላት ጌዲንም እስከዛሬ በፍቅራችሁ ጣልቃ ገብቼ ስለበጠበጥኩ ይቅርታ አለችው ጌዲዮን በጥፋቱ እስከመጨረሻ የፀና እንጂ ጥፋቱን ተረድቶ ንስሀ የገባ ክፉና ወንጀለኛ አይባልም አላት አይኗ እንባ ሲሞላ አቅፎ አባበላት ምንም ብትበጠብጪንም ዛሬ ፍቅራችንን መልሰሽልናል ትላንት ባደውዪልኝ ኖሮ መቅደስ ላይ ሊፈጠር የሚችለው አደጋ ከባድ ነበር ስለዚ በፍቅራችን ስም ላመስግንሽ አላት ወይና በደስታ እንባዋን ጠራርጋ በቃ አንተ ሂድ የዮናስ አይን ብዙ ስለሆነ ካየኝ አይለቀኝም ብላ መልሳ ተሸፋፍና ቻው ብላው ሄደች...... ፖሊሶቹም ወዲያው ወንጀለኛውን ዮናስን ፍለጋ ሀይል አሰማሩ ወይናም ወዲያው ከጌዲዮ ትንሽ እንደራቀች በመኪና አፋፍሰው ወሰዷት......... ጌዲዮ ግቢ እንደደረሰ ለመቅደስ ደወለላት እሷም ቅድም ደማምቶ በዛ ላይ በሽታውም ተነስቶበት እንደነበር አይታም ተነግሯትም ስለነበር ተይዛ እያለቀሰች ነበር ስልኳም እንደጮኸ አንስታ ስታየው ጌዲ ነው በህልሟ በሀሳቡዋም መሰላት ብቻ በደመ ነብስ አንስታ ሄሎ...ሄሎ...ስትለው ተፈቶ ግቢ መናፈሻው ጋር እየጠበቃት መሆኑን ሲነግራት ህልሟን በውን ለማየት ስልኩንም ሳትዘጋ እየከነፈች ሄደች አንገቱም ላይ ተጠምጥማ ይቅርታ አውቄ አይደለም አለችው ጌዲዮ በትንፋሹዋ ተሸሽጎ እንደተረዳት ነገራት ወዲያውም የክፍል ጓደኞቹ መጥተው እያቀፉ በመፈታቱ መደሰታቸውን ገለፁለት ብርሀንና ሰአዳም መተው አቅፈው እንኳን ደስ አለህ አሉት እሱም ስለመልካም ምኞታቸው በፈገግታ አመሰገናቸው..... ከዛም ሁለቱ ጥንዶች ተያይዘው መናፈሻው ውስጥ ገቡ .... ........ከዛም በስስትና በናፍቆት ትቅፍቅፍ ብለው ተ0ቀመጡ........ ወይንሸትን ዮናስ ጋር ወሰዷት ውይ ዮናስ ያ ውበቱ እርግፍ ብሏል ፊቱ ደረቱም ሳይቀር እዛም እዚም ታሽጓል እንዳያትም በጥፊ አጋጫት ምንም አላለችውም ደገማት የወይና ሰውነት እንደበረዶ ቀለጠ ለነገሩ መስሏት እንጂ ፖርቲው ላይ ጌዲዮ እንዲመጣ ማድረጓን እንጂ ማስፈታቷን አላወቀም ይህን ቢያውቅማ በነብስም አልተረፈች በቀጥታ መጥቶ አንገቷን አነቃት ለምን ለጌዲ እንደተናገረችም አፍጥጦ ጠየቃት እሷም የዛሬውን ማስፈታቱዋን አለማወቁ ሲገባት እኔ አይደለሁም ብላ ካደች ያሰበውን በቀል ከሷ ውጪ ማንም ስላላወቀ ክደቷ ይበልጥ አግሎት እንዳህያ እረገጣት ብዙም ከደበደባት እሷም ከዋሸች ቡሀላ እስኪ አባቴን ይንሳኝ አልተናገርኩም በይ አላርት ወይና ባባቷ በውሸት እንደማትምል ስለሚያውቅ እውነትም መማሉ ከበዳት እያለቀሰችም አዎ እኔ ነኝ አለችው ደግሞ በጥፊ ሲላት ሴትን ስለተማታህ ጀግና የምትባል መስሎክ ነው ወንድ ከሆንክ ትላንት መማታት ቢያቅትህ እንኳን እራስህን አትከላከልም ነበር ስትለው በብስጭት በቦቅስ ሲላት እስከታሰረችበት ወንበር ተዘረረች ወዲያውም ፖሊሶች በሩን በርግደውት ገቡ ያሉትንም ሁሉንም አፋፍሰው ይዘዋቸው ሄዱ......... #ክፍል19 ይቀጥል የምትሉ እና ታሪኩን የወደዳችሁት ሼር ና ላይክ በማድረግ አብሮነታችሁን ልገፁልን፡፡ ....... 👍 Join @feta_belu
Show all...
❤️የልቤ ትርታ❤️ #ክፍል_17 ..............ከዛም በተቤሉበት ሰአት ወክ ብላ ይዛት ወጣች ሰአቱ መሽቷል የወይንሸት ሳቅ የውሸት ቢሆንም እየተሳሳቁ መንገድ ጀመሩ.....መድረስ አይቀርምና ዮናስ ያላት ቦታ ደረሱ ከዛም ከየት መጡ ሳይባል በጥቁር ጨርቅ የተሸፈኑ አራት ጎረምሶች አፋፍሰው ሁለቱ ወይንሸትን ሁለቱ መቅደስን ተሸክመው በግራና በቀኝ ወሰዷቸው ሁለቱ ጓደኛሞች እየተወራጩ ተለያዩ በርግጥ ለማስመሰል እንጂ ወይንሸት ውሸቷን ነበር..... ........ከዛም ቀጥታ በጣም አስፈሪና ጨለማ የሆነ ቦታ ወሰዷት ማን ይያዛት ማን ይልቁቃት ምንም አታውቅም ወዲያው አንዱ በደንብ ያዛትና አንዱ አደንዛዥ እፅ ወጋት ከዛም ከቆይታ ቡሀላ ሁለቱ ወንዶች ጥለዋት ወጡ ከመውጣታቸውም ሶስተኛው ዮናስ ዋሻ የመሰለውን አስፈሪ ቤት መብራት አበራው........ ......በሰአቱ ሌላ ሰው ሆና ነበር ምንም አታስታውስም ዮናስንም እንዳየችው ዋው ምን አይነት ውበት ነው አለችው እየተቅበጠበጠች እሱም ታዲያ ስንቱ ያረገደለትን ውበት እንዴት እረግጠሽው ሄድሽ አላት እሷም ግራ በመጋባት እኔ አለችው ...አዎ አንቺ አላት ቀጥላም አረ ይሄን የመሰለ ገላ እንቢ ብል እራሱ ሀጢያት ይሆንብኛል ስትለው የወጓት እፅ መስራቱን ተረዳ........ .........ሊበቀላት ያሰበው በህዝብ መሀል ነበር ዛሬ ደግሞ የቀወጠ ፓርቲ አለ ለዛም ነው ይህንን ቀን የመረጠው.... ......መጨፈር ትፈልጊያለሽ አላት እሷም አዎ በደንብ አለችው እየተሻሸችው እሺ እንደዛ ከሆነ ዛሬ ፓርቲ ስላለ አብረን ሄደን እንቀውጠዋለን አላት በደስታ ዘለለች አቀፈችውም እሱ ግን ከዛ በፊት ባንድ ነገር እንስሜ አላት እሷም ምንድነው አለችው ቀጠለ ማንም ሰው ዮናስ ምንሽ ነው ቢልሽ ፍቅረኛዬ ነው ትያለሽ አሁንም መቅደስ ግራ በመጋባት ዮናስ ማነው አለችው እሱም እየውልሽ ዮናስ ማለት እኔ ነኝ ለዛሬ ማለትም ለፓርቲው ፍቅረኛሞች ሆነን ነው የምንታየው ገባሽ አላት እሷም በደስታ ተስማማች..... .....ገና ተቃቅፈውም ሲገቡ ብዙ የሚያውቋት ተማሪዎች ስለነበሩ ሰላም ሊሏት ተጠጉ እሷ ግን ማንንም ልታውቅ አልቻለችም ግራ ተጋቡ መቅደስ መንታ እህት አላት እንዴ እስከማለት ደረሱ እውነትም ታስብላለች ቅብጥብጥ ብላ ዮናስ ላይ እንደማስቲሽ ተለጥፋ ለመጣው ለሄደው ትስቃለች ምንም አላሳፈረችውም አንዴ ካንገቱ አንዴ ከወገቡ እየተጠመጠመች ትስመዋለች ለማያውቃቸው አዲስ ፍቅረኛሞች ነው የሚመስሉትግን አብዛኛዎቹ የጌዲዮ ፍቅረኛ መሆኗን ስለሚያውቁ ግራ በመጋባት ጭፈራቸውን አቁመው እነሱን ያያሉ.... .......ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ግን ዮናስ እንዳሰበው ሳይሆን ተቃራኒ ሆኖ በቀሉን ከግብ ሳያደርስ ጌዲዮ ፊቱ በርበሬ መስሎ እሳት ለብሶና ጎርሶ ከፊትለፊቱ ቆመ ዮናስ የታወቀ ተደባዳቢ ስለሆነ አልፈራውም...ከዛም ጌዲዮ መቅደስን ከቅፉ ጎትቶ አስወጣት እሷም ምንድነው ብላ ጮኸችበት ዮናስም ፈልጋ እንጂ አስገድጃት እኮ አይደለም ምን ያበሳጭሀል አለው ጌዲም የመቅደስን ጉንጮች በሁለት እጆቹ ይዞ አይናይኗን እያየ መቅዲ ምንድነው የተፈጠረው አላት እሷም ማናት መቅደስ ምንድነው የምታወራው ብላ መልሳ ከጠየቀችው ቡሀላ ወደ ዮናስ ዞራ ፍቅር ምን ፈልጎ ነው አለችው...ዮናስም መልስ ለመመለስ ሲቃጣ ሁኔታዋ ግራ ያጋባው ጌዲዮ ምን አርገሀት ነው ብሎ ከመቅፅበት በቦቅስ አፍንጫውን ሲለው ዮናስ ደም በደም ሆነ የፓርቲው ሙዚቃ ባንዴ በጩኸት ተቀየረ......... .........ዮናስ ደሙን ጠራርጎ ሊመታው ሲል እንዳልነበር አርጎ ቀጠቀጠው ከዛም የዮናስ ጓደኞችም ተጨመሩ ቢሆንም ከጌዲዮ ቦቅስ ተቋደሱ እንጂ አላስጣሉትም ምናልባት አንድ ሁለቴ እንጂ ከዛ በላይ አልተመታም ጌዲዮ በቃ ከዚያን ቡሀላ ቆሞ የሚቀርፅና የሚጮህ እንጂ አገላጋይ ጠፋ ብዙ ተደባደቡ...... ......ጌዲዮ በበሽታው ይፈራል እንጂ ከማንም ጋር ተደባባድቦም ሆነ ተሰዳድቦ አያውቅም ነበር ዛሬ ግን በዝምታው ውስጥ ወንድነት ባንገት ደፊነቱ ውስጥ ጀግንነት መያዙን አስመሰከረ ወዲያው ነበር በሼር እየተቀባበለ ያየው............ ......ብርሀንና ሰአዳም ወዲያው እንዳዩት እየበረሩ ቦታው ላይ ደረሱ ሲደርሱ ግን አካባቢው በፖሊስ ተከቦ ነበረ ወዲያውም መቅደስን ጌዲዮንና ዮናስን ጥያቄ እየጠየቁዋቸው ተመለከቱ......ፓሊሶቹም የማን እንደሆነች ሲጠይቋቸው ሁለቱም የኔ የኔ ማለትና መከራከር ጀመሩ ሁኔታው ግራ ያጋባቸው ፓሊሶች ወደ መቅደስ አፍጥጠው የማን ነሽ አሏት እሷም ዮናስ እንዳላት የዮናስ ፍቅረኛ ነኝ አለች ጌዲዮ በሰላሟ እንደልሆነ ቢገባውም እንዲህ ስትል ደነገጠ ጓደኞቿም በድንጋጤ አፋቸውን ይዘው ደርቀው ቀሩ... ወዲያውም ፓሊሶቹ ጌዲዮን እስር ቤት ዮናስን ደግሞ በጣም ደም እየፈሰሰው ስለነበር ሆስፒታል ይዘዋቸው ሄዱ። መቅደስን ደግሞ እንደምንም ብለው በጌዲ መታሰር በሀዘን ተኮራምተው ግን ምንም ማድረግ ስላልቻሉ ወደ ዶርም ይዘዋት ሄዱ........ #ክፍል_18 ይቀጥላል.... Join @feta_belu
Show all...
❤️የልቤ ትርታ❤️ ክፍል 16 ...........ጌዲና መቅዲ ባሁን ሰአት ለደቂቃ እንኳን መለያየት ይከብዳቸዋል በቀን ቀን ፍቅራቸው እየጨመረ አማላይ ጥንዶች ሆነዋል ጌዲም በብዙ ነገር ተቀይሯል አሁን ከሰው ጋር ይውላል ከክፍል ጓደኞቹም ጋር ይጮታል አብሮ ይበላል አብሮ ይጠጣል በመዘነጥም ቢሆን የግቢውን ቆንጆዎች አስንቋል ግን ለዚህ ሁሉ መሆን መቅደስ በፍቅሯ ቃል አስገብታው ነው አረ አሁንማ ከማድነቅ አልፈው ብዙ ሴቶች ለፍቅር እየተመኙት ነው ጌዲ ግን በፊቱ ፋሽን ሾ ሲሰሩ ቢውሉም ዘወር ብሎም አያያቸውም በርግጥም ትክክል ነው የፍቅር ጀግና የሚባለው መቶ ያሰለፈ ሳይሆ ከመቶዎቹ ላንዷ ብቻ መኖር ሲችል ነው መቅደስም ብትሆን ለማንም ቦታ የላትም ግን አንዳንድ ሰዎች ግርም ይሉኛል ወድቆ እያዩት አይጠቅምም ብለው ያላነሱት ነገር ሌላ ሰው አንስቶ ሲያዩ ለምን ቅጥል እርር እንደሚሉ አይገባኝም...... ጌዲዮ ካፌ ቁጭ ብሎ ሻይ እየጠጣ መቅደስ ከክፍል እስክትወጣ እየጠበቃት ነው አንዲትም ልጅ መጥታ አጠገቡ ተቀመጠች ጌዲዮም ይቅርታ የኔ እህት ወንበሩ ተይዟል አላት እሷም በተሞላቀቀ አፏ እኔ ሰው አይደለሁ ስትለው እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ፍቅረኛዬን እየጠበኳት ነው ስለዚህ ቦታ ቀይሪ ብሎ ሳይጨርስ ምን መቅደስን አይደል ሶ እኔ ከሷ በላይ ፍቅርን ልሰጥህ ዝግጁ ነኝ ብላ ጠረንቤዛው ላይ ያረፉትን እጆቹን ጭብጥ አርጋ ያዘችው መቅደስም እየመጣች ስለነበረ ፊትለፊት እያየቻት ነበር ጌዲዮ እጇን ከጁ አመናጭቆ አስለቀቃት በጥፊ ሳልልሽ ተነስተሽ ከፊቴ ጥፊ ብሎ ሲጮህባት ደንግጣ እየበረረች ሄደች መቅደስ ፊቷ በደስታ ተሞልቶ በፈገግታ ታጀበ እንደደረሰችም አቅፋ ሳመችውና ተቀመጠች ........ .........ጌዲዬ ዛሬ ላይብረሪ እናጥና ድብርብር ብሎኛል አለች መቅዲ ከደበረሽ ለምን ቤተ ክርስቲያን ደርሰን አንመጣም አላት መቅደስም ደስ ይለኛል ነጠላዬን ላምጣና እኔዳለን አለችው። ከግቢም ሲወጡ ዮናስ አያቸው ወዲያው ወይንሸት ጋር ደውሎ ጠራት ከዛም ይዟት ወጣ እሷም ዮኒ ምን ፈልገክ ነው እዚሁ ንገረኝ ካንድ ሰአት ቡሀላ መቅደስ አስጠናችኋለሁ ብላናለች ስትለው ዮናስ ዶማ አጠና አላጠና ያው ዶማ እኮ ነው አላት ወይንሸት ንቀቱ አናደዳት ውስጧ ገብቶ ነዘራት መልሳ ዶማ እያልከኝ ነው አለች እሱም ገብቶሻል አታድርቂኝ ሲላት አሁን ትርፍ ማውራትህን አቁመህ ምን እንደፈለክ ንገረኝ አለችው እሱም ቀለል አርጎ ወደማታ መቅደስን እኔ ጋር እንድታመጪያት ነው አላት ወይናም ዮናስ ውላችንን የጨረስን መሰለኝ የተሰጠኝን ግዳጅ ባግባቡ ተወጥቻለሁ ውርርዱን የተሸነፍከው በራስህ ድክመት ነው ታዲያ ምን ችግር አለው አዲስ ውል እንዋዋል ገንዘብም ቢሆን ከባለፈው በላይ እከፍልሻለሁ ሲላት ወይና ፊቷን አኮሳትራ ......በቃኝ ዮናስ በቃኝ አልፈልግም አለችው እሱም ምኑ ነው የበቃሽ አላት በቃ ከዚህ ቡሀላ ካንተ ጋር መስራት አልፈልግም አለችው እሱም እየቀለድሽ መሆን አለበት ዮናስ እየቀለድኩ አይደለም በሀጢያት መጨማለቅ መሮኛል አይገርምህም መቅደስን እስከዛሬ የበደልኳት እየቆጨኝ ነው ደግሜ ሌላ ስተት መስራት አልፈልግም አለችው ወይንሸት የተቀየረችበትም ምክንያት ትላንትና ተደውሎላት አባቷ በጣም እንደታመመ ሲነግሯት ስታለቅስ መቅደስ አየቻት ምን እንደሆነችም ስጠይቃት አባቷ መታመሙን ነገረቻት መቅደስም በየዋህ ልቧ አብራት እያለቀሰች እግዚአብሔር ይረዳቸዋል ደግሞ አንቺን የመሰለ መልካም ልጅ አላቸው አይደል አይዞሽ ፀልዪ እኔም እፀልይልሻለሁ ብላ ስታፅናናት በደሏ ተሰማት ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ውስጧ ሲረበሽ ነበር ለዚያም ነው ዛሬ ለዮናስ ገንዘብ አልፈልግም ያለችው ዮናስ ግን............ መቼም ጨክነሽ ባባትሽ ነብስ አትፈርጂም ሲላት ስማኝ ይኸው ካይስኩል ጀምሮ በነውር በሀጢያት በምሰበስበው ገንዘብ አሳከምኩት ግን ዳነ አልዳነም አየህ እግዚአብሔር ካላለ እኔ ስላልኩ ወይም ማንም ስላለ አባቴ አይሞትም ደግሞ ቆሽሼ ከማገኘው ገንዘብ ንፁ ፀሎቴ ይሻለኛል መቼም ከዚህ ቡሀላ ወደኋላ አትመልሰኝም መቅደስ ጥሩና ደስ የሚል ስሜት ውስጥ ነው ያለችው ደግሜ ልበጠብጣት አልፈልግም ደግሞ የማላቅ አይምሰልህ ሆን ብለክ አንድ ዩኒቨርሲቲ እንዲደርሰን የጣ ድልድሉ ውስጥ እጅህን ያስገባኸው እኔ ካንተ ከማገኘው ጥቅም በላይ አንተ ከኔ የምታገኘው ጥቅም ስለሚበልጥ ነው ለፍቅር ብቀርብህም አንተ ግን ከየትም እንደተገኘ ገላ ተጫወትክብኝ መጫወትክም ሳያንስ አሳልፈህ ለሹገር ዳዲዎች ሸጥከኝ እኔ ከማገኘው መቶ ፕርሰንት ዘጠናውን አንተ እንደምትወስድ አውቃለሁ ግን አስሯ ፕርሰንት ላባቴ መኖር ምክንያት ስለመሰለችኝ የከተትከኝ ሀጢያት ውስጥ እንደተስማማኝ ሆኜ ኖርኩኝ በርግጥ የኔን ትክክለኛ ማንነት ማንም አያውቅም ግን ይሁን እስከዛሬ ያልሆንኩትን ሆኜ ብኖርም የኖርኩትም ላባቴ ቢሆንም ባርቴፊሻል ማንነቴ አባቴ ድኖ ከሚያዝንብኝ በትክክለኛው ማንነቴ የሆነውን ቢሆንም ወይና አባቷን እጅግ ከሚባለው በላይ ስለምትወደው እንባዋ እንደጎርፍ ወረደ ዮናስም እንዳመረረች ሲረዳ ኦኬ እንደዛ ከሆነ መቅደስ ላይ ያረግሽውን ሁሉ አንድም ሳይቀረኝ እነግራታለሁ ይህ ወሬ ተማሪዎች አወቁ ማለት ሳምንት እንኳን እዚህ ግቢ አትማሪም እኔን እንደሆነ አንዴ ጠልታኛለች የሆነው ቢሆን ማንም ከቁብ አይቆጥረኝም አንቺን ግን ሲላት ሰውነቷን ድንጋጤ ወረረው ዮናስ አታደርገውም አለችው ከት ብሎ ሳቀባት ዮናስ እኮ ነኝ ጭካኔዬን ያኔ ካይስኩል ጀምሮ ከማንም በላይ ታውቂዋለሽ አላት ወይንሸት ከመስማማት ውጪ አማራጭ አልነበራትም እሺ ግን እንዴት ብዬ ለፍቅር ከመጠየቅክ በላይ ደጋግመክ ጌዲዮን እንድትጠላው ለማድረግ በመሞከርክ ላይኗ እንኳን ጠልታሀለች ታዲያ የት ምን ብዬ ነው የማመጣት አለችው ለሱ አታስቢ ወክ እናርግ ብለሽ ውስጥ ውስጡን ትወስጂያታለሽ ከዛም እላይኛው ጫካ ጋር ስትደርሱ ሁለታችሁም የታፈናችሁ አስመስለን አንቺን በጎን ይወስዱሻል እሷ እጄ ትገባለች......... ************* የልብ ትርታ ክፍል 16 እንዲት አያቹት እስኪ አብራችሁን ከሆናችሁ 👍👍👍.... #ክፍል 17 ይቀጥላል!......... Join @feta_belu
Show all...
engorogbaeshi guys
Show all...
❤️የልቤ ትርታ❤️ ክፍል 15 የልብ ትርታ ክፍል 15 በመዘግየታችን ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ 🙏🙏🙏 መልካም ንባብ! ታሪኩን ሼር ያርጉ! ....ጌዲዮ እንደምንም እንባውን ጠራርጎ ታሪኩን ቀጠለላት አየሽ እኔን ማንም ከሰው ተራ ቆጥሮኝ ስላላደኩ ዛሬም ሰው እፈራለሁ ብቸኝነቴን እመርጣለሁ ዝምታዬን እወደዋለሁ ለኔ የመኖር ምክንያቴ እናቴ ናት እሷ ናት ታሪኬ እንዳባት ሞፈር ተሸክማ እንደህት መክራ እንደወንድም ጋሻ ሆናኝ ከናት በላይ ብዙ ሆና ያኖረችኝ ታሪኬ እናቴ ብቻናት አየሽ መቅደስ አንቺ እኔን ከመደገፍሽ በፊት ከናቴ በቀር ማንም ጎንበስ ብሎ አንስትትምኝ አያውቅም ለዚም ነው አንቺን እንደናቴ ያየሁሽ አላት ሳያውቀው ለሷ ያለውን ስሜት ነገራት መቅደስ እጆቿን ከጉንጩ ሰዳ እንባዉን ጠረገችለት ለብዙ ጊዜ ፍቅራቸውን እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው ሲጨነቁ የነበሩት ጥንዶች ዛሬ ያለማንም ጣልቃ ገብነት አንድ ሜዳ ላይ ተገናኙ በርግጥም እውነተኛ ፍቅር የቃላት ድርደራ አይፈልግም ለካ እውነተኛ ፍቅር ባይን ጥቅሻ ብቻ ያግባባል በቃ በዝምታ ተያዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌዲዮ ከንፈሩን ከሴት ከንፈር አገናኘው መቅደስ ለብዙ ጊዜ የናፈቀችውን ጌዲን በቅፎቿ አስገባችው በቃ ያለምንም አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ ያለማንም አጃቢ በከንፈራቸው ቃልኪዳን አሰሩ የፍቅር ድግሳቸው ትተጠነሰሰ ማንም ባይገምትም የጌዲዮና የመቅደስ ፍቅር እውን ሆነ የዛኑ ቀን ነበር ግቢው ይህን እውነት የሰማው ዮናስ ጌሙን ባደባባይ ተሸነፈ መቅደስ ከሱ ቁንጅና ይልቅ የጌዲዮ መልካምነት አሸነፋት ከዮናስ ማስመሰል የጌዲዮ ፍቅር በለጠባት የውጭ ማንነቱን ሳይሆን በውስጥ መልካም ስብእናው ባደባባይ የጌዲዮ ነኝ አለች ዮናስ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ አይነት ጌም ሲሸነፍ ከፍተኛ ገንዘብና እሱ የሚያምንበትን ክብሩን አጣ የመጨረሻ እርምጃ ያለውን በቀል በውስጡ አበቀለ በክፋትም ሊጥላት አሰበ ጌዲና መቅዲ ግን ግቢውን ያስቀና ፍቅር ጀመሩ አይቶ ካይን ያውጣችሁ የማይል ምቀኛ ብቻ ነው በፍቅራቸው አልተደነኩም የሚል ካለ ውሸታም ነው.......... #ክፍል_16 ዛሬ ማታ ይቀጥላል...... 👍👍👍 Join @feta_belu
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.